05.05.202513:23
👇English Grammar Rule Quiz 👇
Every sentence must have a subject and___.

04.05.202520:00
✨✨ፍቅር ቅብ-15✨✨
"በሁለተኛ እድል ታምናለህ....."......አልኩት መክብብን ምሳ የምንበላበት ሬስቶራንት ተቀምጠን....
"እንደ ሁኔታው ይለያያል...."....አለኝና ለአፌ መጥኖ አጎረሰኝ.....ቀጥሎም "እየበላሽ አይደለም ምን ሆነሻል....."....አለኝ።
"ምንም አልሆንኩም....".....አልኩትና ያጎረሰኝን ውጬ እጄ ላይ ሳድበለብል የቆየሁትንም ደገምኩና እየበላሁ መሆኔን አስመሰከርኩ....
"ኧረ....ረ እንዲህ ከሆነማ ሁሌ ነው ምጋብዝሽ....አበላልሽ ኪስ አይጎዳም...."....አለና ያን ምትሀት ጥርሱን ገለጥ አደረገው።
"ስለ ሁለተኛ እድል እያወራሁህ ነበር.....".....አልኩት ለማስታወስ ያህል....
"ያው ሁለተኛ እድል እንደቦታው እና እንደሁኔታው ይለያያል....ለምሳሌ አንድ ነብስ ያጠፋ ወንጀለኛ...."....ከማለቱ አቋርጬው ከፍርድ ቤት ህግና መሰል ነገሮች የወጣ መልስ እንደምፈልግ ነገርኩት....
"specific አርጊልኛ.....እንዲሁ ሁለተኛ እድል የሚባል ነገር የለም እኮ እድሌ....."....አለኝ....እድሌ ስላለኝ ልቤ ሰላሳ ሁለት ጥርሱን አሳየ....ቢሆንም ግን ዮናስ የነገረኝን ነገር ሳስታውስ መክብብን ከሩቅ የማየው እንጂ የማልዳስሰው.....የማልነካው የእኔ የማልለው 'የማይበላ ወፍ' እንደሆነ ትዝ አለኝ።
"ስለ HIV አስበህ ታውቃለህ....."......አልኩት ድንገት....እንዳልኩት ያወቅኩት ካልኩት በኃላ ነበር።
"እኔንጃ ያው በሽታ ነው....ግን እንዴት አስበዋለሁ....አንዳንዴ በዙሪያሽ ያለ ሰው ሲታመም ነው በሽታውን የምታስተውይው አልያም 'በሽታ' የሚባል ነገር መኖሩን የምታስታውሽው እና እንደሚሞት ሰው የምትኖሪው....".....አለኝና አንድ ጉርሻ ደገመኝ።
"የሚሞት ሰው እንዴት ነው ሚኖረው...."....አልኩት አጣድፌ ጉርሻውን ከዋጥኩ በኃላ.....
"በርግጥ ሁላችንም ሟቾች ነን....ነገር ግን እንደሚሞት ሰው የሚኖረው በቁጥር ነው....ብዙ ሰው ግን እንደሚሞት የሚያስታውሰው ሲታመም ነው....እንደምትሞቺ ስታስቢ ለነገ የምታስቀምጪው ደስታ የለም....'ነገ' የምትይው ስራም ምግብም አይኖርም....እንደምትሞቺ ስታስቢ ነው መግቢያሽ የሚያሳስብሽ....የመጨረሻዎቹ ደይቃዎች ላይ ነው የነብስሽን ድምፅ የምትሰሚው....."
"ማን ታሞ ነው....?....."....አለኝ ቀጠል አድርጎ......"እኔ" አይባል ነገር ሆኖብኝ "አንድ ጓደኛዬ ታማ ነው..."....አልኩት....
"እንዴት ያዛት....".....ሲለኝ ደነገጥኩ....
"እንዴት ይይዛታል....እንደተለመደው ነዋ.... ትንሽ ስህተት ነበር ከፍቅር ጓደኛዋ ተጋብቶባት...."....አልኩትና ፊት ለፊቴ ያለውን ውሀ ባንድ ትንፋሽ ጨለጥኩት....
"ትንሽ ስህተት እንኳን አይደለም....ህይወት የሚያስከፍል 'ትንሽ' የለም....እንዴት ብዬ የጠየቅኩሽም እንዳልተለመደውም የሚታመሙ ሰዎች ስላሉ ነው....."
"ማለት....."...
"በደም ንክኪ..."....ሲለኝ የኢለመንተሪ ተማሪ የሆኖኩ መሰለኝ....ትንሽ ቆይቶ ስለ ሶስቱ የ'መ' ህጎች ሊያስተምረኝም ይችላል....እኔ ጭንቀቴ እንጂ እንዲህ የሚያስለፈልፈኝ ከመክብብ ጋር ሲጀመር ስለ በሽታ አይወራም....ከሱ ጋር መወራት ያለበት ስለ እሱ ብቻ ነበር....ስለ እሱ ውበት....ስለ ጥርሶቹ....ስለ አይኖቹ....ነፍስ ድረስ ስለሚሰማው ስለሚያረሰርሰው ድምፁ....ስለ መዳፎቹ....በቃ መወራት ያለበት ይሄ ነው.....
ድሮ ድሮ መልክ የበዛበት ወንድ አልወድም ነበር....ጭንቅላቴ ምን ሲል ይሄን መልክ የተትረፈረፈለት ወንድ እንደከጀለ አላውቅም.....
ከዮናስ የሰማሁትን ሰምቼ አልቅሼ አልወጣልኝም....አልወጣልኝም....እዚህ ከመክብብ ጋር ቁጭ ብሎ ምሳ ለመብላት ምን ያሀል እንደታገልኩኝ የማውቀው እኔ ነኝ....ስሜቱን ይሄ ነው ብዬ የምገልፀው አይነት አይደለም....
"ስለ HIV እናውራ...."....አልኩት ስለዩንቨርሲቲ ቆይታው ሲያጫውተኝ...ፊቱ ላይ ግርታ አነበብኩ።
"በጣም ተጨንቀሻል በጓደኛሽ ጉዳይ...."....ሲለኝ በአዎንታ አንገቴን ነቀነቅኩለት...
"ቆይ ሀኒም ታውቃታለች...."....ሲለኝ "ቀላል" ልለው ከአፌ ነው የመለስኩት.....
"አይ አታውቃትም....."..
"አንድ ዶክተር ጓደኛ አለኝ....ስልኩን እሰጥሽና መጠየቅ የምትፈልጊውን ጠይቂው...."
"..በርግጥ በጣም rare ኬዝ ነው....normally ግን በዚህ ፍጥነት ይሄን ያሀል weight loss አታደርግም...." የሚለኝ የደወልኩለት ዶክተር ነው.....'ከእኔ ጋር ከተለያየ በኃላ ነው የያዘው' ብዬ ለመቀበል የቻልኩትን እያደረግኩ ነው....ዶክተሩ የመለሰልኝ መልስ ተስፋዬን አሟጦ ጣለው.....
"ጓደኛሽ ቲቢ endemic area move አርጋ ነበር....?...."....አለኝ ቀጠል አድርጎ...
"አላውቅም ምነው...."...አልኩትና መልሱን በጉጉት መጠበቅ ጀመርኩ።
"ምን አልባት እንደዚያ አካባቢ ከሄደች እና እንደ ቲቢ ባሉ ተጓዳኝ በሽታ የመጠቃት እድል ከነበራት በተጨማሪም immunityዋ የሞተ ከሆነ significant weight loss በዚህ ፍጥነት ሊኖራት ይችላል።" ሲለኝ ትንሽ ልቤ ተስፋ ጫረ....የዮናስ አከሳስ የዘመናት ታማሚ እንጂ የቅርብ አላስመሰለውም ነበር።
ትንሽ እፎይ አልኩ.....
"ለማንኛውም ነገ እኔ ክሊኒክ ትምጣና ልያት...አንድ አንዴ misdiagnosed የመደረግ ሁኔታም ስለሚኖር ድጋሚ ትታይ".... አለኝና ተሰነባበትን.......
ጭንቀቴን መደበቅ እንዳቃተኝ የታወቀኝ ታናሽ እህቴን ክፉኛ ሳመናጭቃት ነበር....
አላለቀም....
✍ሸዊት
https://t.me/shewitdorka

