tapswap community
tapswap community
Notcoin Community
Notcoin Community
Whale Chanel
Whale Chanel
tapswap community
tapswap community
Notcoin Community
Notcoin Community
Whale Chanel
Whale Chanel
𝕗𝕖𝕖𝕝𝕚𝕟𝕘𝕤 𝕖𝕔𝕙𝕠 avatar

𝕗𝕖𝕖𝕝𝕚𝕟𝕘𝕤 𝕖𝕔𝕙𝕠

T h e s o u n d o f s i l e n c e 🔇 🌠
TGlist 评分
0
0
类型公开
验证
未验证
可信度
不可靠
位置
语言其他
频道创建日期Трав 06, 2025
添加到 TGlist 的日期
Трав 07, 2025
关联群组

记录

16.05.202523:59
510订阅者
07.05.202523:59
0引用指数
16.05.202513:08
228每帖平均覆盖率
16.05.202523:06
0广告帖子的平均覆盖率
10.05.202518:02
23.53%ER
16.04.202521:11
114.40%ERR
订阅者
引用指数
每篇帖子的浏览量
每个广告帖子的浏览量
ER
ERR
08 ТРАВ '2510 ТРАВ '2512 ТРАВ '2514 ТРАВ '25

𝕗𝕖𝕖𝕝𝕚𝕟𝕘𝕤 𝕖𝕔𝕙𝕠 热门帖子

"ሁሉም ሰው ጨረቃ ነው፥ ለማንም የማያሳየው ጨለማ ጎን አለው።"

_ማርክ ትዌይን
  ያለፉት ትዝታዎች እንደ የማይታዩ ጥላዎች ይከተሉኛል። ፈገግታዬ ከእነሱ ለመራቅ የለበስኩት ጭምብል ነው ። በውጭ የተረጋጋ ብመስልም፣ በውስጤ ግን ከባድ ማዕበል አለ። ማንም ወደ ልቤ ጥልቀት ዘልቆ አይገባም። የዚህን ስቃይ ምስጢር የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ።
  "እናቴ ሕይወት ልክ እንደ ቸኮሌት ሳጥን ናት ምን እንደምታገኝ ፈጽሞ አታውቅም ትለኝ ነበር ።... ሞት የሕይወት አካል እንዲሁም እጣ ፈንታችን ነው። ስለሱ ምንም ማድረግ አንችልም... አንዳንድ ጊዜ ግን አንድ ዓይነት ዕጣ ፈንታ ያለን ይመስለኛል፣ ልክ ነፋስ እንደሚወስደን። እናቴ ትክክል ነበረች እላለሁ፣ እጣ ፈንታችንን አንወስንም ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በራሳችን የምንሄድ ይመስለኛል።"

     📽️; forrest gump
"የምንሆነው የምናስበውን ነው። አእምሮ ንጹህ ሲሆን ደስታ እንደ ጥላ ይከተለናል። ጥላው አካሉን እንደሚከተለው ሁሉ ደስታም ንጹሕ አእምሮን ይከተላል። ስለዚህ አስተሳሰባችሁን ማስተካከል አለባችሁ ወደ ቃል ያድጋልና፤ ቃላችሁን ተጠንቀቁ ልማዳችሁ ይሆናልና፤ ልማዳችሁን ተጠንቀቁ ባህሪያችሁ ይሆናልና፤ ባህሪያችሁን ተጠንቀቁ እጣ ፈንታችሁ ይሆናልና ስለዚህ እጣ ፈንታችሁን ለማስተካከል ሀሳቦቻችሁን መቀየር የመጀመሪያው እርምጃ ነው።"

