Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች avatar

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ
እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው።
ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc & @Kiya988
Buy ads: https://telega.io/c/amazing_fact_433
TGlist рейтингі
0
0
ТүріҚоғамдық
Растау
Расталмаған
Сенімділік
Сенімсіз
Орналасқан жеріЕфіопія
ТілБасқа
Канал құрылған күніFeb 06, 2025
TGlist-ке қосылған күні
Aug 10, 2024
Қосылған топ

"4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች" тобындағы соңғы жазбалар

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ማን ናቸው?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ 1 ሺህ 300 በሚጠጉ ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ከአውሮፓ ውጭ ያሉ የቫቲካን መንበር የበላይ ጠባቂ ናቸው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትሁት፣ ወደፊት የሚመለከቱ፣ የሞት ቅጣት እና የሴቶች ሚና የመሳሰሉ ማኅበራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምትከተለውን ቀኖና ለማቅለል ጥረት ያደረጉ እንደሆነም ይነገርላቸዋል።

በዛሬው ዕለት 88 ዓመታቸው ቫቲካን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ያረፉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እ.አ.አ ታኅሣሥ 17 ቀን 1936 ፍሎረስ ቡኖስ አይረስ፣ አርጀንቲና ውስጥ ነበር የተወለዱት።

የሕይወት ጉዞአቸው....

እ.አ.አ በ1958 በ21 ዓመታቸው ወደ ኢየሱሳውያን ማኅበር (ጀስዊቶች) ተቀላቀሉ

በ1969 የካቶሊክ ቄስ ሆነው ተሾሙ

አርጀንቲና በሚገኘው የኢየሱሳውያን ኮሌጆች ሃይማኖታዊ ትምህርት እና ሥነ ጽሑፍ አስተምረዋል፤

ከ1973 እስከ 1979 በአርጀንቲና የሚገኘው የኢየሱሳውያን ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሆነው ሠርዋል፤

በአርጀንቲና ወታደራዊ አምባገነናዊ አገዛዝ ወቅት ጠንካራ መንፈሳዊ አቋም በመውሰድ አገዛዙን በመቃወም ይታወቃሉ፤

በ1992 የቦነስ አይረስ ረዳት ጳጳስ ሆነው ተሾሙ፤

በ1998 ካርዲናል ኳራሲኖ ሕልፈት በኋላ የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ ሆኑ

በቀለል ያለ አኗኗራቸው የሚታወቁት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፣ ቀለል ባለ አለባበስ፣ ለትራንስፖርት የሕዝብ መጓጓዣዎችን እንዲሁም ለመኖሪያ አነስተኛ የሆኑ አፓርታማዎችን ይጠቀሙ ነበር፤

በ2001 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዳግማዊ ጆን ፖል ወደ ካርዲናልነት ከፍ አደረጉአቸው፤

በማኅበራዊ ፍትሕ ረገድ ለድሆች እና ችግረኞች ጥብቅና በመቆም መልካም ስምን አትርፈዋል፤

መጋቢት 13 ቀን 2013 266ኛውን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመርጠዋል፤

የአየር ንብረት እንቅስቃሴን እና በሃይማኖቶች መካከል ንግግር እንዲኖር በማበረታታት ይታወቃሉ፤

በቫቲካን እና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሃድሶ እንቅስቃሴ እንዲካሄድ ያበረታታሉ፤

በአየር ንብረት እና አከባቢ፣ በወንድማማችነት እና በማህበራዊ ወዳጅነት እንዲሁም በቤተሰብ ፍቅር ላይ ያተኮሩ ሦስት መጽሐፍትን አሳትመዋል፤

ስፓኒሽ፣ በጣሊያንኛ እና ላቲን ቋንቋዎችን አቀላጥፈው ይናገራሉ፤

• ለእግር ኳስ፣ ለታንጎ እና ለሥነ ጽሑፍ ጥልቅ ፍቅር አላቸው


(EBC)