04.05.202513:15
✅አዲስ የተጋቡ ጥንዶች የበፊት መኖሪያቸውን ይለቁና ሌላ ሰፈር ተከራይተው መኖር ይጀምራሉ ። አዲሱ ቤታቸው በገቡ ማግስት ጠዋት ላይ ቁጭ ብለው ቁርሳቸውን በመብላት ላይ ሳሉ ፡ ሚስትየው በመስኮቱ መስታወት በኩል ውጪውን ስትመለከት ፡ አንዲት የጎረቤት ሴት ልብስ አጥባ ስታሰጣ አየች ።
✔️ከዚያም ፊቷን ቅጭም አድርጋ ወደ ባሏ ዞረችና "ውዴ ! ልጅቷ ልብስ ማጠቡን አልቻለችበትም መሠለኝ ምንም ሳይፀዳ እስከ ቆሻሻው ነው ያሰጣችው!" አለችው ። ባሏ ግን ምንም አልመለሰላትም ፤ ፈገግ ብሎ ብቻ በዝምታ አለፈ ።
የጎረቤቷ ልጅ ሁሌ ዘውትር ጠዋት ጠዋት እየተነሳች የቤተሰቦቿን ቤት ታፀዳና ልብስ አጥባ ታሰጣለች ። አዲሶቹ ሙሽሮችም ለቁርስ በተቀመጡበት ቦታ ሆነው በመስኮታቸው መስታወት በኩል ይህን የዘውትር የጎረቤታቸውን ስራን ያያሉ ። ሚስትየውም ሁሌም "ያሰጣችው ልብስ ዛሬም አልፀዳም !" የሚለውን ትችቷን ለባሏ ትነግረዋለች ።
ባልየውም የምፀት ፈገግታ ፈገግ እያለ በዝምታ ያልፋታል ። አዲሱ ቤታቸው በገቡ በወራቸው ጠዋት ላይ እንደተለመደው ቁርሳቸውን ሲበሉ ፡ ሚስትየው በመደነቅና በመደሰት ወደ ባሏ ዞራ "ውዴ ተመልከትማ ! ጎረቤታችን ዛሬ ጎብዛለች ። ልብስ የማጠብ ልምድ አካበተች መሠለኝ ዛሬ ልብሶቹን ፅድት አድርጋ ነው አጥባ ያሰጣችው!" አለችው በደስታ እየተፍለቀለቀች ።
ዛሬ ግን ባልየው ዝም አላለም ። የምፀት ፈገግታውን እያሳያት "ዛሬኮ በለሊት ተነስቼ የቤታችንን መስኮት መስታወቶችን አፀዳሁት !" አላት !🙄 ለካ እስከዛሬ ሚስትየው በጎረቤቷ ላይ የምታቀርበው ትችት ልክ አልነበረም ።
በእውነትም ጎረቤቷ የምታሰጣው ልብስ ያልፀዳ ሆኖ ሳይሆን ፡ ሚስትየው አሻግራ የምታይበት የመስኮታቸው መስታወት ያልፀዳ በመሆኑ ነበር ልብሱን ቆሻሻ አስመስሎ ያሳያት ።
እናረጋግጥ
እና ምን ለማለት ነው፦ ሌሎች ሰዎችን ስናይ ፡ የምናየው ነገር ፡ በምናይበት መነፅር ንፁህነት ይወሰናል እንደማለት ነው !
ስለ ሌሎች ሰዎች የባህሪም ሆነ የተግባር መቆሸሽ ከማውራታችን በፊት ፡ ያንን ነገር ያየንበት የእይታ መነፅራችን ንፁህ መሆኑን !!! 🙏
➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988

04.05.202510:07
በዚህ ኑሮ ውድነት Protein powder ገዝቶ ለግል አሰልጣኝ ተከፍሎ የማይቻል ነው ለዚህም ነው Viable Ebooks ከተለያዩ አለምአቀፍ ዌብሳይቶች እና Virtual አሰልጣኞች ጋር በመተባበር ይሄንን "የጡንቻ ግንባታ በኢትዮጵያ ምግቦች" የሚል EBook ይዘንላችሁ የመጣነው።
✅መጽሀፉ የያዛቸውን ሀሳቦች ለማወቅ እና መጽሀፉን ለማግኘት
🔵 በ t.me/viable_Ebook
🌐 በ t.me/viable_Ebook ያናግሩን።
☑️ አስታውሱ መጽሀፉን ስታገኙ አብሮ የ አንድ ወር ከእናንተ ጋር የሚስማማ Workout plan ይኖረዋል በተጨማሪም ይህ መጽሀፍ ሌሎች ቦታዎች ላይ አይገኝም‼️
✅✅ ዋጋ:-100ብር ብቻ(ለ 3 ቀን የሚቆይ ቅናሽ)
ቻናላችን:- t.me/Viable_books

03.05.202518:59
✅ #አንዲት "በገበያ ሽያጭ ረዳትነት /Marketing Assistance/" ሙያ ለሥራ የተወዳደረች ሴት፤ ለቃለ መጠይቅ ከተቀጠረችበት ረፋድ 4 ሰዓት ዘግይታ ከቀኑ 6:30 ላይ ትደርሳለች።
ልክ እንደገባችም፣ ፈገግታ በተሞላ ፊት ቃለ-መጠይቅ ለማድረግ የተሰየሙትን ሁለት ሰዎች ሰላምታ ትሰጣለች። አንደኛው ፈገግ በማለት መልሶ ሰላም ሲላት፤ ሁለተኛው ሰው ግን ደስተኛ እንዳልሆነ በሚያሳይ ፊት "ቃለ መጠይቁ አብቅቷል!" ሲል በማመናጨቅ ይመልስላታል።
✅ ሴቲቱ ግን አሁንም ፈገግ አለች። መቼም ዘግይታ መድረሷን በፈገግታ ፊት ለመሸፈን መሞከሯ የሚገርም ነው...
ታዲያ ይህ ሁኔታዋ ግራ ያጋባው አንደኛው ፈታኝ፦ "ይሄ ሁሉ ፈገግታሽ ከምን የመጣ ነው?" ሲል ይጠይቃታል። እርሷም መልሳ፦ "አንዳንድ ጊዜ በህይወትህ የሚገጥሙህን ችግሮች ለመደበቅ የሚያስፈልግህ- ፈገግታ ብቻ ይሆናል፤...
✅ ...እዘገያለሁ ብዬ ፈጽሞ አላሰብኩም ነበር፤ ለዚህ ቃለ-መጠይቅ ብዬ ሳምንታትን ስዘጋጅ ነው የከረምኩት ነገር ግን አጋጣሚዎች ለሁሉም ነገር ምክንያት ነበሩ፤ አሁን በቀጥታ የመጣሁት ከልጄ ትምህርት ቤት ነው፣ ምክንያቱም 'ልጅሽ ታሟል ድረሽ' ተብሎ ስለተደወለልኝ፤ ከዛ መልስ ደግሞ እዚህ ለመድረስ ስል በመኪና እየበረርኩ ስመጣ መሀል መንገድ ላይ ጎማው ተነፈሰ፤ እሱን መንገድ ዳር ማስያዝ አንድ ስራ ነበር፤
በመጨረሻ እንግልቴን ያየ ሰው ነው አዝኖልኝ ወደዚህም በነጻ ያደረሰኝ። በቃ!
✅ በበቂ ሁኔታ ለዚህ ቃለ-መጠይቅ በመዘጋጀቴ ብቻ ማለፍ አልቻልኩም። የቤት ኪራይ ክፍያ እኔን ነው የሚጠብቀው ሌላ ተስፋ የለም፡ ብቸኛው ተስፋዬ የነበረው ይሄ ስራ ነበር። ነገር ግን አሁን "አብቅቷል!" ተብሎ ተነገረኝ!
እናማ አሁን ማድረግ የምችለው ነገር ለራሴ የማይታየውን ተስፋ ለመስጠት ስል ፈገግ ማለት ብቻ ነው"።
✅ ይሄንን ስትናገር እንባዋ ዱብ ዱብ አሉ። ልትሄድም ከተቀመጠችበት ተነሳች።
ይሁንና ቀደም ሲል አመናጭቋት የነበረው ሰው ፊቱ በሃዘን ተሞላ፣ ዐይኖቹም እንባን መቆጣጠር አቃታቸው። ሴቲቱንም እንድትቀመጥ ካድረገ በኋላ፣ ቃለ-መጠይቁን በጋራ አደረጉላት፤ ብቁ ሆናም በመገኘቷ ስራውን ተቀጠረች።
‼️ልብ በል፤
✅👌 ሲንቀሳቀስ የምታየው ሰው ሁሉ የሞላለት/የደላው አይምሰልህ- ዘወትር ኑሮን ለማሸነፍ ሲል የራሱን ትግል እየታገለ ነው።
📨@Enmare1988

