Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 avatar

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka
TGlist рейтингі
0
0
ТүріҚоғамдық
Растау
Расталмаған
Сенімділік
Сенімсіз
Орналасқан жері
ТілБасқа
Канал құрылған күніMar 18, 2023
TGlist-ке қосылған күні
Aug 22, 2024
Қосылған топ

Рекордтар

20.04.202523:59
9.9KЖазылушылар
20.03.202520:35
600Дәйексөз индексі
28.02.202513:54
1.4K1 жазбаның қамтуы
28.02.202510:35
1.4KЖарнамалық жазбаның қамтуы
29.03.202523:59
56.82%ER
10.09.202423:59
23.32%ERR

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 танымал жазбалары

07.04.202514:05
True story😁


በቅርቡ ነው የለጠጥኩት አለች አንዷ ቲክቶክ ላይ😁....እኔም ገና ሁለት ወር የቤት ኪራይ መክፈሌ ነው....

ታድያ ተከራይነት ምን ይመስላል ብትሉኝ "መከልከል ይበዛዋል" ነው መልሴ።

እኔም በሁለት ወሬ የመጀመሪያውን ክልከላ አስተናግጃለሁ.....


"ቆጣሪ በጣም እየቆጠረብኝ ነው.... ከዚህ በኃላ በስቶቭ እንዳትሰሩ...."....የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ከተሰጠን በኃላ እኔና ጎረቤቶቼ ሰይጣን ልጁን የሚድርበትን ሰአት ጠብቀን ድስታችንን ማንቋቋት ሆኗል ስራችን....

'እንደው ይቺህ ልጅ በፀሎት ነው ምትኖረው'....ብለው እንዳይሉኝ በሳምንት ሁለት ቀን ከእንቅልፍ በሚቀሰቅስ ጭስ ግቢውን አጥነዋለሁ....

እሳት ቶሎ አይያያዝልኝም(ነገረኛ ሰው መሆን ነበረብኝ 😁)


"ጎሽ....ቆቅ እኮ ነሽ....በሳምንት ሁለት ጊዜ በሰራሻት ሳምንት ምትቆዪ....አለች እንጂ የኔዋ ጉድ እንደው አፍሼ ማመጣው ነው ሚመስላት...ነጋ በርበሬውን ድፍት...ነጋ ሽሮውን ድፍት...ዘይቱን ግልብጥ....ወጡን ትጠጣዋለች ስልሽ....እንደው ምከሪያት...."....አከራዬ ልጃቸውን ያሙልኛል....


"ሙያ በልብ ነው"....የምትለዋን የእናቴ ተረት  በሆዴ ብዬ ለልጃቸው የምክር ቀጠሮ ሰጥቼ ወደስራዬ እሄዳለሁ....


የሆነ ነገር ከጉዳይ የማይቆጠረው ለካ ያ ነገር ሲኖረን ነው....ለምሳሌ ገንዘብ ያለው ሰው ገንዘብን ጉዳዬ ብሎ ከየት ላምጣው አይነት ጭንቀት አይጨነቅም....

እንደዛ ነው እኔም ላይ የሆነው።


"እስከ ዛሬ እንዴት 10 ከሰል በቀላሉ የማቀጣጠያ መንገዶች የሚል መፅሀፍ አልተፃፈም....ይሄ ነገር እኮ እንደ ሀገር የሚያሳስብ ጉዳይ ነው....." ምናምን እያልኩ ነው ቀኔን የምጀምረው.....


"ለክርስትና ልጅሽ አልብሺ እንጂ....ፋሲካ ደርሷል....ምን የመሰለ ቀሚስ ተሰቅሎ አይቻለሁ እዚ ወንዴ ጋር ብር ላኪና ለበአል ከድፎ ጋር ይዤው ሄዳለሁ....".... እናቴ በጠዋት ደውላ እንዲህ ስትለኝ ይሄን ሊያሰማኝ ነው ሲያቃዠኝ ያደረው ብያለሁ....... አላየችኝም እንጂ እንደ ማልቀስ ነገርም አርጎኝ ነበረ ..."እንኳን እናቴ ሞታ እንዲሁም አልቅሽ አልቅሽ ይለኛል" የሚለው ተረት ቦታውን ያገኘ መሰለኝ...."እንኳን ላኪ ተብዬ እንዲሁም አበዳሪ ጨርሻለሁ".....

