Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Big Habesha Tech avatar
Big Habesha Tech
Big Habesha Tech avatar
Big Habesha Tech
O'chirildi23.04.202522:02
የscholarship እድል የሚያስገኘው የALX Pathway ፕሮግራም የመጨረሻ ምዝገባ ቀን!!

የALX ‘Pathway’ ፕሮግራምን በመውሰድ፣ የአለምአቀፍ ዲግሪ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ እድል ለማግኘት ይመዝገቡ። የዚህ ስኮላርሺፕ እድል በጥቅሉ በአመት የ85,000 አሜርካን ዶላር፣ ወይም የ11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር፣ ተመጣጣኝ ዋጋ አለው።

ALX ከ14 በላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት አለው። አብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙት America ሲሆን፣ በEurope እና South Africa የሚገኙም አሉ።

የዚህ የትብብር ስምምነት ዋና ይዘት፣ የALX Pathway ኘሮግራምን በስኬት የሚጨርሱ ልጆች፣ በእነዚህ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት እና የስኮላርሺፕ እድሎች የሚያገኙበትን መንገድ ማስፋት ነው።

የምዝገባውን ሂደት ደረጃ በደረጃ ማብራሪያ ለማየት፣ እንዲሁም ምዝገባውን በተሳካ ሁንያ ለማጠናቀቅ፣ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ፡- https://t.me/ALXScholarship2ndBatch.

ወደ ምዝገባው ቀጥታ ለመሄድ ይህንን ተጫኑ - https://www.alxafrica.com/join-pathway/
#Phone_tip

የስልካችሁ status bar ጥግ ላይ አረንጓዴ ነጥብ ሲበራ አስተውላችሁ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ይቺ ነጥብ አንሮይድ 12 በላይ በሆኑ ስልኮች የምትገኝ ሲሆን እየበራች ምልክት የምትሰጠውም የስልኩ camera እና microphone ሲከፈቱ ወይም መቅዳት ሲጀምሩ ነው።

የነጥቧ ዋና ጥቅም የስልካችን camera ወይም microphone ለኛ በማሳወቅ ደህንነታችንን ይበልጥ ታጠናክራለች።

ነገር ግን ይቺ ነጥብ እና ከሁለት አንዱ ማለችም camera ወይም microphone ሳትከፍቱ የምትበራ ከሆነ የናንተ ምስል ወይም ድምፅ እየተቀዳ ሊሆን ይችላል። ይህንንም ለማስቆም permission የሰጣችኋቸውን መተግበሪያዎች check ማድረግ ይኖርባችኋል። ይሁን እንጂ ስልካችሁ ውስጥ ያሉ መተግበሪያዎች ላይ ድምፅ ስትቀዱ እና ፎቶ ስታነሱ የምትበራ ይሆናል።

©bighabesha_softwares
ማንኛውንም የYouTube ቪዲዮ download ማድረግ ከፈለጋችሁ ይህንን website ተጠቀሙ።
https://cobalt.tools/

ዌብሳይቱን ከከፈታችሁ በኋላ download የምታደርጉትን የYouTube link በማስገባት Video ወይም audio ማውረድ ትችላላችሁ።
15.04.202517:10
Good lock app ሳምሰንግ ስልካችንን እንደተመቸን customize አድርገን እንድንጠቀም የሚያስችለን application ነው።

በውስጡ የተለያዩ ተግባራትን የሚያስጠቅሙ በጣም ብዙ plugins ይዟል።
⚫One hand operation
⚫Theme pack
⚫Wonderland
⚫LockStar
⚫Keys Cafe
⚫HomeUp
⚫Nice Shot
⚫Routines +
⚫Navstar
⚫Camera assistant
⚫Quick start
⚫Edge lightning+
⚫Dropship
⚫NotiStar
⚫Edge Touch

እነዚህ ፕለጊኖች ስልካችንን ደስ በሚሉ ፊቸሮችን ያስውባሉ።

ለምሳሌ፥
✔️የስልካችን keyboard customize ለማድረግ Theme park እና Keys cafe
✔️Home screen customize ለማድረግ ደግሞ Theme park, Home Up, Wonderland
ሌሎችን እናንተ ሞክሯቸው።

➡️ሁሉም ስልክ ላይ አልተለቀቀም ጠብቁ።
የSocial media አንድ ከፍተኛ ችግሩ ብዙዎች የመንጋ አስተሳሰብ እንዲላበሱ ማድረጉ ነው።

