Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Ethiopian Digital Library avatar

Ethiopian Digital Library

በዚህ ቻናል ስለ
👉ትምህርት፣
👉ሥራ እና
👉ማህበራዊ ጉዳይ
መረጃ ያገኛሉ!
Contact: @ethiodlbot
TGlist reytingi
0
0
TuriOmmaviy
Tekshirish
Tekshirilmagan
Ishonchnoma
Shubhali
JoylashuvЕфіопія
TilBoshqa
Kanal yaratilgan sanaКвіт 11, 2025
TGlist-ga qo'shildi
Квіт 11, 2025
Muxrlangan guruh

Rekordlar

10.04.202511:35
71.5KObunachilar
11.04.202511:35
100Iqtiboslar indeksi
23.04.202523:59
7KBitta post qamrovi
23.04.202516:02
7KReklama posti qamrovi
21.04.202523:59
2.66%ER
12.04.202513:07
9.21%ERR

Rivojlanish

Obunachilar
Iqtibos indeksi
1 ta post qamrovi
Reklama posti qamrovi
ER
ERR
БЕР '25БЕР '25БЕР '25БЕР '25КВІТ '25КВІТ '25КВІТ '25

Ethiopian Digital Library mashhur postlari

15.04.202510:44
ሰሙነ ሕማማት እና የቀናት ስያሜዎች

የዐብይ ጾም የመጨረሻው ሳምንት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ያሉት ቀናት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ። በነዚህ ቀናት የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብ ሲሆን፤ ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ በማዜም ቀኑን ሙሉ በስግደትና በጸሎት ያሳልፋሉ።

ካህናተ ቤተክርስቲያን ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ አምስት ሺህ 500 ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። በዚህ ሳምንት ከክርስቶስ ልደት በኋላ የመጡት የድኅነት ምልክቶች አይደረጉም። ከሰኞ እስከ ትንሳኤ ዋዜማ ያሉት ስድስቱ የሰሙነ ሕማማት ዕለታትም ትርጉም ተሰጥቷቸው ይታሰባሉ፡፡

☄️ ሰኞ:- ርግመተ በለስ እና አንጽሖተ ቤተመቅደስ ትባላለች።

በዚህ ዕለት ኢየሱስ ክርስቶስ ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ። ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ ያስወጣበት ዕለት ነው።

☄️ ማክሰኞ:- የጥያቄና የትምህርት ቀን ትባላለች።

ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ? ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። በዕለተ ማክሰኞ በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ትባላለች።

☄️ ረቡዕ፡- ምክረ አይሁድ፣ የመልካም መዓዛ እና የእንባ ቀን ይባላል። ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል።

የመልካም መዓዛ ቀንም መባሉ ደግሞ በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቶዋ ማርያም) ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ነው።
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማየእንባ ቀን ይባላል።

☄️ ሐሙስ:- ፀሎተ ሐሙስ፣ ህጽበተ ሀሙስ፣ የምስጢር ቀን፣ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ እና የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

ፀሎተ ሐሙስ ጌታ ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል። ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። የምስጢር ቀን ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

☄️ ዓርብ:- የስቅለት ዓርብ እና መልካሙ ዓርብ ይባላል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና የስቅለት ዓርብ ይባላል። ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታ በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

☄️ ቅዳሜ:- ቅዳም ስዑር፣ ለምለም ቅዳሜ እና ቅዱስ ትባላለች።

ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ትባላላች። ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን፤ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲዖል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

Credit: GazettePlus

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
09.04.202512:35
#Inbox

ደደብ በመሆኔ ተመስገን


ጎበዝ ተማሪ ብሆን ኖሮ በ 9000 ብር ደሞዝ አማርር ነበር። ትምህርቴን ከ9 ነው ያቋረጥኩት አሁን ላይ የዶክተሮችን የወር ደሞዝ በቀን ላገኘው እችላለሁ :: ብቻ ደደብ በመሆኔ ፈጣሪን የማመስግንበት ቀን ይመጣል ብዬ አስቤ አላውቅም። ተመስገን!

