Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
እንማር avatar
እንማር
እንማር avatar
እንማር
09.05.202520:22
📣💥 ዛሬ የምጋብዛችሁ ቻናል ከ10 በላይ ምሁራን ያሉበት ድንቅ ቻናል ነው።

በየቀኑ በማይጠገቡ ምክሮቻቸው እየመከሩ ለቀጣዩ የህይወት ገፆችህ መሰረት ለመሆን ዝግጁ ሆነው እየጠበቁህ ይገኛሉ። ከእናንተ የሚጠበቀው "እለወጣለው" ብሎ ማመን ብቻ ነው።

ይቀለቀሉ
Join Now👇
@mikre_aimro
@mikre_aimro
@mikre_aimro
✔️ አክሽን ፊልም ያን ያህል አይደለሁም — በነገራችን ላይ ቃሉን ሲተረጉሙት በድርጊት የተሞላ የሚሉት ብዙ ምቾት አይሰጠኝም። ማንኛውም ፊልም በድርጊት የተሞላ ነው። ያን ያህል የአክሽን ፊልም ተመልካች አይደለሁም። የLuc Besson ፊልሞች ግን ያዝናኑኛል። ድብድቡን ለታሪክ እንጂ ታሪኩን ለድብድብ አያስገዛም።

ፈረንሳዊ ነው። ከ50 በላይ ፊልሞች ውስጥ እጁ አለበት። ፊልሞቹ ውስብስብ አይደሉም፣ ግን በጣም አዝናኝ ናቸው። በጣም የተወደዱ፦

✅Leon/ The Professional
✅Taken
✅Lucy
✅The Fifth Element

🌟 አክሽን ቢሆኑም ግን የሉክ ቤሰንን ፊልሞች አላልፍም።

ለመጀመሪያ ግዜ ያየሁት የሉክ ቤሰን ፊልም Leon or The Professional ነው።

🌟 ጎረቤታሞች ናቸው―እሱ hitman(ቅጥር ነፍሰገዳይ) ነው፣ እሷ የ12 አመት ልጅ ናት። ሁለቱም ብቸኞች ናቸው። መላ ቤተሰቧ በወንጀለኛው የDEA ፖሊስ አለቃ ከተገደሉባት በኋላ ያስጠጋታል። ያልተለመደ ጓደኝነት መሰረቱ። እሱ የመሳሪያ አጠቃቀም ያስተምራታል፤ እሷ ምግብ ታበስልለታለች። እሱ የአካል ብቃት ስልጠና ይሰጣታል፤ እሷ ቤቱን ታፀዳለታለች። እሱ እንደ ልጅ ይንከባከባታል፤ እሷ ማንበብና መፃፍ ታስተምረዋለች።

🌟 ቤተሰቦቿ ጋጠወጥ ነበሩ። ማቲልዳ የምትወደው የአራት አመት ታናሽ ወንድሟን ብቻ ነበር። ለመበቀል የምትዘጋጀውም የሱን ደም ብቻ ነበር።

🌟 አሁን ላይ አክሽን ፊልሞች እምብዛም ብሆንም ይሄ ታሪክ ልብ አለው። ከፊልሙ በጣም የሰረፀብኝ ትእይንትም ይሄ በምስሉ ላይ የሚታየው ነው። ማቲልዳ እና ሊዎን ቤት ለመቀየር በጎዳናው ላይ ይራመዳሉ። ከተማው ጭር ብሏል። ፀጥ ረጭ ያለ ድባብ ነው። ሊዎን ከፊት ሲቀድም ማቲልዳ ከጎኑ ድክድክ እያለች ትከተለዋለች። እሱ ሳጥኑን እሷ የአበባ ተክሎቿን ይዛለች። ሳጥኑ በድን ነው። አትክልቱ ህያው ነው። ሳጥኑ ውስጥ ሞት አለ። የላስቲክ አፈሩ ላይ ሕይወት በቅሏል። የሆነ የሕይወት እና የሞት መንታነት የሚያንፀባርቅ ይመስለኛል።

አንዳንድ ነገሮች ስለ Leon/The Professional

✔️፨ ጌሪ ኦልድማን villain(ክፉ ሰው) ሆኖ ሲተውን ይዋጣለታል
፨ ፊልሙ የናታሊ ፖርትማን የመጀመሪያ ፊልሟ ነው። ገፀባህሪዋ አጫሽ ብትሆንም ናታሊ አንድም ሲጋራ አልነካችም
፨ የፈረንሳዊው ሉክ ቤሰን ሰቃይ ፊልም ይሄ ይመስለኛል



አክሽን ፊልም እምብዛም ነኝ በቂ የኋላ ታሪክ ሲኖረው ግን አላልፍም። ከአክሽን ፊልም ዳይሬክተሮች ፈረንሳዊው ሉክ ቤሰን ከድብድቡ ባሻገር ትልቅ ርእስ ይዞ ይነሳል። ለምሳሌ Leon: The Professional, Taken and Lucy.

✔️ጌታዬ! ተራ የድብድብ ፊልም እንዳይመስልህ። ግዙፍ ቁም ነገር ላይ ነው የሚያጠነጥነው። ለምሳሌ፦

ዝግመተ-ለውጥ
—ንቃተ-ህሊና
—የተፈጥሮ ባህሪ ወዘተ ወዘተ


✔️ሴራው እንዲህ ነው፦

✔️ሉሲ ትባላለች። የምትኖረው ታይፔ፣ ታይዋን ነው። ያለ ፈቃዷ አደገኛ እጽ አስተላላፊ ትሆናለች። ይሁን እንጂ የተሸከመችው እጽ ወደ ሰውነቷ ሰርጎ ገብቶ፣ የአእምሮዋን እምቅ ጉልበት ነጻ አውጥቶ ከሰው አእምሮ በላይ የሆነ ድንቅ ሃይል ይሰጣታል።

✔️አንድ በሳይንስ ያልተረጋገጠ ነገር ግን በስፋት የሚታመንበት ነገር/myth አለ። ሰዎች ከአእምሯቸው የሚጠቀሙት 10% ብቻ ነው። ችግሩ we haven't been able to access the rest 90%. But, what if we could?

