ዓርብ
ዓርብ ማለት መካተቻ መፈጸሚያ ማብቂያ ማለት ነው
፩, , እግዚአብሔር ፳፪ቱን ሥነፍጥረት ፈጥሮ የጨረሰበት ዕለት ነው
እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።
እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአል ዘፍ ፪÷ ፪
፪, አዳም አርባ ቀን የምድር ኑሮውን ጨርሶ ወደ ገነት የገባበት ዕለት ነው
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው ዘፍ ፪ ÷ ፲፭
፫, አዳም የገነት ኑሮውን ፈጽሞ የተባረረበት ዕለት ነው
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ።
አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ ዘፍ ፫ ÷ ፳፫~፳፬
፬, እስራኤል ፵ ዘመን መና ከደመና እየወረደላቸው ሲመገቡ ኑረው ርደተ መናው ተፈጽሞ የከነአንን ፍሬ መመገብ የጀመሩበት ዕለት ነው
ወዓርበ መና በፊንቆን እን
እንጀራም በፊንቆን ቀረ የከነዓንንፍሬም መመገብ ጀመሩ
፭, የክርስቶስ የሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ጉዞ የነፍሳት አምሥት ሺኽ አምሥት መቶዘመን ጉዞ ተፈጸመ
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ “ተፈጸመ፡” አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ ዮሐ ፲፱÷፴
ሲኦል ተነዋወጠች መሠረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ ምድርን ያለጊዜዋ እንዳታልፍ አጸናት ደሙን በምድር ላይ አፈሰሰ ከኅልፈት ጠበቃት በእርሷ ያለውንም ሁሉ ጠበቀ
ስለ ፍጥረት ሁሉ ሥጋውን በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ ተወው ነፍሱ ግን ወደ ሲኦል ወርዳ ከዚያው ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን አዳነች ሲኦልንም በዘበዘች ፍጥረትንም ሁሉ ገንዘብ አደረገች ሥጋውም በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ ነፍሱም በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን ፈታች
ሃይ አበ ዘአትና ፳፮ ÷ ፲፰~፳፩
፮, በዕለተ ከእሑድ እስከ ዓርብ ተፈጥሮ በዕለተ ዓርብ ፍጻሜ ያገኘ ሥነፍጥረት በኅልፈት ፍጻሜ የሚያገኝ በዚህ እለት ነው ።
ወሶበ ተፈጸመ ኵሉ አሜሃ ለእሊአሁ ለኅሩያኒሁ ወለጻድቃኒሁ ደብተራ ብርሃን ይተክል ወመንጦላዕተ ብስሃን ይሰፍሕ ዘቦ ፯ቱ ምሥዋር
ትርጕም፦ ሉሉ ከተፈጸመበኋላ ያን ጊዜ ለመረጣቸው ለወዳጆቹ ለጻድቃኖቹ የብርሃን ድኖኳን ይተከላል ሰባት መሠወሪያ ያለው የብርሃን መጋረጃ ይዘረጋል
ቅዳ አት ፩÷ ፺፫