Credit: Gursha Page

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ከ38 ዓመት በኋላ በድጋሜ ኑ ተፈተኑ ተባለ

ኔዘርላንድ ወስጥ በ1987 የባዮሎጂ የመውጫ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ ሊጠሩ ነው። የተሰጠው ምክንያት ደግሞ የባዮሎጂ ፈተና መሰረቁ ተረጋግጧል የሚል ነው።

ይህ እንግዲህ የተረጋገጠው ከ38 ዓመት በኋላ ነው። የያኔዎቹ ተማሪዎች ዛሬ እድሜያቸው 55 ደርሷል ።

ባለስልጣኑ ለሁሉም ጥሪ እንደሚደረግና ፈተናውን በድጋሜ እንደሚወስዱ ገልፀው ፣ ካልወሰዱ ግን ዲፕሎማቸው ሙሉ እንደማይሆን አስጠንቀቀዋል ።

ከ38 ዓመት በኋላ በድጋሜ ተፈተኑ ብትባሉ ምን ትላላችሁ? በሚል ብዙዎች እየተነጋገሩበት ነው።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሐሙስ ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም. በትምህርት ቤት ዙሪያ በደረሰ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።

በዞኑ እናርጅ እናውጋ ወረዳ ገደብ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ የትምህርት ቤት አጥር ለማጠር እና ቤት ለመሥራት 'ለልማት ሥራ' የወጡ "ሰላማዊ ሰዎች" በጥቃቱ መገደላቸውን ገልፀዋል።

የአካባቢው አስተዳደር ግን ጥቃቱ በአካባቢው ተሰብስበው በነበሩ የፋኖ ታጣቂዎች ላይ እንጂ በንፁሃን ነዋሪዎች ላይ አለመፈጸሙን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃት ክትትል እያደረገ መሆኑን አመልክቷል።

BBC News Amharic

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የሁዋዌ ቴክፎርጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸነፉ

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል።
ውድድሩ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየውና በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎችን ካካተተው ዝግጅት ጋር የተካሄደ ሲሆን ውጤቱ ይፋ የተደረገው ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ከአዲስ አበባ፣ ሃራማያ፣ ጅማ፣ ወልቂጤ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች አሰባስቧል። በውድድሩም ከሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ አርጀንቲና አየርላንድ፣ ማላዊ፣ ቬትናም፣ አረብ ኤምሬትስ እና ሌሎችንም ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ 12 ልዩ ቡድኖች ጋር ተወዳድሯል። የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋም በዝግጅቱ በእንግድነት ተገኝታለች።

ተማሪዎቹ የእንስሳትን ህመሞች አስቀድሞ ለመለየት በተዘጋጀውና በአርተፊሻል አስተውሎት በጎለበተው ኤርሊ ቬት (EarlyVet) በተሰኘው ፕሮጀክታቸው የተወዳደሩ ሲሆን በዚህም ትኩረት ለመሳብ ችለዋል።
ይህ የፈጠራ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በተለይም ግብ 2 "ዜሮ ርሃብ" እና ግብ 15 "ህይወት በምድር" ከሚለው ጋር የተጣጣመ መሆኑና በግብርና እና በእንስሳት ጤና ላይ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን በውድድሩ ተብራርቷል።

የሁዋዌ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ሊሚንግ ዬ በቡድኑ ስኬት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ድሉ የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ልዩ ችሎታ እና ፈጠራ የታየበት ነው ብለዋል። አክለውም መጪው ትውልድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የቴክኖሎጂ ገጽታ ውስጥ እንዲበለጽግ በሚያስፈልገውን ድጋፍ እና እድሎች ማመቻቸቱን ለማስቀጠል ሁዋዌ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ቡድኑ ለዓለም አቀፋዊ ውድድር እድል ያገኘው በግንቦት 2016 ዓ.ም በኤሳውራ ሞሮኮ በተካሄደው የክፍለ አህጉራዊ የቴክፎርጉድ (Tech4Good) ውድድር ወቅት ከ17 የአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ 28 ቡድኖች ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በወጣበት ወቅት መሆኑ ይታወሳል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2008 የተጀመረው የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ፕሮግራም በአገር ውስጥ ያለውን ውድድር ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጅ ሲሆን ለተሳታፊ ተማሪዎች ከውድድር ባለፈ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI)፣ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ፣5ኛ ትውልድ: ሳይበር ደህንነት፣ አይኦቲ እና ቢግ ዳታን ጨምሮ በቴክኖሎጂዎች ላይ አጠቃላይ ስልጠና የሚወስዱበት እድል ያመቻቻል።

#MoE

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የscholarship እድል የሚያስገኘው የALX Pathway ፕሮግራም ምዝገባ ሊያልቅ 4 ቀን ብቻ ቀረው!

