tapswap community
tapswap community
Notcoin Community
Notcoin Community
Whale Chanel
Whale Chanel
tapswap community
tapswap community
Notcoin Community
Notcoin Community
Whale Chanel
Whale Chanel
✍ዮ_ሚን avatar

✍ዮ_ሚን

ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡
ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡
@Yobminn
TGlist 评分
0
0
类型公开
验证
未验证
可信度
不可靠
位置
语言其他
频道创建日期Jun 06, 2023
添加到 TGlist 的日期
Nov 11, 2024
关联群组

"✍ዮ_ሚን" 群组最新帖子

ምንድነው ሁሉንም
ሸፍኖ ማስቀመጥ
ነይ ብርድ እንመታ
ሆድ አንገላለጥ


ገጣሚ ጥላሁን ከብካቦ
@yomim1_2
እንኳን ተገናኘን....
እንኳን ተለያየን....
እንኳን ሁሉን አየን....

እሰየው!

እኛስ ተገናኝተን
ተፋቅረን ጨረስነው
ስንት አለ መሰለሽ
የፍቅርን ጣዕም
በቅጡ ያላወቀው።

@yomin1_2
ወዴት

አንቺየዋ እመስላለሁ የደስታ ሰው
እስቃለሁ በጣም በጣም
በመሄድሽ በመጥፋትሽ
መከፋቴን አላስጠጣም

የት ነኝ ወዴት
የት ነኝ የምር
አንቺ ሳለሽ
የማበራ የም.. አምር
አሁን የት ነኝ
ከየት መንገድ
አንቺ ሳለሽ
የነበረኝ ሁነኛ እቅድ...

ስቴጅም አሁን አሁን
ጠፍቶብኛል ኑሮ ተስፋ
ያለኝ ነበርኩ እቅድ ብርቱ
በአንቺ ልክ የተሰፋ.....
ይዤ ነበር አላማዬን
አንቺ ዳሻሽ የምታዥው
ስትስቂማ ደስታ ነበር
ስታነቢም እንደ.... ከፋው
አለመድኩኝ ያላንቺማ
አለመድኩኝ ውሃዬዋ
አለመድኩኝ
ለብቻዬ መንቀሳቀስ
የጠፋሽ ቀን ሸጋዬዋ
ከየት በዬ ወዴት ልድረስ..... 🏃

ልጠይቅሽ አንድ ነገር
መልሽልኝ ዉበት መልኬን
ልጠይቅሽ ሁለተኛ
መልሺልኝ ተስፋ ሳቄን
ልጠይቅሽ..ሶስት... ልጠይቅሽ..አራት.....
መልሽልኝ....መልሽልኝ......
መልሽልኝ.... ልድመቅበት
መልሽልኝ.... ልዋብበት
መልሽልኝ.... ላቅድበት
መልሽልኝ.... ልሳቅበት
አንቺ ዳለሽ ገላዬዋ
አንቺ ዳለሽ እንደ...ድሮው
ሆኜ ልገኝ የተሟላ
ስቆ እሚውል ተስፋ ያለው...
.
.
.
ግና ደግሞ
አይጠየቅ ከሰው ተስፋ
አምላክ እንጂ የሚያበራ
ሁሉም ነገር ሲጠፋፋ



.. ተስፋ... ሳቄ... አምላክ ጋር ነው..... 🙏🙏🙏


በ ሚክያስ(mirak)

https://t.me/yomin1_2
መለስ ብል ቀለስ
እልፍ አላፉን ባስስ
ጎንበስ ብል ቀና
በባልሽ ብቀና
ፈገግ ብል ባነባ
ምን ግራ ብጋባ
አውቃለሁኝ
ውዴ እንደማንጋባ።