🌐@Amazing_fact_433
🌐@Amazing_fact_433
ለ10 ዓመታት ቆጥቦ የገዛው አዲስ ‘ፌራሪ’ መኪና በ1 ሰዓት ውስጥ ነደደበት
*

ወጣቱ ጃፓናዊ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር ሆንኮን ለ10 ዓመታት ቆጥቦ ሕልሙ የነበረውን ‘ፌራሪ 458 ስፓይደር’ መኪና ከገዛ በኋላ ያሽከረክረው በጀመረ በ1 ሰዓት ውስጥ መኪናው ሲነድ ቁጭ ብሎ ተመልክቷል።

ሕልሙ የነበረውን እና የሚወደውን ፌራሪ መኪና በገዛበት በመጀመሪያው ቀን መንደዱ ብዙዎችን አሳዝኗል፤ ጉዳዩም መነጋገሪያም ሆኗል።

የ33 ዓመቱ ወጣት መኪናውን በገዛበት ዕለት በጃፓን፣ ቶኪዮ ውስጥ በሚገኝ በሹቶ ፈጣን መንገድ ላይ እየተደሰተ የነዳው ቢሆንም ደስታው አብሮት የቆየው ለደቂቃዎች ብቻ ነበር።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ዕለት ነበር ሆንኮን መኪናውን የተረከበው፤ መኪናውን እንደተረከበም ለሙከራ መንዳት ይጀምራል፤ በዚህ መሃል በውጭ በኩል ከጎኑ ጭስ ይመለከታል፤ ከሌላ መኪና የሚወጣ ይመስለውና ችላ ይለዋል።

አጠገቡ የነበረው መኪና ርቆ ቢሄድም ጭሱ ከጎኑ አልተወገደም፤ ይሄኔ እየጨሰ ያለው የራሱ አዲስ ፌራሪ መኪና መሆኑን ይጠረጥርና ዳር ይይዛል፤ እየነደደ ያለው በእርግጥም የእርሱ መኪና ነበር።

ስልክ አውጥቶ ለእሳት አደጋ ይደውላል፤ እሳት አደጋ እስኪደርስለት ከ20 ደቂቃ ያላነሰ ጊዜ ፈጅቷል፤ ይህ ሲሆን ምንም ማድረግ ያልቻለው ሆንኮን የገዛው አዲስ ፌራሪ መኪና ሙሉ በሙሉ ሲነድ ቁጭ ብሎ ለመመልከት ተገዷል።

ሆንኮን ከክስተቱ በኋላ በX ገጹ ላይ ባጋራው ጽሑፍ፥ "በጃፓን ውስጥ እንዲህ ዓይነት አስቀያሚ ክስተት የገጠመኝ እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኛል፤ 306 ሺህ ዶላር አውጥቼ ሳልመው የኖርኩትን አዲስ ፌራሪ መኪና ብገዛም ከ1 ሰዓት በኋላ ለማስተዛዘኛ የተረፈኝ ይህ ፎቶ ብቻ ነው" ሲል ከተቃጠለ መኪናው ፎቶ ምስል ጋር አያይዞ አስነብቧል።
ይህንን ያውቃሉ⁉️

በርካታ የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ስልክ ከሰዎች ጋር ስናወራ በተደጋጋሚ በቀኝ ጇሯችን መሆን የለበትም ምክንያቱም አእምሯችን ለቀኝ ጆሯችን ስለሚቀርብ ከስልኩ የሚመነጨው የማይታይ ጎጂ ጨረር አይምሮዋችንን ሊጎዳ ይችላል ... ስለዚህ ስልክ በምናዋራበት ሰአት በግራ ጆሯችን ቢሆን ተመራጭ እንደሆነ ይገልፃሉ 🤳🤳
አርሰናል በነበረበት ወቅት ጎል ባስቆጠረ ቁጥር ታዋቂ ሰዎች ይሞቱ ነበር።አሮን ራምሴ ትናንት የካርዲፍ አሰልጣኝ ሆኖ የተሾመ ሲሆን ዛሬ በማግስቱ የፖፕ ፍራንሲስ ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።መጥፎ እድል ወይስ አጋጣሚ?

