Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Thoughts avatar
Thoughts
Thoughts avatar
Thoughts
06.05.202518:42
እኔ እንደሚመስለኝ የኛ case severe acute malnutrition (SAM) ሳይሆን pica ይመስለኛል። pica የምንለው ለሰውነታችን ጠቃሚ ያልሆኑ የምግብነት ባሕሪ የሌላቸው ወይም ጎጂ የሆኑ ቁሶችን መመገብ ነው እንደ ወረቀት አፈር or so on .. አብዛኛዎቻችን ለፍቅር ልባችንን የመክፈት ችግር ሳይሆን ፍቅር ላልሆነ ነገር፣ የነፍሳችንን ክፍተት ለማይሞላልን ሰው ልባችንን መክፈት ነው then we will be hurt then we will no longer believe in love
Deleted06.05.202521:32
02.05.202507:21
ታምናለህ?
:
“ውስኪን ከብርጭቆ
መጎንጨት አንስቶ
ጭኗን ከገለጠች…
ማውራት እንቶፈንቶ ፤
አያድርስ በደሉ !
የሀብታም ሰው ግፉ
ተናግሯል መጽሐፉ”
ብሎ የሚታዘብ…
አረቄ ቤት ያለ …
የዛ ድሀ ምኞት ፤
:
በሴቶች ታጅቦ...
ውስኪ መጠጣት ነው
እ’ሱም ገንዘብ ኖሮት።

(ሚካኤል አ)
Deleted06.05.202521:32
Reposted from:
እንማር avatar
እንማር
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። አንዱ አጠገቡ ላለው ጓደኛው እንዲህ አለው። "ቄሱ ቆንጆ ሚስት አለቻቸው። እንዋደዳለን። አሁን እሷ ጋ ልሄድ ነው። አንተ ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን በወሬ ያዝልኝ። ከመምጣትህ በፊት አስቀድመህ ደውልልኝ አደራ" አለው።

ጓደኛው ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን አስቁሞ የባጥ የቆጡን ያወራላቸው ጀመር። ቄሱም በሰውዬው የተዘበራረቀ ንግግር ግራ ገባቸውና ምን እንደፈለገ በቁጣ ጠየቁት።

ሰውዬም የሃጢአተኝነት ስሜት ተሰማውና ዕውነቱን ነገራቸው "ይቅር ይበሉኝ አባቴ! ጓደኛዬ ከእርስዎ ሚስት ጋር ሊተኛ ሄዶ እኔ እርስዎን በወሬ እንድይዝሎት ነግሮኝ ነው" ብሎ እግራቸው ላይ ወደቀ።

ቄሱም ፈጥነው አነሱትና እንዲህ አሉት "አንተ ሞኝ! አሁኑኑ ወደ ሚስትህ ፈጥነህ ሂድ! እኔ ሚስቴ ከሞተች 5 ዓመት አልፏታል
"....... !🙆‍♂️

ምን ልልክ ፈልጌ ነው ላጤነት ይለምልም 🖐


Tesfaye Hailemariam
📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
19.04.202514:03
ሲመጣ አየሁት አረማመዱ ከራስ በተማመንም በላይ ኩራት አለበት። አልጣመኝም።

ሩትን "ማነው" አልኳት "እኔም አንቺም ካላወቅነው የሮቤል ጓደኛ ነው የሚሆነው"  አለቺኝ

የሆነ አይነት ግርማ ሞገስ አለው የሚስብም የሚገፋም አይነት ነገር ሁለተኛ ያልጣመኝ ነገር

ገና ገብቶ አንዱ ጥግ ላይ ከመቀመጡ ሮቤል ካለበት ግርግር መሀል ወጥቶ ሄዶ ሰላም ብሎት ማውራት ጀመሩ። ሀሳቤን ወስዶት ሩት የምታወራውን እንኳን መስማት አቁሜያለሁ

"አንቺ ስሚኝ እንጂ ለ25 አመት ልደት የምን ግርግር ማብዛት ነው እያልኩሽ እኮ ነው አትሰሚኝም እንዴ" አለች ትከሻዬን ገፋ አድርጋ

"እህ??...አዎ... ይገርማል" አልኳት በደመ ነፍስ

ስለ ሮቤል ልደት ነው የምታወራው ልደቱን ማክበሩ ሳያንስ ጓደኞቹን በሙሉ ደግሶ መጥራቱ ገርሟታል።

እሷን ላወራ ዞሬ ስመለስ አይናችን ተገጣጠመ። የሚያስፈራ አስተያየት ውስጥ ማየት የሚችል የሚመስል የአይኑ አካባቢ አጥር እንዲሆነው ይመስል የጎደጎደ ጥልቅ አይን ቶሎ ብዬ አይኔን አሸሸሁ ሶስተኛ ያልጣመኝ ነገር

ወዲያው ሮቤል መጠጥ አምጥቶለት አብረው ተቀመጡ እኔ ላይ የሰራው መግነጢሳዊ ነገሩ ሌላውም ላይ ሰርቷል መሰል ቀስ ቀስ እያለ ሰዎች እየከበቡት መጡ

እንደውም ከዛ አቅጣጫ የሚመጣው የሴት ሳቅ ድምፅ በረከተ። በብዛት አይስቅም በሸራፋው በከንፈሩ ጠርዝ ነው ፈገግ የሚለው። በጣም ስለሚወደው ነገር እያወራ እንደሆነ ያስታውቃል እጁን ሰብስቦ በአይኑም በእጁም ነው የሚያወራው። በጣም ያልጣመኝ ከቀደሙት ሶስቱ የበለጠ ያልጣመኝ ነገር

እያየሁት ስብሰለሰል "ኤርሚያስ ነው ስሙ" አለኝ የሆነ ድምፅ ክው ብዬ ደንግጬ ስዞር ውስኪው ውስጥ በረዶውን እያሟሟ ብርጭቆውን እያሽከረከረ ሮቤል ቆሟል። ፊቱ ላይ ያ የማልወደው ፈገግታ ረብቧል።

"ማን ጠየቀህ አሁን" አልኩት ያልተበላሸውን ፀጉሬን እያስተካከልኩ

"የቀላው ጉንጭሽ" ብሎ ከት ብሎ ሳቀ

"አውቀህ ነው አይደል የጠራኸው?!" አልኩት

"አዎ ያው ምን አይነት እንደሚመችሽ ስለማውቅ ከልምድ በመነሳት ነው" አለ ፈገግታው ከፊቱ ሳይጠፋ

"ልሄድ ነው" አልኩት

"አታረጊውም" አለች ሩት የሰማችንም አልመሰለኝም ነበረ

"አትሄድም ባክሽ እንኳን ኤርሚን የመሰለ አግኝታ እንዲሁም ታቂያት የለ" አለ የድግስ ልክፍቴን ስለሚያቅ

"በሉ በሉ ቻው" ብዬ በአይኔ እንኳን ልሰናበተው ወደሱ ስዞር ድጋሜ ተገጣጠመ። አይናችን።

ይሄኔ run away በቃ ምንም የምጠብቀው ነገር የለም። ማንም ተመሳሳይ ስህተት እየደጋገመ አይሳሳትም። ያ ጊዜ አብቅቷል አይደል?! የሰዎችን ትኩረት ለማግኘት የምጋጋጥበት ለትንሽዬ ትኩረት የምዘልበት፥ ሁሉንም ጉረኛ ወንድ እንደ challenge የምቆጥርበት ወቅት አብቅቷል አይደል

