Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ዳን ŦËŁŁ avatar

ዳን ŦËŁŁ

ያገኘነውን አንዘግንንና "የአእምሮ" ቁርጠት ከያዘን....
ከዚህ ሰፈር ማስታገሻ አለ🤗
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
Location
LanguageOther
Channel creation dateJun 20, 2020
Added to TGlist
Jan 18, 2025
Linked chat

Records

18.01.202523:59
2.4KSubscribers
20.10.202423:59
0Citation index
19.04.202523:59
647Average views per post
31.03.202516:36
66Average views per ad post
22.03.202523:59
30.00%ER
20.04.202515:35
29.00%ERR

Popular posts ዳን ŦËŁŁ

06.04.202504:41
🖤

በእንተ ማርያም ተዘከሪኝ ~ጥላቻሽን አደርጉችኝ፣
ንጣይ ጥሬ ጥላቻሽን~ ከደጅሽ ነኝ አትንፈጊኝ።

መወደድ እንጅ ለሰው~መጠላት ምን ያስቸግራል?
እንዴት በስቃይ ግዞት.............?
ስሰቃይ እያየ ውስጥሽ~ህሊናሽ እንዴት ዝም ይላል?

እውነት ነው ይሄን አውቃለሁ፣
ሁሌም ለውስጤ እነግረዋለሁ።

እንቶ ፈንቶ ሥራ ሰርቶ ~አትችይም ሰው ማስቀየም፣
እጹብ ፍጥረት እንከን የለሽ~የትም ብሄድ አላገኝም፣

ያንችን ምትክ ያንችን ቦታ~አንችን መሠል በዚህ አለም፣
ሰው ማስቀየም ባትለምጅም~በጣም ለአንች ቢከብድሽም፣
እርጅኝ ውቧ አልሰቃይ~ልለምንሽ በእንተ ማርያም።

እንድጠላሽ ማድረግ እኔን ~ምንም ስንኳ ብትፈሪ፣
ከልብሽ ቤት ምንም ባይኖር ~ፍቅር እንጀራን ባትጋግሪ፣
በእንተማርያም ልለምንሽ.........
በፍቅርሽ ራብ ከምሰቃይ~ጥላቻሽን ተዘከሪ።

:- ፍቅረሰብ


Friday, 20 Jan 2017 06:43 PM
20.04.202503:07
ክርስቶስ ተንስዐ ሙታን
በአብይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዜሰ
ኮነ
ፍሰሃ ወሰላም 🙏

"እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላው ገደለ።"መዝ ፸፯(፸፰)፡፮፭

    መልካም የትንሳኤ በዓል
01.04.202507:12
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን
@marda129
27.03.202516:50
Share 'የብርሃን እናት @gbw_dan ዲያቆን ሔኖክ ሃይሌ.pdf'
እርሱ ፦

« ሳንኳኳ ስኖር ከደጅህ
መች ቀና ሊከፍተኝ እጅህ ?»

እኔ ፦

«ታውቃለህ ብኩን ነኝ እኔ - ለራሴ እንኳ የማልረባ
ዝም ብለህ በርግደህ ግባ !»
31.03.202517:12
መክብብ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከመልካም ሽቱ መልካም ስም፥ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።
² ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ በልቡ ያኖረዋልና።
³ ከሳቅ ኀዘን ይሻላል፥ ከፊት ኀዘን የተነሣ ልብ ደስ ይሰኛልና።
⁴ የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።
⁵ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል።

ፋኖስ ገፄን ተመልክተው፥
ሰዎች ለጉድ አደነቁ
ህጻናት እኔን መሆን ተመኝተው ፥
አዛውንት በደስታ ሳቁ
"ዘላለም ብራ "
ብለው መረቁ...
(የቀኑም አሉ በ'ውነቱ...)

እንስቶች አይናቸው ሞቀ ፥
ባ'ይኔ ፍም ተጥበረበሩ
{ አይተውኝ ግን ያልወደዱኝ
በቁጥር ስንት ነበሩ?}

( ቢሆንም...)

