से पुनः पोस्ट किया:
ካሊድ አቅሉ

01.05.202520:47
ሲጠቅሱት ማይገባዉ
( ፍቅር )
ካሊድ አቅሉ
እኔ ጋር የረሳችዉን መፅሀፍ ልሰጣት እንዳገኘዋት የእጆችዋን ጥፍሮች አየዋቸዉ ከበቂ በላይ ተከርክመዋል ። ድምፄን ዝግ አድርጌ “ጥፍርሽን መብላት ጀመርሽ አይደል ?”አልኳት እሷም የመፃሀፉን ሽፍን ትክ ብላ እያየች “ አዎ ሲያድግ አንተን እያስታወሰ አስቸገረኝ ከዚህ ሁሉ ብዬ ወደ ቀድሞ ልምዴ ተመለስኩኝ !” አለች መጨለም መቆጣት እና ፊት መንሳት ማይችለዉን ፊትዋን ያቅሟን ለማደብዘዝ እየሞከረች።
ልብዋ ከኔ ለመሸሽ ያቅሙን እያረገ እንዳለ ያኔ ተረዳዉ ጥፍርዋን በጥርሷ ልጣ ከአፍዋ እንደተፋችዉ ፍቅሬን አንቅራ ለመትፋት ዳር ላይ እንዳለች ተገለጠልኝ ። ልምዶች ለካ መዉደዳችንን ይገልፃሉ ወፍራም ሴት ወዳለዉ ያልኩትን ይዛ ይሄኔ ለመክሳት ጂም መስራት ጀምራለች ፍቅር በትግል ሚወጣ መስልዋት …..
ከዛ ቀን ብሃላ አላገኘዋትም ምን ትምሰል ምን አላዉቅም ምወዳቸዉን ነገሮችዋን ለማርገፍ ስትታገል ይባስ እያጌጠች ይሆናል ደግሞ እንደፍቅር ማን አለ እልህኛ ሊቀድሙት በሮጡ ቁጥር በአቆራጭ መንገድ ካለንበት ሚደርስ ሲጠቅሱት ማይገባዉ ፍራ !

Bemnet Library

26.04.202517:16
አቤ........ት! ምን ያህል ነገሮች በውስጤ ታምቀው እንደሾርባ እየተነንኩ እንዳለው ምነው ባየሽልኝ ኪትዬ! ትክክለኛ ማንነቴን መረዳት ጨርሶ ከተሳናቸውና እንደ አንዳች ትክት እያሉኝ ከመጡ ሰዎች ጋር የግዴን ተቻችዬ ለመኖር የማደርገው ጥረት ምን ያህል አድካሚ እንደሆነ ምነው ባወቅሽልኝ ኪትዬ!
ለዚህ እኮ ነው በስተመጨረሻው ምንግዜም የስሜቴ ብቸኛ ተጋሪ ወደሆንሽው ወደ አንቺ ወድ ዳያሪዬ ፊቴን የማዞረው።የምጀምረው የምጨርሰውም አንቺ ላይ ነው ኪቲ።ምክንያቱም የማያልቅ ትዕግስት ያለሽ አንቺ ብቻ እንደሆንሽ አውቃለሁ።መቼም ባለውለታዬ ነሽና እኔም አንድ ነገር ቃል ልግባልሽ።
ኪቲ ምንም ይሁን ምን....እንባዬን ዋጥ አድርጌ.....ከዚህ ችግር የምወጣበትን የራሴን መንገድ እስከማገኝ ድረስ በጭራሽ ተስፋ አልቆርጥም።ይሄ ቃሌ ነው።እንደማላሳፍሽም እርግጠኛ ሁኚ።በተረፈ አንድ የምመኘው ነገር ቢኖር የጥረቴን ውጤት የማይበት ጊዜ ሩቅ ባልሆነ ወይ ደግሞ አንድ በትክክል የሚያፈቅረኝና ከስር ከስር አይዞሽ እያለ የሚያበረታታኝ ሰው በኖረኝ ብዬ ነው።ይሄን ያህል አማረረች ብለሽ አትፍረጂብኝ ኪትዬ...ይልቁንም ሁልጊዜ አንድ ነገር አስታውሺ....አንዳንዴ...እኔም ብሆን እንደርችት ልፈነዳ ከምችልበት ነጥብ ልደርስ እችላለሁ።
📓ርዕስ፦የአና ማስታወሻ
✍️ፀሀፊ፦አና ፍራንክ
⚡️የ15 ታዳጊ.. ግን ህይወትን የተረዳች ትልቅ ሰው❤️
📚 @Bemnet_Library

