04.05.202519:06
ምን ሆንኩኝ ክርስቶስ
ፅድቄን ግፍ በለጠው?
ለምን በድዬ እንኳን
የማልደነግጠው?
ምንሆንኩኝ ጌታ ሆይ
ተው ቅጣ ዝም አትበል
ልክ ነው ብዬ ነው
ድፍረቴን ምቀበል።
@mikiyas_feyisa
ፅድቄን ግፍ በለጠው?
ለምን በድዬ እንኳን
የማልደነግጠው?
ምንሆንኩኝ ጌታ ሆይ
ተው ቅጣ ዝም አትበል
ልክ ነው ብዬ ነው
ድፍረቴን ምቀበል።
@mikiyas_feyisa
16.04.202519:19
እንደምነህ አንተ ሰው
እንደምነህ ቀያፋ
የወነጀልከው ንፁህ ሰው
መስቀሉን ይዞ ተደፋ
እንደምነህ አዛዡ
እንደምነህ ጲላጦስ
አስቀየምካቸው ህዝብህን
ፊትህ ባቆምከው
አምላክ ጦስ?
ምንተሰምቶህ ይሁን ሲንፏቀቅ
ምን ተሰማቶህ ይሁን ሲያቃስት
እጅህን ታጥበህ ከዳኸው
ወይስ አነሳኸው በስስት
ሸንጎ ላይ ስታቆመውስ
የፍትህ ሻማ ሲለኮስ
ከፊትህ ፃዲቅ የሆነው
በርባን ነው ወይስ ክርስቶስ?
እንደምነህ አንተ ሰው
እንደምንነህ በርባን
ክርስቶስን ገለን
አንተን ይዘን ገባን
ያስቃል አይደለ
የሞኝ ሰው ጩኸት
ያስቃል አይደለ
የቂል ፍትህ ምርጫ
ከወንበዴ ይብሳል
የንፁህ መቀጫ
በል አሁን ቶሎ ሂድ
የሟች ቤተሰቦች
ያንተን መውጣት ሰምተው
ሳያፈላልጉ
እሺ ወዳንተ ልምጣ
እንዴት ነህ መፃጉ?
አልጋህን የት ጣልከው
ጌታህን ምን አልከው
ባይገባው እንኳን
ያጨደውን መብላት
የዘራውን መቃም፥
እንደው ላነሳህ ሰው
ግርፋቱ አይበቃም?
የታመመ አይደል ወይ
የተጎዳ አይደል ወይ
በግፍ የሚበቀል?፥
ለምን ያዳነህ ሰው
እርቃኑን ሚሰቀል?
ተው እዘን መፃጉ
ተው እዘን ጲላጦስ
ተው እዘን ግን በርባን
ያልበደለ ሰቅለን
ወንበዴ ታቅፈን
መቅደስ እየገባን፦
ቀና አትበል ቀያፋ
ለአይሁድ አታዳርስ
ሀሰት የድል ቅጂ ፤
"ገድለኸው አይደለም
ሞቶልህ ነው እንጂ!"።
@mikiyas_feyisa
እንደምነህ ቀያፋ
የወነጀልከው ንፁህ ሰው
መስቀሉን ይዞ ተደፋ
እንደምነህ አዛዡ
እንደምነህ ጲላጦስ
አስቀየምካቸው ህዝብህን
ፊትህ ባቆምከው
አምላክ ጦስ?
ምንተሰምቶህ ይሁን ሲንፏቀቅ
ምን ተሰማቶህ ይሁን ሲያቃስት
እጅህን ታጥበህ ከዳኸው
ወይስ አነሳኸው በስስት
ሸንጎ ላይ ስታቆመውስ
የፍትህ ሻማ ሲለኮስ
ከፊትህ ፃዲቅ የሆነው
በርባን ነው ወይስ ክርስቶስ?
እንደምነህ አንተ ሰው
እንደምንነህ በርባን
ክርስቶስን ገለን
አንተን ይዘን ገባን
ያስቃል አይደለ
የሞኝ ሰው ጩኸት
ያስቃል አይደለ
የቂል ፍትህ ምርጫ
ከወንበዴ ይብሳል
የንፁህ መቀጫ
በል አሁን ቶሎ ሂድ
የሟች ቤተሰቦች
ያንተን መውጣት ሰምተው
ሳያፈላልጉ
እሺ ወዳንተ ልምጣ
እንዴት ነህ መፃጉ?
አልጋህን የት ጣልከው
ጌታህን ምን አልከው
ባይገባው እንኳን
ያጨደውን መብላት
የዘራውን መቃም፥
እንደው ላነሳህ ሰው
ግርፋቱ አይበቃም?
የታመመ አይደል ወይ
የተጎዳ አይደል ወይ
በግፍ የሚበቀል?፥
ለምን ያዳነህ ሰው
እርቃኑን ሚሰቀል?
ተው እዘን መፃጉ
ተው እዘን ጲላጦስ
ተው እዘን ግን በርባን
ያልበደለ ሰቅለን
ወንበዴ ታቅፈን
መቅደስ እየገባን፦
ቀና አትበል ቀያፋ
ለአይሁድ አታዳርስ
ሀሰት የድል ቅጂ ፤
"ገድለኸው አይደለም
ሞቶልህ ነው እንጂ!"።
@mikiyas_feyisa
07.04.202512:51
የኔ ልዕልት ፡ ስሚኝ አሁን
አይጠፋሽም
ውስጥሽ ያውቃል፤
ችግር አቅፈን ምናድርበት
የስካሁኑ ጊዜ ይበቃል።
ምናድግበት ሚስጥር ታየኝ
ሰውነቴን ሀሴት ዋጠው፤
ግድ የለሽም ትንሽ ቆርሰን
ፍቅራችንን እንሽጠው!።
የሚገዛ ሀገር ሞልቷል..
ነጠላ ነው ሚገጥመኝ ሰው
ብቸኛ ነው የማየውም፤
የከተማው ባለትዳር
ገንዘብ እንጂ ፍቅር የለውም።
ያሳዝናል ቀዬው ብታይ
እስቲ ይቅመሰው የኛን መገን፤
ፍቅር እንደሆን ሞልቶን ተርፏል
ትንሽ ካሽ ነው ሚያስፈልገን።
እንዳትሰጊ ፡ አንዲት እንኳን
ይሄ ይሆናል የእግዜር ውጥን፤
አልኳትና በረብጣ ብር
ከኛ ሰፍረን ፍቅር ሸጥን!።
ከዛን..
ተመቻቸን
ህይወት ደላን
ገርበብ አለ የአይናችን ዘብ፤
"ያለፈው ዓለም አይገባው
ፍቅር ኖሮት ያጣ ገንዘብ።"
ብለን ሳቅን
ተቃቀፍን
ፍስሃችን ምድርን ሞላ፥
ዓለም ለኛ ገነት ሆነች
ምድር ሆነች የኛ ተድላ።
የመንደሩን አይን ገዛን
ታላቅ ታናሽ አከበረን ፤
ሁሉ ሞልቶን ተደላድሎ
ትንሽ ብቻ ፡ ገንዘብ ቀረን።
ሰልችቶናል ስናገኘው
አሸዋ ላይ መልክን መሳል፤
ለታደልነው ብዙ ምኞት
የነበረን ገንዘብ ያንሳል።
ሰማዩ ላይ ስናማትር፡
መርከቡ ላይ ስናማትር፡
ስናይ ውለን የባህሩን
ግራ የገባው ፡ ውዝዋዜ ፤
ቁጭ ስንል ሀሳብ መጣ
አለን ለካ ፡ ብዙ ጊዜ!።
ተነጋገርን
ተማከርን
ካረጀ ሀብታም አንጋጠጥን፤
ሻንጣ ሙሉ ገንዘብ ወስደን
ሽርፍራፊ ጊዜ ሸጥን!።
አቤት ሀሴት
አቤት ፌሽታ
ህዝቡ ባዶ ቅኔ ያምጣል፤
ገንዘብ ደስታ ባይገዛ እንኳን
እልፍ ደስታ ይዞ ይመጣል።
የሚያቆመን ፍጥረት ጠፋ
ፍስሃችን ምድርን ሞላ፥
ግን አሁንም አልተነሳም
የህዝባችን አይነ-ጥላ!።
ምናገባን እኛ ኖርን
እኛ ኖርን ምናገባን፤
ግን አንድ ሌት በህልማችን
ስልል ያለ ሀሳብ ገባን፦
"ፍቅራችንን ከላይ አይቶ
ይህን ፀጋ እርሱ ሰጠን፤
አንድ ወንበዴ ገፍቶ ቢዘርፍ
ምንድነው ግን የሚውጠን?"
ብለን አሰብን
ተብከነከን
ያ ደላላ ፡ መጣ ዳግም፤
ያገናኘን ፅኑ መድህን
ከፍቅር ውጪ አይፈልግም።
ተመካከርን .... በቃ ይሁን!
ይህ ይሆናል የእግዜር ውጥን፤
ብለን ትንሽ ፡ የማትጎዳ
በድጋሚ ፡ ፍቅር ሸጥን!።
እርሱ ይክበር
ሰላም ተኛን
ህልማችንን እርሱ ረዳ፤
የሚጣፍጥ ለሊት አድረን
ደግሞ ነቃን በማለዳ።
ግና...
የትላንቱ ህመም ቢሻር
ምቾት ዛሬን ቢንሰራፋም፦
እየሳቅን ውለን አድረን
የሚያውከን ነገ አይጠፋም።
ትንሽ ብለን ፦ ስንቀንስ
ጥቂት ብለን ስናወጣ፥
እለት በለት እ.የ.ባ.ሰ
ያልታሰበ ጉድ ሲመጣ፤
ትንሽ ፍቅር ፣ ትንሽ ጊዜ
ትንሽ .. ትንሽ "ትልቅ" ሆኖ ፤
ሳናስተውል ያለን ፍቅር
በየዳናው ተበትኖ ፤
ዝም ማለት ልማድ ሆነን
መቀላለድ ወዙ ጠፋን
ደስታችንን ለማስቀጠል
አንጀት ቋጥረን ብዙ ለፋን።
ግን አልሆነም ውጥናችን
ቅዠት ገዛን ተገላብጦ፤
ህይወታችን መንቀፍ ሆነ
ያንዱን ድክመት ብቻ መርጦ።
"አንተ እኮ ነህ እንዲህ ያልከኝ"
"አንቺ እኮ ነሽ እንዲ ያረግሽው"፥
"ከዚህ ኋላ ይሄ በቃኝ"
"የስካሁኑን ፍቅር እርሺው!"።
ተቃቃርን እንደ ሩቅ ሰው
ባላንጣ ሆንን በኛው ሜዳ
እንስፍስፉን አንጀት ጥለን
በአዳር ሆንን እንደ ባዳ።
አንገርምም?
