Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
እንማር avatar
እንማር
እንማር avatar
እንማር
አባቴን አልወደውም ምክንያቱም የሞተር ሳይክል መካኒክ በመሆኑ ፤ እንደ ጓደኞቼ አባትና እናት ጠበቃ ወይም ዶክተር አይደለም ።

ጆሮ በሚረብሽ የሞተር ድምፅ ፣በጥቁር ሞተር ዘይት በቆሸሸ ፣ባረጀ ሞተር ሳይክል እየነዳ እኔን ከኋላ በትከሻው ተሸክሞኝ ትምህርት ቤት ሲያመጣኝ እና ሲወስደኝ ሃፍረት ይሰማኛል።

በጓደኞቼ ፊት "አባቴ" ብዬ መጥራት እንኳን አልፈልግም ወላጆቹ ባወጡለት ስም 'ፍራንክ' ብዬ ነው የምጠራው።

በምርቃት ሥነሥርዓቴ ቀን ጂንስ እና ቲሸርት ለብሶ ሰፍ ብሎ እንኳን ደስ አለሽ ብሎ ሊያቅፈኝ ሲጠጋኝ ፊቱን ሳላየው ኮስተር ብዬ እጄን ብቻ ለሰላምታ ሰጥቼው ከአጠገቡ ቶሎ ሄድኩኝ።

በሃዜኔታ አይን ሲመለከተኝ አየሁት ፤ከዚያን ቀን በኋላ አባቴን አይቼው አላውቅም።

ከሶስት ሳምንት በኋላ ስልክ ተደውሎ አባቴ በሞተር ሳይክል አደጋ እንድሞተ ተነገረኝ፣ የአባቴን መሞት ስሰማ ምንም የኅዘን ስሜት አልተሰማኝም ነበር።

ያለ እናት ብቻውን ያሳደገኝ አባቴ በመሞቱ ምንም ሀዘን አልተሰማኝም ።

የአባቴ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ትንሽ ሰው ነበር የጠበኩት፤ ነገር ግን ከተለያዩ ከተማ የመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቀብር በሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

በእሱ እንዴሜ ያሉ ብዙ ሰዎች 'ወንድሜ ' እያሉ በመረረ ኅዘን ሲያለቅሱ አየሁኝ።

እኔ ለአንድ ቀን እንኳን አባቴ ለማለት ያሳፈረኝ ወጣቶች "ደጉ አባቴ" በማለት የማያባራ እንባቸውን ሲያነቡ ተመለከትኩኝ ።

አንድ ሰው "ወድቄ ያነሳኝ ፣ህይወቴን ያዳነ" የእኔ አባት እንደረዳው ሲያወራ ሰማሁ።

የህይወት ታሪኩን ሲነበብ ስለ አባቴ ይህንን ሰማሁ:-

"ወንድም ፍራንክ ወላጅ አልባ እና ድሃ ህፃናት ሆስፒታል እንዲሄዱ መኪና ያስተባብራል፣ገንዘብ ይሰጣል፣ ያሰባስባል ፣ጦሪ ለሌላቸው ለሕመምተኛ አዛውንቶች መድሃኒት ይገዛል....።"

ስለ አባቴ ጥሩነት፣ ደግነት ስሰማ "አባቴን አላውቀውም" ብዬ አሰብኩኝ።

የቀብር ስነስርዓቱ ከተፈፀመ በኋላ የአባቴ ጠበቃ አንድ ፖስታ አውጥቶ ሰጠኝ፤ ፖስታውን ስከፍተው እንዲህ የሚል ደብዳቤ አነበብኩ :-

"ውድ አንድ ልጄ! እንደ እምታፍሪብኝ አውቃለሁ፣ በግሪስ እና በጥላሸት የቆሸሹ የእጅ ጥፍሬን እትወጂም፣ የሞተር ዘይትና ጭስ ጠረኔን ትጠያለሽ ፤እኔ ግን ባንቺ መኩራቴን ለሰከንድ እንኳ ማሰቤን አቁሜ አላውቅም ።

አንድ ቀን እኔ የጠገንኩትን ሞተር ሳይክል ብቻ ሳይሆን የተጠገንኳቸውን ብዙ የተሰበሩ ልቦችንም ታያለሽ፤ እኔ ከማይቀረው አለም ሄጃለው ፤አታልቅሺ፣ ከልብሽ የራስሽን ህይወት ኑሪ ፣ ለሰዎች ደግ ሁኚ፣ ልብሽ ጀግና ይሁን፣ እጆችሽን ቆሻሻ እንዳይነካሽ በማለት አብዝተሽ አትኩሪ።"

በጣም የሚወድሽ አባትሽ

ልጅቷ በፀፀት እና በኅዘን ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።
27.04.202519:10
📣💥 ዛሬ የምጋብዛችሁ ቻናል ከ10 በላይ ምሁራን ያሉበት ድንቅ ቻናል ነው።

በየቀኑ በማይጠገቡ ምክሮቻቸው እየመከሩ ለቀጣዩ የህይወት ገፆችህ መሰረት ለመሆን ዝግጁ ሆነው እየጠበቁህ ይገኛሉ። ከእናንተ የሚጠበቀው "እለወጣለው" ብሎ ማመን ብቻ ነው።

ይቀለቀሉ
Join Now👇
@mikre_aimro
@mikre_aimro
@mikre_aimro
ተማሪ ልጅ ላላቹ እና ተማሪ ለሆናቹ ብቻ

✔ ልጆት የ High school ተማሪ አልያም remedial ነው?
መልሶት አዎ ከሆነ ይሄ መልዕክት ለእርሶ ነው።

    Alpha book series ይሰኛል በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በአማርኛ እና በእንግሊዝ ቋንቋ ከ solved ከሆኑ problem ኦች ጋር አዘጋጅተን እንጠብቃቹሀለን ከእናንተ የሚጠበቀው መጥታቹ የጥናትን ጭንቀት መላቀቅ ብቻ ነው።

የተዘጋጀው መፅሐፍ 🪅 በነፃ 🪅 የምትመለከቱበት ቻናል ሊንክ፡
🔶 GRADE-9
📚 https://t.me/+dGb1gOZfip8wZTE0

🔶 GRADE-10
📚 https://t.me/+er76JbJ0tZc2MDQ0

🔶 GRADE-11
📚 https://t.me/+GR89dZuI5-5iYjA0

🔶 GRADE-12
📚 https://t.me/+or0KJDsT75FiOWVk


✔ Remedial https://t.me/+x_eY8u9jno84ZDk0
ቀይ መስመር ይኑረን!

