19.04.202516:55
"ሌላ ፋሲካ" ትረካ
በሐረገወይን አሰፋ
በሐረገወይን አሰፋ
07.04.202507:00
‹‹እፉዬ ገላ››
-----
ክለብ ለመውጣት አላሰብኩም ነበር፡፡ ጓደኞቼ ናቸው ጨቅጭቀው ይዘውኝ የመጡት፡፡
አንቺም እዚህ ትሆኛለሽ ብዬ አልገመትኩም፡፡
ክለብ ሄደሽ እንደማታውቂ ስንቴ ነገረሽኛል፡፡
ጫጫታ እንደምትጠይ፣ ግርግር እንደሚሸክክሽ፣ ጮክ ያለ ሙዚቃ እንደሚበጠብጥሽ፡፡
ጥግ ላይ ያለ ረጅም፣ ጥቁርና ተቀጣጣይ ሶፋ ላይ ተቀምጠን የምንጠጣውን ነገር እንዳዘዝን ነው ያየሁሽ፡፡ ልብሽ እስኪጠፋ ስትደንሺ፡፡
እንዳየሁሽ ያስተዋልኩት ነገር ሁሌ ከማውቅሽ ፍቅረኛዬ ለየት ብለሽ መታየትሽን ነበር፡፡
ደስተኝነትሽን፡፡ እኔ አጠገብሽ ሳልሆን ሳልሆን እንዲህ ደስተኛ ነሽ እንዴ?
በተቀመጥኩበት ለረጅም ደቂቃዎች ተመለትኩሽ፡፡
ካንጀትሽ እየሳቅሽ ነበር፡፡
ጭንቅላትሽን ከሙዚቃው ጋር እያወዛወዝሽ፡፡ አይኖችሽን ስልምልም፣ የሚያምር አፍሽን ከፈት ዘጋ እያደረግሽ፡፡
ሰውነትሽን እስኪርገፈገፍ ትስቂ ነበር፡፡ አይቼው፣ ሰምቼው የማላውቀውን ሳቅ፡፡
አንድ ዓመት ያህል አብረን ቆይተናል።
ግን ይህንን ሳቅ ፣ ይህንን ብርሃን የለበሰ ጸዳል ፊትሽን አላውቀውም፡፡ እንዲህ እንደ እፉዬ ገላ ቅልል ብለሽ ስትንሳፈፊ አይቼሽ አላውቅም፡፡
ክንዶችሽ ወደ ላይ ተዘርግተዋል፣ ዳሌሽ ከዘፈኑ ምት ጋር ይንቀሳቀሳል፡፡ የዘፈኑን ግጥም አጥንተሽዋል ልበል…?
አንድ ሳያልፍሽ ትይዋለሽ…አንዳንዶቹን ቃላት የልብሽን የነገሩልሽ ያህል እጆችሽን የተጋለጠ ደረትሽ ላይ አድርገሽ በጩኸት ታወጪያቸዋለሽ፡፡ እኔ በስንት ተማፅኖ እና ምልጃ የማያቸው ጡቶችሽ ስለምን ያለ ከልካይ ለአላፊ አግዳሚው ተሰጡ?
ትሽከረከሪያለሽ፣ ትዘያለሽ…የክለቡ ድብልቅልቅ መብራት በጸጉሮችሽ መሃከል እያለፈ….
ከዚያ አንድ ፈርጣማ ወንድ አንዱን እጅሽን አፈፍ አድርጎ ያዘ፡፡
በማታውቂው ሰው ቀርቶ በፍቅረኛሽ ሳትጠየቂ መነካትን ስለማትወጂ ካሁን ካሁን አጮለችው ስል እሺ ብለሽ ተያዝሽለት፡፡
እንዴ! ምንድነው ጉዱ?
አብራችሁ ተወዛወዛችሁ፣ ልክ እድሜሽን ሙሉ ስትጠብቂው እንደነበረ ሁሉ ሲወዘውዝሽ ተወዘወዝሽለት፤ ሲያሽከረክርሽ ተሽከረከርሽለት፡፡ ሲያቅፍሽ ታቀፍሽለት፡፡
ወቸው ጉድ፡፡
አብረን ባሳለፍነው አመት ስላንቺ የማውቃቸውን፣ ያስተዋልኳቸውን ብዙ ነገሮች አስታወስኩ።
ጭምትነትሽን፡፡
አትንኩኝ ባይነትሽን፡፡
ወግ አጥባቂነትሽን፡፡
አንገት ደፊነትሽን፡፡
አይን አፋርነትሽን፡፡
ቤት ቤት፣ ጓዳ ጓዳ ማለትሽን፡፡
ሶፋ ላይ በድብርት የምትጎለችው፡፡
ጭፈራ አልወድም የምትይኝ፡፡
ውጪ ውጪ ማለት ደስ አይለኝም የምትይኝ፡፡
ሙዚቃ ትንሽ ጮክ ሲል ‹‹አቦ ቀንስልኝ፤ ራሴን ያመኛል›› የምትይኝ፡፡
ሰው ፊት እጄን እንዳትይዘኝ፣ መንገድ ላይ እንዳታቅፈኝ የምትይኝ፡፡
---
አገር ያሳቀ ቀልድ ብነግርሽ እንኳን ከእኔ ጋር እንደዚያ ስቀሽ አታውቂም።
ብለማመጥሽ እንኳን ከእኔ ጋር እንደዚህ ደንሰሽ አታውቂም።
ይህችን፣ አሁን ፊት ለፊቴ ያለችውን ደስተኛ ሴት ሆነሽ አታውቂም፡፡
‹‹አፈር ስሆን ትንሽ ፈታ በይ›› ብዬ ሳሎንሽ ውስጥ ልሳምሽ ስል እንኳን ሳትሽኮረመሚ፣ ደጅ ሳታስጠኚኝ፣ ሳትኮሳተሪ እሺ አትይኝም፡፡
ከእኔ ጋር ፈራ ተባ ባይ፣ ዝምተኛ እና ወግ አጥባቂ ነሽ፡፡
አሁን ግን..እዚህ ግን….
አንጀቴ ተበጠሰ፡፡ መጠጡ ደም ደም አለኝ፡፡ መተንፈስ ከበደኝ፡፡
እስክታይኝ ትንሽ ጠብቅኩ። አላየሽኝም፡፡ በየት በኩል ፋታ አግኝተሽ?
ስለዚህ ብድግ አልኩና ሰበብ ፈጥሬ ከክለቡ ወጣሁ፡፡
ለምን ሳላናግርሽ መሰወርን መረጥኩ?
ፈሪ ስለሆንኩ ? እውነቱን ለመጋፈጥ ተንቦቅቡቄ?
ስለምወድሽ ነው፡፡
ስለምወድሽ ለእኔ ስትይ (ወይም በምንም ምክንያት) በሃዘን ተቆራምደሽ፣ ተደብተሸ፣ ተከፍተሸ እንድትኖሪ አልፈልግም፡፡
ስለምወድሽ ሌላ ሰው መስለሽ ከእኔ እንድትቆዩ አልሻም፡፡
ምክንያትሽ ምንም ይሁን ስለምወድሽ ደስተኛ ያለመሆንሽ ሰበብ መሆን አልፈልግም፡፡ አንቺን ማጣቴ ቢጎዳኝም የሃዘንሽ መንስኤ፣ የድባቴሽ ምንጭ እኔ መሆኔን ሳስብ ግን ልቤ ተጨራመተ፡፡
ምን መሰለሽ?
እኔ በሌለሁበት ያለሽን እውነተኛውን እፉዬ ገላ ማንነትሽን አንዴ አይቻለሁና በእጄ ጨብጨ እንዳትበሪ አስሬ መቆየቱን የሚያፈቅርሽ ልቤ አይፈቅልኝም፡፡

04.04.202507:12
የትርፍ ጊዜ ሥራ
————————-
(ከማታ ማታ መፅሐፌ ላይ)
(ክፍል አንድ)
🌝🌝🌝
ቅዳሜ ስምንት ሰዓት ተኩል፡፡
አዲሱን ቤቴን ለማደራጀት፣ ቀስ እያልኩ የቤት እቃዎች ገዝቶ ማሟላት ከጀመርኩ አንድ ዓመት ሞላኝ፡፡
የቀረኝን የመጽሐፍ መደርደሪያ ለመግዛት በባልደረቦቼ ጥቆማ መሰረት፣ “ፍሎውለስ ፈርኒቸርስ” የሚባል ቤት መጥቻለሁ፡፡
የሱቁ ስፋት የትየለሌ፣ ምርጫውም ብዙ ዓይነት ነው፡፡ “የእንጨት ይሻልሻል የብረት?” አለኝ፣ ቀለብላባው የሽያጭ ሠራተኛ፡፡ በራሴ አይቼ ልወስን ብለውም ከገባሁ ጀምሮ እየተከታተለ ይነዘንዘኛል፡፡
“ያለውን አይቼ ልወስን… በራሴ አያለሁ…” አልኩት በመታከት፡፡
“አዳዲስ ሞዴሎች አስገብተናል፡፡ እዚያ ጋር የምታያቸው ከእንጨት የተሠሩት በቅርብ ከብራዚል የመጡ ናቸው፡፡ ንጹህ እንጨት ናቸው፡፡ ዋጋቸው ትንሽ ቢወደድም የዘለዓለም እቃዎች ናቸው፡፡ የብረቶቹ… እነዚያ እዛ ጋር ያሉት የቻይና ናቸው፡፡ ዋጋቸው ዝቅ ያለ ነው፣ ግን ጥራታቸውም ምንም አይልም… እኔ የምመክርሽ ግን…
“በናትህ በራሴ ልይ!” ሳላስበው ጮኽኩበት፡፡
በርግጎ ሄደ፡፡ ኡፍፍፍ!
ረጋ ብዬ ከብራዚል መጡ ወዳላቸው የእንጨት መደርደሪያዎች ሄድኩ፡፡ ቀልቤን ወደሳበው ሄጄ መነካካት ስጀምር፣ ከኋላዬ በጣም የማውቀው የወንድ ድምፅ ስሜን ሲጠራ ሰማሁ፡፡
ደቤ? ዞርኩ፡፡
ደቤ ነው፡፡
“እንዴት ነሽ?” አለኝ በቆመበት ከላይ እስከታች እያየኝ፡፡
እንዴት ነሽ አባባሉ ቅርበታችንን የማይመጥን የሩቅ ሰው ድምፀት ነበረው፡፡
ምናባቱ ቆርጦት ነው መጥቶ አቅፎ የማይሰመኝ?
“ደህና ጋሽ ደቤ…” በሹፈት መልክ እየሣቅኩ ተጠጋሁት፡፡
ስጠጋው እንደ መጠጋት ወደ ኋላ ሸሸት አለና፣ ሊገባኝ ባልቻለ ምክንያት ለተሰበሰበ ሕዝብ የሚያወራ ያህል ጮኽ ብሎ፣
“ምን ልትገዢ መጣሽ እዚህ….? እኛ ለልጆቹ አልጋ መቀየር ፈልገን ልናይ ብለን ነው… ነይ ገኒንና ልጆቼን ላስተዋውቅሽ…” አለ፡፡
አመዴ ጨሰ፡፡
ደቤና በግምት አርባ አመት የሚሆናት ደርባባ፤ ቀጭንና ጸጉረ ረጅም ሴት፣ ከትንሽ ልጅ ጋር ወደኔ እየመጡ ነው፡፡
ከልጁ ከፍ የምትለው ሴት ልጅ አንዱ የሚሸጥ ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ ከእጆቿ በእጥፍ የሚበልጥ ስልክ እየጎረጎረች ነው፡፡
እኔስ? እኔ ደግሞ ድንገተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ መቀመቅ እንዲያወርደኝ እየተመኘሁ ነው፡፡
“ፍሬሕይወት! እንዴት ነሽ…? ገነት እባላለሁ” አለችኝ ሴትዮዋ፡፡ እጆችዋን በትህትና ለሰላምታ እየሰጠችኝ፡፡
ከድንጋጤዬ ሳላገግም፣ “ሃ… ገነት! ፍሬሕይወት እባላለሁ” አልኩና ጨበጥኳት፡፡ “አውቃለሁ…. ደብሽ ብዙ ጊዜ ስላንቺ ያወራል እኮ….” አለች፡፡
ፈገግታዋ የደግ ሰው ነው፡፡ ሁለት የወለደች የማትመስል፣ ቅርጿ የተስተካከለና ተረከዝ አልባ ጫማ ብታደርግም፤ ከገመትኩት በላይ ረጅም ሴት ናት፡፡ ጠይም ፊቷ ላይ ትንሽ ድካም ቢታይም፣ መረጋጋትና ደግነት የሰፈነበት ቆንጆ ሴት ናት፡፡
ረጅም ግን ሣሣ ያለው ጸጉሯ በየመሀሉ ጥቂት ሽበቶች Aሉት፡፡ ቢሆንም ግርማ እንጂ እድሜ አልጨመረባትም፡፡
“ይሄ ደግሞ ማርኮን ይባላል… ማርኮን ፍሬሕይወትን ሰላም በላት….” አለች፣ ፈገግታዋ ሳይጠፋ፡፡ ማርኮን ሚጢጢ እጆቹን ለሰላምታ ዘረጋልኝ፡፡ ልቤ ከልክ በላይ እየመታ ጎንበስ ብዬ እንደ ትልቅ ሰው ጨበጥኩት፡፡
“ያቺ ደግሞ የአርሴማ ትባላለች…” አለ ደቤ፣ ስልክ ወደ'ምትጎረጉረው ትንሽ ልጅ እያመለከተ፡፡ ድምፁ ይንቀጠቀጣል፡፡
የአርሴማ ለአመል ቀና አለችና፣ ቀኝ እጇን በቻው ቻው Aውለበለበችልኝ፡፡ ቁርጥ እናቷን ናት፡፡
“የአርሴማ… ሰው እንዲዚህ ነው ሰላም የሚባለው? ነይና ሳሚያት!” አለች ገነት ባልገመትኩት የቁጣ ድምፅ፡፡
የአርሴማ ፍንጥር ብላ ተነስታ መጣችና ቀኝ እጇን ዘረጋችልኝ፡፡
“ሳሚያት…” አለች ገነት፡፡ የአርሴማ ልትስመኝ ስትንጠራራ ጎንበስ ብዬ ሁለት ጊዜ አገላብጬ ሳምኳት፡፡
“ጎበዝ የኔ ልጅ!” አለች ገነት፡፡
እሺ… ቀጥሎ ምን ሊሆን ነው በሚል እጆቼን ወደ ኋላ አጣምሬ በግራ መጋባት ቆምኩ፡፡
ገነትን ላለማየት ሰፊውን ቤት፣ ልጆችዋንና አልፎ አልፎ ደቤን አያለሁ፡፡ የገነትን አይኖች ሽሽት አንዴ አረንዴውን ሶፋ፣ አንዴ ወድጄው የነበረውን መደረደሪያ፣ አንዴ ቀይ በነጩን ምንጣፍ፣ አንዴ ቅድም እየተቅለበለበ ሲረብሸኝ የነበረውን ልጅ አያለሁ፡፡ ምናለ አሁን መጥቶ ከዚህ ሁኔታ ቢገላግለኝ?
ምን ሰበብ ፈጥሬ እግሬ Aውጪኝ ልበል?
“ደቤ የባህርዳር ልጅ እንደሆንሽና ለሥራ ብለሽ አዲሳባ እንደመጣሽ ነግሮኝ ነበር…” አለች ገነት፡፡
“አዎ… ገና አንድ ዓመቴ ነው ከመጣሁ…” አልኩ፣ Aሁንም አይኖቿን Eየሸሸሁ፡፡
“ለበአል ቤት ይዘኻት ና ብለው፣ እሱ ልብ የለው፤ ሳይነግርሽ ቀረ መሰለኝ… እንግዳ ሆነሽ ብቻሽን…”
“ኧረ ችግር የለም…” አልኩ ሳላስጨርሳት፡፡
ወሬያችንን በአጫጭር መልሶች የምደመድመው ላውቃት ስለማልፈልግ ነው፡፡
ባጭሩ ተገላግዬ ከዚህ ቦታ መፈርጠጥ ስለምፈልግ ነው፡፡
“ነውር ነው ኧረ….” አለች ገነት፡፡
ለምን አትተወኝም?
ደቤን አየሁት፡፡ በናትህ ከዚህ ጉድ ገላግለኝ በሚል አይን አየሁት፡፡
“እስካሁን የቤት እቃ እየገዛሽ ነው እንዴ?” አለ፣ ነገሬ እንደገባው ሁሉ፡፡
(ቤቴን አብጠርጥረህ የማታውቅ ይመስል እንዲህ ዓይነት ጥያቄ መጠየቅ አግባብ ነው ደቤ? አግባብ ነው ወይ?)
ጭራሽ ወሬ ይቀጥላል እንዴ? ለራሴ ሚስቱ እና ልጆቹ ፊት ከእሱ ጋር በመቆሜ የጥፋተኝነት ስሜት ጥርስ አውጥቶ ሊበላኝ ነው፤ ጭራሽ ወሬ ይቀጥላል?
“እ… አዎ… ቀስ እያልኩ ነው… ይሄ ግን የመጨረሻ እቃ ነው… ለጊዜው….” አልኩ እያየሁት፡፡
“ቤትሽ የት Aካባቢ ነው….?” አለች ገነት ረጅም ጸጉሯን በግራ እጇ ከፊቷ እየመለሰች፡፡ የሚያንጸባርቀውን የጋብቻ ቀለበቷን አየሁት፡፡ አንደኛው ባለ ትልቅ ፈርጥ፣ ሌላኛው ልሙጥ ግን ሰፊ ወርቅ፡፡
“ሰሚት… ሰሚት ኮንዶሚኒየም ነው የምኖረው” አልኩ፣ አይኖቼ ቀለበቷ ላይ ተሰክተው፡፡
“እንዴ…? እኛም እኮ ታዲያ አያት ነን ያለነው!”
(አውቃለሁ ገነት- አውቃለሁ)
“እንዲህ ቅርብ ለቅርብ ሆነን ነው እስካሁን ያላመጣሃት….?”
(ወይዘሮ ገነት…! በ‘ናትሽ… በፈጠረሽ መልካም ሴት አትሁኚ፡፡ በ‘ናትሽ መልካም ሴት አትሁኚ!)
“በቃ… ለመስቀል እንዳትቀሪ… ደቤ ነግሬሃለሁ… ለመስቀል ይዘሀት እንድትመጣ… ኦሪጂናል የጉራጌ ክትፎ ትበያለሽ…”
(ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ የዋህና ደግ ሴት ናት፡፡ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡)
“ኦኬ… እኛ ጨርሰናል… እዚህ የሚረባ ነገር Aላገኘንም፡፡ ምሳ ለመብላት እዚህ ቃተኛ ልንሄድ ነበር…” አለ ደቤ፡፡
ምጤ ገብቶት ሊገላግለኝ በመዘጋጀቱ እፎይታ ተሰማኝና፣
“አሪፍ…. እኔም ደህና ነገር አላገኘሁም… መሄዴ ነበር ኤኒዌይ…” አልኩ ቶሎ ብዬ፡፡
“ብቻሽን ነሽ አይደል?” አለች ገነት ቆሜ የነበርኩበትን ቦታ በአይኗ Eያሰሰች፡፡
(አዎ… ብቻዬን ነኝ፡፡ ብቸኛ ነኝ ገነት)
“አዎ… ግን ቅዳሜ አይደል… ወደ ቤት ሄጄ ቤት ማጽዳት ምናምን አለብኝ…” አልኩ፣ ደቤን እያየሁ፡፡
“ውይ በቃ ምሳ አብረን እንብላና ትሄጃለሻ? እ?” ያ ምስኪን ፈገግታዋ ፊቷ ላይ ተመልሶ ተሳለ፡፡ ወደ ላይ ሊለኝ ፈለገ፡፡