ልቤ ግን ደስ አላለውም፥
ለብቻ ስመረምረው
አንቺ አይተሽ ያልተሳብሽበት፥
ፀዳሉ ለ'ሱ ምኑ ነው?

:- ግዑዝኤል
02.04.202504:13
በዓለም አንዲት ጥላ
---
ሀሳብ ይዘው የሚያርፉባት
ትንሽ አፀድ ፤
ወዳጅ ጋር ሚዘፍኑባት
ትንሽ መንገድ ፤

ትንሽ ጣፋጭ
ለጨዋታ ፤
ትንሽ ህመም
ለትዝታ ፤

ዘፈን ፣ . . .
ለስለስ ያለ
ዕድሜን ማስታወሻ ፤
ወዳጅ ፣
ደመ - ግቡ
ቢጠልቁት ቢጠልቁት ፤ የማይጎድል
ልቡ ።

ደግሞ ፍቅር
የልብ እሳት፤ እንዳይጠፋ የምትነግር።

ሕይወት ይሄን ካደላት
ምን ጎድሎባት ! ?
ምን ጎድሎባት! ?

የዱር አበባ - ቴዎድሮስ ካሳ ☕
___

[
ሰምታቹሃል ?የምር አይቀርም

#በነፃ
28.03.202522:47
እባካችሁን ቤተሰብ ይህን ቻናላችንን ሰብስክራይብና ላይክ በማድረክ አበርቱን 🙏


በሸጋ ሸጋ ስራዎች እኛም አናስከፋዎትም !!!


Hiyab Kids ❤👪
18.04.202506:18
ሕማማተ ከንፈር
...................

ውሃ ጠጥታችሁ አልረካ ብላችሁ አታውቁም? ምግብ በልታችሁስ ሆዳችሁ ጢቅ ብሎ ሞልቶ አፋችሁ ላይ የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ተሳምቷችሁ አያውቅም ?
.
እሷን ስስማት የሚሰማኝ ይህ አልረካ ባይነት ነው። በምን መልኩ ብስማት የልቤ እንደሚደርስ አላወቅም ። ያልሞከርኩት መንገድ የለም። በቃ መጨረሻ ላይ ትግሌ ሁሉ በድካም ይጠናቀቃል።
.
ሁሌ ከንፈሯ ይናፍቀኛል።
.
" ምኔን ነው የወደድከው ? "
'' ከንፈርሽን "
" ምን ላርግልህ ?''
" ሳሚኝ ! "
.
የተዋወቅው የሆሳዕና ለት ነበር... አንገትና ፀጉሯን በነጠላዋ ሸፍና መዝሙር ስትዝምር። ቃላቶቿን ከአፏ ላይ ለመልቀም ትኩረቴን ወደ ከንፈሯ ግድም አደረኩኝ። ቢሳለሙት የሚያፀድቅ ታቦት !... የሰዎች ግርግር ሊከልለኝ ሲያጣጥር እንደምንም እያደረኩ ሳያት አረፈድኩ። የዛን ቀን ነበር የተዋወቅነው... ወደ ኋላ ጠብቄ ሰላም አልኳት...

" ስትዘምሪ ደስ ትያለሽ ? "

" አመሰግናለሁ " የሰንበት ተማሪ ሀፍረት ፊቷ ላይ ይነበባል... አንገቷ ወደ ታች ተደፍቶ አይኗ ሺህ ቦታ ያያል...

" ሆሳዕና በአርያም... ሆሳዕና በአርያም... ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም፡... "...አይደለም ለመዝሙር ለዘፈን በማይሆን ድምፄ የተወሰነ ሲሉት ከነበረው አልኩላት ፊቷ...

" ቃለ ሕይወት ያሰማልን ! "

" እንዴት ነኝ ? "

" አንደበት ያለው በሙሉ ፈጣሪውን ማመስገን አለበት። ማማር አለማማር ሁለተኛ ጥያቄ ነው። ከልብህ መሆኑ ነው ዋናው..."

" ከንፈርሽ ያምራል " ከከንፈሯ ይልቅ ሀሳቧን ማድነቅ እንደነበረብኝ የተረዳሁት የተናገርኩትን ካልኩት በኋላ ነበር..