20.04.202503:28
✨
እንኳን አደረሳችሁ!!
መልካም የትንሣኤ በዓል🤍
https://t.me/yeesua_queen
ክርስቶስ ተንስዐ ሙታን
በአብይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዜሰ
ኮነ
ፍሰሃ ወሰላም 🙏
እንኳን አደረሳችሁ!!
መልካም የትንሣኤ በዓል🤍
https://t.me/yeesua_queen
07.04.202509:44
✨✨✨.........ችግሬን ሁሉ በመደበቅ እሸሻት ይመስል ኮሽ ባለኝ ቁጥር መሮጥ መሸሽ ከአለም መደበቅ ያምረኛል። መዞር እወዳለው። ድንገት ተነስቼ ከአለም እሰወራለው........... ከዛ ራሴን አንድ ተራራማ ቦታ አገኘዋለው።
.........ከዓለም መሸሸግ አምሮኝ ኮፊያ ያላትን ጃኬቴን(ሁዲ) ብቻ ተከናንቤ ነበር የወጣሁት። በመኪናው ጥጋት ላይ ተቀምጬ መስኮት መስኮቱን ሳማትር ነው። የተዋወቅኳት። በትከሻዋ ተጠጋልኝ አይነት ነገር ስታሳብቅ ነበር። የባጥ የቆጡን አላወራንም ሰው ሁሉ አጠገቡ ካለው ጋር ሲሳሳቅ ሲጨዋወት ዞርም ብዬ አልገረመምኳትም። ለማውራት በሚመስል ቅላጼ በየቆይታው ድምጽዋን ትጠርጋለች። ዓለምን ሽሽት ድምጼን ሳላሰማ በአርምሞ ጉዞ ላይ ነኝ። ድንገት እንደመደገፍ አይነት መጥታ ትከሻዬ ላይ ጋደም አለችበት። ምቾት አልነሳኝም አልቆረቆረኝም።
ደቂቃዎች ደቂቃዎችን እየወለዱ ሳታስበው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ከትማለች ትከሻዬን የያዘችው አያያዝ አትልቀቀኝ አይነት ጥብቅ አድርጋ ነው። ከነፍሴ ነው ምወድህ አይነት ነገር.......የሲሳይ ንጉሱ ወጉን የጀመረ ያክል ምተውን መሰለኝ!
ጠይም ናት መልከ ስሯዋ አነጋገሯ ሁሉ ያቺ ሰመመን በብእሩ የሳላት አቤልን በፍቅር ክንፍ ያደረገችው ትዕግስትን ትመስላለች። "ጠይም ናት ፤ ካውያ ያልነካው ፀጉርዋ ከማጅራቷም ባያልፍ ለማበጠር የሚያስቸግር አይነት አይደለም። ቁመቷ አጭር ነው ፤ አለባበሷ እንደነገሩ ይመስላል ፤ ገና ሲያያት አጠገቧ ካሉት ልጃገረዶች ጋር በሆነ ጨዋታ ትሣሣቅ ነበር። ስትስቅ ጉንጮቿ ስርጉድ ይላሉ...
የሆነች ነፍስ ትከሻዬ ያመነች መሰለኝ እና ደስአለኝ። አምናኝ የተጠለለችብኝ መሰለኝ ሙሉ ሰው የሆንኩ መሰለኝ ። የግራ እጄን ኩምትር አድርጋ እንደያዘች በደስታ ፈገግ አልኩ ። በቀኝ እጄ ሉጫ መሳይ ጸጉሮቿን መዳበስ ያዝኩኝ ይበልጥ ተጠጋችኝ እንደ እናት ጉያ ሽሽግ አለችብኝ። እጄን አመቻችቼ አቀፍኳት መኪናው እንዳያንገላታት ይበልጡኑ ወደራሴ ሳብኳት። ታሳዝናለች ራሴን በሷ ውስጥ ሳልኩት። ያመንኳቸው የተደገፍኳቸው እንዲህ ቢያቅፉኝ ብዬ ተመኘው። ለምንድን ነው የምወደው ነገር ሳፈጥበት ገሸሽ የሚለው ? ብዬ አፈጠጥኩባት የሆነ ምታደምጠኝ ያህል ተሰምቶኝ በአርምሞ እጠይቃታለው የምጠላው ሳይቀር እኮ መውደድ ስጀምር ጥላ ያጠላበታል ። እያጡ ማዘን እኮ ደከመኝ። ተረግሜ ፣ተደግሞብኝ ወይ ደግሞ አይነጥላ ይሆን? እንጃ? በስስት አይኔ እያየዋት በስሱ ግንባሯን ስስማት ነቃች። ሰርቆ እንደተያዘ ሌባ ቅብዝብዝ አልኩ። እጆቼን በፍጥነት ሰበሰብኩ ደግሜም ማየት አሳፈረኝ..........
እሷ ግን ዓይኗን መግለጥ የፈራች ይመስል እዛው እኔን ላለማየት ዓይኖቿን ጨፍና ትንሽ ቆየች በአንድ ዓይኗ አጮልቃ ወደኔ አየችኝ:: መልሳ አይኗን አላዞረችም። ረጅም ዝምታ ውስጥ ድረስ ሚሰብር ዝምታ.........ምን እያሰበች ይሆን?.......
የመጋቢትን የሚጋረፍ ቀዝቃዛ አየር ለመከላከል ሁዲዬን እስከላይ ድረስ ተከናንቤው ከመኪናው ወረደኩ፡፡ እንደ ጩቤ የሚዋጋው ብርድ ነበር የተቀበለኝ፡፡
ሁለት እጆቼን የሱሬዬ ኪሶች ውስጥ ከትቼ ወደተራራማዋ ቤቴ መገስገሴን ተያያዝኩ...............
✍ዮዳሄ

05.05.202507:06
"እኔ የማምነው በአንድ እግዚአብሔር ነው። የምቀበለው የነጻነታችን ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ብቻ ነው። ኢጣሊያ የሚባል ገዥ አላውቅም። ለፋሺስት ኢጣሊያ የተገዛ እንደ አርዮስ የተረገመ ይሁን። እንኳንስ ሕዝቡ ምድሪቱም እንዳትገዛላቸው አውግዣለሁ።"
(ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ቀዳማይ ዘጎሬ)
መልካም የአርበኞች ቀን
https://t.me/yeesua_queen
(ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ቀዳማይ ዘጎሬ)
መልካም የአርበኞች ቀን
https://t.me/yeesua_queen
30.04.202512:51
✨ሂድ ብለሽኛል....!?💎
ሰው ሐረግ አይደል ሁሌ ጉዞውን እርስ በራሱ አይተሳሰር
ለምን ከበደሽ ያውና ብሎ የመለያያ መንገዱን ማብሰር
አብቅቷል ካልሽኝ ቆለፍኩት ካልሽን ሳንኳኳ አልኖርም የልብሽን በር
ግን እንዳይቆጨኝ አንዴ ንገሪኝ የሰለቸሁሽ የቱ ጋር ነበር ?
ሂድ ብለሽኛል ምን አደርጋለሁ!?
'ወደድኩህ ያለኝ አፍቃሪ ልብሽ እንዴት አስቻለው መፍረድ ያለ ክስ
ሂድ ያልሽው ልቤስ ምን ብሎ ያርፋል ያስቀየመሽን በደሉን ሳይክስ
እጅሽን ጭነሽ አድምጪው እስኪ ይህ አልነበረም ልቤ ትርታው
'ሚናገርበት አንደበት አጣ ምስጢር ቃልሽን ምን ብሎ ይርታው
ሂድ ብለሽኛል ምን አደርጋለሁ!?
ሕልም ያነገተ ሩቅ መንፈሴ አበቃ ብሎ እንዴት ይደምድም
ሒድ ብለሽኛል እስከምን ልሂድ መለየት እንጂ መራቅ አይከብድም!
መንገደኛ እግሬ አንድ ጊዜ ብቻ ይራመድ እንጂ መለያየቱን እያደር ያምናል
ግን እባክሽን ብቻውን አይሁን እስከጫፍ ድረስ ብትሸኚኝ ምናል
ሂድ ብለሽኛል ምን አደርጋለሁ
ፍቅርሽ ነው እንጂ ጥም መቼ ረታኝ ለነገ ብዬ አልያዝኩም ስንቄን
ትቼልሻለሁ ሁሉን ከአንቺ ጋር አንጀትና ሆድ እውነትና ሃቄን
ሂድ ብለሽኛል እንግዲህ ልሂድ
እንድቆም ካሻሽ ንገሪኝ ልቁም
በድካም ኩርፊያ ያርፉታል እንጂ ፍቅርና መንገድ ጨርሶ አያልቁም
ሂድ ብለሽኛል ምን አደርጋለሁ!?
✍አስታወሰኝ ረጋሳ
https://t.me/yeesua_queen
08.04.202508:19
✨✨ሞገደኛው ነውጤ - 1✨✨
ትረካ ሲባል ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው ወጋየው ንጋቱን ነው። ምንም እንኳን በሱ ዘመን ኖሬ ስለሱ ባላውቅም ደጋግሜ የሰማውት የፍቅር እስከመቃብር ታሪክ ድምፀቱ ልቦናዬን ይሰውራታል።
ሌላኛው እንቁ ደግሞ ጋሽ ፍቃዱ ተክለማርያም ናቸው። "ሞገደኛው ነውጤ" ደግሞ በጋሽ ፍቃዱ ድምፀት አብዝቼ የምወደው ትረካ ነው።
ከ እነ ድምፀቱ የባለሃገርን የዋህነት፣ ገራገርነት ቁልጭ አድርጎ አበራ ለማ በመቆያ መጽሃፉ ላይ ፅፎት ጋሽ ፍቃዱ ተክለማርያም በግሩም ድምጸት ተርኮታል።
ተጋበዙልኝ ክፍል አንድ'ን