      -ማሃትማ ጋንዲ
በዚህ ሩጫ በበዛበትና በጩኸት በተሞላ ዓለማችን ውስጥ፣ የዝምታን ኃይልና ዋጋ ብዙ ጊዜ እንረሳዋለን። ዝምታ የድምፅ እጦት አይደለም፤ ነገር ግን ወደ ውስጣችን በምናደርገው ጉዞ፣ ሐሳባችንን የምናጠራበት፣ እና ከራሳችን ጋር የምንገናኝበት ቅዱስ ቦታ ነው።
አንድ ሰው ዝም ሲል፣ ውጫዊው ግርግር ይቀንሳል፣ ውስጣዊው ድምፅ ይሰማል። በዚህ ጸጥታ ውስጥ ጥልቅ ግንዛቤዎች ይፈነጥቃሉ፣ አዲስ ሀሳቦች ይወለዳሉ፣ እናም ለሕይወት ያለን አመለካከት ይበልጥ ግልጽ ይሆናል። ልክ አንድ የሙዚቃ ኖታ በዙሪያው ባለው ባዶ ቦታ እንደሚደምቅ፣ የሕይወታችን ትርጉምም በዝምታ ውስጥ ይበልጥ ጎልቶ ይታያል።
አንዳንድ ጊዜ፣ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት ከውጪ ድምፆች ይልቅ ወደ ውስጣችን ማዳመጥ ያስፈልገናል። ዝምታ የነፍሳችን ቋንቋ ነውና።
"እያንዳንዱ ሰው የራሱን ምርጫ ይወስን። መሄድ የሚፈልግ መሄድ ይችላል። እኛ ግን እንቆማለን። ለአንድ ነገር መቆም ና ለአንድ ነገር መሞት ሕይወት ትርጉም የምታገኘው ያን ጊዜ ነው። ፈሪዎች መሸሽ ይችላሉ፤ እኛ ስፓርታውያንና ከእኛ ጋር ለመሞት የወሰኑት ጀግኖች ግን እዚህ እንቆማለን።"
📽️; three hundred (300)

እ.ኤ.አ. በ2006 የተለቀቀ ሲሆን ስፓርታ አቴንስን ሳትቆጣጠር የሶቅራጥስ ፍልስፍናዎችም የግሪክን ወንዶች ጀግንነት ሳያዳክሙ በፊት የነበረውን ጊዜ ያሳያል።

በተለይም በንጉሥ ሊዮናይድስ እና በ300ዎቹ የቅርብ ወታደሮቹ ጀግንነትና መስዋዕትነት ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን  'የወንድነት' (masculinity) ጽንሰ-ሀሳብ እና ከእሱ ጋር የተያያዙ እሳቤዎችን በግልጽ ያሳያል።
የስፓርታውያንን ከልጅነት ጀምሮ ለጦርነት የሚዘጋጅ ከባድ ሥልጠና፣ አካላዊ ብርታት፣ የማይናወጥ የሥነ ልቦና ጥንካሬ፣ ለሕግና ለሥርዓት ያላቸውን ተገዥነት እንዲሁም የማይበገር መንፈሳቸውን ያሳያል። ንጉሥ ሊዮናይድስ ደግሞ የዚህ ሁሉ የወንድነት መገለጫዎች ቁንጮ ተደርጎ ይቀርባል። የእሱ መሪነት፣ ቆራጥነት፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን የማይበገር መንፈሱ ከመሪነቱም ባሻገር ወንድነቱን አጉልቶታል።

ፊልሙን ለየት የሚያደርገውም በእውነተኛ ታሪክ ላይ መሰረቱን በማድረጉ ነው። ከክርስቶስ ልደት በፊት በ480 አ.አ በንጉሥ ሊዮናደስ የሚመሩት 300 የስፓርታ ወታደሮች ከሌሎች ጥቂት የግሪክ ሌሎች ከተማ ወታደሮች ጋር በመሆን፣ እጅግ በጣም ብዙ ቁጥር ካለው በፋርስ ንጉሥ በዘሪከስ ከሚመራው ሠራዊት ጋር the  Battle of Thermopylae ተብሎ የሚጠራ ጦርነት ላይ ተዋግተዋል።  ፊልሙም ይሄን ታሪክ መሰረቱን አድርጎ ሊሰራ ችሏል።
"ሁሉም እርካታ ወይም በተለምዶ ደስታ ተብሎ የሚጠራው ስሜት ሁልጊዜ አሉታዊ ነው፣ ፈጽሞ አዎንታዊ አይደለም። በራሱ ጊዜ ወደ እኛ የሚመጣ ስሜት ሳይሆን የህመም መቆም ነው። ምክንያቱም ረሃብ የመጀመሪያው ነገር ነው፣ ይህም በመብላት ይወገዳል። ህመም የመጀመሪያው ሁኔታ ነው፣ ይህም በፈውስ ይወገዳል። ውጥረት የመጀመሪያው ሁኔታ ነው፣ ይህም እርካታ በማግኘት ይወገዳል። ስለዚህ፣ ደስታ የሥቃይ መቆም ብቻ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሥቃይ የህይወት አዎንታዊ እውነታ እና ሁልጊዜ የሚከሽፍ ወይም ያልተሳካ የመሞከር ፍላጎት ነው።"