100% አእምሯችንን ብንጠቀምስ?
✅—ወደ ኢነርጁ እንቀየራለን
✅—በሁሉም ቦታ እንገኛለን ወዘተ ወዘተ


✔️የሉሲ አእምሮ ብቃት እየጨመረ ሲመጣ የተለያዩ ችሎታዎችን እያዳበረች ትመጣለች telepathy, telekinesis, mental time travel, heightened perception, and the ability to control her own body at will.

✔️በዚህ የተነሳ ከፍተኛ የአካል ብቃት ታዳብራለች። ተጋጣሚዎቿን በቀላሉ ትረታለች። እውቀቷ እየደረጀ ሲመጣ ዩኒቨርስን፣ ህልውናን በጥልቀት ትረዳለች። ከሰው ስሜት እየራቀች፤ ከሰው ውሱንነት እየተላቀቀች ትመጣለች። ወደ መለኮት ትጠጋለች። በቦታና በግዜ አትወሰንም።

✔️ሞርጋን ፍሪማን የሚመጣው እዚህ ጋር ነው። ሞርጋን ፕሮፌሰር ሳሙኤል ኖርማን የሚባል ተመራማሪ—ብልህ ሽማግሌ—ነው። ሉሲ እያለፈችበት ያለው ለውጥ ከፕሮፌሰሩ ምርምር ጋር ስለሚገጥም ፕሮፌሰሩ ስለ ሁኔታው እንዲያስረዷት ግንኙነት ትፈጥራለች።

✔️በፕሮፌሰሩ ላብ ውስጥ ሉሲ የእጹን ተጨማሪ መጠኖች ትወስዳለች። ከግዜና ቦታ ውሱንነት ተላቃ ከአስትሮፊታከስ ሉሲ ጋር ትገናኛለች (Hence, the name Lucy) በተጨማሪ ወደ ሁሉም መጀመሪያ ሄዳ ቢግ ባንግን በገዛ አይኖቿ ትመለከታለች።

✔️ታዲያ ፊልሙ አንኳር፣ አንኳር የሆኑ የፍልስፍናዊ ጥያቄዎች ቢያነሳም the 10% mythን የሚደግፍ በመሆኑ ክፉኛ ተተችቷል። ያም ሆነ ይህ የፊልሙ ፈጠራ እና ምናብ የሚደነቅ ነው። What if the myth were true? ያንን ልብወለድ— ሰዎች ያን ያህል ብቃት ቢኖራቸው ኖሮ የሚለውን እስከ ጥግ ድረስ ወስዶ፣ ለአይን በሚማርክ መልኩ ያሳያል።

✅️ሌለው ደግሞ የፊልሙ ቁምነገር ፈጣን መሆኑ ነው። ታሪኩ ቶሎ ቶሎ ይቀያየራል፤ ውጥረቱ በፍጥነት እየደረጀ ይመጣል። ትእይንቶቹ ቶሎ ቶሎ ይለዋወጣሉ። ለተመልካቹ ለሃሳብ ፋታ አይሰጥም። ልክ ፊልሙን አይተህ እንደጨረስክ ግን የሃሳብ ጎርፍ ያጥለቀልቅሃል፤ የጥያቄ መአት ይግተለትልብሃል። የሉክ ቤሰን ጥበብ ይሄ ነው—በቀላል ታሪክና ሴራ ያዝናናሃል፤ በጥልቅ ፍልስፍናናዊ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ያሳስብሃል። ሁለቱም አለው—ተዝናኖትም ቁምነገርም።

✅️የፊልሙም ሲኒማቶግራፊ የሚደነቅ ነው። ሳይንስ ፊክሽን ፊልም ሲሰራ፣ ፊልምሰሪው በምናቡ ለሚፈጥራቸው ነገሮች በተራቀቀ ቴክኖሎጂ የሚመሩ ቪዥዋል ኢፌክትስ ያስፈልጉታል። የሉሲን ለውጥ ለአይን በሚማርክ መንገድ ለስክሪን አብቅተውታል።

✅️ፊልሙ ከሚያነሳቸው ሃሳቦች መካከል intelligence, existence and mortality ይገኛሉ።. ሰዎች የመረዳት አቅማችን ውሱን ነው፤ ሟቾች ነን። ሉሲስ? እንደ ሉሲ የመሆን እምቅ አቅም/potential አለን?

