Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Thoughts avatar
Thoughts
Thoughts avatar
Thoughts
Қайта жіберілді:
Open reading 🕊⃤ avatar
Open reading 🕊⃤
29.04.202506:40
አንዲት ሴት ፕሮፈሰር ስለ "አንድ ወንድ ብዙ ሚስቶችን ማግባት" በተሰኘ አርእስት በአንድ አካባቢ ለሚኖሩ ሴቶች እና ወንዶች ገለፃ እንድታደርግ ትጋበዛለች።

ፕሮፈሰሯ የተጠቀሰውን አርእስት ገለፃ ለማድረግ እራሷ ነበረ የመረጠችው።

ፕሮፈሰሯ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ሲያገባ ለሴት ልጅ ያለውን ጠቀሜታ በዝርዝር አስረዳች።

ሴቶችም ይህን የጋብቻ ልምድ ተቀብለው ቢፈፅሙት ያለውን ጠቀሜታ አስተማረች።

ጥቅሙ ለእራሷ ለሴቷ እንደሆነና መቃወም እንደሌለባት አዳራሽ ውስጥ ላሉት ታዳሚዎች አስረግጣ ገለፃ አደረገች።

በአዳራሹ የፕሮፈሰሯን ገለፃ ስትከታተል የነበረች አንዲት ሴት እጇን አውጥታ ለፕሮፈሰሯ  እንዲህ በማለት አስትያየት ትሰጣለች ።

"በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ ስላደረግሽልን አመሰገናለሁ!"

"ከባለቤትሽ ጋር አንቺ ሳታውቂ ፣ አብረሸው እያለሽ  ከተጋባን አሁን  አራት አመታችን ነው ፣ መንታ ልጆችም አለን አለቻት።"

ፕሮፌሰሯ ከሴትየዋ ይህንን ስትሰማ  በአዳራሹ ውስጥ እራሷን ስታ ወደቀች ፣ሆስፒታልም ተወሰደች።

ፕሮፌሰሯ ሆስፒታል ከአልጋ ላይ ሆና ስትነቃ ያቺ አዳራሽ ውስጥ አስተያየት የሰጣቻት ሴት ከአልጋዋ አጠገብ ሆና አየቻት ።

ሴትየዋ  ለፕሮፌሰሯ እንዲህ አለቻት:-

"ባለቤትሽን እንኳን ላገባው በአይኔም አይቼው አላውቅውም ይህን ያልኩት ልፈትንሽ ነበረ፤ ፈተናውን ወድቀሻል።"

"ለሌላ ግዜ ስለ አንድ አስተሳሰብ ተቀበሉና አድርጉት ብለሽ  ሌሎችን ስታስተምሪ ፣መጀመሪያ አንቺ ራስሽ አምነሽና ፣ ተቀብለሽ  መሆን አለበት" በማለት ለፕሮፈሰሯ ነገረቻት።

◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆

                   @open_reading1
                   @open_reading1
23.04.202516:27
ተኝቼ ነበር። መተኛት ሁሉ እንቅልፍ መወሰድ ነው ያለው ማነው?! እንዲሁ ስገላበጥ ሮቤል ለሁለተኛ ጊዜ ሲደውልልኝ ስልኬን ሰማሁት።

አንዴ ደውሎ ካላነሳሁ ማንሳት አለመፈለጌን ይረዳ ነበር እኮ ደጋግሞ የሚደውለው የሚፈልገው ነገር ሲኖር ስለሆነ ነው።

የማስተዋውቅህ ሰው አለ ቶሎ ና ነው ያለኝ ልደቱ መሆኑን እንደተጨማሪ ነገር ነው ነግሮኝ ስልኩን የዘጋው።

ልብስ መልበስ እና ተዘጋጅቶ መውጣት እንደድሮ አስጨናቂ አይደለም። የትኛው ያምርብኛል የቱ ይሆነኛል ብሎ ጭንቀት እድሜ ብረት ለመግፋት ድራሹ ጠፍቷል። ልብሴን ሁሉ ከመስቀያው ነው እስኪባል ድረስ መስቀያው ላይ ሰርቻለሁ።

ቆሜ በራሴ ስደነቅ ሮቤል ደግሞ ደወለ እና እንግዶቹ ሁሉ መጥተው እኔ ብቻ እንደቀረሁ ነገረኝ።

የህዝብ ሀብት ከሆነ ሰው ጋር ጓደኛ መሆን ጦሱ ይሄ ነው ብዬ እየተነጫነጭኩ ስደርስ ቤቱ ሞልቷል። የጠበኩት ምን እንደነበረ ባላውቅም ስገባ ሮቤልም ሆነ "እንግዶቹ" መምጣቴን ያስተዋለ ሰው አለመኖሩ ብዙ ቅር አላለኝም።

ከእሷ በስተቀር...

አረማመዴን አጥንታ ስትጨርስ ወደጓደኛዋ ዞራ የሆነ ነገር አለቻት። ያለእቅዴ አስፈገገቺኝ። በደረስኩበት ትኩረት ማግኘት ብርቄ አይደለም። የእሷ አኳኋን ግን ከረሜላ እንደተሰጠው ህፃን አስቦረቀኝ።

ከእሷ በስተቀር የተዘጋጀው ድግስ እዚ ግባ የሚባል አልነበረም።ሮቤል እሷን ለማስተዋወቅ እንዳስመጣኝ ነጋሪ አላስፈለገኝም። ግን መጠንቀቅ ነበረብኝ ገና እንዳየኋት የሞተው የስዕል ሀሞቴ እንደተነሳሳ ማወቅ የለባትም።

ሰዎች ስዕልን መውደድ ስለ ስዕል ብቻ ይመስላቸዋል። ስዕል ግን ስለሚሳለው ነገር አድናቆትም ጭምር ነው። በቀለም አስፍሮ ይዞ መሄድም ነው። እንጂማ ለምን በያዘችው ብርጭቆ ዙርያ ያሉትን ቀጫጭን አጫጭር ጣቶቿን ቤት ገብቼ እንዳይጠፉብኝ ደጋግሜ በምናቤ ሳልኳቸው?

አይኖቿን በደንብ ልሸምድድ ብዬ ሳያት ተገጣጠምን እያየቺኝ ነበር። የሰውነቴ አካላቶች ተባብረው ስራ አቁመው ጥንካሬው ሁሉ አይኗን ለመቋቋም ውሎ ነበር። አስተያየቷ ሀይል አለው የሀምራዊ ቀለም አይነት ስበት በጣም ሳይለፋ ማሰገድ የሚችል ሀይል ደረቴ ጋር መጨናነቅ ሲሰማኝ ነው መተንፈስ አቁሜ እንደነበር ያወቅኩት።

አይኗን ቶሎ አሽሽታ የተጋነነ "አልተዘበራረቅኩም አይደል" ሁለመናዋን አስተካከለች። ሰው እንዴት እኩል ሁለት ተቃራኒ ስሜት ይሰማዋል?! የኔ ሁኔታ ይቆይና የእሷን አይኔን መሸሽ ሳይ እንዴት ለኩሩ ልቤ ደስታ ብቻ አይሰጠውም ለምን በደንብ እንድታየኝ ተመኘሁ መርበትበቷ ለምን አናደደኝ?! እንጃ...

ብቻ የሀሳቤ አቅጣጫ ስላላማረኝ ወደእሷው ስዕል ተመለስኩ። ፀጉሯን ለመሳል ብዙ ጭረት ማስፈለጉ አይቀርም በግድየለሽነት የተዝረከረከው እሷን አሳምሯታል እኮ እኔን በኋላ ሊያቸግረኝ ከዛ ደግሞ ገርበብ ያሉት አይኖቿን እና የሚያሳሱ ከንፈሮቿን አይኔን ጨፍኜ እግሬ ላይ በጣቴ ለመሳል እየሞከርኩ እያለ ሮቤል መጠጥ ይዞልኝ መጣ

"እንኳን ተወለድክ ይቅር ሰላምታ እንኳን አይገባኝም" አለ አጠገቤ እየተቀመጠ "ምን ቸገረኝ እኔ አንተን ለማግኘት አልመጣሁ ባይሆን አንድ ጊዜ ብትዞር እኮ ፀጉሯን አየው ነበር" አልኩት

"አጅሬ ማን እንደሆነች ሳልነግርህ ጭራሽ እንደምትስላት ወስነሀል" ብሎ ረጅም ሳቅ ሳቀ

"አሁን አትረብሸኝ" እስኪ ስለው የድሮ ጓደኞቻችን ቀስ በቀስ ከበቡን ጓደኝነታችን ከእኔ ይልቅ ለእሱ ስለሚያደላ ብዙ ምቾት አልሰጠኝም ነበረ።

ከዛ ግን ሳባ "ኤርሚ አሁንም ትስላለህ እንዴ?!" አለቺኝ በቃ ከዛ በኋላ ማን ይቻለኝ የለበስኩትም ኮት ጠበበኝ ሸሚዙም ወደክንዴ ተሰበሰበ። ረጅሙን መግለጫ ሰጠኋቸው።

ደጋግማ ሰርቃ ስታየኝ በአይኔ ዳርቻ አይቻታለሁ። "ሄጄ ላውራት?! ግን ልታወራኝ ባትፈልግስ?!" በሚል ሰጣገባ ውስጥ ስታገል ራሴን አገኘሁት። የውሳኔ ሰው አልነበርኩ እንዴ?