አንድ ሰው የተናገረውን ሁሉም በጅምላ ይናገሩታል። አንዱ የቀለደውን ሌሎች ቋቅ እስኪለን እየደጋገሙ ይቀልዱታል።

በተለይ አሁን አሁን የኢትዮጵያ ቲክቶክ ለየት ያለ content እየጠፋ የተወሰኑ ቪዲዮዎችን scroll ካደረጋችሁ በኋላ ሌላው አንድ አይነት ነው። 
ከcontent በተጨማሪ  ከቪዲዮው ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የcomment አይነቶች ስታዩ ሰውን ምን ነካው ያስብላሉ።

የተወሰኑ ሰዎችን ባህሪ አይተህ ሌሎችን መገመት አይከብድህም። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የራስ ሃሳብ የግል ፈጠራ የሚባል ነገር እየጠፋ ነው።

አስተውላችሁ አታውቁም?
ጎረቤታችን ሶማሊያ ለSTARLINK የስራ ፈቃድ ሰጠች።

የሶማሊያ ብሄራዊ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ስታርሊንክን በመላ ሀገሪቱ የሳተላይት የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር በይፋ ፍቃድ ሰጥቷል።

በሞቃዲሾ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ የስታርሊንክ ተወካዮች አገልግሎቱ በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፣ ይህም ከከተማ ርቀው በሚገኙ ገጠራማ የሀገሪቱን ክልሎች የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስፋት ይረዳል።

ምንጭ: Bloomberg

ከዚህ በፊት ስለ Starlink የፃፍነውን አንብቡ።
https://t.me/bighabesha_softwares/2771

እኛ ሀገር የሚጀመር ይመስላችኋል? 😋
19.04.202508:11
መሰረታዊ የprogramming language እውቀት የምታገኙባቸው ጠቃሚ ዌብሳይቶች

https://www.geeksforgeeks.org/

https://quickref.me/

Check አድርጓቸው።
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመከባበርና ለሰራነው ሃጥያት ይቅርታ የምናገኝበት ያደርግልን።

መልካም በዓል!!
Spotify Fix update 🔥🔥🔥

Spotify Logout እያደረጋችሁ ከሆነ ይህን app ተጠቀሙ። ቀጥታ update ማድረግ ትችላላችሁ።

ከዛ Manually Login አድርጉ።


Download link
https://t.me/big_habesha/289
Good Lock app ኢትዮጵያ ውስጥ መስራት ጀምሯል።

ስልካችሁ Samsung ከሆነ Samsung store ላይ ግቡና download አድርጉት።

ካልሰራላችሁ ትንሽ ቀን ጠብቁ ለሁሉም ይለቀቃል።
14.04.202512:04
በሚመጡት ጥቂት አመታት ውስጥ አዲስ ከሚመጡ የስራ ዘርፎች ውስጥ prompt engineering አንዱ ነው።

እያንዳንዱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተጠየቀውን ጥያቄ የሚመልሰው እኛ በምናስገባለት ፅሁፍ ላይ የተወሰነ ነው። ስለዚህ Prompt engineering ማለት አንድ AI Large Language Model (LLM) የተሻለ ውጤት እንዲሰጥ ምን አይነት ጥያቄ እናስገባ የሚለውን የምናጠናበት ዘርፍ ነው።

አለማችን በAI LLM እየተጥለቀለቀችበት ባለችበት በዚህ ዘመን ይህ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ መጥቷል።
ሰሞኑን Google በPrompt engineering ላይ ትኩረት የሚያደርግ ባለ 69 ገፅ ዶክመንት ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህ ዶክመንት መሰረታዊ የPrompt engineering መረጃዎችን ይዟል።

ዶክመንቱን ከላይ አያይዘንላችኋል።
13.04.202511:17
engineering ተማሪ ከሆናችሁ እነዚህን ድረገጾች ሞክሯቸው። (part 1)

ለcivil engineering፦
CivilDigital.com ከዚህ ፊልድ ጋር የተያያዙ የተለያዩ መፅሀፎች፣ PowerPoint, መረጃዎች እና ቲቶሪያሎች ታገኙበታላችሁ።

structville.com ስለ civil engineering በርካታ articles, researchs, እና ሯርካታ መረጃዎችን ትቀስሙበታላችሁ።

ለSoftware Engineering፦
stackoverflow.com የprogramming ልምዳችሁን ለማካበትና የተለያዩ bugs ለመቅረፍ ያስችላችኋል።

leetcode.com ከcoding ትምህርት በተጨማሪ ለinterview ለመዘጋጀትና ለተያያዩ Algorithms ለመለማመድ ጥሩ website ነው።