05.04.202519:42
ተማሪዎች ወደ ዚህ ቤት ጎራ እያላችሁ🌟💫
https://t.me/stuentsE
https://t.me/stuentsE
से पुनः पोस्ट किया:
የኔ' ማስታወሻ ...️️✍️

03.04.202512:45
ውስጠኛው እኔ -
@poethaymi
ፃፊለት ፃፊለት ይለኛል፡😊
ታዲያ ልፅፍልህ እነሳና ምላሹን እፈራዋለሁ ፤ ዳግም እንዳይሰብረኝ ..
እንደበፊቱ መነሳት እንዳይከብደኝ ...😔
ምን ተሻለኝ ?
@poethaymi

02.05.202519:32
✨✨ኦሮማይ😢...... እስመ ኢተኀድጎሙ ለእለ የሐሡከ ......
से पुनः पोस्ट किया:
የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw

28.04.202510:09
‹‹ጭስ እና ጭነት››
--------
እራት ሊበሉ ወጥተው ፣
እሱ ‹‹ምን ሆነሻል›› ሲላት፣ እሷ ‹‹ምንም›› ብላ የጀመሩት ቀላል የዘወትር ንትርክ በፍጥነት አድጎና ሁለቱንም በስሜት አግሞ ሰው ፊት በጩኸት ያጨቃጭቃቸው ጀመር፡፡
ቦይፍሬዷ እንዲህ እንዲህ ቶሎ ቶሎ መጣላታቸውን እንደማይጠላው ደጋግሞ ነግሯታል፡፡
‹‹ጭስ እንደማውጣት በይው…ጭነት እንደማራገፍ…›› እያለ፡፡
እሷ ግን ለእሱ ያላት ፍቅር በለጠው እንጂ ቶሎ ቶሎ፣ በትንሹም በትልቁም መነታረኩ ታክቷታል፡፡
አብዛኛው ጠባቸው እዚያው ሞቆ፣ እዚያው ፈልቶ የሚበርድ ነበር፡፡
የዛሬው ግን ጫን ያለው ይመስላል፡፡
ዙሪያቸውን ተቀምጠው እራት የሚመገቡት ሌሎች ሰዎች እስኪያፈጡባቸው፡፡ አስተናጋጆች እስኪጠቋቆሙባቸው፡፡
ቦይፍሬንዷ ራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው በድንገት ብድግ አለና ስድስት ወይ ሰባት የሁለት መቶ ብር ኖቶች ጠረጴዛው ላይ ወርውሮ በተቀመጠችበት ጥሏት ሄደ፡፡
ሲበርድለት እንደሚደውልላት፣ ሲደውልላት ኩርፊያዋ እንደሚለቃት፣ ኩርፊያዋ ሲለቃት ስትበር ቤቱ እንደምትሄድና፣ ቤቱ ስትሄድ የእንታረቅ ጣፋጭ ፍቅር እንደሚሰሩ ታውቃለች፡፡
ያም ሆኖ እዚህ ሁሉ ሰው ፊት ተጣልቷት፣ እዚህ ሁሉ ሰው ፊት ጥሏት መሄዱ አሳፈራት፡፡
---
ፊቷን በሃፍረት ቀብራ ፊት ለፊቷ የተቀመጠውንና ሁለት ሳትጎረስለት መቀርዘዝ የጀመረውን ላዛኛ በሹካዋ መወጋጋት ጀመረች፡፡
ረሃቧ በኖ ጠፍቷል ግን ቀና ብላ ሰዉን ከመጋፈጥ እንደነገሩ ለመብላት ወስና ሶስት ጊዜ ጎረሰችለት፡፡
ትንሽ ቆይቶ፣ ሬስቶራንቱ ወደ ቀድሞው ጫጫታው፣ የከበቧት ሰዎች ወደ በፊቱ ወሬያቸው ሲመለሱ ቀስ ብላ ቀና አለች፡፡
በቅርብ ርቀት ሌላ ጠረጴዛ ደገፍ ብሎ ብቻውን የተቀመጠ ሰውዬ ትክ ብሎ ሲያያት ተመለከተች፡፡
አርባዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለ ጎልማሳ፡፡ የጋብቻ ቀለበት ያላጠለቀ ወንድ፡፡ ሰርሳሪ አይኖች ያሉት ሰውዬ፡፡
ፊቷን ወደ ላዛኛዋ መልሳ በሹካው የለዘዘ ቺዙን መቆፋፈር ስትጀምር ግን ከበዳት፡፡
ቀና አለች፡፡
ሰውየው አጠገቧ ቆሟል፡፡
‹‹አንቺ ነሽ ልክ!›› አላት ልክ ከዚህ በፊት ጨዋታ ጀምረው እንደሚቀጥሉ ሁሉ ዘና ብሎ፡፡
‹‹እ…?›› ሽቅብ እያየችው መለሰች፡፡
‹‹አንቺ ነሽ ልክ ነው የምልሽ››
‹‹እ…ስለ ምኑ…?››
‹‹ስለምንም ይሁን አንቺ ልክ ነሽ››
ፈገግ አለች፡፡
‹‹ግን እኮ በምን እንደተጣላን አልሰማህም››
‹‹ባልሰማም ልክ ነሽ…››
‹‹እንዴ…ስለምን ጉዳይ እንደተጣላን እንኳን ሳታውቅ?››
‹‹ስለምንስ ቢሆን አንቺን ከመሰለች ልእልት ጋር ምን ቆርጦት ይጣላል?››
አሁንም ፈገግ አለችና፣
‹‹አይ ለነገሩ የእኔም ጥፋት ነው…ሁሉም ነገር ላይ እኔ ያልኩት ይሁን ስለምል…››
አቋረጣትና ቦይፍሬንድዋ ተቀምጦበትና ሲሄድ ስቦት የነበረው ወንበር ላይ በፍጥነት ቁጭ አለ፡፡ በግርምት አየችው፡፡
‹‹እሱን ተይው…የእኔ ብትሆኚ ሁሌም ያልሽው ይሆናል…›› አላት፡፡
ቀጥተኝነቱ፣ ፈጣጣነቱ ገረማት፤ ደስም አላት፡፡
---
ከዘጠኝ ወራት በኋላ ነትራካውንና የምታፈቅረውን ቦይፍሬንዷን ረስታ
‹‹ምን ብታጠፊ ሁሌ ልክ ነሽ›› ያላትን ጎልማሳ አገባችው፡፡
ባሏ ቃሉን ጠብቋል፡፡
ፈጽሞ አይነተርካትም፣ ጭራሽ አይጨቀጭቃትም፡፡ የጠየቀችውን ሁሉ እሺ፣ ያደረገችውን ሁሉ አበጀሽ ባይ ነው፡፡
‹‹ደስ እንዳለሽ››
‹‹እንዳልሽ››
‹‹ከቃልሽ አልወጣም›› የዘወትር ቃላቱ ናቸው፡፡
እሷ እንዳፈተታት የሚመራው ኑሯቸው ለጊዜው ያስደስታታል፡፡
አልፎ አልፎ ግን፣
‹‹ትዳራችን እንዲህ ሰላማዊ የሆነው የሚያጨቃጭቀን ነገር ጠፍቶ ነው ወይስ ባሌ ችሎ ችሎ ችሎ ከአመታት በኋላ በአንድ ጊዜ የሚያራግፍብኝ ጭነት እየተሸከመ፣ ሳላስበው የሚለቅብኝ ጥቁር ጭስ እያጠራቀመ ስለሆነ ነው?›› የሚል ስጋት ይወራታል፡፡

