Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Инсайдер UA
Инсайдер UA
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Инсайдер UA
Инсайдер UA
Thoughts avatar

Thoughts

ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው ፥ እናንተስ ጎራ አትሉም?
comment for the writer : @nhymn
discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk
Tiktok: https://www.tiktok.com/@the_author_nani?_t=8pGCAO5NksY&_r=1
Since: Dec-10-2022
TGlist रेटिंग
0
0
प्रकारसार्वजनिक
सत्यापन
असत्यापित
विश्वसनीयता
अविश्वसनीय
स्थानУзбекістан
भाषाअन्य
चैनल निर्माण की तिथिMay 09, 2025
TGlist में जोड़ा गया
Aug 22, 2024
संलग्न समूह

समूह "Thoughts" में नवीनतम पोस्ट

(አጉል ታዛቢ ለመሆን ወይ ደግሞ አቃቂር ለማውጣት ያልሆነ እይታ መሆኑ ይታወቅልኝ)

ነገሮቻችን በሙሉ ገለባ እየሆኑ ነው። የማዳበርያ ውጤት ትውልድ መሆናችን በየፊልሞቻችን እና በየሙዚቃችን አደባባይ ወጥቶ ደጋግመን ተዋርደናል።

አሁን ግን ትኩረቴን እየሳበው ያለው የየቴሌቭዥን ማስታወቂያዎቻችን ነገር ነው። ለምን ቢሉ አስር አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ የነበሩ ማስታወቂያዎችን ማየት በቂ ነው። በደንብ የተለፋባቸው መሆኑን ዜማዎቻቸው ከአፋችን ሳይጠፉ መቆየታቸው ምስክር ነው።

የአሁኖቹ ግን እንኳን ዜማቸው ከአፋችን ላይጠፋ ቀርቶ እንዴት ጤነኛ ሰው ይሄንን ሀሳብ ብሎ አስቦ ተዋናዮቹም ተቀብለው ማስታወቂያውን ሰሩት ተብሎ የሚያተዛዝብ ነው

ይሄንን ሁሉ ያስባለኝ ለብዙ ወራት በየቲቪ ቻናል ላይ እየተደጋገመ የሚታየው የዳይፐር ማስታወቂያ ነው። የዳይፐር ማስታወቂያዎች ከመብዛታቸው የተነሳ የሰውን ትኩረት ለማግኘት በልጦ ለመገኘት ከመጣጣር ተመሳሳይ ነገር ያሳዩናል።

ከሁሉም ግን የገረመኝ የአንዱ ዳይፐር ማስታወቂያ ነው ሲጀምር አባትየው ዳይፐሩን እየመረጠ ጋሪው ላይ ሲያደርግ ሁለት የተቀባቡ ቀጫጫ ሴቶች እየተሯሯጡ ይመጡና ስለዳይፐር እውቀቱ እየተሻሙ ይጠይቁታል እሱም በፈገግታ ይመልሳል

ማለት?! ምን ማለት ነው?! are they flirting with a married guy and a father?!

ከዛ እናትየው ልጇን አቅፋ ትመጣና እሷም ስለዳይፐሩ ማብራሪያ ትሰጣለች። ከዛ ሁለቱ ሴቶች ወደ አባትየው ዞረው ስለዳይፐር እውቀቱ አድንቀውት ይሄዳሉ።

ማለት እነሱ ሲያሳዩ የነበረው ባህሪ ትክክል ስለሆነ ነው ማለት ነው ለወራት እየተደጋገመ እየታየ ያለው?!

✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss
हटा दिया गया17.05.202500:02
से पुनः पोस्ट किया:
Naivety✍️ avatar
Naivety✍️
Remember

I love it when I hear people say to their friends or loved ones like "I wanna try my very best, I want to hold onto this bond till the very end, till I have the energy ."
The way I understand this statement is like: it's hard sometimes to maintain any bond and they acknowledge that feeling (the feeling that not all things are everlasting/permanent) but they are willing to try, to hold onto till the very last.....

And blessed are those who have these kind of people in their relationship/kinship/friendship.

And blessed are even more those who are those people who acknowledge and wanna try their best.

Since they've sought men when they could go for other and chase other things. Let me tell you one thing, at the end of the day everything you wished, pursued and dreamed of will perish except for the people who will be there for you even on your death bed. Those people are your money, your joy, worthy to try for and all your blessing will be in them too.

You ain't called to be alone.



✍Benon/Me
For my Ethiopian readers...."ሰው የተጠማውን ይፅፋል።" Check it out, it works with every writer.
हटा दिया गया17.05.202500:02
से पुनः पोस्ट किया:
ዳን ŦËŁŁ avatar
ዳን ŦËŁŁ
📚ርዕስ: አይቤን ማን ወሰደው (who moved my cheese?)
📝ድርሰት:- ዶክትር ስፔንሰር ጆንሰን
ትርጉም:- በላይ ደስታ
📜ይዘት:- one of the most successful business books ever
📆የመጀመሪያ ዕትም:- 2009
📖የገፅ ብዛት:- በአማረኛ 70ገፅ : በ English 67
📌አዘጋጅ:- kassa belay
हटा दिया गया17.05.202500:02
से पुनः पोस्ट किया:
DAILY THOUGHTS (የዕለተ ዕለት ሀሳቦች) avatar
DAILY THOUGHTS (የዕለተ ዕለት ሀሳቦች)
ሥነ ውበትና ስሜት

የየትኛውንም የሥነ ጥበብ ውጤት ውበት ለማጣጣም አዕምሮአችን የሚገኝበት ድባብ /ስሜት (Mood/ Emotion) ወሳኝነት አለው። ኃይለኛ ጉንፋን ይዞህ ምርጥ ሥዕል ወይም ኪነ ሕንፃ እየተመለከትክ ምላሽህ ምንም ላይሆን ይችላል። ጭራሹኑ የጥበብ ሥራውን ያለኃጢአቱ ልትጠላው ሁሉ ትችላለህ። ምክንያቱም አዕምሮ ሰላሙን ሲነፈግ ሥነ ውበት ከቅንጦትነት አያልፍም። ከመደበኛ የአርት ቴራፒ አቅም በላይ የሆነ ሐዘንና ድባቴ አለ። በአንፃሩ ሎተሪ በደረሰህ ሰሞን በአዛቦት ቀናት የሚያስጠላህ ፎቅ ውብ ሆኖ ሊከሰትልህ ይችላል። ምክንያቱም አንጎልህ የሎተሪ ዕድለኛነት ፌሽታህን ለአስቀያሚውም ፎቅ ሊያጋራው (Mood sharing/ extension) ይችላልና። አንዳንድ ሰዎች ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ደስታ ሲያጋጥማቸው አላፊ አግዳሚውን ያለ ልዩነት እያቀፉ ሲስሟቸው አስተውላችሁ ይሆናል። ለዚህም ነው የሥነ ውበት ፈላስፎች የሰው ልጆች ለጥበብ ሥራዎች የሚሰጡትን ግብረ መልስ ከነበሩበት ስሜት ጋር አቆራኝተው የሚያጠኑት። እና ምን ለማለት መሰላችሁ ? አካባቢን ከማስዋብና በሚያማምሩ ዲዛይኖች ከማሸብረቃችን በፊት በሀገሪቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ይሰሩ፤ ያው አበባውንም ይሁን ሕንፃውን የማታ ማታ የምናጣጥመው በአዕምሮአችን አይደል? አዕምሮ ሰላሙን ካጣ በዙሪያችን ሺህ የውበት ትንግርት ቢኮለኮል በምናችን እናጣጥማዋለን ? ለዚህም ነው ጠቢቡ ሰለሞን በመፅሐፈ ምሳሌ "Singing cheerful songs to a person with a heavy heart is like taking someone’s coat in cold weather or pouring vinegar in a wound." በማለት ምክሩን የለገሰው! እኛም እንላለን፦ Do not sing cheerful songs to a heavy heart!