የALX ‘Pathway’ ፕሮግራምን በመውሰድ፣ የአለምአቀፍ ዲግሪ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ እድል ለማግኘት ይመዝገቡ። የዚህ ስኮላርሺፕ እድል በጥቅሉ በአመት የ85,000 አሜርካን ዶላር፣ ወይም የ11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር፣ ተመጣጣኝ ዋጋ አለው።

ALX ከ14 በላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት አለው። አብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙት America ሲሆን፣ በEurope እና South Africa የሚገኙም አሉ።

የዚህ የትብብር ስምምነት ዋና ይዘት፣ የALX Pathway ኘሮግራምን በስኬት የሚጨርሱ ልጆች፣ በእነዚህ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት እና የስኮላርሺፕ እድሎች የሚያገኙበትን መንገድ ማስፋት ነው።

የምዝገባውን ሂደት ደረጃ በደረጃ ማብራሪያ ለማየት፣ እንዲሁም ምዝገባውን በተሳካ ሁንያ ለማጠናቀቅ፣ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ፡- https://t.me/ALXScholarship2ndBatch.

ወደ ምዝገባው ቀጥታ ለመሄድ ይህንን ተጫኑ - https://www.alxafrica.com/join-pathway/
10.04.202511:13
“መምህራን እየተራቡ የትምህርትን ጥራት ማረጋገጥ አይቻልም” መምህራን

ለዩኒቨርሲቲ መምህራን እየተከፈለ ያለው ክፍያ ከአንድ የባንክ ቤት የጥበቃ ሰራተኛ ያነሰ ነው!

“የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ትምህርትን ለማሻሻል በጣም ወሳኝ ነው” የትምህርት ሚኒስቴር


ትውልድ ፊደል ቆጥሮ ከህልሙ እንዲደርስ መንገድ ጠራጊው፣ አቅጣጫ ጠቋሚው መምህር ለሞያው የሚከፈለው ክፍያ ዝቅተኛ በመሆኑ ለማስተማር ፍላጎት እንዲጣ ምክንያት እንደሆነ ጥናት አሳይቷል፡፡ በደባርቅ ዩኒቭርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ ፈለቀ ወርቁ “የዩኒቭርሲቲ መምህራን ሀገር እንድትቀጥል የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረው ይህን ማድረግ የሚችሉት ግን ሳይርባቸው ማስተማር ሲችሉ ነው” ብለዋል፡፡

“የዩኒቨርሲቲ መምህራን እየተራቡ ሀገርን አያስቡም ያሉት መምህሩ አሁን ለመምህራን እየተከፈለ ያለው ክፍያ ከአንድ የባንክ ቤት የጥበቃ ሰራተኛ ያነሰ ነው” ሲሉ ነግረውናል፡፡ በዚህም ምክንያት መምህሩ ሞያውን ለቆ ወደ ሌላ ስራ እየገባ ነው ያሉት አቶ ፈለቀ ወርቁ ‘’መምህሩ ኑሮ አይደለም እየኖረ ያለው  ከኑሮ በታች ነው’’ ብለዋል፡፡ የመምህር ኑሮ በቃል የሚገለጽ አይደለም ከሚያስተምረው የሚማረው ተማሪ የተሻለ ለብሶ እየገባ፣ የተሸለ ኑሮ እየኖረ በሁሉ ነገር ዝቅ ያለ መምህር እንዴት ተማሪ ፊት ቆሞ ነው ማስተማር የሚችለው? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ‘’መምህሩ ዛሬ የተቀደደ ሱሪ ነው ልብሶ የሚሄደው ካለሲ መቀየርያ አጥቷል’’ ሲሉ መምህሩ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፍተና ውጤት ማሽቆልቆልን ምክንያት ለማውቅ ያስጠናው ጥናት መምህራን የሚከፈላቸው ክፍያ ዝቅተኛ መሆኑ የማስተማር ፍላጎታቸው ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን የጠቆመ ነበር፡፡ ጥናቱ ለውይይት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በቀረበበት ወቅትም በወይይቱ የተሳተፉ የትምህርት ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ መምህራን እና የምክርቤት አባላት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የመምህሩን ኑሮ ማሻሻል ተገቢ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በወቅቱ የተገኙት እና ማብራሪያ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የመምህራንን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ከፋይናንስ ሥርዓት ጋር ለማስተሳሰር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ይሁንና የመምህራን የደመወዝ ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ቢደርስም ለዓመታት እልባት ሳያገኝ የቀጠለ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ሸገር ኤፍኤም

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በ2017 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.04.202512:14
የዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ ደሞዜ 99 ዶላር ነው:: ይህ ደሞዝ ዝቅተኛ ብቻ ሳይሆን ኢምሞራላዊም ነው! መምህራን ለልጆቻቸው መሆን አልቻሉም! ኢምሞራላይዝድ የሆነ መምህር ይዘህ ነገ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ያፈራሉ ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው::