ወዳጅ ዘመድ በርቱ ሲለን
ሲቀናብን የውጪ ሰው፤
ያቀፍነውን ጥሬ ገንዘብ
አይነተን ቆጥረን ሳንጨርሰው፥
ከጓዳችን ተትረፍርፎ
ንዋይ ፣ ዝና ፣ ሀብት ፣ ስልጣን፤
ከባድ ቀንን ምናልፍበት
ቅንጥብጣቢ ፍቅር አጣን!።
@mikiyas_feyisa
አይጠፋሽም
ውስጥሽ ያውቃል፤
ችግር አቅፈን ምናድርበት
የስካሁኑ ጊዜ ይበቃል።
ምናድግበት ሚስጥር ታየኝ
ሰውነቴን ሀሴት ዋጠው፤
ግድ የለሽም ትንሽ ቆርሰን
ፍቅራችንን እንሽጠው!።
የሚገዛ ሀገር ሞልቷል..
ነጠላ ነው ሚገጥመኝ ሰው
ብቸኛ ነው የማየውም፤
የከተማው ባለትዳር
ገንዘብ እንጂ ፍቅር የለውም።
ያሳዝናል ቀዬው ብታይ
እስቲ ይቅመሰው የኛን መገን፤
ፍቅር እንደሆን ሞልቶን ተርፏል
ትንሽ ካሽ ነው ሚያስፈልገን።
እንዳትሰጊ ፡ አንዲት እንኳን
ይሄ ይሆናል የእግዜር ውጥን፤
አልኳትና በረብጣ ብር
ከኛ ሰፍረን ፍቅር ሸጥን!።
ከዛን..
ተመቻቸን
ህይወት ደላን
ገርበብ አለ የአይናችን ዘብ፤
"ያለፈው ዓለም አይገባው
ፍቅር ኖሮት ያጣ ገንዘብ።"
ብለን ሳቅን
ተቃቀፍን
ፍስሃችን ምድርን ሞላ፥
ዓለም ለኛ ገነት ሆነች
ምድር ሆነች የኛ ተድላ።
የመንደሩን አይን ገዛን
ታላቅ ታናሽ አከበረን ፤
ሁሉ ሞልቶን ተደላድሎ
ትንሽ ብቻ ፡ ገንዘብ ቀረን።
ሰልችቶናል ስናገኘው
አሸዋ ላይ መልክን መሳል፤
ለታደልነው ብዙ ምኞት
የነበረን ገንዘብ ያንሳል።
ሰማዩ ላይ ስናማትር፡
መርከቡ ላይ ስናማትር፡
ስናይ ውለን የባህሩን
ግራ የገባው ፡ ውዝዋዜ ፤
ቁጭ ስንል ሀሳብ መጣ
አለን ለካ ፡ ብዙ ጊዜ!።
ተነጋገርን
ተማከርን
ካረጀ ሀብታም አንጋጠጥን፤
ሻንጣ ሙሉ ገንዘብ ወስደን
ሽርፍራፊ ጊዜ ሸጥን!።
አቤት ሀሴት
አቤት ፌሽታ
ህዝቡ ባዶ ቅኔ ያምጣል፤
ገንዘብ ደስታ ባይገዛ እንኳን
እልፍ ደስታ ይዞ ይመጣል።
የሚያቆመን ፍጥረት ጠፋ
ፍስሃችን ምድርን ሞላ፥
ግን አሁንም አልተነሳም
የህዝባችን አይነ-ጥላ!።
ምናገባን እኛ ኖርን
እኛ ኖርን ምናገባን፤
ግን አንድ ሌት በህልማችን
ስልል ያለ ሀሳብ ገባን፦
"ፍቅራችንን ከላይ አይቶ
ይህን ፀጋ እርሱ ሰጠን፤
አንድ ወንበዴ ገፍቶ ቢዘርፍ
ምንድነው ግን የሚውጠን?"
ብለን አሰብን
ተብከነከን
ያ ደላላ ፡ መጣ ዳግም፤
ያገናኘን ፅኑ መድህን
ከፍቅር ውጪ አይፈልግም።
ተመካከርን .... በቃ ይሁን!
ይህ ይሆናል የእግዜር ውጥን፤
ብለን ትንሽ ፡ የማትጎዳ
በድጋሚ ፡ ፍቅር ሸጥን!።
እርሱ ይክበር
ሰላም ተኛን
ህልማችንን እርሱ ረዳ፤
የሚጣፍጥ ለሊት አድረን
ደግሞ ነቃን በማለዳ።
ግና...
የትላንቱ ህመም ቢሻር
ምቾት ዛሬን ቢንሰራፋም፦
እየሳቅን ውለን አድረን
የሚያውከን ነገ አይጠፋም።
ትንሽ ብለን ፦ ስንቀንስ
ጥቂት ብለን ስናወጣ፥
እለት በለት እ.የ.ባ.ሰ
ያልታሰበ ጉድ ሲመጣ፤
ትንሽ ፍቅር ፣ ትንሽ ጊዜ
ትንሽ .. ትንሽ "ትልቅ" ሆኖ ፤
ሳናስተውል ያለን ፍቅር
በየዳናው ተበትኖ ፤
ዝም ማለት ልማድ ሆነን
መቀላለድ ወዙ ጠፋን
ደስታችንን ለማስቀጠል
አንጀት ቋጥረን ብዙ ለፋን።
ግን አልሆነም ውጥናችን
ቅዠት ገዛን ተገላብጦ፤
ህይወታችን መንቀፍ ሆነ
ያንዱን ድክመት ብቻ መርጦ።
"አንተ እኮ ነህ እንዲህ ያልከኝ"
"አንቺ እኮ ነሽ እንዲ ያረግሽው"፥
"ከዚህ ኋላ ይሄ በቃኝ"
"የስካሁኑን ፍቅር እርሺው!"።
ተቃቃርን እንደ ሩቅ ሰው
ባላንጣ ሆንን በኛው ሜዳ
እንስፍስፉን አንጀት ጥለን
በአዳር ሆንን እንደ ባዳ።
አንገርምም?
ወዳጅ ዘመድ በርቱ ሲለን
ሲቀናብን የውጪ ሰው፤
ያቀፍነውን ጥሬ ገንዘብ
አይነተን ቆጥረን ሳንጨርሰው፥
ከጓዳችን ተትረፍርፎ
ንዋይ ፣ ዝና ፣ ሀብት ፣ ስልጣን፤
ከባድ ቀንን ምናልፍበት
ቅንጥብጣቢ ፍቅር አጣን!።
@mikiyas_feyisa
26.03.202513:12
ቀሽም አይደለሽ
እምላለው፡
በጉብዝናሽ ነው
ሽሬ የዳንኩት ፤
በጥንካሬ አይበልጡሽም
ለስላሳ ነበር የፈለኩት።
@mikiyas_feyisa
እምላለው፡
በጉብዝናሽ ነው
ሽሬ የዳንኩት ፤
በጥንካሬ አይበልጡሽም
ለስላሳ ነበር የፈለኩት።
@mikiyas_feyisa
18.03.202503:36
እኔ እና አንቺን ያጣመረን
ልባችንን ሊከፍል ወዷል፤
አብረን ሆነን ምንድንበት
የተሰጠን ጊዜ ሄዷል።
እንለያይ ሳይፈርድብን
ሳያነደን የሲዖል ፍም፤
መሳሙን ተይ ብቻ እንሩጥ
ካልፈጠንን አንደርስም።
ብያት ስሮጥ..
እሷም ስትሮጥ..
ሳያት ዞሬ
ስታይ ዞራ
ፍዝዝ አርጋው
የአይኗን ብሌን
የፍቅሯን ዳር ሙሾ እንዲዳኝ፤
እያየሁኋት እግሬ እምቢ አለ
ተመለስኩኝ አምላክ ይርዳኝ!።
በቃ አልፈራም
ከዚህ ኋላ
እንኳን እቶን ቢዘራ ደም፤
ደልቶኝ ይሁን እያየኋት
ከረፈደም .. ከፈረደም!
@mikiyas_feyisa
ልባችንን ሊከፍል ወዷል፤
አብረን ሆነን ምንድንበት
የተሰጠን ጊዜ ሄዷል።
እንለያይ ሳይፈርድብን
ሳያነደን የሲዖል ፍም፤
መሳሙን ተይ ብቻ እንሩጥ
ካልፈጠንን አንደርስም።
ብያት ስሮጥ..
እሷም ስትሮጥ..
ሳያት ዞሬ
ስታይ ዞራ
ፍዝዝ አርጋው
የአይኗን ብሌን
የፍቅሯን ዳር ሙሾ እንዲዳኝ፤
እያየሁኋት እግሬ እምቢ አለ
ተመለስኩኝ አምላክ ይርዳኝ!።
በቃ አልፈራም
ከዚህ ኋላ
እንኳን እቶን ቢዘራ ደም፤
ደልቶኝ ይሁን እያየኋት
ከረፈደም .. ከፈረደም!
@mikiyas_feyisa
无法访问
媒体内容
媒体内容
14.01.202504:37
28.04.202517:24
ሀሳብ እንዳይገባሽ
እንደ ባዕድ ቢያዩሽ
እንዳሳቀቂ፡
ተፈጥሮሽ ወገኑን
እስክናውቀው ድረስ
ያለ ገደብ ሳቂ።
ተይው የትም ይድረስ
ባሻው ተንፀባርቆ
አለምን ይጠቁም፥
እንኳን የሰው ልጆች
መላዕክትም እንኳ
ነገድሽን አያውቁም።
እንደሄደ አይቀርም
ተመልሶ ይመጣል
ይጠየቃል ሰሪው ፤
ግድየለም አይክፋሽ
እንከዛ ብቻ ነው ፡ የምትቸገሪው።
@mikiyas_feyisa
እንደ ባዕድ ቢያዩሽ
እንዳሳቀቂ፡
ተፈጥሮሽ ወገኑን
እስክናውቀው ድረስ
ያለ ገደብ ሳቂ።
ተይው የትም ይድረስ
ባሻው ተንፀባርቆ
አለምን ይጠቁም፥
እንኳን የሰው ልጆች
መላዕክትም እንኳ
ነገድሽን አያውቁም።
እንደሄደ አይቀርም
ተመልሶ ይመጣል
ይጠየቃል ሰሪው ፤
ግድየለም አይክፋሽ
እንከዛ ብቻ ነው ፡ የምትቸገሪው።
@mikiyas_feyisa


16.04.202508:57
06.04.202503:04
እንዳትረሺኝ!
