Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ገዳማውያን avatar
ገዳማውያን
ገዳማውያን avatar
ገዳማውያን
                         †                         

🕊    †    ሰሙነ ሕማማት   †    🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

           [   ሕማማት ዘረቡዕ   ]


[ † ምክረ አይሁድ ይባላል † ]

ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው [ ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ] ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

[ † የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል † ]

ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በስምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት [ ባለሽቶዋ ማርያም] ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው [ ማቴ ፳፮፥፮-፯ ] የመዓዛ ቀን ይባላል።

[ † የእንባ ቀን ይባላል † ]

ባለሽቱዋ ሴት [ ማርያም እንተ እፍረት ] ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና [ ማር ፲፬፥፱ ] የእንባ ቀን ይባላል።

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

- [  ብፁዕ አቡነ እንድርያስ ስለ ሰሙነ ሕማማት ያስተማሩት ትምህርት [ ክፍል - ፩ - ]


- [  የሰሙነ ሕማማት ዘረቡዕ [ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ]

💖    ድንቅ ትምህርት   💖

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
                        👇
                       †                       

  [   🕊  ሕ ማ ማ ት   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕማማት + ለምን + እንዴት  ]

🕊             

[  የሕማማት ሳምንት ሥርዓቶች ! ]

- የሕማማት ትርጉምና ምሥጢር
- ጸሎትና የጸሎት መጻሕፍት
- የጾም ሰዓትና ሥግደት
- ሌሎችም ሥርዓቶች

    💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇
15.04.202503:36
13.04.202516:27
[     ሰ ሙ ነ ሕ ማ ማ ት      ]


[ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕለተ ዓርብ መከራ በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ]

[   ሕማማት   ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
ለዋይፋይ ተጠቃሚዎች በምስል ወድምፅ [ Video ]
13.04.202512:59
“ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል፤ ወንድምም ለመከራ ይወለዳል።”
— ምሳሌ 17፥17
15.04.202518:40
15.04.202518:28
13.04.202516:27
13.04.202512:59
†                †                †

[   † ሰሙነ ሕማማት  †   ]

                      †                       

‹ ሰሙን › – " ሰመነ ስምንት [ ሳምንት ] አደረገ " ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከዕለተ ሆሣዕና ሠርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ወይም ቀናት የሚያመለክት ነው፡፡ ‹ ሕማም [ ሕማማት ] › – ‹ ሐመ ታመመ › ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ይህም የሰውን ዘር ዂሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኵነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት ፣ የሚያለቅሱበት ፣ የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚማጸኑበት ፤ ጧት ማታ ደጅ የሚጠኑበት ፤ ኀጢአታቸውን በቤተ ክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው፡፡

                      †                       

በዚህ ሳምንት ብዙ አዝማደ መባልዕት አይበሉም ፤ ይልቁን በመራብ በመጠማት በመውጣት በመውረድ በመስገድ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራዎች በማሰብ አብዝቶ ይሰገዳል፡፡ መከራውን ፣ ሕማሙን ፣ ድካሙን የሚያስታውሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ኢሳይያስ ፣ ኤርምያስ መዝሙረ ዳዊት ፣ ግብረ ሕማማት ወዘተ በየሰዓቱ ይነበባል፡፡ መስቀል መሳለም የለም፡፡ ካህናትም " እግዚአብሔር ይፍታህ " አይሉም፡፡ ሥርዓተ ፍትሐት አይፈጸምም፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወቅት ምሳሌ በመኾኑ ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት መላእክት የመለከት ድምፅ በማሰማት የዳግም ምጽአትን ዕለት ለማሳሰብ ምእመናን ጥሪውን ሰምተው ለዚህም አስቀድመው ተዘጋጅተው የበዓሉ ታዳሚዎች መኾናቸውን በማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ በየሰዓቱ ምእመናኑን ያሳስባል፡፡

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🕊                      †                        🕊