(ሲዲ ስፖርት
)
"Today is a gift"
The Deepest Movie Quotes

@Films_433 @Films_433
ክፋትን እና ውሸትን በፊልም የሚያስውበው ባለሙያ (የታሪክ ገጽ)

በ Youtube ቻናላችንን ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/Nky1TY59bco?si=72xwOAO7V9ACw28g
ያልተማሩት የ60 አመት እናት ወደ ባንክ ጎራ ይላሉ። አንድ ወጣት የባንክ
ሰራተኛ እያስተናገዳቸዉ ነው።
ልጁ; ማዘር

እናት; አቤት

ልጁ; ኑ እዚህ ጋር ይፈርሙ

እናት; በጣታቸው እንደሚፈርሙ ሲነግሩት

ልጁ; በአካዉንታቸዉ ያለዉን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አይቶ በመገረም…

"እማማ ይህ ሁሉ ብር እያሎት እንዴት አልተማሩም?" ብሎ ድምፁን ከፍ
አድርጎ በኩራት ደረቱን ነፍቶ በተሽከርካሪዉ ወንበር ወዲህ ወዲያ እያለ
ሲጠይቃቸው።
እናት; ወጣቱን ልጅ በአንክሮ

ሲመለኩቱ ቆዩና…በተራቸዉ ድምፃቸውን ከፍ
አድርገው "አዬ ልጄ ተምረህም እኮ እየቆጠርክ ያለኸው የኔን ብር ነው…"
አሁንም እናት ዞር ዞር ብለዉ ዙሪያ ገባዉን አዩና "ማናጀሩን እየኸዉ?
ልበልጠዉ የምችለው በትንሽ አመታት ነው እሱም እንዳንተ ተምሯል

አሁንም ግን እየዉ ተወጥሮ ሰዎች ብር አመጡልኝ አላመጡልኝ ብሎ ተጨንቋል።
አንተም ካላሰብክበት እጣ ፋንታህ ይህ ነው። ተምረህ
ላልተማርነዉ ትሰራለህ።
ልጁ; ደነገጠና "ምንድነው ማስብበት?"

እናት; እኔ ባልማርም ጡረታ የወጣሁት በአንተ እድሜ እያለሁ ነው።
ተማርን ብለዉ የሚንቁትን ስራ እሰራ ነበር። ለዚህ ሁሉ ሚስጥር ደሞ ዝቅ
ብሎ መስራቴ ነው። ሀብታም የመሆንም ሚስጥር ኩራትን አሶግዶ ዝቅ
ብሎ መስራት ነው!!!!!

ወዳጄ መለወጥ ስኬታማ መሆን ከፈለክ የግድ መማር አይጠበቅብህም ምክንያቱም ከትምህርት ቤት ይልቅ ህይወት እጅግ ብዙ ብዙ ነገሮችን
ታስተምርሀለች።

ስለዚህ ከታሪኩ ላይ የምንማረው ሀብታም የመሆናችን
ሚስጥር ዝቅ ብሎ ጠንክሮ የመስራታችን ዉጤት መሆኑን ነው
አመሰግናለሁ።😎😎
የ20 አመቷ ወጣት ጃዝሚን ያለአባት የምታሰድገውን የአንድ አመት ልጇን በእቅፎ ይዛ ወደ አንድ አነስተኛ ሱፐር ማርኬት ትገባለች።

ወተት፣ የህፃን ልጅ ምግብ እና ዳቦ መግዛት ፈልጋ በቦርሳዋ ያለው አንድ ዶላር ብቻ ነው፣ ለመግዛት የፈለገችው ምግብ እና እሷ የያዘችው ገንዘ አይመጣጠንም፣ ገንዘቡ ያንሳል።