'ከመሬት ሰው ቢትረፈረፍ
ደም ቢለብስም ሳር ቅጠሉ፥
ካለፈው ጣር ለማገገም
መርሳት ቢሆን ስኬት ድሉ
ማርትሬዛ ሀብል ሆኜ
ከአንገትሽ ላይ ባታስሪኝም
ጡትሽ መሃል ሸሽገሺኝ፤
እንዳትረሺኝ
ቢቋደሱት የአለምን ጣ'ም
ቢነቃቀል እሾህ አጋም
ጭፍግግ ያለው ሌሊት ገፎ
ተስፋ ያለው ጧት ቢነጋም፥
እኩለ ሌት ባደርንበት
ግርግዳ ላይ ለጥፈሺኝ
እንዳትረሺኝ!
እንዳረጀ ሸማ ፈትል
ቢደበዝዝ ትዝታዬ
ፀአዳ አለም ተሸፍኖኝ
እልም ቢሆን ገፅታዬ
ከልብሽ ላይ ባታንዣብብ
የመንፈሴ ልዝብ ልኳ
ሁሉም እዳው ገፈት ቢሆን
ጥጥ ሰማዩ ቢጠቁር እንኳ፤
ያደፈውን ሰማይ ቀደሽ
ከርሰ ምድር ሰነጣጥቀሽ
በሽንቁሩ እያየሺኝ
እንዳትረሺኝ!
ከሰው መንጋ ባይነጥለኝ
አመል ማይለቅ ያይንሽ ቀሽም
እንደ ራቁት የሰው ጠረን
ያሳለፍነው ቢጠፋሽም፥
እንዳልነበር
እንዳልኖረ ፦
እርሺኝና ፡ አለቅሽም!
@mikiyas_feyisa
'ከመሬት ሰው ቢትረፈረፍ
ደም ቢለብስም ሳር ቅጠሉ፥
ካለፈው ጣር ለማገገም
መርሳት ቢሆን ስኬት ድሉ
ማርትሬዛ ሀብል ሆኜ
ከአንገትሽ ላይ ባታስሪኝም
ጡትሽ መሃል ሸሽገሺኝ፤
እንዳትረሺኝ
ቢቋደሱት የአለምን ጣ'ም
ቢነቃቀል እሾህ አጋም
ጭፍግግ ያለው ሌሊት ገፎ
ተስፋ ያለው ጧት ቢነጋም፥
እኩለ ሌት ባደርንበት
ግርግዳ ላይ ለጥፈሺኝ
እንዳትረሺኝ!
እንዳረጀ ሸማ ፈትል
ቢደበዝዝ ትዝታዬ
ፀአዳ አለም ተሸፍኖኝ
እልም ቢሆን ገፅታዬ
ከልብሽ ላይ ባታንዣብብ
የመንፈሴ ልዝብ ልኳ
ሁሉም እዳው ገፈት ቢሆን
ጥጥ ሰማዩ ቢጠቁር እንኳ፤
ያደፈውን ሰማይ ቀደሽ
ከርሰ ምድር ሰነጣጥቀሽ
በሽንቁሩ እያየሺኝ
እንዳትረሺኝ!
ከሰው መንጋ ባይነጥለኝ
አመል ማይለቅ ያይንሽ ቀሽም
እንደ ራቁት የሰው ጠረን
ያሳለፍነው ቢጠፋሽም፥
እንዳልነበር
እንዳልኖረ ፦
እርሺኝና ፡ አለቅሽም!
@mikiyas_feyisa
23.03.202506:31
ቱ!
እኔን ብሎ ደግሞ
የሲግማ ህግ አውጪ
አሁን ልቤን አምጪ
ይኸው እጅና እግሬ
ከጠቀመሽ እንደው
ልቤ ነው ሚከብደው
ሚሆንብሽ ሸክም
ቀኔን በምን ላክም?
እኔን በምን ላክም?
ወይኔ ሲግማነቴ
ወይኔ ሲግማነቴ
ባልበሰለ ጀብዱ
ሰው ያጣውን ነፍሱን
በዲስኩር ሚያረካ
ቆንጆ ያጣ ወንድ እንጂ
ሲግማ የለም ለካ
ወይ ሲግማ : ተግማማ
ወይ ሲግማው : ተግማማው
አንድሪው ቴት በቃኝ
አንቺን ነው ምሰማው።
ከአለም ጥበብ ያልፋል
የተፈጥሮሽ ግጥም ፤
ቀነኒሳም ቢሆን
አንቺን ካየ አይሮጥም።
ሀይሌም በተአምር
ለሰው ብር ያድላል
ላርሰናል ዋንጫ ምን?
ዱባ ወጥ ይበላል።
ወይ መፈቀር እቴ
ድንቄም ቀልብን መጣል ፤
አንቺን ያየ ለታ
እንኳንስ ጃል መሮ
ጅብ ከጫካ ይወጣል።
ሳቂ ምናለብሽ
የኔ ነው ጥፋቱ
መንጌ ምናባቱ
መሌ ምናባቱ
ቀይ ሽብር ለመልክሽ
ኮማንዶ ለክብርሽ
ያውጅልሽ አድማ
የታባቱን ሲግማ!
ተይ አትሳቂብኝ
ተይ አትመሪብኝ
ፊትሽን እያየው
ያመልጠኛል ሳቄ ፤
ካንቺ ጋር ከሆነ
እንኳንና ህይወት ፡ ይረዝማል በውቄ።
ውይይ ተረዱኝ በቃ
ዓለም ሀቁን ይስማ፤
ፍፁም አለነበረም
ከኔ በላይ ሲግማ።
ግግር አለት ነበርኩ
ከስራ እና ከጂም
ውጪ የማልገኝ፤
እርሾ ውበቷ ነው
እንዲህ ሊጥ ያረገኝ።
ወይኔ ሲግማነቴ
ማርና ወተቴ
ወይኔ ሲግማነቴ
ማርና ወተቴ
"ጀንታላው ወንዳወንድ
የተሽቀረቀረ
እንደ ፖለቲካ
ተልከስክሶ ቀረ"
ይሉኛል ሰማለው
ያሙኛል ሰማለው
ሆኖም ተደፍቼ
አንቺን አልማለው
ምናገባኝ ግና
ምንያደርጉልኛል?
አንቺን ይሰጡኛል?
ሲያሻቸው ያምፁ
ያረጀ ሲግማነት
ማዕረጌን ይቀሙት፤
ብቻ ላንድ ጊዜ
ሳሚኝና ልሙት።
@mikiyas_feyisa
እኔን ብሎ ደግሞ
የሲግማ ህግ አውጪ
አሁን ልቤን አምጪ
ይኸው እጅና እግሬ
ከጠቀመሽ እንደው
ልቤ ነው ሚከብደው
ሚሆንብሽ ሸክም
ቀኔን በምን ላክም?
እኔን በምን ላክም?
ወይኔ ሲግማነቴ
ወይኔ ሲግማነቴ
ባልበሰለ ጀብዱ
ሰው ያጣውን ነፍሱን
በዲስኩር ሚያረካ
ቆንጆ ያጣ ወንድ እንጂ
ሲግማ የለም ለካ
ወይ ሲግማ : ተግማማ
ወይ ሲግማው : ተግማማው
አንድሪው ቴት በቃኝ
አንቺን ነው ምሰማው።
ከአለም ጥበብ ያልፋል
የተፈጥሮሽ ግጥም ፤
ቀነኒሳም ቢሆን
አንቺን ካየ አይሮጥም።
ሀይሌም በተአምር
ለሰው ብር ያድላል
ላርሰናል ዋንጫ ምን?
ዱባ ወጥ ይበላል።
ወይ መፈቀር እቴ
ድንቄም ቀልብን መጣል ፤
አንቺን ያየ ለታ
እንኳንስ ጃል መሮ
ጅብ ከጫካ ይወጣል።
ሳቂ ምናለብሽ
የኔ ነው ጥፋቱ
መንጌ ምናባቱ
መሌ ምናባቱ
ቀይ ሽብር ለመልክሽ
ኮማንዶ ለክብርሽ
ያውጅልሽ አድማ
የታባቱን ሲግማ!
ተይ አትሳቂብኝ
ተይ አትመሪብኝ
ፊትሽን እያየው
ያመልጠኛል ሳቄ ፤
ካንቺ ጋር ከሆነ
እንኳንና ህይወት ፡ ይረዝማል በውቄ።
ውይይ ተረዱኝ በቃ
ዓለም ሀቁን ይስማ፤
ፍፁም አለነበረም
ከኔ በላይ ሲግማ።
ግግር አለት ነበርኩ
ከስራ እና ከጂም
ውጪ የማልገኝ፤
እርሾ ውበቷ ነው
እንዲህ ሊጥ ያረገኝ።
ወይኔ ሲግማነቴ
ማርና ወተቴ
ወይኔ ሲግማነቴ
ማርና ወተቴ
"ጀንታላው ወንዳወንድ
የተሽቀረቀረ
እንደ ፖለቲካ
ተልከስክሶ ቀረ"
ይሉኛል ሰማለው
ያሙኛል ሰማለው
ሆኖም ተደፍቼ
አንቺን አልማለው
ምናገባኝ ግና
ምንያደርጉልኛል?
አንቺን ይሰጡኛል?
ሲያሻቸው ያምፁ
ያረጀ ሲግማነት
ማዕረጌን ይቀሙት፤
ብቻ ላንድ ጊዜ
ሳሚኝና ልሙት።
@mikiyas_feyisa
14.03.202520:15
~
ፍቅርን በቃላት መግለጽ አልችልም። ትልቁ ችግሬ ነው። እርሷ ደግሞ ትልቁ ችግሯ ፤ አትረዳኝም!። እንዴት አብሪያት እየኖርኩኝ በየቀኑ ማለዳ ስነሳ እንደምወዳት ልነግራት እችላለው?። እራሴን እንኳን የምረሳ ሰውዬ እንዴት የርሷን በየሰከንዱ የሚቀያየር ባህሪ ላውቅ እችላለው።
“ቆይ አንተ ችግርህ ምንድነው?” ትላለች ከመሬት ተነስታ።
“ምናጠፋው ?”
“ለምንድነው ቅድም ሰዎች ፊት ያላቀፍከኝ?”
“ለምን አቅፍሻለው?”
“ባለቤቴ ስለሆንክ ነዋ”
“እና ሁሉም ሰው ያውቅ አይደል እንዴ”
“ቢሆንም እንደሰው በሰው ፊት ልትንከባከበኝ ይገባል”
“ያንቺው ጓደኞች እኮ ናቸው ቤብ ። ድራማ መስራት አያስፈልግም ብዬ ነው።”
“እንደውም እነሱ ፊት ነው እንድታቅፈኝ የምፈልገው።”
“እሺ ይቅርታ የኔ ውድ.. እኔ ትዝም አላለኝም።” ብዬ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ሰባ ምናምነኛ ጊዜ ይቅርታ እጠይቃለው። አየር ሰብስቤ ወደ ስራ ልገባ ስል እየተንከወከወች በድጋሚ ትመጣለች።
“ኧ ቤብ ይሄ ቲሸርቲ ከዚህ ቀሚስ ጋር አይሄድም አይደል?” ትለኛለች። ምላሹን አላውቅም። በዚህም ሆነ በዛ መናደዷ ስለማይቀር የተሰማኝን ልናገር እልና...