" እ.....?." ደንግጣለች " እሺ ቻው... መልካም በዓል " ብላ በመርበትበት ጥላኝ ልትሄድ ስትል...

'' አልተዋወቅንም ግን ? "

" ማሕደር "

" ባሮክ ። ስልክሽን ለውስድ ? "
ሰጠችኝ።
.
የዛኑ ለት ደወልኩላት። ብዙ አወራን። አብዛኛው ወሬዎቻችንን ሀይማኖት እየጠለፋቸው ጉባኤ ውስጥ ያለን ይመስል ነበር። ስለ ራሷ ነገረችኝ። አባቷ ወታደር እንደነበርና በሰሜኑ ጦርነት እንደምተ። እናቷን ደግሞ እንደማታውቃት - (በህፃንነቷ በመኪና አደጋ ነበር የሞተችባት። ) አብራት የምትኖረው አያቷ ስትሆን እሷንም ደክሟታል... 70 ከተሻገረች አመታትን አስቆጠረች።....
እሷን መስማት ላይ ተጠምጄ ስለኔ ብዙም አላወራኃትም።
.
በቀጣዩ ቀን ሕማማት የመጀመሪያ ቀን ነበር። በጠዋቱ ቤተ ክርስቲያን ሄድኩ ። ልጠብቃት።

" አባታችን ሆይ...
የዘላለም ማሕደሬን አትንሳኝ
ወዳቂ ብሆንም በፊትህ - እሷ ፊት ግን ቀና አርገህ አንሳኝ !
..... "

ከሩቅ ስትመጣ አየኋት ። ከሩቅ እየመጣች አየችኝ። መሀላችን የተፈጠረውን የአንድ ቀን ተዓምር አላውቅም። ብቻ ስትመጣ ያየሁት ፊቷ ሁሉ ነገር እንዳለቀ ይናገር ነበር። ከቤተ ክርስቲያኑ ትንሽ ራቅ ወዳለና ወንድና ሴት አብረው መቀመጥ ወደሚችሉበት ቦታ አመራሁ... በጄ ምልክት ሰጥቻት። ተሳልማ መጣች። ተነስቼ ላቅፋት ነበር።

" እንዴ ሕማማት እኮ ነው..." አለችኝ... አፈርኩ ። ብቸኝነት፣ ድብርት፣ ራስህን አለመሆን የሚባሉ ሕማማቶቼን ታክምልኛለች ብዬ ተስፋዬን የጣልኩባት ሴት ፊት ስለ ጌታ ሕማም ዝንጉ ብሆን ማን ይሆን የሚፈርድብኝ ?...
.
በየመሀሉ እየሰገድን ብዙ አወራን (በየመሀሉ እያወራን ብዙ ሰገድን )... ማክሰኞም ያኑ ቀን ተደገመ.. ሮብም... ሐሙስም.....።
.
ምክንያት ስላገኝለት ውስጤ እንደ ወደደችኝ ይነግረኛል። ሁሉ ነገር እንዲህ በፍጥነት በመሆኑ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ተጋባሁ። አሁን 'ተመስገን ' ነው ሚባል ? ወይስ 'እንዴት' ?... ግራ ገባኝ... የስቅለት 'ለትም አብረን ስንሰግድ አመሸን። እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት የቤተ ክርስቲያኒቱን ስርዓት ሰንከታተል ቆይተን... ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲበተኑ እኛ እዛው ቁጭ አልን ( ግርግሩ ይረጋጋ ብለን )....
.
ቁጭ ስንል ወግ ያዝን...