ወተት፣ የህፃን ልጅ ምግብ እና ዳቦ በመያዝ ወደ ባለቤቱ ጋር በመሄድ ቀስ ብላ ማንም ሳይሰማ እንዲህ አለችው።

ያላትን ገንዘብ እየሰጠችው "ያለችኝ እቺ ናት ቀሪውን ገንዘብ ነገ አመጣለሁ የያዝኩትን ልውሰድ " አለችው ።የሱፐር ማርኬቱ ባለቤት ከማዘን ይልቅ አሳቀቃት፣ አሸማቀቃት ፣ አዋረዳት።

የሱፐር ማርኬቱ ባለቤት፣ እየጮኸ ሌሎች ሰዎች እንዲሰሙ እያመናጨቃት እንዲህ በማለት ተናገራት ።

አንቺ እና መሰሎችሽ ሁልግዜ ምንም ሳይኖራቹ እዚህ እየመጣቹ የሆነ ነገር ማግኘት ትፈልጋላችሁ ፤ መክፈል የማትችይ ከሆነ ለመለመን ሁለተኛ እዚህ እንዳትመጪ"

ባለቤቱ ጃዝሚንን ሲናገራት ሰዎች ሁሉ ጃዝሚንን እንደጉድ ይመለከቷት ነበር፤ ጃዝሚን በሃፍረት ሰውነቷ ቀዘቀዘ፤ የአንድ አመት ልጇ ምን እንደተባለ የሰማ ይመስል እሪ ብሎ እየጮኸ አለቀሰ።

ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ማይክል ጆርዳን በሱፐር ማርኬቱ ውስጥ እቃ እየገዛ ነበረ። ባለቤቱ ጃዝሚንን ምን ሲላት እንደነበር ይሰማል።

ጆርዳን በልጅቷ መሸማቀቅ በጣም በማዘን ወደ ባለቤቱ በመሄ፣ የኪስ ቦርሳውን በማውጣት የዛሬን ብቻ ሳይሆን ለጃዝሚን እና ለህፃን ልጇ ለአንድ ወር የሚሆናቸውን የሚያስፈልጋቸውን የምግብ ሂሳብ ከፈለ።

የዛን ግዜ ሁሉም ፀጥ አለ።

ጆርዳንም ለሱፐር ማርኬቱ ባለቤት እንዲህ አለው:-

" የአንተ ስራ ደንበኞችን ማገልገል ነው፣ መፍረድ የለብህም ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው፤አንዳንዴ ለተቸገረ ሰው ትንሽዬ ደግነት ያስፈልጋል ።"
ይህንን ያውቃሉ⁉️

✔️ጥንታዊ ግብፃዊያን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እርግዝና መለያ መንገድን ከዛሬ 3300 አመታት በፊት እንዳስተዋወቁ ይነገራል ታዲያ በዚህ ጊዜ አንዲት ሴት ነፍሰጡር መሆኗን አለመሆኗን እንዲሁም የልጁን ፆታ ለመለየት የግድ በተዘጋጀ የገብስ እና የስንዴ ዘር ላይ እንድትሸና ይደረጋል።

ከዛም ከቆይታ በኃላ የገብሱ ቡቃያ እሚያድግ ከሆነ ወንድ ልጅን እንደፀነሰች፤ ስንዴው ከበቀለ ደግሞ ሴት ልጅን እንደፀነሰች ይታሰባል። ሁለቱም ካልበቀለ ደግሞ ነፍሰጡር እንዳልሆነች ይነገራል። ሁለቱም ቢበቅሉስ?🤔 ምን ይባላል ካላችሁ እኔ ግብፃዊ ስላልሆንኩ አላቅም ነው መልሴ

በነገራችን ላይ በ1960ዎቹ በተደረጉ ጥናቶች መሰረት የአንዲት ነፍሰጡር ሴት ሽንት ከመጠን በላይ ኢስትሮጂን በውስጡ ስለሚገኝ አንድ ዘር እንዲበቅል ሊያደርግ እንደሚችል ነገር ግን የልጁን ፆታ ማወቅ እንደማይቻል ይጠቁማል።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ክፋትን እና ውሸትን በፊልም የሚያስውበው ባለሙያ (የታሪክ ገጽ)