02.05.202518:22
✨✨ፍቅር ቅብ -13✨✨
መኝታ ቤቴ እንደገባሁ ጥቁር ልብሴን አራገፍኩ....ሀዘን ማርዘም አልፈለግኩም.... ሽሮ መልክ ቢጃማዬን ለብሼ መክብብን ማሰብ ጀመርኩ.....ሰላም።
*
ከሞት የማይተናነስ እንቅልፍ ውስጥ ሆኜ ነበር ስልኬ የቀሰቀሰኝ....መክብብ ሊሆን ይችላል ብዬ ተንደርድሬ ስልኬን ማታ ከወረወርኩበት አነሳሁ....ዮናስ ነበር።
የዘጋሁትን ፋይል መክፈት ላይ ጎበዝ አይደለሁም....ቢሆንም ግን ስልኩን ማንሳት ጨዋነት ነው ብዬ ስላሰብኩ ብቻ አንስቼ የሚለኝን ለመስማት ጆሮዬን አመቻቸው....
"ሄ...ሄለው"....አለኝ የሱ በማይመስል ድምፅ....
"አቤት" አልኩት ቆፍጠን ብዬ....
"እድል....?"....አለኝ እርግጠኛ ለመሆን በሚመስል ድምፀት።
"አዎ ማን ልበል.....".....አልኩት ሳቄን አፍኜ....ሲያስነጥስ ብቻ ሰምቼ ድምፁን እለየዋለሁ.....ሲያስል ብሰማው በሆዱ ያሰበውን አውቃለሁ....
"አላወቅሽኝም....ዮ...ዮናስ ነኝ....".....አለኝ በተቆራረጠ ድምፅ።
"ብዙ ዮናስ አውቃለሁ.....".....አልኩት በቅድሙ ድምፅ።
"ጊቢያችሁ ጋር ነኝ.....ነይ ውጪ የማወራሽ ጥብቅ ጉዳይ አለኝ...."
"ይቅርታ አልችልም።"
"አንቺ ካልወጣሽ ይሄንኑ ጉዳይ ከአባትሽ ጋር እነጋገራለሁ.....".....አለኝ ደንደን ብሎ።
"ምንድን ነው የምትነጋገረው....ምን ቀረን...."....አልኩት ሳላስበው ድምፄን ከፍ አድርጌ.....የምሬን ነበር....ምን ቀረን....የዘር ፍሬውን እኔ ጋር ያስቀመጠው ካልመሰለው በስተቀር እኔን የሚፈልግበት ቁም ነገር የለውም....አልያም ማርሽ አልነሳ ብሎት እንቁ ቀያይሮ ሊሞክር ካልሆነ በቀር እኔ ዘንድ አይመጣም....እንዲያስ ቢሆን እኔ ጋር ከመምጣት መሪጌታ ጋር ቢሄድ አይቀልም ነበር...?
ከብዙ መጯጯህ በኃላ በረንዳ ላይ ዳዊት እየደገመ ያለ አባቴን ጉንጭ ስሜ ፌስታል አንጠልጥዬ ወጣሁ....
ዮናስ ሳር አክሎ ከጊቢያችን ፊት ለፊት ካለው ስልክ እንጨት ጋር ተጣብቋል....'እድል' ብሎ ባይጠራኝ እንሽላሊት መስሎኝ ላልፈው ነበረ።
ሳየው አመዴ ቡን አለ....አዲስ ለያዛት ፍቅረኛው አክሱሙን ሳይሆን ስጋውን እየቆረሰ የሚሰጣት እስኪመስል ድረስ ላልቷል....ፀጉሩ እና ፂሙ ያለልክ አድጎ ሽፍታ አስመስሎታል.....ልብሱ ላዩ ላይ ከመስፋቱ የተነሳ ለለቅሶ የተደኮነ ድንኳን ውስጥ ጋቢ ለብሶ የተቀመጠ የኔቢጤ አስመስሎታል.....የጫማውን አተላለቅ እና የእሱን አከሳስ ላየ ሳሙና ላይ የቆመ ሰንደል ነው ይላል እንጂ ስጋ ለባሽ ሰው ነው አይልም።
እንዳየኝ እንደፋርማሲ እባብ ተጠመጠመብኝ....."ኡኡቴ አልቀረብህም ትናንት እንዴት እንደታቀፍኩ ብታይ ...."....አልኩ በሆዴ....እውነቱን ለመናገር አየር እንጂ ሰው ያቀፈኝ አልመሰለኝም ነበር....
"እንዴት ነሽ" አለኝ ከእግር እስከራሴ እየገረመመ....
"ደህና ነኝ ክብሩ ይስፋ.....".....አልኩትና እንዴት ነህም ሳልለው የሚለኝን መጠባበቅ ያዝኩ።
"የሆነ ካፌ እንቀመጥ እና እንነጋገር.....".....እንዳለኝ አባቴ የጊቢያችንን በር ከፍቶ ወጣ....ፊት ለፊት ተፋጠጥን....ቄሱም ዝም መፅሀፉም ዝም ማለት ይሄኔ ነው።
"ሂድ ዮናስ ሂድ....ቦሀላ እደውልልሀለሁ አባዬ ነው.....".....አልኩትና እሱን በተቃራኒው አቅጣጫ መርቼ ወደ አባቴ ሄድኩ።
"በሰው የምጠላውን ምነው እድል.....አንቺ አጥር ላጥር በጠራራ ጠሀይ እየታከክሽ እህትሽ ምን ትማር ...".....አለኝ በትኩረት እያየኝ....
"አልታከኩም አባ....ኮሌጅ የማውቀው ልጅ ነው....ለሆነ ጉዳይ ፈልጎኝ....."....ከማለቴ አቋረጠኝ።
"ይሄ በልቶ የማያድር የመሰለ ሱሪው የሰፋው ወጠጤ ሀምን ይፈልግሻል....ኧረ በየተራ አቃጥላችሁ ልትደፉኝ ነው....እናታችሁስ....."....ከማለቱ በተራዬ አቋረጥኩት።
"በየሰበቡ ስሟን አትጥራ አባዬ....ለአንተ ሚስት የነበረችው ሴት ለእኛ እናታችን ነበረች....አካልህ የነበረችው ሴት ደሟ ደማችን ውስጥ አለ....ተው አባዬ....ተው".....ብዬው በከፈተው በር ቀድሜው ገባሁ።
ንገሩኝ እስቲ ተመሳሳይ ህመም ይወዳደራል እንዴ....ተመሳሳይ ቁስል እግር እና እጅ ላይ ቢወጣ እግር እኔ ብሳለሁ ይላል....እጅስ እግርን የእኔን ማን አየ እየለገምክ እንጂ እንደ እኔ አልታመምክም ይለዋል....በጭራሽ....ሁላችንም የየራሳችንን ስንታመም ነው መዳኛችንን የምናቀርበው እንጂ 'የኔ ህመም ይብስ' በማለታችን የሚጠጋን ጤና የለም...
ተፈናጥሬ ገብቼ መኝታ ቤቴን ዘጋሁት.... ማልቀስ አልፈለግኩም....ስልኬን አንስቼ ሰላም ወደማገኝበት ቦታ ልደውል እጄን ከመላኬ ሁለት የፅሁፍ መልዕክት ገባልኝ.....
አንዱ ከገነት....አንዱ ደግሞ ከገሀነም።
"እንዴት አደርሽ እድል...."....የሚል የመክብብ መልዕክት እና......
"ዞሮ መግቢያዬ ካፌ እየጠበቅኩሽ ነው....".....የሚል የዮናስ መልዕክት.....ይዙርብህ አቦ ብዬ የመክብብን መልዕክት መለስኩ...
"ዛሬስ ምሳ አታባዪኝም....?"....አለኝ ቀጣዩ መልዕክት....
"ኧረ አባላሀለሁ.....".....አልኩት እንደሚያየኝ ነገር ሸኮርመም እያልኩ።
ትናንት ጨምድጄ ወደቁምሳጥን የላኩትን ቀይ ቀሚሴን ተኮስኩ....ቀይ ቻፒስቲኬን አወጣሁ....በዚህ በኩል የዮናስ ንዝንዝ አቅሌን ሊያስተኝ ሲደርስ አናግሬ ልሸኘው ብዬ ፀጉሬን ልሰራ በሚል ሰበብ ከቤት ወጥቼ ዞሮ መግቢያዬ ተሰየምኩ.......
ዮናስ እጁን አውለበለበልኝ.....የአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ድብልቅ የሆነ ሹራቡ ውስጥ ያለው እጁ ሲውለበለብ 'የዜግነት ክብር' ሊዘመር መስሎኝ ተስተካክዬ እንደመቆም ስል ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደመቀመጫው መራኝ።
አሁን ገና ልቤ ሰንጠቅ ሲል ታወቀኝ.....ይሄ gut feeling የሚባለው ነገር የለም.... ቀልቤ 'የሆነ ነገር አለ' ይለኝ ጀመረ.....
"አንድ ሲንግል ድገመኝ....ለሷም ታዘዛት...."....አለው አስተናጋጁን።
"ምን ልታዘዝ....?....".....አለኝ አስተናጋጁ ጠብ እርግፍ እያለ።
"እኔ ምንም አልፈልግም...."....ስለው የገላመጠኝ አገለማመጥ ካፌው የሱ ነው እንዴ እንድል አረገኝ።
"እንዴት እንደምነግርሽ አላውቅም.....".....አለኝና ሲንግሉን በአንድ ትንፋሽ ጨለጠው።
አላለቀም......