አንድ ከዛፍ ስር የሚኖር አደገኛ እባብ ነበረ። አቅራቢያው የሚጠጉትን ሁሉ እየነደፈ ይገድላል። ሁሉም የአከባቢው ሰው አደገኝነቱን ካወቀ በኋላ እባቡ ከለበት ዛፍ አከባቢ ድርሽ አይልም።

ከለታት አንድ ቀን ለመንደርዋ እንግዳ የሆነ ጠቢብ በጠራራ ፀሀይ መንደሯን እያቋረጠ ድካም ተሰማውና ይህ አደገኛ እባብ ወዳለባት ዛፍ ስር ሊጠለል ወደዛፏ መራመድ ጀመረ። ድንገት ሰዋች ደርሰው "ሰውየው ቁም እባብ አለ… አደገኛ እባብ…"ሲሉ ተጯጩኾ ሊያስቆሙት ሞኮሩ....
ጠቢቡ ሰው ፈገግ አለና "እኔ ከጥላው እንጂ ከእባቡ ምን አለኝ" በማለት ጩኸታቸውን ከቁብ ሳይቆጥር ወደ ዛፏ ተጠጋ…ሰዋች ጤንነቱን እየተጠራጠሩ ወደ ኋላ ሸሹ።

እባቡ ኮሽታ ሰማና እራሱን ለጥቃት አዘጋጀ።
ጠቢቡ ሰው በዝግታ እየተራመደ አባቡ አጠገብ እንደደረሰ በፍቅርና ፈገግታ የእባቡን አይኖች ተመለከተ። እባቡ ለአፍታ በፈገግታና ፍቅር የተሞሉ የጠቢቡ አይኖችን አስተዋለና "አንተ ሰው ከአይኖችህ በፍርሀት ፈንታ ፍቅርና ደስታ ይነበባል ወደኔ ትቀርብ ዘንድ እንዴት ደፈርክ? አለው።
"እኔ ለመኖር ምጓጓ ሞትን የምፈራ ሰው እይደለሁም። በምድር የሚያስፈራኝ ነገር የለም። ይልቅ አንተ ትፈራለህ ሰዋች ሲጠጉህ ገና ለገና ሊገድሉኝ ነው ብለ ትነድፋቸዋለህ። የቀረበህ ሁሉ አይገድልህም ስለዚህ አንተ ያገኘሁን ሁሉ አትንደፍ" አለ ጠቢቡ፡፡
እባቡ የጠቢቡና ምክር በመስማት ያገኘውን ሁሉ መንደፍ አቆመ። ከዚያ ሰዋች ቀስ በቀስ ይቀርቡት ጀመረ፡ ቀስ በቀስ ይዳብሱት ያጫውቱት ጀመረ። እባቡ ከሰዋች ጋር በጣም በተለማመደ ቁጥር መናደፍ የተው ሳይሆን መናደፍ የማይችል መሰላቸው። መፍራት መከበሩ ቀረ፡ ህፃን ትልቁ ይጥሉት፡ያነሱት፡ይወረውሩት ያንገላቱት ጀመር።

➡️ ሌላ ቀን ጠቢቡ ሰው ወደዚያች መንደር መጣና እባቡን ሊጠይቀው ወደሚኖርበት ቦታ ሄደ።
ጠቢቡ ሰው እባቡ ጎስቁሎና ቆሳስሎ ሳለ አየ። "ምን ሁነ ነው ወዳጄ ምን ገጥምሆ ነው እንዲህ የጎሰቀልከው?" ሲል ጠየቀው።

✅️"ጠቢብ ነህ ብየ ምክርህን ሰምቼ መናደፍ ብተው ይኸው እንደምታየው የትልቅ ትንሹ መጫወቻ ሆንኩ" አለ በተሰበረ ድምፅ።
"አይ ምክሬን በትክክል አልሰማሀም ማለት ነው፡ ያገኘህውን ሁሉ አትናደፍ እንጂ እራስህን አትከላከል አልኩህ"

ትግስተኛነት ታላቅነት ቢሆንም ገደብ ሊኖረው ይገባል!

📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
25.04.202512:38
አለም ላይ እንደሚጠላኝ ነፃነት የሚሰጠኝ የለም። ድል የሚናፍቀኝ ድል ለመቀናጀት እምታገለው ለሚጠሉኝ ሰዎች ለማስደመም አይደለም።

እሚጠላ ሰው ይቀናል እንጂ አይደመምም..!

አለም ላይ እንደሚጠላኝ ሰው እንደልቤ የሚያደርገኝ ነፃነት የሚያጎናፅፈኝ ማንም የለም..

የጠራኝ ሰርግ ላይ በቁጣ እና በሲልፐር ልሄድ እችላለሁ ... ቀልዶ እንዳይከፋው ብዬ በውሸት አልስቅም ...ተባበረኝ ሲለኝ ካልቻልኩ ውሸት አልፈበርክም ....

ሎተሪ ደርሶት "ይደረሰዋ አይነት ፊት" ሳልሳቀቅ ማሳየት የሚያስችል ጉልበት እንዳንፀባርቅ መብት ይሰጠኛል.....

ድክመቴ የሚወዱኝ ሰዎች ናቸው ።

አሞኝ እንዳለመመኝ የማስመስለው..
አጥቼ አለኝ አይነት ወሬ የማወራው..
የተቀየሙኝ ከመሰሉኝ ደንግጬ የማብራራው..

ለሚወዱኝ ሰዎች ብቻ ነው !!

እምባዬን በፈገግታ የምሸፍነው ...
ተስፋ አጥቼ ተስፋን የማስሰው ..
ሳዝን ሃዘኔ እንዳይጋባባቸው የምደበቀው ..
ከምችለው በላይ የምጥረው ..
እንዳይቀየሙኝ የምዋሸው ..

ለምወደው ሰው ብቻ ነው ...

ችርስ የምንወዳቹ ሰዎች ❤🍻
©Adhanom Mitiku
24.04.202518:39
✨✨ፍቅር ቅብ-7✨✨





እህቴ እግር ማውጣቷን ጠብቃ እናቴም እግር አወጣች....


ብዙ ጥያቄ አሸክማን ደብዛዋን አጠፋች....ለወቀሳ እንኳን የሚሆን የተሸነቆረች ደይቃ አልተወችልንም..... የመጨረሻዋ ምሽቷ ላይ  እንኳን የመሄድ አዝማሚያ አላሳየችንም....


እናቴ ከመሄዷ በፊት ጥድፊያ ያለበት ሙያ ስታስተምረኝ እንዴት አልጠረጠርኩም .....ጠብቃ ነበር.....አባቴ የሚወዳቸውን ምግቦች አጣፍጬ መስራት እስክጀምር ታግሳለች....ጠብቃ ነበር....እህቴ እግር እስክታወጣ በትዕግስት ጠብቃለች....'እህት ሁለተኛ እናት ናት' ብላ እጇን አስይዛ መቼም እንደማልተዋት በስሟ ስታስምለኝ መጠርጠር ነበረብኝ አይደል....አልጠረጠርኩም።


እህቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የደብረብርሃን አረቄ እንደቀመሰ ሰው እየተንገዳገደች በእግሯ ስትሄድ አይታት ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ እንዴት አልጠረጥርም....


ጡጦ አስጠጣጠብ እና አዘገጃጀት ከጥናት ሰአቴ ቀንሳ ስታስጠናኝ እንዴት አላስተዋልኩም....


በአስር አመቴ ስለ ወር አበባ ቁጭ አርጋ ስታስረዳኝ እና እኔ ባልኖር እንደዚህ አድርጊ ብላ ሞዴስ አጠቃቀም ስታስተምረኝ እንዴት ዝግጅቷ አይተገለፀልኝም....


**



የአመት በአል እለት ማልዳ ቤተክርስትያን ስማ ትመጣ ነበር.... ከእንቅልፋችን ስንነሳ ከቤተክርስትያን ተመልሳ ሽንሽኗን ለብሳ ጉድ ጉድ ስትል ማየት ለምደናል....


ቀጤማው....ቡናው....እጣኑ.....የማናለቦሽ ዲቦ ዘፈን....እና እናቴ ናቸው ለኔ የበአል ጠዋት ትውስታዎች።


በሆነኛው ቀን በአል ግን ቀጤማውም ቡናውም እጣኑም የማናለቦሽ ዲቦ ዘፈንም እናቴም አበሩብን....ዝም ጭጭ እንዳልን እሷን ጥበቃ ያዝን።


አባቴ ትሄድባቸዋለች ካላቸው ደብሮች ያልበረበረው አልነበረም....ቤተልሄሙ ሲቀረው ጊቢውን....ቤተመቅደሱን....የክርስትና ቤቱ ውስጥ ሳይቀር አገላብጦ ፈትሿል.....የዘበኛ ቤት እና መቃብር ስፍራም አልቀረውም....