ለwater engineering፦
www.wateronline.com water ነክ የሆኑ ዜናዎች፣articles፣ ትምህርታዊ መረጃዎችን ታገኙበታላችሁ።

ለtextile engineering፦
textiletoday.com.bd ይህንን መስክ የተመለከቱ ዜናወሸችና መረጃዎችን ታገኙበታላችሁ።

©bighabesha_softwares
Number: 0950520860
17.04.202510:20
የተለያዩ Programming languages እና ጥቅማቸው

Java
✔️Android apps
✔️Desktop apps (e.g., using JavaFX, Swing)
✔️Web apps (e.g., using Spring framework)
✔️Big data (used in Apache Hadoop ecosystem)

Swift
✔️iOS Apps
✔️macOS Apps
✔️Client-side development

Python
✔️Web apps (Django, Flask)
✔️Machine learning (TensorFlow, scikit-learn)
✔️Data science (Pandas, NumPy, Matplotlib)
✔️Artificial intelligence
✔️Cybersecurity (used in automation, scripting, penetration testing)

C#
✔️Game Development (Unity engine)
✔️Desktop Applications (via .NET and Windows Forms/WPF)
✔️Enterprise Applications (e.g, with ASP.NET)

C++
✔️Operating Systems
✔️Database Engines (MySQL, MongoDB internals)
✔️Embedded Systems
✔️Game Engines (Unreal Engine)

JavaScript
✔️Web Development (client-side and server-side with Node.js)
✔️Server-side Apps
✔️Web Servers  (with Node.js or Deno)
✔️Mobile Applications  (via React Native, Ionic)

እናንተ የምታቋቸው ሌሎችን comment ላይ ፃፉ በPart 2 እንመለሳለን።
Android ስልኮች ለቀናት ሳይከፈቱ ከቆዩ ራሳቸውን reboot ሊያደርጉ ነው።

የGoogle operating system የሆነው Android ተጠቃሚዎች ለሶስት ቀናት ያህል ስልኩን ካልከፈቱት ራሱን በራሱ reboot ያደርጋል።

ይህኛው የGoogle play service feature ስልኩን Before first unlock (BFU) ሁኔታ ላይ በመመለስ የመረጃን ደህንነት ይጨምራል ተብሏል።

Reboot በሚሆንበትም ጊዜ ስልኩ በ passcode/password እስከሚከፈት ድረስ እንደ fingerprint ያሉ የተለያዩ የባዩሜትሪክ መረጃዎች አይሰሩም። ይህም ከሆነ የተለያዩ የforensic መሳሪያዎችን በመጠቀም ስልኩ መከፈት እንዳይችል ይሆናል።

እንዲሁም reboot ሲሆን የተለያዩ ከስልኩ ጋር የተገናኙ ቀላል ችግሮች ሊቀረፉ ይችላሉ። አንድ ስልክ reboot በሚሆንበት ጊዜ ምንም አይነት መረጃዎች አይጠፉም።

አሁን ላይ ይህ feature የgoogle play services የመጨረሻ update በሚያገኙ ስልኮች ላይ ይገኛል።

©bighabesha_softwares
15.04.202506:29
የengineering ተማሪ ከሆናችሁ እነዚህን ድረገጾች ሞክሯቸው። (part 2)

ለelectrical Engineering
allaboutcircuits.com ከቀላሉ ohm's law እስከ embedded system እና በርካታ circuit ነክ የያዙ ነፃ ትምህርቶችን ታገኙበታላችሁ።

circuitdigest.com circuit ፕሮጀክቶች፣ዲያግራሞች፣መረጃዎች እና ቲቶሪያሎችን ማግኘት ያስችላችኋል።

falstad.com/circuit ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የcircuit simulator website ነው።

ለmechanical engineering
ocw.mit.edu/courses ከዚህ filed ጋር የተየገኛኙ በርካታ courses,lectures እና መፅሀፎችን ማግኘት ትችላላችሁ።

www.asme.org ይህንን ድረገፅ በመጠቀም ፕሮጀክቶችን እና ዘፈመረጃዎችን ማግኘት እንዲሁም ያላችሁን network/ግንኙነት ማሳድግ ትችላላችሁ።

ለchemical Engineering
cheresources.com ትምህርታችሁን አንድ ደረጃ ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ አጋዥ መፅሀፎችና መረጃዎች የምታገኙበት ደረገፅ ነው።

©bighabesha_softwares
🧑‍💻 #GTSTv2 Round_11

WE ARE BACK ❗️

📣አሁኑኑ ተመዝገቡ!!!
Course Contents:

✅ Cyber Security Fundamentals
✅ Programming ( Python, bash, HTML ) – basic + For hackers
✅ Networking for hackers
✅ Linux/UNIX Systems
✅ Web Security Fundamentals
✅ Defensive Security Fundamentals
✅ System Penetration Testing
✅ Network Penetration Testing
✅ Report and Documentation

🔥 ለ 100 ሰው ቦታ ነው ያለዉ
👑 ትምህርት ሚያዚያ 15 ይጀመራል

🏪 ለበለጠ መረጃ + Registration ☄️

🎥LINK: https://course.geezsecurity.com

Contact Us
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 info@geezsecurity.com


#geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
ስልካችሁ ላይ በGoogle develop የተደረገ ምን application ትጠቀማላችሁ?