©
ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ
हटा दिया गया17.05.202500:02
से पुनः पोस्ट किया:
ዳና🐾 avatar
ዳና🐾
መንግሥት የኛ ሀገር ሀኪሞች ስራ ካቆሙ ከውጭ እንደሚያመጣ ሰማን ። ይሄ ጥሩ ነው በውነቱ። ችግሩ አንድ ፓኪስታናዊ ሀኪም የኢትዮጵያን ታማሚ በምንም ሁኔታ አያክምም እያልን ነው።

ላስረዳ ፦ ከህክምና ቀዳሚ ነገሮች patient history ነው። ይሄ ፓኪስታናዊ " መላ ሰውነቴን አርገፍግፎ እንደገና ወገቤን ይከረክርና ደሞ አሁንም አለድልዶ ይነሳብኛል። ከብሽሽቴ አንስቶ እስከ ቁርበቴ ውርር ያደርገኝና ጉሮሮዬን ጠምዝዞ ደፍቶ ከጣለኝ በኋላ ሰቅስቆ አንስቶ ይቀውረኛል" ከሚለው የታማሚ ሂስትሪ ላይ ገብቶት መድሃኒት አዞ ማዳን ከቻለ ይሞክር🫶😂😂

via fb
"And the human race is filled with passion. And medicine, law, business, engineering, these are noble pursuits and necessary to sustain life. But poetry, beauty, romance, love, these are what we stay alive for."


Robin williams በdead poets society film(የኔ የምን ጊዜም ምርጥ ፊልም) ላይ ከላይ ያለውን ንግግር ተናግሮ ነበር። ይሄንን ነገር ካየሁበት ጊዜ ጀምሮ የart እና የሌላውን የስራ ዘርፍ መጣጣም ከዚህ በተሻለ የገለፀው አላየሁም። ምክንያቱም ስለህክምና እና ስለምህንድስና አስፈላጊነት ምንም ንግግርም አያስፈልግም።

ኪነ ጥበብን በተመለከተ ግን የቅንጦት እና የስራፈትነት ማሳያ ማድረግ ማቆም እንደሚያስፈልግ ከላይ ያለው ጥቅስ ይናገራል። ኪነ ጥበብ የነፍስ መተነፈሻ ተፈጥሯዊ እፅ ስለሆነች ከነፍስ ማራቅ የማይቻል ነው።

እንደውም ኪነ ጥበብን ለማድነቅ መታደል ራሱ ትልቅ ፀጋ ነው ምክንያቱም እስኪ አስቡት በደንብ የተመጠነ ግጥም በደንብ በጎረነነ ድምፅ እየተገጠመ ከጀርባው ለስላሳ ዋሽንት ሲንፎለፎል አብሮ በሀሴት መፍሰስ የማይችል ነፍስ እንዴት ያሳዝናል?!

ከዛ ደግሞ ከኪነ ጥበብም specifically ፅሁፍን በተመለከተ ከአንባቢነት ተሻግሮ የፀሀፊነትን ፀጋ መላበስ የማይፈልግ አንባቢ ብዛቱ ጥቂት ነው። በተወለደው ጥበብ የተደሰተ ሰው ጥበቡን እሱ ቢሆን የወለደው ደስታው እጥፍ ድርብ የሚሆን እየመሰለው አብዛኛው አንባቢ ፀሀፊ መሆንን ይመኛል።

መመኘት ብቻ ሳይሆን አብዛኛው የመጀመሪያ ፅሁፉን ይሞክራል። ከዛ ግን ጥሩውንም መጥፎውንም አስተያየት ችሎ መቆየት ለሁሉም አይደለምና ከሚዘልቀው የሚተወው ሁሉም ነው ማለት ይቻላል።

ይሄ መልዕክት ግን ራሳቸውን መፅሀፋቸውን ሲያስመርቁ ለሚታያቸው ለአንባቢዎቻቸው ሲፈርሙላቸው ለሚያልሙ ሰዎች ነው:- መቼም እንዳታቆሙ ማንም አትችሉም ቢሏችሁ ማንም የት ልትደርሱ ነው ቢሏችሁ እንዳትሰሙ ምክንያቱም ይሄ የእናንተ ህልም ነው ለእናንተ የታያችሁ እንዲታያቸው አትጠብቁ።

እኔም ይሄ መከረኛ ህልም የሚያንቀዠቅዠኝ አንድ ነፍስ ነኝ። ራሴን እዛ መድረክ ላይ እስለዋለሁ ከብዙ ሺህ አንባቢ ፊት መፅሀፌን ሳስመርቅ ደጋግሜ ራሴን አስተኝቼበታለሁ። ግን ይሄ የማይጨበጥ ጉም ቢጤ ህልም ነበር። ምክንያቱም ደሀ ሀገር ላይ አንድ ሰው እየሰራ ወይ እየተማረ እንዴት ስኬታማ ፀሀፊ ይሆናል?! ነበረ የሁሉም ሰው አስተያየት እናም እንደው genie መጥቶ ቢያሳካልኝ ብዬ የምመኘው ምኞት ነበረ።

ከዛ ግን ዛሬ ጥበብ ሹክ ብላኝ እየተክለፈለፍኩ ብሄራዊ ቲያትር ከተምኩ። ከዛ የማላውቀው ስሜት ወረረኝ ምክንያቱም ይሄ እውነታ ነው እዚህ ሰዎች ህልማቸውን እየኖሩ ነው እየፃፉ ነው ፅፈውም እያሳተሙ ነው። ከዚ በላይ ምን የሚያነቃቃ እና የሚያበረታታ ነገር አለ?!