✅️የተነሳበትን ሳይንሳዊ ጽንሰሃሳብ ትክክልነት እንተወውና
ፊልሙ በአጭሩ ሶስት አስደናቂ አንኳር ነገሮች አሉት፦

የአክሽን ሲኩዌንሱ ያዝናናል
ፍልስፍናዊ ሃሳቦቹ ያመራምራሉ
ቪዥዋል ኢፌክቱ ቀልብ ይይዛል

ሌላ ደግሞ ተመሳሳይ ጉዳይ የያዘ ፊልም አለ—Limitless.ፈልጋችሁ እዩት።



➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
06.05.202517:47
📗📗#የመፅሀፉ_ርዕስ ➠በቀለኛው ሰላይ
                             ( Deep lie )
📝ትርጉም ፦
     👨‍💼 ሙሉጌታ ይፍሩ
     🤵‍♂ ሚሊዬን ግዛው

ይህ መፅሀፍ .. ለፍቅር ሲባል ከአላማ ውጪ የሚደረግ ጉዞን፣ ለገንዘብ ሲባል የጣምራ ሰላይነት ሚናን፣ ከደረሰባቸው በደል የተነሳ የበቀል ፅዋን የመጎንጨት እና የተጠበቀው እንዳልተጠበቀ የሆኑና ያልሆኑ ድርጊቶች እየተፈፀሙ፣ የአከባቢን ቀልብ በመግዛት
ከመጀመርያ ገፅ አንስቶ ሚስጥሩ እስከሚፈታ የመጨረሻው ገፅ ድረስ በጉጉት የሚነበብ መፅሀፍ ነው።


#መልካም_ንባብ_ጓደኞቼ 😊

➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
➡️@Enmare198
06.05.202511:22
⇲⇲ 📖 ✘ የተራቡ ጭኖች ✘ ⇲ ⇲
❏ ❐ ✅️✅️✅️❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒✅️

❈ ደራሲ ፦ ንጋቱ ክፍሌ


➠➠➠➠ ሼር ያድርጉ!! ➠➠➠➠

         💠ይህ መጽሐፍ ሽብርና አክራሪነት ከኢራን ተነስቶ ያቆጠቆጠባት የሲኦል ሞት የበረታባት፣ የሴቶች ጭቆና ጣራ የነካበት፣ የፍትወተ ስጋ የእንስሳት አይነት የሚፈጸምባት፣ የስለላ መረብ የተዘረጋባት፣ ሐሺሽና ጫት በገፍ የሚወሰዱባት፣ የጎሳ ጦርነት ስለሚያምሳት ሲኦላዊት አገር ነው፡፡

💠በሚያስደንቅ ሁኔታ ሰላዮቹ መረጃን ለማግኘት ሲሉ በእምነታቸው ክልክል የሆነውን የወሲብ አይነት በባለስልጣኖች ሚስቶች ላይ በመፈጸምና በማባበል የሚፈልጉትን ከማግኘታቸውም በላይ በሌላ እቅዳቸው ማስፈጸሚያነት ይገፏፏቸዋል፡፡ ያሳኩት ይሆን?

✅️መጽሐፉ የሶማሌ፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የየመንና የሌሎች አረብ ሀገሮች ሰላዮች የሚራኮቱበት፡፡ ሁሉም : አላማቸውን ለማስፈጸም የሚጥሩበት፤ አሸባሪነትንና _ የአክራሪነት ጥንስስ ተወልዶ አድጎ ሕዝቦቹን _ የሚገርፍበት፤ ነፍስ መጠፋፋት፤ መከዳዳት፣ ፍቅርን ፍለጋ የሴቶች የስሜት ጥማት መዋተትን በቀል ሴራ ጭፍጨፋ የሚካሄድባት ከመጀመሪያው ገጽ አንስቶ ልብን በማንጠልጠል መጨረሻውን _ ለማወቅ ትንፋሽን ይዞ የሚጓዝ ሁሉን ያካተተመጽሐፍ

✅️@Enmare1988
✅️✅️@Enmare1988
" ያኔ ፡ አሳ እያጠመድኩ በምሸጥበት ጊዜ ይህች ሴት ከኔ ጋር ነበረች
አንዳንዴ በመረቤ ውስጥ አንድም አሳ ሳይገባ ቀርቶ ባዶ ኪሴን ወደቤት ስመጣ ፡ በፍቅር አይን እያየችኝ ፡ አይዞህ ይሄ ሁሉ ነገር አንድ ቀን ይለወጣል አታስብ እያለች ፡ የቤት ወጭ ከምሰጣት ላይ የተረፋትን ብር ጥቅልል አድርጋ በእጄ አስጨብጣኝ ፡ ሻይ ቡና ብለህ ና ትለኛለች ።
......
አምላክ ብቻዬን እንዳልተወኝ አውቅ ዘንድ ከኔ ጋር እንድትሆን የላካት ይህች ሴት አብራኝ ባትሆን ኖሮ ፡ ዛሬ የደረስኩበት ደረጃ አልደርስም ነበር " ይላል ካርሎስ ባካ ስለ ባለቤቱና ስለ ሶስት ልጆቹ እናት Shayira Santiago ሲናገር
.....
ከአመታት በኋላ. .
ዛሬ ላይ ያ በኮሎምቢያ ጎዳናዎች ላይ የሚሸጥ አሳ ይዞ ፡ ይዞር የነበረው ይህ ሰው ፡ የአሳ መረቡን ጥሎ የእግር ኳሱን አለም ከተቀላቀለ ከጥቂት አመታት በኋላ 24 ሚሊየን ፓውንድ ሀብት በባንክ ያከማቸ በተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች የተጫወተና ፡ በአሁኑ ወቅት የአትሌቲኮ ጁኒየር የፊት አጥቂ የሆነ ዝነኛ ተጫዋች ሆኗል ።



➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
➡️@Enmare1988
አንዳንድ ፎቶ ደግሞ አለ 🙌🏼

👇🏾

በህይወትህ አድካሚ ናቸው ብለህ የፈረጅካቸውን ነገሮች ዋጋ የሚያሳጣ

ከአልጋህ ተነስተህ በእግርህ ለመቆም የያዘህን የስንፍና መንፈስ የሚሰብር

ዙርያህን አይተህ ጎሎብኛል ብለህ በተነጫነጭክበት ነገር አምላክህን ይቅርታ ጠይቀህ ለምስጋና ቀና የምትልበት



ምን ያህል ብርቱ ነሽ?