ድምጿ ምን አይነት ይሆን እንደ ሀምራዊ መግነጢሳዊ ወይስ እንደ ፈዛዛ ሮዝ ለስላሳ?! ብቻ ላወራት ይገባል ብዬ ስዞር ሮቤል ከጀርባዋ የሆነ ነገር ሲላት አየሁት ፊቷ ሲቀላ ሳየው ደነገጥኩ።

የመጨረሻው ክፍል እስኪለቀቅ ድረስ react እያደረግን😄



✍ናኒ




https://t.me/justhoughtsss
22.04.202507:04
8123

<<<<<>>>>>>



ይሄኛውን ቴክስት የላከችልኝ ረቡዕ ነበር፡፡ በስራ ሰዓት ፡፡


‹‹ሄይ  ቆንጂት…! እኔ የምልሽ፣  ሴቭ ዘ ችልደርን HR ውስጥ ያለ ሰው ታውቂያለሽ እንዴ? ››



ደምበኛ ሰላምታ የለ፣  ናፍቀሽኛል የለ፣ ደህና ነሽ ወይ የለ።

‹‹ሄይ ቆንጂት›› ያለችውም ለምትፈልገው ነገር ስታመቻቸኝ ነው፡፡




በረጅሙ ተነፈስኩ፡፡



ለስሙ ጓደኛሞች ነን፡፡


ለመጨረሻ ጊዜ ካወራን ግን ሁለት ወር ያልፈናል፡፡  ያኔም የሆነ ሰው ስልክ ቁጥር ፈልጋ ነው የደወለችልኝ፡፡አፍሪካ ህብረት የሚሰራ ሰው፡፡


…..ከዚያ በፊት ደግሞ የጻፈችልኝ ቴክስት፣


  “ስሚማ ፍቅር፣  ያ ዩ ኤን ዲፒ የሚሰራው ሰውዬ ስልክ  አለሽ እንዴ? ያ እንደውም ዶሎ አዶ ፕሮጀክት ማኔጀር የነበረው?”  የሚል ነበር፡፡



ከዚያ በፊት ደግሞ አንዱን ቅዳሜ ጠዋት ምን ብላ ጽፋልኝ ነበር…?


አዎ…

“ሄይ….በናትሽ ያ የአጎትሽ ልጅ፣ ቴሌ የሚሰራው… አሁንም እዛ ነው እንዴ? ሲምካርዴ እኮ ድጋሚ ተዘጋብኝ”


እንዴት ነሽ፣ እንዴት አደርሽ እንኳን ሳትል፡፡




አንዱን ቀን ደሞ ለእኩለ ሌሊት ትንሽ ሲቀረው ደወለችና፣ በጣም ለምትፈልገው ስራ ልታስገባው የጻፈችውን ‹‹ሞቲቬሽን ሌተር›› ቶሎ ብዬ እንዳስተካክልላት ላከችልኝ፡፡ 



ወሊሶ ነበርኩ። ከስራ ድካም አረፍ ልበል ብዬ ቤተሰብ ጋር፡፡
ግን ጭንቀትዋን አየሁና፣   ‹‹እሺ ጠዋት አይቼ አስተካክልልሻለሁ›› ብያት ስልኩን ዘጋሁ፡፡



ማለዳ፣ ገና በቅጡ ሳይነጋ ደውላ ፣

“እ እንዴት አረግሽልኝ?” አለችኝ።



የናፈቀችኝ እናቴ ቤተክርስትያን አብሬያት እንድሄድ እየለመነችኝ ለእሷ ብዬ ቤት ቀረሁ፡፡




ይህ ከሆነ ከሶስት ሳምንት በኋላ ስትጠፋብኝ፣
‹‹እሺ፣ ያ ጉዳይ እንዴት ሆነልሽ..ተሳካ?›› ብዬ ስለስራው ስጠይቃት ሌላ ነገር ሳትለኝ፣ በብልጭልጭ መብራት ውስጥ የምትደንስ ትንሽዬ ልጅ "ጂ አይ ኤፍ "ብቻ ልካ ደግሞ እንደ ልማዷ ጥርቅም አድርጋ ዘጋችኝ፡፡



አንዴ ደግሞ ለራሴ እንኳን የምሳሳለትን ሀበሻ ቀሚሴን ለአክስቷ ልጅ ሰርግ ልትለብሰው አውሺን አለችኝ፡፡ 


አይሆንም ብላት
አጃቢ ነኝ ..
ደህና ነገር መልበስ አለብኝ…
ስሞትልሽ…ስከተፍልሽ

ምናምን ብላ አለቃቀሰችብኝ፡፡

ንዝንዝ ስታደርገኝ፣



‹‹ስሚ ! በእቁብ ነው የገዛሁት፡፡ አንድ ነገር ብታደርጊው የመጨረሻችን ነው፡፡ ደግሞ በስርአት ራስሽ አጥበሽ ነው የምትመልሺው›› ብዬ እያንገራገረኩ ሰጠኋት፡፡



እሺ እሺ ብላ፣ ምላ ተገዝታ ወሰደችው፡፡




በነጋታው አጥቤ አመጣለሁ እንዳላለችኝ በስንት ልመና ከአስር ቀን በኋላ የመለሰችልኝ በአሮጌ ኩርቱ ፌስታል ውስጥ ጎስጉሳው ነበር፡፡


አላጠበችውም፡፡
ላቧና ሽቶዋ ያበላሸውን ቦታ አይቼ ከንዴቴ ሳላገግም ጥለቱ ላይ አዋዜ መፍሰሱን ሳይ ጨስኩ፡፡ 



ያደረገችውን ነገር ስለምታውቅ ጥፍት አለች፡፡




ከብዙ ጊዜ በኋላ እንዲሁ ጉዷን ልይ እስቲ፣ ዝም ብዬ ሰላም ልበላት ብዬ ደወልኩላት።

ያው ስለማንገናኝ። ሁለቴ ጠራ፤ ስልኳን አላነሳችም።



ነገሩን ረስቼው፣ ከሶስት ቀን በኃላ ቴክስት ላከች፡፡



‹‹ ይቅርታ ብታይ አዲሱ ቦታ ስራ ብዝት ብሎብኛል። እኔ የምልሽ…የጥላ ስፓ ስልክ አለሽ አይደል? ዌብሳይታቸው ላይ ያለው አይሰራም፡፡ ካለሽ በናትሽ ቶሎ ላኪልኝ፡፡ ጀርባዬ ቆስሎልሻል፡፡  ዛሬውኑ ማሳጅ መሄድ አለብኝ።›› ይላል፡፡




እንደ ጓደኛ ለሆነ ጉዳይ ካላስፈለኳት አብረን ምሳ በልተን አናውቅም።
እሷን በሆነ መልኩ የማይጠቅማት ከሆነ ሻይ ቡና እንኳን አንባባልም።





ስንት አመት ሳባብላት ኖሬ፣ የእሷ ነገር የቆረጠልኝ ግን የሚከተለው ነገር ሲፈጠር ነው፡፡

እናቴ በጠና ታማ አዲሳባ አምጥቻት ሆስፒታል ገብታ ነበር፡፡



አንዱን ቀን ብቸኝነትና መከፋት ሲያሸንፉኝ ስለመታመሟ ፌስቡክ ላይ ፖስት አደረግኩ፡፡



ለራሴም በገረመኝ ፍጥነት ወዲያው ቴክስት አደረገችና፣


“ወይኔ የእኔ ቆንጆ ሶሪ…ማዘር ምን ሆና ነው…?እስኪ ማታ እደውልልሽና አወራሻለሁ።” አለች።


ሰው ባጣሁ ሰአት ሰው ልትሆን ነው ብዬ እንደ ሞኝ ጠበቅኳት፡፡


እሷ እቴ፡፡


አልደወለችም።



ከ አራት ወይ አምስት ቀን በኃላ ሌላ ቴክስት ላከች፡፡


“ፍቅርዬ፣ እማዬ እንዴት ሆነች?  ተሻላት አይደል? በነገርሽ ላይ ባለፈው ፖስት ስታደርጊ ላንሴት ናት ብለሽ ነበር አይደል ? እስኪ ላንሴቶች ደህና neurosurgeon ካላቸው ጠይቂልኝ በናትሽ፡፡ አጎቴ ታሟል፡፡”




ስያሜ ልሰጠው ያልቻልኩት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ዝም፣ ጭጭ አልኩ፡፡

ዝግት- ቁልፍ አደረግኳት፡፡


---

ይሄው ዛሬ፣ በረቡዕ ምድር፣ በስራ ሰአት፣ አይኗን በጨው እጥብ አድርጋ፣ ሌላ ውለታ ፈልጋ፣ የተፈጠረው ነገር ሁሉ እንዳልተፈጠረ፣ የሰራችኝን ነገር ሁሉ እንዳልሰራችኝ፣

  ‹‹ሄይ  ቆንጂት…! እኔ የምልሽ፣  ሴቭ ዘ ቺልደርን HR ውስጥ ያለ ሰው ታውቂያለሽ እንዴ? ›› ብላ ቴክስት ላከችልኝ፡፡




ወዲያው አልመለስኩላትም፡፡
ለቡና ወጣሁ፡፡
ከባልደረቦቼ ጋር ምሳ በላሁ፡፡
እህቴ ጋር ደወልኩ፡፡ እናቴ መድሃኒቷን መውሰዷን አረጋገጥኩ፡፡


ከዚያ ግን መለስኩላት፣


‹‹አንቺ ግን በቃ ማፈር ተውሽ አይደል….?ለማንኛውም እስቲ ዛሬ እንኳን አፋላጊዎችን ጠይቂ፡፡  8123 መሰለኝ ቁጥራቸው›› ብዬ፡፡


አልመለሰችልኝም፡፡

በዚያው ተቆራርጠን ቀረን፡፡ 

ለነገሩ እኔ አልቆርጥ አልኩ እንጂ እንደ ጓደኛ ከተቆራረጥን እኮ ቆየን፡፡
17.04.202518:04
ባህላዊ date

"ከዚህ በኋላ ባንገናኝ ደስ ይለኛል አልኩት" አለች እጇን አጣምራ

"ማለት?! date ማድረግ ከጀመራችሁ ስንት ጊዜያችሁ ቢሆን ነው?!"