አንድ አዳራሽ ውስጥ ከአለማየሁ ገላጋይ እና ከኤፍሬም ስዩም ጋር መገኘት እንደምን ያለ ነው?! ከአድሀኖም ምትኩ ጋር መነጋገርስ?! በቴለቪዥን እና በኢንተርኔት የምጎበኛቸውን ሰዎች እንደዚህ በጥቂት ሜትሮች ርቀት ማየት ምንም የሚመስለኝ አይመስለኝም ነበር።

ከዛ ግን ሁሉም ሆነ ትንሿ ልቤን ፈንጠዝያ ሞላት ለካ ቅዠት አልነበረም ጉምም አልነበረም ሊሆን የሚችል ነገር ነው ተጨባጭ ነገር ነው ለካ አልኩ

እና እናንተም ሂዱ እና በቅርብ እዩአቸው ከዛ እነሱን መሆን ቅዠት ብቻ አይሆንም።


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
से पुनः पोस्ट किया:
...ነጠብጣብ ✨💙 avatar
...ነጠብጣብ ✨💙
✨✨...........ከትላንት ይልቅ ዛሬ ክፉ ነው። አይነኬ ንጽህናዎች ፈሰዋል። ፍቅራችን በዛሬ ዘመን ቋንቋ "ላይፍ" ተብሎ ይቀጫል። የምናገባት ሴት ወይም ለባልነት የተመረጠው ሙሽራ ዘንድ የሚቀርብ የጨዋ ደንብ ጨርሰናል። አያዛልቅ ፍቅር ጀምረን ሁሉን ህይወት ባጨርነው፣ ሁሉን ዳገት ቧጠጥነው። ትዳር መቆሸሽ እስኪመስለን ድረስ......እውነት በልጅነት ተቋጨ! ክብር በልጅነት ተሸኘ። እኛ.....በአባቶቻችን ልክ፣ በ እናቶቻችን ልብ አልተሰራንም።!

https://t.me/yeesua_queen
से पुनः पोस्ट किया:
ጥንቅሻ✍🏼🦋 avatar
ጥንቅሻ✍🏼🦋
አስተናጋጁ የተቀደደ ጫማዉን ሳይ አይቶኝ አፈረ፣
ስላስተናገደኝ ደህና ሰዉ መስዬዉ፣
የልቤን መቦርጨቅ በምን’ነዉ ማሳየዉ፣
से पुनः पोस्ट किया:
የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw avatar
የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw
‹‹እናትነት ይከብዳል›› ይላሉ፡፡

ታውቃለች።

በአይኖቿ አይታለች፤ በጆሮዋ ሰምታለች፡፡


ትስማማለች፡፡


ግን ደግሞ እናት ከመሆን በላይ የሚከበድ ነገር እንዳለም ታውቃለች፡፡


እናት ለመሆን ጥሮ፣ ሞክሮ፣ ታግሎ አለመቻል
እናትንን አልሞ፣
እናት ለመሆን ፀልዮ፣
አይንን በአይን ለማየት ተስሎ በእንጥልጥል መቅረት፡፡


ለአመታት ያጎበጣትና ያሳቀቃት፣ውስጥ ውስጡን የበላት እውነት ነውና፣ ይህች ሴት ከእናትነት በላይ ያልተሳካ የእናትነት ምኞት የበለጠ መክበዱን ከልቧ ታውቃለች፡፡

መልካም የእናቶች ቀን ዛሬም እናት ለመሆን ጓጉተው ለሚጠብቁ ሴቶች!
እናንተ እያላችሁ እኔ በመቶ follower ብቻ መቅረት አለብኝ🙇‍♀

रिकॉर्ड

17.05.202523:59
7.8Kसदस्य
29.03.202514:12
2400उद्धरण सूचकांक
19.04.202513:56
3.3Kप्रति पोस्ट औसत दृश्य
27.02.202510:53
1.5Kप्रति विज्ञापन पोस्ट औसत दृश्य
05.02.202523:59
266.67%ER
11.09.202423:59
50.02%ERR

विकास

सदस्य
उद्धरण सूचकांक
एक पोस्ट का औसत दृश्य
एक विज्ञापन पोस्ट का औसत दृश्य
ER
ERR
OCT '24JAN '25APR '25

Thoughts के लोकप्रिय पोस्ट

हटा दिया गया06.05.202521:32
से पुनः पोस्ट किया:
እንማር avatar
እንማር
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። አንዱ አጠገቡ ላለው ጓደኛው እንዲህ አለው። "ቄሱ ቆንጆ ሚስት አለቻቸው። እንዋደዳለን። አሁን እሷ ጋ ልሄድ ነው። አንተ ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን በወሬ ያዝልኝ። ከመምጣትህ በፊት አስቀድመህ ደውልልኝ አደራ" አለው።

ጓደኛው ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን አስቁሞ የባጥ የቆጡን ያወራላቸው ጀመር። ቄሱም በሰውዬው የተዘበራረቀ ንግግር ግራ ገባቸውና ምን እንደፈለገ በቁጣ ጠየቁት።

ሰውዬም የሃጢአተኝነት ስሜት ተሰማውና ዕውነቱን ነገራቸው "ይቅር ይበሉኝ አባቴ! ጓደኛዬ ከእርስዎ ሚስት ጋር ሊተኛ ሄዶ እኔ እርስዎን በወሬ እንድይዝሎት ነግሮኝ ነው" ብሎ እግራቸው ላይ ወደቀ።

ቄሱም ፈጥነው አነሱትና እንዲህ አሉት "አንተ ሞኝ! አሁኑኑ ወደ ሚስትህ ፈጥነህ ሂድ! እኔ ሚስቴ ከሞተች 5 ዓመት አልፏታል
"....... !🙆‍♂️

ምን ልልክ ፈልጌ ነው ላጤነት ይለምልም 🖐


Tesfaye Hailemariam
📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
हटा दिया गया06.05.202521:32
से पुनः पोस्ट किया:
Open reading 👐 avatar
Open reading 👐
29.04.202506:40
አንዲት ሴት ፕሮፈሰር ስለ "አንድ ወንድ ብዙ ሚስቶችን ማግባት" በተሰኘ አርእስት በአንድ አካባቢ ለሚኖሩ ሴቶች እና ወንዶች ገለፃ እንድታደርግ ትጋበዛለች።

ፕሮፈሰሯ የተጠቀሰውን አርእስት ገለፃ ለማድረግ እራሷ ነበረ የመረጠችው።

ፕሮፈሰሯ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ሲያገባ ለሴት ልጅ ያለውን ጠቀሜታ በዝርዝር አስረዳች።

ሴቶችም ይህን የጋብቻ ልምድ ተቀብለው ቢፈፅሙት ያለውን ጠቀሜታ አስተማረች።

ጥቅሙ ለእራሷ ለሴቷ እንደሆነና መቃወም እንደሌለባት አዳራሽ ውስጥ ላሉት ታዳሚዎች አስረግጣ ገለፃ አደረገች።

በአዳራሹ የፕሮፈሰሯን ገለፃ ስትከታተል የነበረች አንዲት ሴት እጇን አውጥታ ለፕሮፈሰሯ  እንዲህ በማለት አስትያየት ትሰጣለች ።

"በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ ስላደረግሽልን አመሰገናለሁ!"