       -arthur schopenhauer
በታኦይዝም ፍልስፍና ዓለም እንደማይቆም ወንዝ በታኦ ይመራል። ሀዘን የምንሰማው ነገሮች በኛ በፈለግነው መንገድ ባለመሆናቸው ነው። የምንወዳቸውን ሰወች በሞት ስናጣ፣ ይህን የሕይወት ተፈጥሯዊ ፍሰት መቃወም ሀዘንን ያመጣል። ልክ ጅረት ሲገታ ትክክለኛ መስመሩን ጥሶ እንደሚፈስ፣ የማይቀርን ስንቃወም እንሰቃያለን።
ታኦይስቶች "ዉ-ዌይ" በማለት ሀሳባቸውን ይገልፃሉ። ትርጉሙ ሁሉንም መተው ሳይሆን፣ ነገሮች በራሳቸው እንዲሆኑ መፍቀድ እና ከመጠን በላይ ቁጥጥርን ማስወገድ ነው። በሀዘን ጊዜ ስሜታችንን መቀበል እንጂ መዋጋት የለብንም። ጀልባ በወንዝ ላይ እንደምትጓዝ፣ በሕይወታችን ለውጦች ውስጥ በጸጋ ማለፍ ያስፈልጋል።
የምንወዳቸው ትዝታ በልባችን ይኖራል፣ ነገር ግን በሌሉበት ዓለም መኖርን መማር እና የሕይወትን ቀጣይነት መቀበል አለብን። ልክ ወንዝ እንደሚቀጥል፣ ሕይወትም እንዲሁ ነው። ቁጥጥርን ከመፈለግ ይልቅ እጅ መስጠት እና በተፈጥሮ ፍሰት ውስጥ ሰላምን መፈለግ የሀዘንን ሸክም ያቃልላል።
የጊዜ ጥቁር ጥላ ልጅነቷን ሸፈነባት
የሳቀችበትን ሜዳ መሪር ሀዘን አጠላበት
የደስታ ዜማዋ ጠፋ ትዝታ ልቧን ቧጨረ
በጊዜ ወንዝ ተንሳፎ ትኩሳቷ ተቀበረ
ተስፋዋ ሀዘን ወለደ ብቸኝነቷ በረታ
መከራ ቀኗ ረዘመ ድህነቷ በድሜ ተገታ
መከፋቷ ነፍስ ዘርቶ ህይወቷ ትርጉም ስታጣ
ሞት የሀሳብ ገፅ ተላብሶ ወደ አእምሮዋ መጣ።
ድሮ ላይ እሷን ከመተዋወቄ ከወራት በፊት ብዙ ብቸኝነትን የተላበሱ ቀዝቃዛ ምሽቶች ነበሩኝ። ፀሐይ ወደ መጥለቂያዋ ስትቃረብ ግንባሬን ለ Sunset ሰጥቼ፣ በዝምታ እግሮቸ ወደ መሩኝ አቅጣጫ እጓዛለሁ። በዚያ ሰዓት አእምሮዬ ሁሌም የምሸሸውን ጥያቄ ያነሳብኛል። ከሰዎች አመለጥኩ ብዬ ሳልጨርስ፣ አእምሮየ ባሳቻ ሰአት ፀጥታውን ተጠቅሞ ይጋፈጠኛል። ከአለም ጣጣ በብቸኝነት ጭምብል ተከለልኩ፣ ከራሴስ ማን ያድነኛል? ያኔ የሀሳቦቸን ድምጽ ለመሸፈን፣ የልቤን ትርምስ ለማረጋጋት ሙዚቃን መደበቂያ አደረኩት። የሙዚቃ ዜማዎች የውስጤን የባዶነት ስሜት ለጊዜውም ቢሆን ይሸፍኑልኝ ነበር።

ከጊዜያት በኋላ ግን ሙዚቃ አላስፈለገኝም። ከእራሴ ጋር ሰላም አውርደን ሳይሆን ሌላ ሙዚቃ አገኘሁ። ከሙዚቃ በላይ ለነፍስ ሀሴት የሆነ ድምፅ፤ ማንኛውንም ጥያቄ አእምሮ ላይ አስረስቶ ለልብ መልስ የሚሰጥ ፈገግታ የተቸረች ናት። እኔ የተፈጠርኩት እሷ ስታወራ ለማድመጥ፣ የፈገግታዋን ብርሃን ለነፍሴ ምግብ ላደርግ ይመስላል። ፈጣሪ በሷ መልክ ደስታን ሸለመኝ። ስለ እሷ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም። በየቅጽበቱ በሀሳቤ ትመላለሳለች። ልቤ ለእሷ በናፍቆት ይመታል።