"እኔ አሁን አልችልም ቀጣይ ልክልሻለሁ.....".....ያልኳት ማስታወሻ ደፍተሬን አውጥቼ የብድር ዝርዝሬን እያየሁ ነበር...

"ቱ ቱ ቱ አንቺስ አትረቢም....እንደ ልጄ ላሳድጋት ላስተምራት ብለሽ ቃል ገብተሽ....አንቺን ብሎ የክርስትና እናት....."....ታዘበችኝ።

"እንዴ ምን አደረግኩ....እንደ ልጄ ላሳድጋት የሚለው ቃልኪዳን በሀይማኖት ነው....በሀይማኖት ማሳደግንና በገንዘብ ማሳደግን አምታተነዋል".....አልኳት አፌን ሞልቼ....ከልቤ ነበር...

"ኡኡቴ ኪኪኪኪኪ ድንቄም....የኛ ሀይማኖተኛ....ለማንኛውም እኔ ራሴ ገዛላታለሁ ወደፊት ትሰጪኛለሽ.... ከኔ ራስ መች እኖደምትወርጂ አላቅም ወደ እናንተ የሚመጣ ሰው ካገኘሁ ቂቤ አንጥሬ እልክልሻለሁ ለበአል ".....ብላኝ ተሰነባበትን....ማሳረጊያውን ወደድኩት።

እናቴ ያልገባት አንድ ነገር አለ...ትምህርት መጨረስ ብቻ ከእነሱ ራስ አያወርደንም...እንደውም ክብደታችንን ጨምረን ነው የምንወዘፍባቸው.....

ስልኩን እንደዘጋሁት የአከራዬ ድምፅ ጆሮዬን ሰነፈጠኝ....

"ደግመህ እየው....ቆጣሪው ከተበላሸ ደግሞ ወስዳችሁ ስሩት....ተከራዮቼ ጨምሮ ሁላችንም በከሰል ነው ምንሰራው አልበዛም እንዴ....."....አከራዬ ጆሮ በሚሰነጥቅ ድምፅ መብራት ከሚቆጥረው ልጅ ጋር ሲያወሩ አጠገባቸው ካለ ሰው ጋር ሚያወሩ አይመስልም ነበር ....

"ኧረ በጣም አበዙት....ተረጋጉ እርሶ....".....ያለው ለሊት የሰራትን ምስር ወጥ በስቶቭ ለማሞቅ ቤተክርስትያን መሄጃ ሰአታቸውን የሚጠብቀው ጎረቤቴ ባልቻ ነበር...



ሸዊት ነበርኩ።



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
20.04.202517:38
✨✨ፍቅር ቅብ...3✨✨



"በናትሽ ሀኒ አትቀልጂ...ጭንቅ ብሎኛል..."...ስላት የማያባራ የመሰለኝ ሳቋን ባንዴ ቁርጥ አደረገችውና ማውራት ጀመረች...


"ይኧውልሽ ዮናስ ትዳር በትክክል ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቀው ነገር የለም...'ለምን ማግባት ፈለግክ' ተብሎ ሲጠየቅ ውስጡ ቢመልስ ኖሮ መልሱ 'የአልጋ ላይ ቡጊ ቡጊን የመሰለ ምን አለ...ያለ ገደብ እሱን ለማስነካት ነው' ነበር የሚሆነው..ግን የሚመልሰው አፉ ነው...'ስለምወድሽ ስለማፈቅርሽ...ማሬ ቅብርጥሴ' እያለ ይጠግርሻል....አይንሽን ክፈቺ...ከቃላቱ በላይ ድርጊቱን እይው...ላንቺም ቢሆን በባዶ ሆድ ነጋ ጠባ አልጋ ላይ መጨፈሩ ጥሩ አይደለም...u know energy የሚባል ነገር አለ...በባዶ ሆድ ስራ ካካካካካ...."...የተለመደው ሳቋን አስከተለች።


እኔ ውስጤ በጥያቄ መራወጥ ጀመረ...
ስራ ላይ የሌለ ትዕግስት ለኔ ከየት መጣ...ለሌላ ሰው የሌለው አክብሮት ለእኔ ከየት ተፈበረከ....የሚበላው አጥቶ እርሱን ለሚለምን ህፃን የሌለ ርህራሄ ለእኔ ከወዴት ተገኘ....?....በጥያቄ ታጨቅኩ....