ምንድነው የጥንካሬህ ልኬትስ?

❤️
🙌🏼
08.05.202519:56
✨✨ፍቅር ቅብ-18✨✨




ከክሊኒኩ እንደወጣሁ ቅርብ ያለ ቤተክርስትያን ጠይቄ ላመሰግን ሄድኩ.........ከተወሰኑ ቀናት በፊት "እዚህ አካባቢ መቃብር ስፍራ ካለ ጠቁሙኝ" ያልኩ ሴትዮ ዛሬ "ቤተክርስትያን ጠቁሙኝ" እያልኩ ነው....



ጊዜ እንዲህ ነው...."የማይነጋ ለሊት ማያልፍ ቀን የለም....." የሚል የመዝሙር ስንኝ አቃጨለብኝ...."እውነትም" አልኩኝ በለሆሳስ.....ይሆናል ብለው ከነገሩን በላይ ሆኖ ስናየው እናምናለን.....እኛ እንደሀገርም ሆነ እንደ ህዝብ....እንደ አህጉርም ቢሆን እንደ አለም የሚያመሳስለን ነገር አለ.....እንደ ቶማስ ካላየን አናምንም....እንደ ኤሳው ሆዳችን ከብኩርናችን ይበልጥብናል....ፈጣሪ የሰጠንን ፀጋ ከላያችን ለመላጨት ደሊላ ትበቃናለች.....


የኢዮብን ስም የያዝን ከጂዎች.....የስምኦንን ስም የያዝን አሳቾች....የአብርሀምን ስም የያዝን ንፉጎች....የኢያሱን ስም ይዘን ለአምላካችን ግድ የሌለን ከንቱዎች ሆነናል....ሙሴ ተብሎ አሻጋሪ ጠፍቷል.....የዘመኑ ሙሴ ላሻግራችሁ ብሎ ባህር ከፋይ....ህዝብ አምኖ ከክፋዩ ውሀ መሀል ሲገባ ውሀ የሚያስበላ ነው.....



የዘመኑ ስምኦን እንደ "ስምኦን ጫማ ሰፊው" ሰው አሳትኩኝ ብሎ አይኑ ላይ ወስፌ አይሰድም....ይልቁንም ሰው ለማሳት ጫማው እስኪያልቅ ይኳትናል እንጂ...


ስማችን አይከብደንም.....ምግባራችን አንገት አያስደፋንም.....ደህና ነገር እንደሰራ ሰው እንታበያለን.....እንዳልከፋን እንስቃለን....እንዳለለት እንዘላለን.....መፍራት ያለብንን አንፈራም....መፀየፍ ካለብን ጋር እንጣበቃለን.....ስጋችንን እናምነዋለን....ስጋ ብቻ እንዳለው ሰው እንኖራለን.....





***



"ዛሬ ምሳ የምጋብዝሽ እኔ ነኝ" አልኳት ሀኒን ....የሆነ የማላውቀው መንፈስ ውስጤ አለ አምጫት አምጫት የሚለኝ....ደስታሽ ደስታዋ ነው ንገሪያት የሚለኝ.....ለምን ብቻሽን እሷ እያለችልሽ የሚለኝ መንፈስ ሲታገለኝ ነበር የደወለችልኝ....እግዜር ይስጣት።


ከተገናኘን ወር ሊያልፈን ነበር.....ለአመታት እንዳልተገናኘ ዘመድ ተቃቀፍን.....ደስ አለኝ።


የምንወደውን ምግብ አዘን ሳንጎራረስ እና ሳንተያይ በላን.....እዚህ ጋር ከመክብብ ጋር ስለነበረን የመጀመሪያ ቀን አስታወስኩ.....ትንሽ ትንሽ መደበር እንደጀመርኩ አስተውላ "ምነው.....?" አለቺኝ


"ኧረ ምንም...."....አልኩና ለምን እንደዘጋችኝ ጠየቅኳት....


"አንቺም ዘግተሽኛል እኮ....".....የሚል የሰነፍ መልስ መለሰችልኝ....


"ያንቺን አይደል የጠየቅኩሽ ለምን አትመልሺም".....አልኳት።


"ልጠላሽ አልፈለግኩም.....ትንሽ ትግል ውስጥ ነበርኩ....".....አለችኝ ድምጿ ቀዝቅዞ።



ትንሽ አርፋ ቀጠለች...."ትግል ውስጥ ነበርኩ....እየታገልኩ ነበር.....እኔ በፈለግኩት እና የፈለግኩት በሚፈልገው መሀል ያለውን ልዩነት ላጠብ ስጣጣር ነበር...አንቺን ከመክብብ ጭንቅላት ለማስወጣት እየታገልኩ ነበር...."......አለችና በልምምጥ አይነት አየችኝ......


"ተይልኝ ልልሽ አይደለም.....ምን ብለሽው እንዲህ እንደሆነልሽ ብቻ ንገሪኝ.....እኔ ለሰባት አመት የእሱን ትኩረት ለማግኘት የተጋጋጥኩትን በአንድ ቀን እንዴት ከመሬት ቀላቀልሽው.....እንዴት አርገሽ ብታይው ነው.....አሳሳቅሽ እንዴት ነበር.....ፀጉርሽን አንጨባረሺው ነበር አይደል....የዛን እለት የለበስሽው ልብስ መናኛ ነበር አይደል.....እንዴት ያለ አስተያየት እንዴት ያለ አወራር ነበረሽ.....?.....ወይስ አበላልሽ ነው....አስታውሳለሁ አካሄድሽ እስከዚም ነበር.....ጫማሽ አቧራ ጠጥቶ ነበር.....ትዝ አለሽ ቀሚስሽ ጭቃ ነክቶት ነበር.....".......አለችኝ እና ያለቀው ትሪ ላይ አፈጠጠች.....