ደህና ነበርኩ እኮ እስካየው ድረስ አሁንም ቢሆን አልረፈደም አሁን ተሻሽያለሁ መሄድ እችላለሁ ችግሮቼን ራሴ ላይ አልጠራም እንደውም መሄድ አይደለም እሮጣለሁ

"ኤፊ ኧረ ኤፍራታ..." ሩት ስትጣራ እየሰማሁ ጥያት በሩጫ እልም

ክፍል ሁለት ይቀጥል???


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
06.05.202517:12
የሆስፒታል ወግ...

የህፃናት ክፍል ተመድበን ካርድ ስናገላብጥ "አሳጥረው ሲፅፉት ከባድ ነገር አይመስልም እንደውም የሰው ስም ነው የሚመስለው አይደል?" አለቺኝ ዶክተሮቹ የፃፉት ካርድ ላይ አልነበብ ያለውን ፅሁፋቸውን ለማንበብ እየሞከረች

አየሁት የበሽታ አይነት የሚለው ላይ "SAM" ይላል severe acute malnutrition ማለት ነው በምግብ እጥረት በጣም የቀነጨረ ህፃን ማለት ነው።

"ቆይ ግን SAM ላለበት ሰው ምንድነው የሚደረገው?!" አለችው አጠገቧ ላለው ነርስ

"ያው acute malnutrition ከሆነ ቶሎ ቶሎ ምግብ እና ፈሳሽ እንሰጠዋለን በጣም severe ደረጃ ላይ ከደረሰ ግን ምግብ ትንሽ ትንሽ ነው የሚሰጠው" አላት እጁን በአልኮል እያፀዳ

"እንዴ እንደውም በደንብ የሚያስፈልገው ለባሰበት አይደለ እንዴ ጭራሽ ትንሽ እንሰጠዋለን?!" አለች ወገቧን ይዛ

"አየሽ ሰውነትሽ አንድን ነገር በጣም ፈልጎ ሲያጣ ያለሱ መኖርን መለማመድ ይጀምራል ስለዚህ ያ በጣም የተፈለገው ነገር ጠላት ይሆናል ሰውነትሽ ያለሱ ለመኖር ሲጣጣር አሰራሩ ይቀየራል ምግብን በአግባቡ ከመጠቀም በትንሽ ምግብ መኖር መለማመድ ይጀምራል

ስለዚህ ብዙ ምግብ ሲያገኝ እንደባዕድ ነገር ይቆጥረው እና ለማውጣት ሲጨነቅ ያልተጠበቀ ጉዳት ሊያመጣበት ይችላል አሁን ገባሽ" አላት

"ዋው ወይ ጉድ ሰውነታችን እኮ ሁሌም ነው የሚደንቀኝ" አለችው እና ወደ እኔ ዞራ "አይገርምም" አለቺኝ

"ቀላል እንደውም ከዘመኔ ትውልድ ጋር ተመሳሰለብኝ" አልኳት ራሴን በግርምት እየነቀነቅኩ ተመሳስሎው ገርሞኝ

"ረሀብ ላይ ስለሆንን ብለሽ ነው?!" አለች ግራ መጋባቷ ፊቷ ላይ እየተስተዋለ

"አይደለም ስለ አካላዊ ርሀብ እና መቀንጨር አይደለም እኔ የማወራው ስለ ፍቅርን እንደ ምግብ ስለተራበው ልባችን ነው የፆታዊ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አይነት ፍቅር ነው የምልሽ እና በጣም የሚያስፈልገን ፍቅር ሆኖ acute የሆነውን ፍቅር ብናገኝ የምናልፍበትን stage አልፈን

አሁን severe love-deficit ሆነን ብቻችን መኖር ብቻችንን መደሰት ብቻችንን ማዘን ብቻችንን ከሀዘን መውጣት እየተለማመድን ሳለ ልባችን "ሰውን መውደድ" የነበረው መደበኛ ስራዋን ትታ "ብቻ መኖርን" ለመደች

አሁን ጠብታ ፍቅር ሲቀርበን ልባችን ይገፋዋል ምክንያቱም መራራቅን እንጂ መቀራረብን ረስተናል ፍቅር እንዴት መቀበል እንዳለብን እንዴት መስጠት እንዳለብን ባጠቃላይ እንዴት ፍቅርን handle ማድረግ እንዳለብን ረስተናል

ስለዚህ እንደ SAM ታካሚ ፍቅርን በጥቂት በጥቂቱ መለማመድ አለብን ምክንያቱም በብዙ የመጣ ፍቅር ለእኛ ጠላት ነው እንዴት እንደሚያዝ አናውቅበትም ለዛ እኮ ነው የቀረበንን በሙሉ ሰበብ እየፈለግን ስንርቅ የኖርነው አይገርምም መመሳሰሉ" አልኳት ጥርስ ጥርስ ሆኜ

"ለዛ እኮ ነው ነርሲንግን ትተሽ ፍልስፍና ተማሪ ስልሽ የነበረው አሁን ነይ ለልጆቹ መድሀኒታቸውን እንስጣቸው በረሀብ ሳያልቁ" አለች

የእኛንስ ልብ ማነው በትንሽ በትንሽ በትንሹ ፍቅር የሚያስለምደው??


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
Deleted06.05.202521:32
01.05.202518:06
Deleted06.05.202521:32
ሁለት ሰዎች በጠና ታመው በአንድ ክፍል ውስጥ ተኝተዋል።

አንደኛው ታማሚ ሳንባው የቋጠረው ውኃ ለማድረቅ ሲባል ብዙውን ሰዓት ቁጭ እንዲል ተደርጓል።

ሌላኛው ደግሞ በጀርባው ተኝቶ ነው ሕክምናውን የሚያገኘው በፍፁም መንቀሳቀስ አይችልም።

ሁለቱ ታካሚዎች በቆይታቸው ተግባብተዋል ስለ ሥራቸው፣ስለቤተሰባቸው፣ስለኑሮ ፣ስለ ሀገር፣ስለወታደር ቤት ብቻ ብዙ ነገር አውግተዋል።

ብዙውን ግዜ ቁጭ የሚለው ታካሚ ሁልግዜም በጀርባው ለተኛው እና መንቀሳቀስ ለማይችለው ታካሚ ጓደኛው ስለውጪው እንዲህ እያለ ይነግረዋል....

በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ትንሽዬ የሚያምር ሐይቅ ይታየኛል፣ በሐይቅ ላይ ዳክዬዎች ይዋኛሉ፣ሕፃናትም በወረቀት የሠሩትን መርከብ በሐይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ፣ፍቅረኛሞች በአንድ እጃቸው ተያይዘው በሌላው አበባ ይዘው በፍቅር እየተያዩ ብዙ ግዜያቸውን አብረው ያሳልፋሉ.

ከሐይቁ ባሻገር በቅርብ ርቀት ላይ በውስጧ ለመኖር የምታጓጓ አንዲት ውብ ከተማ ትታየኛለች.... እያለ ይነግረው ነበር በጀርባው የተኛውም ታካሚ ሁሉንም ነገር በዓይነ ህሊናው እየሳለ ለመረዳት ይሞክራል

ከቀናት በኃላ ያ ብዙውን ግዜ ቁጭ የሚለው ታካሚ ሕይወቱ ያልፋል በጀርባው የሚተኛውም ታካሚ መንቀሳቀስ ሲጀምር ጓደኛው ይነግረው የነበረው ነገር በመስኮቱ ለመመልከት ሲሞክር የሆስፒታሉ ሌላ ግንብ በትንሽ ርቀት ብቻ ነበር የሚታየው....

በጓደኛው ተግባር በጣም ተገረመ ለካ ጓደኛው የማይታየውን እንደታየው እያደረገ የሚነግረው እርሱን በተስፋ ለማኖር እና ውስጡን አጠንክሮ ከበሽታው ቶሎ እንዲያገግም ነበር

ወዳጄ ነገሮች ላንተ ባይሆኑ፣ እንደማይሆንልህ ቢገባህም ለሌላ ሰው ተስፋ እና ሕይወት መሆን ትችላለህ እና በፍፁም በራስህ ተስፋ አትቁረጥ።

ባንተ መልካምነት አንድ ነፍስ እንኳን ማዳን ከቻልክ እንዳንተ ጀግና የለም
23.04.202510:50
ወገኖቼ ትንሽ busy ሆኜ ነው ዛሬ ማታ ጠብቁ ክፍል ሁለት ይለቀቃል
17.04.202507:18
መቼ ነው ህይወት ለዛዋ የጠፋው? መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ከልባችን የሳቅነው?! መቼ ነው በልተን የተደሰትነው? መቼ ነው ማማረር የሌለበት ወሬ ያወራነው? መቼ ነው የጨላለመብን? መቼ ነው የምንሰማው የምናየው ሁሉ የበጠበጠን? መቼ ነው
መዝናኛችን እንደ አዙሪት ከድብርታችን ያበረብን?

መቼ ነው በደንብ መኖር ያቆምነው?

በደንብ መሳቅ? በደንብ ማልቀስ? በደንብ መውደድ? በደንብ መግባባት? በደንብ መናፈቅ? በደንብ ማለም? በደንብ ለህልም መጋጋጥ? በደንብ መጎዳት? በደንብ መድመቅ?

መቼ ነው ህይወት እንደነገሩ የሆነችብን?

ከላይ ከላይ ብቻ የሆንነው መቼ ነው? ትልቋን ህይወት አጥብበን ጥቂት ሙከራ፥ ጥቂት ጥረት፥ ጥቂት ሀዘን፥ ጥቂት ተስፋ ግን ብዙ ጨለማ የከበበን መቼ ነው?! የቱ እጦት ነው ቋጥኝ ድብርት የጣለብን? የቱ እድሜ ነው ብዙ አሳይቶ ብዙ ያደከመን? የቱ እውቀታችን ነው ወደፊቱን የጋረደብን? ማነው እድሜያችን ቢበዛ ሰላሳ ብሎ በጊዜ መንፈሳችን ጡረታ ያወጣው? ምንድነው የዞረብን?!

መቼ ነው እንደዚህ የሆንነው?

✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss
Deleted06.05.202521:32
Reposted from:
ዳን ŦËŁŁ avatar
ዳን ŦËŁŁ
30.04.202509:03
📚ርዕስ:- ሾተላዩ ሰላይ • Eye Of The Needle
📝ደራሲ ኬን ፌሎት
👤ተርጓሚ ፦ ማሞ ውድነህ
📖የገፅ ብዛት:- 405
የተለያዩ አዋርዶችን ያሸነፈ በፊልምና በድራማ መልክም ተሰርቶ ለመታየት የበቃ ድንቅ የስለላ መፅሐፍ!
23.04.202517:56
የመጨረሻው ክፍል

እሷ ደንግጣ ፊቷ ሲቀላ ሮቤል ድክም ብሎ እየሳቀ ነው "ማለት ሊያስቃት እንደሚችል ሊያሳየኝ ነው?! ወይስ ምን እያደረገ ነው?!" እያልኩ ደምስሬ ሲገታተር ይሰማኛል። 'በሰላም የተኛሁትን ሰውዬ ቀስቅሶ ጠርቶ መበጥበጥ ምንድነው' ብዬ ስበሰጫጭ ቦርሳዋን ይዛ ስትወጣ አየኋት

እሱን ሳየው ግራ ገብቶት ከጓደኛዋ ጋር ስሟን ይጣራል እሷን ሳያት ስታየኝ ተገጣጠምን። በአይን ይለመናል?? በአይኔ ለመንኳት በአይኗ እምቢ አለቺኝ

ምን ብሏት ነው የሚል እልህ አነቀኝ። የከበቡኝን ሴቶች ገለል አድርጌ ሮቤል ጋር ሄድኩ። "ደሞ አንተ ምን ሆንክ" አለኝ ንዴቴን ሳልነገረው አውቆ "ምን ሆና ነው የወጣችው ምን አድርገሀት ነው የሄደችው"

"ምንም አላልኳትም ግን በሰበቡ ልታወራት ከፈለክ በእግሯ ስለሆነ የምትሄደው ብትሮጥ ትደርስባታለህ" አለኝ እየሳቀ አይ ሮቤል አሁን እኔ የእሱ ነገር ጠፍቶኝ በሱ መናደዴ እሱ እዚህ ይስቃል