****


ሶስት ቀን ከሞላው የልብ ካልሆነ ኩርፊያ በኃላ የሉሲ እኩያ የሚመስል ካፌ ቀጠረኝ...ዛሬ ስለዚህ ግንኙነት በግልፅ ላወራው ነበር ሀሳቤ....በአልጋ ላይ ትርኢት እና በውብ ቃላቶች ብቻ የታጀበው ግንኙነት እንዲያበቃ አልያም መስመር እንዲይዝ...


"እድሌ..."


"እድልክ አይደለሁም...እድል ካልከኝ ይበቃል...."...ከዚህ አጠራሩ በኃላ ምን እንደሚከተል ስለማውቅ እየተጠነቀቅኩ ነው...በኔ ቤት።


የፈራሁት አልቀረልኝም ተጠጋኝ...ከእርሱ ሌላ ማየት እስከማልችል ድረስ ቀረበኝ...ከዛም የምወድለትን አስተያየት አየኝ...እጄን አጥብቆ ይዞ ወደራሱ ሲያስጠጋኝ አር የነካው እንጨት እንደያዝከኩ ነገር መነጨቅኩት...'ጎበዝ እድል እንዲህ ነው መጀገን' ብዬ ራሴን አበረታታው...ቢያንስ እናውራ አይባልም...?...አኩርፌ ነበር እኮ...


"እድሌ ይገባኛል አጥፍቻለሁ...በጣም እያበሳጨሁሽ እንደሆነ ይገባኛል...ግን እመኚኝ እለወጣለሁ...በቅርቡ አንድ አሪፍ ስራ አግኝቻለሁ...እንደሚሳካ አልጠራጠርም...ከዛ እንጋባለን...."


"ኧረ ጉድጓድ ግባ"....በሆዴ ነው...በአፌ ምንም አልተነፈስኩም...ግን ምናለ ትንሽ ራቅ ብሎ ቢያወራ...የትንፋሹ ሙቀት እስኪሰማኝ ድረስ ተጠግቶኛል...ከአይኑ ግጭት እንዳልወድቅ እየተጠነቀቅኩ ነው....


"አፈቅርሻለሁ...አፈቅርሻለሁ...ሌላውን እርሺው..."...ካለኝ በኃላ ገፄን ገፁ ውስጥ አገኘሁት...አላስገደደኝም...ግን አስገድዶኛል...ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ነው...ግራ መጋባት አለው...መወሰንም አለመወሰንም...አዎ ከዚህ በኃላ በ'አፈቅርሻለሁ' ትርክት ላለመቀጠል መወሰኔን ላውጅ ነበር አመጣጤ...በነበር ቀረ እንጂ...


"ክክክ-ክክክ".....የሆነ አጠገባችን ያለ  ሰው ጉሮሮውን ሲጠራርግ ነው ከንፈሮቻችን ወደየ ቦታቸው የተመለሱት...


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገና ስሙ ሲጠራ ያ ለግላጋው ቁመቱ አይታወሰኝም...ከዛ ይልቅ የሚጎላብኝ የአክሱሙ ርዝመት ነው...ዘናጩ ዮናስ አእምሮዬ ውስጥ የለም...ራቁቱን ቅልብጭ ይልብኛል...


ዮናስ ሲባል ሰው ሁሉ የሚደነግጥለት መልኩ እና ጆሮ ሚጠልፈው ድምፁ ጭራሽ አይታወሰኝም...ከጠራው ቆዳው በላይ በላብ የተጠመቀ ሰውነቱ ነው የሚመጣልኝ.....ከምወድለት ድምፁ በላይ አልጋ ላይ ስንጨፍር የሚያወራቸው ትርጉም የለሽ መዘላበዶች እና ቅስቻዎች ናቸው ትውስታዎቼ....