አንጀቴ ተላወሰ......"ሀኒ ካንቺ አይበልጥም.....የምሬን ነው.....ይኧውልሽማ....."......ከማለቴ አቋረጠችኝ......እውነቱን ለመናገር "ካንቺ አይበልጥም" ያልኩትን ቃል ስሜታዊነቴ ነው ያበጃጀው.....አንዳንዴ የማናወዳድራቸው ነገሮች አሉ.....እንደ እኔ እንደ እኔ ደረጃ ከመስጠት ሁሉንም እንደ ራሱ መውደድ ይሻላል።


"እንደስምሽ ነሽ ታውቂያለሽ.....እድል አለሽ.....ምን አልባት ፈጣሪ በእሱ ሊክስሽ ይሆናል......"


"የሚክሰው በዳይ ነው.....ሰው እንጂ ፈጣሪ በድሎኝ አያውቅም.....ሀኒ....".......በድጋሚ አቋረጠችኝ.....


"ትናንት መክብብ እንዴት አድርጎ የፍቅር ጥያቄ እንደሚያቀርብልሽ ሲጨነቅ ነው ያመሸው.....ምን ትወድ ይሆን እያለ ልቤን ሲጠባ ነበር.....የምትወጂውን ሳይሆን የምወደውን ልነግረው ስንቴ ከአፌ እንደመለስኩት አታውቂም.....ስንት ጊዜ እድል ፊት እንዳለህ እያሰብክ "አፈቅርሻለሁ" በል እንዳልኩት እና በልቤ ጮክ ብዬ "እኔም አፈቅርሀለሁ" እንዳልኩት አታውቂም.....አንቺን እያሰበ ስንት ጊዜ አፈቅርሻለሁ ሲለኝ እንዳመሸ አታውቂም.....አእምሮዬ ሊፈነዳ አንድ ሀሙስ እንደቀረው አታውቂም....."......አለችና መንታ መንታ እምባ ከአይኖችዋ ተንቆሮቆሩ።



በወደድኩት በመወደዴ ደስ ባለኝ ቅፅበት እንባዋ እንደ እሳት ፈጀኝ.....ልቡ ውስጥ ለመግባት በተመኘሁት እኩል መውጣት አሰኘኝ.....አሳዘነችኝ.....


"ትዝ ይልሻል ልጅ እያለን ያየነው ሻሩክ የሚሰራበት የህንድ ፊልም......"


በህይወት ዘመኔ ያየሁት የህንድ ፊልም እሱ ብቻ ስለነበር አልረሳሁትም.....አንገቴን በአዎንታ ነቀነቅኩላት.....


"እሱ ላይ እንዳለችው እንስት ሳሳሁ.....'ለአንድ ወንድ ምነው እንደዚህ' እንዳላልኩ ለአንድ አሱ ቆዳዬ ሳሳ....".....ከቦርሳዋ ሶፍት አውጥታ አይኗን አደራረቀች።


"ሀኒ......".....አልኳት ጠረጴዛ ላይ ያዳደመችውን ያልበላችበትን እጇን ባልበላሁበት እጄ ጨብጬ.....


"ውሰጂው....."......አልኳት.....የምሬን ነበር።


"ሰው እኮ ነው እድል ኳስ አይደለም.....እንደ ኳስ በጠለዝሽው በኩል አይሄድም.....ልቡ በሚመራው መንገድ እንጂ.....ወደ እኔ ብትገፊው አይደለም ንፋስ አምጥቶ ከእኔ ጋር ቢያላትመው እንኳን ንፋሱ ሲሸሽ ይሸሻል.....ሰው ነው"......አለችኝ እና ፈገግ ነገር አለችልኝ.....



ወዲያው "ፍቅሬን ቀማሽኝ" የሚባባሉ እንስቶች እና ተባዕቶች አእምሮዬ ላይ መጡ.....ሀኒ እውነቷን ነው.....ሰው ናቸው ጆተኒ አልያም ኳስ አይደሉም.....ፈቅደው ይሄዳሉ እንጂ በተወረወሩበት እግር አቅጣጫ አይነዱም።



የሀኒ ስልክ ሲነዝር ያልበላበትን እጇን አስለቀቀችኝ.....



ጉሮሮዋን ጠራርጋ "ሄለው መኬ" ስትል አንገቴን ቀበርኩ.....





አላለቀም......




✍ሸዊት





https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
✔️የናፈቀኝ እንዲህ ያለ ነፍስ ማግኘት ነው።

የፊልሙ ርእስ Twilight ይባላል። በእርግጥ አንድ ፊልም ብቻ አይደለም—4 ፊቸር ፊልሞች ናቸው። ደግሞ ሌላም ጉዳይ አለ። ፊልሙ ፊልም አይደለም። ማለቴ መነሻው መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ተወዳጅ ሲሆን በፊልም ተሰርቶ መጣ