"ከባለቤትሽ ጋር አንቺ ሳታውቂ ፣ አብረሸው እያለሽ  ከተጋባን አሁን  አራት አመታችን ነው ፣ መንታ ልጆችም አለን አለቻት።"

ፕሮፌሰሯ ከሴትየዋ ይህንን ስትሰማ  በአዳራሹ ውስጥ እራሷን ስታ ወደቀች ፣ሆስፒታልም ተወሰደች።

ፕሮፌሰሯ ሆስፒታል ከአልጋ ላይ ሆና ስትነቃ ያቺ አዳራሽ ውስጥ አስተያየት የሰጣቻት ሴት ከአልጋዋ አጠገብ ሆና አየቻት ።

ሴትየዋ  ለፕሮፌሰሯ እንዲህ አለቻት:-

"ባለቤትሽን እንኳን ላገባው በአይኔም አይቼው አላውቅውም ይህን ያልኩት ልፈትንሽ ነበረ፤ ፈተናውን ወድቀሻል።"

"ለሌላ ግዜ ስለ አንድ አስተሳሰብ ተቀበሉና አድርጉት ብለሽ  ሌሎችን ስታስተምሪ ፣መጀመሪያ አንቺ ራስሽ አምነሽና ፣ ተቀብለሽ  መሆን አለበት" በማለት ለፕሮፈሰሯ ነገረቻት።

◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆

                   @open_reading1
                   @open_reading1
हटा दिया गया17.05.202500:02
से पुनः पोस्ट किया:
ዳና🐾 avatar
ዳና🐾
13.05.202521:08
መንግሥት የኛ ሀገር ሀኪሞች ስራ ካቆሙ ከውጭ እንደሚያመጣ ሰማን ። ይሄ ጥሩ ነው በውነቱ። ችግሩ አንድ ፓኪስታናዊ ሀኪም የኢትዮጵያን ታማሚ በምንም ሁኔታ አያክምም እያልን ነው።

ላስረዳ ፦ ከህክምና ቀዳሚ ነገሮች patient history ነው። ይሄ ፓኪስታናዊ " መላ ሰውነቴን አርገፍግፎ እንደገና ወገቤን ይከረክርና ደሞ አሁንም አለድልዶ ይነሳብኛል። ከብሽሽቴ አንስቶ እስከ ቁርበቴ ውርር ያደርገኝና ጉሮሮዬን ጠምዝዞ ደፍቶ ከጣለኝ በኋላ ሰቅስቆ አንስቶ ይቀውረኛል" ከሚለው የታማሚ ሂስትሪ ላይ ገብቶት መድሃኒት አዞ ማዳን ከቻለ ይሞክር🫶😂😂

via fb
हटा दिया गया06.05.202521:32
से पुनः पोस्ट किया:
𝗕𝗘𝗠𝗡𝗘𝗧 ✍️ avatar
𝗕𝗘𝗠𝗡𝗘𝗧 ✍️
ሁለት ሰዎች በጠና ታመው በአንድ ክፍል ውስጥ ተኝተዋል።

አንደኛው ታማሚ ሳንባው የቋጠረው ውኃ ለማድረቅ ሲባል ብዙውን ሰዓት ቁጭ እንዲል ተደርጓል።

ሌላኛው ደግሞ በጀርባው ተኝቶ ነው ሕክምናውን የሚያገኘው በፍፁም መንቀሳቀስ አይችልም።

ሁለቱ ታካሚዎች በቆይታቸው ተግባብተዋል ስለ ሥራቸው፣ስለቤተሰባቸው፣ስለኑሮ ፣ስለ ሀገር፣ስለወታደር ቤት ብቻ ብዙ ነገር አውግተዋል።

ብዙውን ግዜ ቁጭ የሚለው ታካሚ ሁልግዜም በጀርባው ለተኛው እና መንቀሳቀስ ለማይችለው ታካሚ ጓደኛው ስለውጪው እንዲህ እያለ ይነግረዋል....

በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ትንሽዬ የሚያምር ሐይቅ ይታየኛል፣ በሐይቅ ላይ ዳክዬዎች ይዋኛሉ፣ሕፃናትም በወረቀት የሠሩትን መርከብ በሐይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ፣ፍቅረኛሞች በአንድ እጃቸው ተያይዘው በሌላው አበባ ይዘው በፍቅር እየተያዩ ብዙ ግዜያቸውን አብረው ያሳልፋሉ.

ከሐይቁ ባሻገር በቅርብ ርቀት ላይ በውስጧ ለመኖር የምታጓጓ አንዲት ውብ ከተማ ትታየኛለች.... እያለ ይነግረው ነበር በጀርባው የተኛውም ታካሚ ሁሉንም ነገር በዓይነ ህሊናው እየሳለ ለመረዳት ይሞክራል

ከቀናት በኃላ ያ ብዙውን ግዜ ቁጭ የሚለው ታካሚ ሕይወቱ ያልፋል በጀርባው የሚተኛውም ታካሚ መንቀሳቀስ ሲጀምር ጓደኛው ይነግረው የነበረው ነገር በመስኮቱ ለመመልከት ሲሞክር የሆስፒታሉ ሌላ ግንብ በትንሽ ርቀት ብቻ ነበር የሚታየው....

በጓደኛው ተግባር በጣም ተገረመ ለካ ጓደኛው የማይታየውን እንደታየው እያደረገ የሚነግረው እርሱን በተስፋ ለማኖር እና ውስጡን አጠንክሮ ከበሽታው ቶሎ እንዲያገግም ነበር

ወዳጄ ነገሮች ላንተ ባይሆኑ፣ እንደማይሆንልህ ቢገባህም ለሌላ ሰው ተስፋ እና ሕይወት መሆን ትችላለህ እና በፍፁም በራስህ ተስፋ አትቁረጥ።

ባንተ መልካምነት አንድ ነፍስ እንኳን ማዳን ከቻልክ እንዳንተ ጀግና የለም
06.05.202517:12
የሆስፒታል ወግ...

የህፃናት ክፍል ተመድበን ካርድ ስናገላብጥ "አሳጥረው ሲፅፉት ከባድ ነገር አይመስልም እንደውም የሰው ስም ነው የሚመስለው አይደል?" አለቺኝ ዶክተሮቹ የፃፉት ካርድ ላይ አልነበብ ያለውን ፅሁፋቸውን ለማንበብ እየሞከረች

አየሁት የበሽታ አይነት የሚለው ላይ "SAM" ይላል severe acute malnutrition ማለት ነው በምግብ እጥረት በጣም የቀነጨረ ህፃን ማለት ነው።

"ቆይ ግን SAM ላለበት ሰው ምንድነው የሚደረገው?!" አለችው አጠገቧ ላለው ነርስ

"ያው acute malnutrition ከሆነ ቶሎ ቶሎ ምግብ እና ፈሳሽ እንሰጠዋለን በጣም severe ደረጃ ላይ ከደረሰ ግን ምግብ ትንሽ ትንሽ ነው የሚሰጠው" አላት እጁን በአልኮል እያፀዳ

"እንዴ እንደውም በደንብ የሚያስፈልገው ለባሰበት አይደለ እንዴ ጭራሽ ትንሽ እንሰጠዋለን?!" አለች ወገቧን ይዛ

"አየሽ ሰውነትሽ አንድን ነገር በጣም ፈልጎ ሲያጣ ያለሱ መኖርን መለማመድ ይጀምራል ስለዚህ ያ በጣም የተፈለገው ነገር ጠላት ይሆናል ሰውነትሽ ያለሱ ለመኖር ሲጣጣር አሰራሩ ይቀየራል ምግብን በአግባቡ ከመጠቀም በትንሽ ምግብ መኖር መለማመድ ይጀምራል

ስለዚህ ብዙ ምግብ ሲያገኝ እንደባዕድ ነገር ይቆጥረው እና ለማውጣት ሲጨነቅ ያልተጠበቀ ጉዳት ሊያመጣበት ይችላል አሁን ገባሽ" አላት