#ኢዮብ_አሰፋ

@yomin1_2
ለሁሉም ጊዜ አለው


ለመረዳት፣ ላለመረዳት፣ ለመሳሳት፣ ለመስተካከል፣ ቀና ለማለት፣ ለመጉበጥም፣ ስኳር ከሰማይ የሚረግፍበት ዘመን አለ፣ ጥብስም የሚመለክበት፣ የመጠጣት ጊዜ አለው፣ የመጥመቅ ጊዜ አለው፣ ጠጥቶም የመሽናት፣ የመውለድ ጊዜ አለው፣ የማደግም ጊዜ አለው፣ የመጎርመስም ጊዜ አለው፣ ጎርምሶ የመውደድም፣ ብስክሌት የመጋለብ፡፡ የጋለቡትንም የመስበር፡፡ የሰበሩትንም የመጠገን፡፡ የጠገኑትን መልሶ የመጋለብ፡፡

ጊዜ አለው በሬ የሚያርስበት፡፡ ለስጋም ወደ ገበያ የሚነዳበት፣ ከገበያም ተወስዶ የሚታረድበት፡፡ ጊዜ አለው ወደ ጥብስ የሚለወጥበት፡፡ ጊዜ አለው ማዕዳችን ላይ የሚከነበልበት፡፡ ጊዜ አለው ዲያቆን መሆን፣ ጊዜ አለው ነጋዴም መሆን፣ በተፃብኦ ማፍቀር እሱም አልፎ በቀን ሕልም መውደድ፣ ቀለበትን የማጣት እሱንም መልሶ የማግኘት፣ ጊዜ አለው ለማፍቀርም፣ ጊዜ አለው አፍቅሮ ለመለያየትም ጊዜ አለው ገመና ገመና ላይሆን፡፡ ጊዜ አለው ግዙፉ አውድ ረቂቅ አውድ የሚሆንበት፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው ይላል

<<ልበሙሉነት ብቻውን ያለ ትክክለኛ መረጃ ምንም ነው። ሳታውቅ 'አውቀሃል' ካለህ አገልግሎትህ መስዋዕት መሆን ብቻ ነው።>>

(መረቅ ~ በአዳም ረታ)

   
https://t.me/yomin1_2
የማንም ጓጆ በእውነት ብቻ አልተሰራም ። እውነት በመውደድ ፊት አቅም የለውም ። እውነት ላይ ክችች ያሉ ሰዎች ቤታቸው ሲፈርስ ፣ ከስራ ሲባረሩ ፣ ስራ ሲበላሽባቸው ነው ያየሁት ....

Undeniable truth !!

የሞቀ ቤት ያላቸው ብዙ ቤታቸውን ሊያቀዘቅዘው የሚችል ነገር ታግሰው ነው !! ሳድግ ያየሁት ጥበብ እሱን ነው ። መኖር ያሳየኝ እውነት ይሄ ነው ።

የሚያኖረው መለሳለሳችን ነው !!

ደረቅ እውነት አያሸንፍም። እውነት ብቻውን አያሻግርም ። እሚያኖረን ጥበባችን ነው ። የጎጆ መሰረት እውነት አይደለም መተላለፍ ነው።

ሁሉም የሞቀ ቤት ውስጥ የታለፈ ፣ይቅር የተባለ አደባባይ የማይነገር፣ ያልተነገረ ገበና አለ ።
እየተላለፍን ! ✋
© Adhanom Mitiku

https://t.me/yomin1_2
ጊዜ ይጠይቀናል መልስ እያዘጋጀን🤞🏻

@yomin1_2
የካልሲህ ብዛት ስንፍናህን እንጂ ሃብትህን አይገልፅም።

@yomin1_2
ላለመለያየት መዋደድ አይበቃም !

@yomin1_2
ያልወለድነው እምቢ ብሎን ሊሆን ይችላል ... የተፋታነው ስላልተስማማን ነው... ያላገባነው ልባችን ስላልሞላ ይሆናል ...