'' ባለፈው እንዲያ ዘምረንለት የሆነ ቀን ምናልባት እንከዳው ይሆናል እኮ!? ''

'' ይሆናል !... አይሆንም የሚባል ነገር እየጠፋ ነው ''

'' የምሬን እኮ ነው የምልህ... አሁን እንደ ፈጣሪ የከሰረ አካል አለ ትላለህ ?... ፈጥሮ መና... ሰርቶ ገደል "

'' የእውነትሽን ነው "
.
ሰዓቱን ስናየው ሁለት ሰዓት አልፏል። ከኔ ጋር እንድትሄድ ጠየኳት ( መሽቷል በሚል... ሰበብ)... ትንሽ አቅማምታ ተሰማማች። ለአየቷ ደውላ አሳወቀችና ወደ 'ኔ ቤት አመራን ። ብቻዬን ነው የምኖረው - ከማንም ጋር። ሴት ወደ ቤቴ ሲገባ እራሱ የመጀመሪያ ቀን ዛሬ ነው ።
ራት በላን ( የወንደ ላጤ ቤት 'ምን 'አይባልም)
.

ከዛም አንድ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን። ድንገት ሳናውቀው ተቀራርበናል። ብዙ ሰዓት እሷ ስታወራ እኔ አደምጣታሁ። ከንፈሯን ለማየት ስል።
.

ሳላ(ታ)ስበው ቀስ ብዬ ከንፈሯን ሳምኩት። አልከለከችኝም። ዝም ብላ ተሳመችኝ። ዝም ብዬ ሳምኳት ። ከዛ የተወሰነ ገፋ አረገችኝና
" ሕማማት ነው ! '' ብላኝ ወደ መኝታ ቤቱ አመራች። በሰራሁት ስራ አፈርኩ። እዛው ሶፋው ላይ አደርኩ።
.
ጠዋት ስነሳ ቤት ውስጥ የለችም። ስልክ ደወልኩላት - አታነሳም። ቤተክርስቲያን ሄድኩ - የለችም። እዛው ጠበኳት - አልመጣችም።
ቅዳሜን እዛው ቤ/ክ ውስጥ እሷን ስጠብቅ አመሸሁ... ማታም እዛው አደርኩ። የሌሊቱ ድባብ የተለየ ቢሆንም እኔ ግን አልተሳተፍኩም ነበር ( አንድም ማታ በልቻለሁ - ሁለትም ማሕደርን ተርቤያለሁ )... ሲነጋ ትመጣ ይሆናል በሚል ተስፋ (ሙሉ ተስፋ ) ጠበኳት...አልመጣችም። እኔን ላለማግኘት ሌላ ቤ/ክ ሄዳ ይሆን 'ዴ ? ስል አሰብኩ።
.
ቁርሴን አንድ ቁርስ ቤት ዶሮ ወጥ በላሁና ወደ ቤቴ አመራሁ ። እንኳን አደረሰህ ለማለት የተደወሉ ስልኮችን ስመልስ አረፈድኩና ከሰዓት ለማሕደር ደግሜ ደወልኩላት። አታነሳም። " እንኳን አደረሳሽ " የሚል text ላኩላት :: አትመልስም።
.
የዛው ለት እሁድ ወደ ማታ አስራ ሁለት ሰዓት በሬ ተንኳኳ። ሄጄ ስከፍት እሷ ናት ።

" ይይ.. ይቅርታ... '' እያልኳት ሳለ ሌባ ጣቷን ከንፈሬ ላይ አረገችና ወደ ቤት ገባች። ከንፈሬን ከጣቷ አላቃ በከንፈሯ ተቀበለችው።....

.
የዛን አመት በሙሉ ባገኝኋት ቁጥር ዘልዬ ከንፈሯ ላይ ቁብ እላለሁ ... ላልጠግባት ጉዳይ:: እየሳምኳት ራሱ ትናፍቀኝ ነበር::
.
" መጀመሪያ ቀን ምኔን ወደድከው ''

" ከንፈርሽን ! ''

'' እንዴ ድምፄንስ ? "

" ከንፈርሽን!... በውነቱ በሰዓቱ ያንቺን ድምፅ ለይቶ ሙሉ ለሙሉ መስማት ከባድ ነበር። ነገር ግን ወደ ከንፈርሽ የመራኝ.. ጥቂትም ቢሆን ውበቱ የሳበኝ ድምፅ ነበር ። ''

'' እሺ ምን ላርግህ ? ''

" ልሳምሽ! "

" ሌላስ ? "

" ሳሚኝ ! ''
.