"ዋው ወይ ጉድ ሰውነታችን እኮ ሁሌም ነው የሚደንቀኝ" አለችው እና ወደ እኔ ዞራ "አይገርምም" አለቺኝ

"ቀላል እንደውም ከዘመኔ ትውልድ ጋር ተመሳሰለብኝ" አልኳት ራሴን በግርምት እየነቀነቅኩ ተመሳስሎው ገርሞኝ

"ረሀብ ላይ ስለሆንን ብለሽ ነው?!" አለች ግራ መጋባቷ ፊቷ ላይ እየተስተዋለ

"አይደለም ስለ አካላዊ ርሀብ እና መቀንጨር አይደለም እኔ የማወራው ስለ ፍቅርን እንደ ምግብ ስለተራበው ልባችን ነው የፆታዊ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አይነት ፍቅር ነው የምልሽ እና በጣም የሚያስፈልገን ፍቅር ሆኖ acute የሆነውን ፍቅር ብናገኝ የምናልፍበትን stage አልፈን

አሁን severe love-deficit ሆነን ብቻችን መኖር ብቻችንን መደሰት ብቻችንን ማዘን ብቻችንን ከሀዘን መውጣት እየተለማመድን ሳለ ልባችን "ሰውን መውደድ" የነበረው መደበኛ ስራዋን ትታ "ብቻ መኖርን" ለመደች

አሁን ጠብታ ፍቅር ሲቀርበን ልባችን ይገፋዋል ምክንያቱም መራራቅን እንጂ መቀራረብን ረስተናል ፍቅር እንዴት መቀበል እንዳለብን እንዴት መስጠት እንዳለብን ባጠቃላይ እንዴት ፍቅርን handle ማድረግ እንዳለብን ረስተናል

ስለዚህ እንደ SAM ታካሚ ፍቅርን በጥቂት በጥቂቱ መለማመድ አለብን ምክንያቱም በብዙ የመጣ ፍቅር ለእኛ ጠላት ነው እንዴት እንደሚያዝ አናውቅበትም ለዛ እኮ ነው የቀረበንን በሙሉ ሰበብ እየፈለግን ስንርቅ የኖርነው አይገርምም መመሳሰሉ" አልኳት ጥርስ ጥርስ ሆኜ

"ለዛ እኮ ነው ነርሲንግን ትተሽ ፍልስፍና ተማሪ ስልሽ የነበረው አሁን ነይ ለልጆቹ መድሀኒታቸውን እንስጣቸው በረሀብ ሳያልቁ" አለች

የእኛንስ ልብ ማነው በትንሽ በትንሽ በትንሹ ፍቅር የሚያስለምደው??


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
से पुनः पोस्ट किया:
የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw avatar
የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw
11.05.202514:41
‹‹እናትነት ይከብዳል›› ይላሉ፡፡

ታውቃለች።

በአይኖቿ አይታለች፤ በጆሮዋ ሰምታለች፡፡


ትስማማለች፡፡


ግን ደግሞ እናት ከመሆን በላይ የሚከበድ ነገር እንዳለም ታውቃለች፡፡


እናት ለመሆን ጥሮ፣ ሞክሮ፣ ታግሎ አለመቻል
እናትንን አልሞ፣
እናት ለመሆን ፀልዮ፣
አይንን በአይን ለማየት ተስሎ በእንጥልጥል መቅረት፡፡


ለአመታት ያጎበጣትና ያሳቀቃት፣ውስጥ ውስጡን የበላት እውነት ነውና፣ ይህች ሴት ከእናትነት በላይ ያልተሳካ የእናትነት ምኞት የበለጠ መክበዱን ከልቧ ታውቃለች፡፡

መልካም የእናቶች ቀን ዛሬም እናት ለመሆን ጓጉተው ለሚጠብቁ ሴቶች!
हटा दिया गया06.05.202521:32
02.05.202507:21
ታምናለህ?
:
“ውስኪን ከብርጭቆ
መጎንጨት አንስቶ
ጭኗን ከገለጠች…
ማውራት እንቶፈንቶ ፤
አያድርስ በደሉ !
የሀብታም ሰው ግፉ
ተናግሯል መጽሐፉ”
ብሎ የሚታዘብ…
አረቄ ቤት ያለ …
የዛ ድሀ ምኞት ፤
:
በሴቶች ታጅቦ...
ውስኪ መጠጣት ነው
እ’ሱም ገንዘብ ኖሮት።

(ሚካኤል አ)
से पुनः पोस्ट किया:
ጥንቅሻ✍🏼🦋 avatar
ጥንቅሻ✍🏼🦋
11.05.202518:32
አስተናጋጁ የተቀደደ ጫማዉን ሳይ አይቶኝ አፈረ፣
ስላስተናገደኝ ደህና ሰዉ መስዬዉ፣
የልቤን መቦርጨቅ በምን’ነዉ ማሳየዉ፣
हटा दिया गया06.05.202521:32
से पुनः पोस्ट किया:
ዳን ŦËŁŁ avatar
ዳን ŦËŁŁ
30.04.202509:03
📚ርዕስ:- ሾተላዩ ሰላይ • Eye Of The Needle
📝ደራሲ ኬን ፌሎት
👤ተርጓሚ ፦ ማሞ ውድነህ
📖የገፅ ብዛት:- 405
የተለያዩ አዋርዶችን ያሸነፈ በፊልምና በድራማ መልክም ተሰርቶ ለመታየት የበቃ ድንቅ የስለላ መፅሐፍ!
06.05.202518:42
እኔ እንደሚመስለኝ የኛ case severe acute malnutrition (SAM) ሳይሆን pica ይመስለኛል። pica የምንለው ለሰውነታችን ጠቃሚ ያልሆኑ የምግብነት ባሕሪ የሌላቸው ወይም ጎጂ የሆኑ ቁሶችን መመገብ ነው እንደ ወረቀት አፈር or so on .. አብዛኛዎቻችን ለፍቅር ልባችንን የመክፈት ችግር ሳይሆን ፍቅር ላልሆነ ነገር፣ የነፍሳችንን ክፍተት ለማይሞላልን ሰው ልባችንን መክፈት ነው then we will be hurt then we will no longer believe in love
से पुनः पोस्ट किया:
የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw avatar
የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw
22.04.202507:04
8123

<<<<<>>>>>>



ይሄኛውን ቴክስት የላከችልኝ ረቡዕ ነበር፡፡ በስራ ሰዓት ፡፡


‹‹ሄይ  ቆንጂት…! እኔ የምልሽ፣  ሴቭ ዘ ችልደርን HR ውስጥ ያለ ሰው ታውቂያለሽ እንዴ? ››



ደምበኛ ሰላምታ የለ፣  ናፍቀሽኛል የለ፣ ደህና ነሽ ወይ የለ።

‹‹ሄይ ቆንጂት›› ያለችውም ለምትፈልገው ነገር ስታመቻቸኝ ነው፡፡




በረጅሙ ተነፈስኩ፡፡



ለስሙ ጓደኛሞች ነን፡፡


ለመጨረሻ ጊዜ ካወራን ግን ሁለት ወር ያልፈናል፡፡  ያኔም የሆነ ሰው ስልክ ቁጥር ፈልጋ ነው የደወለችልኝ፡፡አፍሪካ ህብረት የሚሰራ ሰው፡፡


…..ከዚያ በፊት ደግሞ የጻፈችልኝ ቴክስት፣


  “ስሚማ ፍቅር፣  ያ ዩ ኤን ዲፒ የሚሰራው ሰውዬ ስልክ  አለሽ እንዴ? ያ እንደውም ዶሎ አዶ ፕሮጀክት ማኔጀር የነበረው?”  የሚል ነበር፡፡



ከዚያ በፊት ደግሞ አንዱን ቅዳሜ ጠዋት ምን ብላ ጽፋልኝ ነበር…?


