Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ምስለ እኔነት🤩 avatar

ምስለ እኔነት🤩

ቃል ህይወት አለው.....ምድርም በፍጥረቷ ፡ሰማይንም በኑረቱ አቁሟልና'
እናም በኖርኩትም ባየውትም ስሜትን እና እኔነትን ለመግለፅ ይህ ገፅ ተመስርቷል።
TGlist 评分
0
0
类型公开
验证
未验证
可信度
不可靠
位置
语言其他
频道创建日期Серп 18, 2023
添加到 TGlist 的日期
Серп 19, 2024
关联群组

记录

29.03.202523:59
311订阅者
26.03.202521:10
200引用指数
30.03.202519:37
60每帖平均覆盖率
27.02.202513:40
42广告帖子的平均覆盖率
06.04.202509:40
13.16%ER
05.04.202523:59
19.48%ERR

ምስለ እኔነት🤩 热门帖子

转发自:
እንማር avatar
እንማር
27.03.202518:29
#13

በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት


አለም አንድ ናት ሲባል እኔ ፕላኔቶቼን የምቆጥረው ከርሷ አካል ነበር።
አለሜ ስላት ሁሉ እኔነቴን በመስጠት መሀል ስላገኘኃት ነበር....ያሳለፍነውን ሳስብ ወደ ፊት ምንም ማለፍ እንደማያቅተን በሙሉ ልብ ሳወራ እገኛለው።።።ለምን?ብባል መልሴ...የርሷ ጥንካሬና የእኔ ትግስት አብሮ መጓዙ ለዚህ አብቅቶናል......ዳሩ ነበርነት መሀል ተሰይመን ተገኘን......ቅድሚያውኑ.....
ነበርነቴ የጀመረው ያን ዕለት ..ነው...

ንዴት፤ብስጭት፤ጭንቀት፤ፍርሀት፤ራስን ማጣት ውስጤ የነበሩ ዕለት ፊቴ የነበረችው እርሷ ነበረች።የዳበስኩት እሷነቷን ሌላ ጋር ሳገኘው....በሳቀችልኝ ጥርሶቿ እርሱ ጋር ስንቴ እንደሳቀች እያሰብኩ እኔነቴ ከላዬ ሲወርድ ታወቀኝ....ዝም ብላ አይኔን መመልከቷ አበሳጨኝ ንቄሀለው...አሳፋሪ ስራ አልሰራውም አይነት አተያይ እያየችኝ አገኘኃት።
አብራት ኗሪው ላይ ትኩረቴ አልነበረም የኔ የሆነ ላይ ነው እይታዬ
የኔ የነበረ.....
ድንገት ብቻችንን ሆንን ይብረር..ይሩጥ ሳላውቅ ያ ሰው ፊቴ አልነበረም።
እኛነታችንን እንደ ቀላል በስሜት ግለት ስትጫወትበት እንደቆየች ሳስብ...ማሰቢያዬ ራሱን ሲስት ታወቀኝ
ዘልዬ አነቅኳት...የምሳሳላቸው አይኖቿ...ገና ያኔ ስታየኝ ፍስስ የሚያደርጉኝ ውብ እይታዋ ተቀየረ...ምን እያረክ ነው ?የሚል አተያይ...
እጆቿ አንገቴ ስር አድነኝ በሚል ሲቃ ሲዞሩ ይሰማኛል
ድምጷ ሲለወጥ...ደም ስሯ ለመውጣት ሲወጣጠር እያየው ነው።በዚህ ሁሉ መሀል እጆቼ ከጉሮሮዋ ስር ነበሩ....


የኔ በሆነ ልቧ ውስጥ የኖረው እሷነቷን በአንድ ቀን ይሁን በተደጋጋሚ ነው??እየኖረ አለ ብዬ ሳስብ ያፈተለከው..??መች ይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተወችኝ??ያወራሁላት ጥንካሬ የት ተሰወረ....ማለፍ ያልቻለችውን ምንስ ህመም ብሰጣት ነው....
ሳናድዳት?ሳበሳጫት ነው??እልኃን ለመወጣት ጀምራ ማቆም ተስኗት ነው???
እንጃ መች ይሆን እያለች የጠፋችው...ቀን ከርሱ ውላ ማታ እንደ ይሁዳ አቅፋ የሸጠችኝ መች ነበር.....ያ ውብ ሳቋ ትዝ ሲለኝ አሁን እንዲያ በሲቃ መውጣት ስላቃተው ደስ አለኝ...
ስትስመኝ..ደስ ያለኝን...ስትነካኝ ልቤ ስውር ያለውን አሰዋወር...ማስመሰል መሆኑን ሳውቅ..ምን ጊዜ ነበር ህይወቴ ውሸት የሆነው....?ነገና ዛሬዬ መሀል ድልድይ ሳደርጋት ልቤን ያለ ስስት ስሰጣት ነው....ይህ ይሆን በደሌ.....