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የውጭ አገር የትምህርት ዕድል ያገኘውን ጓደኛውን በመርዝ ገደለ

በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የዘንድሮ ተመራቂ የነበረው ውብሸት አስቤ ከአሜሪካ ፊሊድያ ዩንቨርስቲ ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ ለጉዞ እየተዘጋጀ ባለበት የቅርብ ጓደኛው ዶርም ውስጥ #በመርዝ እንደተገደለ የአስክሬን ውጤቱ ያሳያል።

ወጣት ውብሸት እጅግ በጣም ትሁትና ታታሪ መሆኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ። ይሁን እንጂ በጉብዝናውና በመልካም እድሎቹ ላይ በመቅናት እጅግ በሚከረፋ መርዝ ህይወቱን ነጠቁት።

በአረብ ሀገር እየለፋች ያስተማረችው እህቱ በወንድሟ ፅኑ ተስፋ የነበራት ቢሆንም በምቀኝነትና በክፋት ተነሳስተው የወንድሟን ነፍስ ፣ ህልሙንና ተስፋውን በማጨናገፋቸው ከመሞት ያልተናነሰ ተስፉ መቁረጥ ውስጥ ትገኛለች። እጅግ ከባድ የመንፈስ ስብራት ደርሶባታል።

በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይህንን ከባድ ወንጀል የፈፀመው ተጠርጣሪ ጓደኛው የህግ ጠበቃ ይዘው የተከራከሩ ሲሆን በሟች ቤተሰብ በኩል "ቸልተኛ" አቃቤ ህግ ብቻ በመሆኑ #ገዳይ ከእስር ሊፈታ ጫፍ ደርሷል።

የሟች ቤተሰብ ተስፋና ማረፊያቸው የነበረውን ወጣት ልጃቸውን መነጠቃቸው ሳይበቃ ጭራሽ የልጃቸው ገዳይ በነፃ መፈታቱ የእግር እሳት የሆነ ህመምና ለልጃቸውም ሁለተኛ ሞት ነው።

Sentayehu Hailu

https://www.youtube.com/watch?v=yJ8dwVf1NA0

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
Dr. Seid Adem እባላለሁ፡፡ ስራ ከጀመርኩ አንድ አመት ሆኖኛል፡፡ በ6ኛ ወሬ እናቴ ደውላ "ልጄ መጥቼ ልይህ?" አለች፡፡ ደነገጥኩ!! አትምጭ እናቴ እኔ መጥቼ አይሻለሁ ብዬ መለስኩላት፡፡ እሷም የቅሬታ በሚመስል ድምፅ "እሺ" አለችኝ፡፡

አትምጭ ያልኳት ሀኪም ሆነልኝ ያለችኝ እናቴ የምኖረውን ህይወት አይታ ልቧ እንዳይሰበርና እንዳታዝን ነበር፡፡ ቤት ውስጥ ከአንድ ፍራሽ ውጭ ምንም ነገር የለኝ... ምን ላይ ታርፋለች? እስካሁን እኔም ሄጄ አላየሗት፡ ምን ይዤ ልያት!

Credit: hakim

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
19.04.202506:44
" የ12ኛ ክፍል ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው  " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ፥ " ይሄ አራተኛው ነው በአዲሱ የፈተና አሰጣጥ ፈተና የሚሰጥበት " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከትምህርት ቤቶች ወጥቶ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስገብቶ ፈተና እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ስለዘንድሮው የ2017 ዓ/ም ፈተና በተናገሩበት ወቅት 150 ሺህ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይ እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) ፥ " እንደ ከዚህ ቀደሙ አድካሚ በሆነ ከቦታ ቦታ ልጆችን እያዘዋወሩ ከመሄድ ባለፈው ዓመት 29 ሺህ ተማሪ ነበር ኦንላይን ፈተና የሰጠነው ዘንድሮ ደግሞ 150 ሺህ ተማሪ ኦንላይን ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጀን ነው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ቆርጠው ባይናገሩም ፈተናው ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንዲሰጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከ177 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 47,790 (27%) ብቻ ናቸው ::

#Exit_Exam_Result

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
O'chirildi12.04.202510:55
14.04.202511:22
ዘንድሮ 150,000 ተማሪዎች 12ኛ ክፍል በኦላይን (online) ይፈተናሉ :: የፈተናው ጊዜ አንድ ወር ተኩል አካባቢ ይቀረዋል:: 84,000 መምህራን በክረምት ስልጠና ይወስዳሉ::

Prof. Birhanu Nega

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
Ko'proq funksiyalarni ochish uchun tizimga kiring.