ገና "እድሌ" ከማለቱ ከስሜ በላይ ኩርፊያዬን የሚያስረሳ አለም ውስጥ እንደሚከተኝ በስውር ስለሚነግረኝ ነው ከራሴ ጋር ትግል ውስጥ የሚጨምረኝ....የሚያንቀለቅለኝ መጨረሻዬ ሁለት በሁለት የሆነች ጎጆ ውስጥ እንደሚሆን ስለማውቅ ነው....በራሱ ሜዳ... ራሱ ፈረስ ሆኖ...ራሱ ጋሪ ሆኖ... ራሱ ነጂ ሆኖ ነው የሚሾፍረኝ...


ከባነንኩ በኃላ ተበሳጨሁ...'ለዚህ ነበር ይሄ ሁሉ ፉከራ'...ጠየቅኩ ራሴን...በቃ በቅፅበት ለምረሳው ነው እንዲህ ያዙኝ ልቀቁኝ አልኩ ደግሜ።


"ይቅርታ ከዚህ ካፌ ብዙም ሳትርቁ ፔንሲዮን አለ...."....አለ የቀሰቀሰን አስተናጋጅ...ጉሮሮ አጠራረጉ ግን ይቺን ለመናገር ብቻ አይመስልም ነበር...ነብሳቸውን ይማረውና የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ጉሮሮ እንኳን ያን ሰረቅራቃ ድምፅ ጀባ ለማለት እንደዚህ የሚጠራረግ አይመስለኝም።


"እሺ እሺ ሂሳብ አምጣልን..."....እኔ የሆነ ቦታ ለመሄድ ስጣደፍ በማወጣው ድምፅ ከአስተናጋጁ ጋር ያወራል...እኔ ሽምቅቅ እንዳልኩ አለሁ...

"የኔ ጌታ ምንም አላዘዛችሁም እኮ...."....ከማለቱ ሳቄ አመለጠኝ...አስተናጋጁም ከእኔ ጋር ተደመረ...የዮናስ ግንባር ላይ ችፍ ያለው ላብ የሀፍረት ብቻ አይመስልም...አይኑም በመደፍረስ አገዘው...ከመርበትበቱ የተነሳ ላልተጠቀምነው ነገር ቲፕ ሰጠ...ባሁኑ አልሳቅኩም ጤንነቱን ጠረጠርኩ እንጂ.....


ከካፌው ወጣንና ከእኔና እሱ ውጪ ደንበኛ ከሌለው ቁርቁዝ ካለ  ፔንሲዮን ገባን...የተለመደው እርግጫ...የተለመደውን ጭፈራ ጨፈርን....ይሄን ጭፈራ ለሳምንት ቀጠልን...እንዳይደብረኝ ብሎ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ፖዝሽን መቀየር ብቻ ነው...ያኔ አንድ ጭፈራ የነበረው ወደ ብሄር ብሄረሰቦች ጭፈራ ይቀየራል...'በባዶ ሆድ ስራ' አለች ሀኒ...



***


✍ሸዊት



ይቀጥላል....react እያረጋችሁ






https://t.me/shewitdorka
15.04.202515:31
I don't know why ግን dark ነገር ፃፊ ፃፊ የሚለኝ መንፈሴ ተቀስቅሷል....እንኳን ደህና መጣህ በሉትማ😁



የዛሬው dark story ይሄ ነበር....ነገ በተመሳሳይ ሰአት በሌላ dark story እንገናኝ።


ቆዩልኝ💙
Қайта жіберілді:
✍ዮ_ሚን avatar
✍ዮ_ሚን
20.04.202509:15
ትንሳኤውን ለትንሳኤ ያድርግልን !