በነዚህ ሁሉ መለል በእልህ አፍጥጬ እጆቼ እርሷ ጋር ነበሩ.....

ድንገት.......


......ዝም..........አለች።የፈጠጡብኝ አይኖቿ ተከደኑ።
ሲታገለኝ የነበረው ሰውነቷ ደነዘዘ......አንገቴ ስር ሲዛወር ያላየውት ፤ያልገባኝ ፤ያልተሰማኝ የእጇ ንክኪ...እጆቿ ሲወርዱ ነቃው...
ፊቷን አዞረች...ተሸናፊ መሆኗን በዝምታዋ ነገረችኝ....
ላትመለስ በገዛ እጆቼ አይኔ እያየ መጓዟን በሰውነቷ ቅዝቃዜ አስረዳችኝ።።

ለመጀመሪያ ጊዜ ከሬሳ ጋር ተፋጠጥኩ።
ጨነቀኝ፤ትንሽ ቆይታ የምትነሳ መሰለኝ ጠበኳት.....ዝም....
ቀሰቀስኳት...ጭጭ
የማላውቀው ፍርሀት....ጭንቀት...ብቸኝነት....በቅፅበት
ወረሱኝ...ሀጢአተኝነት ተፀናወተኝ
እኔነቴን ልቤን ህይወቴን ውሸት ማረጓ ሳያንስ...ሰውነቴን ቀማችኝ...ህሊናዬን የገዛ እጆቼ ነጠቁኝ.....ምንም አላልኩም...ያደረግኩትንም አላውቅም.....

ግን......

አፈቅራት አልነበር....እወዳትስ አልነበር...
ለምን?ለምን አረግሽው አላልኳትም?

አላፈቅራትም ነው ።ባልወዳት ነው ያ ሁሉ የሆንኩላት??


እንጃ
እኔም ዝም እርሷም .... ዝም
ፍቅር እንዲህ ነው?? ገሳጭ እንጅ መላሽ የሌለበት ትግል ውስጥ ገባው።
......
ሁሉም ውሸት ነበር "አትወደኝም" ብትወደኝ አትክደኝም።
"ብወዳት"
አልገላትም.....

በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት ።ውሸት....




ኢሊ ዲያ ✍️



https://t.me/justhoughtsss
https://t.me/justhoughtsss
በዚህ ዘመን ሰው ሆድ እንዲብሰው እንደማድረግ ቀላል ነገር የለም ። ሰዉ እንዳለ ስስ ሆኗል ። ቀኑ እንዲጨረብ ትንሽ ምክንያት ይበቃዋል ።

አጠገብህ ያለውን ስራ ፈት በብሄርህ ምክንያት ነው ስራ ያላገኘኸው ብትለው ሲብሰከሰክ ይውላል ።

አንዱ ጓደኛህ ሲደውልልህ "እየነዳሁ ነው መልሼ እደውልልሃለሁ" ብትለው ቀኑን ሙሉ ይቆዝማል ።

የሆነችን ልጅ "በጣም ወፍረሻል" ብትላት ለጊዜው የሆነ የሆነ ነገር ትልህና መስታወት ፊት ቆማ ትብሰለሰላች ።

እስኪ አንዱ ሲስቅ ጠብቀህ "ሳይኖርህ አትሳቅ" በለው ፤ ወዲያው ይከስማል።

እፊቱ እንግሊዘኛ ስታወራ የሚከፋው ሰውም አለ።

አፍቅሮ የተጎዳ ሰው "እህህህ" እንዲል የፌስቡክ ጨለምተኞች ከblack and white ፎቶ ጋር የሚለጥፉት አጭር ጽሑፍ ይበቃዋል ።

ናፋቂውን ምንም አትበለው ፤ ገና ደመና ሲያይ ውስጡ ይረበሻል ።

ለማልቀስ "ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ" የሚል ዘፈን ብቻ የሚበቃው አለ ።

ደህና ነሽ ? ስትላት እንባዋ ግጥም የሚል አለች ።

ህልምህ ምን ነበር ? ብለህ ብትጠይቀው የማይከፋው አለ ? ።

ፀሐይ ሲመታው ብቻ ኑሮ የሚመረው አለ ።

ሰዉ እንደ ድሮው ረጅም የታክሲ ሰልፍ የመጠበቅ አቅም የለውም ። መኪና የለኝም ወይም የራይድ የለኝም ብሎ ያዝናል ።

እና ይሄ በሆዱ እንባ ያጠራቀመ ህዝብን ማስለቀስ ምን ሞያ ይጠይቃል ?