[ + ሆ ሳ ዕ ና + ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬


❝ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ላካቸው ፤ በፊታችሁ ወዳለችው ሀገር ሂዱ የታሠረ የአህያ ውርንጫ ታገኛላችሁ ፈታችሁ አምጡልኝ አላቸው ፤  ደቀ መዛሙርቱም እንዳዘዛቸው አደረጉ ፤ የአህያ ውርንጫ አመጡለት ጫኑት ፤  በጎዳና ላይ ልብሳቸውን የሚጎዘጉዙ ነበሩ ፤ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው አመሰገኑት ፤ ብዙ ሕዝብ ሽማግሌዎች ሕፃናት ለዳዊት ልጅ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት ፤ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ገባ ፤ በነቢይ እንደተነገረው እግዚአብሔር የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ እኔ ወደ አንቺ እመጣለሁ በመካከልሽም እመላለሳለሁ ፤ ለዘለዓለም ደስ የማሰኝሽ እኔ ነኝ አለ። ❞

[ ቅዱስ ያሬድ  ]


🕊                        💖                       🕊
13.04.202516:27
                       †                       

   [    ሰ ሙ ነ   ሕ  ማ  ማ  ት    ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[     በምሽቱ መርሐ-ግብር     ]


[ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕለተ ዓርብ መከራ በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ]

[   ሕማማት   ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
13.04.202511:51
Пераслаў з:
ማኅደረ ተዋህዶ avatar
ማኅደረ ተዋህዶ
15.04.202518:32
የሰሙነ ሕማማት
ሦስተኛው ቀን
#ምክረ አይሁድ
#የመልካም መዓዛ
#የእንባ ቀን
15.04.202503:36
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

[ † እንኩዋን ለጻድቅ ሰው "ቅዱስ ኢያቄም" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊   † ቅዱስ ኢያቄም  †    🕊

ቅዱስ ሰው ኢያቄም የሰማይና የምድር ንግስት እመቤታችን ድንግል ማርያም አባት ነው:: ቅዱሱ ከቅስራ አባቱ የተወለደ የቅዱስ ዳዊት ዘመድ ሲሆን "ኢያቄም : ሳዶቅ እና ዮናኪር" በሚባሉ ፫ [3] ሰሞቹ ይታወቃል::

ቅዱስ ኢያቄም እንደ ኦሪቱ ሥርዓት አድጎ : ከነገደ ሌዊ የተወለደች : የማጣትና ["ጣ" ጠብቆ ይነበብ] ሔርሜላን ልጅ ሐናን አግብቷል:: ሁለቱም በንጽሕናና በምጽዋት እንደ ሕጉ ቢኖሩም መውለድ የማይችሉ መካኖች ነበሩ::

በዚሕ ምክንያት ከወገኖቻቸው ሽሙጥን ታግሰው በታላቅ ሐዘን ኑረዋል:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ስም አጠራሯ የከበረ : ደም ግባቷ ያማረ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር መረጣቸውና ከተባረከ ሰውነታቸው ድንግል ማርያምን ወለዱ::

እርሷ "ወላዲተ አምላክ" ተብላ እነርሱን "የእግዚአብሔር የሥጋ አያቶች" አሰኘቻቸው:: ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችንን ቤተ መቅደስ ካስገቡ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ በመልካም ሽምግልና አርፎ ከቅድስት ሐና ጋር በጌቴሴማኒ ተቀብሯል::

+ ቅዱሱ ሰው ያረፈበት ዓመት ግልጽ ባይሆንም ድንግል እመቤታችን ፰  ዓመት ሲሞላት ፪ ቱም ቅዱሳን ወላጆቿ በሕይወተ ሥጋ እንዳልነበሩ አበው ነግረውናል:: በማረፍ ደግሞ ቅድስት ሐና ትቀድማለች:: መቃብሩ ዛሬ ድረስ አለ:: ያደለው ከቦታው ደርሶ ይሳለመዋል::

አምላካችን ከቅዱስ ኢያቄም በረከት ያሳትፈን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ኢያቄም [ የድንግል ማርያም አባት ]
፪. ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት
፫. ቅድስት ቴዎድራ ሰማዕት
፬. ቅዱስ አባ መቅሩፋ ጻድቅ

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ሥሉስ ቅዱስ [ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ]
፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፫. አባ ሲኖዳ [ የባሕታውያን አለቃ ]
፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፭. አባ ባውላ ገዳማዊ
፮. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፯. ቅዱስ አግናጥዮስ [ ለአንበሳ የተሰጠ ]

" መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጥዋም ሰው ተወለደ:: እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት::
" [መዝ.፹፮፥፩-፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
13.04.202516:27
         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
ለዳታ ተጠቃሚዎች በድምፅ [ Audio ]
13.04.202514:00


💖

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
Паказана 1 - 24 з 89
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.