አዎ…

“ሄይ….በናትሽ ያ የአጎትሽ ልጅ፣ ቴሌ የሚሰራው… አሁንም እዛ ነው እንዴ? ሲምካርዴ እኮ ድጋሚ ተዘጋብኝ”


እንዴት ነሽ፣ እንዴት አደርሽ እንኳን ሳትል፡፡




አንዱን ቀን ደሞ ለእኩለ ሌሊት ትንሽ ሲቀረው ደወለችና፣ በጣም ለምትፈልገው ስራ ልታስገባው የጻፈችውን ‹‹ሞቲቬሽን ሌተር›› ቶሎ ብዬ እንዳስተካክልላት ላከችልኝ፡፡ 



ወሊሶ ነበርኩ። ከስራ ድካም አረፍ ልበል ብዬ ቤተሰብ ጋር፡፡
ግን ጭንቀትዋን አየሁና፣   ‹‹እሺ ጠዋት አይቼ አስተካክልልሻለሁ›› ብያት ስልኩን ዘጋሁ፡፡



ማለዳ፣ ገና በቅጡ ሳይነጋ ደውላ ፣

“እ እንዴት አረግሽልኝ?” አለችኝ።



የናፈቀችኝ እናቴ ቤተክርስትያን አብሬያት እንድሄድ እየለመነችኝ ለእሷ ብዬ ቤት ቀረሁ፡፡




ይህ ከሆነ ከሶስት ሳምንት በኋላ ስትጠፋብኝ፣
‹‹እሺ፣ ያ ጉዳይ እንዴት ሆነልሽ..ተሳካ?›› ብዬ ስለስራው ስጠይቃት ሌላ ነገር ሳትለኝ፣ በብልጭልጭ መብራት ውስጥ የምትደንስ ትንሽዬ ልጅ "ጂ አይ ኤፍ "ብቻ ልካ ደግሞ እንደ ልማዷ ጥርቅም አድርጋ ዘጋችኝ፡፡



አንዴ ደግሞ ለራሴ እንኳን የምሳሳለትን ሀበሻ ቀሚሴን ለአክስቷ ልጅ ሰርግ ልትለብሰው አውሺን አለችኝ፡፡ 


አይሆንም ብላት
አጃቢ ነኝ ..
ደህና ነገር መልበስ አለብኝ…
ስሞትልሽ…ስከተፍልሽ

ምናምን ብላ አለቃቀሰችብኝ፡፡

ንዝንዝ ስታደርገኝ፣



‹‹ስሚ ! በእቁብ ነው የገዛሁት፡፡ አንድ ነገር ብታደርጊው የመጨረሻችን ነው፡፡ ደግሞ በስርአት ራስሽ አጥበሽ ነው የምትመልሺው›› ብዬ እያንገራገረኩ ሰጠኋት፡፡



እሺ እሺ ብላ፣ ምላ ተገዝታ ወሰደችው፡፡




በነጋታው አጥቤ አመጣለሁ እንዳላለችኝ በስንት ልመና ከአስር ቀን በኋላ የመለሰችልኝ በአሮጌ ኩርቱ ፌስታል ውስጥ ጎስጉሳው ነበር፡፡


አላጠበችውም፡፡
ላቧና ሽቶዋ ያበላሸውን ቦታ አይቼ ከንዴቴ ሳላገግም ጥለቱ ላይ አዋዜ መፍሰሱን ሳይ ጨስኩ፡፡ 



ያደረገችውን ነገር ስለምታውቅ ጥፍት አለች፡፡




ከብዙ ጊዜ በኋላ እንዲሁ ጉዷን ልይ እስቲ፣ ዝም ብዬ ሰላም ልበላት ብዬ ደወልኩላት።

ያው ስለማንገናኝ። ሁለቴ ጠራ፤ ስልኳን አላነሳችም።



ነገሩን ረስቼው፣ ከሶስት ቀን በኃላ ቴክስት ላከች፡፡



‹‹ ይቅርታ ብታይ አዲሱ ቦታ ስራ ብዝት ብሎብኛል። እኔ የምልሽ…የጥላ ስፓ ስልክ አለሽ አይደል? ዌብሳይታቸው ላይ ያለው አይሰራም፡፡ ካለሽ በናትሽ ቶሎ ላኪልኝ፡፡ ጀርባዬ ቆስሎልሻል፡፡  ዛሬውኑ ማሳጅ መሄድ አለብኝ።›› ይላል፡፡




እንደ ጓደኛ ለሆነ ጉዳይ ካላስፈለኳት አብረን ምሳ በልተን አናውቅም።
እሷን በሆነ መልኩ የማይጠቅማት ከሆነ ሻይ ቡና እንኳን አንባባልም።





ስንት አመት ሳባብላት ኖሬ፣ የእሷ ነገር የቆረጠልኝ ግን የሚከተለው ነገር ሲፈጠር ነው፡፡

እናቴ በጠና ታማ አዲሳባ አምጥቻት ሆስፒታል ገብታ ነበር፡፡



አንዱን ቀን ብቸኝነትና መከፋት ሲያሸንፉኝ ስለመታመሟ ፌስቡክ ላይ ፖስት አደረግኩ፡፡



ለራሴም በገረመኝ ፍጥነት ወዲያው ቴክስት አደረገችና፣


“ወይኔ የእኔ ቆንጆ ሶሪ…ማዘር ምን ሆና ነው…?እስኪ ማታ እደውልልሽና አወራሻለሁ።” አለች።


ሰው ባጣሁ ሰአት ሰው ልትሆን ነው ብዬ እንደ ሞኝ ጠበቅኳት፡፡


እሷ እቴ፡፡


አልደወለችም።



ከ አራት ወይ አምስት ቀን በኃላ ሌላ ቴክስት ላከች፡፡


“ፍቅርዬ፣ እማዬ እንዴት ሆነች?  ተሻላት አይደል? በነገርሽ ላይ ባለፈው ፖስት ስታደርጊ ላንሴት ናት ብለሽ ነበር አይደል ? እስኪ ላንሴቶች ደህና neurosurgeon ካላቸው ጠይቂልኝ በናትሽ፡፡ አጎቴ ታሟል፡፡”




ስያሜ ልሰጠው ያልቻልኩት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ዝም፣ ጭጭ አልኩ፡፡

ዝግት- ቁልፍ አደረግኳት፡፡


---

ይሄው ዛሬ፣ በረቡዕ ምድር፣ በስራ ሰአት፣ አይኗን በጨው እጥብ አድርጋ፣ ሌላ ውለታ ፈልጋ፣ የተፈጠረው ነገር ሁሉ እንዳልተፈጠረ፣ የሰራችኝን ነገር ሁሉ እንዳልሰራችኝ፣