25.04.202513:40
✨
https://t.me/yeesua_queen
የመጨረሻ እቅፍ...
ልትሄድ ነው..ልሄድ ነው...የመጨረሻ ቃሌ 'ወድሻለሁ ነው...ግን .. ከመሄዷ በፊት ግን: ግዝፈቷ ትዝታ ከመሆኑ በፊት ግን :ነበር ከመሆናችን በፊት ግን :እጄን ከመልቀቋ በፊት ..ከዓይኔ ሳትጠፋ ልቤ ውስጥ ብቻ ሳትከትም በፊት አቀፍኳት...
ረጅም ደቂቃዎች ተቆጠሩ...እስክንገናኝ አይደለምና:እስክትመጣ ያልሆነ ለሕይወት ዘመን የሚበቃ ረጅም ማቀፍ ...የልብ ምት የሚቆጠርበት ...ከልብ የሚደርስ ማቀፍ...የመጨረሻ እቅፍ.....አቀፍኳት🫂
https://t.me/yeesua_queen
से पुनः पोस्ट किया:
Thoughts

07.04.202513:54
#14
በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት
ጠንካራ በራሷ ምትተማመን አንገቷን ቀና አርጋ ምትራመድ ኩሩ ሴት....መውደድ ትንፋሽ የሆነላት ድምቀት ራሱን የሆነች ተግባቢ አስተዋይ.....የእንዲህም ይታሰባል የሀሳብ ውቂያኖሳም.....ሴት ነበረች ያኔ ገና...
እንደንጉስ ዙፋን ከፍ ካለው የቤታችን በረንዳ ላይ እንደ እናትናልጅ የልብ የልባችንን ተቀምጠን ከጎኗ ሆኜ ወደሷ ዞሬ እያወጋን ነው....ብርሃን ትባላለች...ስሟ ለሆነችልኝ የተሰጣት ትርጓሜ ነው የሚመስለኝ....ድቅድቅ ያለ ጨለማ ታውቃላችሁ አይደል? አዎ ህይወትም አንዳንዴ ድቅድቅ ጨለማ ትሆንብን የል? ያኔ መውጫ መንገዴ ብርሃኔ ናት.. በድቅድቁ መውጫ ሲጠፋኝ ከሩቅ እንደሚታይ ብርሃን ደርሼባት ይዣት ጨለማዬን እየገፈፍኩ ምጓዝባት...የብሩህ ቀኔም ፀሃዬ እርሷዉ ናት የኔ ብርሃን ተስፋዬ መፅናኛዬ ድምቀቴ ናት የኔ እናት....
የመጀመሪያና ብቸኛ ሴት ልጇ ነኝ ስል በኩራት ነው....
"በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት" ከልጅነቴ የምታውቀኝ ጎረቢታችን በጨዋታ መኃል ስለኔ የተናገረችው ነበር...." ብላ ዝምም አለች....ጥላታችሁ ይደንግጥ ክውው ብዬ አየኋት....የስሜን ትርጉም ማወቅ ያጓጓኝ ነበር...."ንገሪኝ" የዘወትር ዜማዬ....."አንድ ቀን" የሁል ጊዜ ምላሿ ነበር.....ዛሬ ያቺ 'አንድ ቀን' ናት.....
"ስለኤላሜኔ በደንብ አውርቼሽ አላውቅም አይደል ወንድሜ ኤላም ከወንድምም አባት ጓደኛ ሁሉ ነገር የሆነ እንደስሙ የሆነልኝ ዘላለም ድረስ ነው... አባትሽንም ያገኘሁት በእሱ ነው...." ከስስ ፈገግታ ጋር ፊት ፊት አሻግረው የሚያዩ ዓይኖቿ እንባ ችፍፍ አለባቸው ናፍቆት መውደድ ሰፍረዋል ከገጿ....." አባትሽ ሸበላ ወንዳወንድ ብዙ የማያወራ ሲያወራ አፍ ሚያስከፍት ጥበበኛ ጎበዝ ሃይማኖተኛ ሰው ነበር....ትዕግስቱ አለት ያቀልጣል(አብረን የሆነው በምን ሆነና)"አለች ሳቅ እያለች....."በጣም ታግሎኛል በሰዓቱ ትምህርቴ ላይ ብቻ ነበር ትኩረቴ ለምንም ግድ አልነበረኝም.....ኤላምዬ የልብ ወዳጁ ነበርና ቢያቅተው መውደዱን እየፈራ ነገረው(ደካማ ጎኔን ሁላ አውቆልሽ ነበር) ወንድሜ ግን ሲሰማ ደስ ነበር ያለው.....ትንሽ ተግደረደርኩ (አውቄኮ ነው ኤላሜ ሲዖል ገነት ነው ቢለኝኳ መከራከር ሀሳቡ ራሱ ከየት መቶ? ህስስስ አሃ እንደዛ ነው ለካ? ብዬ ባገኘው አዲስ እውነት ሌላ ዓለም እፈጥራለው)....እናልሽ ልመና ራሱ ከሰለቸው ብዙ ልመና በኋላ አባትሽን ቀረብኩት.....ልዕልትነት ሴት መሆንን አሳየኝ አከበረኝ....
የሆነለት ስቅስቅ ብዬ በሶፍት ተከብቤ እያለቀስኩ ከሥራ ደክሞት የመጣው ወንድሜ ሶፋ ላይ እየተነፋረኩ ሲያየኝ "ምንሆንሽብኝ?!" ብሎ ደንግጦ ወደኔ መጣ...."አንተ ነህ ለዚህ ሁሉ ያበቃኸኝ" አልኩ በሶፍት ንፋጤን እየጠራረኩ በድንጋጤ ፈጠጠ "ምን አረኩሽ ብርሃኔ?"...."አልፈልግም እያልኩህ....." አልጨረስኩትም እንደልጅ ነው ያረገኝ ወንድሜ ፊቴ ላለመሳቅቢሞክርም አልቻለበትም.....ታቅፌው የነበረውን ትራስ ወርውሬበት እኚኝኛኝኝእእ እያልኩ ወደ ክፍሌ.....