“ብዙም አይደለም። ከክሬም ከለሩ ሸሚዝ ጋር ብትለሺው ያምራል።”
“ነው አይደል? .. እሱ እኮ ግን ሰሞኑን ትንሽ ስለወፈርኩ ሳይዘኝ አይቀርም።”
“በቃ ይሄ እንደዚው ያምራል እኮ የኔ ውድ”
"አንተ ግን ወይኔ ውፍረቴ ያስታውቃል አይደል?"
"ኧረ በፍፁም! .. እንደውም ሸንቀጥ ብለሺብኛል እኮ"
“አትዋሸኝ ባክህ ያስታውቅብሃል።”
“እሺ ምን እንድልሽ ነው ምትፈልጊው?"
"ምንም .. ለምንድነው ግን ባል መሆን የሚያቅትህ ቆይ"
"እስቲ አንዴ ተንፈስ በይ ቤብ .. ተጨንቀሽ አስጨነቅሺኝ እኮ"
እየተንቀዠቀዠቾ በሩን በሀይል ዘግታው ወጣች። እሺ አሁን ምን እንድላት ነው የፈለገችው?። ያምራል ኩርፊያ አልወፈርሽም ግልምጫ ኤጭ አሁንስ።
ለማንኛውም እንደምንም መሸላትና ወደ 1:00 አከባቢ ላይ ለአንድ አርቴፊሻል ጓደኛዋ አሳሩን በልቶ propose የሚያደርግላት ባሏን(ገና አልሆነም) ለማጀብ ሄድን። እንደ ድራማቸው ከሆነ ጓደኛዋ ምንም አታውቅም። ፅድት ያል የእራት ቀሚስ ስትገዛም ሆነ ከሩቅ መነፅር የሚያስወልቅ ሜካፕ ተሰርታ ስትመጣም ምንም የምታውቀው ነገር የለም። እስቲ ይሁንላቸው እኔ ምን አገባኝ። ዋናው ደስተኛ መሆናቸው ነው። ብቻ እዛ ቦታ ላይ እስከምደርስ ድረስ የመጣውበት ምክንያት አልገባኝም ነበር። ከሬስቶራንቱ ስንደርስ ሌሎች ቁሌታም ጓደኞቿ ከእርጉዝ(ማለቴ ቦርጫም) ባሎቻቸው ጋር ከበው ቁጭ ብለዋል። ከመቼው እጇን እጄ ውስጥ እንደጠመጠመችው አላውቅም ፤ ዞር ስል እንደ አራስ ጥብቅ ብላብኝ ነው ያገኘኋት። አንድ የምትፈልገው ነገር ቢኖር እነዚህ ቅንቅናም፣ ቁሌታም ጓደኞቿ ፊት እነርሱ ያላገኙትን የንግስት እንክብካቤ እንዳደርግላት ነው። (AKA እንዲቀኑባት)። እርሷን በብዙ ነገር ሳያስቀኗት እንዳልቀሩ እገምታለው። "እንደ ሀሳብሽ ይሁን" አልኩና በሆዴ በወጉ ያልተፈታ የሂል ጫማዋን ማስያዣ በርከክ ብዬ ጠበቅ አደረኩት። አቋቋማ የአለማት ንጉስ ሰግዶ እሺታዋን እየለመናት ነው የሚመስለው። የፀጉሯን ጉንጉን ወደጆሮዋ እያሾለከች ፈገግ ትላለች። እኔ እራሱ ቀናሁባት። እንደ ንጉሳውያን ቤተሰብ በጣም ረጋ ባለ እርምጃ ወደነሱ ደረስን።ሻሩክ ምናባቱ የሚባል ህንድ ፊልም እየሰራን ያለን ነው የሚመስለው። ወንበሯን ስቤ ከማስቀመጤ በፊት ቁልፉን እየፈታች የነበረውን ሌዘር ጃኬቷን ተቀብዬ የወንበሯ መደገፊያ ላይ አስቀመጥኩት። በዚህ መሃል ግን ፊቷ ላይ ትንሽዬ እንኳን ፈገግታ አላየውም። ልክ ሁሌ እንደዚህ አይነት እንክብካቤ እንደማደርግላት ነው አካኋኗ። ይመቻት።
የዛን ምሽት ያ ምስኪን ከርፋፋ ተንበርክኮ መጀመሪያም ያልተከለከለውን ጠይቆ በደነገጠ አኳኋን እሺ ተብሎ ፣ ጨፍረው ተሳስመው ፣ በልተን ፣ ጠጥተን እስከምንሄድ ድረስ ያላደረኩላት ነገር አልነበረም። ወደ ፕሮግራሙ መጨረሻ አከባቢ ሞቅ ሊላት ሲፈልግ ግንባሯ ላይ ያቸፈቸፈችው ላብ እንኳን ጠብ አላለችም። እንዴት ደስተኛ እንደነበረች እና ምን ያህል ኩራት እንደተሰማት ውስጤ calculate አድርጎ ነግኖኛል። "ድርሻዬን በአግባቡ ተወጥቻለው ንግስቲቷ" አልኩ በሆዴ። በስተመጨረሻም ኘሮግራሙ አለቀልኝና ጨርሰን፣ ተሰናብተን ወደጠራነው ራይድ መሄድ ጀመርን። ፊቷ ላይ የረበበው ፈገግታ መጠን አልነበረውም። ልክ ከሬስቶራንቱ በር እንዳለፍን ግን ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ተቀያየረ። ሬት የጠጣች ነው የምትመስለው።
"ምንሆንሽ?" አልኩ በመደናገጥ አይነት።
"ወይኔ መዋረድ .. ወይኔ መዋረድ" እጇን ጭንቅላቷ ላይ አደረገች። ይበልጥ ግራ ገባኝ።
"ምን አደረኩኝ ደግሞ?"
"ምን እየሆንክ ነበር የነበረው?"
"ንግስቴን እየተንከባከብኩ ነዋ"
"ያ እኮ መንከባከብ አይደለም። ስልምልም እኮ ነው ያልከው። እንዴት ስኮሳተር እንኳን አይገባህም።"
"ይሄን አይደለም እንዴ ምትፈልጊው?"
"ይሄ እኮ ወንዳወንድነት የለውም። ባሌ እኮ ነህ። ሰው ፊት ቆፍጠን ብለህ እንድትታይ ነው የምፈልገው። ጭራሽ ከቦርሳዬ ሶፍት ታቀብለኛለህ?" እየተወራጨች ወደመኪናው ገባች። በዚህ ሰዓት ምን ማለት እንዳለብኝ ምንም አላውቅም። ለነገሩ ግን እኔም ትንሽ ሳላበዛው አልቀርም። ቢሆንም ግን እኮ ተንከባክቢያታለው። ሲጀመር እራሷ አይደለች እንዴ ጎትታ ያመጣቺኝ። የራሷ ጉዳይ።
@mikiyas_feyisa
ፍቅርን በቃላት መግለጽ አልችልም። ትልቁ ችግሬ ነው። እርሷ ደግሞ ትልቁ ችግሯ ፤ አትረዳኝም!። እንዴት አብሪያት እየኖርኩኝ በየቀኑ ማለዳ ስነሳ እንደምወዳት ልነግራት እችላለው?። እራሴን እንኳን የምረሳ ሰውዬ እንዴት የርሷን በየሰከንዱ የሚቀያየር ባህሪ ላውቅ እችላለው።
“ቆይ አንተ ችግርህ ምንድነው?” ትላለች ከመሬት ተነስታ።
“ምናጠፋው ?”
“ለምንድነው ቅድም ሰዎች ፊት ያላቀፍከኝ?”
“ለምን አቅፍሻለው?”
“ባለቤቴ ስለሆንክ ነዋ”
“እና ሁሉም ሰው ያውቅ አይደል እንዴ”
“ቢሆንም እንደሰው በሰው ፊት ልትንከባከበኝ ይገባል”
“ያንቺው ጓደኞች እኮ ናቸው ቤብ ። ድራማ መስራት አያስፈልግም ብዬ ነው።”
“እንደውም እነሱ ፊት ነው እንድታቅፈኝ የምፈልገው።”
“እሺ ይቅርታ የኔ ውድ.. እኔ ትዝም አላለኝም።” ብዬ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ሰባ ምናምነኛ ጊዜ ይቅርታ እጠይቃለው። አየር ሰብስቤ ወደ ስራ ልገባ ስል እየተንከወከወች በድጋሚ ትመጣለች።
“ኧ ቤብ ይሄ ቲሸርቲ ከዚህ ቀሚስ ጋር አይሄድም አይደል?” ትለኛለች። ምላሹን አላውቅም። በዚህም ሆነ በዛ መናደዷ ስለማይቀር የተሰማኝን ልናገር እልና...
“ብዙም አይደለም። ከክሬም ከለሩ ሸሚዝ ጋር ብትለሺው ያምራል።”
“ነው አይደል? .. እሱ እኮ ግን ሰሞኑን ትንሽ ስለወፈርኩ ሳይዘኝ አይቀርም።”
“በቃ ይሄ እንደዚው ያምራል እኮ የኔ ውድ”
"አንተ ግን ወይኔ ውፍረቴ ያስታውቃል አይደል?"
"ኧረ በፍፁም! .. እንደውም ሸንቀጥ ብለሺብኛል እኮ"
“አትዋሸኝ ባክህ ያስታውቅብሃል።”
“እሺ ምን እንድልሽ ነው ምትፈልጊው?"