✍️እስኪ comment ላይ ዘርዝሩ።
19.04.202507:48
የscholarship እድል የሚያስገኘው የALX Pathway ፕሮግራም ምዝገባ ሊያልቅ 4 ቀን ብቻ ቀረው!

የALX ‘Pathway’ ፕሮግራምን በመውሰድ፣ የአለምአቀፍ ዲግሪ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ እድል ለማግኘት ይመዝገቡ። የዚህ ስኮላርሺፕ እድል በጥቅሉ በአመት የ85,000 አሜርካን ዶላር፣ ወይም የ11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር፣ ተመጣጣኝ ዋጋ አለው።

ALX ከ14 በላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት አለው። አብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙት America ሲሆን፣ በEurope እና South Africa የሚገኙም አሉ።

የዚህ የትብብር ስምምነት ዋና ይዘት፣ የALX Pathway ኘሮግራምን በስኬት የሚጨርሱ ልጆች፣ በእነዚህ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት እና የስኮላርሺፕ እድሎች የሚያገኙበትን መንገድ ማስፋት ነው።

የምዝገባውን ሂደት ደረጃ በደረጃ ማብራሪያ ለማየት፣ እንዲሁም ምዝገባውን በተሳካ ሁንያ ለማጠናቀቅ፣ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ፡- https://t.me/ALXScholarship2ndBatch.

ወደ ምዝገባው ቀጥታ ለመሄድ ይህንን ተጫኑ - https://www.alxafrica.com/join-pathway/
👑 JOIN The Future👑

የሀኪንግ ስልጠና ለመመዝገብ 🧑‍💻

🆘LINK: https://course.geezsecurity.com

✅ ለበለጠ መረጃ

✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
ℹ️ info@geezsecurity.com

#geezsecurity #geeztech @geeztechgroup
14.04.202518:57
የEBS 20-30 የወጣቶች ፕሮግራም ላይ ተጋብዤ እንደቀበጣጠርሁ ሳልነግራችሁ።🙈
Main stream media ላይ ስቀርብ የመጀመርያየ ስለነበር ነው መሰል I was not comfortable.😄
ካላያችሁት በዚህ ሊንክ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ።
https://youtu.be/ZOJKFD4pgLs?si=-hsNqtTIPf4tGftu
Zero-day exploit ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ? ምን ማለት ይመስላችኋል?

Internet ላይ search ሳታደርጉ እስኪ የምታስቡትን comment ላይ ፃፉ።
ሰሞኑን መነጋገሪያ ስለሆኑት የDirewolf ጉዳይ ሰምታችኋል?

Colossal Biosciences የተባለ የዘረመል አጥኚ ተቋም ከ13,000  አመታት በፊት የነበሩ የተኩላ ዝርያዎችን ዘረመል ከአፅማቸው ላይ በመውሰድ እንደገና ወደ ህይወት እንዳመጣቸው በስፋት እየተዘገበ ይገኛል።

በብዙዎች መነጋገሪያ የሆኑት እነዚህ 3 ተኩላዎች Romulus, Remus እና Khaleesi የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።

Game of thrones በተባለው ተከታታይ adventure ፊልም ላይ በምናብ ለህዝብ የተዋወቁት እነዚህ የተኩላ ዝርያዎች አሁን በገሀድ መመለሳቸው ብዙዎችን አስገርሟል።

በgenetic extraction የጠፋ እንስሳትን መመለስ ከተቻለ Dinosaurን ይመልሱት ይሆን? ሉሲንስ?

ይህ ነገረ ከተፈጥሮ አሰራርና አሁን ካለን አስተሳሰብ ጋር አይጋጭም ወይስ ሳይንስ የደረሰበትን ጥበብ በፀጋ እንቀበል? ምን ታስባላችሁ?

✍️ሀሳባችሁን በcomment አካፍሉን።
Ko'rsatilgan 1 - 24 dan 73
Ko'proq funksiyalarni ochish uchun tizimga kiring.