🌟 የቫምፓየር ፊልሞች ማየት አቁሜ የነበረ ቢሆንም ግርግሩ ጋብ ሲል፣ ሲረሳ ፊልሙን አየሁት። በባህሪዬ አንድ ነገር እጅግ ሲገን ራቅ ብዬ መመልከት እመርጣለሁ። አያችሁ! ያ ነገር አልሰከነም። እጅ በዝቶበታል፤ ተመልካችም እንዲሁ። እጅ የበዛበት ነገር ደግሞ የሚሰክነው ግዜ ወስዶ ነው። አለም ሁሉ ነገሩን ረስቶ በሚቀመጥበት ግዜ የኔ ተራ ነው—ያኔ መጽሐፉን አነበዋለህ፤ ፊልሙን አየዋለህ። የወረት ፍቅር አልወድም።

🌟 ሌላው ደግሞ መጽሐፉ በዋነኛነት የተጻፈው፣ ፊልሙም የተሰራው አስራ እድሜ ውስጥ ላሉ ታዳጊዎች ነው። ፈረንጆቹ young adults ይሏቸዋል—አለ አይደል በልጅነትና በአዋቂነት ዘመን መካከል ያለው እድሜ ውስጥ ለማለት። እኔ ደግሞ ታዳጊ መሆን ካቆምኩ ግዜም የለኝ።

✅ ለማንኛውም ፊልሙ ምርጥ ነው ባ ከፊልሙ ውስጥ በጣም የማረከኝን አንድ ቁምነገር ልንገራችሁ፦

✅ ፊልሙ ውስጥ ኤድዋርድና ቤላ የሚባሉ ዋነኛ ገጸባህሪያት አሉ። ኤድዋርድ ቫምፓየር ሲሆን ቤላ ሰው ናት። ኤድዋርድ ቤላን የወደደበት ምክንያት እጅግ አስደናቂ ነው።

ኤድዋርድ እንደ ቫምፓየርነቱ ሱፐርፓወር አለው። ከሱፐርፓወሮቹ አንዱ የሰዎችን ሃሳብና ፍላጎት ማንበብ መቻሉ ነው። እናም 99% ግዜ የሰዎች ፍላጎት ከሁለቱ አንዱ ነው። ሰዎች በብዛት የሚያልሙት ስለ ገንዘብና ወሲብ ነው። አለማችን በስግብግብና ቅንዝራም ሰዎች የተጥለቀለቀች ናት። ታዲያ ኤድዋርድ የሰዎችን ፍላጎት ሲያነብ ቆይቶ ቤላ ጋር ሲደርስ እጅግ አስደናቂ ነገር ገጠመው። ቤላ ምንም ፍላጎት የላትም። ቡድሂስቶች ቢያገኟት ኒርቫና ላይ የደረሰች ነፍስ ነች ይሏት ነበር።

ፎርብስ የሚያወጣውን የቢሊየነሮች ዝርዝር ተዉትና ቤላ የአለማችን ቁጥር አንድ ሃብታም ሴት ትሆን ነበር። ሃብቷ በቁጥር የማይገለጽ ኢንፋናይት ነው። ኤድዋርድ ለዚህ ውብ ነፍስ ነው የተንበረከከው፤ ለዚህ ትንግርት ነው የተረታው። ገንዘብ ፣ ንብረት ቁጥር ነው። እውነተኛ ረቂቅ ሃብት ከነፍስ ዘንድ ነው። በአለም ላይ እንደዚህ አይነት ሰዎች አሉ። ቢኖሩም ግን ጥቂት ናቸው። እናም ይህቺን ረቂቅ ነፍስ በመጨረሻ አገኘኋት . . .

➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
06.05.202517:12
የሆስፒታል ወግ...

የህፃናት ክፍል ተመድበን ካርድ ስናገላብጥ "አሳጥረው ሲፅፉት ከባድ ነገር አይመስልም እንደውም የሰው ስም ነው የሚመስለው አይደል?" አለቺኝ ዶክተሮቹ የፃፉት ካርድ ላይ አልነበብ ያለውን ፅሁፋቸውን ለማንበብ እየሞከረች

አየሁት የበሽታ አይነት የሚለው ላይ "SAM" ይላል severe acute malnutrition ማለት ነው በምግብ እጥረት በጣም የቀነጨረ ህፃን ማለት ነው።

"ቆይ ግን SAM ላለበት ሰው ምንድነው የሚደረገው?!" አለችው አጠገቧ ላለው ነርስ

"ያው acute malnutrition ከሆነ ቶሎ ቶሎ ምግብ እና ፈሳሽ እንሰጠዋለን በጣም severe ደረጃ ላይ ከደረሰ ግን ምግብ ትንሽ ትንሽ ነው የሚሰጠው" አላት እጁን በአልኮል እያፀዳ

"እንዴ እንደውም በደንብ የሚያስፈልገው ለባሰበት አይደለ እንዴ ጭራሽ ትንሽ እንሰጠዋለን?!" አለች ወገቧን ይዛ

"አየሽ ሰውነትሽ አንድን ነገር በጣም ፈልጎ ሲያጣ ያለሱ መኖርን መለማመድ ይጀምራል ስለዚህ ያ በጣም የተፈለገው ነገር ጠላት ይሆናል ሰውነትሽ ያለሱ ለመኖር ሲጣጣር አሰራሩ ይቀየራል ምግብን በአግባቡ ከመጠቀም በትንሽ ምግብ መኖር መለማመድ ይጀምራል

ስለዚህ ብዙ ምግብ ሲያገኝ እንደባዕድ ነገር ይቆጥረው እና ለማውጣት ሲጨነቅ ያልተጠበቀ ጉዳት ሊያመጣበት ይችላል አሁን ገባሽ" አላት