መጣ ተከትሎኝ...."እሺ እንታረቅ?" ተለማመጠኝ.....አጠገቤ ቁጭ አለና......ዓለም ፀጥጥጥ ብላ የምታደምጠው የሚመስለኝን አወራሩን ጀመረ....."የኔ ትንሽዬ አደግሽ ማለት ነው አፍቅረሽ መናፈቅ ጀመርሽልኝ.....ማፍቀር ደስ ይላል መታደል ነው.....ልጓም ካላበጀሽለት ቦይ እንደሌለው ውሃ ወደ ፈለገ ይወስድሻል እንደፈለገ ያደርግሻል"...."እሺ ምን ላርግ ኤላዬ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ"...."ማቃት አለመቻል አይደለም አይደል?"...
በስስት ትኩርር ብሎ ካየኝ በኋላ እጁን ትከሻዬ ላይ አርጎ እየተመለከተኝ.."ያለመስነፍ መታገል አለብሽ ስሜቶችሽን ማሸነፍ ብቸኛ አማራጭ ነው ከተሸነፍሽላቸው ግን ምንም አይደለም የሚያደርጉት አንቺን ነው ሚነጥቁሽ" ካቀረቀረበት ከሀሳቡም መለስ አለና..."አንዳንድ ትግሎች lifetime ናቸው እየተጋገልሽ መኖር ነው ሚያኖርሽ....መናፈቅ ቆንጆ ነገር ነው ግን የምታስተናግጂበት ጤናማ መንገድ ማኖር አለብሽ(ቦይ ያለው ውሃ አድርጊው).....ፈገግ አለና አይ ትንሿ ለአንድ ቀን እናቱን ጥየቃ ቢሄድ እዬዬ....." "ሂዛ ክፉ ነክ እሺ" አልኩ ለንቦጬን ዘርግፌ.....ምወዳትን ሳቁን ሳቅ አለልኝ....እንባዬን ስጠራርግ.....ግንባሬን ስሞኝ ወጣ......ያኔ ነበር ከአባትሽ ከይሳኮር ድብን ያለፍቅር እንደያዘኝ የገባኝ ያኔ ነበር የቱንም ያህል አልበገሬነት ከፍቅር ከናፍቆት እንደማያስመልጥ የገባኝ ......
አምላኬን "ምን ባረግልህ ነው ግን?" እስክል ድረስ ህይወት አመረችብኝ.....
በክብር ተጋባን...የሰርጋችንለት "በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል...የኔ ፍሬ ሽልማቴ አንቺ ነሽ" አንሽካሾከልኝ....እኔ ለእሱ እንደታደልኩት ነው ሚያስበው ግን እኔ ነኝ እሱን የታደልኩት..."ኣ ኣ ሁለታችሁም ናቹ የታደላችሁት" አልኩ ፈርጠም ብዬ...አላመነችልኝም ... የብዙዎች ችግር ነውና እረዳታለው.... ከውስጥ ወደውጭ እንጂ ከውጭ ወደውስጥ እራሳችንን አናውቀውም በራስ መነፅር ማየትን ያህል በሰዎች መነፅር ማየት ቀላል አይሆንም....
"ሆስፒታል በስስት አቅፎሽ በተጨፈኑ አይኖችሽ አልፎ ከልብሽ ጋር ሲያወራ እንባ ከአይኑ ሲያመልጠው ከአልጋዬ ደገፍ እንዳልኩ አየሁት....ዓለሙን በአንቺ አሳየሁት ዓለማችን ሆንሽን....
እናቱ አያትሽ.....ላንቺ ያላት መውደድ ይገርመኛል...."እንዴ እማ እኔምኮ ነፍሴ ድረስ ነው ውድድ ማደርጋት"...."አውቃለው አውቃለው አለችኝ" ለልቤ ሙቀት የሚሰጥ ፈገግታ ፈገግ እያለች....."4ኛ ዓመት ልደትሽን እሷጋር ነበር ያከበርንልሽ ስንመለስ አንቺ ሆዬ አቅፈሻት ኡኡኡ አልሽ....አያትሽ ይችን እድል አጊንታ ነው ሂዱ ልጄን ተዋት ባይሆን ትንሽ ሰንበት ብለን እንመጣለን አለችን.....እኛም የ3 ሰዓት መንገዳችንን መኪና ውስጥ ገብተን ጉዞ ጀመርን እኔ ወንድሜ እና ውዱ ባለቤቴ አባትሽ ሆነን.....
ሲጢጢጥጥጥ የሚል ድምፅ ከሚነዋውጥ ኃይለኛ አዙሪት ጋር የሰማሁት የመጨረሻ ድምፅ ነበር.....
አይኔን በስሱ እየታገልኩ ገለጥኩ "ዶክተር ዶክተር...."...ብዥዥዥዥ አለብኝ ወደነበርኩበት ተመለስኩ ዓለም ቀርታ እኔዉ ምን ብሆን ወደማላውቅበት ማንም ሊያውቀው ወደማይችለው ሄድኩ ዝምምምምም.....
ዓይኔ ተስፋ አትቆርጥም.....ታግላ በሯን ስትከፍት የጠዋት ፀኃይ በክፍሉ የበተነችውን ጨረር ድርግም ክፍት እያረገች ቃኘች ሰውነቴ አላውቅሽም አለኝ....በቅኝቴ ውስጥ ጥቁር በጥቁር የለበሱ ይታዩኛል አእምሮዬም ሲክደኝ አየሁ ዝምምም አለብኝ....."ወይኔ ልጆቼ ወይኔ ህይወት ዓለሞቼ እኔ እያለው?....እናት እንዴት ልጇን ትቀብራለች?!"...".ማበድ ምንድንነው"? በሚያሰኝ ከርዳዳ ቃላቶች ሙክክ ባለ ድምፀት ከእኔ ራቅ ብሎ ካለ የታካሚ አልጋ መተው ከጆሮዬ ተገፈታትረው ገቡ ጆሮዬን የበጣጠሱት የከራደዱት ነው የመሰለኝ ድምፁ ከእጄ መዳፍ በላይ የማውቀው ድምፅ ነው ......ብዥዥዥዥዥዥ....ጭውውውውውውው.....