የአባቴ አይኖች ለመጀመሪያ ጊዜ እንባ ሲያረግዙ ያየሁት ያኔ ነው....."አስካል መጣች....?"...ብሎ የጠየቀው እኔና አፍ ያልፈታችውን እህቴን ነበር....ደብሩን አዳርሶ ሲመለስ ቤት እንደሚያገኛት ጭላንጭል ተስፋ ነበረችው....እንዳልተመለሰች ሲያውቅ እንዴት አንገቱን ደፍቶ እንደተንሰቀሰቀ ሳስታውስ አሁን ድረስ እንባዬን መቆጣጠር ያቅተኛል....እናቴ አንጀቴን ከምታላውሰው በላይ ሆዴ ተገለባበጠለት.....


እሷ ከሄደችበት ቀን ጀምሮ የአባቴን ድምፅ ያለ ገደብ እንሰማው ጀመር....

ዝምታው የሸኛት መለጎሙ ያስኮበለላት እንደመሰለው ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም....በሚያሳብቅ ሁኔታ ማውራት እኛን ማጫወት ጀመረ....አንድም አለመኖሯ እንዳያጎለን እየተጋጋጠ ....ደግሞም ያስኮበለላት ዝምታው እኛ ልጆቹንም እንዳያሳጣው የሰጋ መሰለኝ.....

እናቴ ጥላን ሄዳለች....ምክንያቷ ምንም ይሁን ምን ውጤቱ መሄዷ ነው....እንደ እኔ እንደ እኔ እኛን መተው ባይቀላት እግሯን አታነሳም ነበር....ብዙ የማላውቃቸው ነገሮች መሄጀ ቀኗን እንደወሰኑላት ግልፅ ነው....ምን አልባት ብዙ መከፋት....ውጤቱ ግን ጥሎ መሄድ ነው....ምን አልባት ብዙ እንባ...ውጤቱ ግን አሁንም መሄድ ነው....ምክንያት ከቅጣት ቢያድን አዳምና ሄዋን ከገነት አይባረሩም ነበር አይደል....እንደዛ....የእናቴ ምክንያት ምንም ይሁን ምን ከልቤ ላለመባረር አላዳናትም....


እናቴ ጥላኝ ሄዳለች....


ከማህፀኗ ያወጣችኝ ጥላኝ ከሄደች ማህፀን የማይመርጥ አክሱሙን ተሸክሞ የሚዞር ዮናስ መሄዱ ምን ይገርማል.....


*


አንድ ሁለት እያለ ወራትን ቆጠርኩ.....የእናቴ የውሀ ሽታ መሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቀመኝ.....ሰው ሲርቀኝ ሳይሆን ሲቀርበኝ የምደነግጥ አይነት ሰው አረገኝ....ነካክቶ 'ሂድ ሂድ ብረር ብረር' የሚለው በበዛበት ዘመን የእናቴ መሄድ በማንም መሄድ እንዳልደነግጥ አረገኝ....በዚህ በኩል ደግሞ የአዲስ አበባ ስፋት ጠቀመኝ....ከዮናስ ጋር በአጋጣሚ እንኳን ተገናኝተን አናውቅም... ግዛቱ የመሰሉኝ ሰፈሮችም ቀስ በቀስ ዮናስ ዮናስ መሽተታቸውን ቀነሱ...


ከእርሱ ጋር የማሳልፋትን ቅዳሜ ለአባቴ ቡና በማፍላት ማሳለፍ ጀመርኩ...የእርሱ "አፈቅርሻለሁ" ትርክት በአባቴ እውነተኛ ምርቃት  ተተካ...



**



ከሀኒ ጋር በትርፍ ጊዜያችን ብቻ ሳይሆን እንዲሁ ገርበብ ባለ ጊዜያችን መገናኘት የበፊት ልምዳችን ነው...ምሳ ሰአት አብሮ መብላት...አልያም ከስራ ስንወጣ አብረን መሄዱ አስር አስር ፍቅረኛ እንኳን ብንይዝ የማይቀየር ህጋችን ነው....ዮናስ የውሀ ሽታ ከሆነ በኃላ ደግሞ ብሶብናል...



እንዳልኳችሁ ነው...ባገኘናት ሽንቁር መገናኘት ለምደናል...አንዱ ሽንቁር ደግሞ ምሳ ሰአት ነው....የዛሬው ሽንቁራችን ላይ ድንኳን ሰባሪ እንደነበር ያወቅኩት ከደረስኩ በኃላ ነው...ሀኒ ከሆነ ሰው ጋር ናት...


"መክብብ እባላለሁ..."....ብሎ እጁን ለትውውቅ ከዘረጋበት ቀን ጀምሮ የሆነ ነገሩ ውስጤ ቀርቷል...እንደተነገረኝ ከሆነ መክብብ እሳት የላሰ ጠበቃ ነው...እድሜው ከሰላሳ መግቢያ አካባቢ የሚሆን...ቁመቱ ብቅል አውራጅ የሚባል አይነት ባይሆንም ዘለግ ያለ...ግርማ ሞገስ ያለው...ፊቱ የሀብታም ወዝ ያለው...እጁ ከጥጥ የሚለሰልስ....አናቱ ላይ የደፋው ጥቁር ኮፍያ ፊቱ ላይ ካጀበው ፂሙ ጋር ተደምሮ የሆነ ዘፈን ላይ የማውቀው የትግርኛ ዘፋኝ የሚመስል....ለሰላምታ ገርበብ ያደረገው ከንፈሩ ውስጥ ተአምር የሚመስሉ ባዘቶ ጥርሶቹን ያየ  እንደ እኔ ቆሞ አይሄድም..... እፍፍፍፍ ሚያስብለኝ አይነት ውበት ያለው ....




አላለቀም....



✍ሸዊት




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
ዛሬ ደግሞ የምጠቁማችሁ ቻናል የሚገራርሙ ዓለም አቀፍ እውነታዎችን ሳይኮሎጂዎችን የሚለቅ የሚያስገርሙ ለማመን የሚከብዱ የዓለማችንን ጉዶች  የምታገኙበት ትምህርት ምትቀስሙበት ምርጥ ቻናል ነው!

ቻናሉን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ  ንኩት

👇👇👇

@yegudalem
@yegudalem
@yegudalem
@yegudalem

ቤተሰብ ይሄን ሼር በማድረግ ተባበሩኝ !
27.04.202517:48
✨✨ፍቅር ቅብ-9✨✨




እንደ ትናንት ትዝ ይለኛል ስምንተኛ ክፍል ነበረ....ከእስፖርት  ክፍለ ጊዜ መልስ ምሳቃዬ መማሪያ ጠረጴዛዬ ላይ በግላጭ ተቀምጧል....እየተንደረደርኩ ሄጄ ሳነሳው ገለባ ሆነብኝ.....ፈራ ተባ እያልኩ ስከፍተው በግዢ እንጀራ እና በአባቴ ምስር ያሸበረቀችው ምሳቃዬ ሌጣዋን ነች....ድንጋጤዬን ሳስታውሰው ምግብ የተበላብኝ ሳይሆን የአባቴን መርዶ የተረዳሁ ነበር የምመስለው።


ደንግጬ ብቻ ብተወውም መልካም ነበር...ጡጦውን እንደተቀማ ህፃን እሪሪሪሪ ብዬ አለቀስኩ.....ያኔ ነው ሀኒ ወደ ህይወቴ የገባችው.....


