Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ዳን ŦËŁŁ avatar
ዳን ŦËŁŁ
ዳን ŦËŁŁ avatar
ዳን ŦËŁŁ
04.05.202509:51
ከበቀል አንስቶ እስከ የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ እና ሌሎቹም ታሪኮቹ አንድ ነገር ልብ እንድንል ያደርጉናል። ይኸውም የማንኛውም ሰው ሞት አላስፈላጊ መሆኑን ነው። በተለይ እንደ ጠመንጃ ላለ ዋጋ ቢስ ነገር ሲባል። .......

እነዚህ ታሪኮች በሚሥሉት ዐለም ውስጥ ሕይወት ደግማ ደጋግማ በጠመንጃ ርኩስ መንፈስ ስትጎበኝ እና ስትሸበር ትታያለች። ትረካዎቹ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የነበረውን ራሱን የሚደጋግም በመደቦች መሀል ያለ የክህደት ዑደት ታሪክ ይነግሩናል። በተጨማሪም ግን ታሪኮቹ በሰው ልጅ ሕይወት ክቡርነት እና ታላቅነት ያምኑ ስለ ነበሩ ቁርጠኛ ስለ ሆኑ እና ዘመን ተሻጋሪ ኀብረት ስለነበራቸው ሰዎችም ያጫውቱናል።


መግቢያ: ገፅ Vi
📚 የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ
✍️ ደራሲ: ሐማ ቱማ
👉👈 ተርጓሚ: ሕይወት ታደሰ


መፅሃፉ በ pdf እንዲዘጋጅ ሼር እያረጋችሁ ቻናላችን ለሁሉም አዳርሱ 🙏
#ሼር #JOIN
002 [ወሳኝ ትውልድ]

ከኛ ጥቂት አመታት በኋላ የተወለዱ ልጆች (በተለይ ከሚሊኒየም ጀምሮ) ለውሳኔ ችኩልና ቶሎ ወሰንሰን ሲያደርጉ ስመለከት በብዙ እንደቀደሙን አስቤ እገረማለሁ፤ እደነግጣለሁም።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አደንቃቸዋለሁ። ምክንያቱም እነሱ ዛሬ በምንም ሁኔታ የወሰኗት ውሳኔያቸው ወይ ለነገ መሰረት ይሆናቸዋል ፤ አልያ መሰረታቸውን ያናጋዋል።

እኛ ድሮ የሚያስፈራንና የሚያስደነግጠን ለነሱ ውሃ በብርጭቆ አንስቶ የመጠጣት ያህል ቀሎ ሳየው " ምንድነው ያለፈኝ " ብዬ ጠይቃለሁ።

ለምሳሌ፦ ድሮ በኛ ጊዜ (2000ዎቹም አርጅታ ድሮ ተባለች...😒) ከቤት ብንወጣ ብለን እናስባለን። እንወጣለን! አንድ ቀን እንደማንም እንውላለን፤ በፆም በፀሎት! ሲመሽ ግን ያቺ ፍርሃት ትመጣና "የት ልታድር ነው? ነገ ምን ልትበላ? በቃ በዚህ ጭለማ አውሬ አነከተህ !" ስትለን ልባችን ልትወጣ ምንም አይቀራት። ከዛ እየሮጠ የወጣ እግራችን መሰስ ብሎ የቤታችንን አጥር እየታከከ አንገታችንን ደፍተን እንገባለን። ወላጅም "የትም አይሄድም እያልኳቹ " እየተባባሉ ለቀጣዩ መሰደጃ እንደሌለን በማስረጃ አስረግጠው ይነግሩናል።
24.04.202503:27
ሰቀቀን ፤ጉጉትን ያጋተው ፍቅርህን
በልቤ እንዳኖርኩት ስገፋ ቀን ቀኑን
ጨለማ ከቦኛል
ብቸኝነት ብቻነቴን አስጥሎኛል
ባካል በጥላዬ ድንጉጥ አድርጎኛል
...
አንተን የሚመስል እኔኑ የሚያክል
የነፍሴ ነፅባራቅ ጥላ እያበጀ
በእቶን ናፍቆትህ አካሌን ከፈጀ
መክሰም ነው ፍፅመቴ ፣
አትሄድ አትለየኝ አትጥፋ ከፊቴ
ቅረብ ጠጋ በለኝ ላብብ ከክስመቴ
ቅሰመኝ ከምከስም ፣የትም ከምበንን
ብዬ አንጀት አልበላም!...
ብቻ ውሰድ የድርሻህን ናፍቆት ሰቀቀንክን
ያኔ ሙሉ አካሌ ጥላህን ያክለል
ስጋት ሰቀቀኔም ፣ናፍቆቴን ይተፋል
ፍቅር በኔና አንተ አካሉን ይጠርባል
ውሰድ የድርሻህን
ፍቅር ናፍቆትህን!
.....
✍️ዳጊ አሰፍ
Reposted from:
Marda graphics avatar
Marda graphics
🎯 rectangle collage design