የሆነ ቀን ላይ አይኖቼን በትኩረት እያየች ሁሌም የምሸሸውን ጥያቄ በድንገት አነሳችብኝ። "ወጣትነትህን በብቸኝነት እንድታባክን ያደረገህ ያለፈው ህይወትህ ምን ቢመስል ነው?" ውስጡ እውነታ ያለው ግን ለመቀበል የማልችለውን ሀሳብ የተሸከመ ጥያቄ...  ያቺን ቅጽበት ፈራኋት፣ የፈራሁት የጥያቄዋን ምላሽ አልነበረም።  እውነት ወጣትነቴ ባክኗል? እንደ ልጅነቴ ወጣትነቴም እያለቀ ነው?
"ህልምን ማሳካት የማይቻል የሚያደርገው አንድ ነገር ብቻ ነው ያለው፡ የውድቀት ፍርሃት። ... 'ህልምህን ለመከተል ደፋር ስትሆን፣ ሁሉም ነገር አንተን ለመርዳት ይጥራል። የመጨረሻው ፈተና ይህ የእምነት ፈተና ነው። በተስፋ መቁረጥ አፋፍ ላይ ስትሆን፣ ልታሳካው ስትተጋ የነበረውን ልታሳካ እንደሆነ ማመን አለብህ።' ሕልም እውን ከመሆኑ በፊት፣ የዓለም ነፍስ በመንገዱ ላይ የተማርከውን ሁሉ ትፈትንሀለች። ይህን የምታደርገው ክፉ ስለሆነች ሳይሆን፣ ሕልሞቻችንን ከማሳካታችን በተጨማሪ፣ ወደዚያ ሕልም ስንጓዝ የተማርናቸውን ትምህርቶችም እንድንገነዘብ ነው። አብዛኞቹ ሰዎች እዚህ ነጥብ ላይ  ተስፋ ቢቆርጡም ፤ ምሳሌው እንደሚለው ነው "ሊነጋ ሲል ይጨልማል"

      📚 አልኬሚስቱ
"ፍልስፍና... በጎ አድራጎት የሌለው ፣ የተተወ፣ በጣም የሚናቅ ዕውነትን ፍለጋ ነው። ያም የሚያሰቃይ ነው። የዕውነት ፍለጋው ራሱ ሥቃይ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ለዘመናት ትክክል ነው ብለን ያመንባቸው ነገሮች ሁሉ ስህተት መሆናቸውን ስንገነዘብ ነው። የሰው ልጅ ራሱን ሲያታልል መኖሩን ማወቅ ልብ ይሰብራል።"

          -ኒቼ
"አትክልት ሻጩ 'ዓለም አቀፍ ሠራተኞች ተባበሩ!' የሚለውን መፈክር በመስኮቱ ላይ ማስቀመጥ የነበረበት በሃሳቡ ተስማምቶ ሳይሆን፣ ሁሉም ስለሚያደርገውና ከእሱም ስለሚጠበቅበት ነበር። ይህን በማድረግም በሰላም የመኖር መብቱን ገዛ። ይህን እንዲያደርግ አልተገደደም፣ ነገር ግን ሊመጡ የሚችሉ መዘዞችን በመፍራት፣ የስርዓቱ ስውር ግፊት እንዲስማማ አደረገው። ይህች ትንሽ፣ ትርጉም የሌላት የምትመስል ድርጊት፣ በሚሊዮኖች ስትባዛ፣ የስርዓቱ ስልጣን መሰረት የሆነውን የአለም አቀፋዊ ተቀባይነት ገጽታን ትፈጥራለች። በትንንሽ ነገሮችም ቢሆን እውነትን መኖር እና፣ በውሸት ውስጥ ለመሳተፍ እምቢ ማለት ይህን ገጽታ የሚገዳደር የፖለቲካ ችግር ነው።"