አመት አልፎ ሌላ ሕማማት መጣ... በዚሁ ሕማማት እንዲሁ ስንሰግድ፣ ስናወራ.. ስናወራ፣ ስንሰግድ ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስ አለፉ........
05.04.202505:58
በታችም በምድር
(ልብወለድ)

በሌሊሳ ግርማ

ይኼ ለብቻው በስሙ ከጻፋቸው መጻሕፍት (ማለትም ሙሉ በሙሉ የእሱ የሆነ) 7ኛ መጽሐፍ መሆኑ ነው። በበርካታ እና የተለያዩ መድብሎች ውስጥ በብዛትም ጽፏል። ከእነዚህ መጻሕፍት ውጭ በየጋዜጣዎቹ እና መጽሔቶችም በኔ ዘመን በሙሉ ሲጽፍ፣ ሲፈላሰፍ፣ ሐሳብ ሲያቀነቅን፣ በግጥሞቹ ሲያንሳፍፈኝ የማውቀው ደራሲ እንደመሆኑ መጠን እሱ የጻፈው መጽሐፍ መሆኑን ማወቄ የሆነ ባያዝ እንዲኖረኝ ሊያደርገኝ ይችላል ---

ደራሲ ወንድሙ ገዳ ሮናልድ ባርትስን የተባለ ምሁርን ጠቅሶ «የደራሲ ሞትና የአንባቢ ልደት» ጽንሰ ሐሳብ ብሎ ያስነበበን ጽሑፍ ላይ - በተለይ ድሕረዘመናዊ ድርሰቶች ሲነበቡ ደራሲው ‹ቢገደል› ጥሩ ነው የሚል ትልቅ ጉዳይ አስገንዝቦኛል። ማለትም የፈጠራን ድርሰት ስናነብ ጸሐፊውን (ፈጣሪውን) ከሕሊናችን ብናወጣው ብሎ ጠቁሞኛል። እናማ በታችም በምድርን ሳነብ፤ ደራሲው ሌሊሳ መሆኑን ባላውቅ ኖሮም ከኔ ጋር የሚቀሩ ብዙዙ ፍልስፍናዎችና ቁምነገሮች የሰጠኝ ድርሰት ነው።

ምናባዊ ፈጠራ፣ ወጥ ድርሰት ነው።

ሌላው ሌሊሳን የምናውቅበት መገለጫው ደግሞ የአጫጭር ታሪኮች ደራሲ መሆኑን ነው። ይኼ ረጅም ወጥ ልብወለዱ ውስጥ የአጭር ትረካ ዝንባሌውን - አጠር አጠር ባሉ ምዕራፎች እና መቋጫዎች ያሳየናል። ሆኖም ግን ረጅም ልብወለድ ነው። መጽሐፉ መጀመሪያ አካባቢ ገጸባሕሪያቱ ትንሽ በዝተውብኝ ተደናግሬ ነበር። ታሪኩ እየጎለበተ ሲሄድ እና ዋናው ገጸባሕሪ ከለየ በኋላ ግን በቃ ጭልጥ አድርጎ የሚወስድ ትረካ ነው።

የተራራዋ ከተማ ቱርኪሚርኪን እናውቃታለን፤ ግን ደግሞ የፈጠራ ከተማም ናት። ኧረ ምን ቦታውን ብቻ፣ ከተማዋ ውስጥ ያሉትን ሰዎችም እናውቃቸዋለን፤ ስማቸው ግን አይያዝልንም። ማለቴ የገጸባሕሪያቱ ስሞች በአመዛኙ የማይያዙ የፈጠራ ስሞችም ናቸው። የቦቱ ቤት፣ የኮነሬሉ ቤት / ማቅለጫው - የቀለጠው መንደር ይመስለኛል፤ ምናልባት ጥበብ ጠራችኞች እና ሌሎ ራሱ በሰየመው ስማቸው የ‹ጀዝቢቲዮዶች› መሰባሰቢያ። የኮነሬሉ ቤትም በመባል ይታወቃል፤ ምናልባት ቤተመንግሥት ይሆን እንዳልል ደግሞ - ስነጥበብ፤ ኪነጥበብ፤ አርቲስቶች፣ ዲስኩረኞች እና ጋዜጠኞች (ሰላዮችም) የሞሉበት ቤት ነው። ምናልባትም ድብን ያለ ፈጠራ ውስጥም ሆነን ፖለቲካ የለውም የሚባል ነገር የለም መሰለኝ።