"ምንም .. ለምንድነው ግን ባል መሆን የሚያቅትህ ቆይ"
"እስቲ አንዴ ተንፈስ በይ ቤብ .. ተጨንቀሽ አስጨነቅሺኝ እኮ"
እየተንቀዠቀዠቾ በሩን በሀይል ዘግታው ወጣች። እሺ አሁን ምን እንድላት ነው የፈለገችው?። ያምራል ኩርፊያ አልወፈርሽም ግልምጫ ኤጭ አሁንስ።
ለማንኛውም እንደምንም መሸላትና ወደ 1:00 አከባቢ ላይ ለአንድ አርቴፊሻል ጓደኛዋ አሳሩን በልቶ propose የሚያደርግላት ባሏን(ገና አልሆነም) ለማጀብ ሄድን። እንደ ድራማቸው ከሆነ ጓደኛዋ ምንም አታውቅም። ፅድት ያል የእራት ቀሚስ ስትገዛም ሆነ ከሩቅ መነፅር የሚያስወልቅ ሜካፕ ተሰርታ ስትመጣም ምንም የምታውቀው ነገር የለም። እስቲ ይሁንላቸው እኔ ምን አገባኝ። ዋናው ደስተኛ መሆናቸው ነው። ብቻ እዛ ቦታ ላይ እስከምደርስ ድረስ የመጣውበት ምክንያት አልገባኝም ነበር። ከሬስቶራንቱ ስንደርስ ሌሎች ቁሌታም ጓደኞቿ ከእርጉዝ(ማለቴ ቦርጫም) ባሎቻቸው ጋር ከበው ቁጭ ብለዋል። ከመቼው እጇን እጄ ውስጥ እንደጠመጠመችው አላውቅም ፤ ዞር ስል እንደ አራስ ጥብቅ ብላብኝ ነው ያገኘኋት። አንድ የምትፈልገው ነገር ቢኖር እነዚህ ቅንቅናም፣ ቁሌታም ጓደኞቿ ፊት እነርሱ ያላገኙትን የንግስት እንክብካቤ እንዳደርግላት ነው። (AKA እንዲቀኑባት)። እርሷን በብዙ ነገር ሳያስቀኗት እንዳልቀሩ እገምታለው። "እንደ ሀሳብሽ ይሁን" አልኩና በሆዴ በወጉ ያልተፈታ የሂል ጫማዋን ማስያዣ በርከክ ብዬ ጠበቅ አደረኩት። አቋቋማ የአለማት ንጉስ ሰግዶ እሺታዋን እየለመናት ነው የሚመስለው። የፀጉሯን ጉንጉን ወደጆሮዋ እያሾለከች ፈገግ ትላለች። እኔ እራሱ ቀናሁባት። እንደ ንጉሳውያን ቤተሰብ በጣም ረጋ ባለ እርምጃ ወደነሱ ደረስን።ሻሩክ ምናባቱ የሚባል ህንድ ፊልም እየሰራን ያለን ነው የሚመስለው። ወንበሯን ስቤ ከማስቀመጤ በፊት ቁልፉን እየፈታች የነበረውን ሌዘር ጃኬቷን ተቀብዬ የወንበሯ መደገፊያ ላይ አስቀመጥኩት። በዚህ መሃል ግን ፊቷ ላይ ትንሽዬ እንኳን ፈገግታ አላየውም። ልክ ሁሌ እንደዚህ አይነት እንክብካቤ እንደማደርግላት ነው አካኋኗ። ይመቻት።
የዛን ምሽት ያ ምስኪን ከርፋፋ ተንበርክኮ መጀመሪያም ያልተከለከለውን ጠይቆ በደነገጠ አኳኋን እሺ ተብሎ ፣ ጨፍረው ተሳስመው ፣ በልተን ፣ ጠጥተን እስከምንሄድ ድረስ ያላደረኩላት ነገር አልነበረም። ወደ ፕሮግራሙ መጨረሻ አከባቢ ሞቅ ሊላት ሲፈልግ ግንባሯ ላይ ያቸፈቸፈችው ላብ እንኳን ጠብ አላለችም። እንዴት ደስተኛ እንደነበረች እና ምን ያህል ኩራት እንደተሰማት ውስጤ calculate አድርጎ ነግኖኛል። "ድርሻዬን በአግባቡ ተወጥቻለው ንግስቲቷ" አልኩ በሆዴ። በስተመጨረሻም ኘሮግራሙ አለቀልኝና ጨርሰን፣ ተሰናብተን ወደጠራነው ራይድ መሄድ ጀመርን። ፊቷ ላይ የረበበው ፈገግታ መጠን አልነበረውም። ልክ ከሬስቶራንቱ በር እንዳለፍን ግን ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ተቀያየረ። ሬት የጠጣች ነው የምትመስለው።
"ምንሆንሽ?" አልኩ በመደናገጥ አይነት።
"ወይኔ መዋረድ .. ወይኔ መዋረድ" እጇን ጭንቅላቷ ላይ አደረገች። ይበልጥ ግራ ገባኝ።
"ምን አደረኩኝ ደግሞ?"
"ምን እየሆንክ ነበር የነበረው?"
"ንግስቴን እየተንከባከብኩ ነዋ"
"ያ እኮ መንከባከብ አይደለም። ስልምልም እኮ ነው ያልከው። እንዴት ስኮሳተር እንኳን አይገባህም።"
"ይሄን አይደለም እንዴ ምትፈልጊው?"
"ይሄ እኮ ወንዳወንድነት የለውም። ባሌ እኮ ነህ። ሰው ፊት ቆፍጠን ብለህ እንድትታይ ነው የምፈልገው። ጭራሽ ከቦርሳዬ ሶፍት ታቀብለኛለህ?" እየተወራጨች ወደመኪናው ገባች። በዚህ ሰዓት ምን ማለት እንዳለብኝ ምንም አላውቅም። ለነገሩ ግን እኔም ትንሽ ሳላበዛው አልቀርም። ቢሆንም ግን እኮ ተንከባክቢያታለው። ሲጀመር እራሷ አይደለች እንዴ ጎትታ ያመጣቺኝ። የራሷ ጉዳይ።
@mikiyas_feyisa
10.01.202517:36
ማህሌት ስር ቅዳሴ ላይ
ሌላ ቦታ አታነጊም
ቤተ መቅደስ የእግዜር ብቻ
የሰው መሆን አትፈልጊም
አላገኘሽ አንድም እንኳን
ለባህሪሽ ሚሆን አቻ
አዚያዚያሙ የሚገዛሽ
የደብርሽ ዲያቆን ብቻ
እምነት ሰቶሽ በስልጣኑ
በልብሽ ላይ አሳትሞ
ሲያስቀና ክርስትናሽ
እኔን ብሎ አማኝ ደግሞ
እንደ ሴቱ አትታበይ
ተኳኩለሽ አትታዪው
ተንበርክከሽ እያነባሽ
ለማን ነበር ምትጸልዪው?
የደብርሽ ዛፍ እርግቦች
እንደ እህት ነው የለመዱሽ
ታውቂዋለሽ መምሬ እንኳን
እንደ ልጅ ነው የሚወዱሽ
ሁሉም ሴቶች አስመሳዮች
እሁድ ጠዋት መንፈሳዊ
የሰማዩን አባት ምህረት
እያሰቡት በሰዋዊ
በንግስ እለት ወለም ዘለም
በቁልምጫ ለማወደስ
የማታዋን አትመስልም
ጠዋት ማያት ቤተ መቅደስ
የነጠላ ፋሽን እንጂ
የሚፀልይ የለም የምር
እስከዛሬ ካየኋቸው
ክርስትና ባንቺ ሲያምር
በየት በኩል አበጀሽው
የእሳቱን መግቻ ልጓም
ማይመለስ ወጣትነት
ብልጭልጩ አያጓጓም?
እርጋታሽ ነው ቅጥረ ሰላም
ትህትናሽ የተስፋ በር
ሳታጠፊ ተንበርክከሽ
ምትጸልዪው ለማን ነበር?
@mikiyas_feyisa
ሌላ ቦታ አታነጊም
ቤተ መቅደስ የእግዜር ብቻ
የሰው መሆን አትፈልጊም
አላገኘሽ አንድም እንኳን
ለባህሪሽ ሚሆን አቻ
አዚያዚያሙ የሚገዛሽ
የደብርሽ ዲያቆን ብቻ
እምነት ሰቶሽ በስልጣኑ
በልብሽ ላይ አሳትሞ
ሲያስቀና ክርስትናሽ
እኔን ብሎ አማኝ ደግሞ
እንደ ሴቱ አትታበይ
ተኳኩለሽ አትታዪው
ተንበርክከሽ እያነባሽ
ለማን ነበር ምትጸልዪው?
የደብርሽ ዛፍ እርግቦች
እንደ እህት ነው የለመዱሽ
ታውቂዋለሽ መምሬ እንኳን
እንደ ልጅ ነው የሚወዱሽ
ሁሉም ሴቶች አስመሳዮች
እሁድ ጠዋት መንፈሳዊ
የሰማዩን አባት ምህረት
እያሰቡት በሰዋዊ
በንግስ እለት ወለም ዘለም
በቁልምጫ ለማወደስ
የማታዋን አትመስልም
ጠዋት ማያት ቤተ መቅደስ
የነጠላ ፋሽን እንጂ
የሚፀልይ የለም የምር
እስከዛሬ ካየኋቸው
ክርስትና ባንቺ ሲያምር
በየት በኩል አበጀሽው
የእሳቱን መግቻ ልጓም
ማይመለስ ወጣትነት
ብልጭልጩ አያጓጓም?
እርጋታሽ ነው ቅጥረ ሰላም
ትህትናሽ የተስፋ በር
ሳታጠፊ ተንበርክከሽ
ምትጸልዪው ለማን ነበር?
@mikiyas_feyisa
21.04.202518:49
ሙቅ ወንበር የተውንላቸው
ውለው አድረው መቆሚያ ነሱን
አክብረን ዝቅ ያልንላቸው
በሰው ፊት አስተናነሱን ።
በፍቅር ያጎረስናቸው
በእጅ አዙር አስቦጠቦጡን
ጠበል ውስጥ አጥበን አንፅተን
እቶን ላይ አገላበጡን።
ስንለካ እየቀነሱ
ስናቆም እያፈረሱ
ተምረው ላይለወጡ
ተዘክረው ላይለወጡ
ጭላንጭል ትዕግስታችንን
እንደ ሰም እያቀለጡ፦
ሲዘልፉን እጅ እየነሳን
ሲጥሉን እየተነሳን
ለጥፊ ፊት እየቀየርን
ብንመስል የአርብ ለት በጉን
አሻጥር የማይገባቸው
ያልነቃ ፋራ አደረጉን።
ድሮውም ወጉ እንዲያው ነው
ድሮውም ሀቁ እንዲያው ነው
እኛ ነን ቅሪል ቡቱቶ፤
ለጋ አይብ አይጠበቅም
ለህፃን ልጅ ወተት ተሰጥቶ።
@mikiyas_feyisa
ውለው አድረው መቆሚያ ነሱን
አክብረን ዝቅ ያልንላቸው
በሰው ፊት አስተናነሱን ።
በፍቅር ያጎረስናቸው
በእጅ አዙር አስቦጠቦጡን
ጠበል ውስጥ አጥበን አንፅተን
እቶን ላይ አገላበጡን።
ስንለካ እየቀነሱ
ስናቆም እያፈረሱ
ተምረው ላይለወጡ
ተዘክረው ላይለወጡ
ጭላንጭል ትዕግስታችንን
እንደ ሰም እያቀለጡ፦
ሲዘልፉን እጅ እየነሳን
ሲጥሉን እየተነሳን
ለጥፊ ፊት እየቀየርን
ብንመስል የአርብ ለት በጉን
አሻጥር የማይገባቸው
ያልነቃ ፋራ አደረጉን።
ድሮውም ወጉ እንዲያው ነው
ድሮውም ሀቁ እንዲያው ነው
እኛ ነን ቅሪል ቡቱቶ፤
ለጋ አይብ አይጠበቅም
ለህፃን ልጅ ወተት ተሰጥቶ።
@mikiyas_feyisa
14.04.202517:19
ሰው ፍቅርን በክፉ ያነሳል
ሰው ፍቅርን በግፉ ያነሳል
ቆይ ግን ሰው ፡ ወዶ ይከሳል?