በ Youtube ቻናላችንን ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/Nky1TY59bco?si=72xwOAO7V9ACw28g
🙀እኩለ ቀን ላይ መተኛት(nap madreg) ስራችንን በሰላም እንድንሰራ እና አእምሮአችን ነቃ እንዲል ያደርጋል ሲሉ ተመራማሪዎች የተናገሩ ሲሆን የልብ ድካምን በ37% እና የመሞት አደጋንም ይከላከላል ሲሉም አክለውበታል!!!!
አዳሜ ደሞ ይህንን ሰማው ብለሽ ከምሳ በኋላ ተጋደሚና ስራና ክላስ ያምልጥሽ!😁

@AMAZING_FACT_433
@AMAZING_FACT_433
#ይሄን_ያውቃሉ❓

አራት አፍሪካዊ ሴቶች ይሄን የምታዩትን ጀነሬተር ሰርተዋል። ጀነሬተሩም ለ6 ሰአታት በአንድ ሊትር ሽንት ብቻ የሚሰራ ነው እማማ አፍሪካ ቴክኖሎጂ ማለት ይሄ አደለ 😱

@AMAZING_FACT_433
@AMAZING_FACT_433
የscholarship እድል የሚያስገኘው የALX Pathway ፕሮግራም ምዝገባ ሊያልቅ 1 ቀን ብቻ ቀረው!

የALX ‘Pathway’ ፕሮግራምን በመውሰድ፣ የአለምአቀፍ ዲግሪ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ እድል ለማግኘት ይመዝገቡ። የዚህ ስኮላርሺፕ እድል በጥቅሉ በአመት የ85,000 አሜርካን ዶላር፣ ወይም የ11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር፣ ተመጣጣኝ ዋጋ አለው።

ALX ከ14 በላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት አለው። አብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙት America ሲሆን፣ በEurope እና South Africa የሚገኙም አሉ።

የዚህ የትብብር ስምምነት ዋና ይዘት፣ የALX Pathway ኘሮግራምን በስኬት የሚጨርሱ ልጆች፣ በእነዚህ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት እና የስኮላርሺፕ እድሎች የሚያገኙበትን መንገድ ማስፋት ነው።

የምዝገባውን ሂደት ደረጃ በደረጃ ማብራሪያ ለማየት፣ እንዲሁም ምዝገባውን በተሳካ ሁንያ ለማጠናቀቅ፣ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ፡- https://t.me/ALXScholarship2ndBatch.

ወደ ምዝገባው ቀጥታ ለመሄድ ይህንን ተጫኑ - https://www.alxafrica.com/join-pathway/

Рекордтар

22.04.202523:59
92.4KЖазылушылар
22.04.202511:31
200Дәйексөз индексі
08.02.202508:36
11.5K1 жазбаның қамтуы
08.02.202508:36
11.5KЖарнамалық жазбаның қамтуы
28.01.202506:37
34.38%ER
07.02.202516:12
13.37%ERR
Жазылушылар
Цитата индексі
1 хабарламаның қаралымы
Жарнамалық хабарлама қаралымы
ER
ERR
OCT '24JAN '25APR '25

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች танымал жазбалары

የቡርኪና ፋሶው ትራውሬ ማስደመሙን ቀጥሎበታል!

ቡርኪና ፋሶ ከአሜሪካ ታስገባ የነበረው ልባሽ ጨርቅ ከዚህ ወዲያ እንዳይቀጥል በይፋ አገደች።

የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራዎሬ በጉዳዩ ላይ “አፍሪካ አህጉር እንጅ የቆሻሻ ገንዳ አይደለችም!” ብሏል


እስኪ ለዚህ ሰውዬ👍👍

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ቁጥር 1ዱ በአለም ብዙ ሰዎች የተሰየሙት ስም ''ሙሀመድ''ነዉ።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
የ መድፉን ድምፅ የሰማ በ 👍 ያልሰማ 💔