"ዋው ወይ ጉድ ሰውነታችን እኮ ሁሌም ነው የሚደንቀኝ" አለችው እና ወደ እኔ ዞራ "አይገርምም" አለቺኝ

"ቀላል እንደውም ከዘመኔ ትውልድ ጋር ተመሳሰለብኝ" አልኳት ራሴን በግርምት እየነቀነቅኩ ተመሳስሎው ገርሞኝ

"ረሀብ ላይ ስለሆንን ብለሽ ነው?!" አለች ግራ መጋባቷ ፊቷ ላይ እየተስተዋለ

"አይደለም ስለ አካላዊ ርሀብ እና መቀንጨር አይደለም እኔ የማወራው ስለ ፍቅርን እንደ ምግብ ስለተራበው ልባችን ነው የፆታዊ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አይነት ፍቅር ነው የምልሽ እና በጣም የሚያስፈልገን ፍቅር ሆኖ acute የሆነውን ፍቅር ብናገኝ የምናልፍበትን stage አልፈን

አሁን severe love-deficit ሆነን ብቻችን መኖር ብቻችንን መደሰት ብቻችንን ማዘን ብቻችንን ከሀዘን መውጣት እየተለማመድን ሳለ ልባችን "ሰውን መውደድ" የነበረው መደበኛ ስራዋን ትታ "ብቻ መኖርን" ለመደች

አሁን ጠብታ ፍቅር ሲቀርበን ልባችን ይገፋዋል ምክንያቱም መራራቅን እንጂ መቀራረብን ረስተናል ፍቅር እንዴት መቀበል እንዳለብን እንዴት መስጠት እንዳለብን ባጠቃላይ እንዴት ፍቅርን handle ማድረግ እንዳለብን ረስተናል

ስለዚህ እንደ SAM ታካሚ ፍቅርን በጥቂት በጥቂቱ መለማመድ አለብን ምክንያቱም በብዙ የመጣ ፍቅር ለእኛ ጠላት ነው እንዴት እንደሚያዝ አናውቅበትም ለዛ እኮ ነው የቀረበንን በሙሉ ሰበብ እየፈለግን ስንርቅ የኖርነው አይገርምም መመሳሰሉ" አልኳት ጥርስ ጥርስ ሆኜ

"ለዛ እኮ ነው ነርሲንግን ትተሽ ፍልስፍና ተማሪ ስልሽ የነበረው አሁን ነይ ለልጆቹ መድሀኒታቸውን እንስጣቸው በረሀብ ሳያልቁ" አለች

የእኛንስ ልብ ማነው በትንሽ በትንሽ በትንሹ ፍቅር የሚያስለምደው??


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
Ads

ዛሬ ማታ ትልቅ GIVEAWAY አለ የSTAR, የTON ወይም ብር የምንሸልም ይሆናል ማንም እንዳይቀር ✌️FAMILY✅

GIVEAWAY ላይ ለመሳተፍ በቅድሚያ የዚህን CHANNEL JOIN ማለት አለባችሁ 😏@UNIQUECRYPTO_24l7😮


GIVEAWAY? 🤝 @UNIQUECRYPTO_24l7 👈JOIN HERE
05.05.202519:34
ረጅም ፀሎት ኖሮኝ አያውቅም.....ይሄ በህይወት ዘመኔ የፀለይኩት ሁለተኛ ፀሎቴ ነው.....አንደኛው "እናቴን ቤቷ መልስልኝ...."....ነበር.....


ውጤቴ እስኪደርስ ከዚህ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ ዝብርቅርቅ ስሜት ተጫወተብኝ.....


የምፅአት ቀን እራሱ እንደዚህ የሚርቅ አይመስለኝም።



"እድል ሰጠኝ......".....ተጠራሁ።




አላለቀም.....



✍ሸዊት






https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
✔️ልጁ በከባድ መከራ ውስጥ እያለፈ ነበር። ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ከዚህ መከራ አውጣኝ ይላል።

አንድ ቀን ፈጣሪ ተገለጠለትና መከራህን በሌሎች ሰዎች መከራ ልለውጥልህ አለው። ልጁም በጣም ተደስቶ የጓደኞቹን፣ የዘመድ ወዳጆቹን መከራ ማጠያየቅ ጀመረ። አና በመጨረሻ ወደ ፈጣሪ ሲመለስ የራሴን መከራ ተቀብዬ እኖራለሁ አለው።

ሁላችንም የመረጥነውን መከራ ነው ተሸክመን የምንኖረው

➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
✔️በስተርጅና እድሜው ላይ ሆኖ. . የወጣትነቱን ፎቶ እያየ በትዝታ እንደሚተክዝ ትልቅ ሰው ፡ ከሁለት አመታት በፊት የነበራትን መልክ እያየች የምትተክዘው ይህች የ12 አመት ታዳጊ Rahaf Ayyad ትባላለች ።
....
✔️...Rahaf Ayyad በዚህ እድሜዋ ይህንን መልክ እንድትይዝ የሚያደርግ ህመም የለባትም ነበር ።
ታዳጊዋ Rahaf እንዲህ ስጋዋ አልቆ በአጥንቷ ያስቀራት ረሀብ ነው ። ሰው ሰራሽ ረሀብ 😥
የአለም ህዝብ አይቶ እንዳላየ ችላ ያለው ረሀብ ። እሱ ነው እንዲህ የልጅነት መልኳን የመጠጠው ።
.....
🟢በተለይ ከባለፉት 70 ቀናት ወዲህ እስራኤል የእርዳታ ምግብ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በማገዷ ፡ ያቺ ታምር የነበረችው ታዳጊ ችግሩ ተባብሶ ረሀብና የተመጣጠነ ምግብ እጦት እንዲህ አድርጓታል ።
...
🔵ይደክማታል ፡ አቅም ያንሳታል ፡ ትንሽ እንኳን ቀምሳው የሚያበረታት ምግብ በሀገሩ የለም ፡ እና ፡ የአሁን መልኳን ሳይሆን በወላጆቿ ስልክ ላይ የተነሳችውን የዛን የመልካም ጊዜ ምስሏን እያየች ከድካምና ከረሀቧ ጋር ስትታገል ትውላለች ።
.....
✔️ፍትህ ያለወንጀላቸው እየተቀጡ ላሉ ፍልስጤማውያን ህጻናት ❤️