ተጓዳኝ ድውይ ተጣብቆት
ውጭ ውስጡን ካላነደደ ፥
ሰው እንዴት ወዙ ቡን ይላል
ሌላ ሰው ፡ ስለወደደ?
እንጃ ግን የኔ ረሃ ነው
በምቾት ያደነዝዛል፥
ቀን በቀን ፍቅሬ ሲጨምር
እንደ ስልብ ፊቴም ይወዛል።
እንጃልኝ ጥጋብ ነው መሰል
ሚያፋፋኝ የልቤ ላይ ጥም፥
ሰው ሳልወድ የነበረኝ ሳቅ
ሳፈቅርም አይለወጥም!።
@mikiyas_feyisa
ሰው ፍቅርን በግፉ ያነሳል
ቆይ ግን ሰው ፡ ወዶ ይከሳል?
ተጓዳኝ ድውይ ተጣብቆት
ውጭ ውስጡን ካላነደደ ፥
ሰው እንዴት ወዙ ቡን ይላል
ሌላ ሰው ፡ ስለወደደ?
እንጃ ግን የኔ ረሃ ነው
በምቾት ያደነዝዛል፥
ቀን በቀን ፍቅሬ ሲጨምር
እንደ ስልብ ፊቴም ይወዛል።
እንጃልኝ ጥጋብ ነው መሰል
ሚያፋፋኝ የልቤ ላይ ጥም፥
ሰው ሳልወድ የነበረኝ ሳቅ
ሳፈቅርም አይለወጥም!።
@mikiyas_feyisa
04.04.202519:15
፨
ልሻር እንጂ ላንዴ
ከሚለበልበኝ ፡ ስውር የጣር ስቃይ፥
ይክሰምልኝ እንጂ
ስራስሩ ያነቀኝ
የመከዳት ብቃይ ፤
ብሞትም ጨክኜ
በምሬት ተግቼው ሀቁን እንደ ኮሶ፤
አንደው ልዳን እንጂ
እህህ ያስባለኝን
ህመሜን ጨርሶ ፦
..
ብቻ ልትረፍ እንጂ
ቤትም ተፍጨርጭሬ
ባለኝ ቁንፅል አቅም ፤
"ሴት" የሚባል ፍጡር
በጥርሴም ፡ አለቅም!።
@mikiyas_feyisa
ልሻር እንጂ ላንዴ
ከሚለበልበኝ ፡ ስውር የጣር ስቃይ፥
ይክሰምልኝ እንጂ
ስራስሩ ያነቀኝ
የመከዳት ብቃይ ፤
ብሞትም ጨክኜ
በምሬት ተግቼው ሀቁን እንደ ኮሶ፤
አንደው ልዳን እንጂ
እህህ ያስባለኝን
ህመሜን ጨርሶ ፦
..
ብቻ ልትረፍ እንጂ
ቤትም ተፍጨርጭሬ
ባለኝ ቁንፅል አቅም ፤
"ሴት" የሚባል ፍጡር
በጥርሴም ፡ አለቅም!።
@mikiyas_feyisa
20.03.202512:36
አፈቅርሻለሁኝ
አልወድሽም ግና
ፀሀይ ቪዛ አወጣች
ጨፈረች ደመና
ሰው ነበርኩኝ ድመት
በደረቱ ሚሳብ እንዳሳነባሪ
ሞተሻል አውቃለው
የሰርግሽን ለቅሶ
ነገረኝ ፈጣሪ
አምሮብሻል ደግሞ
ወዝሽም ገርጥቷል፤
አጎትሽ ጋሽ ዳምጤ
ወንድ ልጅ ሞቶበት
መታወቂያ አውጥቷል።
ምናገባኝ እኔ ..
እራሴን መች ላጥፋ?
መቼም ተስፋ አልቆርጥም ፤
ይቅር በዪኝ በቃ
አለቀብኝ ግጥም።😂
@mikiyas_feyisa
አልወድሽም ግና
ፀሀይ ቪዛ አወጣች
ጨፈረች ደመና
ሰው ነበርኩኝ ድመት
በደረቱ ሚሳብ እንዳሳነባሪ
ሞተሻል አውቃለው
የሰርግሽን ለቅሶ
ነገረኝ ፈጣሪ
አምሮብሻል ደግሞ
ወዝሽም ገርጥቷል፤
አጎትሽ ጋሽ ዳምጤ
ወንድ ልጅ ሞቶበት
መታወቂያ አውጥቷል።
ምናገባኝ እኔ ..
እራሴን መች ላጥፋ?
መቼም ተስፋ አልቆርጥም ፤
ይቅር በዪኝ በቃ
አለቀብኝ ግጥም።😂
@mikiyas_feyisa
09.03.202509:28
የሚበድላት ሰው
ይሰብካታል ቆሞ ፤
አንቅሮ የሚተፋት ፡ ያነሳታል ስሞ።
አጥንቷን ሚሰብራት ፡ እስክትቆም ይጓጓል፤
ሲያሰተምራት ውሎ ፡ ሲመኛት ያነጋል!።
የትኛውን ትመን?
መሸሸጊያ ያለችው
ውስጡ ይኮሰኩሳል፥
ስትወድቅ የደገፋት ፡ ከጣላት ይብሳል።
በፈሪ ይፈነጫል ፡ የታደለው አቅም፥
ያከበረችው ሰው ፡ ክብሩን አይጠብቅም።
ለርሷ ታሪክ ሲሆን ፡ ምሁር ያበዛል ዝም፤
ሽበት ያለው እንኳን ፡ በደል አያወግዝም!
ሁሉም ተደራጅቷል
ህሊናውን አቷል
ስሜት አይገባውም፥
ሰቆቃ አይገባውም ፡ የሴት"ወየው ወየው"፤
የናቀውን እምባ ፡ በልጁ እስካላየው!።
@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa
ይሰብካታል ቆሞ ፤
አንቅሮ የሚተፋት ፡ ያነሳታል ስሞ።
አጥንቷን ሚሰብራት ፡ እስክትቆም ይጓጓል፤
ሲያሰተምራት ውሎ ፡ ሲመኛት ያነጋል!።
የትኛውን ትመን?
መሸሸጊያ ያለችው
ውስጡ ይኮሰኩሳል፥
ስትወድቅ የደገፋት ፡ ከጣላት ይብሳል።
በፈሪ ይፈነጫል ፡ የታደለው አቅም፥
ያከበረችው ሰው ፡ ክብሩን አይጠብቅም።
ለርሷ ታሪክ ሲሆን ፡ ምሁር ያበዛል ዝም፤
ሽበት ያለው እንኳን ፡ በደል አያወግዝም!
ሁሉም ተደራጅቷል
ህሊናውን አቷል
ስሜት አይገባውም፥
ሰቆቃ አይገባውም ፡ የሴት"ወየው ወየው"፤
የናቀውን እምባ ፡ በልጁ እስካላየው!።
@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa
02.01.202506:19
ፍልቅልቅ ሳቋን ሚገድል
ገሃዱን እየከለለ
ጉድፏን መርጦ ሚነግራት
በውስጧ አንድ አካል አለ
"ሰው ለምን ቀርቦሽ ይርቃል
ከልብሽ እንዳለበት ቂም
እውነቱን አምነሽ ተቀበይ
ለመውደድ ለፍቅር አትበቂም
እስቲ እዪ ጓደኞችሽን
ሰው አለ በሄዱበት ሁሉ
አንቺ ጋር ለአፍታ ተቀምጠው
በስንት አይን ይለመናሉ
አንቺ ግን ሁሉም ሚርቅሽ
በምክንያት በቃል ደልሎ
ሚወደድ አንድም የሌለሽ
ፀባይሽ መልክሽ ጎዶሎ
ባጣ ቆዪ ነሽ ለሁሉም
ለምርጫ አንዴም ማትበቂ
አዳርሰው እስከሚመጡ
እየሳቅሽ የምጠብቂ
ሞኝ ነሽ ምስኪን ከርፋፋ
ያልቀመስሽ አንዲት ከአለም
ሚያስቀና ትዝታ የሌለሽ
ብቸኛ ኦና ዘላለም "
የሚላት አንድ አካል አለ
ህሊና ስሯን ተጣብቆ
በቁስሏ ጦርን የሚሰድ
ፍርሃቷን ጭንቋን ሁሉ አውቆ
አንድ አለ የምታምነው ድምጽ
ሚወስን የሀሳቧን እድል
ባዶ ነሽ ኢምንት እያለ
ተስፋዋን ልቧን ሚገድል
አንድ አለ ሚያንገበግበኝ
እንደ ልጅ ስቤ ማልቀጣው
ያረጀ ያፈጀ እምነት
ከውስጧ የማላወጣው
አንድ አለ የውሸት መዝገብ
ላይሻር ከልቧ የፀና
እንዳታምን የሚከልላት
ልነግራት እሞክርና
ምን ያህል እንደሚወረኝ
ከጀርባ ሆና ስታቅፈኝ
እንኳን ሳቅ ድርብርብ ጥርሷ
ምራቋም እንደማይቀፈኝ
ልነግራት እሞክርና
ሰው መውደድ ትህትናዋ
ከሁሉም ልብ እንደሚቀር
ቀልቃላ የህፃን ፀባዩዋ
ምን ያህል እንደሚፈቀር
ልነግራት እሞክርና
በዜማ እንደሚሰማ
የወጣ ከእርሷ አንደበት
ከጥፍሯ እስከ ጠጉሯ
የሚጣል እንደሌለበት
ልነግራት እሞክርና
ላስረዳት እፈልግና
መደበቅ ማፈን ሲጨንቀኝ
ፈራለው "ውሸታም" ብላ
እኔንም እንዳትርቀኝ።
@mikiyas_feyisa
ገሃዱን እየከለለ
ጉድፏን መርጦ ሚነግራት
በውስጧ አንድ አካል አለ
"ሰው ለምን ቀርቦሽ ይርቃል
ከልብሽ እንዳለበት ቂም
እውነቱን አምነሽ ተቀበይ
ለመውደድ ለፍቅር አትበቂም
እስቲ እዪ ጓደኞችሽን
ሰው አለ በሄዱበት ሁሉ
አንቺ ጋር ለአፍታ ተቀምጠው
በስንት አይን ይለመናሉ
አንቺ ግን ሁሉም ሚርቅሽ
በምክንያት በቃል ደልሎ
ሚወደድ አንድም የሌለሽ
ፀባይሽ መልክሽ ጎዶሎ
ባጣ ቆዪ ነሽ ለሁሉም
ለምርጫ አንዴም ማትበቂ
አዳርሰው እስከሚመጡ
እየሳቅሽ የምጠብቂ
ሞኝ ነሽ ምስኪን ከርፋፋ
ያልቀመስሽ አንዲት ከአለም
ሚያስቀና ትዝታ የሌለሽ
ብቸኛ ኦና ዘላለም "
የሚላት አንድ አካል አለ
ህሊና ስሯን ተጣብቆ
በቁስሏ ጦርን የሚሰድ
ፍርሃቷን ጭንቋን ሁሉ አውቆ
አንድ አለ የምታምነው ድምጽ
ሚወስን የሀሳቧን እድል
ባዶ ነሽ ኢምንት እያለ
ተስፋዋን ልቧን ሚገድል
አንድ አለ ሚያንገበግበኝ
እንደ ልጅ ስቤ ማልቀጣው
ያረጀ ያፈጀ እምነት
ከውስጧ የማላወጣው
አንድ አለ የውሸት መዝገብ
ላይሻር ከልቧ የፀና
እንዳታምን የሚከልላት
ልነግራት እሞክርና
ምን ያህል እንደሚወረኝ
ከጀርባ ሆና ስታቅፈኝ
እንኳን ሳቅ ድርብርብ ጥርሷ
ምራቋም እንደማይቀፈኝ
ልነግራት እሞክርና
ሰው መውደድ ትህትናዋ
ከሁሉም ልብ እንደሚቀር
ቀልቃላ የህፃን ፀባዩዋ
ምን ያህል እንደሚፈቀር
ልነግራት እሞክርና
በዜማ እንደሚሰማ
የወጣ ከእርሷ አንደበት
ከጥፍሯ እስከ ጠጉሯ
የሚጣል እንደሌለበት
ልነግራት እሞክርና
ላስረዳት እፈልግና
መደበቅ ማፈን ሲጨንቀኝ
ፈራለው "ውሸታም" ብላ
እኔንም እንዳትርቀኝ።
@mikiyas_feyisa


19.04.202505:20
12.04.202518:33
መሲሁን እየጠበቀ
የሰው ዘር በሞት ሲያዘግም
ተናንሶ እታች አገኙት
ንጉሱን ታቅፎ በግርግም፥
ገረማቸው...