@yomin1_2
02.04.202519:02
አባቴ ጥቁር ነበር ፊቱ አይፈታም። ወታደር ነበር መቶ አለቃም ነበር ። ፀጉር ጥቅጥቅ ያለ ነበር ። አናፂ ነበር ። ብዙ አያወራም ነበር ።

ይወደኝ ነበር ። ያለውን ብር አውጥቶ ሱሪ ጥልፍልፍ ጫማ አቡወለድ ይገዛልኛል ።  አታጨማልቀው ይሉት ነበር ። መቶኝ አያውቅም ።

ከጁ ሲጋራ ከእጁ እኔ አልጠፋም ነበር ። ሲጋራ ሽታው አባቴን ስለሚያስታውሰኝ ሲጋራ እወዳለሁ ። ሲጋራ አጤሳለሁ ።

           አባቴ ኮስተር እንዳለ ነበር ውለታ የሚውለው ። አኮሰታተሩ አዲስ ሰው አያቀርብም ። የቀረበው ሁሉ ግን ይወደዋል ።  ዝናብ ይወድ ነበር ። ፀሃይ ከረረ ብሎ አይነጫነጭም ብርድ ነው ሙቀት ነው እያለ ስለ አየር ሁኔታው አያብራራም ። ከተፈጥሮ ጋ ሲጨቃጨቅ ሰምቼው አላቅም ።

አባቴን እወደዋለሁ ። አይኑ ላይ የማየው ቸርነት እና ፍቅር የትም ስፍራ የትም ፊት ላይ አይቼው አላውቅም ። ምንም ነገር ለኔ ከሆነ ሲሳሳ አይቼ አላውቅም ። አለም ላይ ብቸኛ እንድበልጠው የሚፈልገው አባቴ ነው ።

አባቴ ሲናፍቀኝ ፎቶውን አያለሁ ኮቱን እለብሳለሁ ። ያለኝን አስታውሳለሁ ። ሳላማርር እናፍቀዋለሁ ። ከተፈጥሮ ጋር ሳልጨቃጨቅ ያወረሰኝን መልካምነት እኖረዋለሁ ።

መልኬን እምወደው ስለማምር አይደለም እሱን ስለምመስል ነው። አምሳያዬ ሶስት ቀን ብሎኝ ያውቃል ። እሱ እወዳቸዋለሁ ያለኝን ሰዎች ሁሉ እወዳቸዋለሁ ።
ናፈቀኝ .....ማግኘት የሌለበት  ናፍቆት ደስ አይልም መሰለኝ ።
   
     ©    Adhanom Mitiku
Қайта жіберілді:
Open reading 🕊⃤ avatar
Open reading 🕊⃤
1-ድግስ ላይ አንዲት ቆንጆ ልጅ አይተ በመሄድ "ሃብታም ነኝ አግቢኝ" ብትላት፤ ይህ “Direct marketing” ቀጥታ ማርኬቲንግ ነው።

2-የሆነ ግብዣ ላይ ቆንጆ ሴት አይተህ አንዱ ጓደኛህ ወደዛች ልጅ በመሄድ ወደ አንተ እየጠቆመ ሀብታም ነው አግቢው ካለ ይህ “Advertising” ማስታወቂያ ነው።

3-አንዲት ቆንጆ ልጅ ወደ አንተ በመምጣት፡-"ሀብታም ነህ አግባኝ" ካለችህ ይህ “Brand” የምርት ስም እውቅና ነው።

4-አሁንም እቺ ልጅ ጋር ተጠግተህ "ሀብታም ነኝ አግቢኝ" ስትላት በምላሹ በጥፊ ብትመታህ ይህ “Costumer feedback” የደንበኛው አስተያየት ነው።

5-ግብዣው ጋር ወዳለችው ሴት ሄደህ ልታወራ ስትል አንድ ሌላ ቦርጫም ሰውዬ መጥቶ "ሀብታም ነኝ አግቢኝ" ቢላት ይሄ “competition” ውድድር ይባላል።

6-አንተ የፍቅር ጥያቄ አቅርበህላት እሷ ግን ከባሏ ጋር ብታስተዋውቅህ ይህ “Supply and demand gap” የአቅርቦት እና የፍላጎት ክፍተት ነው።