"ሁለት ወይ ሶስት ወር እኔንጃ" ትከሻዋን ሰበቀች

ግራ ገባኝ "ቆይ date ማድረግ ቀልድ ነው እንዴ?! እኔስ የማዝነው ለወንዶቹ ነው" አልኳት

"እዚህ ጋር እኮ ነው እኔና አንቺ የማንስማማው date ማድረግ ማለት እኮ ዘሎ ፍቅረኛሞች ሆኖ boyfriend girlfriend ለመባባል አይደለም ለመተዋወቅ ነው አሁን እኮ ነገር አለሙ ተቀላቅሎብን ነው እንጂ የድሮ date እና ትዳር ቢሆን..."

"ስለ arranged marriage ነው የምታወሪው?!" አልኳት ቅንድቤን ሰቅዬ

"አዎ በቤተሰብ ምርጫ ቤተሰብ ያለበት dating ማድረግ ማለት ነው። ለምን እንደሚጠቅም ታውቂያለሽ ዘሎ አካላዊ ነገር ውስጥ እንዳይገቡ ይጠብቋቸዋል ሌላስ አትዪም?!" አለች እጇን እየሰበሰበች

"ሌላስ"

"ከዛ ደግሞ መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች መጠየቃቸውን ቤተሰብ check ያደርጋል 'ፍቅር ነው ታውረናል' ምናምን እንዳይሉ ማለት ነው። እንደውም የዛ ዘመን ትዳሮች ፍቺ በብዛት አይጎበኛቸውም ነበረ የዘንድሮ በእውር ድንብር እየተገባ እኮ ነው"

"ይሄ ካንቺ ጋር እንዴት ይገናኛል?!"አልኳት እየሳቅኩ

"እንዴት ይገናኛል መሰለሽ ዘመኑ አሁን የነገርኩሽን የdating መንገድ አልፎበታል ቢልም arranged marriage የፋራ ተብሎ ቢቀርም እኔ ለራሴ የቤተሰቦቼን ሀላፊነት ነው እየተወጣሁ ያለሁት date ነው ያደረግነው በይፋ የተባለ ነገር የለም"

"ስለዚህ ተጠናናን ነው የምትዪኝ እና ምኑ ነው ያልጣመሽ" አልኳት ገርማኝ

"ከአንድ መንገደኛ የተሻለ ሊያደንቀኝ አልቻለም 'አይንሽ ያምራል ቁመናሽ ቀሚስሽ' ምናምን ለራሴ ታክቶኛል" አለች በስጨት ብላ

"ማለት ወዶ አይደለም እኮ አትፍረጂበት" አልኳት የተዋጣላት ቆንጆ መሆኗን ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው

"ማድነቁ እኮ አይደለም ምን የሰፈር ተላካፊው እንኳን ያደንቅ አይደል?! ግን ጊዜ መስጠት ማለት ይሄ ከሆነ መግባባት ማውራት ጊዜ ማሳለፍ ምናምን ከአካላዊ አድናቆት ካላሳለፈን አስቸጋሪ ነው"

"በቃ?!" ለመለያየት የምታቀርባቸው መስፈርቶች እያስገረሙኝ መጥተዋል

"አልገባሽም እንዴ?! የማወራውን ካልሰማኝ የመልኬን ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰቤ ማማር ካልታየው ይሄ እኮ ፍቅር አይደለም"

"እና ምንድነው"

"ምኞት ነዋ አፍጥጦ ሰምቶሽ ያልሽውን አንዱንም ካልሰማ ወይ ሀሳቡ ሌላ ጋር ነው ወይ ደግሞ ከአካላዊ ምኞት የዘለለ አላማ የለውም ማለት ነው"

"ነገረሽዋል ግን" አልኳት ባላወቀበት እየተጨፈጨፈ ከሆነ ብዬ

"አዎ ብዙ ግዜ አውርተንበታል ያው ሁሉንም በንግግር የሚፈታ ሳይሆን ግዜ የሚፈታው ስለሆነ በሰላም ተለያየን እልሻለሁ"

"ፐ ዘመናዊነት ብዬ እንዳላደንቅሽ ይሄ ዘመናዊነት አይደለም ግን ጥሩ ነገር ስለሆነ ያወራሽው ይሁን  አልኳት

እንደዚህ ስሜት ላይ ጥገኛ ሳይሆኑ ውሳኔ መወሰን ምንኛ መታደል ነው


✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss
Жойылды17.04.202521:19
Жойылды17.04.202521:19
Қайта жіберілді:
ጥበብ ፍልስፍና avatar
ጥበብ ፍልስፍና
¹ አብ ልጁን ለደረው፣ ምን አስቀናት ፀሐይ?
      ፊቷን  ያጠቆረች፣ ዓለሙን እንዳያይ::

² ሊጠቅመው አስቦ፣ አባቱ በመላ
ላጀበው ሰው ሁሉ፣ ፅዋዉን ሳይሞላ
ልጁን ብቻ አጠጣዉ፣ የድግሱን ጠላ።

³ ደሀ አባት ደግሶ፣ ታዳሚዉን ሁሉ
በሬ ሳያዘጋጅ፣ ነው የጠራው አሉ፣
ካጀቡት ቡኋላ፣ ተጠምተው ተርበው
ከልጁ በስተቀር፣ የለም የሚያቀረበው።

⁴ ስንት ቢታረድ ነው፣ ምን ያክል ቢደገስ
ስጋዉ የሚበላዉ፣ እስከ ዛሬ ድረስ?

⁵ የተሰቀለዉን፣ ስጋዉን ሳይቀምሱ
አጃቢዎች ምነዉ፣ ተሻሙ ለልብሱ?

⁶ለሙሽራዉ ሀሞት፣ ምን ያህል ቢጥም ነው?
ለሚዜውቹ እንኳ፣ አላጠጣም ያለዉ?
            

@ethiosecret
Қайта жіберілді:
እንማር avatar
እንማር
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። አንዱ አጠገቡ ላለው ጓደኛው እንዲህ አለው። "ቄሱ ቆንጆ ሚስት አለቻቸው። እንዋደዳለን። አሁን እሷ ጋ ልሄድ ነው። አንተ ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን በወሬ ያዝልኝ። ከመምጣትህ በፊት አስቀድመህ ደውልልኝ አደራ" አለው።

ጓደኛው ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን አስቁሞ የባጥ የቆጡን ያወራላቸው ጀመር። ቄሱም በሰውዬው የተዘበራረቀ ንግግር ግራ ገባቸውና ምን እንደፈለገ በቁጣ ጠየቁት።

ሰውዬም የሃጢአተኝነት ስሜት ተሰማውና ዕውነቱን ነገራቸው "ይቅር ይበሉኝ አባቴ! ጓደኛዬ ከእርስዎ ሚስት ጋር ሊተኛ ሄዶ እኔ እርስዎን በወሬ እንድይዝሎት ነግሮኝ ነው" ብሎ እግራቸው ላይ ወደቀ።

ቄሱም ፈጥነው አነሱትና እንዲህ አሉት "አንተ ሞኝ! አሁኑኑ ወደ ሚስትህ ፈጥነህ ሂድ! እኔ ሚስቴ ከሞተች 5 ዓመት አልፏታል
"....... !🙆‍♂️

ምን ልልክ ፈልጌ ነው ላጤነት ይለምልም 🖐


Tesfaye Hailemariam
📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
19.04.202514:03
ሲመጣ አየሁት አረማመዱ ከራስ በተማመንም በላይ ኩራት አለበት። አልጣመኝም።

ሩትን "ማነው" አልኳት "እኔም አንቺም ካላወቅነው የሮቤል ጓደኛ ነው የሚሆነው"  አለቺኝ

የሆነ አይነት ግርማ ሞገስ አለው የሚስብም የሚገፋም አይነት ነገር ሁለተኛ ያልጣመኝ ነገር

ገና ገብቶ አንዱ ጥግ ላይ ከመቀመጡ ሮቤል ካለበት ግርግር መሀል ወጥቶ ሄዶ ሰላም ብሎት ማውራት ጀመሩ። ሀሳቤን ወስዶት ሩት የምታወራውን እንኳን መስማት አቁሜያለሁ

"አንቺ ስሚኝ እንጂ ለ25 አመት ልደት የምን ግርግር ማብዛት ነው እያልኩሽ እኮ ነው አትሰሚኝም እንዴ" አለች ትከሻዬን ገፋ አድርጋ

"እህ??...አዎ... ይገርማል" አልኳት በደመ ነፍስ

ስለ ሮቤል ልደት ነው የምታወራው ልደቱን ማክበሩ ሳያንስ ጓደኞቹን በሙሉ ደግሶ መጥራቱ ገርሟታል።

እሷን ላወራ ዞሬ ስመለስ አይናችን ተገጣጠመ። የሚያስፈራ አስተያየት ውስጥ ማየት የሚችል የሚመስል የአይኑ አካባቢ አጥር እንዲሆነው ይመስል የጎደጎደ ጥልቅ አይን ቶሎ ብዬ አይኔን አሸሸሁ ሶስተኛ ያልጣመኝ ነገር

ወዲያው ሮቤል መጠጥ አምጥቶለት አብረው ተቀመጡ እኔ ላይ የሰራው መግነጢሳዊ ነገሩ ሌላውም ላይ ሰርቷል መሰል ቀስ ቀስ እያለ ሰዎች እየከበቡት መጡ

እንደውም ከዛ አቅጣጫ የሚመጣው የሴት ሳቅ ድምፅ በረከተ። በብዛት አይስቅም በሸራፋው በከንፈሩ ጠርዝ ነው ፈገግ የሚለው። በጣም ስለሚወደው ነገር እያወራ እንደሆነ ያስታውቃል እጁን ሰብስቦ በአይኑም በእጁም ነው የሚያወራው። በጣም ያልጣመኝ ከቀደሙት ሶስቱ የበለጠ ያልጣመኝ ነገር

