🕊
[ † እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † በዓለ ጽንሰት † 🕊
† ይሕች ቀን ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ልዩ ናት:: በዓመቱ ከሚከበሩ በዓላትም አንደኛውን ሥፍራ ትይዛለች::
በዚሕ ዕለት አምላካችን እግዚአብሔር:-
፩. ሰማይና ምድርን ፈጠረ:: [ዘፍ.፩፥፩]
፪. በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ [ተጸነሰ]:: በዓሉም "በዓለ ትስብእት" ይባላል:: "አምላክ ሰው : ሰው አምላክ የሆነበት" ማለት ነው:: [ሉቃ.፩፥፳፮]
፫. የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ:: [ማቴ.፳፰፥፩ ፣ ማር.፲፮፥፩ ፣ ሉቃ.፳፬፥፩ ፣ ዮሐ.፳፥፩]
፬.ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚሕች ቀን ይመጣል:: [ማቴ.፳፬፥፩]
††† በነዚሕ ታላላቅና ድርብርብ በዓላት ምክንያት ቀኑ "ርዕሰ በዓላት" [የበዓላት ራስ] : "በኩረ በዓላት" እየተባለም ይጠራል::
† ቸሩ እግዚአብሔር ዓለምን ከመፍጠሩ : ከጽንሰቱ : ልደቱና ትንሣኤው በረከትን ይክፈለን:: በጌትነቱም ሲመጣ በርሕራሔው ያስበን::
† ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እልዋሪቆን ገብቷል:: ይህች ሃገር የምድራችን መጨረሻ ናት:: ከዚያ በኋላ ሰውና ሃገር የለም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን የሰበከ ሐዋርያ የለም::
† ከቅዱሱ ሐዋርያ ትጋት : ቅናት : መንፈሳዊነትና ንጽሕና አምላካችን ይክፈለን::
🕊
[ † መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]
፩. ጥንተ ዕለተ ፍጥረት [ዓለም የተፈጠረችበት]
፪. በዓለ ትስብእት [የጌታችን ጽንሰቱ]
፫. ጥንተ በዓለ ትንሣኤ
፬. ዳግም ምጽዐት
፭. ቅድስት ማርያም መግደላዊት
፮. ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ
፯. ቅዱሳት አንስት [ትንሣኤውን የሰበኩ]
፰. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ [ጽንሰታ]
፱. አብርሃ ወአጽብሐ [ጽንሰታቸው]
፲. ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ [ጽንሰቱ]
፲፩. ቅዱስ ላሊበላ [ጽንሰቱ]
፲፪. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ [ጽንሰታቸው]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫. ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]
† " እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል:: ዓይንም ሁሉ : የወጉትም ያዩታል:: የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ:: አዎን አሜን:: ያለውና የነበረው: የሚመጣውም: ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ: አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ ይላል::" ††† [ራእይ ፩፥፯]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