  ‹‹ሄይ  ቆንጂት…! እኔ የምልሽ፣  ሴቭ ዘ ቺልደርን HR ውስጥ ያለ ሰው ታውቂያለሽ እንዴ? ›› ብላ ቴክስት ላከችልኝ፡፡




ወዲያው አልመለስኩላትም፡፡
ለቡና ወጣሁ፡፡
ከባልደረቦቼ ጋር ምሳ በላሁ፡፡
እህቴ ጋር ደወልኩ፡፡ እናቴ መድሃኒቷን መውሰዷን አረጋገጥኩ፡፡


ከዚያ ግን መለስኩላት፣


‹‹አንቺ ግን በቃ ማፈር ተውሽ አይደል….?ለማንኛውም እስቲ ዛሬ እንኳን አፋላጊዎችን ጠይቂ፡፡  8123 መሰለኝ ቁጥራቸው›› ብዬ፡፡


አልመለሰችልኝም፡፡

በዚያው ተቆራርጠን ቀረን፡፡ 

ለነገሩ እኔ አልቆርጥ አልኩ እንጂ እንደ ጓደኛ ከተቆራረጥን እኮ ቆየን፡፡
से पुनः पोस्ट किया:
ታዖርያ avatar
ታዖርያ
05.05.202510:30
ሰው ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ሊሳለም ወደ አንድ አቅጣጫ ይዘማል። ቀኑም እሁድ ስለሆነ ህፃን አዋቂው ሁሉ ሀጫ በረዶ መስሎ ነጠላውን አጥፍቶ ወደ ትልቅ ድግስ የሚጓዝ ይመስለል።
......ለመጨረሻ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የሄደበትን አያስታውሰውም ።
ዛሬ ግን መጠጊያ ቢያጣ፤ የታመነበት ሀብትና ጉልበት እንደ ጉም ከፊቱ ተኖ ቢቀር፤ ወዳጄ ብሎ ሲከበው የኖረ ሰው ሁሉ ሲያጣ ሲነጣ ጊዜ ባላየ ሲያልፉት ፤ የሚሸሸግበት ቦታ አሰኘው። ይህን በሀሳቡ እያመላለሰ ሳያውቀው ተጉዞ ነበር እራሱን ደጀሰላሙ ላይ ያገኘው።
ከሀሳቡ ያነቃው የዲያቆኑ ዜማ ነበር.....
.'
ፃዑዑዑዑዑዑ ንዑሰ ክርሰቲያን

....
ዲያቆኑ'
ተንስኡ ለጸሎት

...
ህዝቡ  ተቀብሎ '
እግዚኦ ተሣሃለነ

....
ለመጸለይ ፈልጓል ግን ምን ማለት እንዳለበት አያውቅም። ዝም ብሎ አጥሩን ተደግፎ ወጪው ወራጁን አተኩሮ ይመለከታል ። ህፃናት ይሯሯጣሉ ይስቃሉ ይጮታሉ እነሱን አያየ ፈገግ አለ ሳያውቀው ።
በዚህ መሀል ነበር ዲያቆኑ በቅዳሴው ላይ የተናገራት ሀይለቃል ጆሮውን አልፍ ልቡን ሰርስራ የገባችው።
እንባው  በጉንጮቹ መንታ መንታ ሆነው ሲወርዱ ፤ ከልቡ ላይ የከበደው ሲቀለው ታወቀው።  ለምን ያህል ሰዓት እንኳን እንደቆየ ሳያስተውለው በሰላም ግቡ ተብሎ ህዝቡ ወደ ቤቱ መመለስ ሲጀምር እሱም እንባውን ጠራርጎ መመለስ ጀመረ። በልቡም የሰማትን ቃል መላልሶ እያሰበ ነበር ።
'በልቡ መጠራጠር ያሰበ ቢኖር ይመን

Abu ✍✍
https://t.me/taoriia
23.04.202516:27
ተኝቼ ነበር። መተኛት ሁሉ እንቅልፍ መወሰድ ነው ያለው ማነው?! እንዲሁ ስገላበጥ ሮቤል ለሁለተኛ ጊዜ ሲደውልልኝ ስልኬን ሰማሁት።

አንዴ ደውሎ ካላነሳሁ ማንሳት አለመፈለጌን ይረዳ ነበር እኮ ደጋግሞ የሚደውለው የሚፈልገው ነገር ሲኖር ስለሆነ ነው።

የማስተዋውቅህ ሰው አለ ቶሎ ና ነው ያለኝ ልደቱ መሆኑን እንደተጨማሪ ነገር ነው ነግሮኝ ስልኩን የዘጋው።

ልብስ መልበስ እና ተዘጋጅቶ መውጣት እንደድሮ አስጨናቂ አይደለም። የትኛው ያምርብኛል የቱ ይሆነኛል ብሎ ጭንቀት እድሜ ብረት ለመግፋት ድራሹ ጠፍቷል። ልብሴን ሁሉ ከመስቀያው ነው እስኪባል ድረስ መስቀያው ላይ ሰርቻለሁ።

ቆሜ በራሴ ስደነቅ ሮቤል ደግሞ ደወለ እና እንግዶቹ ሁሉ መጥተው እኔ ብቻ እንደቀረሁ ነገረኝ።

የህዝብ ሀብት ከሆነ ሰው ጋር ጓደኛ መሆን ጦሱ ይሄ ነው ብዬ እየተነጫነጭኩ ስደርስ ቤቱ ሞልቷል። የጠበኩት ምን እንደነበረ ባላውቅም ስገባ ሮቤልም ሆነ "እንግዶቹ" መምጣቴን ያስተዋለ ሰው አለመኖሩ ብዙ ቅር አላለኝም።

ከእሷ በስተቀር...

አረማመዴን አጥንታ ስትጨርስ ወደጓደኛዋ ዞራ የሆነ ነገር አለቻት። ያለእቅዴ አስፈገገቺኝ። በደረስኩበት ትኩረት ማግኘት ብርቄ አይደለም። የእሷ አኳኋን ግን ከረሜላ እንደተሰጠው ህፃን አስቦረቀኝ።

ከእሷ በስተቀር የተዘጋጀው ድግስ እዚ ግባ የሚባል አልነበረም።ሮቤል እሷን ለማስተዋወቅ እንዳስመጣኝ ነጋሪ አላስፈለገኝም። ግን መጠንቀቅ ነበረብኝ ገና እንዳየኋት የሞተው የስዕል ሀሞቴ እንደተነሳሳ ማወቅ የለባትም።

ሰዎች ስዕልን መውደድ ስለ ስዕል ብቻ ይመስላቸዋል። ስዕል ግን ስለሚሳለው ነገር አድናቆትም ጭምር ነው። በቀለም አስፍሮ ይዞ መሄድም ነው። እንጂማ ለምን በያዘችው ብርጭቆ ዙርያ ያሉትን ቀጫጭን አጫጭር ጣቶቿን ቤት ገብቼ እንዳይጠፉብኝ ደጋግሜ በምናቤ ሳልኳቸው?