28.03.202506:37
‹‹አይለመደኝም››
-----
“የእኔና የእሱ ነገር እኮ ካከተመ ቆየ” አለች፡፡
“ሰው ከስህተቱ አይማርም እንዴ?…ስንት እድል ሰጠሁት…ስንት ጊዜ ጎዳኝ….? ከእንግዲህ አቅም የለኝም፡፡ የእኔና እሱ ነገር አብቅቷል››
“ባክሽ ተይ…! ሁሌ ስትለያዩ እንዲህ ነው የምትይው ” ጓደኛዋ መለሰች፡፡
“ከዚያ ሲደውልልሽ ሁሉን ነገር እርስት….ብትንትን ትያለሽ…”
“ከእንግዲህ ቢደውልም አላነሳማ!”
“አንቺ…? መቼ አስችሎሽ…? እንዲህ ብለሽ ምለሽ ተገዝተሽ ከደወለ ሁሌ እንዳነሳሽ ነው….”
“እሱ ድሮ ነው፡፡ ያለፈ ነገር፡፡ ከእንግዲህ ሺህ ጊዜ ቢደውል እንዲች ብዬ አላነሳለትም…አይለመድልኝም ስልሽ!”
ጓደኛዋ ቃሏን እንዳላመነች በሚሳብቅ ሁኔታ፣
‹‹እስቲ እናያለን›› በሚል አኳሃን ተመለከተቻት፡፡
አብራት አምሽታ ወደቤቷ ሄደች፡፡
---
በነጋታው በጣም ከመሸ ደወለላት፡፡
ስልኳ ላይ ስሙን አፍጥጣ እያየች ከራሷ ሙግት ገጠመች፡፡
አታንሺ፡፡ እንዳታነሺ፡፡
+
+
+
+
አነሳች፡፡
ሞቅ ብሎታል፡፡
‹‹ናፍቀሽኛል፡፡ ››
‹‹አፈቅርሻለሁ፡፡››
‹‹ ካንቼ ተለይቼ መኖር አልቻልኩም››
‹‹ከባህር የወጣ አሳ ሁንኩልሽ› አላት፡፡
“ሁሌም ስንለያይ እንዲህ እንዳልክ ነው” መለሰችለት፡፡
“እውነት ስለሆነ ነዋ…እውነት እኮ አይቀያየርም የእኔ ልእልት….”
ልታምነው ዳዳት፡፡
ልምጣና ልይሽ ብሎ ጠየቃት፡፡
“አይሆንም” አለችው፡፡ “መልሰህ ልትጎዳኝ…..አላሳዝንህም?”
“ስሞትልሽ የእኔ ልእልት…እኔስ አላሳዝንሽም…? ደግሞ አልገባም እኮ…ከደጅ እመለሳለሁ”
ደጅ ቆሞ እንደማይቀር እያወቀች አልገባም ሲላት ልታምነው ፈለገች፡፡
‹‹እሺ ግን ዛሬ አትገባም››
መጣ፡፡
እጆቹን ኪሱ ውስጥ ከትቶ ደፏ ላይ እየተወዛወዘ፡፡ ፈገግ እያለ፡፡
ስንቴ የሰባበራት ልቧ ምቷ ጨመረ፡፡
እሳት እንደተጠጋ ቂቤ ባንዴ ቀለጠች፡፡
‹‹አልቆይም…ገባ ብዬ ልውጣ?›› አላት መዳከሟን አይቶ፡፡
በረጀሙ ተነፈሰች፡፡ ከበሩ ገለል ብላ ወደ ውስጥ አሳለፈችው፡፡
ገባ፡፡
ጉንጯ ላይ ሳማት፡፡
ከጉንጯ በላይ ሊስማት እንደፈለገ ሁሉ በዝግታ፣ በእርጥብ ከንፈሮቹ ሳማት፡፡ ከዚያ ደግሞ አንገቷን፡፡
ትንፋሽ ሲያጥራት፣
‹‹ሰክረሃል፡፡ ቡና ላፍላልህ ›› ብላ አመለጠችውና ወደ ኪችን ሄደች፡፡
ተከተላት፡፡
ቡናውን አላፈላችም፡፡
አደረ፡፡
ነግቶ ሲነቃ ፊቱ ላይ ፀፀት ቢጤ ያነበበች መሰላት፡፡ እርግጠኝነት ማጣት፡፡
ይህንን ፊት ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ አይታዋለች፡፡ አሳምራ ታውቀዋለች፡፡
ሰበብ ፈጠረና የሰራችውን ቁርስ ሳይቀምስ ለባብሶ ወጣ፡፡
ስለተፈጠረው ነገር ግድ እንደሌላት ለራሷ ነገረች፡፡
ከዚያ ግን ለጓደኛዋ ደውላ ለቅሶ ቀር ኑዛዜዋን አቀረበች፡፡
‹‹ነግሬሻለሁ…ታነሻለሽ ብያለሁ…›› ጓደኛዋ በሰማችው ሳትገረም መለሰች፡፡
‹‹ከእንግዲህ አይለመደኝም›› አለቻት፡፡
--
ሳምንታት አለፉ፡፡
ደግሞ አንዱን ምሽት ደወለ፡፡
ከራሷ ጋር ትግል ገጠመች፡፡ እንዳታነሺ። አታንሺ፡፡

19.03.202511:46
እንደኔማ ቢሆን፣ እንደ ፍላጎቴ
አስራ ሁለቱም ወር ክረምት ሆኖ ቢወጣ ደስታውን አልችለውም።
እህስ...
ሰሞኑን ምን እያነበባችሁ ነው?
አስራ ሁለቱም ወር ክረምት ሆኖ ቢወጣ ደስታውን አልችለውም።
እህስ...
ሰሞኑን ምን እያነበባችሁ ነው?
11.03.202507:15
ለቦይፍሬንዴ ምስር ወጥ የሠራሁ’ለት
(ክፍል ሁለት)
------------
የቅብጠት አፍታዎቻችን ረዘሙ፡፡
በስሜት የምንቃትትባቸው ደቂቃዎች ለጉድ ተለጠጡ፡፡
አየሩ ከበደ፣ ወፈረ፣ በእንፋሎት ተሞልቶ ከእኛ ጋር አብሮ ሻፈደ፣ ቀበጠ፡፡
‹‹በሉ እንጂ በሉ እንጂ›› የሚል ይመስል አብሮ አሸቃበጠ፡፡
አልጋው ለ‹‹ከዚህም በላይ›› ዝግጁ ነኝ በሚል ከፍተኛ ምቾትን ሳያስጠጣ አቀበለ፡፡
ትንሽዋ ቤት በጠራራ ፀሃይ ጨለምለም ብላ፣ ፋይቭ ስታር ሆቴል ነኝ አይነት ነገር እያለች አቃጠረች፡፡
የሁለታችንም ልብ ድው ድው እያለ በፍቅር በሰነፉ አይኖቻችን ተያየን፡፡
ሳንነጋገር የቀደመ ስምምነታችን ለማፍረስ ተስማማን፡፡
እናም….
ያለ አጀብ፣ ያለ አስቴር አወቀ የፍቅር ዘፈን፣ ያለ ሻማ ብርሃን፣ ያለ ማባበል….
የምወደው ልጅ ቬሎ ሳያለብሰኝ ገለበኝ፡፡
ቦይፍሬንዴ ሚስቱ ሳያደርገኝ አወቀኝ፡፡
እናቱን ያ ምስር ወጥ፡፡
-----
ሊሸኘኝ ስንወጣ እጄን ጥብቅ አድርጎ ያዘኝ፡፡ እኔም ከወትሮው ጠበቅ አድርጌ ያዝኩት፡፡
የነሃሴ እኝ እኝ ዝናብ አባርቶ መንገዶቹ ሁሉ እርጥብ ነበሩ፡፡
ስለሚሰማኝ ስሜት እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም፡፡ በየሰከንዱ ይቀያየራል፡፡
እግሮቼ አሁንም ይራመዳሉ፤ ዓለም ጠዋት ትቻት እንደነበረው ቀጥላለች፡፡
ግን አላፊ አግዳሚው ያደረግኩትን ነገር በሰአት የዜና እወጃ የሰማ ይመስል ያወቀብኝ መሰለኝ፡፡
‹‹አዲስ ገቢ ›› አይተው ያውቃሉ እንዴ…?
የታክሲ ወረፋ ይዘን በቆምንበት አንዱ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጣ በትልቅ የብረት ድስት ላስቲክ የለበሱ በቆሎዎች የምትቀቅለው ያቺ ጠና ያለች ሴትዮ ለምን እንደዚህ ትክ ብላ አየችኝ…?
አውቃለች አልኩ በልቤ፡፡ አውቃብኛለች፡፡
ይሄስ ካልጠፋ መንገድ በእኔ በኩል ሰልፉን ሰብሮ ለማለፍ የመጣው ሰውዬ ለምን በሚቀፍ ሁኔታ ፈገግ ብሎ ‹‹ይቅርታ እ…›› አለኝ…?
ፈገግታውን ሳይ፣ ‹‹እሰይ በቃ ደግ አደረግኩ…በቃ ሰው የሚያደርገውን አደረግኩ..ዞር በል ከፊቴ›› ልለው ቃጥቶኝ ነበር፡፡
አካሄዴስ እንዴት ነው..?
ተቀይሯል እንዴ…ያስጠጣል እንዴ…?
ስላደረግኩት ነገር ያሳብቃል እንዴ…?
ተራችን ደርሶ ታክሲ ውስጥ ገባን፡፡ እንደ ሁልጊዜው ሰፈር ድረስ በታክሲ ሊሸኘኝ ነው፡፡
‹‹መስኮቱ ጋር ትሆኛለሽ?›› አለኝ በከፊል የተከፈተውን መስታወት እየጠቆመኝ፡፡
ንፋስ እፈልጋለሁ…ንፋስ! በብርድ ይሞቀኛል፡፡
ያደረገ ሰው እንዲህ ነው የሚያደርገው?
አዎ አልኩት፡፡
ብዙ መንገድ በዝምታ ተጓዝን፡፡
እንዲህ፣ ይሄን ያህል ጊዜ ዝም ብለን አናውቅም፡፡
ንፋሱ ግን አወራኝ ልበል..?
‹‹አንቺ ባለጌ….ያረግሽውን የማላውቅ እንዳይመስልሽ….ዋ ለፀሃይ ባልነግርብሽ….ዋ…ለጨረቃ ባላቃጥርልሽ…..…ዋ!›› አለኝ መሰለኝ፡፡
---
ቤት ስገባ አባቴ እንደተለመደው ሶፋውን ሞልቶ ተቀምጦ መፅሐፍ ያነባል፡፡
‹‹ እንዴት አመሸሽ?›› አለኝ፡፡
አፈር በበላሁ፡፡
መሬት ስልቅጥ፣ ዋጥ ባደረገችኝ፡፡
አወቀብኝ ይሆን…?
ብልግናዬ ግንባሬ ላይ ታተሞ ይሆን…?
ከንፈሮቼ እስኪጣመሙ እንደተሰሙ…አንገቴ እስኪበልዝ እንደተነከሰ…ገላዬ ሰምበር እስኪያወጣ….
‹‹ደህና አመሸህ አባብዬ? ›› ብዬ መለስኩና ሹክክ ብዬ ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡
----
ሲነጋ የተቀየረ ነገር አልነበረም፡፡
ሕይወት የተፈጠረውን ነገር፣ የተገረሰሰውን ክብረ ንጽህና ከቁብ ሳትቆጥረው ቀጠለች፡፡
ከእንቅልፌ ተነሳሁ፡፡ ጥርሴን ቦረሽኩ፡፡ ጸጉሬን አበጥሬ አስያዝኩ፡፡
እማምዬ አዲሷ ሰራተኛችን እንደማትረባ አንስታ አማረረች፡፡
ትንሹ ወንድሜ ሃምሳ ብር ስጪኝ ብሎ ለመነኝ፡፡
አባብዬ ጓደኛውን ሊጠይቅ አስኮ ሄደ፡፡
ሕይወት ትላንት የተፈጠረው ነገር ቅምም ሳይላት ቀጠለች፡፡
ድንግልናዬን ባጣሁ/በሰጠሁ ማግስት ራሴን በተለየ ቦታ የማገኘው መስሎኝ ነበር፡፡
ደረጃ እንደመውጣት፡፡ ቦታ እንደመቀየር፡፡
አሁን የሚሰማኝ ግን አጥር ዞሮ እዛው የመመለስ ስሜት ነበር፡፡
በዚህ ደግሞ ትንሽ ቅር ተሰኘሁ፡፡
ትልቅ ትዝታ ጥሎ ያልፋል ብዬ የጓጓሁለትና ስንት ያሰብኩለት ጉዳይ እንዲህ እንደዋዛ እልፍ ማለቱ አስከፋኝ፡፡
ማታ ቤተሰቡ ለእራት ሰብሰብ ብሎ አዲሷ ሰራተኛችን ምን የመሰለ ምስር ወጥ ስታቀርብ ግን ፈገግ አልኩ፡፡

19.04.202508:07
(ከላይ የቀጠለ)
ለአክስቴ በተልባ፡፡ ለቀረነው በእርጎ፡፡ መቀዝቀዙ፡፡ መጣፈጡ፡፡
ከዚያ የማይቀመስ የለም፡፡ ዶሮው፡፡ ስጋው፡፡ ቅቤው፡፡
እኔ ግን ቅድም የጮኸው ሆዴ ይቆለፋል፡፡ ትንሽ እንደጎረስኩ የቅድሙ ሽሮ ያምረኛል፡፡
ባንድነት ምስጋና አቅርበን ከበላን በኋላ ወደ መኝታ፡፡
------
ነጋ!
ፋሲካ!
ቄጠማው ተጎዝጉዟል፡፡ ቡናው ቀራርቧል፡፡ እጣኑ ይጨሳል፡፡ ሁሉም ጸአዳ ለብሷል፡፡ የማያቋርጥ የመልካም ፋሲካ ስልክ ወዲያው ወዲያው ያቃጭላል፡፡
አባዬ ከቡራኬ ጋር ድፎውን ይቆርሳል፡፡
የታደሰ አለሙ ‹‹በቀራኒዮ ላይ ታየ…ታየ ታየ›..›› በቲቪ ማስታወቂያዎች መጀመሪያ ላይ ተደጋግሞ ይሰማል፡፡
ወንድሜ አፈታቱ ከብዶት ከሽንት ቤት መውጣት አቅቶት መሽጓል…
ቤቱ በፌሽታ ተሞልቷል….
አጎቴ ደውሎ ለቁርስ እየመጣን ነው ብሏል….
ከሁሉ በላይ ግን በደሙ የዋጀን ጌታ ተነስቷል!

05.04.202508:17
(ከላይ የቀጠለ)
ከባሏ ጋር በየሆቴሉ ስጋደም፣ ስለ ሚስቱ መኖር እንጂ ምን ዓይነት ሰው እንደሆነች ለማሰብ ሞክሬ አላውቅም፡፡ የዋህና ደግ ሴት ትሆን ይሆን ብዬ ገምቼ አላውቅም፡፡ እኔን መርጦ ጥሏት ቢሄድ፣ ትጎዳ ይሆን ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡
ለፍታ ስላቀናችው ትዳር፣ ደክማ ስላቆየችው ጋብቻዋ፣ ስለ መልካም ሚስትና እናትነቷ፤ በፍጹም አስቤ አላውቅም፡፡
ልጆቹስ? ሁለት ስለመሆናቸው፣ በደምሳሳው በአባትነት እንደሚወዳቸው እንጂ፤ አብሬው በመሆኔ የአባታቸውን ጊዜ እንደተሸማሁባቸው ገምቼ አላውቅም፡፡ ጨዋና ሰው ወዳድ፣ እናታቸውን የሚታዘዙ ቆንጆ ልጆች ስለመሆናቸው አስቤ አላውቅም፡፡ እኔን መርጦ እናታቸውን ቢተው ስሜቷ በተጎዳ እናትና ያለ አባት ወይ ደግሞ
ነጋ ጠባ በሚደበድባቸው እንጀራ አባት የማደግ እጣ ፈንታ ላይ ልጥላቸው ስለመቻሌ አስቤ አላውቅም፡፡
“ፍሬ! መልሺልኝ እንጂ… የት ሄድሽ?” አለ ደቤ፡፡
“ሚስትህና ልጆችህ ጋር ሂድ… ልብሴን አስለቅቄ መጣሁ” አልኩና ሴቶቹ ክፍል ገባሁ፡፡
እንደገባሁ ቀሚሴን ማስለቀቄን ትቼ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡
ለቅሶዬን ጨርሼና በደንብ ያልለቀቀ ብልሹ ቀሚሴን ለብሼ ስመለስ፣ ምግቡ ቀርቧል፡፡
“አልለቅ አለሽ አይደል? አይ ማርኮን…! ፍርዬ በቃ ቤትሽ ድረስ እናደርስሻለን…” አለች ገነት፣ ያለመልቀቁን ስታይ፡፡
በወሬ ብዙም ሳልሳተፍ፣ ምግቡን ለኮፍ ለኮፍ አድርጌ በደቤ የሚሾፍረው መኪና ውስጥ ገብተን መንገድ ጀመርን፡፡
ገነት ከፊት ስትቀመጥ፤ እኔ ከልጆቹ ጋር ከኋላ ተሳፈርኩ፡፡
ማርኮን ተለጥፎብኛል፡፡ የምኖርበትን ሕንጻ አቅጣጫ፣ ልክ እንደ አዲስ ሰው እየነገርኩት ቤቴ ደረስን፡፡
ለምሳውም ለመሸኘቴም ምስጋና አቅርቤ እየተደናበርኩ ቤቴ ገባሁና፤ ቀሚሴን አውልቄ፣ የተበላሸው ቦታ ላይ ብቻ ውሃና ሳሙና አድርጌ የእጅ መታጠቢያው ላይ ማጠብ ጀመርኩ፡፡
አስቸገረኝ፡፡
ይሄን ስጎ ከምንድነው የሠራችለት? ማስቲሽ ጠብ አድርጋበታለች?
ብስጭት ብዬ እዛው ውሃ ውስጥ ዘፈዘፈኩትና ሳሎን ሄጄ ሶፋ ላይ ተዘርፍጬ እንደገና ማልቀስ ጀመርኩ፡፡
ብዙ ሳይቆይ ስልኬ ሲርገበገብ ተሰማኝ፡፡
አየሁት፡፡
ቴክስት፡፡
ደቤ፡፡
ከፈትኩት፡፡
“የኔ ቆንጆ… በጣም ይቅርታ… እንድክስሽ አሥራ ሁለት ሰአት ላይ የለመድናት ቤታችን እንገናኝ? ያቺ የምትወጃትን ነገር ይዤልሽ እመጣለሁ፡፡” ይላል፡፡
ህም፡፡ ደግሜ አነበብኩት፡፡
ከሚያባብል መልእክቱ ይልቅ የማርኮን ልብ የሚያሟሟ ሣቅ ታየኝ፡፡ የገነት፣ “ለመስቀል እንዳትቀሪ… አሪፍ ክትፎ ትበያለሽ” ታወሰኝ፡፡ የአርሴማ እኔን ለመሳም መንጠራራት ውል አለኝ፡፡
አሥር ደቂቃ ቆይቼ፣ “አልችልም… የእኔና አንተ ነገር አብቅቷል፡፡ ተወኝ…” ብዬ መለስኩለትና፣ ሌላ ጭቅጭቅ ውስጥ ላለመግባት ስልኬን አጥፍቼ እግሬን እየጎተትኩ ወደ መታጠቢያ ቤት ተመለስኩ፡፡
ቀሚሴን ከውሃው አውጥቼ አየሁት፡፡ ስጎው ውልቅ ብሎ ወጥቷል፡፡
ቀሚሴ በደንብ ለቅቋል፡፡ ለምን እንደሆነ አላወቅኩም፣ ግን መንፈሴ ሲታደስ፣ የደከመው ሰውነቴ ሲበረታ ተሰማኝ፡፡ 😘😘😘