የበላብኝን ልጅ ፈልጋ ለማግኘት የፈጀባት ረፍት ሰአት ብቻ ነበረ.....ፊት ለፊቴ አምጥታ እንደ እባብ ስትቀጠቅጠው ፊቴ ላይ የነበረውን ደስታ አስታውሳለሁ...


ያን እለት ምሳቃዋን አጋርታኝ ጓደኝነታችንን ሀ ብለን ጀመርን.....'ጓደኛሞች እንሁን' ሳንባባል ጓደኛሞች ሆንን....እንዴት ብለን እንደተግባባን....ምን ሰአት ነብሶቻችን እንደተሳሰሩ ሁለታችንም አናውቅም።


*



ዛሬ ፊት ለፊቴ ተቀምጣ አፍ አፌን የምትለኝ ሴት ግርድፍድፍ ቃሌን አቃንታ የምታስተጋባልኝ....ገበና ከታቼ....ጓዳዬ....ጓ'ደኛዬ እንደሆነች ማሰብ ከበደኝ.....


"case አለ እንዴ" አለ ሸዋፈራሁ ደስአለኝ....ጉዳይ ቢኖራትስ ገና ፀጉር ይኑረው አይኑረው ላላወኩት ወንድ አናት አናቴን ማለት አለባት....ደግሞ እኔ የማላውቀው ጉዳይ ከመቼ ጀምሮ።



****



በአንድ ትሪ የቀረበልንን ቋንጣ ፍርፍር እና ዶሮ ቀና ሳልል መብላት ጀመርኩ....እኔ እና ሀኒ ስንበላ አንተያይም.....ምግብ እና ጓደኝነት ይለያያል ባይ ነን.....አንጎራረስም.....ይቺን ያዙልኝ አንጎራረስም።


"መኬ ግን ይሄ ወስፋታምነትህ መቼ ነው ሚለቅህ".....ካለች በኃላ እብድ የሚያህል ጉርሻ ወደ አፉ ሰደደች.....ሁለቱ ጉንጮቹ እንደፊኛ ተነፍተው ጥርሱ አልታዘዝ ያለው ይመስል ለሰከንዶች ከቆየ በኃላ ነው ተንፈስ ያለው....ጉርሻ ሳይሆን የግድያ ሙከራም ይመስል ነበር።


"ሀኒ በቃ ካላጎረስሽ አይሆንልሽማ...."....አለ ጉርሻውን በውሀ አለቃልቆ ከዋጠ በኃላ....ይሄን ጊዜ እኔ ጋር ያለችው ሀኒ እና እሱ ጋር ያለችው ሀኒ  የተለያዩ ሰዎች እንደሆኑ ተገለጠልኝ....

"ርቀትሽን ጠብቂ እድል...."....አልኩኝ በሆዴ።


'አይኗ ካንተ ላይ አይነቀልም....እንስፍስፍ ብላ ነው የምታይህ....አውቃለሁ ሰው ሲያፈቅር ምን እንደሚሆን....በተለይ ሴት ስታፈቅር....'....የሀኒ አሰተያየት እና አኳሀን አሌክስ አብርሀም መፅሀፍ ላይ ያነበብኳትን ፅሁፍ አስታወሰኝ....አይኗ ፍቅር አለበት....ድርጊቷ የተጠና ባይሆንም እንከን አልባ ለማድረግ እንደለፋችበት ያስታውቃል።


በየመሀሉ መታጠቢያ ቤት እየሄደች የምታረጥበው ከንፈሯ እና መላ ምትለው ፀጉሯ  ላይ ሳይቀር ፍቅር አለ....እኔ ሳውቃት እጇን አነባብራ ጥፍሯን የምታፍተለትለው አስተማሪ መልስ ሲጠይቃት ብቻ ነበር....ጭንቀት ከእግር እስከራሷ የሚወራት....ትንፋሽ የሚያጥራት ፕረዘንቴሽን ላይ ነበረ.... የተቆራረጠ ድምፅ ከተገለጠ ቅናት ጋር ያየሁት ዛሬ ነው....አሁን።


አስር አስር ፍቅረኞች ብንይዝ አይቀየርም ያልኳችሁን የአብሮነት ጊዜያችንን የጣሰው አንዱ መክብብ ነው....ከማውቃቸው የተፈቀደለት እርሱ ብቻ ነው....


"በህይወቴ የምጠላው ነገር ቢኖር በወንድ ምክንያት ከሴት ጓደኛ ጋር መናቆር ነው....ለምን ጥርግ አይልም ጓደኝነት ይበልጣል...."....ያለችኝ በቅርቡ ነበር....


"እድሌ ስለ ዮኒ አጫውችን እስኪ እንዴት ሆናችሁ...ብታይ መኬ እንዴት ደስ የሚሉ ጥንዶች መሰሉህ"....ስትል በንዴት አፍንጫዬ ራሱ ቀላ....በዮናስ ጉዳይ አይኔን ያስከፈተችኝ ሀኒ ናት ይቺ....?....እንዳልኳችሁ ይቺን ሀኒ አላውቃትም።


በጀርመንኛ 'ፍቅረኛ አላት አይንህን አንሳ' ማለቷ ነው....ሀኒ በወንድ ፊት pick me ጨዋታ ስትጫወት ሳያት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው....ለድርጊቷ እንዴት ያለ ምላሽ እንደምሰጥም አላውቅም.....አኳሀኗ ያልሆነ እልህ ውስጥ እንዳይከተኝ እየፈራሁ በደፈናው "ደህና ነን" ብቻ አልኳት....


"ይሄ ቅዳሜን ጠብቆ ካላወጣሁሽ የሚለው ልጅ አለ.....?.....".....ስትለኝ ንዴቴ ፀጉሯን እንዳያስነጨኝ እየተጠነቀቅኩ ደረቅ ፈገግታ አሳየኃት.....'ምን ነካሽ ሀኒ' መሆኑ ነው.....በእርግጥ የሆነ ነገሬ 'የእሷን ጉድ ለምን አታፍረጠርጪውም' ሲለኝ ነበረ.....የሆነ ነገሬ ደግሞ 'እንዲያ ካደረግሽማ እሷኑ ሆነሽ አረፍሽው' ሲለኝ ተውኩት እንጂ።


"ወንድ ልጅ የተያዘች ሴትን መጠጋት ላይ እንብዛም ነው....ልቧ ሙጫ እንደሆነ ያውቃል....ድንግልናሽን የሚፈልገው ትግል አምሮት ብቻ አይምሰልሽ....አብዛኛዋ ሴት ልቧን  ከተኛችው ወንድ ጋር ታጣብቃለች....እዚም እዚያም ጋር የተበታተነ  ልብ ርጋፊው ከውስጥ አይገባም....አለ አይደል ብዙ እጅ የነካካው አበባ መአዛው እስከዚም ነው.....".....ያለቺኝ እሷ ነበረች.....



ከጅምሩ እኔ በመምጣቴ የተቆጨች ትመስላለች.....እውነቱን ለመናገር መክብብን ልቧ እንደከጀለው ለማወቅ ደይቃዎች አልፈጁብኝም....ቀድማ ብታሳውቀኝ እንደ ሎጥ ዘመን ዘር ሊጠፋ ሆኖ አንድ ያንጠለጠለ እርሱ ብቻ ቢቀር በእንጨት አልነካውም ነበር.... የተጠቀመችው ግን ተቃራኒውን ነበር....እኔን በእሱ ፊት እፍኝ ማሳከል.... በፊቱ ልታሳንሰኝ ስትሞክር ፍላጎቴ ናረ.... ውበቱ  ባሳነሰችኝ ቁጥር ጎላ.....መላጣ ይሁን በራ ያልታወቀ አናቱ ሚዶ የተሰካበት ጎፈሬ መስሎ ታየኝ።


አላለቀም....