7-አንተ ወደ እርሷ ሄደህ ምንም ከማለትህ በፊት ሚስትህ ብትመጣ እነዚህ አዳዲስ ገበያዎች ወደ አንተ እንዳይመጡ የቀረጥና የቦታ ገደቦች ተጥሎብሃል እንደማለት ያለህ ነው።

ይህ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ ፕሮፌሰሩ ስለማርኬቲንግ ለተማሪዎቻቸው በአሪፍ እውነታ ምሳሌዎችን በመስጠት ያስረዱት ነው!
◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆
                   ~ @open_reading1 ~

                   ~ @open_reading1 ~
06.04.202511:19
ዝግመተ ለውጥ

ከአለማየሁ ገላጋይ 🙌

በሶፊ 😃

👉👂😜 @bestletters
so true🙌
26.03.202502:45
📚ርዕስ፦ የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች
✍️ደራሲ፦ ዶ/ር ዮናስ ላቀው

አማኑኤል ሆስፒታል ብዙ የሚገመቱና የማይገመቱ ነገሮች ይከሰታሉ።

✈️ @Bemnet_Library
27.03.202504:11
ለፍቅር ሲሉ ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ በድራማ በልብወለድ ወይም በውኑ አለም ያሉ ሰዎችን እንደጀግና ነው የምንቆጥራቸው....እናጨበጭብላቸዋለን....'ጀግና' እንላቸዋለን... ናቸው ግን....?....የፍቅር ግቡ ራስን ማጥፋት ነው....?

ፍቅር ራስን ከማጥፋት ሳይሆን ከማኖር ...ራስን ከመውደድ ራስን ከማክበር ነው የሚጀምረው እንደውም....ጀግንነት ያለው ራስን በመውደድ እና በማክበር ወስጥ ነው...ፍቅር ማለት መስጠትና መቀበል ነው....ሰጥቶ መቅረት አይደለም....መቀበል ብቻም አይደለም....ለመስጠት መጀመሪያ አንተ ራስህ ሊኖርህ ይገባል....ኖሮህም ደግሞ ለመስጠት መፍቀድ አለብህ....በመስጠትህ ልትደሰት ይገባል....ራስህን ልታዋርድ ሳይሆን ልታከብር ነው ሚገባህ።

ራስህን ስትወድ ሌሎችንም ትወዳለህ....ምክንያቱም መውደድን በራስህ ተለማምደኃዋል....አይከብድህም....ለሌሎች ክብር መስጠት አይከብድህም።....ራስህን እንድትጠላ እና ራስህን እንድትጎዳ...ትራስህን በእንባ እንድታረሰርስ አያደርግህም ፍቅር...

ፍቅር ገድሎ አያውቅም....ሰዎች ግን ራሳቸውን ጎዶተዋል....ራሳቸውን በድለዋል....ራሳቸውን አጥፍተዋል...ሌሎችንም አጥፍተዋል...እሱ ፍቅር ሳይሆን የታመመ ፍቅር ነው።




"📚ምን ሆኛለሁ"



https://t.me/shewitdorka
04.04.202519:58
"እምባዬ ጠብ ሲል ያየሁት የምትናገረውን ሰምቼ ሳላበቃ ነበር። ካንተ አልጠብቅማ። አንዱ መንገደኛ ሊገለኝ ቢያስፈራራኝ አንተ እጄን ከጠመዘዝከው ጋር አላወዳድረውም።
ምክንያቱም ካንተ ሲመጣ ; እንኳን መመታትን መገልመጥን  ፈራዋለው። ከብዙ ሰዎች ስድብ ይልቅ ፤  ያንተ እኔን ስታወራኝ ድምጽህን ከፍ ማድረግ ለመከፋት በቂዬ ነው። ምክንያቱም አንተን ራሴን በማምነው ልክ አምንሀለው።
 