02.04.202506:44
‹‹በመላ ውደደኝ ፍቅሬ››
----
በሰማሁት ቁጥር የሚገርመኝ ሙዚቃ ነው፡፡
ዘፋኟ የምወዳት ፍቅረአዲስ ነቃጥበብ ናት፡፡
ዜማው ልብ የሚመዘምዙ ዜማዎችን በመድረስ የሚታወቀው የባለቤቷ አበበ ብርሃኔ፡፡
ካልተሳሳትኩ ግጥሙን የጻፈው ደግሞ ተሻገር ሽፈራው ነው፡፡
ስራው በቀደመው ዘመን ህዝቡን ስለ ኤች አይ ቪ ለማስተማር በሲዲ ደረጃ የወጣው የብዙ ምርጥ ድምጻዊያን የህብረት ስራ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ (ስለ እሱ ሲዲ ሌላ ጊዜ እንጫወታለን)
‹‹በድንገት›› ይሰኛል ዘፈኑ፡፡ በሁሉ ነገር የተዋጣለት ነው ግን ለእኔ ከሁሉ በላይ እያደር የሚያስደምመኝ ግጥሙ ነው፡፡
ግጥሙ ስለሚጥም ብቻ አይደለም፤ በእኔ ግምት ያኔም ሆነ ዛሬ ‹‹የህዝብን ንቃተ ህሊና ለማሻሻል›› ከተሰሩ የኪነጥበብ ስራዎች መካከል በእኛ የኪነት ባህል ያልተለመደ አቅጣጫን የጠቆመ ለየት ያለ ግጥም ስለሆነ ነው፡፡
ሰውን ሳይኮንኑ ማስተማር፣ ጥምብ እርኩሱን ሳያወጡና ሳያሸማቅቁ የማያዋጣውን ጉዞ እንዲቀይር ማሳሰብና አመለካከቱን መቀየር፣ ከሁሉ በላይ ግን ባለበት ቦታና ሁኔታ ‹‹አንተም ኪነ ጥበብ ትገባሃለች›› ብሎ ማገልገል ይቻላል የሚል መንገድ ያሳዩ ይመስለኛል የገጣሚው ስንኞች፡፡
አብሶ አይነኬ የሆነውንና በማህበረሰቡ ዘንድ (በይፋ) የተኮነነ ወሲባዊ ባህሪ መኖሩን ባላየ ከማለፍ ይልቅ፣ ‹‹ለአንተም ቢሆን ከሞት ሌላ አማራጭ አለ›› ብሎ በድፍረት፣ በግልጽ መንገድ መጠቆሙ ይገርመኛል፡፡
ኤች አይ ቪ የኢትዮጵያ ወጣቶችን በሚያጭድበት ዘመን የንቃት ዘመቻዎች ሶስቱን ‹‹መ›› ዎች ደጋግመው ያስታውሱን ነበር፡፡
መታቀብ፣ መወሰን፣ መጠቀም፡፡
መታቀብና መወሰን ከማህበረሰቡ የቀደመ እሴት ጋር ስለሚጣጣሙ ብዙ ተብሎባቸዋል፡፡
መጠቀም ግን ‹‹ለእናንተ ቅብዝብዞች ደግሞ ኮንዶም አለላችሁ›› ከሚል ደምሳሳ መልእክት ባለፈ ጠለቅ ብሎ ሲብራራ፣ እንደ መጨረሻ ግን ደግሞ ሕይወት እንደሚታደግ አማራጭ በጥበብ ሲወሳ ያየሁት እዚህ ዘፈን ላይ ነው- ተመካሪዎቹን ሳይኮንን፣ ሳይወቅስ፣ ሳያሸማቅቅ፡፡፡
እየጣፈጠ ሲያስተምር አፍ ያስከፍታል፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው…
ፍቅር አዲስ ድምጽዋን ያዋሰቻት ሴት በራሷ አባባል ‹‹ልቧ የቢራቢሮ አመል ያለውና ለሳር ቅጠሉ የሚማረክ ነው›› ፡፡
ከመጀመሩ የሚያልቅ የቅፅበትና የአፍታ ፍቅር አፍቃሪ፡፡
የድንገት ወዳጅነት ወዳጅ፡፡
በዘፈኑ መጀመሪያና ወደ ኋላ ይህንን ድክመቷን ያለ መሽኮርመም አብራርታ ትነግረናለች፡፡
እሷም ሆነች የዛሬ ፍቅሯ አንድ አበባ ላይ ማረፍ ያልቻሉ ቢራቢሮዎች እንደሆኑ ታስረዳናለች፡፡
ዋናው ቁም ነገር ግን ይሄ አይደለም፡፡
እንዲህ ያሉ ሰዎች መሆናቸው ግን መተኪያ የሌላትን ሕይወታቸውን እንደ ሸክላ እንዳይሰብራት ትሰጋለች፤ ካልተጠነቀቁ፣ "ካልተጠቀሙ" አደጋ እንደሚጠብቃቸው ታውቃለች፡፡
ስለዚህ የአፍታ ፍቅረኛዋን ምን ትለዋለች?
‹‹እስክናርፍ አንድ አበባ ላይ መፅናቱን እስከምንፀና
በመላ ውደደኝ ፍቅሬ ሽፍንፍን ሁንልኝና››
ሽፍንፍን ሁንልኝና!
እንዳልኳችሁ ዘፈኑ በሁሉ ነገር የተዋጣለት ነው ግን ለእኔ ከሁሉ በላይ እያደር የሚያስደምመኝ ግጥሙ ነው፡፡
ዛሬም ለማስተማር የኪነት ስራዎችን የሚሰሩ ከያኒዎች ሁሉ የተሻገር መንገድ ቢያድርባቸው ብዙ ሰው ይታደጋሉ ብዬ አስባለሁ::
https://youtu.be/cQ_gRVd4_ys?si=IE7j7zDa6fdeRE0i

26.03.202506:48
ቢያረፍድም
(ከቡና ቁርስ መጽሐፌ ላይ)
----
ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው በቅርብ የሥራ ባልደረባዬ ግፊት ነበር፡፡
“በፊት የምሠራበት ቢሮ ነው የማውቀው” ብላ ጀምራ፣ ስለ መልካምነቱ ማዛጋት እስከጀምር ድረስ የሚያሰለቸኝ ዝርዝር ውስጥ ገብታ ታወራኝ ነበር፡፡
“በጣም ነው የምትግባቡት፤ በጣም፡፡ ሁለታችሁንም አሣምሬ ስለማውቃችሁ እርግጠኛ ነኝ ትግባባላችሁ” እያለች፡፡
እንድንገናኝ ያላት ጉጉት፣ ግኑኙነታችን እንደሚሠምር ያላት እርግጠኝነት አስገራሚ ነበር፡፡ አብራኝ ስለምትሠራና ስለምትውል፣ ውስጤን አብጠርጥራ የምታውቅ ይመስል፤ አብራው ትሠራ ስለነበር፣ እውነተኛ ማንነቱን አጥርታ ታውቅ ይመስል፣ “አሣምሬ ስለማውቃችሁ” ስትል ይገርመኛል፡፡ በዚያ ሰዐት፣ አዲስ ሰው ለመተዋወቅና አዲስ ፍቅር ለመጀመር ያለኝ ፍላጎት ሞቶ ነበር፡፡
ግን፣
“መቼ ነው ተስፋን የምታገኚው…? መቼ ልበለው…? ዛሬ ይመችሻል…? ዓርብ ይሁን?” እያለች መቆሚያ መቀመጫ ስታሳጣኝ፣ “እሺ” አልኳት፡፡
በዚያ ላይ፣ ከዚህ በፊት እንኳን በዐይነ ሥጋ፣ በፎቶ እንኳን ዐይቼው የማላውቀው ሰው ጋር፣ እራት ለመብላት ስስማማ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ ግን አንዳንዴ አዲስ ነገር መሞከር አይከፋም፣ አይደል?
----
አርፍዶ ነበር፡፡ ሃያ አምስት ደቂቃ፡፡ ዝርክርክ፡፡ ዝርክርክ ወንድ አልወድም፡፡
አርፋጅ፣ ጥፍሩን የማይከረክም፣ ንጹሕ ያልሆነና ሲበላ ሥነ ሥርዓት የሌለው ወንድም አልወድም፡፡
በጣም ነው የሚቀፈኝ እንዲህ ዓይነቱ ወንድ፡፡ ያን ያህልም የጠበቅኩት፣ ለአፍታ ላቆመው ያልቻልኩት የሕይወት ተፈራ ቅመም የሆነ መጽሐፍ “ማማ በሰማይ” መስጦ ይዞኝ ነው፡፡
ሲደርስ፣ ይቅርታውን አዥጎደጎደው፡፡
አለባበሱ ጥሩ፣ ንጹሕና ለዐይን የሚጥም ዓይነት ሰው ሆኖ አገኘሁት፡፡
“ሌላኛው በእምነት ሬስቶራንት ተሳስቼ ሄጄ” ነው አለኝ፡፡ ሌላ በእምነት ሬስቶራንት እንዳለ አላውቅም ነበር ግን ይሁን፡፡
ያዘዝነውን በየዓይነቱ በጥንቃቄና ሳይዝረከረክ በላ፡፡
ወሬ አላበዛም፡፡ እኔ ግን እንዳወራ አበረታታኝ፡፡
እኔ ብቻ ካላወራሁ አለማለቱን፣ ለረጅም ጊዜ ከወንዶች ያላገኘሁት እፎይታ የሚሰጥ ጠባይ ሆኖ አገኘሁት፡፡
ጥሩ ጊዜ አሳለፍን፣ አርፍዶ ከመምጣቱ በቀር፡፡
“አርፍዶም ቢሆን፣ እንኳን መጣ” አልኩ በሆዴ፡፡
ሕይወት ተፈራ፣ በመጽሐፏ መጣም፣ ለጥቂት ሊዘጋበት የነበረውን ቶሎ ቶሎ የማይከፈት የመልካም ዕድል በር ተከፍቶ እንዲቆይ ያደረገችለት ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ታላቅ ውለታዋ እቅፍ አበባ ሊልክላት ወይ ደግሞ ጣባ ሙሉ ክትፎ ሊጋብዛት ይገባል ባይ ነኝ፡፡ እስካፍንጫው የታጠቀን የደርግ መንግሥት፣ “ አፍንጫህን ላስ” ላለች ቆፍጣናና እሳት የላሰች የስልሳዎቹ አራዳ፣ የትኛው እንደሚመጥናት እንጃ እንጂ፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ ስንገናኝ፣ ማኪያቶ ከጠጣን በኋላ እንደ አዲስ በሰፋውና በኤልኢዲ መብራቶች በተጥልቀለቀው የቦሌ ጎዳና ላይ በእግራችን ብዙ ሄድን፡፡
ያኔም ወሬው ሁሉ ከእኔ እንዲመጣ ፈቅዶ ስለራሱ ጥቂት ነገሮች ብቻ ነገረኝ፡፡ ዛሬ ግን ከዚህ በላይ እንዲያወራና ስለማንነቱ እንዲነግረኝ ፈልጌ ነበር፡፡ ወሬን እየጠረቅሁ፣ በመንገዳችን መሀል ቀድሜ ያላየሁት በውሃ የተሞላ ጭቃ ውስጥ በሁለቱም እግሬ ዘው ብዬ ስገባ ግን፣ ሌላ ነገር አስተዋልኩ፡፡ የበሰበሱ የስኒከር ጫማዎቼን ጎንበስ ብሎ ካየ በኋላ፣ ባሸበረከበት፣
“ አውልቂያቸውና ላድርቅልሽ” ሲለኝ ተረገምኩ፡፡
ይሄ ሰውዬ ምስኪን ነው ልጄ፡፡ ምስኪን፡፡
ለዐሥራ አንደኛ ጊዜ ተገናኝተን ቤቱ ስሄድ፣ አቧራ የወረሰውን የሚያምር የዕንጨት የመጽሐፍ መደርደሪያውንና ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን አቧራ የጠጣ ጊታር ጊዜ ወስጄ አጸዳሁለት፡፡
ተመላላሽ ሠራተኛ ነበረችው፣ ግን ላይ ላዩን እንጂ በደንብ አታጸዳ ኖሯል፡፡ ያንን ማድረጌን እንደ ትልቅ ውለታ ወስዶ ፊቱ በፈገግታ በራ፡፡
ከዚያ፣ አሪፍ በቅመም ያበደ ሻይ አፈላልኝ፡፡
ግን ለመክሰስ ካልሠራሁ ብሎ የጠበሰው እንቁላል ፍርፍር፣ ድብን ብሎ አርሮ ነበር፡፡ ያም ሆኖ መሞከሩ አጣፈጠውና ጥርግ አድርጌ በላሁ፡፡
የዚያን ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፈሮቼን ቀመሳቸው፡፡
ከመጠን በላይ ጫን ብሎ አልሳመኝም፤ ለሌላ ነገር ቸኩሎ አላስጨነቀኝም፡፡ ሳም ብቻ አደረገኝ፡፡
ይሄ ጨዋነቱና እርጋታው ከበላሁት በፍቅር የተሠራ መክሰስና ከጠጣሁት አሪፍ ሻይ በላይ ጣመኝ፡፡
ለዐሥራ አራተኛ ጊዜ ስንገናኝ፣ ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሄድ መኝታ ክፍሉ ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ያየሁትን ጊታር አወረደና ሙዚቃ ተጫወተልኝ፡፡ ለካስ ከዚህ በፊት ተጫወትልኝ ስለው፣ “ብዙ ጎበዝ አይደለሁም” ያለኝ ትህትና ይዞት ነው፡፡
የቴዎድሮስ ታደሰን “ እየቆረቆረኝ “ ዘፈነልኝ፡፡ ጊታር አጨዋወቱ ከጠበቅኩት በላይ ድንቅ፣ የእሱ ድምፅ ግን ያን ያህል አልነበረም፡፡
ቢሆንም አብሬው አደርኩ፡፡ ያንን ምሽት፣ በትህትናውና በቴዎድሮስ ዜማ ጭኖቼን ያስከፈተኝ የመጀመሪያው ሰው ሆነ፡፡
-----
ፍቅር ከጀመርን ከጥቂት ወራት በኋላ አንዱን ከሰዐት ከቤቴ መጣ፡፡
መንገድ ላይ ውሎ ሞቆት ስለነበር ቀዝቃዛ ሻወር ሊወስድ ገባ፡፡
ጨርሶ ሲወጣና እኔ ስገባ የተጠቀመበትን ፎጣ ዐየሁት፡፡
ታጥቦ ያልተጨመቀ ብርድልብስ ያህል ረጥቦ፣ ማንጠልጠያው ላይ በሰላም ተሰቅሎ የነበረው የእኔ ደረቅ ሮዝ ፎጣ ላይ ተደርቦ ተሰጥቶ ጠብ… ጠብ… ይላል፡፡
ይሄ ነገር በማይገባኝ ምክንያት ከዚህ በፊት የማውቃቸው ወንዶች ሁሉ፣ ኧረ እንዲያውም ሁሉም ፎጣ የሚጠቀም ወንድ፣ የትም የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ በጣም የሚቀፈኝ ነገር፡፡ እርጥብ ፎጣ፡፡ ጠብ ጠቡ፡፡ ሽታው፡፡
በዚያ ላይ ደረቅ ፎጣዬ ላይ ተደርቦ….
ዛሬ ግን ግድ አልሰጠኝም፡፡
የዚያን ዕለት አብረን አድረን ጠዋት ሻወር ሲገባ አድርጌ የማላውቀውን፤ ለማንም የማልሰጠውን ሽቶ የተቀባ ደረቅ ፎጣዬን እንካ አልኩት፡፡
ነግቶ ቁርስ ስንበላ፣ ፊልም ላይ እንዳሉ ወንዶች ሳይንበረከክ፣ እንደ ዘመኑ አርቲስቶች ሳይቅለበለብና ወሬ ሳያበዛ፣ ቅልብጭ ያለች ሚጢጢ ነጭ ፈርጥ ያላት ቀጭን የወርቅ ቀለበት፣ ከአንዲት ቀይ ጽጌረዳ አበባ ጋር አውጥቶ ሰጥቶ እንዳገባው ጠየቀኝ፡፡
ቀለበቷ፣ አይነግቡ ባትሆንም፣ ለወራት ሳያሳልስ ቆጥቦ እንደገዛት ዐውቃለሁ፡፡ ያ የበለጠ እንድወዳት አደረገኝ::
---
ከስድስት ዓመታት ትዳርና ሁለት ለማየት የሚያሳሱና እሱን የሚመስሉ ሴት ልጆችን ካፈራን በኋላ፣ ቀጭኗ ቀለበት ጠባኝ ብትቀመጥም፣ ያቺ አበባ- ከጊዜ ብዛት ከቀይ አበባነት ይልቅ ለቡኒ ዱቄትነት ብትቀርብም- አሁንም በክብር ያስቀመጥኳት ክፍት ሳጥን ውስጥ አለች፡፡
ይሄ ሰው ቢያረፍድም እንኳንም መጣ፡፡