እያየሁት ስብሰለሰል "ኤርሚያስ ነው ስሙ" አለኝ የሆነ ድምፅ ክው ብዬ ደንግጬ ስዞር ውስኪው ውስጥ በረዶውን እያሟሟ ብርጭቆውን እያሽከረከረ ሮቤል ቆሟል። ፊቱ ላይ ያ የማልወደው ፈገግታ ረብቧል።

"ማን ጠየቀህ አሁን" አልኩት ያልተበላሸውን ፀጉሬን እያስተካከልኩ

"የቀላው ጉንጭሽ" ብሎ ከት ብሎ ሳቀ

"አውቀህ ነው አይደል የጠራኸው?!" አልኩት

"አዎ ያው ምን አይነት እንደሚመችሽ ስለማውቅ ከልምድ በመነሳት ነው" አለ ፈገግታው ከፊቱ ሳይጠፋ

"ልሄድ ነው" አልኩት

"አታረጊውም" አለች ሩት የሰማችንም አልመሰለኝም ነበረ

"አትሄድም ባክሽ እንኳን ኤርሚን የመሰለ አግኝታ እንዲሁም ታቂያት የለ" አለ የድግስ ልክፍቴን ስለሚያቅ

"በሉ በሉ ቻው" ብዬ በአይኔ እንኳን ልሰናበተው ወደሱ ስዞር ድጋሜ ተገጣጠመ። አይናችን።

ይሄኔ run away በቃ ምንም የምጠብቀው ነገር የለም። ማንም ተመሳሳይ ስህተት እየደጋገመ አይሳሳትም። ያ ጊዜ አብቅቷል አይደል?! የሰዎችን ትኩረት ለማግኘት የምጋጋጥበት ለትንሽዬ ትኩረት የምዘልበት፥ ሁሉንም ጉረኛ ወንድ እንደ challenge የምቆጥርበት ወቅት አብቅቷል አይደል

ደህና ነበርኩ እኮ እስካየው ድረስ አሁንም ቢሆን አልረፈደም አሁን ተሻሽያለሁ መሄድ እችላለሁ ችግሮቼን ራሴ ላይ አልጠራም እንደውም መሄድ አይደለም እሮጣለሁ

"ኤፊ ኧረ ኤፍራታ..." ሩት ስትጣራ እየሰማሁ ጥያት በሩጫ እልም

ክፍል ሁለት ይቀጥል???


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
Жойылды17.04.202521:19
Қайта жіберілді:
ዳን ŦËŁŁ avatar
ዳን ŦËŁŁ
ካሊፎርኒያ ዴዝ ቫሊ /Death Valley/ ብሔራዊ ፓርክ አንድ አስገራሚ የተፈጥሮ ሚስጥር የሚባል ነገር አለ። የደረቀው በርሃማ መሬት ላይ ድንጋዮች ወደፊት ይንቀሳቀሳሉ። ሲንቀሳቀሱ በቀጥታ አይታዮም ግን ከኋላ የተንቀሳቀሱበትን አሻራ እየተው ፈቀቅ ይላሉ። አንዳንዶቹ ድንጋዮች እስከ 700 ቶን የሚመዝኑ በዘመናዊ ማሽኖች እንኳን ሊንቀሳቀሱ የማይችሉ ቋጥኞች ናቸው። ሳይንቲስቶቹ ብዙ መላ ምት ቢያስቀምጡም የነገሩ ምክንያት በትክክል አልታወቀም። የሆነ ሆኖ "ድንጋይ እንኳን ወደፊት እየተንቀሳቀሰ ነው" ጓዶች። እንደአገር እንደግለሰብ ባሉበት ቁሞ የመቅረትን መንፈስ ወጋሁት🖐

✍️Alex Abreham
Жойылды17.04.202521:19
Қайта жіберілді:
ጥንቅሻ✍🏼🦋 avatar
ጥንቅሻ✍🏼🦋
13.04.202518:49
ደብዘዝ ያለ ቀይ፣ ነጫጭ ትናንሽ አበቦች ምስል ያለበት ረዘም ያለ የሚያምር ቀሚሷን ለብሳ ፀጉሯን እንዲሁ አሲዛ ከሁዋላ ለቃዋለች፣

ከፍ ያለ ጫማ ነው ያደረገችው....

ነጭ ቦርሳዋን ይዛ ወደ ቢሮ ስትገባ ሳያት ተነስተህ እቀፋት እቀፋት አለኝ....

ከውስጤ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ ሳላውቀው ፈገግ አልኩኝ፣

ለልብ ትግል የለውም፣ እንዲሁ ይለመዳል፣ ከአንድ ዕይታ ጀምሮ ራስን እስከመስጠት ይጠልቃል...ይሰፋል፤

ድንገት የሚወደውን አይቶ ስራው የሚጠፋበትን፣ በደስታ የሚዋኝን...እንዴት ነው ሳይማር መውደድ ያወቀን ልብ "ተው" ተብሎ አለመውደድ፤

አለማፍቀር የምናስተምረው?
Қайта жіберілді:
𝗕𝗘𝗠𝗡𝗘𝗧 ✍️ avatar
𝗕𝗘𝗠𝗡𝗘𝗧 ✍️
ሁለት ሰዎች በጠና ታመው በአንድ ክፍል ውስጥ ተኝተዋል።

አንደኛው ታማሚ ሳንባው የቋጠረው ውኃ ለማድረቅ ሲባል ብዙውን ሰዓት ቁጭ እንዲል ተደርጓል።

ሌላኛው ደግሞ በጀርባው ተኝቶ ነው ሕክምናውን የሚያገኘው በፍፁም መንቀሳቀስ አይችልም።

ሁለቱ ታካሚዎች በቆይታቸው ተግባብተዋል ስለ ሥራቸው፣ስለቤተሰባቸው፣ስለኑሮ ፣ስለ ሀገር፣ስለወታደር ቤት ብቻ ብዙ ነገር አውግተዋል።

ብዙውን ግዜ ቁጭ የሚለው ታካሚ ሁልግዜም በጀርባው ለተኛው እና መንቀሳቀስ ለማይችለው ታካሚ ጓደኛው ስለውጪው እንዲህ እያለ ይነግረዋል....

በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ትንሽዬ የሚያምር ሐይቅ ይታየኛል፣ በሐይቅ ላይ ዳክዬዎች ይዋኛሉ፣ሕፃናትም በወረቀት የሠሩትን መርከብ በሐይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ፣ፍቅረኛሞች በአንድ እጃቸው ተያይዘው በሌላው አበባ ይዘው በፍቅር እየተያዩ ብዙ ግዜያቸውን አብረው ያሳልፋሉ.

ከሐይቁ ባሻገር በቅርብ ርቀት ላይ በውስጧ ለመኖር የምታጓጓ አንዲት ውብ ከተማ ትታየኛለች.... እያለ ይነግረው ነበር በጀርባው የተኛውም ታካሚ ሁሉንም ነገር በዓይነ ህሊናው እየሳለ ለመረዳት ይሞክራል

ከቀናት በኃላ ያ ብዙውን ግዜ ቁጭ የሚለው ታካሚ ሕይወቱ ያልፋል በጀርባው የሚተኛውም ታካሚ መንቀሳቀስ ሲጀምር ጓደኛው ይነግረው የነበረው ነገር በመስኮቱ ለመመልከት ሲሞክር የሆስፒታሉ ሌላ ግንብ በትንሽ ርቀት ብቻ ነበር የሚታየው....

በጓደኛው ተግባር በጣም ተገረመ ለካ ጓደኛው የማይታየውን እንደታየው እያደረገ የሚነግረው እርሱን በተስፋ ለማኖር እና ውስጡን አጠንክሮ ከበሽታው ቶሎ እንዲያገግም ነበር

ወዳጄ ነገሮች ላንተ ባይሆኑ፣ እንደማይሆንልህ ቢገባህም ለሌላ ሰው ተስፋ እና ሕይወት መሆን ትችላለህ እና በፍፁም በራስህ ተስፋ አትቁረጥ።

ባንተ መልካምነት አንድ ነፍስ እንኳን ማዳን ከቻልክ እንዳንተ ጀግና የለም
23.04.202510:50
ወገኖቼ ትንሽ busy ሆኜ ነው ዛሬ ማታ ጠብቁ ክፍል ሁለት ይለቀቃል
17.04.202507:18
መቼ ነው ህይወት ለዛዋ የጠፋው? መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ከልባችን የሳቅነው?! መቼ ነው በልተን የተደሰትነው? መቼ ነው ማማረር የሌለበት ወሬ ያወራነው? መቼ ነው የጨላለመብን? መቼ ነው የምንሰማው የምናየው ሁሉ የበጠበጠን? መቼ ነው
መዝናኛችን እንደ አዙሪት ከድብርታችን ያበረብን?

መቼ ነው በደንብ መኖር ያቆምነው?

በደንብ መሳቅ? በደንብ ማልቀስ? በደንብ መውደድ? በደንብ መግባባት? በደንብ መናፈቅ? በደንብ ማለም? በደንብ ለህልም መጋጋጥ? በደንብ መጎዳት? በደንብ መድመቅ?

መቼ ነው ህይወት እንደነገሩ የሆነችብን?

ከላይ ከላይ ብቻ የሆንነው መቼ ነው? ትልቋን ህይወት አጥብበን ጥቂት ሙከራ፥ ጥቂት ጥረት፥ ጥቂት ሀዘን፥ ጥቂት ተስፋ ግን ብዙ ጨለማ የከበበን መቼ ነው?! የቱ እጦት ነው ቋጥኝ ድብርት የጣለብን? የቱ እድሜ ነው ብዙ አሳይቶ ብዙ ያደከመን? የቱ እውቀታችን ነው ወደፊቱን የጋረደብን? ማነው እድሜያችን ቢበዛ ሰላሳ ብሎ በጊዜ መንፈሳችን ጡረታ ያወጣው? ምንድነው የዞረብን?!