"ጫማዋ ስለማያስኬዳት ባትሮጥም ትደርስባታለህ" አለች ጓደኛዋ

እውነትም እንዳሉት ብዙም ሳትርቅ ጫማዋን ለመፍታት ስትታገል አየኋት

እየሮጥኩ ሄጄ እግሯ ስር ተገኘሁ "ለመፍታት አስቸግሮሽ ከሆነ ልፍታልሽ" ብዬ እግሯ ስር ተንበረከኩ ዝም ብላ አየቺኝ እየፈታሁት

"ሮቤል ምንድነው ያለሽ" አልኳት ጫማዋን አውልቄ ባዶ እግሯን ቆማ እኔ በተንበረከኩበት
"ኧረ ቢያንስ ከተንበረከክበት ተነስ" አለች ፊቷ በደማቁ እየቀላ ድምጿም ሀምራዊ ነው

ስቆም አሁን ደግሞ ወደላይ አየቺኝ ቁመት በትንሹ እበልጣታለሁ አይኖቿ ያሳዝናሉ

"ንገሪኛ ምን ብሎሽ ነው" አልኳት

"ስምህ ኤርሚያስ መሆኑን ነግሮኝ ነው" ብላ ፊቷን ሸፈነችው

እንዳየቺኝ ሮቤል አውቆ ነበር?! ሮቤል ስላወቀባት አፍራ ነው የወጣችው?! ልቤ ደስታ ፈሰሰበት

"በቃ ይኸው ነው? የወጣሽው ለዚህ ብቻ አይደለም አይኖችሽ ሌላም ነገር ነግረውኛል እስክረዳሽ ግዜ አልሰጠሺኝም ንገሪኝ መጥቼ እስካወራሽ ለምን ቸኮልሽ ንገሪኝ" ብዬ እጆቿን ከፊቷ ላይ አነሳኋቸው

አምጣ አምጣ ቆይታ "መጎዳት ደክሞኛል"

እስካሁን ያዘነላት ልቤ አሁን እጥፉን አዘነላት

"ሰዓሊ እሱ ሲጎዳ እንጂ ሌሎችን ሲጎዳ ሰምተሽ ታውቂያለሽ?!"  አልኳት መልሷን አልጠበኩም እቅፌ ውስጥ ከተትኳት እንደዚህ መቀራረብ እንድትፈራ ያደረጓትን ሰዎች እየረገምኩ ልጠብቃት ቃል ገባሁ

ቃሌንም ጠበቅኩ

ሞት እሷን ከእኔ እስኪነጥቃት መከዳትን አስረሳኋት የሚገባትን ፍቅር በምችለው ጥግ ደረስ ሰጠኋት አላሳፈረቺኝም እንደውም ህይወቴን አደመቀችው

እድሜ ለሮቤል


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
Reposted from:
Event Addis Media avatar
Event Addis Media
📌ዛሬ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን ነው!

የዓለም መጽሐፍ ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 15 ይከበራል

ሚያዝያ 15 ለዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀንነት የተመረጠበት ምክንያት የዊልያም ሼክስፒር እና ስፔናዊው የታሪክ ጸሐፊ ኢንካ ጋርሲላሶ ዴ ላ ቬጋ የሞቱበት ቀን በመሆኑ እንደመታሰቢያ እንዲሆን ነው።

በእዚህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በተለይ ወላጆች ለልጆቻቸው መጻሕፍትን በስጦታ መልክ በመስጠት ያከብሩታል።

የቀኑም ትልቁ ዓላማ የንባብ በዓል ማዳበረ ነው።

#Worldbookday!

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
Reposted from:
ጥርኝ ጥበብ avatar
ጥርኝ ጥበብ
18.04.202508:46
እኛ ያመጣናቸው እነርሱ በለጡን

እየጎተንት ወደ ቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ይዘነው ገባን።የገዛንለትን ነጠላ ዘርግቶ ለመልበስ ግራ ሲጋባ ከሶስታችን መሀከል አንድኛው ተጠግቶ በአንገቱ ስል አመሳቅሎ አጣፋለትና  
"እንዲህ አይሰገድም እሽ
        እሽ
ምግብስ በልተሀል
   ኧረ አልበላሁም
አዎ ምን ሆነሀላ ውሀ ራሱ ከጠጣህ ነገር ተበላሽቷል በቃ
    አይ እንደዚያ አላደረኩም"     ይቁነጠነጣል...በመሀል 1000 ሰግደን ለመውጣት የምንገፋፋው እኛ ቆመን ሳለ እርሱ ስድስት ሰባት ጊዜ ከፍ ዝቅ ብሎ ጉልበቱ እንደተብረከረከ ሰው በግንባሩ መሬቱን ተደግፎት ቀረ። እንግድህ ላለመነሳት ምክንያት እየፈጠረ መሆኑ ነው ቀና ማለት እንደከበደው ሰው ቁና ቁና ሲተነፍስ ይሰማናል።...

"ቃል እንደጓደኛ ይሄንን ልጅ ምንም መላ አናበጅለትም ማለት ነው"አለ ቢታንያ ወደ አንገቴ ተጠግቶ ... እኔ ደግሞ የአናንያን ህይወት እየሄደ ካለበት ቁልቁለት ለመመለስ መሞከር ውሀን ሽቅብ የማፍሰስ ያህል ድካሙ ብቻ ነው የሚታየኝ።  ለጓደኛ በዚህ ልክ
መጠን ዝሎ መኖር ቢያሳፍርም...  "ሱስ እኮ ነው እየበዛ በጣም ብሶበታል የት እናስጠምቀው በእናትህ"  የየግል አስተያየታችንን ለጣጥፈን ስናበቃ ካጎነበሰበት በርከክ ብሎ አንገቱን ደፍቶ ነጠላውን አናቱ ላይ ጎዝጉዞ ተቀመጠ።

ለካ መቆም ቢያፍር ነው እንባ አርግዞ የወደቀው ድንገት ቀና ሲል ደንግጠን ተያየን በስጋው ላይ እንደተቆጣ የሚያሳብቁት የደም ስሮች ከወደግንባሩ እንድህ ተከታትለው ለመሰለፍ ምን አነቃቃቸው ከምኔው ፊቱ በእምባ ረጠበ አያስቀናም ልታፀድቁ በገሰፃችሁት ሰው ተሰብካችሁ እንደመሄድ ያለ ስብከት ወደየት ይገኛል።

የእኛ ፀፀት አርባአንድ ኪራላይሶን ብለን ከአይናችን ካልወረደ ለእርሱ በሰባት ዝቅ ማለት በዘነበለት እምባ እንዴት አይቀናም አምላኩ በልቡ አደባባይ በታተመለት ሰው ቁኑ ሀቁም ይሄው ነው።

በልምድ መመላለስ የፀና ሐዋርያም አንዳንድ ጊዜ ሊያፀድቅ ይዞ ከመጣው ወንበዴ ተምሮ ይሄዳል።...