17.03.202507:25
‹‹ ልተኛበት››
--------
ብቸኛው ደስ የሚያሰኛት ነገር እንቅልፍ ነው፡፡
ከጠዋቱ 12.30፡፡
አላርሟ ጮኸ ፡፡ አልተንቀሳቀሰችም፡፡
ስልኳን አንስታ ሰዓቱን ተመለከተች፡፡
አቃሰተችና ፊቷን በብርድልብሱ ሸፍና ጥቅልል ብላ ተኛች፡፡
አላርሟ እንደገና ጮኸ፡፡
12.35፡፡
እንዲጮኽ ተወችው፡፡ እሪታው ትንሽ ቤቷን እስኪሞላት፡፡
ትንሽ ዝም አለና ደግሞ ድጋሚ ጮኸ፡፡
12.40፡፡
ትርጉም የሌለው ነገር አጉረመረመች፡፡
ስልኳን አነሳች፡፡ አላርሙን ፀጥ አሰኘች፡፡
ስልኳ ላይ አፈጠጠች፡፡
ከእህቷ የተላከ ቴክስት፡፡ ‹‹እማዬ ስለጠፋሽባት ተጨንቃለች፡፡ ደውይልኝ፡፡››
አልመለሰችላትም፡፡
ስልኩን አሽቀንጥራ ወረወረችና ዘገም ብላ ከአልጋዋ ወጣች፡፡
ሻይ አፈላች፡፡ ቁርስ የመስራት እንጥፍጣፊ ጉልበት ስላልነበራት ባዶ ሆዷን ከቤት ለመውጣት ወሰነች፡፡
መስታወት ፊት ቆማ የሌላ ሰው ፊት ይመስል በትኩረት የመረመረችውን ያባበጠ ፊቷን እንደነገሩ ታጠበች፡፡
ስልኳ ድዝዝዝዝ አለ፡፡
ከአለቃዋ የተላከ ቴክስት፡፡
‹‹ሉዓላዊት፣ ሪፖርቱን መቼ ነው የምትልኪልኝ? ጨርሰሽ ማስረከብ የነበረብሽ እኮ ትላንት ነበር!››
ስልኳ ላይ አፈጠጠች፡፡
ሪፖርቱን አልጀመረችውም፡፡
ስልኳን የነበረበት ቦታ መልሳ አስቀመጠች፡፡
እንቅልፍ ያልጠገቡ ዓይኖቿ ከብደዋታል፤ ፊት ለፊት ያገኘችውን ልብስ እንደነገሩ ለበሰች፡፡
ቦርሳዋን አነገበች፡፡
አንገቷን አቀርቅራ፣ ሰላም የሚሏትን ጎረቤቶቿን ያልሰማች መስላ ጥርቅም አድርጋ ዘግታ፣ የታክሲውን ሰልፍ ተቀላቀለች፡፡
ደጋግማ አዛጋች፡፡
ብቸኛው ደስ የሚያሰኛት ነገር እንቅልፍ፣ አንድ የቀራት የደስታ ምንጯ መተኛት ነው፡፡
በመጨረሻ አንዱ ታክሲ ውስጥ ገባች፡፡
ጭስ ጭስ ከሚል ሰውዬ ጋር ተነባብራ ተቀመጠች፡፡
ስታየውና ሲያያት ፈገግ አለ፡፡
ፊቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞረች፡፡
ቢሮ ገብታ የታከተ ፊቷን እንደያዘች፣ የደከመ ሰውነቷን ዴስኳ ላይ ጎለተች፡፡
አለቃዋ መጣና ስለሪፖርቱ ጠየቃት፡፡
‹‹አሁን እልክልሃለሁ›› አለችው፤ በጥርጣሬ አይቷት ሄደ፡፡
ኢሜይሏን ከፈተች፡፡
14 ያልተነበቡ ኢሜይሎች፡፡ 3 አስቸኳይ ነን የሚሉ፡፡
አንዱንም አላነበበችም፡፡
ስልኳ ድዝዝዝዝ አለ፡፡
ከጓደኛዋ ሙባረክ የተላከ ቴክስት፡፡
‹‹ጠፋሽብኝ እኮ፣ እንዴት ነሽ?››
አልመለሰችለትም፡፡
ምሳ ሰዓት ደረሰ፡፡
ቢሯቸው ስር ከሚገኘው ትንሽዬ ምግብ ቤት ልሙጥ ሽሮ አዘዘች፡፡
መጣላት፡፡
አራት ትንንሽ ጉርሻዎችን እንደጎረሰች አፏ ውስጥ እየተንገዋለለ ሲያስቸግራት ትሪውን ገፍታ እጇን ለመታጠብ ከዴስኳ በቀስታ ተነሳች፡፡
ስትመለስ የስራ ባልደረባዋ ሓየሎም-
‹‹ቡና ልንጠጣ ልንወጣ ነው…አብረሽን አትመጭም?›› ብሎ ጠየቃት፡፡
“አልመጣም” አለችው፡፡
አለመሄድ ይሻላል፡፡ ተሂዶስ ምን ይደረጋል?
በተቀመጠችበት ሶሻል ሚዲያውን አሰሰች፡፡
ጓደኞቿ በየሀይቁ፣ በየምግብ ቤቱ፣ በየኮንሰርቱ የተነሷቸውን ፎቶዎች አየች፡፡
ሲስቁ፡፡ ሲጫወቱ፡፡ ሲኖሩ፡፡
ልቧ መምታት የታከተው ያህል ድም ድሙን ሲያዘገይ፣ ሲያለዝብ ተሰማት፡፡
የሰው ልጣጭ፣ የሰው ፍርፋሪ፣ የሴት ቁሩ የሆነች መሰላት፡፡
ቀኑ እንደ ቀንድ አውጣ ተጎተተባት፡፡
እንደ ስልባቦት ተዝለገለገባት፡፡
እንቅልፍ በተቀመጠችበት አንጎላጃት፡፡
ደህና ነገር ሳትሰራ ስምንት ሰአት ሲሆን አለቃዋ መጣና -
‹‹ሪፖርቱስ?›› አላት፡፡
‹‹ልጨርስ ትንሽ ነው የቀረኝ›› አለችው፡፡
ዋሸችው- በቅጡ አልጀመረችውም፡፡
አስራ አንድ ሰአት ሲሆን እንደሚያናድደው ያወቀችውን የማይረባና በስህተት የተሞላ የይድረስ ይድረስ ስስ ሪፖርት ላከችለት፡፡
ከቢሮ ወጣች፡፡
የታክሲ ሰልፍ ተሰለፈች፡፡
ቤቷ ገባች፡፡
እንደገባች በምሽት ብርሃን የተጥለቀለቀች ቤቷን መጋረጃዎቿን በሙሉ በመዝጋት አጨለመቻት፡፡
ሚጢጢውን የራስጌ መብራት ብቻ አበራች፡፡
ኢንዶሚኗን አዘጋጀች፡፡
እህቷ ዛሬ ብቻ ለአምስተኛ ጊዜ ደወለች፡፡
አላነሳችላትም፡፡
ስልኳ ሁለቴ ጠርቶ አቆመ፡፡
ወዲያው የእህቷ የዋትስ አፕ ቮይስ ሜይል ገባ፡፡
አላዳመጠችውም፡፡
ጨዋም ራቷን በዝግታ በላች፡፡
እላዩ ላይ ሁለት ብርጭቆ ውሃ ቸለሰችበት፡፡
የሰራችበትን ድስትና የበላችበትን ጎድጓዳ ሰሃን የእቃ ማጠቢያዋን የሞላው የቆሻሻ እቃ ክምር ላይ ጨመረች፡፡
በረሮ ይርመሰመስበታል፡፡ ዝምብ ያንዣብበታል፡፡
ይሸታል፡፡
በጊዜ ጥቅልል ብላ ተኛች፡፡
--
በሚቀጥለው ቀን፣ ቅዳሜ አርፍዳ ነቃች፡፡ አራት ሰአት ላይ፡፡
ስልኳን አየች፡፡
ሌላ ያላነሳችው የእህቷ ስልክ፡፡
ሌላ ቴክስት ከሙባረክ፡፡ ‹‹በሰላም ነው…ደህና ነሽ ግን አይደል?›› የሚል፡፡
አልመለሰችለትም፡፡
ስልኳን ለብዙ ደቂቃ ፍዝዝ ብላ አየች፡፡
ስልኳ ድዝዝዝዝ አለ፡፡ እህቷ ናት፡፡ ቴክስት፡፡
‹‹ደውይልኝ፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ነው!››
ስልኳን በአፍጢሙ ደፋች፡፡
ማንንም ማውራት አትፈልግም፡፡
የምታገኛቸው እና የምታወራቸው ሰዎች ቁጥር ከእለት እለት እያሽቆለቆለ፣ እያደር እየሳሳ ነው፡፡
የማታውቀው ሃይል እየጎተታት ወደ ማታውቀው ጥቁርና ጥልቅ ጉድጓድ እየሰመጠች እንደሆነ ይሰማታል፡፡
የስቱዲዮ ኮንዶሚኒየሟ ግድግዳዎች በየቀኑ ጠበብ…ጠጋ…ቀረብ እያሉ ጨፍልቀው ፊጪጭ አድርገው የሚያስቀሯት ያህል ይጨንቃታል፡፡
ከነጋ መጋረጃዎቹን አልከፈተችም፣ እህል በአፏ አልዞረም፡፡
ቀኑን ሙሉ ተኝታ ዋለች፡፡

አስራ አንድ ሰዓት ሲሆን ሞረሞራት፡፡
ሁለት ካርቶን አቡወለድ ብስኩት በላች፣ ግብዲያውን የላስቲክ ሚሪንዳ ጭልጥ አድርጋ ጠጣች፡፡
ተመለሳ ተኛች፡፡
ስልኳ ድዝዝዝዝ ማለቱን አቁሟል፤ ግን አሁንም የብቸኝነት ስሜት አልተሰማትም፡፡
ቆይታ እህቷ ደግማ ደወለች፡፡
አላነሳችም፡፡
ቴክስት ላክች፡፡
‹‹በእማማ ሞት ይዤሻለሁ፤ ደህና ነኝ ብቻ በይኝ››
ምን እንደምትላት ግራ ገባት፡፡ ‹‹ደህና አይደለሁም›› ይባላል እንዴ?
አይባልም፡፡
ማስመሰሉ ይቀላል፡፡
የከበባት ጽልመት ጨርሶ ሊውጣት፣ የተጠናወታት ድባቴ ቆረጣጥሞ ሊበላት ደርሷል፡፡
ራሷን ከድባቴዋ መለየት እስኪያቅታት፣ ገላዋ ሰው በማያየው ጥላሸት የተወረሰ፣ ታጥቦ በማይጠራ ጭቅቅት የተለወሰ እስኪመስላት ጭንቅ ብሏታል፡፡
ውስጧን ያሳክካታል፡፡
ጣራ ጣራውን እያየች ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡
-----
በነጋታው ማልዳ ተነሳች፡፡
ስልኳ ድዝዝዝዝ አለ፡፡
የሙባረክ ቴክስት ነው፡፡ ‹‹በአላህ! አሳሰብሽኝ እኮ…እባክሽ ደውይልኝ…ምን እንደሆንሽ ብቻ ንገሪኝ››
ምን ብላ እንደምትነግረው ቸገራት፡፡
‹‹ተወኝ ልተኛበት›› ማለት ይቻላል?

መልሳ ተኛች፡፡

10.03.202507:18
ለቦይፍሬንዴ ምስር ወጥ የሠራሁ’ለት
(ክፍል አንድ)
-----------
ቀኑ እንደ ሌላው ቀን ነበር።
አዲስና የሕይወቴን ጣእም እስከወዲያኛው የሚቀይር ነገር የሚከሰትበት ቀን ስለመሆኑ ምንም አይነት ምልክት አልነበረም፡፡
ለምሳሌ- አንዳች ሃይል ገፋፍቶኝ መስታወት ፊት ቆሜ፣
‹‹ሰላሚና! ይህንን መልክሽን በደንብ አይተሽ ጥገቢው፤ ከእንግዲህ ልጅነት የለም፡፡ ዛሬ ልጃገረድነትሽ አክትሞ ሴት የምትሆኚበት ታላቅ ቀን ነው›› በይ በይ አላለኝም፡፡
ሌላ መደበኛ ቅዳሜ ነበር፡፡
እቅዳችን ዘወትር ቅዳሜ ቅዳሜ እንደምናደርገው የእሱ ቤት ተገናኝተን መጫወት፣ መሳሳም፣ መተሸሸት፣ መገልፈጥ ደግሞ መጫወት፣ መሳሳም፣ መተሸሸትና ደግሞ መገልፈጥ፤ ከዚያ የአባቴን የማትዛነፍና የማትጣስ የ12.30 ሰዓት እላፊን ቀድሜ፣ ጀምበር ጠልቃ ሳታቃጥርብኝ ቤቴ ክትት ማለት፡፡
----
ምስክር የሌለው ስምምነት ነበረን፡፡
ከመሳሳምና ላይ ላዩን ከመቀማመስ ያለፈ ነገር የምናደርገው ስንጋባ ነው የሚል ስምምነት፡፡
ወንድ አይደል…?
ራሴው አበጀህ ብዬ ገደል እንዳልከተውና ቃልኪዳናችን እንዳይፈርስ፣
አንዳንዴ ደግሞም ‹‹ገገማ ናት›› ብሎ ስሟን በጠየቃት ቀን ቀሚሷን በምትገልብለት ሌላ ሴት እንዳይቀይረኝ ፣ በስምምነታችን እንዳመነበት ደጋግሜ እጠይቀው ነበር፡፡
ወላጆች ከዳይፐር ከተላቀቀ ያልሰነበተ ትንሽ ልጃቸውን ለረጅም ጉዞ ሲያሰናዱ፣
‹‹እርግጠኛ ነህ ግን…ከቤት ሳንወጣ ሽንትህን አትሸናም?›› እያሉ ደጋግመው እንደሚጠይቁት፡፡
እንዲህ እንዲህ እያልን…
‹‹ሃሳብህን አልቀየርክም አይደል?›› ስለው ‹‹ለምን እቀይራለሁ?›› ሲለኝ፣
‹‹አሁንም ታምንበታለህ አይደል?›› ስለው ‹‹በደንብ ነዋ›› ብሎ ሲመልስልኝ፣
‹‹ግን እሷን ደስ ይበላት ብለህ እየተጎዳህ እንዳይሆን? ›› ስለው ‹‹አምኜበት ነው›› ሲለኝ፣
‹‹አሁንም አቋምህ ያው ነው አይደል..? ላረጋግጥ ብዬ ነው›› እያልኩ ስጠይቀው፣
‹‹እኔ አቋሜ በየቀኑ የሚቀያየር ሰው አይደለሁም›› እያለኝ እዚህች ቅዳሜ ላይ ደርሰን ነበር፡፡
ያ ሁሉ መሃላና መገዘት እንደዋዛ አፈር ድሜ ሊግጥ፡፡
ስምምነታችን ያለ ምስክሮች እንደጸና ያለ እማኝ ሊፈርስ፡፡
----
የተዋወቅነው ስድስት ኪሎ ካምፓስ ዋናው ካፌ ውስጥ ነበር፡፡ ፓስታ በእጁ እያቦካ፡፡
ቀፈፈኝ፡፡
‹‹ምን አይነቱ ኒያንደርታል ነው?›› ብዬ አሰብኩ፡፡
‹‹ሹካ እንደሚሰጠን ታውቃለህ አይደል?›› አልኩት፡፡
ፈገግ ብሎ ትከሻውን ወደላይ ሰበቀና፣
‹‹አውቃለሁ፡፡ የሚጥመኝ በእጄ ስበላው ስለሆነ ነው›› ብሎ መለሰልኝ ኤክስሬይ የሚያነሱ በሚመስሉ መርማሪ አይኖቹ እያየኝ፡፡
ባልገባኝ ምክንያትና ፍጥነት በአበላሉ እንዳልተዘገነንኩ በመልሱ እና በአስተያየቱ ደግሞ በሃይል ተወሰወስኩ፡፡
ሆ፡፡
ሆሆ፡፡
ሆሆሆ፡፡
ጮክ ብሎ ሳይናገር የብዙ ሰዎችን ጆሮ የሚያገኝ ዓይነት ሰው ሆኖ አገኘሁት፡፡
የተራቀቀ ነገር ስለሚያወራ አይደለም የአድማጭ ገድ ያለው፤ ተራውን ነገር አራቅቆና አሳምሮ ስለሚናገር እንጂ፡፡
የኔ ለዛ በዝ፡፡ ጨዋታ ሲያውቅበት፡፡
ሰው አክባሪ፣ ጨዋ፣ ሲቀርቡት ደግሞ በጣም አስቂኝ ነበር፡፡ መልኩም ሂድ ወደዚያ የሚባል አይነት አልነበረም፡፡
እና ታዲያ አንዲት ሴት ከአንድ ወንድ ከዚህ ሌላ ምን ትፈልጋለች?
ተጣበቅኩበት፡፡ እንደ አልቅት ተጣበቅኩበት፡፡
---
ከሁለት አመት በኋላ ተመርቀን ስንወጣ እሱ ቤት ሲከራይ እኔ እዚያው የቤተሰቤ ቤት መኖሬን ቀጠልኩ፡፡
ቤቱ በሄድኩ ቁጥር ምግብ አበስልለት ነበር፡፡
ምግብ መስራት ስለምወድ ሳይሆን እሱን ስለምወደው፡፡
ሰርቼ ባበላሁት ቁጥር የእናቱ ምስር ወጥ (ቤተሰቦቹ ባህርዳር ናቸው) እንዴት እንደናፈቀው እየተነጫነጨ ይነግረኝ ስለነበር ዛሬ ደህና ምስር ወጥ ልሰራለት ሰፊ ሰአት ይዤ ሄድኩ፡፡
ጨዉ ላይ ለቀቅ ከማለቴ በስተቀር ተዋጥቶልኝ ነበር፡፡
ተስገብግቦ በላው፡፡
ቆይቶ እንደገባኝ ግን እንደዚያ ተስገበግቦ በላይ በላዩ ያስጎሰረው ወጡ በጣም ጣፍጦት ወይ ደግሞ የእናቱን ምስር ወጥ የሚጠጋ ሆኖ ስላገኘው አልነበረም፡፡
ነገሩ ከምስር ወጥ ተፈጥሮ ጋር የሚገናኝ ነው፡፡
ለካስ ምስር ወጥ እንደ ፈረንጆቹ ኦይስተር እዩኝ እዩኝ ፣ አለሁ አለሁ ሳይል ሁነኛ የሽፍደት ቀስቃሽ፣ ስሜት አቀጣጣይ፣ ዋናው የአልጋ ላይ እሳት አራጋቢ ኖሯል፡፡
እኔ የዋኋ ልጅ በገዛ እጄ የወንድነት እጅ ቦምቡን ቀለበት በምስር ወጥ ማላላትና ማውለቄን መች አውቄው…?
አጅሬ በልቶ ጨርሶ በቅጡ እጁን ሳይታጠብ ምን አደረገ?
እንደ ጦጣ እንጣጥ ብሎ እላዬ ላይ ፊጥ፣ እንደ እባብ ሁሉመናዬ ላይ ጥምጥም፣ ታዳኙን እንበረከከ አንበሳ ክምር አለብኝ፡፡
----
የዛሬን አያድርገውና ገና ካዛንችስን እንደ ሰው ‹‹መጥቼ አጣሁሽ›› ብለን ሙሾ ሳናወርድላት በፊት ቶታሉ አካባቢ ጠባብ አንዲት ክፍል ቤት ነበር የተከራየው፡፡
እኔው ራሴ ነበርኩ ከጨርቆስ ያገለገሉ የቤት እቃዎች ሰፈር ያጋዛሁት፡፡ በቁጥር ሶስት ደህና የቤት እቃዎች ብቻ ነበሩት- አልጋ፣ ሚጢጢ የእንጨት ወንበርና ነካ ካደረጉት እያቃሰተ የሚንቀጠቀጥ ጠረጴዛ፡፡
ሁለት እንግዳ ቢመጣበት አንዱ አልጋ ላይ ለመቀመጥ የሚገደድበት ለምቾት ሳይሆን ለመክረም የተሰናዳ ሚጢጢ ቤት፡፡
----
ያንን ሰበበኛ ምስር ወጥ በሰራሁበት ቅዳሜ ምስሩ ከመሰራቱ በፊት ሁሌም ቅዳሜ እንደምናደርገው እየተቃበጥን ነበር፡፡
ከበላ በኋላ ግን ለወትሮው በማይረቡ ወሬዎች የሚቆራረጠው መሳሳምና መተሻሸታችን በሁለት መቶ እጥፍ ፈጥኖና ጎልብቶ ትንፋሽ አጠረኝ፡፡
ሌላ ጊዜ ቢሆን በሳም ሳም መሃል ‹‹ይህች ሴትዮ ግን ለዚህች ቤት ይሄን ሁሉ መክፈልህ ሳያንስ ባንዴ አምስት መቶ ብር ስትጨምር አታፍርም?…›› አይነት ነገር ወሬ እከት ነበር፡፡
መደባበሱን ገታ አድርጌ ‹‹ስማ…ዛሬ ቀሃስ ያስተማረኝን ክፉ የእንግሊዝ አስተማሪዬን አግኝቼ…›› የሚል ወሬ አስገባ ነበር፡፡
ዛሬ…አሁን ግን ሁሉ ነገር ተገለባበጠ፡፡
(ክፍል ሁለትን ነገ በዚሁ ሰዓት ይጠበቁ)