04.04.202513:37
✨ እነሆ 1k ቤተሰቦቻችን እናመሰግናለን !!
(ልዩ ምስጋናችን ይድረስልን https://t.me/justhoughtsss 👸𝓷𝓪𝓷𝓲 )
ለሃሳብ አስተያየታችሁ @bluessoulmate አድርሱን🤍

02.04.202507:34
✨...ምንድን ነው እንደዚህ መልፈስፈስ? ምንድን ነው እንደዚህ ቶሎ መሸነፍ ?ምንድን ነው የነካችሁ?
ማን ነን እኛ?
ዘመነኞችሽ! እኩዮችሽ!!
ቶሎ መደሰት:ቶሎ ማዘን:ቶሎ መፈንጠዝ:ቶሎ መተከዝ:ወዲያው ስኬት:ወዲያው ደስታ:ወዲያው ተስፋ መቁረጥ እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት ማለት እኔ...እኔ...እኔ...
አቋራጭ...አቋራጭ...አቋራጭ...ከጠፋ ክልትው?! ምንድን ነው እንደዚህ ማነስ?ምንድን ነው እንደዚህ መልፈስፈስ?
እኔ የማውቀው የራሴን ብቻ ነው! ደግሞ ሕይወትን መቀጠል ካልተቻለ መኖር ግዴታ አይደለም።
መኖር ግዴታችን ነው ሁላችንም!!የሞተ ተጎዳ ብሎ ነገር የለም።ሁላችንም ነን የምንጎዳው።ሁላችንም ነን የምንጎድለው።አንዴ መጥተናል የመጣንበትን ሳንጨርስ በራስ ፈቃድ በራስ ቀን መሔድ እፍርታምነት ነው!!
የሚያስከፋን ጠፍቶ:ተስፋ የሚያስቆርጠን አጥተን አይደለም የምንኖረው።መኖር ግዴታችን ስለሆነ ነው።አለበለዚያማ እፍርታምነት ነው!
እፍርታምነት?
አዎን እፍርታምነት!!ኑር እኔም እኖራለሁ ብሎ ጨዋታ ውስጥ ከገቡ በኋላ ጨዋታው ሲከብድ ወይም በግብ ሲመሩ በክፉ በደጉ ያልተለየውን ሰው ሁሉ ደጋፊ የራሱ ጉዳይ ነው ብሎ ከጨዋታ መውጣት እፍርታምነት ነው።
ሕይወት ጨዋታ አይደለማ !!
አዎን ሕይወት ጨዋታ አይደለም!!ሕይወት ሲፈልጉ የሚያቋርጡት ሲያሻ የሚቀጥሉት ጨዋታ አይደለም።ከፈጣሪ ጋር ከሰውም ጋር የሚገቡት ግዴታ አለበት።ራስን ማሰናበት ቀላል ቢመስልም በውስጡ ያለው ፍርሃትና ጭካኔ ግን ሰብዓዊ አይደለም።
በእናት ጨክኖ: በእህት ወንድም ጨክኖ:በወዳጅ ዘመድ ጨክኖ: ከሁሉ በላይ በራስ በክቡር ሰውነት ላይ ጨክኖ የፈሪ ድርጊት ነው።አንቺም ፈሪ ነሽ!!
ፈሪ ለእናቱ..
ለእናት መሆን እንዲህ ነው እንዴ....???
#አጋፋሪ
https://t.me/yeesua_queen
24.04.202508:08
Every night in my dreams
I see you, I feel you,
That is how I know you, go on
Far across the distance
And spaces between us
You have come to show you, go on
Near, far, wherever you are
I believe that the heart does go on
Once more you open the door
And you're here in my heart
And my heart will go on and on
Love can touch us one time
And last for a lifetime
And never let go 'til we're gone
Love was when I loved you
One true time I hold to
In my life we'll always go on
Near, far, wherever you are
I believe that the heart does go on
Once more you open the door
And you're here in my heart
And my heart will go on and on
(Mmhmm)
You're here, there's nothing I fear,
And I know that my heart will go on
We'll stay forever this way
You are safe in my heart
And my heart will go on and on
https://t.me/yeesua_queen
I see you, I feel you,
That is how I know you, go on
Far across the distance
And spaces between us
You have come to show you, go on
Near, far, wherever you are
I believe that the heart does go on
Once more you open the door
And you're here in my heart
And my heart will go on and on
Love can touch us one time
And last for a lifetime
And never let go 'til we're gone
Love was when I loved you
One true time I hold to
In my life we'll always go on
Near, far, wherever you are
I believe that the heart does go on
Once more you open the door
And you're here in my heart
And my heart will go on and on
(Mmhmm)
You're here, there's nothing I fear,
And I know that my heart will go on
We'll stay forever this way
You are safe in my heart
And my heart will go on and on
https://t.me/yeesua_queen
से पुनः पोस्ट किया:
Thoughts