ከባዱ ነገር ተስፋ መስጠት ነው ። ተስፋ ስጠው ስልህ ምክረው ማለቴ አይደለም ። ከምር ተስፋ ስጠው ። አስቀው ። አለሁ በለው ። ራሱን እንዲችል አድርገው ። ባዶ ሆዱን አትሰክሰው ። አብልተህም አትሰክሰው ። ዕድል ስጠው ። እመነው ። እቀፋት ። ተቃቀፉ ። ምናምን...

Via: Hab HD
25.03.202505:28
Healing Energy❤️‍🩹


በህይወትህ ውስጥ የሚያስፈልጉ፤እንግዳ የሆኑ ሰዎች አሉ። ለአንተነትህ ዋጋ የሚሰጡ ፤ ነፍስ የሚዘሩ ደጋግ ሰዎች ። ምድር ከሰማይ ድብልቅልቁ ሲወጣ የሀዘን ፅልመትህን ገፈው እንደ አዲስ ሚወልዱህ፤የሰው መልዐክ የሆኑ።✨️


የሆነ ጊዜ፤ባላስተዋልከው ሁኔታ፤ድንገት ወደ ውስጥህ ስትመለከት ልብህ ላይ ደስታን ለመትከል ከፍ ዝቅ ሲሉ ታገኛቸዋለህ። እስኪበቃህ ትገረማለህም... ማን ይህን አስቦት? እነዛ ሰዎች ላንተ መዳን ይለፋሉ ብሎ ማንስ ጠርጥሮ ?

እሷን ያስተዋልኳት ያኔ ነበር።ቁስልነቱ አልፎ ጠባሳ ሆኖ የቀረ የህይወቴን ክፍል ፈልፍላ ከስሩ ነቅላ ለመጣል ስትጣጣር።የኔ ያልኳቸው የወጉትን እርሷ ሩቅ ሆና ስታክምልኝ ተገናኘን።እንዳልኩህ ነው "እንዴት እሷ ይሄን?... ኸረ ምን ገዷት ከቶስ እንዴት አስተውላው ..." እያልኩ ተገረምኩ፤እስኪበቃኝ ድረስ።💞


በህይወታችሁ እንዲህ ሳጠሩት "አቤት... አለሁ" የሚላችሁ፤ያልሰበረውን የሚጠግን ሰው አያሳጣችሁ የኔ ሰዎች።


✍️🏼ቃል ነበርኩ

https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages
27.03.202505:50
የዕለቱ ስንቅ

"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል" 

አባ ቴዎዶር

ሰናይ ዕለተ ሐሙስ
መታቀፍን የናፈቀዉ
መንፃት አምሮት ከቆሸሸዉ
መዳበስን ከሚመኘዉ ትንሹ እጄ
መገፋትን ተላምጄ
ስዘረጋ ከምመታዉ ለሰላምታም ማነፈገዉ
ምን ባረግ ነዉ
ካይኔ እንባ ለመውረዱ
ከነፃዉ ፊት ሰዉ መስገዱ
ዛሬን ታየኝ የሰዉ ፍጡር
አንዱ አንጪ አንዱ አቁሻሽ አዬ ምድር
ካነፁኝ ፊት መከበሬ
ከረሱኝ ቤት መሰበሬ
ያልፋል አደል ይኸዉ ቀኔ
ራሴን ስፈጥር እኔዉ በኔ


ኢሊ ዲያ✍✍
@onelife21A
እንደ ታሪኬ መኖር ትቼ ነበር።
እንደምንም እንቅልፍ ወስዶኝ የነቃው ሰአት ልቤን መሸከም አቅቶኝ ያውቃል....አውጥቼ ልጣልልሽ የሚል በመጣ ብዬ የተመኘሁባቸው ምሽቶች ብዙ ናቸው...
ሲመሽ ደስ ይለኝ ነበር...ማንም እንባዬን አያይማ...
...ፀሀይ ስትወጣ አልወድም...እንባና እኔን ሳራርቅ እገኝ ነበር..ለምን? እንዳይጠይቁኝ ስለምፈራ ነው ።
ውበቴ ረግፎ ያውቃል...ልብሶቼ ሲሰፉኝ ይታወቀኛል.....
ለራሴ ማሰብ ትቼ ነበር....ትውት....
ይሄ ሁሉ ነበሬ ነበር።
ነበርም ነበር ይሆናል.........
ነበር....ግን ይህም "ነው"ነበር ይሆናል።
ችግሩ ቀስ በቀስ የሚሆን ነገር ያደክማል... አንዴ የለየለት ሞትና ቀስ በቀስ የሚታለፍ ሞትም እኩል አይደሉም...

"መርዝም ቀስ በቀስ ነው ሚገለው "....ቀስ በቀስ..."እየሞትኩ ነው ።



ኢሊ ዲያ ✍️
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ 🤗🤗
28.03.202514:07
登录以解锁更多功能。