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ታሟል 🐑

በ15 ሺህ ብር እልል ብሎ የተገዛው በጉ በድንገተኛ ህመም ምክንያት ታሟል

ይህን ያዩት ገዢዎቹ ህክምና እንዲያገኝ በሆስፒታል ውስጥ አስተኝተውታል

በጎም ጉሉኮስ የተሰጠው ሲሆን

ክህክምናው አገግሞ ለፋሲካ በዓል እንዲደርስ ገዢዎቹ ተማፅነዋል

ለ15 ሺህ ብር ላወጣ በግ ሙሉ ጤንነቱን እየተመኝን

የሰው ዓይን ሳይሆን አይቅረም ያስብላል::

🐑🐑🐑

🌴🌴🌴

Viva Guresha
"ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር መኖሯን ያወኩት ከሶስትና አራት ቀን በፊት ነው" ሙሀመድ ሳላህ

ሳላን የምትወዱ ኢትዮጵያውያን ሜዳ በላችሁ

(Via: ዋልተንጉስ ዘሸገር
)

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ለፈገግታ 😍😂

ሰውዬው ጠዋት ወደ ስራ ሲሄድ ሚስቱ የረሳቸውን ነገሮች ሁሌም ታስታወሰዋለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ ሌላ ጊዜ መንጃ ፈቃድ መጣሉን ትነግረዋለች። ብዙ ጊዜ ግን ሞባይሉን ትቶ እየሄደ ጠርታ ትሰጠዋለች። «በቃ አረጀህ ማለት ነው !» እያለች ታፌዝበታለች።

«እንዲህ የሷ መቀለጃ ሆኜ መቀጠልማ አልችልም» ብሎ ለችግሩ መፍትሄ ለማበጀት ቆረጠ። ከዚህ በፊት የሚረሳቸውን ነገሮች አንድ በአንድ በዝርዝር ማስታወሻ ደብተር ላይ አሰፈረ...

ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ማስታወሻ ደብተሩን ከፍቶ የጻፋቸውን ዕቃዎች መፈተሽ ጀመረ። ምንም የረሳው ነገር እንደሌለ ሲያረጋግጥ በፈገግታ ታጅቦ ቤቱን ለቆ ወጣ። የድል ስሜት ተሰማው። መኪናውን አስነስቶ ገና ከመንቀሳቀሱ ባለቤቱ እንደወትሮው ደወለችበት። «እባክሽን ዛሬ አንድም የረሳሁት ነገር ስለሌለ ሆን ብለሽ ከስራዬ እንዳታስተጓጉሊኝ» ሲላት ምን ብትለው ጥሩ ነው ?? ...

«ባክህ ዛሬ እሁድ ነው ስራ የለም ወደ ቤትህ ተመለስ» 😂

የባሰ አለ አገርህን አትልቀቅ 😜
😍

✅@Amazing_fact_433
✅@Amazing_fact_433
ከእለታት በአንዱ ቀን ሁለት በእድሜ የገፉ አዛውንት ባለትዳሮች ድብር ይላቸውና...

ባልየው...የወጣትነት ጊዚያችንን ብንመልሰው ምን ይመስልሻል ይላታል ሚስትም በጣም ተደስታ እሺ ትላለች።

ከዛም ባል በቃ እኔ ታች ሱቁ ጋር ልውረድና ድንጋዩ ላይ ቁጭ ብዬ አንቺ በዛ በኩል እለፊና ይዤ ላዋራሽ ተስማሙና ባል ወደታች ወርዶ ድንጋዩ ላይ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ጀመረ...ቢጠብቅ ቢጠብቅ ቢጠብቅ አትመጣም...4 ሰአት ሙሉ ጠበቃት አልመጣችም። የሆነ ነገር አጋጥሟት ይሆናል ብሎ ወደቤት ሲመለስ ሚስት ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ያገኛታል።