07.04.202513:54
....የቀጠለ
ፀሃይ የዘረጋችውን ብርሃኗን አፋፍሳ እየሄደች ጨለማ መጣሁባችሁ ማለቻው ላይ.....ሲቃዥ እንደነበረ እራሴን ብንን ብዬ ነው ያገኘሁት.....እኔ ስለመሆኔም እጠራጠራለሁ....መንፈሴ ይሆን?.....ደንግጠው ተጠጉኝ...."ተረጋጊ እሺ ብርዬ ብርዬ ተረጋጊ" አቀፈችኝ የባለቤቴ ሁለተኛ እናቱ የእናቱ ወዳጅ, ጓደኛ አብሮአደግ.....ለምንድነው ለምንድን ነው ጥቁር የለበሳችሁት ኤላሜስ ይሳ ይሳዬ ዋጋዬስ....አብረን አልነበርን? እየሄድን እየሄድን አልነበር? መኪናው መኪናው ....የሚሉኝን የሚያረጉኝን አጡ....ከሁሉም አይን ላይ እንባ ይጎርፋል.......እርርርርርርርርርርርርርሪሪሪሪሪ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ.....ሊያስቆሙኝ ሞከሩ አልጋ የያዝኩ ታካሚ ሳልሆን ጎልያድን ነበር የመሰልኩት.....የታሉ የታሉ ወንድምዓለሜ ባለቤቴ ተቅበዘበዝኩ አወራለው የማወራውን ግን አላውቅም.....እኔ ብሄድ እስትንፋስ እፍፍፍ ብዬ አስነሳቸው ይመስል ተቁነጠነጥኩ....እዛ መሆኔ የገደላቸው ይመስል ብርርርር ብሎ ውልቅ ብሎ መሄድ ተመኘው....አደረኩትም ጎንበስ ቀና እያልኩ እየተደፋው የከዳኝ ጉልበቴን ከራሴ የለየኝ መሪር ሀዘን አስገድዶ አስቆመው.....
በሰማይ ይሁን በምድር እንጃ ደረስን የአያትሽ ቤት አልመሰለኝም ነበር ምንም የማላውቀው ሆኖ ታየኝ ነጠላ አዘቅዝቀው የለበሱ እናቶች ዋይታ, ጥቁር ሻርብ የለበሱ እንስቶች, ወንድነታቸው ያልበገረው እንባን በእንስቅስቅ የሚያፈሱ አባቶች, ጋቢ የለበሱ ቤተዘመዶች.....በር ላይ ስብርብር ብዬ ወደኩ በቀኝና ግራ ደግፈው እግሬን እየጎተትኩ ገባሁ.. ሁ...ሁ ለት ሁለት የ አ..አአስ..ስ..የአስክሬ....ን ሳ...ሳ....ሳ...ጥ......"በቃ በቃሽ ተይው ይቅር ይቅር ይቅር..ይቅር....በቃ አብቅቷል እሺ ይቅር አትንገሪኝ "አልኳት እየተነፋረኩ አንገቴ ውስጥ ጥብቅ አርጌ አቅፊያት....እንደህፃን ታቅፋልኝ ሳግ የበዛው ጮክክ ያለ ለቅሶን ተንሰቅስቃ አለቀሰችብኝ ብርሃኔ ማረፊያዬ መፅናኛዬ አለቀሰችብኝ....ልቤ በሀዘን ቁርምትምት ብርድርድ ስትል ተሰማኝ....አሳዘነችኝ....ተንሰፈሰፍኩ....
"ብርዬ እናቴዋዬ በቃን በቃ እሺ ሌላ ጊዜ ደሞ እ?" እንባዋን እየጠራረኩ ተለማመጥኳት...."lifetime ትግል.....መሸነፍ የሌለበት ላለመሸነፍ መጠንከር.....የኔዋ ቡችላ ነገምኮ ዛሬ ነው ለኔ....." አለችኝ ድክመቷን ባደከመ ጥንካሬዋ መቻልን በመውደድ እየፈገገችልኝ....ልክ ናት ያንን አይቼባታለው...የእሷ ትላንት ሁልጊዜዋ ነው....እኔና ትላንቷ ነን ቀለቧ..
በረዥሙ ተነፈሰች..."ህህህኡኡኡኡኡፍፍፍ"....አተነፋፈሷ ሸክምን እንደመዘርገፍ ያለ ነበር ሰላም አለው....ተጋባብኝ....ከአፍታ መረጋጋት በኋላ ቀጠለች...."ሳምንታት ነጎዱ....ሰፈርተኛው ጓደኞቼ አገር ምድሩ መማርያው ሆንኩ"...."እንዴት?" አልኩ ግራ ገብቶኝ...."ሁሉም ሰው አንድ እንደሆነ ምን ጠንካራ ቢሆን ልፍስፍስነትም አብሮት እንዳለ ዘላለም ብርቱ ጠንካራ ከሰው ልጅ እንደሌለ...ሰው ደካማና ብርቱ እንጂ ብርቱ ወይ ደካማ ብቻ እንዳልሆነ....."በቃ አበደች!" እስኪሉ ከራሴ ተለያየው ደቀቅኩ ተናነስኩ በዘመኔ የጠነከርኳቸው ጥንካሬዎቼ ሁሉ ሂሳባቸውን አወራረዱብኝ....