✍ሸዊት



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
Attention Grade 12 Students of Ethiopia!

The biggest exam of your life is just ONE MONTH away!

Are you ready to MASTER the Aptitude Test?
JOIN
📱 @Aptitude_SAT

✍️ Daily aptitude practice questions.

🤝 Step-by-step explanations!

⏰️ Time-saving tricks!

🌟 Mock exams to boost your confidence!

🏆 Real tips from real top scorers!

🏃‍♀️ Fast revision strategies!

🌟 Motivation and Support!

Don't leave your success 📈to chance — prepare smarter 🤏, not harder !

=> This is YOUR TIME⏰. YOUR FUTURE. YOUR VICTORY🏆.
Let’s crush the exam together!
Join us today and start your winning journey!👇👇👇👇👇

✈️@Aptitude_SAT
✈️@Aptitude_SAT
አንድ ጠበቃ የውሃ ጉድጓዱን ለመምህር ሸጠለት። ከሁለት ቀን በኋላ ጠበቃው ወደ መምህሩ መጥቶ እንዲህ አለው፡ "ጌታዬ፣ ጉድጓዱን ሸጥኩልህ እንጂ በውስጡ ያለውን ውሃ አልሸጥኩልህም! ውሃውን መጠቀም ከፈለግክ ተጨማሪ መክፈል አለብህ።"

መምህሩ ፈገግ አለና እንዲህ ሲል መለሰ፡ "አዎ፣ እኔም ወደ አንተ ልመጣ ነበር። ልልህ የነበረው ውሃህን ከእኔ ጉድጓድ ውስጥ እንድታወጣ ነው፣ አለበለዚያ ከነገ ጀምሮ ኪራይ መክፈል ትጀምራለህ።"

ይህን ሲሰማ ጠበቃው ተደናግጦ "ኦ! ዝም ብዬ እየቀለድኩ ነበር!" አለዉ።

መምህሩ እየሳቀ "እንደ አንተ ያሉ ሰዎች እኮ ከእኛ ዘንድ ተምረው ነው ጠበቃ የሚሆኑት!" አለው። ይባላል
።😜

ክብር ለመምህራን

📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
25.04.202510:21
29.04.202512:01
በAptitude (SAT) አሪፍ ዉጤት ማምጣት ይፈልጋሉ?
አዎ ከሆነ መልሶ: ቻናላችንን በመቀላቀል ይጀምሩ።
ቻናላችንን ስትቀላቀሉ የምታገኙት ጥቅም:-

🔑 የባለሙያ ምክሮች እና ዘዴዎች

🔑 ዕለታዊ የልምምድ ጥያቄዎች

🔑 ዝርዝር ማብራሪያዎች እና ፈጣን መንገዶች
🔑 በተጨማሪም Special short note ያገኛሉ

🔑 ኃይል የሚሰጡ የማጥናት  እቅድና ዘዴዎች።

በዚ መንገድ የSAT ውጤትዎን ማሻሻል ይችላሉ!
የህልምዎ ውጤት ከዚህ ይጀምራል!
Aptitude (SAT) አሁን ይቀላቀሉ!
📩 @Aptitude_SAT
🤝 ህግ ነክ ምኽሮችንም ከፈለጉ ይህን link ይጠቀሙ።
⚖️ " አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!"
📩 https://t.me/law_advice_tip
☑️ አንድ በእድሜ ገፋ ያለ ሽማግሌ ለሚስቱ ለሊት ላይ የማንኮራፏቷ ድምፅ አስቸግሮት ስሞታ ያቀርብላታል። ሚስቱም እኔ የለብኝም ብላው ትክድ ነበር። ይህ ነገር ሲደጋገምበት አንድ ለሊት ላይ ሆን ብሎ ይጠብቅና ለንግግሩ እውነታ ማስረጃ እንዲሆንለት ስታንኮራፋ ለመቅረፅ አሰበ። እንዳሰበውም ቀረፀና አስቀመጠው።

✅ ሌቱ ሲነጋ እሷ ተኝታ ነበር የቀረፀውን ሊያሳያት ይቀሰቅሳታል። እሷ ግን የመጨረሻ ለሊቷ ስለነበር መነሳት አልቻለችም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያቺ የማንኮራፋቷ ድምፅ ማታ ማታ ሁሌም ልክ እንደ አዝካሩን-ነውም እየደጋገመ ይሰማታል። ... 💔😪

ከቅርብ ወዳጅህ
የሚመጣብህን ችግር ቻለውና እለፈው
ምናልባት ይህ ችግር አለኝታ እንዲሆንልህና
ያንን ሰው ከጎንህ እንዳታጣው የምትመኝበት
ጊዜ ሊመጣ ይችላልና። 🙏


📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
25.04.202516:46
✨✨ፍቅር ቅብ-8✨✨




እጁን ከዘረጋበት ቅፅበት ጀምሩ...ስሜ እስኪጠፋኝ ድረስ ልቤ ደንግጦለታል...


"እድል ትባላለች..."...ብላ ሀኒ ስሜን ስታስታውሰኝ በልቤ አመስግኛታለሁ...


"እንደዚች አይነት ቆንጆ ጓደኛ እንዳለሽ ነግረሺኝ አታውቂም...."...ከማለቱ እንደመሽኮርመም ነገር አረገኝ...


"ኧረ መሽኮርመም ካካካ...."...አንዴ ከተጀመረ ማቆሚያ የሌለው ሳቋ ተከተለ...


"ካካካካ ቆ...ቆንጆ ትርጉሙ ተቀየረ መሰለኝ ካካካካ"....ይሄን ስትል ንዴቴ ጣሪያ ነካ.....እንደደበረኝ እንድታውቅልኝ ፊቴን በመዘፍዘፍ ምልክት ሰጠኃት.. በአይኔም ላወራት ሞከርኩ...እሷ ወይ ፍንክች....



"መኬ ግን ጨምረሀል...ቆንጆ ምናምን ካካካ"



"ቆንጆ ናት...እውነቴን ነው..."....ይሄን ያለው እኔን እኔን እያየ ስለነበር የድብርት ፊቴን ፈታሁለት....



"ኧረ መፋጠጥ...እሺ ልነሳላችሁ..."....ይሄን ስትልም ሳቋ አፍኗት ነበር....



"ወሬ አለብሽ..."...ካላት በኃላ አስተናጋጇን በምልክት ጠራት...



"ወሬ አይደለም ይሄ...በት በት ጀምረህልኛል እ...ብትበረታ ነው ጥሩ...ፀጉርህም ወደማለቁ ነው ካካካካ...."



"ቆይ ውበት ማድነቅ አይቻልም..."...አስተናጋጇን ከሸኘን በኃላ መለሰላት...



"ይቻላል...በደንብ ይቻላል...ግን በእኔ ፊት ስታደንቅ ለመጀመሪያ ጊዜህ ነው ብዬ ነው...."



"ለምን አልተደነቅኩም መሰለብሽ..."...ሲላት ሀይለኛ የቃላት ጦርነት እንደሚጀመር ገባኝና ደራሽ ጥይት እንዳያገኘኝ በውስጤ መፀለይ ጀመርኩ።



"ለምን ይከነክነኛል...አይን እንደሌለህ የገባኝ እኮ እድልን ቆንጆ ስትል ነው...ለዚህ ይታዘናል እንጂ አይቀናም..."...የፈራሁት አልቀረልኝም...ለእርሱ የተተኮሰ ጥይት ሽራፊው ደረሰኝ....