ወዮ የሠው ስግደት ቆጥረን ለተመለስን 😢😢😢

ፀሀፊ ✍ ጌታሁን ደጉ

እንኳን አደረሳችሁ
Reposted from:
ታዖርያ avatar
ታዖርያ
05.05.202510:30
ሰው ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ሊሳለም ወደ አንድ አቅጣጫ ይዘማል። ቀኑም እሁድ ስለሆነ ህፃን አዋቂው ሁሉ ሀጫ በረዶ መስሎ ነጠላውን አጥፍቶ ወደ ትልቅ ድግስ የሚጓዝ ይመስለል።
......ለመጨረሻ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የሄደበትን አያስታውሰውም ።
ዛሬ ግን መጠጊያ ቢያጣ፤ የታመነበት ሀብትና ጉልበት እንደ ጉም ከፊቱ ተኖ ቢቀር፤ ወዳጄ ብሎ ሲከበው የኖረ ሰው ሁሉ ሲያጣ ሲነጣ ጊዜ ባላየ ሲያልፉት ፤ የሚሸሸግበት ቦታ አሰኘው። ይህን በሀሳቡ እያመላለሰ ሳያውቀው ተጉዞ ነበር እራሱን ደጀሰላሙ ላይ ያገኘው።
ከሀሳቡ ያነቃው የዲያቆኑ ዜማ ነበር.....
.'
ፃዑዑዑዑዑዑ ንዑሰ ክርሰቲያን

....
ዲያቆኑ'
ተንስኡ ለጸሎት

...
ህዝቡ  ተቀብሎ '
እግዚኦ ተሣሃለነ

....
ለመጸለይ ፈልጓል ግን ምን ማለት እንዳለበት አያውቅም። ዝም ብሎ አጥሩን ተደግፎ ወጪው ወራጁን አተኩሮ ይመለከታል ። ህፃናት ይሯሯጣሉ ይስቃሉ ይጮታሉ እነሱን አያየ ፈገግ አለ ሳያውቀው ።
በዚህ መሀል ነበር ዲያቆኑ በቅዳሴው ላይ የተናገራት ሀይለቃል ጆሮውን አልፍ ልቡን ሰርስራ የገባችው።
እንባው  በጉንጮቹ መንታ መንታ ሆነው ሲወርዱ ፤ ከልቡ ላይ የከበደው ሲቀለው ታወቀው።  ለምን ያህል ሰዓት እንኳን እንደቆየ ሳያስተውለው በሰላም ግቡ ተብሎ ህዝቡ ወደ ቤቱ መመለስ ሲጀምር እሱም እንባውን ጠራርጎ መመለስ ጀመረ። በልቡም የሰማትን ቃል መላልሶ እያሰበ ነበር ።
'በልቡ መጠራጠር ያሰበ ቢኖር ይመን

Abu ✍✍
https://t.me/taoriia
Deleted06.05.202521:32
Reposted from:
Open reading 👐 avatar
Open reading 👐
29.04.202506:40
አንዲት ሴት ፕሮፈሰር ስለ "አንድ ወንድ ብዙ ሚስቶችን ማግባት" በተሰኘ አርእስት በአንድ አካባቢ ለሚኖሩ ሴቶች እና ወንዶች ገለፃ እንድታደርግ ትጋበዛለች።

ፕሮፈሰሯ የተጠቀሰውን አርእስት ገለፃ ለማድረግ እራሷ ነበረ የመረጠችው።

ፕሮፈሰሯ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ሲያገባ ለሴት ልጅ ያለውን ጠቀሜታ በዝርዝር አስረዳች።

ሴቶችም ይህን የጋብቻ ልምድ ተቀብለው ቢፈፅሙት ያለውን ጠቀሜታ አስተማረች።

ጥቅሙ ለእራሷ ለሴቷ እንደሆነና መቃወም እንደሌለባት አዳራሽ ውስጥ ላሉት ታዳሚዎች አስረግጣ ገለፃ አደረገች።

በአዳራሹ የፕሮፈሰሯን ገለፃ ስትከታተል የነበረች አንዲት ሴት እጇን አውጥታ ለፕሮፈሰሯ  እንዲህ በማለት አስትያየት ትሰጣለች ።

"በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ ስላደረግሽልን አመሰገናለሁ!"

"ከባለቤትሽ ጋር አንቺ ሳታውቂ ፣ አብረሸው እያለሽ  ከተጋባን አሁን  አራት አመታችን ነው ፣ መንታ ልጆችም አለን አለቻት።"

ፕሮፌሰሯ ከሴትየዋ ይህንን ስትሰማ  በአዳራሹ ውስጥ እራሷን ስታ ወደቀች ፣ሆስፒታልም ተወሰደች።

ፕሮፌሰሯ ሆስፒታል ከአልጋ ላይ ሆና ስትነቃ ያቺ አዳራሽ ውስጥ አስተያየት የሰጣቻት ሴት ከአልጋዋ አጠገብ ሆና አየቻት ።

ሴትየዋ  ለፕሮፌሰሯ እንዲህ አለቻት:-

"ባለቤትሽን እንኳን ላገባው በአይኔም አይቼው አላውቅውም ይህን ያልኩት ልፈትንሽ ነበረ፤ ፈተናውን ወድቀሻል።"

"ለሌላ ግዜ ስለ አንድ አስተሳሰብ ተቀበሉና አድርጉት ብለሽ  ሌሎችን ስታስተምሪ ፣መጀመሪያ አንቺ ራስሽ አምነሽና ፣ ተቀብለሽ  መሆን አለበት" በማለት ለፕሮፈሰሯ ነገረቻት።

◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆

                   @open_reading1
                   @open_reading1
23.04.202516:27
ተኝቼ ነበር። መተኛት ሁሉ እንቅልፍ መወሰድ ነው ያለው ማነው?! እንዲሁ ስገላበጥ ሮቤል ለሁለተኛ ጊዜ ሲደውልልኝ ስልኬን ሰማሁት።

አንዴ ደውሎ ካላነሳሁ ማንሳት አለመፈለጌን ይረዳ ነበር እኮ ደጋግሞ የሚደውለው የሚፈልገው ነገር ሲኖር ስለሆነ ነው።

የማስተዋውቅህ ሰው አለ ቶሎ ና ነው ያለኝ ልደቱ መሆኑን እንደተጨማሪ ነገር ነው ነግሮኝ ስልኩን የዘጋው።

ልብስ መልበስ እና ተዘጋጅቶ መውጣት እንደድሮ አስጨናቂ አይደለም። የትኛው ያምርብኛል የቱ ይሆነኛል ብሎ ጭንቀት እድሜ ብረት ለመግፋት ድራሹ ጠፍቷል። ልብሴን ሁሉ ከመስቀያው ነው እስኪባል ድረስ መስቀያው ላይ ሰርቻለሁ።

ቆሜ በራሴ ስደነቅ ሮቤል ደግሞ ደወለ እና እንግዶቹ ሁሉ መጥተው እኔ ብቻ እንደቀረሁ ነገረኝ።

የህዝብ ሀብት ከሆነ ሰው ጋር ጓደኛ መሆን ጦሱ ይሄ ነው ብዬ እየተነጫነጭኩ ስደርስ ቤቱ ሞልቷል። የጠበኩት ምን እንደነበረ ባላውቅም ስገባ ሮቤልም ሆነ "እንግዶቹ" መምጣቴን ያስተዋለ ሰው አለመኖሩ ብዙ ቅር አላለኝም።

ከእሷ በስተቀር...