05.05.202510:47
የእድሜያችን ጉዳይ!
(“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ ታሪክ)
☑️ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን በጀመርኩባት በመጀመሪያዋ ቀን ፕሮፌሰራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ካስተዋወቀ በኋላ፣ እኛም በተራችን ሁላችንም እርስ በርሳችን እንድንተዋወቅ አበረታታን፡፡ ከወንበሬ ተነስቼ የምተዋወቀውን ሰው ለመፈለግ ወዲህና ወዲያ በማለት ቃኘት ሳደርግ ከጀርባዬ አንድ እጅ በስሱ ዳበስ አደረገኝ፡፡ ማን እንደነካኝ ለማየት ዘወር ስል ከፈገግታዋ የተነሳ ሁለንተናዋ የሚያበራ አንዲት ፊቷ እጅጉን የተጨማደደ በእድሜ የገፋች ሴት ነች፡፡
☑️“ መልከ መልካም ሆይ፣ እንዴት ነህ? ስሜ ሮዝ ይባላል፡፡ የሰማንያ ሰባት አመት ሴት ነኝ፡፡ እቅፍ አድርጌ ሰላም ልልህ እችላለሁ?” በማለት ያልጠበኩትን ሰላምታ አቀረበችልኝ፡፡
☑️ ፈገግ ካልኩኝ በኋላ በታላቅ ጉጉት፣ “በሚገባ” አልኳት፡፡ እቅፍ አድርጋ ሰላም ካለችኝ በኋላ ጊዜ ሳላባክን አንድ ጥያቄ አቀረብኩላት፡፡
“ለምንድን ነው በዚህ ለጋና የዋህ እድሜሽ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የመጣሽው?” በማለት ቀለድኳት፡፡
እርሷም በቀልድ፣ “እዚህ የመጣሁት ሃብታም ባል ባገኝ ላገባውና ሁለት ልጆች ለመውለድ ነው” አለችኝ፡፡
“እየቀለድኩኝ እኮ አይደለም” አልኳት፣ በዚህ እድሜዋ ለትምህርት ያነሳሳት ምን እንደሆነ ለማወቅ ፍላጎት ስላደረብኝ፡፡
“ሁል ጊዜ የኮሌጅ ዲግሪ እንዲኖረኝ ሕልሙ ነበረኝ፣ አሁን ጊዜው ደርሶ ይኸው ዲግሪዬን ልይዝ ነው” አለችኝ፡፡
☑️ ክፍለ ጊዜው ካለቀ በኋላ ወደ ተማሪዎች መዝናኛው ሕንጻው አቅጣጫ በቀስታ እየተራመድን የሚጠጣ ነገር ተገባበዝን፡፡ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ከትምህርት ሰዓት በኋላ አብረን በማሳለፍ እንነጋገር ነበር፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ያካፈለችኝ በእድሜ ያገኘችው ጥበብና ልምምዷ እጅግ አስገራሚ ነበር፡፡
በቀጣዮቹ አመታት ሮዝ የትምህርት ቤቱ ታዋቂ ሴት ወደ መሆን መጣች፡፡ በሄደችበት ቦታ ሁሉ በቀላሉ ወዳጆችን ታፈራ ነበር፡፡ ዝንጥ ብላ መልበስን ታዘወትር ነበር፡፡ ሴሚስተሩ መጨረሻ ላይ በነበረን የኳስ ጨዋታ ግብዣ ላይ ንግግር እንድታደርግ ጋበዝናት፡፡ ወደ መድረኩ ተጋብዛ ንግግር ስታደርግ ያስተማረችንን በፍጹም አልዘነጋውም፡፡
“መጫወት የምናቆመው በእድሜ ስላረጀን አይደለም፣ መጫወት ስላቆምን ነው የምናረጀው፡፡ ደስተኞችና ስኬታማዎች መሆን ከፈለጋችሁ፣ ምስጢራቱ ግልጽ ናቸው፡፡ በየቀኑ የሚያስቅ ነገር ፈልጋችሁ ማግኘት አለባችሁ፡፡ የምትከታተሉት ሕልም ሊኖራችሁ ይገባል፣ ምክንያቱም ሕልማችሁን ስታጡ ትሞታላችሁ፡፡ በዙሪያችን በርካታ ሰዎች ሞተው እንኳን እንደሞቱ አልገባቸውም፡፡ በማርጀትና በማደግ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ የአስራ ዘጠኝ አመት ወጣት ሆነህ አመቱን ሙሉ ምንም ሳትሰራ በአልጋ ላይ ካሳለፍክ ሃያ አመት ወደ መሆን መምጣትህ አይቀርም፡፡ እኔ ደግሞ ሰማንያ ሰባት ዓመቴ ሆኖ አመቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ባሳልፍ፣ ሰማንያ ስምንት ወደመሆን መምጣቴ አይቀርም፡፡
በአድሜ መግፋት ለሁሉም የተሰጠ እውነታ ነው፡፡ እድሜን መቁጠር ምንም አይነት ልዩ ስጦታና ችሎታ አይጠይቅም፡፡ ለማለት የፈለኩት በሚከናወኑት የሕይወት ለውጦች ውስጥ ሁሉ ያለንን እድል በመጠቀም ማደግ ይኖርብናል ነው፡፡ እኛ በእድሜ የገፋን ሰዎች ያለፈውን ሕይወታችንን አስመልክቶ በአብዛኛው የሚኖርብን ጸጸት ስላደረግናቸው ነገሮች ሳይሆን ስላላደረግናቸው ነገሮች ነው፡፡ ማርጀትንና መሞትን የሚፈሩ ሰዎች ብዙ ጸጸት ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡
በዲግሪ በተመረቀች በአንድ ሳምንት ውስጥ ሮዝ በሰላም ከዚህ አለም ተሰናበተች፡፡ በቀብር ስነስርአቷ ላይ የተገኘን ተማሪዎች በሙሉ፣ መሆንና ማድረግ የምንፈልገው ደረጃ ለመድረስ ከፈለግን በማንኛውም ጊዜ ያንን ማድረግ እንደምንችል ስናስታውስ ዋልን፡፡
ዶክተር እዮብ ማሞ