ለምነው የዳዊት አምላክ
መንግስቱን ክብሩን የካደ?
እንዴት ነው ሰገነት ትቶ
በበረት የተወለደ?
እያሉ ተሳለቁበት..
እርግጥ ነው እንደጠበቁት
ሰራዊት አልነበረውም
ከቀራጭ አሳ አጥማጅ ውጪ
ወታደር አልቀረበውም
እርግጥ ነው እንደገመቱት
አልያዘም ጦር እና ጋሻ
የእርሱን ህዝብ የሚያድንበት
የጠላት ጦርን ድል መንሻ፤
አልያዘም እፍኝ ውሀ እንኳን
ለጠማው ቀድቶ ሚያጠጣው
እስራኤል ግርማ ሲጠብቅ
በአህያ ነበር የመጣው።
@mikiyas_feyisa
የሰው ዘር በሞት ሲያዘግም
ተናንሶ እታች አገኙት
ንጉሱን ታቅፎ በግርግም፥
ገረማቸው...
ለምነው የዳዊት አምላክ
መንግስቱን ክብሩን የካደ?
እንዴት ነው ሰገነት ትቶ
በበረት የተወለደ?
እያሉ ተሳለቁበት..
እርግጥ ነው እንደጠበቁት
ሰራዊት አልነበረውም
ከቀራጭ አሳ አጥማጅ ውጪ
ወታደር አልቀረበውም
እርግጥ ነው እንደገመቱት
አልያዘም ጦር እና ጋሻ
የእርሱን ህዝብ የሚያድንበት
የጠላት ጦርን ድል መንሻ፤
አልያዘም እፍኝ ውሀ እንኳን
ለጠማው ቀድቶ ሚያጠጣው
እስራኤል ግርማ ሲጠብቅ
በአህያ ነበር የመጣው።
@mikiyas_feyisa
28.03.202519:26
*
አድምቄ አድሬ ሲነጋልኝ
የያዝኩት ሁሉ ከእጄ እልም ፤
ምንድነው የነካኝ እመቤቴ
እለፋለው ግን ፈቀቅ አይልም።
ድጥ ና ማጥ ነው ፡ ደጄ ሁሉ
ግራ ይቀናኛል ፡ ልያዝ ካልኩም
የዝናብ ፍሳሽ ፡ የሚያስገባው
የእናቴን ጓዳም አላደስኩም።
ምንድነው ሰልፉ የሚያውከኝ?
አላልፍም አለኝ የእለት መርዶ፥
ምንም ሳልፈጥር ፡ ስንፈራገጥ
ባከንኩኝ እኮ ፡ ልቀር ባዶ።
ቀን ያቀናሁት በሌት ሲፈርስ
በሌት ያቆምኩት ቀን ሲከዳኝ ፤
ማለቅስበት ሰው አንድም ሳይኖር
ቅን በሌለበት ፍትህ ሚዳኝ፦
ለምን ኳተንኩኝ ፡ እናት ዓለም?
ግልገል ሆንኩ እኮ ፡ የተረሳ ፤
ወኔዬን እንኳን ቀን ቢከዳው
እነዛ ሁሉ ፡ ህልሞቼሳ?
ምን አጥፍቼ ነው በልጅሽ ፊት?
ምን ረግጦ ነው ፡ የእግሬ ዳናው?
የምሻው እሺ ፡ ይሁን.. ይራቅ
የያዝኩት ለምን ፡ የማይፀናው?
ምስቅልቅል ብሏል
ተስፋ ፣ ህልሜ፡
ፊት የነበረኝ ፡ ፋና ወጊው ፤
አሁን ላንዴ እንኳን አየር ልውሰድ
እስቲ መንፈሴን ፡ አረጋጊው።
ብዬ ጠረኩኝ
የአይኔን እምባ ፦
ከመደፋቴ ፡ ቀና አልኩኝ ፤
ቁጢጥ ብዬ ስዕሏ ስር
ከሬት የባሰ ሀቄን ዋጥኩኝ።
ከሩቅ የመጣ የስብከት ድምፅ
ከሽውታ ጋር ነክቶኝ ያልፋል፦
"በእግዜር እንመን ወንድሞቼ
እርሱ ጥላ ነው ፡ ያሳርፋል።
እዮብ ምን ነበር ፡ ከእጁ የቀረው
ቸር እግዚአብሄርን ፡ ሲያመሰግን?
ውጪው መልካችን አማኝ መስሎ
በዙር ይጮሃል ፡ ውስጣችን ግን!
ሀቁ ይሄ ነው ፡ ህይወት ህጓ
እሱን ሚያከብር ያልፈለታል፤
ወድቆ ከማያውቅ ሰው በላቀ
ወድቆ የተነሳ ፤ ይበረታል።
እንኳን ሰው ቀርቶ
የእግዜር አምሳል
ኤሎሄ ጌታ ማረኝ የሚል፤
ብረትም እንኳን ሀቁን አውቆ
በ'ሳት አልፎ ነው ሚሆን አክሊል።
አንጠራጠር እረኛችን፦
እኛን ሲጠብቅ ፡ ከቶ አይሰንፍም፤
ማንቸለው ችግር አሸክሞ
እንደ ግብዝ ሰው ፡ ጥሎ አያልፍም።"
....
ሰባኪው ፍቅርን ይተርካል
የድምፁ ቃና ሀይል አለው፥
እኔ ግን ስ'ሏን እያስተዋልኩ
የምትለኝን ፡ እሰማለው።
ለሚያይ ካህኑ ቢያስተምርም
አሜን እያለ ፡ ሲያደምቅ አማኝ፤
እኔ ግን ፡ ከዚህ ተነጥሎ
የእርሷ ቃላት ነው ፡ የሚሰማኝ!።
ምን አልሺኝ ድንግል?
@mikiyas_feyisa
አድምቄ አድሬ ሲነጋልኝ
የያዝኩት ሁሉ ከእጄ እልም ፤
ምንድነው የነካኝ እመቤቴ
እለፋለው ግን ፈቀቅ አይልም።
ድጥ ና ማጥ ነው ፡ ደጄ ሁሉ
ግራ ይቀናኛል ፡ ልያዝ ካልኩም
የዝናብ ፍሳሽ ፡ የሚያስገባው
የእናቴን ጓዳም አላደስኩም።
ምንድነው ሰልፉ የሚያውከኝ?
አላልፍም አለኝ የእለት መርዶ፥
ምንም ሳልፈጥር ፡ ስንፈራገጥ
ባከንኩኝ እኮ ፡ ልቀር ባዶ።
ቀን ያቀናሁት በሌት ሲፈርስ
በሌት ያቆምኩት ቀን ሲከዳኝ ፤
ማለቅስበት ሰው አንድም ሳይኖር
ቅን በሌለበት ፍትህ ሚዳኝ፦
ለምን ኳተንኩኝ ፡ እናት ዓለም?
ግልገል ሆንኩ እኮ ፡ የተረሳ ፤
ወኔዬን እንኳን ቀን ቢከዳው
እነዛ ሁሉ ፡ ህልሞቼሳ?
ምን አጥፍቼ ነው በልጅሽ ፊት?
ምን ረግጦ ነው ፡ የእግሬ ዳናው?
የምሻው እሺ ፡ ይሁን.. ይራቅ
የያዝኩት ለምን ፡ የማይፀናው?
ምስቅልቅል ብሏል
ተስፋ ፣ ህልሜ፡
ፊት የነበረኝ ፡ ፋና ወጊው ፤
አሁን ላንዴ እንኳን አየር ልውሰድ
እስቲ መንፈሴን ፡ አረጋጊው።
ብዬ ጠረኩኝ
የአይኔን እምባ ፦
ከመደፋቴ ፡ ቀና አልኩኝ ፤
ቁጢጥ ብዬ ስዕሏ ስር
ከሬት የባሰ ሀቄን ዋጥኩኝ።
ከሩቅ የመጣ የስብከት ድምፅ
ከሽውታ ጋር ነክቶኝ ያልፋል፦
"በእግዜር እንመን ወንድሞቼ
እርሱ ጥላ ነው ፡ ያሳርፋል።
እዮብ ምን ነበር ፡ ከእጁ የቀረው
ቸር እግዚአብሄርን ፡ ሲያመሰግን?