አረማመዴን አጥንታ ስትጨርስ ወደጓደኛዋ ዞራ የሆነ ነገር አለቻት። ያለእቅዴ አስፈገገቺኝ። በደረስኩበት ትኩረት ማግኘት ብርቄ አይደለም። የእሷ አኳኋን ግን ከረሜላ እንደተሰጠው ህፃን አስቦረቀኝ።

ከእሷ በስተቀር የተዘጋጀው ድግስ እዚ ግባ የሚባል አልነበረም።ሮቤል እሷን ለማስተዋወቅ እንዳስመጣኝ ነጋሪ አላስፈለገኝም። ግን መጠንቀቅ ነበረብኝ ገና እንዳየኋት የሞተው የስዕል ሀሞቴ እንደተነሳሳ ማወቅ የለባትም።

ሰዎች ስዕልን መውደድ ስለ ስዕል ብቻ ይመስላቸዋል። ስዕል ግን ስለሚሳለው ነገር አድናቆትም ጭምር ነው። በቀለም አስፍሮ ይዞ መሄድም ነው። እንጂማ ለምን በያዘችው ብርጭቆ ዙርያ ያሉትን ቀጫጭን አጫጭር ጣቶቿን ቤት ገብቼ እንዳይጠፉብኝ ደጋግሜ በምናቤ ሳልኳቸው?

አይኖቿን በደንብ ልሸምድድ ብዬ ሳያት ተገጣጠምን እያየቺኝ ነበር። የሰውነቴ አካላቶች ተባብረው ስራ አቁመው ጥንካሬው ሁሉ አይኗን ለመቋቋም ውሎ ነበር። አስተያየቷ ሀይል አለው የሀምራዊ ቀለም አይነት ስበት በጣም ሳይለፋ ማሰገድ የሚችል ሀይል ደረቴ ጋር መጨናነቅ ሲሰማኝ ነው መተንፈስ አቁሜ እንደነበር ያወቅኩት።

አይኗን ቶሎ አሽሽታ የተጋነነ "አልተዘበራረቅኩም አይደል" ሁለመናዋን አስተካከለች። ሰው እንዴት እኩል ሁለት ተቃራኒ ስሜት ይሰማዋል?! የኔ ሁኔታ ይቆይና የእሷን አይኔን መሸሽ ሳይ እንዴት ለኩሩ ልቤ ደስታ ብቻ አይሰጠውም ለምን በደንብ እንድታየኝ ተመኘሁ መርበትበቷ ለምን አናደደኝ?! እንጃ...

ብቻ የሀሳቤ አቅጣጫ ስላላማረኝ ወደእሷው ስዕል ተመለስኩ። ፀጉሯን ለመሳል ብዙ ጭረት ማስፈለጉ አይቀርም በግድየለሽነት የተዝረከረከው እሷን አሳምሯታል እኮ እኔን በኋላ ሊያቸግረኝ ከዛ ደግሞ ገርበብ ያሉት አይኖቿን እና የሚያሳሱ ከንፈሮቿን አይኔን ጨፍኜ እግሬ ላይ በጣቴ ለመሳል እየሞከርኩ እያለ ሮቤል መጠጥ ይዞልኝ መጣ

"እንኳን ተወለድክ ይቅር ሰላምታ እንኳን አይገባኝም" አለ አጠገቤ እየተቀመጠ "ምን ቸገረኝ እኔ አንተን ለማግኘት አልመጣሁ ባይሆን አንድ ጊዜ ብትዞር እኮ ፀጉሯን አየው ነበር" አልኩት

"አጅሬ ማን እንደሆነች ሳልነግርህ ጭራሽ እንደምትስላት ወስነሀል" ብሎ ረጅም ሳቅ ሳቀ

"አሁን አትረብሸኝ" እስኪ ስለው የድሮ ጓደኞቻችን ቀስ በቀስ ከበቡን ጓደኝነታችን ከእኔ ይልቅ ለእሱ ስለሚያደላ ብዙ ምቾት አልሰጠኝም ነበረ።

ከዛ ግን ሳባ "ኤርሚ አሁንም ትስላለህ እንዴ?!" አለቺኝ በቃ ከዛ በኋላ ማን ይቻለኝ የለበስኩትም ኮት ጠበበኝ ሸሚዙም ወደክንዴ ተሰበሰበ። ረጅሙን መግለጫ ሰጠኋቸው።

ደጋግማ ሰርቃ ስታየኝ በአይኔ ዳርቻ አይቻታለሁ። "ሄጄ ላውራት?! ግን ልታወራኝ ባትፈልግስ?!" በሚል ሰጣገባ ውስጥ ስታገል ራሴን አገኘሁት። የውሳኔ ሰው አልነበርኩ እንዴ?

ድምጿ ምን አይነት ይሆን እንደ ሀምራዊ መግነጢሳዊ ወይስ እንደ ፈዛዛ ሮዝ ለስላሳ?! ብቻ ላወራት ይገባል ብዬ ስዞር ሮቤል ከጀርባዋ የሆነ ነገር ሲላት አየሁት ፊቷ ሲቀላ ሳየው ደነገጥኩ።

የመጨረሻው ክፍል እስኪለቀቅ ድረስ react እያደረግን😄



✍ናኒ




https://t.me/justhoughtsss
22.04.202507:04
8123

<<<<<>>>>>>



ይሄኛውን ቴክስት የላከችልኝ ረቡዕ ነበር፡፡ በስራ ሰዓት ፡፡


‹‹ሄይ  ቆንጂት…! እኔ የምልሽ፣  ሴቭ ዘ ችልደርን HR ውስጥ ያለ ሰው ታውቂያለሽ እንዴ? ››



ደምበኛ ሰላምታ የለ፣  ናፍቀሽኛል የለ፣ ደህና ነሽ ወይ የለ።

‹‹ሄይ ቆንጂት›› ያለችውም ለምትፈልገው ነገር ስታመቻቸኝ ነው፡፡




በረጅሙ ተነፈስኩ፡፡



ለስሙ ጓደኛሞች ነን፡፡


ለመጨረሻ ጊዜ ካወራን ግን ሁለት ወር ያልፈናል፡፡  ያኔም የሆነ ሰው ስልክ ቁጥር ፈልጋ ነው የደወለችልኝ፡፡አፍሪካ ህብረት የሚሰራ ሰው፡፡


…..ከዚያ በፊት ደግሞ የጻፈችልኝ ቴክስት፣


  “ስሚማ ፍቅር፣  ያ ዩ ኤን ዲፒ የሚሰራው ሰውዬ ስልክ  አለሽ እንዴ? ያ እንደውም ዶሎ አዶ ፕሮጀክት ማኔጀር የነበረው?”  የሚል ነበር፡፡



ከዚያ በፊት ደግሞ አንዱን ቅዳሜ ጠዋት ምን ብላ ጽፋልኝ ነበር…?