ከዚህ ንግግር በኃላ ምግባችን መጣ...ቀጣይ ጥይት ሳይተኮስ በፊት እጄን ልታጠብ በሚል ከመሀላቸው ተነሳሁ...እውነቱን ለመናገር እጄን መታጠብ ሳይሆን መስታወት ማየት ነበር ዋና አላማዬ...ፊቴን በአእምሮዬ መሳል ራሱ ከበደኝ...ሀኒ ምን ሆነች...?...ጠየቅኩ ራሴን።እኔን በማላውቀው ሰው ፊት ማጥላላት ከመቼ ጀምሮ...በእርግጥ እነርሱ በደንብ ይተዋወቃሉ...ከዩንቨርስቲ ጀምሮ...ግን ይሄ እኔን ለማጥላላት በቂ ምክንያት አይደለም...ስደነቅ በእኔ ፈንታ ኩራት የሚሰማት ጓደኛዬ የት ገባች...?ይቺን ሀኒ አላውቃትም...ከማላውቃቸው ሁለት ሰዎች ጋር ያለሁ ያህል ተሰማኝ....

ፊቴን ብቻ በደንብ አይቼ እጄን ውሀ ሳላስነካ ተቀላቀልኳቸው...የቃላት ጦርነቱ በርዶ የደራ ጨዋታ ላይ ደረስኩ...ከመቼው አልኩኝ በሆዴ...መቼስ ስለ እኔ ውበት እንዳይወራ ሆን ብላ ነው ወሬውን ያደራችው አልኩ ደግሜ።..


ወይ ጦጣ መሆን...ቼክም አላደርግ አሉኝ...የእርሷስ ይቅር እሱ ግን ውበቴን ትቶ ምን አባቱ ነው የሚያወራው...ከእኔ ውበት የሀኒ ወሬ በለጠበት...?



"እሺ ቢያንስ ምግቡን ደጅ አታስጠኑት..."...አልኩ አምልጦኝ...


"ማለት ቢያንስን ምን አመጣው...አንቺን ደጅ አስጠናንሽ እንዴ....?"...ሀኒ ናት...አሁን በደንብ ገባኝ...የጥይቷ ኢላማ በትክክል እኔ እንደነበርኩ...እየተፈጠረ ያለው ነገር ጭራሽ ሀገር የማይሰጥበት እንቆቅልሽ ሆነብኝ....


"አይ እንደዛ ማለቴ ብዬ ሳይሆን ከበረደ አያስበላም ብዬ ነው..."


"ልክ ነሽ...እጄን ታጥቤ ልምጣ..."...አለ ባኮፍያው...ይሄን አጋጣሚ ከሀኒ ጋር ለማውራት ልጠቀምባት እያሰብኩ "ጠብቀኝ መኬ እኔም እመጣለሁ"...ስትል ከጥያቄዬ እየሸሸች እንደሆነ ፍንትው አለልኝ።


ከምንም የማልቆጠርበት ቦታ ላይ የተቀመጠች አሻንጉሊት የሆንኩ መሰለኝ...ምን ብዬ ተነስቼ መሄድ እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ...


ብዙም አልቆዩም እያሽካኩ መጡ...


"ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ሳቅ...ንገሩኝና እኔም ልሳቅ..."...አልኩኝ ልቀላቀላቸው በማሰብ።


"ካካካካካካ...."....አሽካካች...ሳቂልኝ አላልኳትም አይደል...በገነኩ...ይሄን ጊዜ ባለኮፍያው አብሯት አልሳቀም...


"ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ...."...አሁንም ወሬው ላይ የለሁበትም...


"ምን ትዝ አለሽ...አያልቅብሽ..."...ምን አልባት ስለ ጊቢ ትውስታቸው ልታወራ ነው ብዬ ባልጠራም ለወሬ ቀላወጥኩ...


"ድሮ ታች ክላስ ስንስቅ አስተማሪዎቻችን ንገሩንና እኛም እንሳቅ የሚሏት ነገር...ካካካ"...ያማታል እንዴ...አሁን ይሄ ከእርሱ ጋር ነው ሊታወስ የሚገባው ወይስ ከእኔ ጋር...እንዳልኳችሁ ነው...ይቺን ሀኒ አላውቃትም...የማይናገረውን መብላት ጀመርኩ።




አላለቀም.....




✍ሸዊት




https://t.me/shewitdorka
Explore Huawei's technology platform! 🎉 Whether you need extra income, savings or flexibility opportunities
Huawei 5g is your perfect solution!
Huawei's new event short-term daily income
Don't miss the welfare products, registration link
https://www.hw5ginvestors.com/?invitation_code=37A93

Channel link: https://t.me/huawei5G_investors

If you want to get started, Without risk, there is no history, no Ferrari If you miss the opportunity, it's really gone

Let's start 🥰
ከጀርባ ሳቅፍሽ የሆነ የሚሰማኝ ስሜት አለ .... ውስጤን የሚወረው .... ልቤን የሚሰውረው .... ዋስትና የሚሰጠኝ .... ደህንነት እንዲሰማኝ የሚያደርገኝ .... በእኔ ላይ ያለሽን እምነት እና ለእኔ ያለሽን ድጋፍ የሚነግረኝ።

እጆቼን በጀርባሽ አሳልፌ ወደ ደረቴ አስጠግቼ ሳቅፍሽ ከአለም ሁካታ እና እረፍት አልባ ኡደት ያስወጣሁሽ፣ ከሁሉም ነገር የከለልሉሽ .... ከሚያውቁሽም ከማያውቁሽም የደበቅኩሽ ያህል ይሰማኛል። ነፍሴ ከነፍስሽ .... አለሜ ከአለምሽ ስትተሳሰር ይታወቀኛል።

ድምፅ ሳላወጣ "አለሁልሽ" እያልኩሽ እንደሆነ ይሰማኛል። አይኖችሽ ሳያዩኝ ልብሽ በደመነፍስ እንደሚያምነኝ ይነግረኛል። በእቅፌ ውስጥ ለመቅለጥ እራስሽን አሳልፈሽ እንደሰጠሽኝ ያሳየኛል። በጭንቀት ሲናውዝ የዋለው አይምሮሽ፣ በሀላፊነት መብዛት የዛለው ሰውነትሽ በአንዴ እርፍ ሲል ይታወቀኛል። አይኖችሽን ጨፍነሽ፣ ደረቴ ላይ ስትጋደሚ እና በረጅሙ ስትተነፍሺ .......ድብርትሽ ብን ብሎ ሲጠፋ አየዋለሁ።

✅️ ለማያምኑት ሰው አይደለም ጀርባ ፊት አይሰጥም፤ ለማያሳርፍ ሰው አይደለም ጀርባ እጅ አይሰጥም። በነገሮች ተጋጭተን፣ አኩርፈሽ አኩርፌሽ፣ ቃላቶች እሳት ሆነው ሲለበልቡን .... ብቻሽን ቆመሽ በአሳብ ስትጠፊ .... ይቅርታ የምጠይቅበት፣ ተሳስቼ አመልሽን አወጣሁት የምልበት፣ በዝምታ ሰላምን የምለምንበት መንገድ ነው። እጆችሽ በዝግታ እጄ ላይ ሲያርፉ በመካከላችን የነበረው የስሜት ርቀት ሲጠብ ይታወቀኛል። ቃል አልባ ይቅርታ .... የማይታይ የስሜት ቁስል ጥገና።