ውጪ ያልሄድነው ፕሮሰሱ ፌል አደርጎ ነው፤ አልያም ተጓ'ቶ ነው ...
ከጎናችን ከማትጠፋው ልጅ ጋር፤ ከጎናችን ከማይጠፋው ልጅ ጋር ተለያይተን ነው።

ልጅ ያልደገምነው ወይ ኑሮ ከብዶን፥ ወይ እምቢ ብሎን፥ ወይ ተስማምተን ነው።
.
.
ገብስ ገብሱን ማውራት ልመዱ!

እንዳላየናችሁ መሄድ ሰልችቶናል። የቸኮልን የምንመስለው ሆን ብለን ነው ... ላጥ ላጥ ብለን ተራምደን ስናመልጣችሁ ደክሞን ቁጭ እንላለን ...

በናንተ ምክንያት ጉራ እና ውሸት ልንጀምር ነው። ...ስልጡን ሰው ኑሮ እና ህመም ውስጥ ሳያንኳኳ ሳያስፈቅድ ዘው አይልም...ግድ ካልሆነበት...

በርግጥ እነሱ አይሰሙም እንደው ልፉ ቢለን ነው 😀
© Adhanom Mitiku

https://t.me/yomin1_2
ከትልቅ ሰው ሁሉ ምክር አትቀበሉ

ደደቦችም ያረጃሉ


@yomin1_2
“መኖር አለመፈለግ እና እራስንም ለማጥፋት አለመፈለግ፤ ይህ ስሜት እንዴት ይገለፃል?።”

             ―ኤሚል ሲዮራን


@yomin1_2
የነበርን ቀንበር መሸከም ከበደኝ
ከውልደት እስከ ሞት እየተከተለኝ !


#ኢዮብ_ዮሚን

@yomin1_2
የከበበህ ሁሉ
ዛሬን ያዋዋለህ
የሳቀልህ ሁሉ
ደስታ የተካፈለህ
የቸገረህ ለታ
በዙሪያህ አይኖርም
የከበበህ ሁሉ-የሳቀልህ ሁሉ
ወዳጅ አይሆንህም
ዛሬ የሚያዋውል
አለ በገፍ በገፍ
የኖረህ ጊዜማ
ያገኘህ ጊዜማ
ይሰለፋል በጥፍ
ያጠፋፋልሃል
ያለህን አንድ ባንድ
ያቅበዘብዘዋል
ይቃጠዋል ሊሰግድ
አሁን አሁንማ
ኖረህ ተገኝ አንጂ አታጣም አሽቃባጭ
አዚም አዛም ስትል
አንተ እንደፈለከው ሁሌ ተለዋዋጭ
ትመለከታለህ
ሳትቀልድ ሲስቁ
የወደቅህ ጊዜ
ፈጥነው ሚሳለቁ
ትመለከታለህ
ላንተ የሚታገል
ጊዜ የጣለህ ቀን
ፍቅሩን ሚከለክል
ትመለከታለህ
ላንተ ኋኝ ጠበቃ
ሀሜት የሚጀምር
ወድቀህ ስታበቃ
ያለህ ይመስልሃል
ወዳጆች ሁነኛ
የሆንክ ይሰማሃል
የሁሉም ጓደኛ
ሁሉም የሚወድህ
ይመስልሃል አንተው
ስላለህ ነው እንጂ
ስታጣ ስትነጣ አይኖርም አንድም ሰው
የከበበህ ሁሉ
ዛሬን ያዋዋለህ
የሳቀልህ ሁሉ
ደስታ የተካፈለህ
የቸገረህ ለታ በዙሪያህ አይኖርም
የከበበህ ሁሉ
የሳቀልህ ሁሉ ወዳጅ አይሆንህም



ምኢክእይአስ(mirak)

@yomin1_2
ላመነ ይሆንለታል ለጸና ግን ይጸድቅለታል!