ብዙ ዓይነት ፍልስፍናዎች እና አመለካከቶችን በብዙ ዓይነቶቹ ገጸባሕሪያት በኩል ይፈትሻል፤ ይጠይቃል፤ እንድናስብባቸውም ያደርገናል። ከሁሉም ጎላ ብሎ በተለይ ፌሚኒዝምን በጣም የሚፈትሽ እና የሚያብሰለስልም ነው። አቤት የሴቶቹ ጉዳይ! ገዳይ ነው!!!

ፍቅርንም ይሰብካል፤ ማጠንጠኛው ግን ያው እምነት ነው። የመጽሐፉ ማካፈያ ምዕራፍም ‹እምነት› ነው። ገጽ 99

አጠቃላይ የመጽሐፉ መልእክት እምነት እና ፍልስፍና ለየቅል ናቸው ለማለት የሚሞክር ሆኖ ተሰምቶኛል (ያው የግል እይታዬ ማለቴ ነው)።

ፍቅር፣ እምነት እና ተስፋ ጸንተው ይቆያሉ አይደል የሚለን ቃሉ።

የዚህ መጽሐፍ ዋነኛ ማጠንጠኛም ‹እምነት› ስለሚባለው ነገር ነው። ፍቅር ከጥላቻ አንጻርም ይፈተሻል። ተስፋ እራሱ እምነት ውስጥ የተሰፋ ነገር እንጂ ተስፋ ያለ እምነት አይኖርም የሚለን መስሎ ተሰምቶኛል። እምነት ውስጥ ጥፋተኝነትን መቀበል እንዳለም ለማሳየት ኤሎም የተከሰሳባቸውን ነገሮች በሙሉ እራሱ ሆን ብሎ ያጠፋቸው ጥፋቶች ባይሆኑ እንኳን፤ እኔም ጥፋተኛ ነኝ ብሎ ይቀበላል።

ከባባድ ፍልስፍና፣ ሐሳቦች እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ብቻ ሆነው እንዳያታክተን ደግሞ አሽሙር እና ወሬ ቢጤዎች ታሪኩን ያዋዙልናል። ቦቶ፣ ኮነሬል፤ ስትሮብ፣ ክላምፕ ወዘተ የሚባሉትን ገጸባሕሪያት የማውቃቸው ጥበበኞች ይሆኑ እንዴ ብዬ ገና ከማሰቤ፣ እልም ያሉ ፈጠራዎች መሆናቸውን የሚያስታውቅባቸው ነገሮችን ይጨምርበታል።

ያው ዞሮ ዞሮ ማጠንጠኛው ግን የእየሱስን መንገድ ስለመከተል እና ጌታን የግል አዳኝ አድርጎ ስለመቀበልም እና በዋናነት ስለ እምነት ነው።

Ironically ደግሞ ዋና ገጸባሕሪውን ወደ እየሱስ አማኝነት ያመጣው መምህሩ ተገልብጦ ሎጂካል ብቻ አማኝ፣ ለሱ ብቻ የሚስማማውን የሚመርጥ ‹አድርባይ› አማኝ ሆኖ ይገኛል። ገጽ 213
«ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ» አለው ኤሎም።
«በጌታ ደስ ይበላችሁ ... ከሚለው ጥቅስ ዛሬ ቀኑ እንዴት ደስ ይላል ወደሚለው ተሸጋግሬያለሁ» ... ገጽ 218
--
ብቻ እኔ ዝም በዬ የተሰማኝን ለመቀበጣጠር ያህል ነው እንጂ - በተለይ የመጽሐፉ መዝጊያ እጅግ የሰቀለ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ደግሜ የማነበውም ነው።