አዎ…

“ሄይ….በናትሽ ያ የአጎትሽ ልጅ፣ ቴሌ የሚሰራው… አሁንም እዛ ነው እንዴ? ሲምካርዴ እኮ ድጋሚ ተዘጋብኝ”


እንዴት ነሽ፣ እንዴት አደርሽ እንኳን ሳትል፡፡




አንዱን ቀን ደሞ ለእኩለ ሌሊት ትንሽ ሲቀረው ደወለችና፣ በጣም ለምትፈልገው ስራ ልታስገባው የጻፈችውን ‹‹ሞቲቬሽን ሌተር›› ቶሎ ብዬ እንዳስተካክልላት ላከችልኝ፡፡ 



ወሊሶ ነበርኩ። ከስራ ድካም አረፍ ልበል ብዬ ቤተሰብ ጋር፡፡
ግን ጭንቀትዋን አየሁና፣   ‹‹እሺ ጠዋት አይቼ አስተካክልልሻለሁ›› ብያት ስልኩን ዘጋሁ፡፡



ማለዳ፣ ገና በቅጡ ሳይነጋ ደውላ ፣

“እ እንዴት አረግሽልኝ?” አለችኝ።



የናፈቀችኝ እናቴ ቤተክርስትያን አብሬያት እንድሄድ እየለመነችኝ ለእሷ ብዬ ቤት ቀረሁ፡፡




ይህ ከሆነ ከሶስት ሳምንት በኋላ ስትጠፋብኝ፣
‹‹እሺ፣ ያ ጉዳይ እንዴት ሆነልሽ..ተሳካ?›› ብዬ ስለስራው ስጠይቃት ሌላ ነገር ሳትለኝ፣ በብልጭልጭ መብራት ውስጥ የምትደንስ ትንሽዬ ልጅ "ጂ አይ ኤፍ "ብቻ ልካ ደግሞ እንደ ልማዷ ጥርቅም አድርጋ ዘጋችኝ፡፡



አንዴ ደግሞ ለራሴ እንኳን የምሳሳለትን ሀበሻ ቀሚሴን ለአክስቷ ልጅ ሰርግ ልትለብሰው አውሺን አለችኝ፡፡ 


አይሆንም ብላት
አጃቢ ነኝ ..
ደህና ነገር መልበስ አለብኝ…
ስሞትልሽ…ስከተፍልሽ

ምናምን ብላ አለቃቀሰችብኝ፡፡

ንዝንዝ ስታደርገኝ፣



‹‹ስሚ ! በእቁብ ነው የገዛሁት፡፡ አንድ ነገር ብታደርጊው የመጨረሻችን ነው፡፡ ደግሞ በስርአት ራስሽ አጥበሽ ነው የምትመልሺው›› ብዬ እያንገራገረኩ ሰጠኋት፡፡



እሺ እሺ ብላ፣ ምላ ተገዝታ ወሰደችው፡፡




በነጋታው አጥቤ አመጣለሁ እንዳላለችኝ በስንት ልመና ከአስር ቀን በኋላ የመለሰችልኝ በአሮጌ ኩርቱ ፌስታል ውስጥ ጎስጉሳው ነበር፡፡


አላጠበችውም፡፡
ላቧና ሽቶዋ ያበላሸውን ቦታ አይቼ ከንዴቴ ሳላገግም ጥለቱ ላይ አዋዜ መፍሰሱን ሳይ ጨስኩ፡፡ 



ያደረገችውን ነገር ስለምታውቅ ጥፍት አለች፡፡




ከብዙ ጊዜ በኋላ እንዲሁ ጉዷን ልይ እስቲ፣ ዝም ብዬ ሰላም ልበላት ብዬ ደወልኩላት።

ያው ስለማንገናኝ። ሁለቴ ጠራ፤ ስልኳን አላነሳችም።



ነገሩን ረስቼው፣ ከሶስት ቀን በኃላ ቴክስት ላከች፡፡



‹‹ ይቅርታ ብታይ አዲሱ ቦታ ስራ ብዝት ብሎብኛል። እኔ የምልሽ…የጥላ ስፓ ስልክ አለሽ አይደል? ዌብሳይታቸው ላይ ያለው አይሰራም፡፡ ካለሽ በናትሽ ቶሎ ላኪልኝ፡፡ ጀርባዬ ቆስሎልሻል፡፡  ዛሬውኑ ማሳጅ መሄድ አለብኝ።›› ይላል፡፡




እንደ ጓደኛ ለሆነ ጉዳይ ካላስፈለኳት አብረን ምሳ በልተን አናውቅም።
እሷን በሆነ መልኩ የማይጠቅማት ከሆነ ሻይ ቡና እንኳን አንባባልም።





ስንት አመት ሳባብላት ኖሬ፣ የእሷ ነገር የቆረጠልኝ ግን የሚከተለው ነገር ሲፈጠር ነው፡፡

እናቴ በጠና ታማ አዲሳባ አምጥቻት ሆስፒታል ገብታ ነበር፡፡



አንዱን ቀን ብቸኝነትና መከፋት ሲያሸንፉኝ ስለመታመሟ ፌስቡክ ላይ ፖስት አደረግኩ፡፡



ለራሴም በገረመኝ ፍጥነት ወዲያው ቴክስት አደረገችና፣


“ወይኔ የእኔ ቆንጆ ሶሪ…ማዘር ምን ሆና ነው…?እስኪ ማታ እደውልልሽና አወራሻለሁ።” አለች።


ሰው ባጣሁ ሰአት ሰው ልትሆን ነው ብዬ እንደ ሞኝ ጠበቅኳት፡፡


እሷ እቴ፡፡


አልደወለችም።



ከ አራት ወይ አምስት ቀን በኃላ ሌላ ቴክስት ላከች፡፡


“ፍቅርዬ፣ እማዬ እንዴት ሆነች?  ተሻላት አይደል? በነገርሽ ላይ ባለፈው ፖስት ስታደርጊ ላንሴት ናት ብለሽ ነበር አይደል ? እስኪ ላንሴቶች ደህና neurosurgeon ካላቸው ጠይቂልኝ በናትሽ፡፡ አጎቴ ታሟል፡፡”