04.05.202511:41
✔️ኡሚ ቴክኖሎጂስ የ Digital Marketing የ ኦንላይን ስልጠና ምዝገባ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ይቀራሉ!
⚡️ ከሌላው ምን ይለየናል
👉 ባሉበት ሆነው ባመችዎት ሰዐት መከታተል የሚችሉት ስልጠና።
👉 ያለ አስተማሪ በራስዎት ፍጥነት መውሰድ የሚችሉበት አማራጭ ያካተተ።
👉ሙሉ በሙሉ በተግባር የሚሰጥ መሆኑ።
👉 ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ ከ ፕሮፌሽናል ሰርተፍኬት በተጨማሪ portfolio website የሚኖርዎት መሆኑ።
⚡️ ስልጠናው ምን ምን ያካትታል ?
✔️ Digital marketing Theories
💥 Graphics design with Canva basics
💥International payment cards
💥Shopify and WordPress website development
💥Upwork
⚡️ ስልጠናው በምን ያክል ጊዜ ይጠናቀቃል ?
With instructor:- በ 1 ወር
self-paced :- depending on your pace from 1 week to 4 weeks.
ሰልጥነው እንደጨረሱ፦
🔥Professional Certificate እና
🖥 ሰልጣኞች የሰሯቸዉን ስራዎች የሚያሳዩበት portfolio website
🌼 ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ቀድመው ይመዝገቡ!
✅ ለመመዝገብ: በአካል ወይም Umi Registration Bot
🔗 ለበለጠ መረጃ:
📞📞+251924868543
➡️ Customer Support
አድራሻ:- 22 ማዞሪያ KW ህንፃ 1ኛ ፎቅ
✨ Umi technilogies ✨
Website | Telegram | Linkdin | Telegram bot