@yomin1_2

记录

19.05.202523:59
1.5K订阅者
28.02.202523:59
1000引用指数
09.05.202520:47
1.8K每帖平均覆盖率
10.05.202514:41
1.8K广告帖子的平均覆盖率
30.03.202515:45
17.09%ER
27.02.202510:55
136.85%ERR
订阅者
引用指数
每篇帖子的浏览量
每个广告帖子的浏览量
ER
ERR
DEC '24JAN '25FEB '25MAR '25APR '25MAY '25

✍ዮ_ሚን 热门帖子

22.04.202521:24
ከአምስት አመት በፊት ለትዳር አላማ
“ዊንታ” ከምትባል ቆንጆ ኤርትራዊት ልጅ ጋር ተገናኘው። ያንን የትዳር አላማ ለማሟላት የህክምና ሙያዬ በቂ ነው ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን ዊንታ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ነበራት።

በጥያቄ ታጣድፈኝ ጀመር፦“በትርፍ ግዜ የምታሳልፋቸው ሆቢዎች አሉህ?”

-አይ

“ፊልሞችን ትመለከታለህ?”

-አይ

“ሌሎች ቦታዎች ጉዞ አድርገህ ታውቃለህ?”

-አይ

“መፅሃፍት ታነባለህ?”

-አይ

“ተራራዎችን ወጥተ ታውቃለህ?”

-አይ

“ታድያ በትርፍ ጊዜህ ምንድነው የምታደርገው?”

-ትርፍ ጊዜ የለኝም በስራ ነው የማሳልፈው።

ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ እንዲህ አለች፦“አየህ አንተ ተራ ሰው ነህ!። ተራ ባትሆን ባንተ ላይ ፍላጎት ይኖረኝ ነበር።”

እነዚያ ቃላት ጭንቅላቴን እንደ ነጎድጓድ መታው።15 አመታትን ብዙ የህክምና መጽሃፍቶች ሳገላብጥ አሳልፌ በመጨረሻም “ተራ” የሚባል ማዕረግ አገኘሁ!።

ወደ ቤት ተመለስኩ እና በዚያ ምሽት እንቅልፍ እንዳልተኛሁ አስታውሳለሁ። በጠዋቱ ወደ አውሮፓ ለመሄድ ትኬቴን ቆርጬ በፕሌን ተጓዝኩ። በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ነገሮችን አድርጌ ወደ አገር ቤት ተመለስኩ። ስመለስ አዕምሮዬ ላይ የመጣው ቀጥታ ዊንታን ማግኘት ነበር። ነገር ግን ይህ ሁኔታ ብቻ በቂ እንዳልሆነ ገባኝ። ብዙ መፅሃፍቶችን ማንበብ አለብኝ። ቤት ውስጥ ራሴን አግልዬ በደርዘን የሚቆጠሩ የፍልስፍና፣ የታሪክ እና የሶሺዮሎጂ መጽሃፎችን በማንበብ ግዜዬን አሳለፍኩኝ።

ከጨረስኩ በኋላ “ይህ በቂ አይደለም” አልኩና ለአንድ ወር ያህል በጣም አስፈላጊ የሆኑ ፊልሞች መርጬ አየሁ። ስጨርስ “ይህ በቂ አይደለም” አልኩና ፈረስ ግልቢያ፣ ሙዚቃን፣ ዲዛይንን፣ ፎቶግራፍን ተማርኩ እና ብዙ አስደናቂ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችን እስከሚዋሃደኝ ድረስ ተለማመድኩ።

ስጨርስ ይህ በቂ አይደለም አልኩኝና ወደ ተራራ ጫፍ መውጣት እንዲለብኝ ወሰንኩኝ። ከሁለት ሳምንት አድካሚ ጉዞ በኋላ ወደ ተራራው ጫፍ ደረስኩና እጆቼን ዘርግቼ ጭንቅላቴን ቀና አደረኩኝ። በርግጥ ይህ በቂ እንደሆነ ተሰማኝ፤ ነገር ግን በድንገት ወደ ዊንታ የመመለስ አምሮቴ እሬት እሬት አለኝ።