ውጪው መልካችን አማኝ መስሎ
በዙር ይጮሃል ፡ ውስጣችን ግን!
ሀቁ ይሄ ነው ፡ ህይወት ህጓ
እሱን ሚያከብር ያልፈለታል፤
ወድቆ ከማያውቅ ሰው በላቀ
ወድቆ የተነሳ ፤ ይበረታል።
እንኳን ሰው ቀርቶ
የእግዜር አምሳል
ኤሎሄ ጌታ ማረኝ የሚል፤
ብረትም እንኳን ሀቁን አውቆ
በ'ሳት አልፎ ነው ሚሆን አክሊል።
አንጠራጠር እረኛችን፦
እኛን ሲጠብቅ ፡ ከቶ አይሰንፍም፤
ማንቸለው ችግር አሸክሞ
እንደ ግብዝ ሰው ፡ ጥሎ አያልፍም።"
....
ሰባኪው ፍቅርን ይተርካል
የድምፁ ቃና ሀይል አለው፥
እኔ ግን ስ'ሏን እያስተዋልኩ
የምትለኝን ፡ እሰማለው።
ለሚያይ ካህኑ ቢያስተምርም
አሜን እያለ ፡ ሲያደምቅ አማኝ፤
እኔ ግን ፡ ከዚህ ተነጥሎ
የእርሷ ቃላት ነው ፡ የሚሰማኝ!።
ምን አልሺኝ ድንግል?
@mikiyas_feyisa
18.03.202520:23
ስሚኝ
ምናለፋሽ
ላጠፊኝ ላልጠፋሽ
እንደነ እነሱ
ማድነቅ ካልቻልኩበት
ባይሽ ምናለበት?
ቁምነገር ካጠረን
ባንስቅ ባንጫወት
ምናችን ይጎላል?
ዝምታም ደስ ይላል!
ማይደበዝዝ መልክሽ
በአይኔ ተንሰራፍቶ
ምን ያረጋል ፎቶ?
እንደነ እዩልኝ
እንደነ እወቁልኝ
ታይታን ባንኮርጅም
አብረን አናረጅም?
ተዪው
ምን አለፋሽ
ላጠፊኝ ላልጠፋሽ
የምታስመስዪው
ፍቅር እንዳነደደው ፤
ምናለበት ብኖር
እንደተለመደው?
@mikiyas_feyisa
ምናለፋሽ
ላጠፊኝ ላልጠፋሽ
እንደነ እነሱ
ማድነቅ ካልቻልኩበት
ባይሽ ምናለበት?
ቁምነገር ካጠረን
ባንስቅ ባንጫወት
ምናችን ይጎላል?
ዝምታም ደስ ይላል!
ማይደበዝዝ መልክሽ
በአይኔ ተንሰራፍቶ
ምን ያረጋል ፎቶ?
እንደነ እዩልኝ
እንደነ እወቁልኝ
ታይታን ባንኮርጅም
አብረን አናረጅም?
ተዪው
ምን አለፋሽ
ላጠፊኝ ላልጠፋሽ
የምታስመስዪው
ፍቅር እንዳነደደው ፤
ምናለበት ብኖር
እንደተለመደው?
@mikiyas_feyisa
26.01.202518:23
ዝምብሎ ነበርኩ ዋዛ ፈዛዛ
የትም እንዳልሄድ ይሉኝታ ያቀፈኝ
እንዳልነበርኩኝ ምንም ሳላውቀው
ሌሎች የኖሩት ደስታ ያለፈኝ
አንድ ሰው ነበርኩ ከመንጋው መሃል
የዛሬን ብቻ መኖር ያደለው
አዳምጡኝ የሚል የተዋቀረ
ለአፍ የሚጥም ታሪክ የሌለው
ተራ ሰው ነበርኩ
አዘቦት ነበርኩ
ድንገት ሳዳምጥ የሰዉን ታሪክ
በድፍረት ሄደው ባገኙት እድል
እያጫወቱኝ ስላለፉበት
ተረት ሚመስል ድራማ ገድል
ስለማይረሱት የልጅነት ፍቅር
ስላጣጣሙት ጣፋጭ ሰቀቀን
የደስታ እንባን የተራጩበት
የህይወታቸው ማይረሳ ቀን
ውሃ ተግተው "ከዛን" እያሉ
ዘመናቸውን - እየተረኩኝ
እግዜር ይመስገን ብዙ ተረዳው
ተወለድኩ አንጂ እኔ መች ኖርኩኝ!
በማይደፈርስ ፡ ትኩረት ታግዘው
ጆሮ ሰክተው ቢያዳምጡኝም፤
የምኮራበት "ስሙኝ" የምለው
ሽሙንሙን ያለ ታሪክ የለኝም።
ባገላብጠው የአይምሮዬን ቅል
ባወጣ ባወርድ ከልቤ ድኩም፤
ለሌሎች ሰዎች የምተርከው
ምንም ትዝታ አላሳለፍኩም!።
@mikiyas_feyisa
የትም እንዳልሄድ ይሉኝታ ያቀፈኝ
እንዳልነበርኩኝ ምንም ሳላውቀው
ሌሎች የኖሩት ደስታ ያለፈኝ
አንድ ሰው ነበርኩ ከመንጋው መሃል
የዛሬን ብቻ መኖር ያደለው
አዳምጡኝ የሚል የተዋቀረ
ለአፍ የሚጥም ታሪክ የሌለው
ተራ ሰው ነበርኩ
አዘቦት ነበርኩ
ድንገት ሳዳምጥ የሰዉን ታሪክ
በድፍረት ሄደው ባገኙት እድል
እያጫወቱኝ ስላለፉበት
ተረት ሚመስል ድራማ ገድል
ስለማይረሱት የልጅነት ፍቅር
ስላጣጣሙት ጣፋጭ ሰቀቀን
የደስታ እንባን የተራጩበት
የህይወታቸው ማይረሳ ቀን
ውሃ ተግተው "ከዛን" እያሉ
ዘመናቸውን - እየተረኩኝ
እግዜር ይመስገን ብዙ ተረዳው
ተወለድኩ አንጂ እኔ መች ኖርኩኝ!
በማይደፈርስ ፡ ትኩረት ታግዘው
ጆሮ ሰክተው ቢያዳምጡኝም፤
የምኮራበት "ስሙኝ" የምለው
ሽሙንሙን ያለ ታሪክ የለኝም።
ባገላብጠው የአይምሮዬን ቅል
ባወጣ ባወርድ ከልቤ ድኩም፤
ለሌሎች ሰዎች የምተርከው
ምንም ትዝታ አላሳለፍኩም!።
@mikiyas_feyisa
无法访问
媒体内容
媒体内容
31.12.202409:11
ጨለማ ውጦት ስጋ ነፍሴን
እድሜ ዘመኔን ብርሃን ያጣው
ለመዳን ሳይሆን ለመጠመቅ
ስንኩልኩል እያልኩ ደጅሽ መጣው
ቤትሽ ግን ስደርስ ስለት ገባው
ተዓምር ካረገ ኪዳን ቃልሽ
በምህረት እጅሽ አይኔን ዳብሰሽ
ቀሪ ዘመኔን ላገልግልሽ
ብዬ ገባሁኝ
ከአጥማቂው ስር
እንዴት ይበርዳል ወየው ወየው
እምነት ከአይኔ ላይ አረኩና
አረፍ እንዳልኩኝ አንቺን አየው
ስዕልሽ አለ ግርዳው ላይ
ልቤ አላመነም ሀቅ ይሸሻል
ትልቅ ዙፋን ላይ ተቀምጠሽ
መድህነ አለም ታቅፈሻል
እንዴት ልካደው ተንተባተብኩ
ፊደል ለጎመ የአፌ መፍቻ
አምላኬን በእጅሽ እያየሁት
የወጣኝ ነገር እምባ ብቻ
የልቤን መቃን ፍቅር ያንኳኳው
ተውጬ ሳለው በሰመመን
እደጅሽ ቆሞ ማሪኝ የሚል
በርጠሚዎስ ነኝ የዚህ ዘመን
የፍቅር እናት የአዶናይ
የጭንቅ ደራሽ የብዙሃን
ድፍኑን አይኔን ገለጥሺልኝ
በልጅሽ በኩል እመብርሃን?
ከህርያቆስ ልዋስ ቅዳሴሽን
ላዚመው ይድረስ ከአርያም
ድቅድቁን ሚገፍ ሀይል ያለው
ፀሀይ ነው ስምሽ ድንግል ማርያም!
@mikiyas_feyisa
እድሜ ዘመኔን ብርሃን ያጣው
ለመዳን ሳይሆን ለመጠመቅ
ስንኩልኩል እያልኩ ደጅሽ መጣው
ቤትሽ ግን ስደርስ ስለት ገባው
ተዓምር ካረገ ኪዳን ቃልሽ
በምህረት እጅሽ አይኔን ዳብሰሽ
ቀሪ ዘመኔን ላገልግልሽ
ብዬ ገባሁኝ
ከአጥማቂው ስር
እንዴት ይበርዳል ወየው ወየው
እምነት ከአይኔ ላይ አረኩና
አረፍ እንዳልኩኝ አንቺን አየው
ስዕልሽ አለ ግርዳው ላይ
ልቤ አላመነም ሀቅ ይሸሻል
ትልቅ ዙፋን ላይ ተቀምጠሽ
መድህነ አለም ታቅፈሻል
እንዴት ልካደው ተንተባተብኩ
ፊደል ለጎመ የአፌ መፍቻ
አምላኬን በእጅሽ እያየሁት
የወጣኝ ነገር እምባ ብቻ
የልቤን መቃን ፍቅር ያንኳኳው
ተውጬ ሳለው በሰመመን
እደጅሽ ቆሞ ማሪኝ የሚል
በርጠሚዎስ ነኝ የዚህ ዘመን
የፍቅር እናት የአዶናይ
የጭንቅ ደራሽ የብዙሃን
ድፍኑን አይኔን ገለጥሺልኝ
በልጅሽ በኩል እመብርሃን?
ከህርያቆስ ልዋስ ቅዳሴሽን
ላዚመው ይድረስ ከአርያም
ድቅድቁን ሚገፍ ሀይል ያለው
ፀሀይ ነው ስምሽ ድንግል ማርያም!
@mikiyas_feyisa
显示 1 - 24 共 58
登录以解锁更多功能。