አይኖቿን በደንብ ልሸምድድ ብዬ ሳያት ተገጣጠምን እያየቺኝ ነበር። የሰውነቴ አካላቶች ተባብረው ስራ አቁመው ጥንካሬው ሁሉ አይኗን ለመቋቋም ውሎ ነበር። አስተያየቷ ሀይል አለው የሀምራዊ ቀለም አይነት ስበት በጣም ሳይለፋ ማሰገድ የሚችል ሀይል ደረቴ ጋር መጨናነቅ ሲሰማኝ ነው መተንፈስ አቁሜ እንደነበር ያወቅኩት።

አይኗን ቶሎ አሽሽታ የተጋነነ "አልተዘበራረቅኩም አይደል" ሁለመናዋን አስተካከለች። ሰው እንዴት እኩል ሁለት ተቃራኒ ስሜት ይሰማዋል?! የኔ ሁኔታ ይቆይና የእሷን አይኔን መሸሽ ሳይ እንዴት ለኩሩ ልቤ ደስታ ብቻ አይሰጠውም ለምን በደንብ እንድታየኝ ተመኘሁ መርበትበቷ ለምን አናደደኝ?! እንጃ...

ብቻ የሀሳቤ አቅጣጫ ስላላማረኝ ወደእሷው ስዕል ተመለስኩ። ፀጉሯን ለመሳል ብዙ ጭረት ማስፈለጉ አይቀርም በግድየለሽነት የተዝረከረከው እሷን አሳምሯታል እኮ እኔን በኋላ ሊያቸግረኝ ከዛ ደግሞ ገርበብ ያሉት አይኖቿን እና የሚያሳሱ ከንፈሮቿን አይኔን ጨፍኜ እግሬ ላይ በጣቴ ለመሳል እየሞከርኩ እያለ ሮቤል መጠጥ ይዞልኝ መጣ

"እንኳን ተወለድክ ይቅር ሰላምታ እንኳን አይገባኝም" አለ አጠገቤ እየተቀመጠ "ምን ቸገረኝ እኔ አንተን ለማግኘት አልመጣሁ ባይሆን አንድ ጊዜ ብትዞር እኮ ፀጉሯን አየው ነበር" አልኩት

"አጅሬ ማን እንደሆነች ሳልነግርህ ጭራሽ እንደምትስላት ወስነሀል" ብሎ ረጅም ሳቅ ሳቀ

"አሁን አትረብሸኝ" እስኪ ስለው የድሮ ጓደኞቻችን ቀስ በቀስ ከበቡን ጓደኝነታችን ከእኔ ይልቅ ለእሱ ስለሚያደላ ብዙ ምቾት አልሰጠኝም ነበረ።

ከዛ ግን ሳባ "ኤርሚ አሁንም ትስላለህ እንዴ?!" አለቺኝ በቃ ከዛ በኋላ ማን ይቻለኝ የለበስኩትም ኮት ጠበበኝ ሸሚዙም ወደክንዴ ተሰበሰበ። ረጅሙን መግለጫ ሰጠኋቸው።

ደጋግማ ሰርቃ ስታየኝ በአይኔ ዳርቻ አይቻታለሁ። "ሄጄ ላውራት?! ግን ልታወራኝ ባትፈልግስ?!" በሚል ሰጣገባ ውስጥ ስታገል ራሴን አገኘሁት። የውሳኔ ሰው አልነበርኩ እንዴ?

ድምጿ ምን አይነት ይሆን እንደ ሀምራዊ መግነጢሳዊ ወይስ እንደ ፈዛዛ ሮዝ ለስላሳ?! ብቻ ላወራት ይገባል ብዬ ስዞር ሮቤል ከጀርባዋ የሆነ ነገር ሲላት አየሁት ፊቷ ሲቀላ ሳየው ደነገጥኩ።

የመጨረሻው ክፍል እስኪለቀቅ ድረስ react እያደረግን😄



✍ናኒ




https://t.me/justhoughtsss
08.05.202511:11
"አርፍጃለሁ መሰል" የተባለ ግጥም
በልድያ ተፅፎ በራሷ በልድያ ይነበባል
እና video ይለቀቅ የምትሉ✋
से पुनः पोस्ट किया:
ጥርኝ ጥበብ avatar
ጥርኝ ጥበብ
18.04.202508:46
እኛ ያመጣናቸው እነርሱ በለጡን

እየጎተንት ወደ ቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ይዘነው ገባን።የገዛንለትን ነጠላ ዘርግቶ ለመልበስ ግራ ሲጋባ ከሶስታችን መሀከል አንድኛው ተጠግቶ በአንገቱ ስል አመሳቅሎ አጣፋለትና  
"እንዲህ አይሰገድም እሽ
        እሽ
ምግብስ በልተሀል
   ኧረ አልበላሁም
አዎ ምን ሆነሀላ ውሀ ራሱ ከጠጣህ ነገር ተበላሽቷል በቃ
    አይ እንደዚያ አላደረኩም"     ይቁነጠነጣል...በመሀል 1000 ሰግደን ለመውጣት የምንገፋፋው እኛ ቆመን ሳለ እርሱ ስድስት ሰባት ጊዜ ከፍ ዝቅ ብሎ ጉልበቱ እንደተብረከረከ ሰው በግንባሩ መሬቱን ተደግፎት ቀረ። እንግድህ ላለመነሳት ምክንያት እየፈጠረ መሆኑ ነው ቀና ማለት እንደከበደው ሰው ቁና ቁና ሲተነፍስ ይሰማናል።...

"ቃል እንደጓደኛ ይሄንን ልጅ ምንም መላ አናበጅለትም ማለት ነው"አለ ቢታንያ ወደ አንገቴ ተጠግቶ ... እኔ ደግሞ የአናንያን ህይወት እየሄደ ካለበት ቁልቁለት ለመመለስ መሞከር ውሀን ሽቅብ የማፍሰስ ያህል ድካሙ ብቻ ነው የሚታየኝ።  ለጓደኛ በዚህ ልክ
መጠን ዝሎ መኖር ቢያሳፍርም...  "ሱስ እኮ ነው እየበዛ በጣም ብሶበታል የት እናስጠምቀው በእናትህ"  የየግል አስተያየታችንን ለጣጥፈን ስናበቃ ካጎነበሰበት በርከክ ብሎ አንገቱን ደፍቶ ነጠላውን አናቱ ላይ ጎዝጉዞ ተቀመጠ።

ለካ መቆም ቢያፍር ነው እንባ አርግዞ የወደቀው ድንገት ቀና ሲል ደንግጠን ተያየን በስጋው ላይ እንደተቆጣ የሚያሳብቁት የደም ስሮች ከወደግንባሩ እንድህ ተከታትለው ለመሰለፍ ምን አነቃቃቸው ከምኔው ፊቱ በእምባ ረጠበ አያስቀናም ልታፀድቁ በገሰፃችሁት ሰው ተሰብካችሁ እንደመሄድ ያለ ስብከት ወደየት ይገኛል።

የእኛ ፀፀት አርባአንድ ኪራላይሶን ብለን ከአይናችን ካልወረደ ለእርሱ በሰባት ዝቅ ማለት በዘነበለት እምባ እንዴት አይቀናም አምላኩ በልቡ አደባባይ በታተመለት ሰው ቁኑ ሀቁም ይሄው ነው።

በልምድ መመላለስ የፀና ሐዋርያም አንዳንድ ጊዜ ሊያፀድቅ ይዞ ከመጣው ወንበዴ ተምሮ ይሄዳል።...

ወዮ የሠው ስግደት ቆጥረን ለተመለስን 😢😢😢

ፀሀፊ ✍ ጌታሁን ደጉ

እንኳን አደረሳችሁ
अधिक कार्यक्षमता अनलॉक करने के लिए लॉगिन करें।