ባል ደንግጦ ምነው የኔ ውድ ምን ሆንሽብኝ

ሚስት ማልቀሷን ሳታቆም እናቴ ከቤት እንዳልወጣ ከልክላኝ ነው 😜

የማያረጅ ፍቅር ለሁላችሁም ተመኘሁ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ስለ ልጁ እንዲህ ይላል
" ልጄ እምቅ ችሎታ አለው ድንቅ እግር ኳስ ተጫዋች እንደሚሆን ወደፊት የምናየው ይሆናል ። አንዳንድ ጊዜ ኮካ ጠጥቶ ቺፕስ ሲበላ ያናድደኛል ።
እሱ ፈጣን እግሮች አሉት። በጥሩ ሁኔታ ኳስ ያንጠባጥባል ፣ ነገር ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም። ሁልጊዜ ስኬት ለማግኘት ጠንክሮ መሥራትና ራስን መወሰን እንደሚያስፈልግ እነግረዋለሁ።
ለእረሱ በጣም አስፈላጊው ነገር  እግር ኳስ ተጫዋች ይሁን ወይም ሐኪም አላውቅም። ብቻ በያዘው ነገር ሁሉ ምርጥ መሆን አለበት። "

ክርስቲያኖ ሮናልዶ አርዓያ ለመሆን ያበቁትን እሴቶች ለልጁ እያስተላለፈ ይገኛ

እስቲ የ cr7 አድናቂዎች በ
🥰

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ይህ ውሻ ከሆኑ ሰዎች ጋር አብሯቸው ይኖር ነበር...የሰዎቹ መኖሪያ ቤት በእሳት ሲቃጠል፤ ሰዎቹ ከአደጋው ለማምለጥ ውሻቻውን ጥለውት ወደ ውጪ ይሮጣሉ።

ሁሉም ሰዎች ወደ ውጭ እየሮጡ ሳለ ውሻው ትንሽ ድመትን ለማዳን ተመልሶ በእሳት እየተቃጠለ ወዳለው ቤት ይገባል...ድመቷን ከእሳት ውስጥ በማውጣት ህይወቷን አድኖታል።

ይህ አስደናቂ ድርጊት ውሾች ምን ያህል ታማኝ እና ጀግና እንደሆኑ ያረጋግጣል 🐕❤
በቻናላችን ለምትገኙ እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት ቀን በሰላም አደረሳችሁ ✝

አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ ❤️🙏


@AMAZING_FACT_433
@AMAZING_FACT_433
#ይህንን_ያዉቃሉ⁉️

ሴቶች ወሲባዊ እርካታ ላይ ሲደርሱ
ሰውነታቸው ከፍተኛ painkiller ያመነጫል። ይህ ማለት እራስ ምታት የያዛት ሴት ወሲብ ብትፈፅም እራስ ምታቱ ይለቃታል ልክ ማስታገሻ መዳኒት የዋጠች ይመስላል።🤭
ኢብራሂም ትራዎሬ

ከ አሜሪካ ሚገባ የቦንዳ ልብስ ካገደ በሁዋላ ለምን አገድክ ተብሎ ሲጠየቅ ።

አፍሪካ አህጉር እንጂ ቆሻሻ መጣያ አደለችም 😄

መሪ በ ቡርኪነፋሶ ተፈጥሩዋል ፈጣሪ ይጠብቀው ብዙ ነገርም እያረገ ነው 👍

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ይሄ ሰው አልተቻለም

በቡርኪናፋሶ የሚገኙ አረጋውያን ምንም አይነት የመብራትና እና ውሃ ክፍያ አይከፍሉም።ፕሬዝዳንት ትራውሬ "ውሃና መብራት መሰረታዊ ነገሮች ስለሆኑ ሁሉም ሰው በነጻ ማግኘት አለበት" ይላል።

ቡርኪናፋሶ በሚገኙ ሁሉም ዮኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ስራ እስከሚያገኙ ድረስ 165 ዶላር ደሞዝ በየወሩ ይከፈላቸዋል።