በአጠቃላይ ግን ዝም ብዬ እንዳመጣልኝ መሞነጫጨሬ
ኧረ ይነበብ! ለማለትም ነው።

ይ ነ በ ብ!!!
18.04.202506:18
አርብ ለት እንደተለመደው አብረን የምናሳልፍ መስሎኝ ነበር። ነገር ግን ብጠብቃት አልመጣ አለች ። ደወልኩላት። አያቷን አሟቸው ክሊኒክ እንዳሉ ነገረችኝ ። እየበረርኩ ለመሄድ የት እንዳሉ ስጠይቃት እኔ እዛው እየፀለይኩ እንድጠብቅ ነገረችኝ። እሷን መቃወም አይሆንልኝም። ቃሏ አይመረመርም..(. ለምን ? የለውም፤ አሜን! እንጂ። ) ማታ አንድ ሰዓት አካባቢ ቤት መጣ አይታኝ እንደምትመለስ ነግራኝ ስልኩ ተዘጋ ።
.
1 ሰዓት ሆነ።
.
ቤት ሆኜ ያለፈው ዓመት በዚች ቀን ያረግነው ሁሉ ትዝ ይለኝ ጀመር... አሁን ፈጣሪ ይቺን እንደ ሀጢያት ቆጥሮ ይበቀለኝ ይሆናል።

.... ምናል ይቅር ቢለኝ... እሱ ለፍቅር ሲል ሲሞት እኔ ምናል ለፍቅር ብዬ ሕጉን ብሽረው... ?
.
2 ሰዓት አለፈ... ስልክ ደወልኩ ። አይነሳም ።
.
3 ሰዓት... ቴክስት ፤ አይመለስም።
.
4 ሰዓት...5.....6...
.
12 ሰዓት ሲል ወደ ቤታቸው በሩጫ አጣደፍኩት። ነገር ግን መሀል ላይ የሰማሁት ዜና እግሬን አስሮ የሚጥል ነበር።
.
ማሕደር ወደኔ ስትመጣ መኪና ገጭቷት ሞታለች።።።።።።
.
በቃ ፈጣሪ ተበቀለኝ ማለት ነው? ግን ለምን እሷ ላይ ? እኔ ምኔ ያስፈራል... አህያውን ሲፈሩ መዳላድሉን አይነት ድርጊት... ነው ከመምቴ በላይ መሞቷ እንደሚያሳመኝ አውቆ ? እውነቱን ነው
.
ከሞት በላይ ሀዘን ያማል። ''ይብላኝ ለሟች እንጂ...." ብሎ ተረት የለም... ይብላኝ ለቋሚ ነው ፤ የሚወዳቸው ሰዎች ሞት ለሚጥለው... ይብላኝ ለኔ ነው....ከማሕደር ዉጭ መቆም ለሌለኝ...
.
ከዛን ዓመት ጀምሮ ሕማማት ሲመጣ ቁጥር ሁሌ ሆን ብዬ እገድፋለሁ... እስከ ሆሣዕና እፃምና ሰኞ በጠዋቱ ቁርሴን እንቁላል እባላለሁ... እስከ አርብ ይቀጥላል... ከዚህ ድርጊቴ ምን እንደምፈልግ ግን አላውቅም...

... ምናልባት በቀል
...ምናልባት ቅጣት
... ምናልባት እረፍት
... ምናልባት ጥል
... ም
...ና
... ል
...ባ
... ት
... ፍትህ.......

© ባሮክ
18.04.202503:17
📚ርዕስ:-  ዐስራ ስድስት
📝ደራሲ:- ደመወዝ ጎሽሜ
📜ዘውግ:-...
📆ዓ.ም:- 2014
📑የገፅ ብዛት :- 481
💰ልጥፋ ዋጋ:-
650  (4ተኛ ዕትም)