04.05.202507:43
✨✨ፍቅር ቅብ-14✨✨
ከዮናስ ጋር ከተለያየን ስድስተኛ ወር አልፎ ሰባተኛውን ይዘናል...ጊዜው እንዴት ይሮጣል.....ፍቅር ቅብ የነበረው አብሮነታችን አንድ አመት ከመንፈቅ የቆየ ነበር....በዚ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ዮናስ እንዲህ ነብስ ውጪ ነብስ ግቢ ሆኖ ያሳለፈበትን ቀን አላስታውስም።
"ምንድን ነው ንገረኝ እንጂ....".....አልኩት የተጋባብኝን ፍርሀት ለማባረር እየታገልኩ።
"እ....እ....".....አለና ተጨማሪ ሲንግል አዘዘ።
"ኧረ በፈጠረህ ዮናስ.....".....አልኩት ቆጣ ብዬ።
"አሞኛል.....".....አለኝ ያልጨረሰው ንግግር እንዳለ በሚያሳብቅ አስተያየት....በግንባሩ እያየኝ ነበር።
"ምንህን.....ሲቀጥል እኔ ምን ቤት ነኝ.....?.....".....ግራ ገባኝ።
"እ....አንቺም ሳያምሽ አይቀርም....."....አለና ትልቅ ሸክም ከላዩ እንዳራገፈ ነገር ተነፈሰ....
"ምንድን ነው የምትለው....ምንድን ነው በሽታዬ....ዝም ብሎ ታመሻል አለ እንዴ....."....አልኩት አይኔን በእንባ አቁሬ.....'እንዲህ ነው' ብሎ ባይናገረውም እያለ ያለው ነገር ገብቶኛል....ግን የገባኝ እንኳን ውሸት እንዲሆን በውስጤ እየፀለይኩ ነው....
"ቫይረሱ በደሜ ውስጥ አለ.....".....ሲለኝ ነብስና ስጋዬ ተላቀቀ....ሰውነቴ በደነብኝ.....ሁሉም ነገር ጭው አለብኝ....እያንዳንዱ ድምፅ "ፅፅፅፅፅፅፅ" ብቻ ሆኖ ይሰማኝ ደመር.....ጆሮዬ የሆነ ጩኧት እያወጣ ራሱን ብቻ መስማት ጀመረ....አንደበቴ ተሳሰረ...."እንዴት....መቼ....ለምን....."...... ሌላ የሚጠየቁም የማይጠየቁም ጥያቄዎች ቢመጡብኝም ራሴን አረጋግቼ መጠየቅ አልቻልኩም.....
ተነስቼ ስወጣ ተከተለኝ......
ብዙ ብዙ ነገር ይለፈልፋል....እኔ ግን አልሰማውም.....የሚሰማኝ የጭንቅላቴ ጭውታ ነው....."ፅፅፅፅፅፅፅ".....ይሄ ብቻ ነው የሚሰማኝ።
"ድር እኮ መድሀኒትነት አለው....ቁስልን ለዘብ ያደርጋል....ላፅዳህ ብትዪውም በጄ ይልሻል.....የዘመናት ቆሻሻን ዘወር ብታደርጊው እንኳን ጠረኑ ከርቤም አይበቃውም....."....ያልኳት እህቴ ትዝ አለቺኝ....አፌ ልክ ነበረ....ያልፀዳ ቆሻሻ.....ያልለቀቀ እድፍ ተሸክሜ አፌን እንዳሽሞነሞንኩ አታውቅም እሷ.....
የምናወራውን ብንኖር የት በደረስን....ውስጣችን ጠልሽቶ አፋችንን ማሽሞንሞናችን ምን ጥቅም...ከረፈደ ማስተዋል እንዴት ይቀፋል....ኪሳራ!
***
ፍጥነቴን በእጥፍ ጨምሬ ገሰገስኩ....."ዘወር በልልኝ አውሬ" አልኩት አብሮኝ የሚሯሯጠውን ዮናስ....
"እኔም በቅርቡ ነው ያወቅኩት.....እመኚኝ እድሌ.....".....አለኝ እየተርበተበተ....
"እድሌ አትበለኝ....."....ብዬ አንዴ ሳንባርቅበት ባለበት ቆመ።
እንደሰከረ ሰው እየተንገዳገድኩ ቤቴ ደረስኩ....
አባዬ ቀዝቀዝ ብሎ ጠበቀኝ.....
"ፀጉርሽን ልትሰሪ አልነበር...."....ጠየቀኝ።
"መ....መብራት የለም...."....ብዬው ተስፈንጥሬ መኝታ ቤቴ ገባሁ....
"ምን ሆናለች ልጅቷ...."....አለና ተከተለኝ...."ንገሪኝ እስቲ ምንድን ነው....እኔ አባትሽም ጓደኛሽም ነኝ አይደል...."....አለኝ ትክ ብሎ እያየኝ.....
"ሞኝ ማለት አንድ ስህተትን ደግሞ ደጋግሞ የሚሰራ ነው....".....የሚል አባባል አቃጨለብኝ....ሞት ቢመጣ ለአባዬ አንድ ነገር አልነግረውም ያልኩበት አጋጣሚ ትዝ አለኝ....እንደ እናት መሆን እንዳለበት ሲሰማው የሆንኩትን ይጠይቀኛል.....የሳትኩትን ያለፍርሀት እንዳብራራ ይገፋፋኛል.....እኔም የልብ ልብ ተሰምቶኝ የሆዴን ከዘረገፍኩ በኃላ አባትነቱ ይመጣበታል.....
ነገሩ እንዲህ ነው....
አስራ ሁለተኛ ክፍል ነበርኩኝ....ኢንትራንስ ልንፈተን አካባቢ የነበረ እረፍት ነው....ፕሮቲን ለጭንቅላት ጥሩ ነው ያለው ማን እንደሆነ ባላውቅም አባዬ በጠዋት እየተነሳ በስጋ ፍርፍርና በእንቁላል ያጨናንቀኝ ጀመር.....አብልቶ መክሮ ወደ ላይብረሪ ይልከኛል....ታዲያ ስመለስ የሚጠብቀኝ መክሰስ ልዩ ነበር.... የሚሰራልኝን ምግብ እንዳይቀርብኝ ፈተናው እንዲራዘም እፀልይ ነበር....ለሊት ድንች ጠብሶ ሻይ አፍልቶ ይቀሰቅሰኛል.....እኔ ሳጠና እሱ ጋቢውን ለብሶ ፊት ለፊቴ ይቀመጥና ያንቀላፋል.....
ታዲያ በአንዱ ቀን ጠዋት ቁርሳችንን እየበላን ጨዋታ አነሳ....."እኔ አባትሽ እንዴት ያለሁ የድሮ አራዳ መሰልኩሽ.....".....ብሎ ጀምሮ ከእናቴ በፊት ስለጠበሳቸው አስራ ስድስት ሴቶች ነገረኝ....አብዛኞቹን በእኔ እድሜ እያለ እንዳበሰላቸው እና የዘር ፍሬውን በአግባቡ ቢጠቀምበት አንድ ቀበሌ የሚያህል ልጆች እንደሚኖሩት ነገረኝ.....
ከዚ በኃላ ነው " እንደ አባት እና ልጅ ሳይሆን እንደ ጓደኛ ንገሪኝ እስቲ እስካሁን ምንም የለም....?....".....ብሎ የጠየቀኝ።
"ኧረ የለም....".....አልኩት አንገቴን ቀብሬ።
"ኧረ ተይ ስድስት በመውለጃ እድሜሽ....".....ብሎኝ ሲስቅ ተፍታታሁ....ቀጥዬም ስለ ሁለቱ ኤክሶቼና በሰአቱ ስለነበረው ፍቅረኛዬ የነገርኩት....
ከዛ በኃላ ነው አባትነቱ የመጣው....አንዴ በጥፊ ሲያዞርብኝ ለወራት ያጠናሁት ትምህርት ከአእምሮዬ ብን ብሎ ወጣ....(ለዛ ነው መሰለኝ ፈተናውን ያላለፍኩት)....ነገሩ በዚህ አላበቃም ውጤት ከወጣ እና መውደቄ ከተረጋገጠ በኃላ ነገሩ ባሰ......
"ለነገሩ ከማንም ጋር አሸሸ ገዳሜ እያልሽ ብታልፊ ነበር የሚገርመኝ ኪሳራ....."....."አቤት አቤት 'ፍቅር' አልቀረብሽም ኩክኒያም".....የሚሉ ስድቦችን ከቀበቶው ጋራ ስጠጣ ከረምኩ.....ከዛ በኃላ ነው ለእሱ መንገር እርም ያልኩት።
አሁን አጠገቤ ቁጭ ብሎ "እንደ ጓደኛ" ይለኛል.....የወጋ ቢረሳ ነው ነገሩ.....
****
ሀኒ በጣም አስፈለገችኝ.....እንዲህ ያለ ዱብዳ ወድቆብኝ ለማን አወራዋለሁ.....ባንድ በኩል ደግሞ መክብብ አለ....ሀኒ ለመክብብ ያላትን ስሜት ካነበብኩ በኃላ እሷ ላይ ነፃነቴ ጠፍቷል....
እንዲህ በራሴ ሀሳብ ሰክሬ ስልኬ ነዘረኝ....
"የምሳው ቀጠሮ እንዳለ ነው አይደል.....".....የሚል መልዕክት ነው።
አልመለስኩለትም።
አላለቀም.....

03.05.202516:31
''...አይዞሽ ታገቢያለሽ የሆነ ጊዜ ላይ ከአንድ ቆንጆ ወጣት ጋር ትተዋወቂና በጣም ስለምትዋደዱ ልጁ ተንበርክኮ ታገቢኛለሽ የሚል ጥያቄ አቅርቦ አንቺም ትስማሚያለሽ
...ልክ እንደ ምኞትሽም አባትሽ ክንድሽን አቅፎ ለዚሁ ልጅ ያስረክብሻል....😍
📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
...ልክ እንደ ምኞትሽም አባትሽ ክንድሽን አቅፎ ለዚሁ ልጅ ያስረክብሻል....😍
📨@Enmare1988
📨@Enmare1988

