አሜሪካ ነበሩኝ ብላ እስከዛሬም ድረስ ከምታወራላቸው የኪነ-ጥበብ ሰወች መሀል ኮሜዲያኑ ጃክ ቤኒ እና የሙያና የትዳር አጋሩ የነበረችው ሜሪ ሊቪንግስቶን ይገኙበታል ።
እነዚህ ሁለት ጥንዶች በጋራ ይሰራሉ ፡ አብረው የሚገርም ፍቅር በሞላበት ትዳር ይኖራሉ ።
በተለይ ጃክ የአንድ ልጁ እናት የሆነችውን ሜሪን ወዷት አይጠግብም ።
......
እነዚህ ፡ ባልና ሚስት ሳይሆን ፡ አዲስ ፍቅረኞች የሚመስሉት ጥንዶች ትዳር የተበተነው ፡ ከአመታት የትዳር ጊዜያት በኋላ የምትወደው ፡ የሚወዳት ባሏ ጃክ ቤኒ በሞት ሲለያት ነው ።
....
ሜሪ ያ ፡ ስሞ የማይጠግባት ፡ አቅፏት የሚናፍቃት ባሏ ሲሞት በጣም አዘነች ።
እናም ባለቤቷ በሞት ከተለያት ከቀናት በኋላ ፡ አንድ ቀን ጠዋት ፡ በሯ ተንኳኳ ፡ ከፈተች ፡ ቀይ የሚያምር አበባ የያዘ ሰው ለእሷ የተላከ እንደሆነ ነግሮ ሰጥቷት ሄደ ።
ይሄን አበባ ተወደዋለች ፡ ነብሱን ይማረውና ፡ ባሏ ጃክ በየጊዜው ይሰጣት ነበር ። እና አበባው ባሏን አስታውርሳት ፡ ማን ልኮልኝ ይሆን ብላ የላኪው ስም ካለ ፈለገች ። ምንም የለም ።
.....
በነጋታው ጠዋት ፡ በሯ ደግሞ ተንኳኳ ።
ልክ የትናንቱ አይነት የላኪው አድራሻ የሌለበት አበባ ተልኮላታል ።
....
ይህ ሁኔታ ቀጠለ ፡ አበባ የሚያደርሰው ሰው ፡ ስለላኪው ጠይቃው የሱ ስራ ዴሊቨር ማድረግ እንጂ ምንም እንደማያውቅ ነግሯታል ።
...
እና ይህ ሁኔታ አንድም ቀን ሳይቋረጥ ቀጠለ ።
...
ሜሪ ይህጉዳይ ከንክኗት ፡ የአበባ መደብሩን በፍለጋ አግኝታ ጠየቀችው ።
....
ባልነግርሽ ደስ ይለኝ ነበር ፡ ሆኖም ይህን ያህል ካስጨነቀሽ ፡ ልንገርሽ አለና በየቀኑ የሚላክላትን አበባ ሚስጥር ነገራት ።
.......
አንድ ቀን ባለቤትሽ ወደ አበባ መሸጫ መደብራችን መጣ ፡ እና ፡ አስገራሚ ትእዛዝ አዘዘኝ ።
ይኸውልህ ፡ መቼም ይሁን መቼ ብቻ ከአመታት በኋላ በሞት ከተለየሁ ፡ ለባለቤቴ ሜሪ በህይወት እስካለች ድረስ ፡ በየቀኑ አበባ ላክላት ብሎ ፡ ለብዙ አመታት የሚበቃ የአበባ ዋጋ ከነማድረሻው ከፍሎኝ ነበር ።
እናም ህልፈቱን ከሰማሁ በኋላ አበባ የምልክልሽ በዚህ ምክንያት ነው አላት ።
.....
ይህ ከሆነ በኋላ ሜሪ ሊቪንግስቶን ከዚህ አለም በሞት እስክትለይ እስከ 1983 ድረስ ፡ በባሏ ትእዛዝ መሰረት በየቀኑ አበባ ይደርሳት ነበር ።