መቼ ነው እንደዚህ የሆንነው?

✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss
Жойылды17.04.202521:19
Қайта жіберілді:
👑 አዳም ረታ 👑 avatar
👑 አዳም ረታ 👑
15.04.202505:51


ነሃሴ 1 1966። አንድ የ25 አመት ወጣት ትልቅ ህንጻ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድንገት መተኮስ ጀመረ። በዚህ ትራጄዲ 13 ሰዊች ሲሞቱ፣ 33 ቆሰሉ። ፖሊስም በመጨረሻ ወጣቱን ተኩሶ ገደለው። ፖሊስ ወጣቱ ቤት ሲሄድ ሁለት አስክሬን አገኘ—የእናቱንና የሚስቱን። ይህ ወጣት ሁለቱንም የገደላቸው፣ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነበር።

በጣም አስገራሚው ነገር፣ ፖሊስ የወጣቱ ቤት ውስጥ ይህንን ትራጄዲ ለመፈጸም የሚያነሳሳው ምንም ምልክት አላገኘም። ወጣቱ የስካውት አባል፣ የባንክ ሰራተኛና የምህንድስና ተማሪ ነበር።

ወጣቱ አናቱንና ሚስቱን ከገደለ በኋላ ኑዛዜ መሰል ነገር ጽፎ ተገኝቷል። ኑዛዜው እንዲህ ይላል።

"ከቅርብ ግዜ ወዲህ ራሴን ለመረዳት አልቻልኩም። ኃላፊነት የሚሰማው፣ ብልህ ወጣት ነበርኩኝ። ነገር ግን ከግዜ ወዲህ(እርግጠኛ ቀኑን አላስታውሰውም) እንግዳ የሆኑ መሰረተ-ቢስ ሃሳቦች በአእምሮዬ ይመላለሱብኛል። ከሞትኩ በኋላ ምርመራ ተደርጎብኝ፣ ያለብኝ አካላዊ ግድፈት እንደሚጣራ ተስፋ አደርጋለሁ።"

ወጣቱ የጠየቀው ተፈቅዶ የሬሳ ምርመራ ተደረገለት። ታዲያ ዶክተሮች አንድ አስገራሚ ነገር አገኙ። በወጣቱ አእምሮ ውስጥ ትንሽ እጢ ተገኘ። እጢው አሚግዳላ የሚባለው የአእምሮ ክፍሉን ተጭኖት ተገኘ። አሚግዳላ ደግሞ በአእምሯችን ፍርሃትን የሚቆጣጠር አካል ነው። ወጣቱ ከመጠን በላይ የሆነ ፍርሃት ተሰምቶት ነው ያንን ሁሉ ትራጂክ ግድያ የፈጸመው። አለበለዚያ በወጣቱ ባህሪ ውስጥ እነዲህ ያለ ተግባር ሊፈጽም ይችላል የሚያስብል አንድም አጣራጣሪ ነገር አልነበረም።



ሄንሪ የሚጥል በሽታ የጀመረው ገና በ15 አመቱ ነበር። ከዚያ ወዲህ ህመሙ ይበልጥ እየከፋ መጣ። በመጨረሻ ሄንሪ ገና በሙከራ ላይ ያለ የአእምሮ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ተስማማ።

ህክምናው ተደረገ። ከሄንሪ አእምሮ ሁለቱም ክፍሎች ሂፖካምፐስ የተሰኘ ክፍሉን በከፊል አስወገዱት። የቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ሄንሪ ከሚጥል በሽታው ዳነ።

ነገር ግን ዶክተሮቹ ያላሰቡት ነገር ተፈጠረ። ሄንሪ ምንም አይነት አዲስ የማስታወስ ተግባር መፈጸም አልቻለም። ይህ ብቻ አይደለም። ሄንሪ የወደፊቱን ግዜም በምናብ መሳል አይችልም። የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ሂፖካምፐስ የሚባለው፣ በአእምሯችን ውስጥ የሚገኝ አስታዋሽ ክፍል ከሄንሪ አእምሮ በመወገዱ ነው።



ማይከ የማየት ችሎታውን ያጣው ገና በሶስት አመቱ ነበር። የኬሚካል ፍንዳታ ተፈናጥሮበት አይነስውር ሆነ። አይነስውር ሆኖ የተሳካለት የቢዝነስ ሰው፣ ከዚህ በተጨማሪ በፓራሎምፒክ የበረዶ ሸርተቴ ውድድር ሻምፒዮና ሆነ።

ከ40 አመት በኋላ ዶክተሮች ዳግም የማየት ተስፋ እንዳለው ነገሩት።። እሱም ቀዶ ህክምና ለማድረግ ተስማማ። ቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ። ከህክምና ሳይንስ አንጻር ውጤታማ ነበር፤ ከማይክ አንጻር ግን ጉዳዩ ሌላ ነው።

አያችሁ! ከቀዶ ህክምናው በኋላ የማይክን አይን የሸፈኑ ሻሾች ሲፈቱ አይኑ የሚያጥበረብር ብርሃን ገጠመው። ማይክ ግራ ተጋባ። ማየት ቢችልም፣ ማየት አይችልም ነበር።

የተፈጠረውን ጉዳይ አብረን እንይ። እንግዲህ አይን እንደ ካሜራ አይደለም። ለማየት አይን ብቻውን በቂ አይደለም። ያየነውን ነገር ፕሮሰስ አድርጎ የሚረዳ አእምሮ ያስፈልጋል። ማይክ በሶስት አመቱ ሲታወር፣ አእምሮው ውስጥ ምስልን ፕሮሰስ የሚያደርግ አካል፣ የድምጽና ሌሎች የስሜት ህዋሳቶችን ፕሮሰስ ወደማድረግ ተሻገረ። ከዚህ የምንረዳው የአእምሮን ዳይናሚክ ባህሪ ወይም ተለዋዋጭነት ነው። አእምሮ ረግቶ ፓሲቭ ሆኖ አይቀመጥም። ራሱን ከተለዋዋጭ ሁኔታ ጋር ያዛምዳል። ለማየት አእምሮ ውስጥ በቢሊየን የሚቆጠሩ ኒውሮኖች ይሳተፋሉ። በማይክ ኬዝ እነዚህ ኒውሮኖች ለ40 አመታት ስራ ሳይፈቱ የማይክን ሌሎች ስሜቶች(መስማት፣ መዳሰስ) ሲያግዙ ኖረዋል።



አንድ ቀን ከሳንፍራንሲስኮ ተነስቶ በጀልባ ወደ ዝነኛው ደሴት አልካትራዝ አመራ። አልካትራዝ ላይ በውሃ የተከበበ እስርቤት አለ። የሚሄደው ጉድጓድ ውስጥ ያለ እስረኛ ለመጎብኘት ነው። አንድ ሰው በአለም ወንጀል ሲሰራ ወደ አልካትራዝ ይላካል፤ አልካትራዝ ውስጥ ደግሞ ወንጀል ሲሰራ ወደ ጉድጓድ ይላካል።

ጉድጓዱ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ ነው። ምንም ነገር መስማት አይቻልም፤ ምንም ነገር ማየት አይቻልም። ነገር ግን ጉድጓዱ ውስጥ የታሰሩ ሰዎች የገጠማቸውን ሲናገሩ ስለ አእምሮ አስደናቂ ጠባይ ተገኘ። እንግዲህ እስረኞቹ በዚህ ጉድጓድ ውስጥ አይናቸውም ከማየት፣ ጆሮዋቸውም ከመስማት ቦዘነ። አእምሯቸው ግን ከውጪ ሌላ አለም እንዳለ አልረሳም። እና በዚህ አይንን ቢወጉ በማይታይበት ጨለማ፣ እስረኞቹ አእምሯቸው የፈጠረውን ምስል ማየት ቻሉ። ታዲያ ያዩት ህልም አይደለም። በእውናቸው ነው። ኒውሮሳይንስም ይደግፋቸዋል።

ኒውሮሳይንስ ምንድነው የሚለው? አእምሮ የምናየውን ነገር ምስል የሚፈጥረው ገና ነገሩን ሳናየው ነው። እስረኞቹ ጨለማ ክፍል ውስጥ ለቀናት ሲያሳልፉ ምስል ማየት የቻሉት በዚህ የአእምሮ ጠባይ የተነሳ ነው። እስረኞቹ ምንም ነገር ባያዩም እንኳን፣ አእምሯቸው የራሱን ስራ ሰርቶ በግምት የሚያቀብላቸው ምስል አለ። ከአለም ብትነጠልም፣ ትእይንቱ ይቀጥላል። ደግሞም ጉድጓድ ውስጥ ሳንታሰር ሁላችንም ይህንን ልምምድ ዘወትር ማታ እንለማመደዋለን። እንቅልፋችንን ተኝተን ብዙ ነገር ስንሰማ፣ ብዙ ነገር ስናይ እናድራለን—ይህንንም አጋጣሚ ህልም ብለን እንጠራዋለን። ደግሞም በህልም የምናየውን በምናይበት ሰአት፣ እውነትነቱን ምንም አንጠራጠርም። ከነቃን በኋላ ነው ህልም መሆኑን የምናውቀው። በወቅቱ አይናችንም እያየ፣ ጆሯችንም እየሰማ አይደለም። አእምሯችን ግን በራሱ ሞዴል የምናየውን፣ የምንሰማውን እየፈጠረልን ነበር። የአእምሮ ነገር እጅግ አስደናቂ ነው።