join us
👉https://t.me/Mardagraphics1221

📮
0931546165
#like
#comment
#share

#marda_graphics_design
#marda_graphics_design
#marda_graphics_design
join us

@mardagraphics1221
Reposted from:
Marda graphics avatar
Marda graphics
🎯 wedding album poster design
#Congratulation
Melese & samrawit

join us
👉https://t.me/Mardagraphics1221

📮
0931546165
#like
#comment
#share
#follow my channel

#marda_graphics_design
#marda_graphics_design
#marda_graphics_design
join us

@mardagraphics1221
23.04.202517:01
🇪🇹

እጮኻለሁ !¡
የማትመጣ እናት እየተጣራሁ።
ደሞ አለቅሳለሁ °°°
የሞተች እናት ትነሳ እላለሁ።

#Now #New
Reposted from:
Marda graphics avatar
Marda graphics
🎯 birth day circle divide design

join us
👉https://t.me/Mardagraphics1221

📮
0931546165
#like
#comment
#share

#marda_graphics_design
#marda_graphics_design
#marda_graphics_design
join us

@mardagraphics1221
21.04.202518:58
እንደሚታወቀው
የሰው ልጅ ሳይጨንቀው
ውድ ህይወት አጥፍቶ
ቤት ንብረት አጋይቶ
በገዛ አምሳሉ ላይ ያን ያህል ይከፋል ፤
ደሞ ተራው ሲደርስ ለሞት ይሰለፋል ፤
ካነደደው ቤት ስር ፥ የተነሳው ጭስ ግን
ባ'የር ይታጠፋል
እንዳማረ ያልፋል ።
በስተመጨረሻም ውበት ያሸንፋል ።
-
በእርግጥ ይላል ቃሉ
"እምነት ፣ ተስፋ ፍቅር ፀንተው ይኖራሉ ።"
እኔ ግን እላለሁ
ያመነም ይከዳል
አፍቃሪም ይጎዳል
ተስፋም ይቆረጣል
የዚህ ሁሉ ግጭት ውብ ቅኔ ይወልዳል
ውብ ግጥም ያፅፋል
በስተመጨረሻም ውበት ያሸንፋል ።
-
ጠጋ ብለው ካዩት
መኖር ካለመኖር በምን ይለያያል ?
መከራና ጠኔስ መቼ ያሰቃያል ?
በውበት ያመነ
ጣዕረ ሞት ላይ ሆኖም ቆንጆ አበባ ያያል ።
-
ድንበር የለሽ ምኞት
ውል አልባ ፍላጎት
ሐሳብና ናፍቆት
እንደ እውር አሞራ በጭምት ቢያከንፈን
በምናብ አሳፍሮ ድንበር ቢያሳልፈን
ወደድንም ጠላንም ውበት ነው 'ሚተርፈን ።
_____
Habtamu Hadera
እንኳን ተወለዱ 🎉
03.05.202513:33
📚ርእስ: ራስን መለወጥ (benefits of change)
📝ደራሲ: Dr Myles Munroe
👤ትርጉም : ብሩክ ደስታ
📜ይዘት:- ምክረ አእምሮ
📖የገፅ ብዛት:- 208
📆ዓ. ም:-..
📌አዘጋጅ :- Mekonnen Dessie🐾🥠
01.05.202513:32
📚ርዕስ:- ሕልምሽን አጫውችኝ (tell me your dreams )
📝ደራሲ:- ሲድኒ ሽልደን
👤ትርጉም :- ግርማ ኃይለስላሴ
📜ይዘት:- ልቦለድ
📖የገፅ ብዛት:- 382
አዘጋጅ :- @Bemnet_Library
21.04.202503:26
‎ባክን....!