        -Vaclav havel
በጥንቷ ግብፅ "ማት" የሚባል አንድ ህግ ነበራቸው። ይህም ልክ እንደ አጽናፈ ሰማይ አሠራር መሰረት ያደረገ ሁሉ ነገር በሥርዓት እንዲሄድ ያደርጋል ተብሎ የሚታመንበት ሕግ  ነው። ግብፃውያን ሁሉም በማት ምክንያት እንደሆነ ያምኑ ነበር። እናም ሰዎች ይህንን ሥርዓት ጠብቀው በሚሰሩት ነገር ሁሉ ማትን የማሳየት ኃላፊነት ነበረባቸው።
ይህ የማት ሃሳብ የግብፃውያንን ጥሩ እና መጥፎ ስለሚባሉት ነገሮች ያላቸውን አመለካከት ይቀርፃል። ፈርዖኖችም እንኳ ለማት ተገዢ ነበሩ። ፍትሕን ማስፈን፣ ነገሮችን በሥርዓት ማቆየት እና ሚዛንን የሚረብሹ ነገሮችን አለማድረግ የሁሉም ሰው ሥራ ነበር።
በግብፃውያን እምነት መሠረት ከሞትን በኋላ ልባችን ይመዘናል ይባል ነበር  የእውነት እና ፍትሕ ምልክት ከሆነ ላባ ጋር ማለት ነው። የሞተው ሰው ልብ ከላባው ከከበደ፣ ይህ ማለት በሕይወቱ ውስጥ ማትን ጥሷል መጥፎ ሰው ነበር ማለት ነው። ልቡ ከላባው ጋር እኩል ከቀለለ ደግሞ፣ ይህ ማለት በሥርዓት እና በፍትሕ መሠረት ኖሯል ማለት ነው።
የማት ፅንሰ ሀሳብ እኛ በምናደርገው ነገር ሁሉ ኃላፊነት አለብን ይላል። የምናደርጋቸው ጥሩ ነገሮች ሥርዓቱን ያጠናክራሉ፣ መጥፎ ነገሮች ደግሞ ያናጉታሉ። በዚህም ምክንያት ግብፃውያን በሕይወታቸው ሐቀኛ፣ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ ለመሆን ይጥሩ ነበር።
ሁሉም ስሜቶች በአንድ ሰፊና ጭር ባለ አዳራሽ ውስጥ ተሰብስበዋል የብቸኝነት ስሜት በዝግታ ይንሳፈፋል። ቀለሙ እንደ ምሽት ሰማይ የጠቆረ፣ እንቅስቃሴው የከባድ ትንፋሽ ያህል የረጋ ነበር። ዙሪያውን የተረሱ ትዝታዎች እንደ ሻማ ብልጭ ድርግም ይሉ ነበር። ደስታ የፈነጠቀባቸው ጊዜያት ደብዛዛ ምስሎች፣ አሁን ግን የሀዘን ጥላ ለብሰው በዝምታ ይመለከቱታል።

ጸጸት ከሩቅ ማዕዘን ተነስቶ በቀስታ ወደ ብቸኝነት ተጠጋ። ድምፁ እንደተሰበረ ዋሽንት ጣዕም የለውም፣ ያለፉ ስህተቶችንና ያመለጡ ዕድሎችን እያስታወሰ ጣዕም በሌለው ድምፅ ያወራል። ሁለቱም ስሜቶች በአንድ ላይ ተቀራረቡ፣ የናፍቆት ዜማ በዝግታ በአዳራሹ ውስጥ ይሰማ ጀመር።

ይህን ሁሉ ሲከታተል የነበረው ክህደት በንዴት ጮኸ። ቀለሙ እንደ እሳት ቀይ፣ እንቅስቃሴው ደግሞ የሰይፍ ምት ያህል ፈጣን ነበር። "ተታለልክ!" ሲል ጮኸ፣ "ተጎዳህ! ወጣትነትህን በከንቱ አባከንክ! " የብቸኝነትና የጸጸት ሀሳቦች በድንጋጤ ወደ ኋላ አፈገፈጉ፣ የክህደት ቁጣ በአዳራሹ ውስጥ ማስተጋባቱን ቀጥሏል።

"ከሁሉም በላይ ትልቁ አደጋ፣ ራስን ማጣት ነው። ምንም እንዳልተፈጠረ ያህል በጣም በጸጥታ ሊከሰት ይችላል። ሌላ ምንም ዓይነት መጥፎ ነገር በጸጥታ ሊከሰት አይችልም፤ ሌላ ማንንም ብናጣ የፍቅር አጋር፣ ጓደኛ፣ ቤተሰብ ሁሉንም ሰው ያስተውላቸዋል።"

     -Søren Kierkegaard
登录以解锁更多功能。