"እንዴት ትተሽኝ ሄድሽ?"ብለህ ጠይቀኸኛል። ልነግርህ ነው የመጣሁት። የሄድኩ 'ለት  አንተን ከማይወዱኝ ሰዎች መሀል ተቀምጠህ አየሁክ። የምትናገረውን ስሰማ ነበር  ፤ ግን አላስጨረስኩህም።
እነሱን መርጠህ እኔን እየተውከኝ መስሎኝ ነበር። ትግልህ እኔን ለማስወደድ እንደነበር ግን ዛሬ ከነዝያ ሰዎች አንዱ አብራርቶልኝ ነው የገባኝ።
ከሁለት ዓመት በፊት ፤ እዛ ክፍል ውስጥ ሁለት ደቂቃ ብቆይ ፤ ምናልባት ሕይወት እንዲህ ከራስ የገጠሙት ትግል አይሆንብኝም ነበር ይሆናል።
ካላንተ ልቤ እንዲመታ ባልታገልኩ ነበር።
ግን እይ ሴኮንዶች የሕይወቴን አቅጣጫ እንደምን እንደቀየሩት?!
አሁን እዚህ ጋር ምናገረው ነገር ምንም ለውጥ አያመጣ ይሆናል።
ግን ማወቅ ስላለብህ እነግርሀለው። የምወደውን ሰው ከነዛ ሰዎች ጋር ሲተባበር ማየት አቅቶኝ ነው ቃልህን ሳትጨርስ ሮጬ ያመለጥኩት።

ልቤን በራሴው ሀሳብ ቀጣሁት።
ይግረምህ!
አንተን ብቻ አይደለም ራሴንም ነው የገደልኩት።
ጊዜ ጌታው>>
ምን አ'ረክ? ተብሎ አይከሰስ ነገር......ጊዜን ለፍቅር ስል መታገስ አቅቶኝ የተቀጣሁትን እኔን መልሰህ ትቀጣኝ??" አለችው።

አይኑ ብቻ አይደለም ልቡም እምባን ዘራ። "ፍቅር አበባ ነው። እንደ አደይ ተናፍቆ ብቅ የሚል" ብሎ ስለሚያምን ሊከሳት አልቻለም ፤ እጇን ላልያዘበት ጊዜ""""""ጊዜን ረገመው።
  "ቢረፍድም ደርሰሻል" በጁ እጇን እንደያዘ በጆሮዋ ነገራት።


ቲና ✍️

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
ጣቶቿን አያቸዋለሁ....ጫፎቻቸው እንደ ቲማቲም የቀሉ....ብትዘቀዝቃቸው የሚንጠባጠቡ የደም ጤዛዎች ይመስላሉ....ውብ ጣቶች....


በእያንዳንዱ ብልጭታ የሀኑንን ውብ ፊት አእምሮዬ እንደ ፎቶ እያተመ ያስቀምጣል....በግራ ትከሻዋ በኩል አልፎ ጡቷ ላይ የሚርመሰመሰው ፀጉሯ በግማሽ ፊቷን የከበበ ውብ ፍሬም መስሏል....እስከ ዛሬ ሀኑንን ሳስብ ያ መልኳ ነው ቀድሞ ሚታወሰኝ....እንደ ቲማቲም የቀሉ ከንፈሮች....ከመቅላቱ ብዛት በወርቃማ ቆዳ የተለበጠ የሚመስል ደረት....ስዕል❤️



አሌክስ አብርሀም
(ከእለታት ግማሽ ቀን)



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
የስነ ልቦና የምክክር ህክምና አንዳንድ ሰዎች ጓደኞቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን እንደሚመክሩት አይነት ይመስላቸዋል....በእርግጥ ተመሳሳይ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ...በሌላ መልኩ ደግሞ መሰረታዊ የሆኑ ልዩነቶች አሉት....ልዩነቱ ልክ እንደ ወጥ ቤት ሰራተኛ እና የ'ሼፍ' አይነት ነው...ሁለቱም መጨረሻ ላይ የሚያቀርቡት ምግብ ነው....

ምግቡ ግን ልዩነት አለው።




(ዶክተር ዮናስ ላቀው)
"የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች"


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
ለመላው የእስልምና ተከታይ  ቤተሰቦቻችን እንኳን  እንኳን ለ1446'ኛው የኢድ አልፈጥር በኣል በሰላም አደረሳችሁ 💛


ኢድ ሙባረክ❤️

    
Көбірек мүмкіндіктерді ашу үшін кіріңіз.