©ብ.መ
28.03.202514:20
ሕይወት ዋጋ ሲኖረው...🤔

የ 9/11 የኒውዮርኩ ጥቃት ከተከሰተ  ከሁለት ሰአታት በኋላ ፡ እዛው አሜሪካን አገር ፍሎሪዳ የሚኖረው ቫን ሰርቲማ በኃይለኛ እባብ ተነደፈ።
......
የማያሚ ባብቲስት ሆስፒታል ሀኪሞች Taipan በሚባል እጅግ  መርዛማ በኾነ  የእባብ ዘር  የተነደፈውን  የ62 ዓመቱን ላውረንስ ቫን ሰርቲማን ለማዳን የቻሉትን መጣር ቢጀምሩም መድኃኒቱ በዚያ ሆስፒታልም ሆነ በከተማው ውስጥ ባለመኖሩ ቁርጥ ሕክምና መስጠት አቃታቸው።
....
በኋላም ባገኙት መረጃ ይህ ሰውየውን ማዳን የሚችለውን የእባብ መርዝ ማርከሻ መድኃኒት ( anti venom ) በሳንዲያጎ በሚገኝ የእንስሳት ዙ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል እንደሚገኝ ታወቀ።
.....

ማለትም ይህንን መድሀኒት ለማግኘት በአንድ ሀገር ውስጥ ቢኾንም  3,649.22 ኪሎ ሜትር ለሰዓታት መጓዝ ግድ ነው።
ግን ችግሩ የቦታው ርቀት አይደለም ፡ ዋናው ችግር የሆነው ፡ ከሰዓታት በፊት መላው አሜሪካንን ያስደነገጠውና የኒውዮርክን መንታ ሕንጻዎችን ባወደመው ጥቃት ምክንያት ፡ በመላው አሜሪካን አየር ላይ ፡ ከጦር አውሮፕላን ውጭ አንድም ፕሌን እንዳይበር ተከልክሎ ነበርና ነው።
........
ስለዚህ በእባብ የተነደፈው አዛውንቱን አሜሪካዊ መድኃኒቱን ካላገኘ በሕይወት አይተርፍም ማለት ነው።
...
ሆኖም የማያሚ ባፕቲስት ሐኪሞች የአንድ አሜሪካዊ ሕይወት በዚህ ኹኔታ ማለፍ የለበትም በሚል  ፡ ሰውየውን ለማዳን ባለስልጣናትና ፡ ኃላፊዎች ጋር መደዋወል ጀመሩ።
....
ከሰዓታት ጥረት በኋላም ያሰቡት ተሳክቶ በረራ ተፈቀደላቸው።
አንድም የህዝብም ሆነ የግል አውሮፕላን በሌለበት ፡ በመላው አሜሪካን በብዙ  በሺህ የሚቆጠሩ በረራዎች ተሰርዘው ፡ ጭር ባለው   ሰማይ ላይ ፡ የላውረንስ ቫን ሰርቲማንን መድኃኒት ለምታመጣው  Cessna 172 Skyhawk አውሮፕላን ብቻ ፍቃድ ተሰጠ።
......
እንደዚህም ኾኖ ይህን የፈቀዱት ባለስልጣናት ፡ ይህ በረራ ከሽብር  ጥቃት ጋር ግንኙነት የሌለው. ..ወይም  ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ አውሮፕላኗ በኹለት ተዋጊ ጀቶች ታጅባ እንድትሄድ አደረጉ።
.....
ከብዙ ሰዓታት በኋላም  የጠፋው መድሀኒት ከሳን ዲያጎ መጥቶ የላውረንስ ቫን ሰርቲማን ሕይወት ከሞት ተረፈ።
...
ሺህዎች በየቀኑ  የሚሞቱባትን የአሳዛኟን አህጉር ፡ የአፍሪካን ነገር አይተን፤ በተቃራኒው ደግሞ አሜሪካ አንድ  ዜጋዋ ያላግባብ እንዳይሞትባት ምን ያህል ዋጋ እንደምትከፍል ስንሰማ ፡ ያለውን ልዩነት ያስገርማል።🤔
........

እዛማ የሰው ሕይወት ዋጋ አለው።


ምንጭ:- ዋስ ይኹን ተስፋዬ

#America
#life
#humanity
#medical
#media
#peace

© ንስር ሕክምና - @NisirHikimna / @Nisirhikimna777

ኹልጊዜም ከእናንተ ጋር
!
Log in to unlock more functionality.