02.05.202518:22
05.05.202508:50
04.05.202517:23
ፍቅር እና ቁጥር
ስንግባባ ሰሞን እኔ መላመድን ለማምለጥ የምባትል ባተሌ ነበርኩ። የተጣመርኩት ባይኖርም ራሴን ብቻዬን እወደዋለሁ።
የማልደራደርበት ማንነት ነበረኝ። ሌሎችን የማደንቅበትና የማከብርበት የማንነት መለኪያያዎችም ነበሩኝ።
እሱ ---- አላውቅም የሱን ፍላጎት........ ብቻ አላጣደፈኝም። የተለየ ፍላጎት እንዳለውም ሊያሳየኝ አልተፍጨረጨረም። የሰው ፍላጎት እና ሀሳብ ሲጫንብኝ እንደማልወድ ገብቶታል።
ማባበሉ አጥንቶ የቀመረበት ነበር። ጆሮዬ ከአንዴም ሁለቴ ከድቶኛል እና በተቆለጳጰሰ የፍቅር ዓረፍተ ነገር የሚደነግጥ ልብ እንደሌለኝ አውቋል። ቀስ በቀስ ለፍፅምና የተጠጋ እሱነቱን ነው የጋተኝ።
በገንዘብ ተተምነው ውድ የሆኑ ስጦታዎች እየገዛ አይደለም ያቀበጠኝ፤ በአንድ አንጎል የምናስብ እስኪመስለኝ ድረስ የሚያስፈልገኝን እና ለልቤ የቀረቡ ስጦታዎችን ነበር የሰጠኝ። ውደጂኝ አላለኝም። እንድወደው ምንም አስተዋፅኦ እንዳላደረገ ዓይነት፣ .....የቀን ተቀን እሱነቱን እየኖረ እንደሆነ ዓይነት
፣....... እኔን ለመማረክ የጨመረው ምናምኒት ትጋት እንደሌለ ፣.......... ለሃጬ እስኪዝረበረብ በሱሱ ለመተብተቤ ያበረከተው ምንም እንደሌለ ሁላ ......ከደሙ ነፃ ነኝ...... እኔ የእለት ተእለት እኔነቴን ነው የኖርኩት ዓይነት እጁን ተለቀለቀ።
የሰው ልጅ አዘቦታዊ ማንነት እንዴት እንዲህ እንከን አልባ ይሆናል ብዬ አልጠየቅኩም። በየእለቱ እየገለጠ ያስነበበኝን የማንነቱን ምሰሶዎች ሰብስቤ እሱ ነው ያልኩትን እሱን በልቤ ገነባሁ ፣ በአዕምሮዬ ሳልኩ። ለዚህ ማንነት እጅ ሰጠሁ።
እዚህ ጊዜ ላይ
ፍቅሩን ፣ ጊዜውን ፣ ጆሮውን ፣ ልቡን ፣ ገላውን ፣ትኩረቱን ያልሰጠኝ የለም። 100% እሱነቱን ያለስስት ነበር የሰጠኝ። እስክበስል ማገዶ እንደምፈጅ ገብቶታል። አልተጣደፈም። ከሞከኩኝ ኋላ እስክበሰብስ እንደምታሽ ገብቶታል።
ሱሴ የሆነ ጊዜ ላይ ....... ያለእርሱ ትንፋሽ እንደሚያጥረኝ የገባው ሰዓት ላይ .......
የሂሳብ ቀመሩን ይጫወት ጀመረ። ቀስ በቀስ ከመቶ እሱነቱ ይገምሰው ገባ። ፍቅሩንም ጊዜውንም ጆሮውኑም ልቡንም ገላውንም ትኩረቱንም በግማሽ ቦደሰው። 50% !! ልቤ የምትደገፈው ምርኩዝ ስታስስ የነጠቀኝን ትንሽ ይጨምርበታል። 75%!! ........ ጨዋታው ይሄ ነው። 100 እንደነበር ይጠፋኛል።
ካጣሁት ግማሽ ይልቅ የተጨመረልኝ እሩብ ያስቦርቀኛል። ልቤ መልሳ እሱን ማምለኳን ትቀጥላለች። መልሶ ከ75% ወደ 25% ሲወርድብኝ የአየር ቧንቧዬ የጠበበ ያህል ደረቴን ያፍነኛል። መልሶ 25% እሱን ይጨምርልኛል። ግማሽ እሱነቱን እንደነሳኝ አላላዝንም። የጨመረልኝ ያስደንሰኛል።
አንድ ቀን ገላውን ለሌላ ሴት አዋሰብኝ። እዚህ ጊዜ ላይ ከሙሉ እሱነቱ 5% ፐርሰንቱን እንኳን አልሰጠኝም።
በብዙ ትዕግስት እና ጥበብ ውስጤ የገነባው እሱነቱ ግን አሁንም አልተገመሰም። ወይም በቀላሉ እንዳይፈርስ አድርጎ ከዓለት ገንብቶታል። ወይም ማመን አልፈልግም። ፍንክች አይልም።
አልካደኝም። በእንባ ታጅቦ ይቅርታ ጠየቀኝ። ይቅርታውን በአግቢኝ ጥያቄ እና ቀለበት አጀበው። የምለው ገባችሁ? ከአምስት 25% ነዳው አይደል? ያደረገውን ሳይሆን ያደረገልኝን እያሰብኩ ተፍለቀለቅኩ። ስለሚወደኝ አይደል አዳራሽ ሙሉ ህዝብ ጠርቶ ፕሮፖዝ ያደረገኝ?
ሶስት ቀን የት እንዳለ እንኳን ሳይነግረኝ ዘግቶኝ ይከርምና በአራተኛው ቀን ለእናቴ ከክርስታል የተሰራ የአበባ ማስቀመጫ ገዝቶ ከች ይላል። ሶስቱን ቀን ረስቼ ለእናቴ ላሳያት ፍቅር እሸነፋለሁ።
እሱ ከሚያሳየኝ የዘቀጠ ማንነት ይልቅ በልቤ ያነገስኩት ማነነት ላይ ሙጭጭ አልኩ። በሂሳብ ቀመሩ ተወናበድኩ።
የእሱን ስዕል ከልቤ ከማፍረሴ ብዙ ቀን ቀድሞ እኔ ፈረስኩ። የእሱን እውነተኛ ማንነት አምኜ ከመቀበሌ ከብዙ ቀናት ቀድሞ የራሴ ማንነት ጠፋኝ።
መላመድን ላመልጠው የምሸመጥጥ አትሌት አልነበርኩ? እሱ ከልቤም ከህይወቴም ሲወጣ ለመሮጥም ለማምለጥም ለማሰብም የተረፈ አቅም አልነበረኝም።
*
ውብ ምሽት አምሹልኝ!!♥️❤️♥️❤️
ሜሪ ፈለቀ

04.05.202510:21
አዕምሮህን ስትወደው ፤ አካልህን ስትወደው፤ንቃትህን ስትወደው፤ውስጥህን ስትወደው ራስህን ላለመጉዳት ምንም ነገር ታደርጋለህ።ምክንያቱም የምትወዳቸው ነገሮች በሙሉ ንቃትን የሚሰጡህ ነገሮች ናቸው ። እነዚህን ከጠላሀቸው ሁሉንም ነገር ቀስ በቀስ ታጣለህ።
❤️ ለወዳጆቾ ማጋራት አይዘንጋ 👍✅
➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
➡️@Enmare1988
❤️ ለወዳጆቾ ማጋራት አይዘንጋ 👍✅
➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
➡️@Enmare1988

04.05.202507:43
已删除04.05.202513:02

03.05.202511:32
✅ዛሬ ደግሞ የምጠቁማችሁ ቻናል የሚገራርሙ ዓለም አቀፍ እውነታዎችን ሳይኮሎጂዎችን የሚለቅ የሚያስገርሙ ለማመን የሚከብዱ የዓለማችንን ጉዶች የምታገኙበት ትምህርት ምትቀስሙበት ምርጥ ቻናል ነው!
✅ቻናሉን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ንኩት
👇👇👇
🔵@yegudalem
🔵@yegudalem
🔵@yegudalem
🔵@yegudalem
ቤተሰብ ይሄን ሼር በማድረግ ተባበሩኝ !
✅ቻናሉን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ንኩት
👇👇👇
🔵@yegudalem
🔵@yegudalem
🔵@yegudalem
🔵@yegudalem
ቤተሰብ ይሄን ሼር በማድረግ ተባበሩኝ !
02.05.202515:56
ንፁህ ናት....ከሩቅ የሚጣራ ሽቶ ፣ ቀይ ቻፒስቲክ ፣ ሜክአፕ ምናምን የምትወድ ታይፕ አትመስልም....ምቾት ያጨናነቃት አይነት እንደሆነች በደንብ ሳላውቃት ነው ያወቅኩት ......እንዳየኃት አንድ የባህል ልብስ ቤት የምትሰራ ጓደኛዬ ያለችኝ ነገር ትዝ አለኝ....
"ሀብታም ያስታውቃል.... ገና እግራቸው ሱቃችን ሲገባ ነው የምናውቃቸው....ብዙም አይሽቀረቀሩም....በቃ እነርሱ ጋር food is makeup ነው..."...የምትለው ነገር ነበራት።
የአለቃችን ልጅ ናት....የዩንቨርሲቲ ትህምርቷን እንደጨረሰች አባቷ የመስሪያ ቤታችን ቁልፍ ቦታ አስቀምጧት ነው(ይሄ ነገር የአማርኛ ፊልም ላይ ብቻ ያለ ይመስለኝ ነበር)
ከስራ ውጪ የመስሪያ ቤት ሰራተኞች በሁለት ወይም በሶስት ተቧድነን ምሳ የመብላት የቆየ ልምድ አለን...
እሷ ከእኔ ጋር እንድትቧደን ያላደረግኩት ጥረት አልነበረም....ቂቤ በሚያቀልጠው ምላሴ በት በት ብዬ የስራ ባልደረባዬ ብቻ ሳትሆን የምሳ ባልደረባዬም አደረግኳት....
ጉድ እና ጅራት ከበስተኃላ ነው እንዲሉ ጉዷንም ጅራቷንም ሳየው ጊዜ መጋጋጤ ፀፀተኝ....
ከተማው ላይ ሁላ የሼፍ ዩሀንስ ምግብ ቤት የተከፈተ እስኪመስል ድረስ ቢጢሌ ቢጢሌ ምግብ በትላልቅ ሹካና ማንኪያ የሚቀርብባቸው ቤቶች ታዞረኝ ያዘች....ለዛች ቢጢሌ ምግብ የምከፍለው ረብጣ ገንዘብ የእግር እሳት ሆኖ ይፈጀኝ ጀመር።
የምግቦቹን ስም በቅጡ ባላስታውስም በሁለት ሳምንት አስር ኪሎ እንደቀነስኩ ግን አስታውሳለሁ.... ጓደኞቼ "እንደው ያ ነገር ከሆነ ለምን አትመረመርም....".....ሲሉኝ....እናቴ ደግሞ "የትም እያደርክ በሽታህን ተከናነብክ....."....ብላ ስታለቅስብኝ ጊዜ ነው የባነንኩት.....
'ምነው ሸዋ ደሀ ነኝ እንጂ መቀለጃ ነኝ እንዴ' ብዬ እርግፍ ብዬ ሳላልቅ እርግፍ አድርጌ ተውኳት....
ከመሞት መሰንበት....