‎መሄድ እፈልግና
‎ከጥልቅ ሃሳቤ
‎ ከእስር ጭንቀቴ
‎ትንሽ ፈቀቅ ልል
‎ትንሽ ጠጋ እስክል
‎አንድ ብዬ እርምጃ
‎ሳልጨርስ ጀምሬ
‎መሄድ ይጠፈዋል
‎ የባከነው እግሬ!!

✍️‎ኤፍታህ
02.05.202503:41
አሁን ላይ ግን ተለምዶ እስኪመስል ድረስ ፋሽን የሆነው የህፃናት ከቤት ወጥተው የራሳቸውን ህይወት ለመኖር የመቁረጥ አባዜ ነው፤ በተለይ ደግሞ ልጆች ሃይስኩል ሲደርሱ ለሁሉ ነገር የበቁ እየመሰላቸው ከቤት እየወጡ ነው።

*አይፈሩም *አያመነቱም *ረጋ ብለውም አያስቡም።

ለምን ይሄ ኖርማል እየሆነ መጣ ብዬ እየጠየኩ ነው ...

-> የወደፊትታቸው በጣም ስለሚያስጨንቃቸው በጭንቀት ነው የሚወስኑት ?
-> በተለያዩ የ "Social Media " ፕላትፎርሞች የሚያዩት አኗኗር ፤ ህይወት ቀላል እንድትመስላቸው ጫና አደረገባቸው ? ( Social Media Push)
-> Peer pressures ?
-> የቤተሰብ ተፅዕኖ ?

ወይስ....?

16-08-17ቀን 7:07ሌሊት ላይ ነው ስለዚህ ሳሰላስል፣ ሳብሰለስል የቆየሁት ።

Dani Yoda

Please support us 🙏
30.04.202513:32
📚ርዕስ:- የፍቅር ትንግርት
📝ደራሲ:- በርታ ክሌይ
👤ትርጉም:- ኃይለ ሥላሴ መሃሪ
📜ዘውግ:- ልቦለድ
📆ዓ.ም:- 1997
📑የገፅ ብዛት :- 186
💰ልጥፋ ዋጋ:-
...
ኄኒዬ ...
የዛሬን አያድርገውና ...
ኧረ አናረጅም ገና!
(ግጥም ነው)

የዛሬን አያድርገውና
ነቁጥም ነበረች፤ እንዲሁም ሀ-ሞት የሆነች ገናና
(ይኼ ደግሞ ሌላ ግጥም ነው)

የዛሬን አያድርገውና
እውይ ኄኒዬ የኔንም የግጥም መጽሐፍ በድምቀት መርቀህልኝልና
ያ ሁሉ ያለፈው፣ መቼ ይረሳኛልና! ና ና ና

የዛሬን አያድርገውና
የራስ ምስል የሚለውን ግጥምህ መቼ ይረሳኛልና
--
የዛሬን አያድርገውና - ወደ ገደለው

ያው መቼም ተሰደኻል ቢባልም፣ መሰደድ ማለት እንዳንተ ከሆነስ ያው ለክፉም አይሰጥም እላላሁ
- በተለይ በተለይ በሀገራዊ የሥነጥበብ ዘርፉ እያደረክ ያለው ተሳትፎ እና ዘመቻ በቃ ምን ልበልህ - ልክ በቃ መዲናዋ መሀል ሆነህ ሁሉንም ነገር እየተቆጣጠርክ ያለህ ነው የሚመስለው። (በእርግጥ አንተ ከተሰደድክ በኋላ የመዲናችን መሀል የት እንደሆነ ተወዛግበናል)

- አዲስ የግጥም መጽሐፍ መውጣቱን እኛ አስኮ ያለነው ሳንሰማ - አንተ ካናዳ ተቀምጠህ ከኛ ቀድመህ ሰምተህ፤ ሰምተህም አስገዝተህ በአክለፍላፊ ወደ ካናዳ አስለከህ፣ አንብበህ፣ ተንትነህ ሄሰኸዋል።

ኄኒዬ - ኑርልን!
እንኳን ተወለድክ


ሮማን ተወልደ (ሮሚና ) እንደፃፈችው !
20.04.202503:07
ክርስቶስ ተንስዐ ሙታን
በአብይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዜሰ
ኮነ
ፍሰሃ ወሰላም 🙏

"እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላው ገደለ።"መዝ ፸፯(፸፰)፡፮፭

    መልካም የትንሳኤ በዓል
Shown 1 - 24 of 80
Log in to unlock more functionality.