ከጀርባ መታቀፍ መታቀፍ ብቻ አይደለም። ራሱን የቻለ ቋንቋ ነው። የፍቅር ቋንቋ .... የምቾት ቋንቋ .... ቃልኪዳን .... የማይደበዝዝ ትዝታ ነው።

📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
28.04.202519:47
“ምን ያህል ዕድሜያችሁ ቢሄድ ምንም ትልቅ ብትሆኑ፤ በጣም ከሚመቻችሁ ሰው ጋር ስትሆኑ በልጅነት ባህሪ ውስጥ እራሳችሁን ታገኛላችሁ..።”

                  ―ማህሙድ ዳርዊሽ

✒️Imagination
ንጉሥ ሻርያር በፋርስ ላይ ይገዛ ነበር። የወንድሙ ሚስት በባሏ ላይ እየማገጠች እንደሆነ ሲረዳ ቁጣው ነደደ። ሁሌም ሴቶች አንድ ናቸውም ብሎ ደመደመ። የገዛ ሚስቱንም ሰይፎ ገደላት።

ከዚህ በኋላ ደናግላን ሴቶችን እያገባ አንድ ሌሊት ብቻ አብሯቸው አድሮ ፣ ማግጠው ሳያዋርዱት በፊት ያስገድላቸዋል። ደናግላቱን እየፈለገ የሚያመጣለት ሚኒስትሩ ነበር። ሚኒስትሩ በመጨረሻ ለንጉሡ የሚያቀርብለት ደናግላን አጣ።

ሚኒስትሩ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዷል። ትልቋ ሻህራዛድ  ታናሿ ዲናርዛድ ትባላለች። ዲናዛርድ ውብ ስትሆን ሻህራዛድ ደግሞ ጥበበኛ ናት። በዚያ ላይ ስል እና ደፋር ናት። አንዴ ያነበበችውን በፍጹም አትረሳም።

ጥሩ የማስታወስ ችሎታ አላት። ራሷን በራሷ ፊዚክስ፣ ፍልስፍና፣ ታሪክ ከማስተማሯም በላይ የበቃች ገጣሚ ነች።

ሚኒስትሩ በመጨረሻ ሻህራዛድን ለንጉሡ ዳረለት። አያችሁ ምርጫ አልነበረውም። ከአንድ ሌሊት በኋላ እንደምትገደል ያውቃል። ግን ከንጉሡ ትእዛዝ መውጣት አይችልም።

✔️ ሻህራዛድ እና ንጉሡ በሰርጋቸው እለት እንግዶቻቸውን ከሸኙ በኋላ ወደ መኝታ ቤታቸው አመሩ። በዚያም ሻህራዛድ እፁብ ድንቅ የሆነ ተረት ለንጉሡ መንገር ጀመረች።

✔️ ንጉሡ አፉን ከፍቶ በአድናቆት ይሰማል። ይህ ተረት እንዲያው ተረት ብቻ አይደለም። ምትሃት ነው። እንደ ጥሩ ወይን ልብ የሚያስደስት፣ በምናብ የሚያንሳፍፍ፣ በሃሴት የሚሞላ ነው።

✔️ ግን ግን ታሪኩን ሳትጨርስ መሸ፣ በጣም መሸ፤ ሌሊቱ ተጋመሰ። ሻህራዛድ ታሪኩን ሳትጨርስ ማቋረጥ ነበረባት። ንጉሡ ልቡ እንደተንጠለጠለ ለራሱ እንዲህ አለ

✔️... ዛሬ ልገድላት አልችልም። ታሪኩን ነገ ከጨረሰችልኝ በኋላ ነገ እገድላታለሁ  ....

ምስኪን ንጉሥ! ዛሬ መሽቶ ነገ ነጋ። ሻህራዛድ እንደተለመደው ትላንት የጀመረችለትን ተረት ጨርሳ ሌላ ጀመረች። ታሪኮቹ የዋዛ እንዳይመስላችሁ። ነፍስን ሰቅዘው የሚይዙ፣ በለዛ የተዋቡ፣ በቋንቋ የረቀቁ ናቸው።

አሊባባ እና አርባዎቹ ሌቦች . . .
አላዲን እና ፋኖሱ . . .
መርከበኛው ሲንባድ . . . ወዘተርፈ ነበሩ።

ቀናቱ እንደዚህ ነጎዱ። አንድ ቀን፣ ሁለት ቀን፣ ሳምንት፣ ወር፣ አመት ሆነ። ንጉሡ የሻህራዛድ ተረቶች ሱሰኛ ሆነ። ሻህራዛድ በጥበቧ በተረት ላይ ተረት እየጨመረች፣ መጨረሻው ላይ ሳትደርስ እያቋረጠች፣ እያሳደረች አንድ ሺህ አንድ ሌሊት ተቆጠሩ።

ንጉሡ በመጨረሻ ከሻህራዛድ ድብን ያለ ፍቅር ያዘው። እንኳን ሊያስገድላት፣ ከሷ መለየት አቃተው። የፍቅሯ ምርኮኛ ሆነ።

ታዲያ ይሄንን ሁሉ ተአምር የሰሩት ታሪኮች ናቸው። ታሪኮች የጨከነ ልብ ያራራሉ፤ የደደረ ልብ ይገራሉ። ሻህራዛድ በጥበቧ የታሪኮችን ጉልበት፣ የልቧን ብልጠት፣ የአእምሮዋን እውቀት ተጠቅማ ኃያሉን ንጉሥ አንበረከከችው።

አንድ ሺህ አንድ ሌሊቶች
☑️ ቆንጆ ናት... አፍላ .... 15 አመቷ ነው።
ጎረምሶች ሲያዩዋት አይናቸው ይጎለጎላል። ጎልማሶች አይተው ይመኛታል። ወንዶች ይከጅሏታል። ሴቶች በቅናት እንደ ሽንኩርት ይልጧታል።

☑️  አንድ ቀን እንዲህ ስል ጠየቅኳት።
<<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን መስፈርት እንዲያሟላ ትፈልጊያለሽ?
>>
☑️ በፍጥነት መለሰችልኝ
የተማረ መሆን አለበት፤ ማስተርስ ያለው ይመረጣል። ከተቻለ የግል ቢዝነስ የሚሰራ፤ ኢንቨስተር ቢሆን አሪፍ ነው፤ ካልሆነ ግን አሪፍ ደሞዝ ሊኖረው
ግድ.ነው። መኖሪያ ቤቱ G+2 ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ከG+1 በታች ግን
አልፈልግም።

✅ መኪና በጣም ነው የምወደው። አሪፍ መኪኖች ቢኖሩት አሪፍ ካልሆነም
ከተጋባን በኋላ እኔ እንዲገዛ አደርገዋለሁ። ሙድ የገባው ቢሆን ደስ
ይለኛል። ሁሌ ግን የሚቅም፤ የሚጨብስ እና የሚያጨስ መሆን
የለበትም። ጨዋታ የሚያውቅ ሁሌ የሚያስቀኝ!!!