ከቀደመው ነጥብ እንደምንረዳው የምናየው በአይናችን አይደለም። በአእምሯችን ነው። የአይናችን ተግባር አእምሯችንን መርዳት ነው። እንዴት ነው የሚረዳው? አይን ከአካባቢው የምስል መረጃ የሚሰበሰብ አካል ነው። ነገር ግን የምናየው ይህንን የተሰበሰበ መረጃ አይደለም። አይናችን ምንም አይነት መረጃ ከመሰብሱ በፊት አእምሯችን የምናየውን መገመት ይጀምራል። የሚገምተው ከልምዳችን፣ ከሜሞሪ ወዘተ ተነስቶ ነው። አእምሯችን የገመተውን በአይን ከተቀበለው ጋር ያወዳድርና ስህተቱን አስቀርቶ ለቪዥዋል ኮርቴክስ ይልክለትና እናያለን።

ታዲያ የምናየውን ነገር ሁሉ አናይም። ይህንን እውነት ከኒውሮሳይንቲስቶች በፊት አስማተኞኝ ያውቁታል። በዚህ እውቀት ነው በእይታዎቻችን መካከል ባለ ቅጽበት፣ አስማተኞች አስማታቸውን የሚሰሩት—እያየን የማናየው ስላለ።

ግን አንድ ጉዳይ አለ። አእምሯችን ለምንድነው ሁሉንም የማያየው? ለምን ስህተት ይሰራል? አያችሁ! ሰውነታችን ከሚጠቀመው ኢነርጂ 20%ቱን የሚጠቀመው አእምሮ ነው። ታዲያ ይሄን ኢነርጂ በብቃት ለመጠቀም መቆጠብ አለበት። ስለዚህ ለቁጠባ ሲባል፣ አእምሮ እያጠጋጋ ይገምታል እንጂ፣ ፍጹም ልክ የሆነ ምስል አያሳየንም። ለምሳሌ ብዙ የመኪና አደጋዎች የሚደርሰት ሾፌሩ በአይኑ እያየ፣ በአእምሮው ሳያይ ሲቀር ነው።



ቀለም መሰረታዊ የአለም ተፈጥሮ ይመስለናል። የሚገኘው ግን በአእምሯችን ብቻ ነው። አለም ቀለም አልባ ናት።

ሌላው ጉዳይ አይናችን ማየት የሚችለው ውሱን ዌቭሌንግዝ ነው—ከአጠቃላይ የዌቭሌንግዝ ውሰጥ 1/10,000,000,000,000 ብቻ። ስለዚህ በዙሪያችን ያሉ ብዙ የማናያቸው ነገሮች አሉ፦ ለምሳሌ ጋማ ዌቭ፣ ሬዲዮ ዌቭ፣ ማይክሮ ዌቭ፣ ኤክስ ሬይ ወዘተ።
Жойылды17.04.202521:19
12.04.202515:45
23.04.202517:56
የመጨረሻው ክፍል

እሷ ደንግጣ ፊቷ ሲቀላ ሮቤል ድክም ብሎ እየሳቀ ነው "ማለት ሊያስቃት እንደሚችል ሊያሳየኝ ነው?! ወይስ ምን እያደረገ ነው?!" እያልኩ ደምስሬ ሲገታተር ይሰማኛል። 'በሰላም የተኛሁትን ሰውዬ ቀስቅሶ ጠርቶ መበጥበጥ ምንድነው' ብዬ ስበሰጫጭ ቦርሳዋን ይዛ ስትወጣ አየኋት

እሱን ሳየው ግራ ገብቶት ከጓደኛዋ ጋር ስሟን ይጣራል እሷን ሳያት ስታየኝ ተገጣጠምን። በአይን ይለመናል?? በአይኔ ለመንኳት በአይኗ እምቢ አለቺኝ

ምን ብሏት ነው የሚል እልህ አነቀኝ። የከበቡኝን ሴቶች ገለል አድርጌ ሮቤል ጋር ሄድኩ። "ደሞ አንተ ምን ሆንክ" አለኝ ንዴቴን ሳልነገረው አውቆ "ምን ሆና ነው የወጣችው ምን አድርገሀት ነው የሄደችው"

"ምንም አላልኳትም ግን በሰበቡ ልታወራት ከፈለክ በእግሯ ስለሆነ የምትሄደው ብትሮጥ ትደርስባታለህ" አለኝ እየሳቀ አይ ሮቤል አሁን እኔ የእሱ ነገር ጠፍቶኝ በሱ መናደዴ እሱ እዚህ ይስቃል

"ጫማዋ ስለማያስኬዳት ባትሮጥም ትደርስባታለህ" አለች ጓደኛዋ

እውነትም እንዳሉት ብዙም ሳትርቅ ጫማዋን ለመፍታት ስትታገል አየኋት

እየሮጥኩ ሄጄ እግሯ ስር ተገኘሁ "ለመፍታት አስቸግሮሽ ከሆነ ልፍታልሽ" ብዬ እግሯ ስር ተንበረከኩ ዝም ብላ አየቺኝ እየፈታሁት

"ሮቤል ምንድነው ያለሽ" አልኳት ጫማዋን አውልቄ ባዶ እግሯን ቆማ እኔ በተንበረከኩበት
"ኧረ ቢያንስ ከተንበረከክበት ተነስ" አለች ፊቷ በደማቁ እየቀላ ድምጿም ሀምራዊ ነው

ስቆም አሁን ደግሞ ወደላይ አየቺኝ ቁመት በትንሹ እበልጣታለሁ አይኖቿ ያሳዝናሉ

"ንገሪኛ ምን ብሎሽ ነው" አልኳት

"ስምህ ኤርሚያስ መሆኑን ነግሮኝ ነው" ብላ ፊቷን ሸፈነችው

እንዳየቺኝ ሮቤል አውቆ ነበር?! ሮቤል ስላወቀባት አፍራ ነው የወጣችው?! ልቤ ደስታ ፈሰሰበት

"በቃ ይኸው ነው? የወጣሽው ለዚህ ብቻ አይደለም አይኖችሽ ሌላም ነገር ነግረውኛል እስክረዳሽ ግዜ አልሰጠሺኝም ንገሪኝ መጥቼ እስካወራሽ ለምን ቸኮልሽ ንገሪኝ" ብዬ እጆቿን ከፊቷ ላይ አነሳኋቸው

አምጣ አምጣ ቆይታ "መጎዳት ደክሞኛል"

እስካሁን ያዘነላት ልቤ አሁን እጥፉን አዘነላት

"ሰዓሊ እሱ ሲጎዳ እንጂ ሌሎችን ሲጎዳ ሰምተሽ ታውቂያለሽ?!"  አልኳት መልሷን አልጠበኩም እቅፌ ውስጥ ከተትኳት እንደዚህ መቀራረብ እንድትፈራ ያደረጓትን ሰዎች እየረገምኩ ልጠብቃት ቃል ገባሁ

ቃሌንም ጠበቅኩ

ሞት እሷን ከእኔ እስኪነጥቃት መከዳትን አስረሳኋት የሚገባትን ፍቅር በምችለው ጥግ ደረስ ሰጠኋት አላሳፈረቺኝም እንደውም ህይወቴን አደመቀችው

እድሜ ለሮቤል


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
Қайта жіберілді:
Event Addis Media avatar
Event Addis Media
23.04.202504:52
📌ዛሬ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን ነው!

የዓለም መጽሐፍ ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 15 ይከበራል

ሚያዝያ 15 ለዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀንነት የተመረጠበት ምክንያት የዊልያም ሼክስፒር እና ስፔናዊው የታሪክ ጸሐፊ ኢንካ ጋርሲላሶ ዴ ላ ቬጋ የሞቱበት ቀን በመሆኑ እንደመታሰቢያ እንዲሆን ነው።

በእዚህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በተለይ ወላጆች ለልጆቻቸው መጻሕፍትን በስጦታ መልክ በመስጠት ያከብሩታል።

የቀኑም ትልቁ ዓላማ የንባብ በዓል ማዳበረ ነው።

#Worldbookday!

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
Қайта жіберілді:
ጥርኝ ጥበብ avatar
ጥርኝ ጥበብ
18.04.202508:46
እኛ ያመጣናቸው እነርሱ በለጡን

እየጎተንት ወደ ቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ይዘነው ገባን።የገዛንለትን ነጠላ ዘርግቶ ለመልበስ ግራ ሲጋባ ከሶስታችን መሀከል አንድኛው ተጠግቶ በአንገቱ ስል አመሳቅሎ አጣፋለትና  
"እንዲህ አይሰገድም እሽ
        እሽ
ምግብስ በልተሀል
   ኧረ አልበላሁም
አዎ ምን ሆነሀላ ውሀ ራሱ ከጠጣህ ነገር ተበላሽቷል በቃ
    አይ እንደዚያ አላደረኩም"     ይቁነጠነጣል...በመሀል 1000 ሰግደን ለመውጣት የምንገፋፋው እኛ ቆመን ሳለ እርሱ ስድስት ሰባት ጊዜ ከፍ ዝቅ ብሎ ጉልበቱ እንደተብረከረከ ሰው በግንባሩ መሬቱን ተደግፎት ቀረ። እንግድህ ላለመነሳት ምክንያት እየፈጠረ መሆኑ ነው ቀና ማለት እንደከበደው ሰው ቁና ቁና ሲተነፍስ ይሰማናል።...