ጥንኩር ሰው የጠነከረውን ያህል ሲሰበርም ስብራቱ ወጌሻውን እስኪሰብር ይደርሳል ......በድኔ ነበር ሚንቀሳቀሰው....በአንድ ወቅት ተሰብስበን ስንጨዋወት በሕይወታችሁ እምነታችሁን የቀየረና ተምራችሁ ያለፋችሁበት እጅግ የሚያስገርማችሁን አጋጣሚ አጫውቱንስኪ ሲባል ጎረቢታችን ተሽቀዳድማ ስለኔ"በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት አንድም ቀን ብርሃንን ከጥንካሬዋ ተናንሳ አያታለው ብዬ ለማሰብኳ አስቤ አላውቅም ሁሌም ደምቃ እንዳበራች የምትኖር እስኪመስለኝ ሁሌም በሁሉም ቦታ ወጋገኗ ያስገርመኝ ነበር ጥንካሬዋን ሳይ እውነት ብርሃንም እንደኛ ሰው ናት እል ነበር....የሰፈራችን ድምቀት ተምሳሌት የኔ የዋህ የደረሰባት ሀዘን ግን ድቅቅ ስብርብር አርጓት ሳይ ተንሰፈሰፍኩ እማደርጋት እገባበት አጣሁ...ሰው ለካ ደካማም ነው አልኩ....እርሱ ምን ይሳነዋል ተመስገን ያም ጊዜ አልፎ እያወራነው ነው ሆይይ ተ አምር " ያለችው ለዚ ነበር....ልክ ናት እኔም ስለራሴ ብቻ ሳይሆን ሰው ስለሚባል ሁሉ ከምን ጊዜውም በላይ የተማርኩበት ጊዜ ነበር
ከዘለገ ዝምታ በኋላ በስሱ ፈገግ አለች...."ቅርፍዝ ፍዝዝ እንዳልኩ ዝምም እንዳልኩ....ከቤታችን ደጅ በዛ ካሉ አፅናኞቻችን ጋር ነበርን.....
ምን ቀና አረገኝ? እንዴት ቀና አልኩ? እንጃ ቀና አልኩ በር..በር ላይ.....አንቺንአየሁ...አ...አ..ን...ቺ...ን....አ...የሁ.... አየው...አየሁሽ...." አለችኝ የስሜን ቃላቶች እንደፊደል ቀስበቀስ እየቆጠረች በሩ ላይ እንባ ያቀረሩ ዓይኖቿን ተክላ
ሚጢጢዬ እራሴን እስካይ ድረስ ታየችኝ... ከዛን በፊትም ይሁን በኋላ ያንን የሚያክል እናቴ ለኔ ያላትን ያስረዳኝ አላገኘሁም.....ሀሴት የታቀፈ እንባ ተስፋ ጉጉት ዳግም መወለድ ያዘለ እንባ ሚያምር አዲስ የተወለደ ልጇን ለመታቀፍ እጅ እንደመዘርጋት ያለ እንስፍስፍት....ልቤ ላይ ቅርፅ አወጣ ምስሏ.....
"አንቺንአየሁ......ባንቺ ሁልነገሬን አበራው.....በአንቺ "ብርሃን ብርሃን ተነሽ" አለኝ መቃብሬን ባንቺ ፈነቀለው መጨረሻ አይደለም አላለቀም አለኝ.....ትኩር ብላ እያየችኝ ቁጭ እሱንኮነው ምትመስዪው.....መከታነትሽ ለሰው ሟችነትሽ ደሞ ኤላዬን....
ተንደርድረሽ ስትጠመጠሚብኝ የጨለመው ዓለሜ ላይ ፀኃይ እጅ እግሯን ዘረጋግታ ስትንጠራራ ተሰማኝ.....ናፍቆት... ፍቅር ...አጥቶ ማግኘት ሲያብሩ...መቼም እንደማታገኝው ተስፋ የቆረጥሽበት ድንገት ላንቺ ሲባል ሲሰጥሽ ያለ አይነት ስሜት, ልብሽን ፍንቅል አርጎ በደስታ ሚያስለቅስ ስጦታ ታውቂያለሽ? እንደዛ ነው የሆንሽልኝ...እኖርለት ዘንድ ምክንያት እንዳለኝ አንቺን አሳየኝ ጥንካሬዬ አደረገልኝ መኖር ጀመርኩ ባንቺ ላንቺ ....ለመኖር ቀመር አንድ አለኜ ሆንሽኝ....አንድ አለኝ አንድ አለሽኝ" አለችኝ በዓይኗ ዓይኔን አልፋ ልቤን የምታይ በሚመስል መውደድ ባደመቀው ሀሴት በወረሰው ስስት በለበሰ እይታ ትኩር ብላ እያየችኝ ድንገት እንባዋ ኩልል አለ.....
"ለልጅ ጥሩ አይደለም ብለው እኔም ከራሴ ጋር ስላልነበርኩ ሌላ ቦታ ወስደውሽ ነበር
በጣም እያለቀስሽ ስታስቸግሪ ከዚ በላይስ ብለው ይዘውሽ መጡ.....
አንቺንአየሁ በአንቺ ውስጥ ሁሉን አየሁ.....አንቺን ማየቴ ድልድይ ሆነኝ አንቺንአየሁ ብዬም ሰየምኩሽ.........ከመቅፅበት ብድግ ብዬ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ጉንጮቿን በእጆቼ ይዤ ግንባሯን ሳምኳት....አልበቃኝም ጥምጥምምም አልኩባት...."ኧረ ልተንፍስበት ልቤን አስጨነቅሻት ልብድካሜ ይነሳ ደሞ...." ደማቅ ሳቅ ረፍት ያለው ሳቅ ተሳሳቅን(እህ ልብድካሟ ልብምቷም እኔዉ ነኛ)
#በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ላጡና ሰዋቸውን ላሳጣቸው ሁሉ መታሰቢያ ይሁንልኝ
✍️ጎዳዳዬ
https://t.me/justhoughtsss

04.04.202513:30

02.04.202507:33
दिखाया गया 1 - 24 का 129
अधिक कार्यक्षमता अनलॉक करने के लिए लॉगिन करें।