✅ ቁመቱ በጣም እንዲረዝም አልፈልግም። እኔ አጠር ስለምል በጣም
እንዳይበልጠኝ። ደረቱ ሰፋ ያለ ሆኖ ቦርጭ የሚባል እንዲኖረው
አልፈልግም።

✅ጸጉሩ ፍሪዝ ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ድሬድ ቢሆን ደግሞ ነፍስ ነው። አይኑ
የሚያምር፤ መልኩ ጸይም መሆን አለበት በጣም ቀይ ወይም በጣም ጥቁር
ወንድ አልወድም። አለባበሱ ዘናጭ መሆን አለበት። የሚወደኝ፤
የሚንከባከበኝ፤ ሮማንቲክ የሆነ፤ በሳምንት ቢያንስ ሁለቴ የሻማ
እራት ያለበት ሆቴል የሚጋብዘኝ፤ ቢያንስ በወር ሁለቴ ጭፈራ ቤት
የሚወስደኝ፤.ከበዓላት እና ከልደቴ ቀን በተጨማሪ ስጦታ እያመጣ ስርፕራይዝ
የሚያደርገኝ፤ ፍቅር የሚያውቅ፤ በተለያየ ቁልምጫ ስም የሚጠራኝ እና
ታማኝ ከእኔ ውጪአንዲት ሴት የማያይ ...

☑️  >>ይበቃል አልኳት እንደማታቆም ስለገባኝ። እንዲህ አይነት ወንድ
ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቶ አስቴር አወቀ ዘፈን ውስጥ እንኳን አይገኝም አልኩ
በውስጤ። ለሷ ግንአልነገርኳትም።


✅ ከአስር አመት በኋላ ሳገኛት 25 አመቷ ነበር። አላገባችም። ዩኒቨርስቲ
ጨርሳ.ስራ ይዛለች። ጥቂት ቦይ ፍሬንዶች ይዛ ለቃለች። አሁንም ታምራለች
እንደድሮው ግን የሰው ሁሉ አይን ማረፊያ አይደለችም። መልሼ ያንኑ ጥያቄ
ጠየቅኳት።

✅ <<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን አይነት ነገሮች ማሟላት አለበት?>>
የማፈቅረው ሰው መሆን አለበት፤ ፍቅር ከሌለ ላገባው አልችልም።
ከማልወደው ሰው ጋር አንድ ቀን ላድር አልችልም። ታማኝ እንዲሆን
እፈልጋለሁ። እንዲያከብረኝ እፈልጋለሁ። ጥሩ ስራ ቢኖረው፤ ማንበብ
የሚወድና በሃሳብ የምንግባባ ቢሆን ደስ ይለኛል። ቆንጆና ሃብታም ከሆነ ጥሩ ነው፤ ካልሆነም ግን አብረን ሰርተን መለወጥ እንችላለን። ዋናው መግባባት ነው። በተረፈ ቤተሰቡን የሚወድ እና የማይዋሽ መሆን አለበት። ወንዱ ሁሉ
የማይታመን ሆነብን እኮ። ዋናው የሚታመን ከሆነ ሌላው ችግር
የለውም>>

✅  ጊዜው ይሮጣል!!! ከአስር አመት በኋላ ስንገናኝ አላገባችም። 35 አመት
እያለፋት ነበር። ደግሜ ያንኑ ጥያቄ ጠይቅኳት።

<<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን አይነት ነገሮች ማሟላት አለበት?>>
ትንሽ አሰብ አደረገኝና
<<የምግባባው ሰው ከሆነ ሌላው ችግር የለውም>> አለችኝ
መልኩ፤ ጸጉሩ፤ ሃብቱ፤ እውቀቱስ አልኳት።
<<ወንድ ልጅ ደግሞ መልክ ምን ያደርግለታል? ከቺምፕ (ቺምፓንዚ)
መለስ ካለ ሌላው ችግር የለውም>> አለች እየሳቀች።

☑️ ከአስር አመት በኋላ ሳገኛት አግብታ ሁለት ልጆች ወልዳ ነበር።ባሏ
አጭር፤ ጥቁር፤ መላጣ፤ የከባዳ መኪና ሾፌር አይነት ቦርጭ
ያለው፤ሱሪውን ቦርጩ መሃከል ላይ የሚታጠቅ፤ ሁልጊዜ መላጣውን
የሚያልበው ዝጋታም ነገር ነው

✅<<እንዴት ነው ትወጂዋለሽ>> አልኳት

✅<<ምን ማለትህ ነው ትዳር አይደል?>>

✅<<ማለቴ ድሮ የነገርሽኝ አይነት ሰው አይደለም ብዬ ነው?>>

✅<<ያኔማ አየር ላይ ነበርኩ፤ እድሜ መስታወት ነው፤ ብዙ ያስተምራል፤
አሁን
ተምረን ልብ ገዝተን ነው>> አለች ተከዝ ብላ።

✅ <<ሁሌ የማይቀያየር አንድ መስፈርት ነበረሽ፤ ታማኝ መሆን አለበት ትይኝ
ነበር።
ባልሽ ታማኝ ነው?>>
<<ታማኝ እግዜር ብቻ ነው፤ በቃ ግን ... ትዳር ስለሆነ ከማይታመን ሰው
ጋር መኖር ትለምዳለህ፤ አየህ አሁን የገባኝ ነገር ትዳር ማለት እንደ ፖለቲካ
ነው።

☑️ ፖለቲከኞች ውሸት እየነገሩን አብረን እንደምንኖር ትዳር ውስጥም ይሄ
ያጋጥማል>> አለች
<<በትዳርሽ ደስተኛ ነሽ?>> አልኳት እያዘንኩ

✅ <<ደስታ አንጻራዊ ነው፤ በልጆቼ ደስ ይለኛል፤ ትዳሬን አከብራለሁ። በተረፈ
ግን እየኖርኩ ነው>> አለች ፈገግ ብላ። በዛች ቅጽበታዊ ፈገግታ ውስጥ
የጊዜን ኃይለኝነት አየሁ።
ጊዜ ነው እንጂ ቁምነገራም
ባላባትነት አያኮራም እንዲሉ እመው


አንብበው ከወደዱት 👍👍

📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
ዛሬ ደግሞ የምጠቁማችሁ ቻናል የሚገራርሙ ዓለም አቀፍ እውነታዎችን ሳይኮሎጂዎችን የሚለቅ የሚያስገርሙ ለማመን የሚከብዱ የዓለማችንን ጉዶች  የምታገኙበት ትምህርት ምትቀስሙበት ምርጥ ቻናል ነው!

ቻናሉን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ  ንኩት

👇👇👇

@yegudalem
@yegudalem
@yegudalem
@yegudalem

ቤተሰብ ይሄን ሼር በማድረግ ተባበሩኝ !
ተማሪ ልጅ ላላቹ እና ተማሪ ለሆናቹ ብቻ

✔ ልጆት የ High school ተማሪ አልያም remedial ነው?
መልሶት አዎ ከሆነ ይሄ መልዕክት ለእርሶ ነው።

    Alpha book series ይሰኛል በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በአማርኛ እና በእንግሊዝ ቋንቋ ከ solved ከሆኑ problem ኦች ጋር አዘጋጅተን እንጠብቃቹሀለን ከእናንተ የሚጠበቀው መጥታቹ የጥናትን ጭንቀት መላቀቅ ብቻ ነው።

የተዘጋጀው መፅሐፍ 🪅 በነፃ 🪅 የምትመለከቱበት ቻናል ሊንክ፡
🔶 GRADE-9
📚 https://t.me/+dGb1gOZfip8wZTE0

🔶 GRADE-10
📚 https://t.me/+er76JbJ0tZc2MDQ0

🔶 GRADE-11
📚 https://t.me/+GR89dZuI5-5iYjA0

🔶 GRADE-12
📚 https://t.me/+or0KJDsT75FiOWVk


✔ Remedial https://t.me/+x_eY8u9jno84ZDk0
显示 1 - 24 1 230
登录以解锁更多功能。