"ቃል እንደጓደኛ ይሄንን ልጅ ምንም መላ አናበጅለትም ማለት ነው"አለ ቢታንያ ወደ አንገቴ ተጠግቶ ... እኔ ደግሞ የአናንያን ህይወት እየሄደ ካለበት ቁልቁለት ለመመለስ መሞከር ውሀን ሽቅብ የማፍሰስ ያህል ድካሙ ብቻ ነው የሚታየኝ።  ለጓደኛ በዚህ ልክ
መጠን ዝሎ መኖር ቢያሳፍርም...  "ሱስ እኮ ነው እየበዛ በጣም ብሶበታል የት እናስጠምቀው በእናትህ"  የየግል አስተያየታችንን ለጣጥፈን ስናበቃ ካጎነበሰበት በርከክ ብሎ አንገቱን ደፍቶ ነጠላውን አናቱ ላይ ጎዝጉዞ ተቀመጠ።

ለካ መቆም ቢያፍር ነው እንባ አርግዞ የወደቀው ድንገት ቀና ሲል ደንግጠን ተያየን በስጋው ላይ እንደተቆጣ የሚያሳብቁት የደም ስሮች ከወደግንባሩ እንድህ ተከታትለው ለመሰለፍ ምን አነቃቃቸው ከምኔው ፊቱ በእምባ ረጠበ አያስቀናም ልታፀድቁ በገሰፃችሁት ሰው ተሰብካችሁ እንደመሄድ ያለ ስብከት ወደየት ይገኛል።

የእኛ ፀፀት አርባአንድ ኪራላይሶን ብለን ከአይናችን ካልወረደ ለእርሱ በሰባት ዝቅ ማለት በዘነበለት እምባ እንዴት አይቀናም አምላኩ በልቡ አደባባይ በታተመለት ሰው ቁኑ ሀቁም ይሄው ነው።

በልምድ መመላለስ የፀና ሐዋርያም አንዳንድ ጊዜ ሊያፀድቅ ይዞ ከመጣው ወንበዴ ተምሮ ይሄዳል።...

ወዮ የሠው ስግደት ቆጥረን ለተመለስን 😢😢😢

ፀሀፊ ✍ ጌታሁን ደጉ

እንኳን አደረሳችሁ
Жойылды17.04.202521:19
Қайта жіберілді:
ባይራ |Bayra avatar
ባይራ |Bayra
14.04.202520:35
የሰኞ ማታ ግብዣ

የማላቅፍህ ስለምሰስትህ ነው……….።
 
ከማሰሮ የዘገንከውን ትኩስ እፍኝ አሹቅ ወደ አፍህስታስጠጋው፣ አፍህ እዚህ የከንፈርህ ጥጋት ጋር ስታደርሰው፣ ብርር'ድ ብሎብህ ያውቃል? ወይ ደሞ መንገድ ላይለማታውቀው ሰው በፈገግታ ሰላምታ ሰጥተህ ስታልፍፈገግታህ በስንት ሰከንድ ይከስማል?

የእግርህን አውራ ጣትየመታህ ትንሽ እንቅፋት ልብ ስር የሚገባ ህመም በስንት ደቂቃበረደልህ? የጣቶችህን አንጓዎች እያጠፍህ 'ቋ' ለማድረግየፈጀብህን ቅፅበት በቁጥር ታውቀዋለህ?

በህልምህ ያየኸውውብ ዓለም ልክ ዓይንህን ስትከፍት ለመጥፋት ከብርሃንይፈጥን አይደል? ልክ እንደዛ ፣ ልክ እንደ ሁሉም ፍቅርይበርድብኛል።

በእጄ ሳልይዘው ይሰበርብኛል። ምን ላድርግ?
...
“ዘንድሮ ፍቅር የለም!” እያሉ በራሳቸው የፍርሃት ድንበርውስጥ እንዳሉት ሰዎች አይደለሁም። ሰው የተባለ ፍጡርበህይወት እስካለ ድረስ ፍቅር የትም አለ።

አይታየንም እንጂያያዘን ቀጭን መሳይ ጠንካራ ድር ፍቅር ነው። አለ ብዬአምኜው እየኖርኹ ታዲያ ስይዘው ለምን ጥብቅ አያደርገኝም? ስዳስሰው ቁንጥጫው የሚብሰው ለምንድን ነው? ስስመውለምን ጥርሱን ያገጣል? መጣ ብዬ “እሰይ! እሰይ! ከመጣህማርያም ታምጣህ!” ብዬ፣ ከንፈሬ ከማሰሪያው ተፈቶ ፈገግሳልል ወዴት ሄዶ ይጠፋብኛል? እንደ ማድጋ ሊጥ፣ ተሟጦእንደሚጋገር፣ አሟጦ የሚያፈቅረኝ የት ነው?
...
ሁላችንም፣ እኔም  አንተም ሳንዘጋው የተውነው የትዝታ በርአለን። በቀጭን የምትነፍስ ትላንትን የምትናፍቅ ንፋስየሚያሳልፍ በር አለን።

አሁን ቁጭ ብዬ ሳስበው አጠገቤየነበሩ፣  ያፈቀርኳቸው ፤ ያቀፍኝ ፤ ሳናይሽ አናድርም ልመናዎችሁሉ የትዝታቸውን በር መሸጎሪያ እንጂ በእያንዳንዳቸው ልብውስጥ የራሴ የትዝታ በር የለኝም። ታዲያ ይሄ አያደክምም?
...
በዓለም ያንተን አይነት ፈገግታ ያለው አይቼ አላውቅም። ፈገግስትል ፊትህ ላይ ያለውን ኃይል አልችለውም። እወድሻለሁስትለኝ እያንዳንዷን ፊደል ሰንጥሬ ባያት ምንም ማብለጭለጫቅመም እንዳልተጨመረበት አውቃለሁ።

ፊቴ ስትመጣየዋህነትን ብቻ ትሰዋልኛለህ። ደስ ትለኛለህ። ዓይኔን ከድኜእጄን ልሰጥህ እፈልጋለሁ። ታዲያ ግን እፈራለሁ። ፍርሃቴንአሸንፌ ባቅፍህ በማግስቱ ትተወኛለህ።

አነሳሴ ጋ አውግተንሳንጨርስ ወድቄ  እነቃለሁ። እንዲሁ ባይህ ይሻላል። እንዲሁበሩቅ ብመኝህ ይሻላል። ምኞቴን ሸሽጌ ፤ ምኞትህን ሸፍኜ እንደሩቅ ዘመድ ብንተያይ ይሻላል። ላጣህ ስለማልፈልግ ነውከጠረንህ አፍንጫዬን ያቀብኩት ፤ እቅፌን ያቀዘቀዝኩትዘላለም በልብህ እንድታቅፈኝ ነዉ። የ40 ቀን እድሌ ትለኝ ነበርአያቴ።

ያኔ ታዲያ እስቅ ነበር። 40 እና እድል ምን እንዳቆራኛቸዉይደንቀኝ ነበር። አሁን በየቀኑ ሳይገባኝ አልቀረም። የ40 ቀንእድል አለን ሁላችንም። በማይታይ ማተብ አንገታችን ላይ ያለ።
 
እና ትወደኛለህ?
 
🎼
ተራራው ሰው፣ ሆኖ ከንፈሬን ባይስመኝ
ተራራው ሰው ሆኖ፣ ጡቴን ባይዳብሠው
ተራራው ሰው ሆኖ፣ ዓይን ዓይኑን ባላይ
ጸሀይ እሞቃለሁ፣ ወጥቼ ከላይ።
.
.
... መናፈቅ ዝም ብሎ ከገላ ላይ የሚጨልፍ ምትሀት ነገርአለው። ማሸጊያው ሳይፈታ ቁጫጭ በልቶት እንደሚያልቅከረሜላ እንደዛ ባሉበት ይጨርሳል። ልብን መነሻና፣ መድረሻአድርጎ ይመላለሳል።

ሲናፍቁ ዓይንን ቢከድኑት ማምለጥ ዘበትይሆናል። እግርን እንዲራመድ ቢያዙት የጉዞው መድረሻውሳይታወቅ ካሉበት ፈቀቅ ሳይሉ መጫሚያ ያልቃል። ጆሮ ጥኡምሙዚቃ ቢሰጡት የእሱን ሹክሹክታ ያመጣል። መሃላን ያስረሳናስለትን ያስመኛል።
 
... ከናፍቆት ጋር ድብብቆሽ መጫወት ስጀምር፣ ልክእንደማንኛዉም ተጫዋች ተናፋቂው ተደብቆ ሲቀርጨዋታዬን አቆማለሁ ብዬ ነበር። የመፈለግ ፅናቴ ተሰብሮወይም ሟሙቶ ያለቀ መስሎኝ ነበር።እንደዚህ የተደበቀበትንጋራና ሰርጣሰርጥ ሁሉ በልቤ አስሳለሁ ብዬ አልነበረም።

ልቤኩስ ኩስ ብላ ከእግሬ ስር እየተራመደች የምትመራኝናየምታወራኝ ይመስለኛል። እንዴ እሱም ጋር እኔም ጋር ልቤልትኖር አትችልም። ሲፈቀር ልብ ይሰ'ጣል ይሉ የለ እንዴ? ታዲያየኔ ልብ ይቺት ከፊቴ። ፍቅር ሳይሆን እልህ ነው እንዴ የያዘኝ? የጨዋታ አሸናፊ አለመሆኔ ተሰምቶኝ ነዉ እንዴ? እያልኩአስባለሁ።
" ሰማሽኝ እቴ አካልሽ ሁሉም እዚህ ነው።  ሀሳብሽ ፤ ህልምሽ ፤እርካታ እና ስሜትሽ ሁሉም ሰዋዊ ስሜቶችሽ ናቸው እሱ ጋርየተደበቁብሽ።

ሰው ሲያፈቅር ሰውነቱን ፣ ሰው የመሆኛ፣ ሰውየመባያ ነገሮቹን ነው አሳልፎ ለሚያፈቅረው የሚሰጠው።

አብሬሽ ያለሁት ልብ ተብዬ እንድጠራ የሚያደርጉ ስሜቶቼንስለወሰደብኝ ነው።" አለች ኩስ ኩስ እያለች።
 
... ለነገሩ ልክ ናት እላለሁ። ምን ታልሚያለሽ ቢሉኝ ከንፈሩ ስርየማርያም ስሞሹ መሆን አይደል? ምን ታስቢያለሽ ቢሉኝ ንፋስየራሱን ፀጉር ስንቴ ዳበሰችው? ጨረቃ ለምን አዘቅዝቃታየዋለች? እንቅፋት መቶት ይሆን? አንዷ ቁሌታም ስታልፍአይታ ተመኝታው ይሆን? አንድ ጤነኛ ሰው እንዲህ ያስባል?
 