ሌላ ፋሲካ!
++++++++
ሰሙነ ሕማማት
-----
የሆሳእና እለት ሰርቼ ያጠለቅኩት የዘምባባ ቀለበቴ አሁንም ጣቴ ላይ ነው፡፡
ይህን ሳምንት መሳሳምና መጨባበጥ ክልክል ነው፡፡
ለምን ተከለከለ ስንል የትልልቅ ሰዎች መልስ ‹‹ይሁዳ ጌታን የካደው ከሳመው በኋላ ስለሆነ ፡፡›› የሚል ነው፡፡
አንዳንድ የሰፈር ልጆች ይህንን ይረሱና ሲጨባበጡ ያዩ ወላጆች ‹‹አዬ…መጥኔ ለእናንተ ልጆች…መጥኔ…!›› እያሉ ይራገማሉ፡፡
የልጆችን ሳቅና ሁካታ ስትሰማ የምታዝነው አያቴ ልብም አደብም እንድንገዛ፣ ስለ ሰሙነ ሕማማት- ስለ ሕማማት ሳምንት ዳግም ታስረዳናለች፡፡
‹‹ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያሉት ቀናት ጌታ በፈቃዱ ከዲያቢሎስ እስራት ነጻ ሊያወጣን ስለ እኛ የተቀበላቸውን መከራዎች የምናስታውስበት ሳምንት ነው›› እያለች ታስተምናለች፡፡
ጸሎተ ሐሙስ
----
የጸሎተ ሐሙስ እለት ከክፍለሃገሩ የሚመጣን ሰው የጫነ አውቶቢስ አዲሳባን ማጨናነቅ ይጀምራል፡፡
በየቤቱ በጎላ ድስት ጉልባን ይቀቀላል፡፡ ቡና ይፈላል፡፡ ጉልባኑ የቡና ቁርስ ሆኖ ለጎረቤት ይከፋፈላል፡፡ በዚህ ቀን ሁሉም ቤት ጉልባን አለ፤ ሁሉም ሰው ቤት ያለን ነገር ሁሉም ሰው ከሚያስፈልገው በላይ ይቀቅልና ስንት ጉልበት የፈሰሰበት እድለ ቢስ ጉልባን የዚያን እለት ሳይበላ ያድራል፤ ለቀናት ሳይቀመስ ይደፋል፡፡
ሃይማኖትዋን አጥባቂዋ አክስቴ ዘንድሮም አክፋይ ናት፡፡
ከስቅለት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ዘጠኝ ሰአት ምግብ አትነካም፣ ውሃም ፉት አትልም፡፡
መጋረጃዎቹን አውርዱና፣ ምንጣፉን አውጡና፣ ቆሻሻ ልብስ ሰብስቡና እጠቡ እንባላለን፡፡
የቤቱን የመስታወት መስኮት በሙሉ ብዙ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ፈጅተን እናጸዳለን፤ ጣውላውን በሰም እንወለውላለን፡፡ የማንጠርገው ቆሻሻ፣ የማናፀዳው አቧራ የለም፡፡ እንደ እማዬ ምኞት ቢሆን ደመና ያዘለውን ሰማይ ሳይቀር ተንጠራርተን ጠረግ ጠረግ እናደርግ ነበር፡፡
ፍግፈጋውና አጠባው ሲያልቅ ሶፋና ወንበሮቹን ቦታ እናለዋውጣለን፡፡ አንዲት እቃ ሳንቀይር የሳሎናችንን መልክ እንቀይራለን፡፡
አመሻሽ ላይ ኢቲቪ ቅዱስ ፓትሪያርኩና ብፁአን አባቶቻችን የታናናሾቻቸውን እግር ሲያጥቡ ያሳያል፡፡
አፋችንን ከፍተን ስናይ አያቴ፣
‹‹ ብጹእ አባታችን እንዲህ የሚያደርጉት ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለማሳየት ነው›› ብላ ሁልጊዜ እንደምትነግረን ሁሉ ዛሬም ትነግረናለች፡፡
እማዬ የዶሮ ዋጋ ስለመጨመሩ አንስታ ትማረራለች፡፡
ስቅለት..
------
ጠዋቱን በተረፈ የፅዳትና ገበያ ስራ ላይ ታች ስንል፣ ስንባትል እናረፍድና ነጠላዎቻችንን ለብሰን፣ መስገጃ ምንጣፎቻችንን አንግበን በህብረት ወደ ቤተክርስትያን እንተማለን፡፡
ሁላችንም እንደ አቅማችን ስንሰግድ ምናችንም የማይዋጥላት እማዬ እያንዳንዳችንን በየተራ ስታይ ትቆይና ፣
‹‹እንደሱ አይደለም…እንደዚህ ነው›› ብላ ትገሰጸናለች፤ ‹‹ይህችን ሰግዳችሁ ልትቀመጡ…ልጆች ገና ካሁኑ ሰንፋችሁ…›› ብላ ታዝንብናለች፡፡
ወፍራም ፍራሽና ትንሽ ድንኳን ይዘው የመጡ ሃብታም ሴቶችን እያየች ‹‹ቱ…ቱ…እነዚህ ደግሞ መዝናኛ አደረጉት እንዴ..መአት ሊያወርዱብን! ›› ትላለች፡፡
እማዬ ሰምታ እንዳትቆጣን በቀስታ፣
‹‹ስትራፖ ያዘሽ.. እኔንም… እኔንም ›› እየተባባልን ሳይጨልም ቤት እንገባለን፡፡ ትላንት ያላለቀው፣ መድረቅ የጀመረው ጉልባን ሲቀርብልን እንነጫነጫለን፡፡
አክስቴ የአክፋይ ጾሟ ላይ ናት፡፡ አልጠወለገችም፡፡ እንደውም ፊትዋ አንጸባርቆ ፈካ አለ ልበል…?
ይልቁንስ አውልቂ ስባል እምቢ ብዬ ያቆየሁት የዘንባባ ቀለበቴ ጣቴ ላይ ጠቁሯል፡፡ እጥለዋለሁ፡፡
ቀዳም ሥዑር
------
አያታችን ጉልበቷ ስር ኮልኩላን፣
‹‹ይህች ቅዳሜ የተሻረች ቅዳሜ ናት›› ብላ ስታስተምረን ለምን እንደተሻረችም ትነግረናለች፡፡ ከሌሎች ቅዳሜዎች ተለይታ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል ነው›› እያለች፡፡
ረፈድ ሲል እማዬ እንደ ቦርሳ አንጠልጥላኝ ሾላ ገበያ እንሄዳለን፡፡
ሁለት ዶሮ ለመግዛት አራት ሰአት እንዞራለን፡፡
መጨረሻ ላይ የምትገዛው ግን መጀመሪያ ያየናቸውን ዶሮዎች ነው፡፡
ከዚያ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ የተረሳ ቅመማ ቅመም፣ ኮባ….ስንቱን ነገር እንገዛና ተሸክመን ቤት እንደገባን ‹‹ውይ ሎሚውን ረሳን›› ብላ ትበሳጫለች፡፡
ሁሌም ሎሚ መግዛትን እንደረሳች ነው፡፡
ብር አስጨብጣኝ መንገድ አቋርጦ ያለው ጉሊት ትልከኛለች፡፡ ‹‹ብርር ብለሽ ገዝተሽ ነይማ›› ብላ፡፡
እምባ እምባ እያለኝ እሄዳለሁ፡፡ ስመለስ ግን ፈገግ ብዬ ነው፡፡
አመጣጥኜ ባስተረፍኳት ሳንቲም ደስታ ከረሜላዬን እገዛና አንዱን ሎሚ በጥርሴ ዘንጥዬ ከፈነከትኩት በኋላ ደስታ ከረሜላዬን ክትት፡፡
እሱን ምጥጥ ምጥጥ እያደረግኩ፣ በደስታ እየነጠርኩ፣ መንገዴን አሳጥሬ ቤቴ ግብት፡፡
‹‹መልስ የታለ›› ስትለኝ ‹‹ኮመዲኖው መሳቢያ አደርጌዋለሁ›› ብዬ ከጴጥሮስ በላይ ስንት ጊዜ ሽምጥጥ፡፡
ከሰአት….
አባዬ በግ ሊገዛ ከጓደኞቹ ጋር ይሄዳል፡፡
በመብሰል ላይ ያለው ድፎ ዳቦ የኩበቱን ሽታ አሸንፎ ሆድ የሚቦረቡር መአዛውን ይለቃል፡፡
ታላቅ ወንድሜ ቤት ውሰጥ ያለውን ቢላ በሙሉ እያፏጨ እያጋጨ ይስላል፡፡
ምስኪን ዶሮዎች ጉዳቸውን ሳያውቁ አጠገቡ ሆነው ያሽካካሉ፡፡
ጥሬ ስታቀብላቸውና ስታጫውታቸው የዋለችው ትንሽዋ እህቴ ምን ሊፈጠር እንደሆነ ስለገባት ማልቀስ ትጀምራለች፡፡
ነገ ቅልጥም ከመላላጫ እንደማትነጭ ዛሬ፣ ‹‹በማርያም አትግደሏቸው›› ብላ ትለማመጣለች፡፡
የዶሮ ሽንኩርት መቁላላት ይጀምራል፡፡ የዶሮ መንፊያ ቀሰም፣ የተከተፈ ሎሚ፣ የተቀጠቀጠ ነጭ ሽንኩርት፣ የተሳለ ቢላዋ፣ ሊቀቀቀል የተዘጋጀ እንቁላል፣ የተወዘተ የመርቲ ጣሳ በየቦታው ይታያል፡፡
ሁለት ሰአት ተኩል ገደማ የቅዳሜ ስኡር እንግልት ከሌላው ጊዜ ቀድሞ ያደክመኝና ማንጎላጀት እጀምራለሁ፡፡
ኢቲቪ Jesus of Nazarethን ያሳያል፡፡ እማዬ ዋ ዶሮ ሳይታረድ ትተኚና ትለኛለች፡፡ ‹‹ከእንግዲህ ልጅነት የለም እኮ…ዶሮ መገነጣጠል ተማሪ እንጂ›› እያለች ቀዝቃዛ ውሃ ትረጨኛለች፡፡
ከዶሮው ቁሌት ላይ ቀንሳ በትንሽዬ ድስት ተአምረኛ፣ ዶሮን የሚያስንቅ ሽሮ ትሰራለች፡፡ ከአክስቴ በስተቀር ተሰብስበን ዶግ አመድ እናደርገዋለን፡፡
‹‹ይኄ ሽሮ ሌላ ጊዜ እንዲህ የማይጣፍጥ›› እላታለሁ፡፡
‹‹የዶሮ ቁሌትና የሽሮ ቁሌት አንድ ነው እንዴ አንቺ ከረፈፍ›› ትለኛለች፡፡
ያን ጊዜ ዶሮዎቹ ታርደዋል፡፡
ጨዋታው ቀዝቀዝ ማለት ጀምሯል፡፡ ከየቤቱ የሚወጣው ጭስ ሰማዩን አስጨንቆታል፡፡
አክስቴ ከጎረቤቶች ጋር ቤተ ክርስትያን ለማንጋት ሄዳለች፡፡
ስምንት ሰአት ተኩል ሲል ቤቱ ፀጥ እረጭ ይላል፡፡ ዶሮው ከምድጃው ወርዷል፡፡
እኔ ቲቪው ፊት ተኝቻለሁ፡፡
እናቴ ‹‹ተነሽ›› ብላ ትቀሰቅሰኛለች፡፡
ሌሎቹንም ቶሎ እየዞርሽ ቀስቅሺ ብላ ታዘኛለች፡፡
የቤተክርስትያኑ ደወል ልብ በሚሰውር ሁኔታ ያቃጭላል፡፡ የትንሳኤ መዝሙር ከሩቅ ይሰማል፡፡
አክስቴ ከቤተክርስትያን ትመለሳለች፡፡
ብትደክምም ነጭ በነጭ ለብሳ እንደ ጨረቃ ታበራለች፡፡ የጌታን መነሳት ልታበስር የተላከች መልአክ መስላለች፡፡
ሙሉ ቤተሰቡ ጠረጴዛውን ከቦ ይቀመጣል፡፡
ሊፈሰክ ነው፡፡ ልንፈስክ ነው፡፡ ሊፈሰክ ነው፡፡
ተፈሰከ፡፡
ጾም ተፈታ፡፡
ግን በዶሮ አይደለም፡፡ በስጋ አይደለም፡፡ በቅቤም አይደለም፡፡

05.04.202508:12
የትርፍ ጊዜ ሥራ
(ክፍል ሁለት)
⚙️⚙️⚙️
“ቀሚስሽ በጣም ያምራል” አለች ገነት፣ ምግብ ቤቱ ውስጥ ገብተን እንደተቀመጥን፡፡
“ይሄ?” አልኩ፣ በመገረም ቀሚሴን እያየሁ፡፡ ተራና ረዘም ያለ ነጭ ቀሚስ ነው የለበስኩት፡፡
“አዎ… ቅልል ያለ ነው… ለነገሩ ከመስቀያው ነው…” አለች አተኩራ እያየችኝ፡፡
(በተሰቀልኩ፡፡ እዚሁ እንዳለሁ ተሰቅዬ በሞትኩ!)
ለአድናቆቷ አፀፋ መስጠት እየፈለግኩ፣ ውብ ሴት ነሽ…ልጆችሽ ያምራሉ… አቋምሽን ያየ እንኳን የወለድሽ ምግብ በልተሸ የምታድሪ አይመስለውም አይነት አፀፋ መመለስ እየፈለግኩ ምላሴ እምቢ አለኝ፡፡
ፈገግ ብዬ አቀረቀርኩና ዝም አልኩ፡፡ አስተናጋጅዋ መጥታ ፊታችን ቆመች፡፡
“ምን እንብላ ፍሬሕይወት?” አለች ገነት፣ የምግብ ዝርዝር የያዘውን ትልቅ ወረቀት አገላብጣ እያየች፡፡
“ደስ ያላችሁን… እኔ ኀይለኛ ቁርስ ነው የበላሁት… ብዙም አልራበኝም” አልኩ፡፡
ሦስት ምግብ አዘዘች፡፡ “ገኒ ሦስት ምግብ አይበዛም? እዚህ ቤት እኮ ፖርሽናቸው ትልቅ ነው” አለ ደቤ፡፡
“ከሚያንስ አይሻልም? የሚጠጣስ ምን ይምጣልሽ ፍሬ?”
(ፍሬ? ፍሬ ነው ያለችኝ? ጭራሽ ታቆላምጠኝ ጀመር? ይህች የዋህ ሴት… ይህች የእግዜር በግ… ይህች ለማዳ እርግብ፣ የሕግ ባሏን ውሽማ እንደምታቆላምጥ ብታውቅ ምን ትል ይሆን? አይደለም፡፡ ውሽማ አይደለሁም…. ውሽማ አልባልም… በጎን በኩል ያለሁ ሁለተኛ ሚስት ነኝ… ሚስት፡፡)
“እ..? ውሃ…” አልኩ፡፡
“በቃ ሁለት ሊትር ውሃ ከውጪ…” ብላ አዘዘች፡፡
ገነት፣ አስተናጋጇ እንደሄደች፤ ሕፃን ልጅ አኩርቶ ሊይዝ ከሚችል ትልቅ ቦርሳዋ ውስጥ ሚጢጢ የምሳ እቃ አወጣች፡፡ በመገረም አየኋት፡፡ ጥያቄዬ እንደገባት ሁሉ፣
“ለማርኮን ነው… የውጪ ምግብ አይስማማውም… ና ማሬ” አለችና፣ ልጇን ከነተቀመጠበት ወንበር ጎትታ አስጠግታው፣ ምሳ እቃውን ከፈተች፡፡ መኮረኒ፡፡
ራሴን በገባኝ ነቅንቄ ወደ ደቤ አየሁ፡፡ አቀርቅሯል፡፡ ወደ አርሴማ ዞርኩ፡፡ አቀርቅራ ስልኳን ትጎረጉራለች፡፡
ገነት ልጇን ጉረስ አትጉረስ እያለች ትታገላለች፡፡ ሰአት መሄድን አሻፈረኝ ብሎ የቆመ፣ ጊዜ አልሄድ ብሎ የተገተረ መሰለኝ፡፡
በረጅሙ ተነፈስኩ፡፡ ሰመመን ላይ ያለሁ፣ በሕልም ዓለም ውስጥ የምመላለስ መሰለኝ፡፡
ማርኮን፣ “ማማ… እሷ ታብላኝ….” ብሎ እየጮኸ፣ ትንሽ እጁን ወደኔ ሲጠቁም ከሰመመኔ ነቃሁ፡፡
“አይሆንም አርፈህ ብላ….” ብላ፣ ማንኪያ ወደ አፉ ሰደደች፡፡
“እምቢ… እሷ ታብላኝ…” ለቅሶ ጀመረ፡፡
(ወይ ታሪክ…)
“ወዶሻል መሰለኝ…” አለ ደቤ፣ ወደኔ ዞሮ፡፡
“ስጪኝ አበላዋለሁ…” አልኩ ነቃ ብዬ፡፡
“ተይው… ሲቀብጥ ነው፤ ያስቸግርሻል፡፡” ገነት ልጇን በመቆጣት እያየች መለሰች፡፡
“ችግር የለውም ስጪኝ…”
“ተይ…?”
“ግዴለም ገነት… አምጪው ላብላው…”
“ምሳ ብዩ ብዬ አምጥቼሽ ሞግዚት አደረኩሽ እንግዲህ…”
“ኧረ ችግር የለውም”
ማርኮን ተንደርድሮ መጣና ጭኖቼ ላይ ተቀመጠ፡፡ ደቤ ፈዝዞ ያየናል፡፡
“እሱ ሰው አንዴ ከወደደ እንዲህ ልጥፍ ነው…. ቻይው እንግዲህ…” አለች ገነት፡፡
“ችግር የለም” (ባልሽን እየተሸማሁሽ ቢያንስ ልጅሽን ልመግብ እንጂ የኔ እናት….)
ማርኮን ስጎ የበዛበትን መኮረኒ ቶሎ ቶሎ መጉረስ ጀመረ፡፡ በመሀል እየሣቀ ቀና ብሎ ያየኛል፡፡ የአባቱና የእናቱ ግሩም ቅልቅል ቆንጅዬ ልጅ ነው፡፡
“አ….!” ስለው ይሥቃል፡፡ አፉን ይከፍታል፡፡ ይጎርሳል፡፡ ያኝካል፡፡ ይውጣል፡፡ ከዚያ ደግሞ መልሼ “አ….!” ስለው ይሥቃል፡፡ ማር ነገር፡፡
“ይገርማል ለማንም እንዲህ አይበላም እኮ በጣም ቢወድሽ ነው…” አለች ገነት፣ እየሣቀች፡፡
(መጀመሪያ ባልሽ አሁን ደግሞ ልጅሽ… ቻይው እንግዲህ አንቺ መልካም ሴት፡፡ ቻይው፡፡)
ትንሽ ቆይቶ፤ የመጨረሻዎቹን ጥቂት መኮረኒዎች ላጎርሰው ስሞክር “በቃኝ…!” ብሎ እጄን ሲመታው፣ ሁለት መኮረኒዎች ከነብዙ ቀይ ስጓቸው ቀጥ ብለው የት ሄዱ?
ነጩ ቀሚሴ ላይ፡፡
ገነት የወደደችው ነጭ ቀሚሴ ላይ፡፡ ጭቦ መሰለኝ፡፡
“ማርኮን! ና… ና ወደዚህ… ፍርዬ ወይኔ… በጣም ይቅርታ በናትሽ… በጣም ይቅርታ…” አለች ገነት እየተርበተበተች፡፡
“ችግር የለውም….” ብዬ፣ መኮረኒዎቹን በእጆቼ አነሰሳሁና ቀዩን ስጎ ለማስለቀቅ ሞከርኩ፡፡ ስፈትገው ጭራሽ አሰፋሁት፡፡
“ኖ ኖ… በውሃ ይሻላል… ቆይ ውሃ ታምጣልሽ… አስተናጋጅ….!” ገነት በሰው በተሞላው ትልቅ ምግብ ቤት መሀል ጥሪዋን ሰምቶ የሚመጣ አስተናጋጅ ስታጣ፣ ራሷ ተነስታ ሄደች፤ ውሃ ልታመጣ፡፡
(ምስኪን፤ የምስኪን ጥግ፡፡)
ራቅ ስትል ደቤን አየሁት፡፡ ስሜት በማይታይበት ሁኔታ ደንዝዞ ያየኛል፡፡
ወደ የአርሴማ ዞርኩ፡፡ አሁንም ስልኳን ይዛ እንዳቀረቀረች ነው፡፡
“ደቤ…. ልሂድ እኔ…” አልኩት ቀስ ብዬ፡፡
“እንዴ? ምግብ ሳይመጣ? ምን እንድታስብ ነው…..?” አለኝ፡፡
ሳልመልስለት፣ ገነት ውሃ ከያዘች አስተናጋጅ ጋር እየተጣደፈች ተመለሰች፡፡
“ሽንት ቤት አይሻልም?” አለች አስተናጋጇ፣ በስጎ የተበላሸውን ቀሚሴን ስታይ፡፡ ሰው ትን ብሎታል ተብላ ስትሮጥ ውሃ ያመጣችና ቀሚስ ለማስለቀቅ መሆኑን ስታውቅ ቅር የተሰኘች ትመስላለች፡፡
“ልክ ናት… እዛ ሄጄ ባስለቅቀው ይሻላል…” አልኩና ተነሳሁ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች ከዚህ መጥበሻ ላይ መውረድ በመቻሌ እፎይታ ቢጤ እየተሰማኝ፡፡
ገነት ራሷን በእሺታ ነቅንቃ ስትቀመጥ፣ ደቤ ተከትሎኝ መጣ፡፡
ማመን አልቻልኩም፡፡ ምንድነው የሚሠራው?
“እጄን ታጥቤ መጣሁ እኔም…” አለ ጮኽ ብሎ፡፡
(ወይ እጅ መታጠብ፡፡)
ሽንት ቤቱ የወንዶችና የሴቶች ተብሎ የሚከፈልበት ኮሪደር ጋር ጠበቅኩት፡፡ እንደደረሰ ጮኽ ብዬ፣
“ጭራሽ ትከተለኛለህ?” አልኩት፡
“እጄን ልታጠብ ነው አልኩ አይደል?”
“ብትልስ?”
“ማለት?”
“ብትጠረጥርስ?”
“ምንድነው የምትጠረጥረው? ሰው አብሮ እጅ አይታጠብም እንዴ?”
ዝም ብዬ አየሁት፡፡
“ምን ሆነሻል?” አለኝ እጆቹን ዘርግቶ፡፡
ሊነካኝ ነው? ሚስትና ልጆቹን በሜትሮች ርቀት አስቀምጦ ሊነካኝ ነው?
“እንዳትነካኝ!” ብዬ ጮኽኩ፡፡
“ምን ሆነሻል?”
“ምን ሆነሻል ብለህ ትጠይቀኛለህ? ሲኦል ውሰጥ ከተኸኝ?”
“አይ ኖው ደስ የሚል ነገር አይደለም፣ ግን ይሄን ያህል ምነው?”
ዝም ብዬ አየሁት፡፡
“ፍሬ…” አለኝ አሁንም ሊነካኝ እጆቹን ዘርግቶ…
“በናትህ እንዳትነካኝ!” ብዬ ሸሸሁት፡፡
“ምንድነው እንዲህ የሚያደርግሽ…? የማታውቂው ነገር ተፈጠረ? ሚስትና ልጆች እንዳሉኝ ታውቂ የለም?”
እውነቱን ነው፡፡ አብሬው መተኛት ከመጀመሬም በፊት ሚስትና ሁለት ልጆች እንዳሉት አውቅ ነበር፡፡ የሚስቱን ስም አውቅ ነበር፡፡
የልጆቹን እድሜና ስም አውቅ ነበር፡፡
ከሚስቱ ጋር ለአሥራ ሁለት ዓመታት በትዳር እንደኖረ አውቅ ነበር፡፡
ከአሥራ ሁለቱ ስምንቱ ጥሩ፣ አራቱ ደግሞ የደባልነት እንደሆኑም አውቅ ነበር፡፡
“እ?” አለኝ፡፡
“አውቃለሁ እሱማ…”
“ታዲያ ምንድነው እንዲህ ያስደነበረሽ?”
ምንድነው እንዲህ ያስደነበረኝ?
አገኘኋቸዋ…! ተዋወቅኳቸዋ…! ሳላገኛቸው በፊት አሃዝ ነበሩ፡፡ አንድ ሚስት ሁለት ልጆች፡፡ ቁጥር ብቻ፡፡ ስም ያላቸው ቁጥሮች፡፡ ከዚያ ባለፈ ስለነሱ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡

31.03.202506:57
‹‹ለቀቀ››
----
እየኖርኩ ነው ብሎ ያስባል፤ ነገር ግን ተረጋግቶ መቀመጥን የማያውቅና የቁጭ ብድግ ሕይወት ነው የሚገፋው፡፡ ይቅበዘበዛል፡፡
ከእረፍቱ ይልቅ ማረፊያውን ፍለጋ በጉዞ የሚያጠፋው ጊዜ ያመዝናል፡፡ የእድሜው እኩሌታ ገመናውን ከምተከትለት ጎጆ ለመግባት መንገድ ላይ እያለፈ ነው፡፡
---------
መጀመሪያ የተከራየው ቤት አራት ኪሎ አካበቢ ነበር፡፡ በንጉሡ ጊዜ የተሰራ ትልቅና ውብ የድንጋይ ቪላ ቤት ጀርባ ጥግ ላይ፣ ከዋናው ቪላ መስሪያ በተራረፉና፣ ‹‹ከሚጣሉ›› ተብለው ከተሰበሰቡ ትርፍ የግንባታ እቃዎች እንደነገሩ ተሰርቶ የተወሸቀ የሚመስል አንድ ክፍል ሰርቪስ ቤት፡፡
ክፍሉ ጠባብ ቢሆንም በቂ ብርሃን ያገኛል፣ አንድ የኮርኒስ ተንጠልጣይ አምፖል አለችው፡፡ ቅር ያሰኘው ለደቂቃዎች ተጉዞና ግቢውን አቋርጦ ወደ ዋናው በር መግቢያ ላይ የሚያገኘው የጋራ ቁጢጥ ሽንትቤት ነው፡፡ ከርቀቱ አለመመቸቱ፡፡
አከራዩ ሁሉን ነገር አሳይቶት ሲያበቃ፣ ‹‹ለረጅም ጊዜ የሰራተኛ ክፍል የነበረ ነው፡፡ ሽንት ቤቱን ከዘበኛውና ከሰራተኛዋ ጋር ነው የምትጠቀመው›› አለው፡፡
ኪራዩ የማይጎዳ፣ ሰፈሩ መሃል ከተማና ለታክሲ አመቺ መሆኑን አይቶ ብዙ እንከኖቹን ችላ አለና እቃውን ሸክፎ ገባ፡፡
‹‹ለጊዜው ነው…ለአመት ወይ ቢበዛ ለሁለት አመት›› ብሎ ራሱን ደልሎ፡፡
በሰባተኛው ወር አከራዩ አንኳኳና፣
‹‹ ስማ፤ የኑሮ ሁኔታ እንደምታየው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪራይ መጨመር አለብህ›› አለው፡፡
ኮተቱን ሰብስቦ ስለመሄድ እያሰበ ጭንቅላቱን በእሺታ ነቀነቀ፡፡ ምን አማራጭ አለው!
-
ለቀቀ፡፡
-
ቀጥሎ የተከራየው ቤት ባምቢስ ጀርባ ነበር፡፡
ይሄኛው ደግሞ የረጅምና ተከታታይ ሰርቪስ ቤቶች አካል የሆነ አንድ ክፍል ነበር፡፡
ከአራት ኪሎው የሚጠብ፡፡ መስኮት የሌለው፡፡ መብራት ካላበራ በቀትር የሚጨልም፡፡
አለቅጥ ዝቅ ያለውን የበሩን ጣሪያ ላለመንካት አጎንብሶ መግባት ነበረበት፡፡ በዚህ ላይ የጎረቤቱ የማያባራ የቴሌቪዥን ጩኸት እረፍት ነስቶት ነበር፡፡
አሁንም ‹‹ለጊዜው ነው እንጂ ዘልአለም አልኖርበት…›› ብሎ ራሱን አሞኝቶ መኖር ቀጠለ፡፡
አስር ወር ከመኖሩ ሰፈሩ፣ ግቢውና ቤቱ ሙሉ በሙሉ ፈርሰው የመኪና ማቆሚያ ሊሆኑ ስለመሆኑ ሰማ፡፡
-
ለቀቀ፡፡
-
ደግነቱ በዚያው ሰሞን የደረጃና የደሞዝ እድገት አገኘ፡፡
ያ ጊዜ ከሰው ኩሽና እና ግልምጫ ልላቀቅ ብሎ ኮንዶሚኒየም ማማተር ጀመረ፡፡
ከብዙ መማሰን በኋላ ስሙ መገናኛ እውነተኛ አድራሻው ግን ኮተቤ የሆነ ባለ አንድ መኝታ የኮንዶሚኒየም ቤት ተከራየ፡፡
በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ገመና ከታች፣ ባሰኘው ሰአት ገብቶ የሚወጣበትና ብቻውን የሚጠቀምበት ሽንት ቤት ያለው ቤት ስላገኘ ተደሰተ፡፡
ቅዳሜና እሁድ ረፋዱ ላይ ጠባቡ ግን የግሉ በረንዳ ላይ ቆሞ ሻዩን እየጠጣ ከታች ጥሩምባቸውን የሚያንባርቁ ሚኒባሶችን የሚያይበት ቤቱ ተስማማው፡፡
ሰፋው፡፡
ሶስት ሰው የሚያስቀምጥ ቆንጆ ሶፋ ገዛ፡፡ የመጽሐፍት መደርደሪያ አሰራ፡፡
የመዝናናትና የመረጋጋት ስሜቴን አጣጥሞ ሳይጨርስ ግን ኪራይ ጨምር ተባለ፡፡
‹‹ያው ጊዜው ነው፡፡›› አለ ባለቤቱ ትከሻውን እየሰበቀ፡፡
‹‹አንተም የምታውቀው ነው፡፡ ኑሮ እሳት ሆኗል››
-
ለቀቀ፡፡
-
አያት ገባ፡፡ ሌላ ኮንዶሚኒየም፡፡ ከከተማው የልብ ትርታ ራቅ ያለ፡፡ ከበፊቱ ጠበብ ያለ፡፡ በረንዳው አዝናንቶ የማያስቆም፡፡
እንደ ድሮው ወጥቶ ሻይ የማይጠጣበት፣ የማይንጠራራበት፡፡
ተሳቀቀ፡፡ የቤት እቃ መግዛት አቆመ፡፡
አመት ሳይሞላው የቤት ኪራይ ጨመረ፡፡
-
ለቀቀ፡፡
-
ኮዬ ፈጬ፡፡
አሁን ከከተማው ያለው ርቀት በኪሎሜትሮች የሚመተር ብቻ አልነበረም፡፡ ጊዜው ታክሲ እና ሃይገር ላይ እምሽክ ብሎ ያልቃል፡፡
ከስራ በኋላ ከጓደኞቹ ጋር ተገናኝቶ አንድ ሁለት ማለት አቁሟል፡፡
ሰው መጠየቅ፣ በሰው መጠየቅ ትቷል፡፡ ከናካቴው መኖር አቁሟል፡፡
ስራ ይውላል፤ ጀምበር ከጠለቀች በኋላ፣ ችምችም ያሉት የሰፈሩ ኮንዶሚኒየሞች በጨለማ ከተዋጡ በኋላ ቤቱ ይገባል፡፡
ጎኑ አልጋ ከመንካቱ ይነሳል፤ ስራ ይውላል….
አዙሪቱ የኑሮውን ጣእም ነጠቀው፡፡
እንደ ሰው የመኖር ፍላጎቱን ሰለበው፡፡
ኪራይ ተጨመረበት፡፡
-
ለቀቀ፡፡
-
እዚያው ኮዬ ፈጬ ከበፊቱ የሚጠብ ኮንዶሚኒየም ተከራየ፡፡ ሶፋውን ሸጦ፡፡ የኪችን ኮተቱን በግማሽ ቀንሶ፡፡ መፅሐፎቹን ለሰው አከፋፍሎ፡፡
ኪራይ ጨመረበት፡፡
-
ለቀቀ፡፡
-
አሁን የገባበት ቤት ስቱዲዮ ነው፡፡ በኮንዶሚኒየም ታሪክ ጠባቡ ስቱዲዮ ውስጥ፡፡ ያልለማው፣ ተከራይ ያልደፈረው የህንጻዎቹ ሁሉ መደምደሚያ የሆነው የኮዬ አካል ውስጥ፡፡ መብራት፣ ብልጭ ድርግም፡፡ ውሃ ሄድ እልም የሚሉበት፡፡
ሰፈሩ ብቻ ሳይሆን ሕይወቱም ከሚወደው ነገር ሁሉ የራቀ፣ ያራቀው መሰለው፡፡
ስምንት ወራት አለፉ፡፡
ከዚያ አከራዩ ደወለ፡፡
እንደነገሩ ሰላም ብሎት ሲያበቃ፣
‹‹እንግዲህ መቼም ሁሉ ነገር ሰማይ እየነካ ነው…እኛም ገና የቤቱን ክፍያ አልጨረስንም…ስለዚህ…›› ሲል አቋረጠው፡፡
‹‹አታፍሩም…!? እግዜርን አትፈሩም?! ቀለም እንኳን ያልተቀባ ቤት…ያውም እዚህ ጅብ የሚተራመስበት የሚያስፈራ ሰፈር እሺ ብዬ ብከራይ ገና አመት እንኳን ሳይሞላኝ ጨምር…በዚህ ላይ ውሃ የለ…መብራት የለ…››
አከራዩ በተራው በቁጣ አቋረጠው፡፡
‹‹ባንተ ብሶ ትቆጣለህ እንዴ…?!! ለምነህ እንጄ ለምነንህ ነው እንዴ የገባኸው…?! ማነህ ባክህ! እንደውም ቤቱን እፈልገዋለሁ…ቶሎ ልቀቅ...!›› ብሎ ጆሮው ላይ ዘጋው፡፡
--
ሳቁ እንደ ገደል ማሚቶ በጨለማውና ወናው የህንጻው ኮሪደሮች እስኪያስተጋባ ድረስ፣
‹‹ልቀቅ ነው ያልከኝ…?! .እ…ልቀቅ ?!….እለቃለሁ…እለቃለሁ…! ምን ችግር አለው እ-ለ-ቃ-ለ-ሁ!›› አለ
ከ-----ት ብሎ እየጮኸ፣ ደግሞ እየሳቀ፡፡
--
ከዚያ ምሽት በኋላ ያዩት ጎረቤቶች ሁሉ፣ በገባና በወጣ ቁጥር እንዲህ እንዲህ እያለ ብቻውን ሲያወራና ሲወራጭ ሲመለከቱ፣
‹‹ወይኔ ይሄ ልጅ ደህና ልጅ አልነበረ እንዴ? …በቃ ለቀቀ እንዴ?! ›› መባባል ጀመሩ፡፡

24.03.202507:00
‹‹ገና…››
--------
ልለያት አልፈልግም፡፡
ገና እያወቅኳት፣ ገና እየወደድኳት ነበር እኮ፡፡ ገና አልጠገብኳትም እኮ፡፡
ገና…
ስቅበዘበዝ የሚያረጋጋኝ፣ ስደክም የሚያበረታኝ፣ ሲከፋኝ የሚያፅናናኝ አንጀቷን ደገፍ ብሎ መተኛትን ከመለማመዴ….
ገና…
የሚስረቀረቅ ሳቋን፣ አንጀት የሚያላውስ ጭንቀቷን፣ እኔን ስታስብ የሚፈነጥዝ ልቧን ከመተዋወቄ…
እንዴት ይሄ ይፈጠራል?
አሁን ትንሽ ብሆንም
ከስጋዋ በልቼ፣
ከደሟ ተጎንጭቼ ፣
ቀን ቆጥሬ ልሟላ፣
ጊዜ ጠብቄ ሰው ልባል ነበር እኮ!
ግን በድንገት ሁሉ ነገር እንዳልነበር ሆነ፡፡
ለወራት አቅፎ የያዘኝ ሙቀት በከባድ ቆፈን ተተካ፡፡
የከበበኝ ብርሃን ከሰመ፡፡ በቦታው ጨለማ ነገሰ፡፡
ከእሷ አጣምሮ ያቆየኝ ገመድ በአንዲት ቅፅበት ተበጠሰ፡፡
እየነካሁ የምነጥርበት ስፖንጅ መሰል ግድግዳዋ በሰከንዶች ተደረማመሰ፡፡
ሰላላ እጆቼን ዘርግቼ ቦታዬን ላለመልቀቅ ተጣጣርኩ፡።
እንደተጣጠፍኩ ከእሷ ዘንድ ለመቆየት የአቅሜን ያህል ተፍጨረጨርኩ፡፡
"ቀስ! ቆይ እንጂ!
ኧረ ቆይ…ቆይ…መውጫ ሰአቴ አልደረሰም፡፡
ገና ጭብጥ ፍሬ እኮ ነኝ…ለመሄድ ጊዜዬ አይደለም..
ቆይ…ኧረ ቆይ… !"
ብዬ ጮህኩ፡፡
ግን የሆነውን ከመሆን አላስቀረሁትም፡፡
በተኛችበት ስትገላበጥ ይሰማኛል፡፡
እንደተገለበጠች በቀኝ እጇ መዳፍ ሆዷን ያዝ ስታደርግ፣ እየሆነ ያለውን ነገር ባታውቅም እንዳወቀች ገባኝ፡፡
በእጇ ይዛ ታስቀረኝ ይመስል ጥብቅ አድርጋ ልታቆየኝ ስትሞክር፣
‹‹አይዞሽ! አለሁ….አልሄድኩም›› ብዬ ላፅናናት እጇ ያረፈበትን ቦታ ከውስጥ ተጫንኩት፡፡
ግን ልገዳደረው ያልቻልኩት ሞገድ እየገፈታተረ ወደ ታች ሰደደኝ፡፡
-
-
-
-
ተምዘግዝጌ ታች ስደርስ…
በጊዜዬ ሰው ሆኜ በመውጣት ፋንታ፣ ደም ሆኜ ተንዠቀዠቅኩ፡፡
ላልታፈስ ፈሰስኩ።
ትንሽ ቆይታ ከእንቅልፏ ትነቃለች፡፡
ብርግግ ብላ አልጋዋ ላይ ስትቀመጥ ቀፎነት ይሰማታል፡፡
ከዚያ የተፈጠረው ይገባታል፡፡
ምርር ብላ እያለቀሰች፣ ባዶ ሆዷን እየዳበሰች፣
‹‹አይሆንም!…አልሆነም!›› ትላለች፡፡
በጥፋተኝነት ማእበል ተመትታ፣
‹‹የእኔ ጥፋት ነው…በዚህ በኩል ባልተኛ፣ ያንን ምግብ ባልበላ፣ የዚያን እለት ቡና ባልጠጣ፣ ያንን እቃ ባላነሳ›› እያለች ቀን ከሌት፣ ሳትስመው ስለሞተባት ልጇ ታነባለች፡፡
ግን ጥፋቱ የእኔ ነው፡፡
የሙጥኝ ብያት መቆየት፣ ሳልላቀቃት መሰንበት አልቻልኩም፡፡
ግን…ግን….ግን…
እውነት እላችኋለሁ…
ከምንም ነገር በላይ አብሬያት መቆየት ፈልጌ ነበር፡፡
መቆየት ፈልጌ ነበር፡፡
መቆየት ፈልጌ ነበር፡፡
እናቴ እንድትሆን እፈልግ ነበር፡፡
ልጇ ብሆን ምኞቴ ነበር፡፡

15.03.202509:13
እንጀራው በዛና ወጡ አነሰ።
ወጥ ጨመረች።
ወጡ በዛና እንጀራው አነሰ።
እንጀራ ጨመረች።
ድጋሚ እንጀራው በዛ። ወጥ ጨመረች።
እንዲህ እንዲህ ብላ ትልቅ ጎድጓዳ ሰሃን ሙሉ ወጥ በአንድ ተኩል እንጀራ ጋር ስትደርስ ለራሷ እንዲህ አለች፤
" እንጀራ እና ወጥ የኑሮ ተምሳሌት ነው ልበል?"