ስያሜ ልሰጠው ያልቻልኩት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ዝም፣ ጭጭ አልኩ፡፡

ዝግት- ቁልፍ አደረግኳት፡፡


---

ይሄው ዛሬ፣ በረቡዕ ምድር፣ በስራ ሰአት፣ አይኗን በጨው እጥብ አድርጋ፣ ሌላ ውለታ ፈልጋ፣ የተፈጠረው ነገር ሁሉ እንዳልተፈጠረ፣ የሰራችኝን ነገር ሁሉ እንዳልሰራችኝ፣

  ‹‹ሄይ  ቆንጂት…! እኔ የምልሽ፣  ሴቭ ዘ ቺልደርን HR ውስጥ ያለ ሰው ታውቂያለሽ እንዴ? ›› ብላ ቴክስት ላከችልኝ፡፡




ወዲያው አልመለስኩላትም፡፡
ለቡና ወጣሁ፡፡
ከባልደረቦቼ ጋር ምሳ በላሁ፡፡
እህቴ ጋር ደወልኩ፡፡ እናቴ መድሃኒቷን መውሰዷን አረጋገጥኩ፡፡


ከዚያ ግን መለስኩላት፣


‹‹አንቺ ግን በቃ ማፈር ተውሽ አይደል….?ለማንኛውም እስቲ ዛሬ እንኳን አፋላጊዎችን ጠይቂ፡፡  8123 መሰለኝ ቁጥራቸው›› ብዬ፡፡


አልመለሰችልኝም፡፡

በዚያው ተቆራርጠን ቀረን፡፡ 

ለነገሩ እኔ አልቆርጥ አልኩ እንጂ እንደ ጓደኛ ከተቆራረጥን እኮ ቆየን፡፡
17.04.202518:04
ባህላዊ date

"ከዚህ በኋላ ባንገናኝ ደስ ይለኛል አልኩት" አለች እጇን አጣምራ

"ማለት?! date ማድረግ ከጀመራችሁ ስንት ጊዜያችሁ ቢሆን ነው?!"

"ሁለት ወይ ሶስት ወር እኔንጃ" ትከሻዋን ሰበቀች

ግራ ገባኝ "ቆይ date ማድረግ ቀልድ ነው እንዴ?! እኔስ የማዝነው ለወንዶቹ ነው" አልኳት

"እዚህ ጋር እኮ ነው እኔና አንቺ የማንስማማው date ማድረግ ማለት እኮ ዘሎ ፍቅረኛሞች ሆኖ boyfriend girlfriend ለመባባል አይደለም ለመተዋወቅ ነው አሁን እኮ ነገር አለሙ ተቀላቅሎብን ነው እንጂ የድሮ date እና ትዳር ቢሆን..."

"ስለ arranged marriage ነው የምታወሪው?!" አልኳት ቅንድቤን ሰቅዬ

"አዎ በቤተሰብ ምርጫ ቤተሰብ ያለበት dating ማድረግ ማለት ነው። ለምን እንደሚጠቅም ታውቂያለሽ ዘሎ አካላዊ ነገር ውስጥ እንዳይገቡ ይጠብቋቸዋል ሌላስ አትዪም?!" አለች እጇን እየሰበሰበች

"ሌላስ"

"ከዛ ደግሞ መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች መጠየቃቸውን ቤተሰብ check ያደርጋል 'ፍቅር ነው ታውረናል' ምናምን እንዳይሉ ማለት ነው። እንደውም የዛ ዘመን ትዳሮች ፍቺ በብዛት አይጎበኛቸውም ነበረ የዘንድሮ በእውር ድንብር እየተገባ እኮ ነው"

"ይሄ ካንቺ ጋር እንዴት ይገናኛል?!"አልኳት እየሳቅኩ

"እንዴት ይገናኛል መሰለሽ ዘመኑ አሁን የነገርኩሽን የdating መንገድ አልፎበታል ቢልም arranged marriage የፋራ ተብሎ ቢቀርም እኔ ለራሴ የቤተሰቦቼን ሀላፊነት ነው እየተወጣሁ ያለሁት date ነው ያደረግነው በይፋ የተባለ ነገር የለም"

"ስለዚህ ተጠናናን ነው የምትዪኝ እና ምኑ ነው ያልጣመሽ" አልኳት ገርማኝ

"ከአንድ መንገደኛ የተሻለ ሊያደንቀኝ አልቻለም 'አይንሽ ያምራል ቁመናሽ ቀሚስሽ' ምናምን ለራሴ ታክቶኛል" አለች በስጨት ብላ

"ማለት ወዶ አይደለም እኮ አትፍረጂበት" አልኳት የተዋጣላት ቆንጆ መሆኗን ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው

"ማድነቁ እኮ አይደለም ምን የሰፈር ተላካፊው እንኳን ያደንቅ አይደል?! ግን ጊዜ መስጠት ማለት ይሄ ከሆነ መግባባት ማውራት ጊዜ ማሳለፍ ምናምን ከአካላዊ አድናቆት ካላሳለፈን አስቸጋሪ ነው"

"በቃ?!" ለመለያየት የምታቀርባቸው መስፈርቶች እያስገረሙኝ መጥተዋል

"አልገባሽም እንዴ?! የማወራውን ካልሰማኝ የመልኬን ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰቤ ማማር ካልታየው ይሄ እኮ ፍቅር አይደለም"

"እና ምንድነው"

"ምኞት ነዋ አፍጥጦ ሰምቶሽ ያልሽውን አንዱንም ካልሰማ ወይ ሀሳቡ ሌላ ጋር ነው ወይ ደግሞ ከአካላዊ ምኞት የዘለለ አላማ የለውም ማለት ነው"

"ነገረሽዋል ግን" አልኳት ባላወቀበት እየተጨፈጨፈ ከሆነ ብዬ

"አዎ ብዙ ግዜ አውርተንበታል ያው ሁሉንም በንግግር የሚፈታ ሳይሆን ግዜ የሚፈታው ስለሆነ በሰላም ተለያየን እልሻለሁ"

"ፐ ዘመናዊነት ብዬ እንዳላደንቅሽ ይሄ ዘመናዊነት አይደለም ግን ጥሩ ነገር ስለሆነ ያወራሽው ይሁን  አልኳት

እንደዚህ ስሜት ላይ ጥገኛ ሳይሆኑ ውሳኔ መወሰን ምንኛ መታደል ነው


✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss
Deleted17.04.202521:19
Shown 1 - 24 of 289
Log in to unlock more functionality.