...አስቀድሰው ሲጨርሱ እንደሚሰጥ ቁራሽ፤ቤቱ ቢሄድምየሚበላ እንደሌለው ሰው ያቺን ቁራሽ እንደሚያጣጥማት(እንደዛ ናፍቆቱ ይጣፍጠኛል) ፤ የመጨረሻ የጎለተችው ድንችተሸጦላት ለልጆቿ ራት መግዛት እንደምትፈልግ እናት ገዢንበጉጉት እንደሚጠብቁ ዓይኖቿ (እንደዛ በየቀኑ ለፍቅሩእጓጓለሁ ) ፤ ረጅም ዓመት በደዌ ተሰቃይቶ ጎኖቹ ሁሉ በቁስልነደው መተኛት እንደናፈቀው ፣ፈውስ መጣልህ፣ ጎንህ አገገመተብሎ የነገ ፈውሱን አስቦ እንደሚጋደም ጎልማሳ (ልክ እንደዛየፍቅር እፎይታን እናፍቃለሁ)።

... ዓይኔን አልነግረውም። ፍቅርህ ላይመጣ ይችላል ብዬአልነግረውም።  በሩቁ እያየነው እንደምንኖር አልነግረውም።ጉጉቱን አውቃለሁና ቢጠብቅ ይሻላል።

እጄን "ደረቱን አትዳብስም ፤ አንገቱ ዙሪያም ላትሆን ትችላለህእኮ" ብዬ እንዴት ላስረዳው?
እግሮቼን "ወዳለበት አትሄዱም፣ ቁሙ!!" ማለት አልችልም።

ከእግሬ ቀድሞ የእርምጃ ሀሳቤ የት እንደሚሄዱ ይነግራቸዋል።
ማንንም ማዘዝ አልቻልኩም። ሀሳቤን ፤ ህልሜን ፤ ዓለሜንሰጥቼ ነዋ የወደድኩት። ግን ትወደኛለህ?
 
 ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 1 የተወሰደ

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
Жойылды17.04.202521:19
10.04.202518:46
የኢትዮጵያ ሕዝብ ግንባሩ አንድ በሆነና...
*
የአንዳንድ ሰው ዕጣ ያሳዝናል፡፡ በቅርቡ ‹ለከበደ ሚካኤል ጎረቤታቸው ነበርኩ፤ የሚገንዛቸው ጠፍቶ እኔ ነኝ የገነዝኳቸው› ካለኝ ጨርቁን የጣለ ዱርዬ ጋር እያወራሁ ነበር፡፡ ከበደ ሚካኤል በንጉሡ ዘመን እንደ ተርቲመኛ ቤተመንግስት የሚመላለሱ፣ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሽልማት ድርጀት የሥነፅሁፍ ተሸላሚ በብዙዎች የሚደነቁ ነበሩ፡፡ ደርግ መጣና ቤታቸውን ወርሶ አጎሳቆላቸው፡፡ 17 ዓመቷን ሙሉ የወዳጅ ሆቴል ክፍል ተጠግተው ተወጧት፡፡ ኢህአዴግ ሲገባ ቤታቸውን ቢመልስም ዝናቸው ግን እየደበዘዘ ሄደ፡፡ ከበደ ዘመን መቀየሩን፣ የፊውዳል ሕብረተሰብ በአንድ አዳር መጤውን አውሮፓዊ ቴክኖሎጂ ሰራሽ ‹ፖፕ ከልቸር› መላበስ መቋመጡን ያወቁት አይመስልም፡፡ እና አንድ ቀን አንድ ወዳጃቸውን ጠየቁ...
"ከተማው ስለኛ ምን ያወራል?"
"ምንም አያወራም፡፡ እረስቶዎታል።" ቢላቸው...
ከበደ በቁጭት
"ምናለ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግንባሩ አንድ በሆነና በፈነከትኩት" አሉ ይባላል፡፡ (ግንባሩ አንድ በሆነ - የእርሳቸው ቃል ለአደባባይ ጸያፍ ብትሆንብኝ መንፈሱን በከፊል ለመግለጽ የተካኋት ናት፡፡)

የኢትዮጵያ ሕዝብ ‹ሾርት ሜሞሪ› መሆኑን የሚያውቀው አብይ አህመድ ብቻ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚያ ተማሪ በጎች መሆኑን ምናውቀው ግን እኔና እግዜር ብቻ ሳንሆን አንቀርም፡፡ ከበደ ሚካኤልም አያውቁ ይሆናል፡፡
በአንድ የገጠር ትምህርት ቤት የሚያስተምር የሒሳብ መምህር አንድ ቀን ከተማሪዎቹ መካከል በትርፍ ጊዜው በጎችን የሚያግድ ታዳጊ ልጅ ቀርቦ ጠየቀ፡፡ 

‹‹ልጅ በበጎችህ ማደሪያ ውስጥ አስር በጎች አሉህ እንበል፡፡ ከአስሩ በጎችህ አምስቱ ከማደሪያቸው ዘለው ቢወጡ በበጎቹ በረት ምን ያህል በጎች ይቀራሉ?››

‹‹ምንም!››
መምህሩ ተገርሞ ‹‹ያልኩህ አልገባህም፡፡ አስር በጎች አሉህ፡፡ አምስቱ ከበረቱ ዘለው ቢወጡ በበረቱ ውስጥ ስንት በጎች ይቀራሉ?››

‹‹ምንም!›› አሁንም ተማሪው ተመሳሳዩን መልስ ሰጠ፡፡
መምህሩ በብስጭት ‹‹እንዴት ይሄን መቀነስ ያቅትሃል?››
ተማሪው ሲመልስ
‹‹መምህር ሂሳቡን መቀነሱን አንተ ልታውቅበት ትችላለህ፡፡ የበጎቼን ጸባይ የማውቀው ግን እኔ ነኝ፡፡ እንኳን አምስቱ አንዲቷን ብቻዋን ዘላ ከወጣች ሁሉም ይከተሏታል እንጂ ሞት ቢመጣ በረት ውስጥ አይቀሩም፡፡››

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚህ ተማሪ በጎች ይመስለኛል፡፡  አስርሺዎችን ማሳመኑ ከሆነልህ ሚሊዮኑ ያንተ ነው፡፡ ሚሊዮኑ አዝማሚያውን አይቶ ነገር ወደቀናው ተጠግቶ ለማደር ተሰልፎ የሚጠብቅ ‹ቁጥር› ነዋ፡፡ አንዳንዱ የሚያደንቅህ በስማ በለው ነው፡፡ እንጂ የነፍስ መቃተት ሀቀኝነት ተሰምቶት አይደለም፡፡ በሌላ ቀን እንዲሁ ፌቡ ላይ የአሉ ወሬ ለቃቅሞ ጥንብ እርኩስህን ያወጣዋል፡፡ የላመ የጣመ በማንኪያ መዋጥ የለመደ አዕምሮ መጠየቅ አይወድማ፡፡ የተማረው ያልተማረው፣ የሚያነበው የማያነበው... ብዙው ቀለም የሌለው ስርዝ ድልዝ ነገር አለው፡፡ እውነት ይፈውሳል አይደል? ስለምን ይሸፋፈናል? እውነት ምኑ ይቀባባል?

እኔ ግን ሀገርን፣ ትውልድን፣ ዘመንንና ግለሰብን እንደምን ታውቀዋለህ? እንደምንስ ትመዝነዋለህ ብትለኝ በጀግኖቹ እልሃለሁ፡፡ የዚህን ዘመን፣ የዚህን ትውልድ ጀግኖች ብንጠይቅ ስንት አምታታው ማኛ አክቲቪስት፣ ጯሂ ታዛቢ ነኝ ባይ፣ ዩቱበር፣ ቲክቶከር ይጠራልን ይሆን? ለመሆኑ አንድን ሰው የምናደንቀው ሰውየው የሚደነቅ ስለሆነ ወይስ ሌሎች ስላደነቁት?

ጥቂት ቀልብ ገዝቻለሁ በሚለው ወገን ስንኳ የአስተሳሰብ ዝንፈት ሥር ሰዶ አንዳንድ pseudo intellectuals የትውልዱን ሁሉ ዳፋ ተሸክመው የሚሻግሩ ተደርገው ሲንቆንጳጰሱ ትመለከታለህ፡፡ ብዙው ነገር እንደተንጋደደ ግልጽ ነው፡፡ 

የትኛውንም ኅብረተሰብ ንቃት ለመመዘን ወንዞቹን አትዩ፡፡ መንገዶች፣ ግድቦች፣ አደባባዮች፣ ድልድዮችም... በችሮታ ሲገነቡ አይተናል፡፡  ይልቁንስ የየትኛውንም ኅብረተሰብ የንቃት ደረጃ የሚበየነው አሰላሳዮቹን (thinkers) የሚይዝበት መንገድ ነው፡፡ ኅብረተሰብ አሰላሳዮቹን በሚይዝበት አኳኋን በዚያ የየንቃት ደረጃው (collective consciousness) ይመዝናል፡፡ ማኅበረሰብ አሰላሳዮቹን በሚይዝበት መንገድ የወደፊት ዕጣው - የባርነት ወይስ የአርነት - የሚለውን መገምገም ቀላል ነው፡፡

ከያዕቆብ ብርሃኑ የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

@zephilosophy
Көрсетілген 1 - 24 арасынан 282
Көбірек мүмкіндіктерді ашу үшін кіріңіз.