09.03.202506:59
ይህንን ታውቃለች፤
ባለ ብሩህ አእምሮ ናት፡፡
አለሁ ባዩን ሁሉ አፍ የሚያስይዝ የዲግሪ ብዛት፣ የሽልማት ክምር አላት፡፡
በተከበሩ መድረኮች ላይ ቆማለች፤ አንቱ የተባሉ ሰዎችን እጆች ጨብጣለች፤በንግግሯ ብስለት፣ በስኬቷ አስደማሚነት የስንቱን አፍ አስከፍታለች፡፡
ከዚህ ሁሉ ጎልቶ የሚታያት ግን ይሄ ነው፤
ቦርጭዋ፡፡
ግዝፈቷ።
ስፋቷ።
ውፍረቷ፡፡
በየአደባባዩ ስኬቷን በሚያነፈነፉና በሚዘግቡ ፎቶግራፎች የተነሱ ፎቶዎቿን ባየች ቁጥር ለራሷ እንዲህ ትላለች….
ምን አይነቱ ድንዙዝ ካሜራማን ነው እንዲህ አይነት አስቀያሚ ፎቶ ያነሳኝ?
የእሱ አነሳስ ነው።
የብርሃኑ ሁኔታ ነው::
የጨርቁ አይነት አጋኖት ነው፡፡
አቋቋሜ ነው፡፡
እንዲህ እንዲህ ብላ ስታበቃ…የሚከተለውን ታደርጋለች፡፡
መጀመሪያ…
ፎቶውን ዙም ኢን አድርጋ ታጠናለች፡፡
ቀጥላ …ያየችው ያስከፋትና፣
ዙም አውት አድርጋው ትሸሻለች፡፡
ወዲያው ደግሞ…
‹‹ቦርጭ እንዳይታይ የሚረዱ የቁም ፎቶ አነሳሶች›› ብላ ትጽፍና ጉግል ታደርጋለች፡፡
ማድረግ ግን ያለባት ይህንን ነበር፤
ስኬቷ ከኪሎዋ እንደሚበልጥ መገንዘብ፡፡
ፎቶውን በትልቁ አሳጥባ መስቀል፡፡
ለዚህ በመብቃቷ መኩራት፡፡
ግን ሴቲቱ በዚህ ፈንታ ምን ታደርጋለች…?
ሌላ የጉግል ገጽ ክፍት አድርጋ-
‹‹ቦርጭን በቀላሉና በፍጥነት የማጥፊያ መንገዶችን›› አስስ ትለዋለች…

15.04.202509:01
‹‹ቅጫሞ››
(ክፍል ሁለት)
-------
ከብዙ አመታት በኋላ፣ በአንዱ ዝናባማ ምሽት ዳዊት ብሌንን አገኛት፡፡
ስለ ብሌን ካሰበ ቆይቷል፡፡
የተገናኙት ለአጭር ጊዜ አዲስ አበባ በመጣበት ወቅት ነበር፡፡ ግማሹ ሕይወቱ አዲስ አበባ፣ ሌላኛው ግማሽ ደግሞ ዱባይ ነው፡፡ ሥራው በየሃገሩ ያዞረዋል። ሙሉና ደስተኛ ሕይወት ስለነበረው ከረጅም ጊዜ በፊት በአፏ ስላቆሰለችውና ይወዳት ስለነበረች ልጅ የሚያስብበት ጊዜ አልነበረውም፡፡
አሁን ግን እዚህ ቁጭ ብላ አገኛት፡፡ ብቻዋን፡፡
በሬስቶራንቱ ባር ጥግ ላይ ፊቷ በተሰቀሉት መብራቶች ፍክት ብሎ በርቶ እንዳያት አወቃት።
ከመሄዱ በፊት ግን አመነታ።
"ብሌን?" ብሎ ጠየቀ አጠገቧ ደርሶ ከመቆሙ፡፡
ቀና ብላ አየችው፡፡
ያ አዚማም ውበቷ ከሚያውቀው ቢደበዝዝም ጨርሶ አልጠፋም፡፡
አይኖቿ ግን ድካምና ሃዘን አጥልቶባቸዋል፡፡ አቀማመጥዋ ዛሬም በቁንጅናዋ እንደምትመካ ሴት ነው፡፡ ስሜቷ ከበፊቱ ሰከን ቢልም በራስ መተማመኗ ግን አብሯት ነው፡፡
ማነህ በሚል ሁኔታ - ግር ብሏት ስታየው ሰከንዶች አለፉ፡፡
‹‹አላወቅሽኝም…? ረሳሽኝ እንዴ ብሌን? ›› አላት በቆመበት፡፡
የአይኖቿን ረጃጅም ሽፋሽፍት አርገብግባ ስታበቃ፣
‹‹እ….ይቅርታ…አላወቅኩህም›› አለችው፡፡
‹‹ ብሌን…ዳዊት እኮ ነኝ…የኮከበ ፅባው…አብረን ነው የተማርነው…››
አሁንም እርግጠኝነት በማጣት አይነት አየችው፡፡
‹‹ዳዊት…! አራት አመት አብረን ተምረን ረሳሽኝ?…››
‹‹ዳዊት ዳዊት…? ›› አሁንም አተኩራ እያየችው መለሰች፡፡
ማለት ያለበት ነገር ሲገባው ሰውነቱ በረሳው ሁኔታ ሲጨማተር ተሰማው፡፡
‹‹ዳዊት ቅጫሞ›› አላት አፉን እየጎመዘዘው፡፡
መጀመሪያ ፊቷ ላይ ድሮ ልቡን ያስደነግጠው የነበረ ፈገግታ ተሳለ፡፡
ከዚያ ደግሞ ቀድሞውን ሃዘን አዝለው የነበሩ አይኖችዋ በእምባ ተሞሉ…
ባልጠበቀው ፍጥነት ብድግ አለች፡፡
የሚያደርገው ጠፋው፡፡
አቀፈችው፡፡
‹‹ዳዊት…ይቅርታ አድርግልኝ….ያኔ ያው ልጅነት…በጣም ደደብ ነበርኩ…ይቅርታ…›› እያለች ጉንጮቹን እያፈራረቀች ሳመችው፡፡
---
ከደቂቃዎች በኋላ አጠገቧ እንደተቀመጠ ደግማ ‹‹በስማም…በጣም አምሮብሃል ዳዊት›› አለችው፡፡
እውነቷን ነው፡፡
አምሮበታል፡፡ ባለፈ ባገደመበት ሁሉ ጥሎት ከሄደ በኋላ አየር ላይ የሚንሳፈፍ ለአፍንጫ የሚጥም ሽቶ ተቀብቷል፡፡ በልኩ የተሰራ ውድ ልብስ ለብሷል፡፡ ከሩቅ የሚያጥበረብር ወርቅ ቅብ የእጅ ሰአት አጥልቋል፡፡
ሕይወት ሸብረክ ያለችለት፣ ኑሮና ብልሃቱ የተሳካለት ሰው መሆኑ በሚያሳብቅ ሁኔታ አምሮበታል፡፡
‹‹ስለረሳሽኝ ገርሞኛል፡፡ አንቺም አምሮብሻል›› አላት፡፡
መጀመሪያ ያላት እውነት፣ ሁለተኛው ነገር ግን ሃሰት መሆኑን ልቡ እያወቀ፡፡
"ወይ ብሌን…ታዲያስ…እንዴት ነሽ? " አላት ዝም ስትለው፡፡
"ደህና ነኝ" በረጅሙ ተንፍሳ መለሰችለት፡፡
ደህና እንዳልሆነች ከሁኔታዋ አውቋል፡፡ ቮድካ የያዘ ብርጭቆዋን በምታሽከረክርበት ግደለሽ ሁኔታ፣ ትከሻዋን በሰበረችበት አሳዛኝ አኳሃን አውቋል፡፡
"አገባሽ?" ብሎ ጠየቃት።
ደብዛዛ ፈገግታ ለገሰችውና፣ ‹‹አግብቼ ነበር›› አለችው፡፡
"እ… አሁንስ?"
ቮድካዋን ተጎነጨች፡፡
"አሁንማ እዚህ ካንተ ጋር ነኝ።"
በመካከላቸው ፀጥታ ወደቀ።
ምግብና መጠጥ ቤቱን የሞላው ሰው በዙሪያቸው ይንጫጫል - ብርጭቆዎች ኪሊል ኪሊል፣ ሹካና ሳህን ገጭ ገጭ፣ የደምበኞች ጨዋታ ደግሞ ከፍና ዝቅ ይላል፡፡ አልፎ አልፎ የሳቅ ፍንዳታ ይሰማል።
"ልጆችሽ አሉሽ?" ብሎ ጠየቃት ልጠይቃት -አልጠይቃት በሚል ከራሱ ሲሟገት ቆይቶ፡፡
"ነበሩኝ"
"ነበሩኝ ስትይ? …ማለቴ… ምን ማለትሽ ነው?"
"አይ ዳዊት…እሱ ረጅምና አሰልቺ ታሪክ ነው፡፡ ከልጆቼ ጋር ተቆራርጫለሁ››
ሌላ ፀጥታ፡፡ ይሄኛው ደግሞ ወፍራምና የሚያፍን፡፡
በተቀመጠበት ተቁነጠነጠ፡፡
"ይልቅ ስለ አንተ እናውራ። አንተ... የተመቸህ ትመስላለህ። እንደ ዳያስፖራ።" በግድ ፈገግ ለማለት ሞከረች።
ለረጅም ጊዜ ፈገግ ሳትል ስለቆየች እንዴት ፈገግ እንደሚባል እንደረሳች ሁሉ፡፡
ሳቀ።
"ሃሃ ፣ ዲያስፖራ እንኳን አልባልም ፣ ግን… ይመስገን ኑሮ ጥሩ ነው ፣ አሁን የምኖረው ዱባይ ነው ግን አዲሳባ እመላለሳለሁ። ስራዬ በየሃገሩ ያዞረኛል››
"አግብተሃል?"
‹‹አዎ…ባለትዳር ነኝ…››
‹‹ልጆችስ ወለድክ?"
"አዎ…ሁለት ልጆች አሉኝ።" አለ ከእሷ ጋር ሲወዳደር ህይወቱ ምን ያህል ጥሩ እንደ ሆነ ተሰማውና በጥፋተኛነት ማእበል ተመታ፡፡
ጭንቀቱ እንደገባት ሁሉ ጭንቅላቷን በስምምነት ነቀነቀች።
"የሚገርምሽ ዛሬ ማታ ወደ ዱባይ ልመለስ ነው፣ እዚህ የመጣሁት ከአንድ ጓደኛዬ የተረሳ እቃ ልቀበል ነው" አላት የእጅ ሰአቱን እያየ፡፡ "ስለዚህ አሁን…ጥዬሽ መሄድ አለብኝ…"
በድጋሚ ጭንቅላቷን በመስማማት ነቀነቀችና፣ ‹‹ገብቶኛል..ሂድ…ሂድ።" አለችው፡፡
ሊሰናበታት ቆሞ ጥቂት እንደቆየ፣ ከሱሪው ኪስ ብዙ ሁለት መቶ ብሮችን አወጣና ሳይቆጥር ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ።
"ብሄድም ልጋብዝሽ ብዬ ነው" አለ ፈገግ ብሎ፡፡
ያለ መግደርደር ፈገግ ብላ አየችውና ሊሰናበታት አቅፏት ሲለቃት -
‹‹ስልክህን አትሰጠኝም?›› አለችው፡፡
አመነታ፡፡
ለረጅም ጊዜ የስቃይና የሃፍረቱ ምንጭ የነበረችንና ይህች የሕይወቱን ክፉ ጊዜ የምታስታውሰውን ሴት ዳግም ሊያገኛት ስለመፈለጉ እርግጠኛ አልነበረም፡፡ ምን ልታደርግለት?
"እሺ፣ ይሄው ያዥው" አላት።
ቁጥሩን ሊሰጣት ባይፈልግም ሁኔታዋን አይቶ ደግነትን ስለመረጠ ብቻ፡፡
እምቢ ማለቱ ታሞ የወደቀን ሰው በእርግጫ ማለት መስሎ ታየው፡፡
ከኮበፅባህ ከወጡ በኋላ ለብዙ ዓመታት ብሌንን ስለማግኘት ያስብ ነበር።
ቢያገኛትና ሲያገኛት ምን እንደሚላት ያወጣና ያወርድ፣ አንዳንዴም ሊላት የሚፈልገውን ነገር ሁሉ እንደ ቃለ ተውኔት ያጠናው ነበር፡፡
‹‹እስቲ አሁን ፀጉሬ ላይ ቅጫም ፈልጊ አንቺ አውሬ!›› አይነት ነገር፡፡
‹‹እይኝማ! አየሽው? ልብሴ..በልኬ የተሰራ ነው…አየሽው ጫማዬ…? ራሴ ከእንግሊዝ ያመጣሁት ነው…ለመሆኑ አንቺ ፓስፖርት እንኳን አለሽ? ሃገር ውስጥ የሚሄድ አውሮፕላን እንኳን ተሳፍረሽ ታውቂያለሽ?›› አይነት ነገር፡፡
በአእምሮው ከሳላቸው እሷን ዳግመኛ የማግኘት ትእይንቶች ውስጥ ግን ዛሬ የተከሰተው ነገር አልነበረም።
ሁሌም እንደ ጀምበር ደምቃ፣ መቼም በሰው ተከባ፣ ዝንትአለም ከእሱ ተሸላ የሚያገኛት ይመስለው ነበር፡፡
ስልክህን ስጠኝ ብላ ጠይቃውና አመንትቶ ሰጥቷት ከብቸኛና አሳዛኝ ሕይወቷ ጋር ጥሏት ወደሞቀ ትዳሩ ሲሄድ የአሸናፊነት፣ የድል አድራጊነት ስሜት እንደሚሰማው ጠብቆ ነበር፡፡
አገኘኋት የሚል፡፡
ከሁሉም በፊትና ከምንም በላይ የተሰማው ስሜት ግን ሀዘን ነበር። ባለቤቱ ደውላ ከሃዘኑ እስክታላቅቀው፡፡
‹‹ሄሎ ማርቲዬ›› ብሎ ድምጽዋን እስኪሰማ፡፡
(አበቃ)🥺

(ከላይ የቀጠለ) (ደቤ - ኧረ ከዚህ ጉድ አውጣኝ በናትህ?)
“አይ… ፕሮግራም ካላት ትሂድ ገኒ” አለ፡፡ ድምፁ የሱ አይመስልም፡፡
“የምን ፕሮግራም? ቤት ማጽዳት? ነይ… ምሳ በልተን ትሄጃለሽ… እኛም ወደ ቤት ስለሆንን እንሸኝሻለን በዛውም….” አለች ገነት፣ ልጆችዋን በግራ እና በቀኝ ይዛ፡፡
ወሰነች ማለት ነው?
ድምፅዋ ውስጥ ሰለዚህ ጉዳይ ከዚህ በላይ አልወያይም ዓይነት… ቅድም የአርሴማን፣ “ነይ ሰላም በያት” ያለችበት ዓይነት ትእዛዝ ነበረበት፡፡ በአንድ ጊዜ ለስላሳም ጠንካራም የሆነችው እንዴት ነው?
ምርጫ እንደሌለው ሰው ከኋላዋ ሱክ ሱክ እያልኩ መከተል ጀመርኩ፡፡ ደቤ ካጠገቤ ይራመዳል፡፡
በሚስቱ፣ በልጆቹና በእኛ መካከል ያለው ክፍተት ሰው አያስገባም፡፡ ቢሆንም ድምፄን ዝቅ Aድርጌ፣ በሹክሹክታ እንዲህ አልኩት፣
“ደቤ በማርያም… የሆነ ሰበብ ፍጠርና ጥላችሁኝ ሂዱ፡፡ ከሚስትህና ልጆችህ ጋር ምሳ መብላት Aልፈልግም፡፡”
መልስ አልሰጠኝም፡፡
-ይቀጥላል-
(ክፍል ሁለት ነገ በዚሁ ሰአት)🚶♂️🚶♂️🚶♂️