የቡርኪናፋሶ እስረኞች በግብርና ዘርፍ ለአንድ ወር ማህበረሰቡን ባገለገሉ ቁጥር የሶስት ወር የእስር ቅጣት ይቀነስላቸዋል።

ይህ ሰው ቡርኪናፋሶን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን የመቀየር አቅም ያለው ጀግና መሪ ነው።ስልጣን ከያዘ በኋላ የሰራቸው ነገሮች ተዘርዝረው አያልቁም።

አፍሪካ ድሮም ጨለማ አሃጉር የነበረችው ጸሐይዎቿን ስለምትገድል እንጅ ጀግና ሳይወለድባት ቀርቶ አልነበረም።አሁን የወጣው ጸሐይ ከራስ አልፏ ለአፍሪካ ጭምር የለውጥ ጮራ ነው።እግዚያብሔር ከምዕራባውያን አይን ይሰውረው።

ኢትዮጵያ ግን ይህን የመሰለ መሪ መቸ ነው ምታገኝ? በረከታቸው ይደርብን!


@Amazing_fact_433
ትራዎሬ ላይ ግ ድያ ሙከራ!

በአፍሪካ ጀግና መሪ ቢፈጠርም መስዕዋት ሁኖ ለማለፍ እንጅ ለመስራት አይታደልም። ትራዎሬ ስልጣን በያዘ ሁለት ዓመት ጊዜ እንኳ ከ 18 በላይ የግ ድያ ሙከራ ተደርጎበታል።

ትናንት ብቻ ትራዎሬ ላይ ግ ድያ ለመፈጸም ሲዘጋጁ የተገኙ 113 በላይ ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከኋላ ሴራውን ሸራቢዎች ምዕራባውያን ቢሆኑም ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ የገዛ ዜጎቹ ናቸው።ፈረንሳይ የመሆን እድሏም ከፍ ያለ ነው።በአንድ ወቅት ትራዎሬ ከፈረንሳዮ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮኒ ጋር ያደረገው ንግግር ኃያላኑን ያስደነገጠ ነበር።ነገሩ እንዲህ ነው

ኢማኑኤል :- "ፕሬዝዳንት ትራዎሬ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ለማጠንከርበሀገርህ ወታደር የማሰፍርበት ቦታ ስጠኝ" በማለት ይጠይቀዋል።

የትራዎሬ ምላሽ :- "አሜሪካ ፣ ብሪታኒያ ፣ ብራዚል ወዳጆችህ ናቸው።ታዲያ ለምን ወዳጅነትህን ለማጠንከር በነዚህ ሀገሮች ላይ የጦር ሰፈርአልኖረህም?" የሚል ነበር
-
አንድ የህግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ ሳለ አንድ በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ ከሚገኘው ወንበር ላይተቀመጠች። በዚህም የህግ ባለሙያው ደስ አለው። ቀና ብሎ ሲመለከታት አይን ለአይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች። አሁን ደግሞ በይበልጥ ደስ አለው። ትንሽ ቆይታ አጠገቡ ሄዳ ተቀመጠች።

በዚህን ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አለው። ትንሽ ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ ''ያለህን ገንዘብ; የATM ካርድህን ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ ካልሰጠኸኝ ስትጎነትለኝ እንደ ነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰብኝ እዚህ ባቡር ውስጥ ላሉት ሁሉ በመንገርእጮኃለሁ።" አለችው።

የህግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታትና ከቦርሳው ውስጥ ወረቀትና እስክሪብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ፃፈላት "ይቅርታ መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ።

እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ ፃፊልኝ።"ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ጽፋ ሰጠችው።

የህግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀብሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ ከከተተው በኋላ ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምጽ ምን ቢላት ጥሩ ነው!

"አሁን እንደፈለግሽ መጮህ ትቺያለሽ።"የታሪኩ ምግባር: ሰነድን በአግባቡ መያዝ ምን ግዜም አስፈላጊ ነው።


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Көбірек мүмкіндіктерді ашу үшін кіріңіз.