Ads
😌😌ዛሬ ማታ ትልቅ GIVEAWAY አለ የSTAR, የTON ወይም ብር የምንሸልም ይሆናል ማንም እንዳይቀር ✌️FAMILY😌😌
#Ads
GIVEAWAY ላይ ለመሳተፍ በቅድሚያ የዚህን CHANNEL JOIN ማለት አለባችሁ 😏@UNIQUECRYPTO_24l7😮
GIVEAWAY? 🤝 @UNIQUECRYPTO_24l7 👈JOIN HERE

04.05.202516:30
ዛሬ ደግሞ የምጠቁማችሁ ቻናል የሚገራርሙ ዓለም አቀፍ እውነታዎችን ሳይኮሎጂዎችን የሚለቅ የሚያስገርሙ ለማመን የሚከብዱ የዓለማችንን ጉዶች የምታገኙበት ትምህርት ምትቀስሙበት ምርጥ ቻናል ነው!
ቻናሉን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ንኩት
👇👇👇
@yegudalem
@yegudalem
@yegudalem
@yegudalem
ቤተሰብ ይሄን ሼር በማድረግ ተባበሩኝ !
ቻናሉን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ንኩት
👇👇👇
@yegudalem
@yegudalem
@yegudalem
@yegudalem
ቤተሰብ ይሄን ሼር በማድረግ ተባበሩኝ !

04.05.202510:18
ለዮቱብ ወይም ለቲክቶክ ቪዲዮ 📱በስልክ ድምፃቹን ስቀዱ ከጎን ላይ የተለያዮ ጫጫታዎች ድምፃቹ ላይ እየገባ አስቸግሯቿል
በ 1 ካርቶን 2 ማይኮችን የያዘ 20 ሜትር ርቀት ድረስ የሚሰራ ከጎን የሚገባ ጫጫታን ፊልተር የሚያደርግ ቭሎግ ለምትሰሩ ለኢንተርቪው ከስልካቹ ቮይስ የበለጠ ጥራት ይሰጣቹሀል🎙
👇in box
@Laday_33
0941546755
0777403952
🤳እርሶ ብቻ ሀሎ ይበሉን...

03.05.202519:29
✔️አንዲት እንስት እራሴን ላጠፋ ነው ነፍሴን ማትረፍ ከቻልክ አውራኝ አለቺኝ በውስጥ መስመር
✔️ደንግጥ ብዬ ስልክ ቁጥሬን ላኩላት በፍጥነት ደወለቺልኝ
ያለሽበት ልምጣ ስላት አንተ ያለህበት መምጣት እችላለሁ ብላኝ ያለሁበት መጣች ።
✅️ዘመናዊ መኪና የያዘች ፤ ፊቶ ጥርት ያለ፣ የቀይ ዳማ ፀዴ ፐርፊውም የተቀባች ልጅ አጠገቤ መጣች ።
✔️የሆነችውን ስትነግረኝ ቦይ ፍሬንዷ ድንገት እንደተጣላት ። ድብርቷን ለማባረር ሳውዝ አፍሪካ Tsitsikamma national park ቦትስዋና chobe park ዱባይ ምናምን ዞራ ድብርቷን ሊያጠፋላት እንዳልቻለ ምን አይነት እድለቢስ ሰው እንደሆነች አተተችልኝ
✔️ቤተሰቦቿ በዚህ ጉዳይ ተጨንቀው ሳይካትሪስት ጋ እንደላኳትና ምንም ሊረዳት እንዳልቻለ አንድ ሁለት እያልን ቀድሚያት ሰከርኩ
ልጠቁማት ያሰብኩት መከራ ዘንቦባቸው እንዴት አለም ላይ ታላቅ የሆኑ ሰዎች ታሪክ ፣ አነቃቂ የመፅሃፍ ቅዱስ ታሪክ ፣ የማቃቸውን መከራ ውስጥ የሚንከባለሉ ሰዎችን ታሪክ
ተውኩት ።
✅ አሁን እሷ ካልሞትኩ እያለች እኔ ካልኖርኩ ማለት አለብኝ ወይ ????
እሷን ማጠንከር የሚችል ጎበዝ ስልኳን የምልክለት ነኝ፦

03.05.202510:17
በዚህ ኑሮ ውድነት Protein powder ገዝቶ ለግል አሰልጣኝ ተከፍሎ የማይቻል ነው ለዚህም ነው Viable Ebooks ከተለያዩ አለምአቀፍ ዌብሳይቶች እና Virtual አሰልጣኞች ጋር በመተባበር ይሄንን "የጡንቻ ግንባታ በኢትዮጵያ ምግቦች" የሚል EBook ይዘንላችሁ የመጣነው።
✅መጽሀፉ የያዛቸውን ሀሳቦች ለማወቅ እና መጽሀፉን ለማግኘት
🔵 በ t.me/viable_Ebook
🌐 በ t.me/viable_Ebook ያናግሩን።
☑️ አስታውሱ መጽሀፉን ስታገኙ አብሮ የ አንድ ወር ከእናንተ ጋር የሚስማማ Workout plan ይኖረዋል በተጨማሪም ይህ መጽሀፍ ሌሎች ቦታዎች ላይ አይገኝም‼️
✅✅ ዋጋ:-100ብር ብቻ(ለ 3 ቀን የሚቆይ ቅናሽ)
ቻናላችን:- t.me/Viable_books
✅መጽሀፉ የያዛቸውን ሀሳቦች ለማወቅ እና መጽሀፉን ለማግኘት
🔵 በ t.me/viable_Ebook
🌐 በ t.me/viable_Ebook ያናግሩን።
☑️ አስታውሱ መጽሀፉን ስታገኙ አብሮ የ አንድ ወር ከእናንተ ጋር የሚስማማ Workout plan ይኖረዋል በተጨማሪም ይህ መጽሀፍ ሌሎች ቦታዎች ላይ አይገኝም‼️
✅✅ ዋጋ:-100ብር ብቻ(ለ 3 ቀን የሚቆይ ቅናሽ)
ቻናላችን:- t.me/Viable_books

02.05.202515:56
显示 1 - 24 共 1 272
登录以解锁更多功能。