ምክንያቱም እኔ ባለብዙ ሆቢዎች ባለቤት ሆንኩ ዊንታ ደግሞ ተራ ሴት ሆነችብኝ።


         አመሰግናለሁ ዊንታ..🚶🏼🙏😌

https://t.me/yomin1_2
11.05.202504:47
የካልሲህ ብዛት ስንፍናህን እንጂ ሃብትህን አይገልፅም።

@yomin1_2
05.05.202518:18
ከትልቅ ሰው ሁሉ ምክር አትቀበሉ

ደደቦችም ያረጃሉ


@yomin1_2
30.04.202512:12
“መኖር አለመፈለግ እና እራስንም ለማጥፋት አለመፈለግ፤ ይህ ስሜት እንዴት ይገለፃል?።”

             ―ኤሚል ሲዮራን


@yomin1_2
13.05.202516:14
ጊዜ ይጠይቀናል መልስ እያዘጋጀን🤞🏻

@yomin1_2
27.04.202518:38
ላመነ ይሆንለታል ለጸና ግን ይጸድቅለታል!

@yomin1_2
20.04.202519:44
አብዛኛውን ግዜ ደካማና የተሰበራችሁ እንደሆናችሁ ከተሰማችሁ ከፈጣሪ በጣም መራቃችሁን እወቁ። ከጠንካራው የራቀ እንዴት ይበረታል?፤ ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ የራቀ ሰው በሁሉም ነገር ይሰበራል!።


@yomin1_2
13.05.202516:53
የማንም ጓጆ በእውነት ብቻ አልተሰራም ። እውነት በመውደድ ፊት አቅም የለውም ። እውነት ላይ ክችች ያሉ ሰዎች ቤታቸው ሲፈርስ ፣ ከስራ ሲባረሩ ፣ ስራ ሲበላሽባቸው ነው ያየሁት ....

Undeniable truth !!

የሞቀ ቤት ያላቸው ብዙ ቤታቸውን ሊያቀዘቅዘው የሚችል ነገር ታግሰው ነው !! ሳድግ ያየሁት ጥበብ እሱን ነው ። መኖር ያሳየኝ እውነት ይሄ ነው ።

የሚያኖረው መለሳለሳችን ነው !!

ደረቅ እውነት አያሸንፍም። እውነት ብቻውን አያሻግርም ። እሚያኖረን ጥበባችን ነው ። የጎጆ መሰረት እውነት አይደለም መተላለፍ ነው።

ሁሉም የሞቀ ቤት ውስጥ የታለፈ ፣ይቅር የተባለ አደባባይ የማይነገር፣ ያልተነገረ ገበና አለ ።
እየተላለፍን ! ✋
© Adhanom Mitiku

https://t.me/yomin1_2
27.04.202509:13
ሳይገባኝ ስላኖርከኝ ተመስገን🙏

@yomin1_2
10.05.202507:03
ላለመለያየት መዋደድ አይበቃም !

@yomin1_2
24.04.202506:08
The hardest thing is not doing what you want—it’s knowing what you want. 🦅💪🏿

@yomin1_2
25.04.202522:11
እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ህይወት
ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው..


ኢዮብ 42:12

@yomin1_2
21.04.202509:04
ለሆነ ሰው የትዳር አጋር መሆን ሳይሆን
የሆነ ሰው ልብ ውስጥ ለዘላለም መቀመጥ ነው ማሸነፍ !


@yomin1_2
ሕያዉን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል በዚህ የለም። የሰው ልጅ በሃጢያአተኞች እጅ ኣልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛዉም ቀን ሊነሣ ግድ ነው ሉቃ 24:5-7

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏🙏

@yomin1_2
17.05.202519:09
እንኳን ተገናኘን....
እንኳን ተለያየን....
እንኳን ሁሉን አየን....

እሰየው!

እኛስ ተገናኝተን
ተፋቅረን ጨረስነው
ስንት አለ መሰለሽ
የፍቅርን ጣዕም
በቅጡ ያላወቀው።

@yomin1_2
登录以解锁更多功能。