30.03.202508:03
ዒድ ሙባረክ💡
20.03.202506:38
ከመሞት ማርጀት
----
ከወጣት የሥራ ባልደረባዬ ጋር በሰው ጢም ካለ፣ በጫጫታ ከጋለ ካፌ ውስጥ ቡና እየጠጣን ተቀምጠናል፡፡
በመሃል ከረጅም ጊዜ በፊት የማውቀው ሰው ወደ ካፌው ሲገባ አየሁና በጉጉት ሰላም ልለው ሄድኩ፡፡
ተቃቅፈን ተሳሳምን፤ ደጋግመን በስስት ተያየን፡፡
ከዚያ የማይቀሩትን ጥያቄዎች ተወራወርን፣ መልሶችን ተቀላለብን፡፡
ደህና ነሽ?
የት ነህ?
አገባሽ?
ወለድክ?
የት ነው የምትሰሪው ?
ምንድነው የምትሰራው .. ?
ማንን ታገኛለሽ ? …ዓይነት ነገር፡፡
ከጥንት ወዳጄ ጋር ጉዳዬን ጨርሼ እንደተቀመጥኩ ለስራ ባልደረባዬ፣
‹‹ይገርማል…የሃይስኩል ጓደኛዬ ነበር፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘነው መቼ እንደነበር ታውቂያለሽ…? ማትሪክ ልንፈተን ስንል…በ1991!›› አልኳት፣ ደስታዬ ሳይለቀኝ፡፡
እንዲህ ስላት፣ ‹‹ውይ ደስ ይላል››
ዓይነት ነገር ብላ ወደ ጀመርነው ወሬያችን እንመለሳለን ብዬ ነበር፡፡ እሷ ግን በእዚህ ፈንታ ምን አደረገች…? ከባድ ወንጀል መፈጸሜን እንደተናዘዝኩላት ሁሉ ክው አለችና፣
‹‹ሃይስኩል የጨረስሽው በ1991 ነው?!››አለችኝ ጮክ ብላ፡፡
‹‹አዎ..ምነው…?›› አልኩ ደንገጥ ብዬ፡፡
‹‹ያ ማለት…እ…አርባዎቹ መጀመሪያ…እድሜሽ አርባ ቤት ገብቷል ማለት ነው …አይደል…?›› አይኖቿ ተበልጥጠው፣ አፏ ተከፍቶ ጠየቀችኝ፡፡
ከሁኔታዋ የማትጠረጥረውን ነውረኛ ነገር ሳደርግ እጅ ከፍንጅ የያዘችኝ ነው የምትመስለው፡፡ መኖርና መሰንበት ነውር፣ መቆየት ወንጀል ሆነ እንዴ..?
‹‹አዎ…ቢሆንስ ታዲያ?›› አልኩ፡፡
‹‹አንቺ ማትሪክ ስትወስጂ እኔ ገና ሁለት አመቴ ነበር…ፓፓ ላይ ነበርኩ በይው›› አለች በራሷ ቀልድ እያሳቀች፤ ልክ አርባ ቤት መግባቴ ሳላስበው የሰራሁት ታላቅ ጥፋት እንደሆነ፣ ልክ ሐያ ቤት መሆኗ ለፍታ ያገኘችው ስኬት እንደሆነ፡፡
ግን አልተቀየምኳትም፡፡
ምክንያቱም እኔም በእሷ እድሜ እያለሁ የማደርገውን ነው ያደረገችው፡፡
እኔም በጊዜዬ፣ ከጓደኞቼ ጋር አፌን በግርምት ከድኜ፣
‹‹ስሚ…እንትና እኮ 31 አመቷ ነው…በስማም እድሜዋ ጭሮታል…››
‹‹እሱ እኮ ሰላሳዎቹን አጋምሷል ነው የሚባለው..ጨረጨሰ እኮ›› ብያለሁ፡፡
መሄጃችን ወደእዚያ እንዳልሆነ ሁሉ በእድሜ በሚበልጡን ሰዎች መሳለቅ የእለት ተእለት መዝናኛችን ነበር፡፡ በወጣትነት ጊዜ ስለጊዜ የሚያስብ ብዙ ሰው የለም፡፡
የእርጅና ክትባት እንደተከተብን ሁሉ ጊዜን በልበ ሙሉነት ስንጋፈጠው ደስ ይለን ነበር፡፡
ጊዜ ነጉዶ የሁሉም ሰው ቆዳ ሲጨማተርና ጉልበቱ ሲዝል የእኛ ገላ እንዳብረቀረቀ፣ እንደጋለ የሚቀጥል ይመስለን ነበር፡፡
ወጣትነት ከብዙ ነገሮች የተሰራ ነው፤ ከእነዚህ ነገሮች አንዱ ደግሞ እብሪት ነው፡፡ በማናባቱ ይነካናል ስሜት የሚንበለበል እብሪት፡፡
ስለዚህ አልተቀየምኳትም፡፡
‹‹እኔ እንኳን ስለ እድሜ ሳይሆን ስለጊዜ መሄድ ነበር ያወራሁሽ›› አልኳት ረጋ ብዬ፡፡ ‹‹አለ አይደል…ሰው ምን ያህል በጊዜ እንደሚለወጥ››
‹‹እሱ አዎ ግን ዋው…እድሜሽ በጣም ሄዷል…እኔ የምልሽ ግን…››
‹‹አንቺ የምትይኝ…›› መለስኩ
‹‹ካልኖርሽው ጊዜ የኖርሽው ጊዜ እንደሚበልጥ አስበሽ ታውቂያለሽ…?››
‹‹ማለት?››
‹‹ማለት…የቀረሽ ጊዜ እስካሁን ከኖርሽው ቢያንስስ?…››
እየመጣሽ ተኚ፡፡
የዚህች ደግሞ ይባስ፡፡
ቡና ልጋብዘሽ ባልኳት እንዲህ ያለን ከቋጥኝ የሚከበድ ፍልስፍናዊ ጥያቄ ትወርውርብኝ?
እርግጥ ነው፤ ልጅቱ ያለችን ነገር በየአቅጣጫው መትሬና አሽሞንሙኜ ሳስበው፣ ሰነጣጥቄ ሳሰላስለው ልውልና ላድር እችላለሁ፡፡
ዞሮ ዞሮ ግን ምን ቢያስቡ፣ምን ቢጠበቡ በእድሜ ጉዳይ ሁሌም የማይቀየር አንድ እውነት አለ፡፡
ይሄ እውነት የሰው ልጅ ከተወለደ ጀምሮ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ በሚፈስ የጊዜ ወንዝ ላይ መሳፈሩ ነው፡፡
በዚህ ወንዝ ላይ ሲጓዙ ወደ ፊት መቅዘፍ እንጂ ወደ ኋላ ማጠንጠን የለም፡፡ መሄድ መሄድ መሄድ እንጂ ፌርማታ ላይ ማረፍ አይታወቅም፡፡ ብቸኛው ፌርማታ፣ ማዞሪያው፣ ያው ሞት ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ልጅ በዚህ አኳያ ያለው ምርጫ ወይ ማርጀት (ከታደለ) አለዚያም መሞት ብቻ ነው፡፡
እኔ በበኩሌ ምርጫው እስካለኝ ድረስ ምርጫዬ ማርጀቱ ነው፡፡
ምክንያቱም እኔ ሕይወት እንጂ ‹‹የምመካበት መልኬ ሲሸበሸብ ከማይ ድፍት ልበል›› ብላ ራሷን ያጠፋችው ማርሊን ሞንሮ አይደለሁም፡፡
ሊያውም ስንት ሊገድለኝ አሰፍስፎ የሚጠብቅ የሞት ጦርን በፈጣሪ ቸርነት አምልጨ እዚህ ለመድረስ የታደልኩ ኢትዮጵያዊት፡፡
ሁላችንም እንደምናውቀው፣ ኢትዮጵያዊን ለመግደል የተሰናዳ የሞት ወጥመድ እጥረት የለም፡፡
ያመለጠ ክትባት፣ ጦርነት፣ ኮሌራ፣ የምግብ እጥረት፣ ወባ፣ የመኪና አደጋ፣ የሳንባ ነቀርሳ፣ ደራሽ ጎርፍ፣ መድሃኒት ማጣት፣ በአሳንሰር ተጨፍልቆ መሞት…. ካለጊዚያችን የሚያሰናብተን ነገር የትዬሌሌ ነው፡፡
እናስ….በዚህ ዞር ስትሉ መርዶ፣ ፈቅ ስትሉ የሃዘን ድንኳን በበዛበት ሃገር ስንቱን አምልጬ አርባ ቤት የገባሁ፣ በማርጀት ላይ ያለሁ እድለኛ ሴት መሆን በወጣትነት ጊዜዬ ማለፍ መነጫነጭን በስንት እጅ አያስከነዳም?
ያስከነዳል እንጂ፡፡
አንዳንዴ ግን የእኛ ነገር ወለፈንዴ አይሆንባችሁም…?
እድሜ ይስጣችሁ ተብለን ከምርቃቶች ሁሉ የላቀውን ምርቃት ስናገኝ ደስታ፣ ምርቃቱ ሰምሮ ስናረጅ ግን መከፋት ምን የሚሉት ግጭት ነው…?
መሰንበት የፈለገ ጣጣውንም አሜን ብሎ መቀበል ግድ ይለዋል፡፡ እድሜዋን ፈልጎ የቆዳ መሸብሸብን፣ የጉልበት መላምን፣ የጡት መውደቅን፣ የጡንቻ መክሰምን እምቢ ማለት አይቻልም፡፡
‹‹ፓኬጅ ዲል ነው›› እንዲል ፈረንጅ፡፡
እኔ በበኩሌ (ከተፈቀደልኝ) ይሄን ሁሉ ነገር ይሁን ብዬ ተቀብዬ ማርጀቱን ነው የምመርጥ፡፡
ከመሞት ማርጀት!

13.03.202506:13
‹‹አልፈልግም!›
-----
አዲስ ሰው መተዋወቅ አልፈልግም፡፡
ስሙን መጠየቅ፣ ስሜን መንገር አልፈልግም፡፡
እንድግባባው ብዬ የባጥ የቆጡን መቀባጠር፤
የቱ ጋር ተወለድክ፣ የቱ ሰፈር አደግክ፣ ከእነማን ጋር ተማርክ፣
ምናምንም ምናምን…. ፣ ማለት አልፈልግም
ሰው አገኘሁ ብዬ…
አራምባና ቆቦ…
እዚያና እዚህ መርገጥ...
አልፈልግም፡፡
ደንታዬ አይደለም፡፡
በማያስቅ ቀልዱ መገልፈጥ፣
ስለሞተ አባቱ መስማት፣ ስለታመመች እናቱ ማዳመጥ፣ ስላዋየኝ ነገር ግድ የሰጠኝ መምሰል...
አልፈልግም፡፡
ስለቤተሰቡ ጣጣ ማወቅ፣
ተቀጣጥሮ ለመገናኘት መስማማት፣
መገናኛ ቦታ መምረጥ፣
ጸጉሬን ተተኩሼ፣ የክት ለብሼ፣ ሽቶ ሽቶ እያልኩ መሄድ…
አልፈልግም፡፡
ከዚያ ደግሞ…
በሃይል ዘነጥኩ ወይስ ተዝረከረኩ ብዬ መጨነቅ
ደርሼ ሳገኘው ጋግርት ቤቱን እስኪሰራብኝ፣ የሚዳሰስ ፅልመት እስኪከበኝ ተሰላችቼ ፊት ለፊቱ መቀመጥ…
አልፈልግም፡፡
ልስቅና ልግባባው አልፈልግም፡፡
ስላሳለፈው ሕይወት
ስለ መጀመሪያ ስራው
ስለ ዩኒቨርስቲ ቆይታው
ውጪ ሃገር ስላለው አጎቱ
ልጅ እያለ ስለሞተበት ውሻው
ግንባሩ ላይ ስለተጋደመ ጠባሳው
መስማት አልፈልግም፡፡
ልስመው አልፈልግም ፡፡
አንተን እስምህ እንደነበረው አይሆንልኝማ፡፡
ሆኖ አያውቅም፡፡
ከንፈሮቹን በከንፈሮቼ ጎርሼ
ያንተን ከንፈሮች እንዳገኘሁ ማስመሰል አልፈልግም፡፡
ለምን መሰለህ….
አንዴ ሳት ብሎኝ፣ ማእቀቤን አንስቼ፣ መሃላዬን አፍርሼ ስላንተ ማሰብ ከጀመርኩ…
አዳልጦኝ እዚያ ሰፈር ከሄድኩ…
ጠረንህ ውል ካለኝ….ከንፈሮችህን ካስታወስኩ….
ኋላ መዘዙን አልችለውማ- ጣጣውን፡፡
ፈንጣጣውን፡፡
ምሽቱን ሳኮርፍና ሳዛጋበት ቆይቼ ፣
ልንለያይና ልገላገለው ስል ፣
‹‹ጥሩ ጊዜ አሳለፍን›› የሚል ውሸት መስማት፣
እኔም ይሉኝታ ይዞኝ ‹‹እኔም›› ብዬ
መወሸከት አልፈልግም፡፡
ደግሞ እንደገና
ለሁለተኛ
ለሶስተኛ …ለአራተኛ ጊዜ…ላገኘው አልፈልግም፡፡
ካንጀቴ ላዳምጠው፣ እህ ብዬ ልሰማው አልፈልግም፡፡
ስለሚወደው ዘፈን፣ ለማንም ስላልተነፈሰው ጥላሸት ምስጢሩ፣ ስለሚያሳፍረው ነገር፣ ስለሚያስለቅሰው ጉዳይ ማወቅ አልፈልግም፡፡
ደንታ የለኝም፡፡
ምን አይነት ማኪያቶ እንደሚወድ፣ ሲደብረው ምን እንደሚያደርግ፣
ዱባ ወጥ ይውደድ አይውደድ፣ ጥርሱን አሞት ይወቅ አይወቅ…ማወቅ አልሻም፡፡
እሱ የሆድ የሆዱን ሲያጫውተኝ…እኔ ግን ስለ አንተ እንደማስብ መደበቅ…
ግን ደግሞ ከእሱ ጋር ሆኜ ስላንተ ማሰብ እንደማልፈልግ እንዲያውቅ…
አልፈልግም።
ግን እኮ ሆድዬ..
አስብሃለሁ፡፡
ሁሌም፡፡
ሳላሰልስ፡፡
ቤቴ ገብቼ ቴክስት ላከ አላከ ብዬ መጠበቅ፣
ከላከ ቶሎ ለመመለስ ፍላጎት ያለኝ መምሰል
ጓደኞቹን መተዋወቅ፣
ቤተሰቡ ቤት መሄድ
በብዙ ሰው ተከብቤ በብቸኝነት መኮማተር…
አልፈልግም፡፡
ስላለፈ የፍቅር ታሪኩ፣ ስለ ወደፊት የትዳር እና የመሰብሰብ ምኞቱ…
ስንት ልጆች ለመወለድ እንደሚመኝ….
ማወቅ አልፈልግም፡፡
ሁሉም ነገር እርባና የለውም፡።
ጊዜያዊ መደበቂያ እንጂ፣ የቅጽበት ትንፋሽ መውሰጃ እንጂ አንዳች የሚዘልቅ ነገር የለውም፡፡
ከአንተ ወዲህ የማገኘው ሰው ሁሉ መዳረሻ ሳይሆን ፌርማታ ፣ ሙሉ መፅሐፍ ሳይሆን የአንዲት ገፅ ብጣሽ ነው።
ድብን ቢል ድጋሚ ልስመው አልፈልግም፡፡ የመጀመሪያውም ይቆጨኛል፡፡
ቢልልኝ ከእንግዲህ አዲስ ከንፈር አልስምም
የአዲስ ሰው ጠረን ለምጄ፣
አዲስ ሰው ፊት ልብሴን አውልቄ፣ ገላዬን ከገላው አላነካካም።
ደግሞ እንደገና መቀጣጠር…
ተቀጣጥሮ ለመፋቀር መታገል…
በግድ የተፋቀሩ መስሎ ስለወደፊት ማውራት…ማለምና ማቀድ ….አልፈልግም፡፡
የእኔ ወደፊት ከኋላዬ፣ ነገዬ ትላንት ነው፡፡
የህልም ዓለም ኑሮዬ ዛሬም ከአንተ ጋር ብቻ ነው፡፡
አንተን መርሳት፣ ከሌላ መላመድ፣
አዲስ ፍቅር…አንተ የሌለህበት ሕይወት….
በቃ አልፈልግም!

07.03.202507:09
"ሽሽት"
--------
ከባለቤቴ ጋር በጠዋት ተነስተን ወደ አውቶቢስ ተራው እንራመዳለን ፡፡
ሶስት ልጆቻችንን ይዘናል፡፡ እኔ የትልቁን እጅ በእጄ ይዤ፣ እሷ የእሱን ታናሽ አዝላ፣ ሶስተኛውን በሆዷ ይዛ፡፡
የምንሄደው የታናሽ እህቷን ሰርግ ለመታደም ነው፡፡
ወደ ሻሸመኔ ነው ጉዟችን፡፡ የትውልድና የእድገቷ ከተማ፡፡
እኔን ከማግኘቷ በፊት ትታት ሄዳ የማታውቀው ሻሸመኔ ሙሉ ዓለሟ፣ የሕይወቷ ምህዋር፣ የኑሮዋ ዛቢያ ነበረች፡፡
የተደላደለ ቤተሰብ፣ የሚንሰፈሰፉላት እናትና አባት፣ እህትዓለሜ የሚሏት ወንድሞች፣ ያለእሷ የማይሆንላቸው የቅርብ ባልንጀሮች፣ እጃቸው ሊያስገቧት ላይ ታች የሚሉ ሁለት ሃብታም አፍቃሪዎች ነበሯት፡፡
ሁለቱ አፍቃሪዎች ደጅ ሲጠኗት፣ ሲለምኑ ሲያስለምኗት አመታት ቢቆጠሩም ለእነሱ ያልራራ ልቧ ለእኔ ለአስተማሪው ወለል ብሎ ተከፈተ፡፡
በተዋወቅን በወራት ጊዜያት ይዣት ከነፍኩ፡፡
አልሰጥም ያሉ ቤተሰቦቿን አፍንጫችሁን ላሱ ብለን ኮበለልን፡፡
አባትና እናቷ በገዛ እጇ ሕይወቷን እንዳበላሸች አምነው በዘመድ አዝማድ ተይ ቢያስብሏት፣ አማላጅ ቢልኩባትም እኔ በልጬባት ጨከነችባቸው፡፡
ከዚያ ወዲህ ስትወልድ የግብር ይውጣ መጥተው ከመጠየቅና ዝቅ ያለ ኑሯችንን ከማሽሟጠጥ ያለፈ ነገር አድርገው አያውቁም፡፡
+++++
አውቶቢሱ ውስጥ ገብተን እሷ መስኮቱ አጠገብ እኔ ደግሞ እሷ አጠገብ ተመቻችተን እንደተቀመጥን ወደ ውጭ አሻግረው የሚያዩ የቦዘዙ አይኖቿን አየሁ፡፡
ሃዘን አጠላባቸው ልበል?
የታናሿን የጋብቻ ብስራት ከሰማችበት ጊዜ ጀምሮ ከዚህ ቀደም የማላውቀው ሃዘን እና ትካዜ ውስጥ ውስጥዋን ይበላት፣ እያደር ይሰረስራት፣ ቀን ከሌት ይቦረቡራት ይመስል እንግዳ የሆነ ስሜት አይባታለሁ፡፡
ሚስቴ አጠገቤ ሆና በሃሳብ እብስ..
እያወጋኋት በመንፈስ ጥፍት ትልብኛለች፡፡
‹‹እውነት ግን አንቺን ሲያስለምን የነበረው ባለ አበባ እርሻ ነው እህትሽን ያጫት?›› አልኳት በነገር ገመድ ወደ እኔ፣ ወደ አውቶቢሱ፣ ወደ ልጆቻችን፣ ወደ ኑሮዋ ልመልሳት ብዬ፡፡
ቅዝዝ እንዳለች፣ ፊቷን ወደ እኔ ሳታዞር-
‹‹አዎ…ኤፍሬም ነው አሉ፡፡ …በጣም ሃብታም ነው…አሁንማ ከዚያ ጊዜ በላይ ሃብታም ሆኗል፡፡ ሻሸመኔ ራሱ የከፈተውን ሆቴል ብታየው----›››
አውቶቢሱ ተንቀሳቀሰ፡፡
የእኔ መንፈስ ግን ቀረዘዘ፡፡
ምንድነው እየሆነ ያለው…?
‹‹የኔ ሚስት ሁሉንም ነገር…ያንን ሁሉ ሃብት ከፍቅር አይበልጥም ብለሽ …ባፍንጫዬ ይውጣ ብለሽ እኔን ምሰኪኑን አገባሽ….ተዓምር እኮ ነሽ….ሚጢጢ ተዓምር…›› አልኩ ያበጠ ሆዷን እየነካካሁ፡፡
ንዝረት ተሰማኝ፡፡
የድንጋጤ ንዝረት፡፡
ያልተወለደ ልጄ ነው እሷ አትንካኝ ያሉኝ?
መልስ አልሰጠችኝም ግን የሚታየኝ የፊቷ ግማሽ ከዚህ በፊት በማላውቀውና ትርጉም ልሰጠው ባልቻልኩት ፈገግታ ሲወረር አየሁ፡፡
ምጸት ነው?
መስሎሃል ነው ?
ፈራሁ፡፡
አውቶቢሱ ደንበኛውን መንገድ ጀመረ፡፡
መጀመሪያ ቀስ፣ ከዚያ ፈጠን ብሎ፡፡
የእኔም ሃሳብ መጀመሪያ ዝግ ብሎ፣ ከዚያ ደግሞ እያጣደፈ ያንገላታኝ ጀመር፡፡
የሰባት አመት ትዳሬ፣ ሕይወቴና የልጆቼ እናት እኔን ብላ ስለተወችው፣ ስለቀረባት ነገር ታስብ ይሆን ብዬ አሰብኩ፡፡
ከሁለቱ ባለጠጎች አንዱን ባገባ ኖሮ፣ አባቴን ብሰማ ኖሮ፣ አርፌ ሻሸመኔ ብቆይ ኖሮ፣ ከዚህ ፎከቴያም አስተማሪ ጋር ባልኮበልል ኖሮ እያለች በፀፀት አለንጋ ትገረፍ ይሆን?
አውቶቢሱ ከፍጥነት ጋር ሲንጠን የእኔም ሃሳብ ይበልጥ ያናውጠኝ ጀመር፡፡
ላልተዘጋጀሁበት ጦርነት ያለ ትጥቅ የተላኩ፣ ጋሻ ሳልይዝ የሚወረወሩ ጦሮችን ለመመከት የቆምኩ መሰለኝ።
እጇን ልያዘው።
ለእኔ ብላ፣ ሁሉን ጣጥላ ስንኮበልል እንዳደረግኩት እጇን አጥብቄ እይዛለሁ። ያኔ እረጋለሁ። ያኔ እረጋጋለሁ።
አንብቤ ልፈታው ያልቻልኩት ፊቷን ለማየት እየታገልኩ በላብ የራሰ እጄን ወደ እጇ ስልክ ግን እንዳሰበችበት በሚያስታውቅ ሁኔታ ስታሸሽው አየሁ።

Көрсетілген 1 - 24 арасынан 42
Көбірек мүмкіндіктерді ашу үшін кіріңіз.