ዕለተ ሠሉስ (ማግሥተ ሰኞ)
➠ እለተ ጉባኤ ፦
አይሁድ ሠላሳ ሦስት አመት ከሦስት ወር በኢየሱስ ክርስቶስ በሚያደርገው ስራ ሁሉ ሲበሳጩና ሲቀኑ ኖረው በተለይ የሆሳዕና ቤተመቅደስ ከገባና ወግዱ ካላቸው በኋላ ምን እናድርግ ብለው መሰብሰብ ጀምረዋል
➠ ዕለተ ምስጢትር ፦
ከዚህ በፊት በዓደባባይ ሲያስተምር ይውላል ማታ ማታ ደቀመዛሙርቱ ያልገባቸውን ቀርበው ተርጉምልን ይሉታል ይተረጉምላቸዋል ማግስተሰኞ ግን ሁሉም (ክፉዎቹም ደጎችም ) ቀርበው ሲጠይቁ ውለዋል ለክፉዎች እንደክፋታቸው ለደጎች እንደደግነታቸው ሲመልስላቸው ምሥጢር ሲገልጥላቸው ውሏል ።
➠ ዕለተ ተስዕሎት ፦
፩, አይሁድ፦ በመባህተ መኑ ትገብር ዘንተ፦ ይህንን በመን ስልጣን ታደርጋለህ ? (ሙት ማንሳቱን ድውይ መፈወሱን ከቤተመቅደስ ጠራርጎ ማስወጣቱን )
ክርስቶስ፦ የዮሐንስ የማጥመቅ ስልጣኑ ከሰመይ ነው ከምድር ብሎ ጠየቃቸው ከምድር እንዳይሉ ሕዝቡን ፈሩ ከሰማይ እንዳይሉ ለምን አላመናችሁበትም ሊላቸው እንደሆነ አውቀው ዝም ብለዋል ማቴ ፳፩÷፳፫~፳፯
፪, ሰዱቃውያን ፦ ሙሴ በጻፈው በኦሪት አንዲት ሴት ባሏ ቢሞት የባሏ ወንድም እርሷን አግብቶ ልጅ ይውለድ የልጁ መጠሪያም በሟቹ ይሁን ይላል ለአንድ ሰው ሰባት ወንዶች ቢኖሩት ሰባቱም እያገቧት ቢሞቱ በትንሳኤ ሙታን ጊዜ ለማን ትሆናለች ?
ክርስቶስ ፦ ሰው ሙቶ ከተነሳ በኋላ አያገባም አይጋባም እንደ እግዚአብሔር መላዕክት ሆኖ ይኖራል ማቴ ፳፪ ÷፳፫
፫, ክርስቶስ ፦ ለአንድ ሰው ሁለት ልጆች አሉት አንዱን ልጁን ዓጸደወይን ጠብቅ ብሎ አዘዘው እሺ ብሎ ሳይሄድ ቀረ ሁለተኛ ልጁን ዓፀደ ወይኑን ጠብቅ አለው መጀመሪያ እንቢ አለ ኋላ ሂዶ ሲጠብቅ ዋለ ያባቱን ፈቃድ የፈጸመ ማን ነው ?
አይሁድ ፦ ሁለተኛው ልጅ ነው
ክርስቶስ፦ እናንተንም ዘማውያን ነፍሰ ገዳዮች አህዛብ ቀድመዋችሁ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ ማቴ ፳፩÷፳፰
፬, አይሁድ ፦ አንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ያለው በአንዱ ገጽታ የቄሳር ስም የተጻፈበት በአንዱ ገጽታ የእግዚአብሔር ስም የተጻፈበት ይዘው መጥተው ይህ ሳንቲም የማን ነው ብለው ጠየቁት ? የቄሳሩን ጽሑፍ ብቻ አይቶ የቄሳር ነው ቢል የእግዚአብሔርን ገንዘብ ለቄሳር ነው ይላል ብለው ከሕዝቡ ጋራ ሊያጣሉት የእግዚአብሔርን ጽሑፍ ብቻ አይቶ የእግዚአብሔር ነው ቢል ለቄሳር አትገብሩ ይላል ብለው ከቄሳር ጋራ ሊያጣሉት ነበር ፧
ክርስቶስ ፦ ተንኮላቸውን ያውቅባቸዋልና የቄሳረን ለቄሳር የእግዘብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ ብሎ ምላሽ አሳጥቷቸዋል ምክንያቱም እንዳይሰነጥቁት አንድ ሳንቲም ነውና ፣
፭, ሐዋርያት ፦ ሐዋርያትም ይህች ዕፀ በለስ በምትለመልምበት ጊዜ እንዴት ፈጥና ደረቀች ?
ክርስቶስ ፦ እምነት ካላችሁ ተራራውን ከዚህ ተነቅለህ ከዚያ ተተከል ብትሉት ይሆንላችኋል ማቴ ፳፩ ÷ ፳
፮, ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ አብረው ተሰበሰቡ።
ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው፦
መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት?” ብሎ ጠየቀው።
ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።
ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።
ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ፡ የምትለው ናት።
በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል። ማቴ ፳፪ ÷ ፴፬ ~፵
🌗 ዘመልአክ ዳግም 🌒
ረቡዕ ..................ይቀጥ..........