Wassihun tesfaye

➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
से पुनः पोस्ट किया:
Thoughts avatar
Thoughts
हटा दिया गया07.05.202512:47
⭐Ads

✅Work visa
✅Student visa
✅Visit visa
✅Contact us

✔️@Classictravelandtureagency
Tg📞 +251983845700
💬whatsapp +251951392587

https://t.me/classictravelandtouragency
05.05.202519:34
✨✨ፍቅር ቅብ-16✨✨




ዮናስ ደጄን ከረገጠበት ቀን ጀምሮ መመንመን የጀመርኩ መሰለኝ.....ጉንጮቼ በሁለት ቀን የሰመጡ አጥንቶቼም የተንኮታኮቱ ...ፀጉሬ ሳልነካው ተነቅሎ ያለቀ አይኔም ያለመነፅር አሻፈረኝ የሚል መሰለኝ....ከበሽታ በላይ እርጅና ተሰማኝ....


ምግብ የሚባል እምቢ አለኝ....በትግል የበላሁትም ወዲያው ይወጣል....አኳሀኔ የታመመም....ያረገዘም.....ያረጀም ሰው አይነት ነበር.....


የመክብብ ጓደኛ ጋር መሄድ አልፈለግኩም....ምንም ቢሆን የመክብብ ጓደኛ ነው....ዛሬ እንደታማሚ በቅንነት ቢያነጋግረኝ ነገ ላይ የመክብብ የሆነ ነገር ሆኜ ቢያየኝ ጣቱን ለመቀሰር አንደኛ ነው.....


ምንም ባደርግ ሊለቀኝ ያልቻለው መክብብ ላይ ያለኝ ተስፋ ነው....እንዲህ ነው ብሎ አፍ አውጥቶ አልነገረኝ ነገር.....ፍቅር ይኑርበት ሀዘኔታ በውል አለየሁት ነገር....ነገ ኖረም አልኖረም ግን ውስጤ የሚጠነቀቅለት ብቸኛው ሰው ነው....


*****



"ከባለቤቴ ጋር ስንተዋወቅ ጀምሮ ቫይረሱ ነበረበት....አልነገረኝም.....እንኳን ይሄ ቫይረስ ጉንፋን አሞት የሚያውቅም አይመስልም ነበር....በጣም እንደሚወደኝ በአስር ጣቴ የምፈርምለት ሰው ነበር....ወደ አልጋ ሲገፋኝ በጄ አላልኩትም ነበር.....እንደሚወደኝ እና ከኔ ሌላ ማግባት እንደማይፈልግ ....ከኔ ሌላ ማንንም እንደማያልም እያለቀሰ ነገረኝ.....ትዝ ይለኛል አለቃቀሱ....ያሳሳ ነበር....ግን ስላለቀሰ አልነበረም ያመንኩት.....እንዲሁ ዝም ብዬ ነው ያመንኩት....


ከሱ ጋር በተኛሁ ማግስት ህዳር ሚካኤል ነበር......ሌላ ጊዜ ማህሌት አድሬ ቅዳሴን አስቀድሼ እስኪያልበኝ የምዘምረው ልጅ አዳሩን እስኪያልበኝ ባለግኩ.....


የሆነ አፋፍ ላይ ቆሜ በርቀት ታቦት ሸኘሁ.....በርቀት አለቀስኩበት....


ቀናት ወራትን ሲወልዱ በእንባ ተለምኜ የሰጠሁትን ገና ሲጠጋኝ ማቀበል ጀመርኩ....ሀጥያት ሲለመድ ፅድቅ ይመስላል...ማፈር ስናቆም ውድቀታችን "ሀ" ብሎ ይጀምራል.....



"ሀ" አልኩኝ....



ልክ ያልሆነ ስራ እየሰራሽ የሚሰማሽ ልክነት ካለ አእምሮሽ ሚዛኑን እየሳተ ነው.....የሰው ልጅ ይለምዳል.....ደግነትንም ክፋትንም....ሀጥያትንም ፅድቅንም....ጉብዝናንም ስንፍናንም.....መልበስንም መራቆትንም....ማግኘትንም ማጣትንም.....ቤተ እምነቱንም ክለቡንም.....ሁሉንም ይለምዳል.....


ጭንቅላት ሞኝም ብልጥም ነው....ያስብልሻልም አያስብልሽምም......ያስለመድሽውን ይለምዳል.....ስታስቀሪበት እንደራበው ህፃን ልጅ ያጣድፍሻል.....ጭንቅላት ባለጌም ጨዋም ነው.....ሁሉንም ይለምዳል.....ጭንቅላት የልብ ወዳጅ ነው አይገምትሽም.....ጭንቅላት ከአባት ገዳይ የከፋ ጨካኝም ነው.....ሲበቃው በቃው ነው።



ባለቤቴ እንክርዳድ የሌለበት ስንዴ ነበረ....የተለቀመ ስንዴ.....እንዲህ ነው ብለሽ እንከን የማታወጪለት አይነት ሰው.....


ከሰጠኝ በሽታ በላይ የሄደበት መንገድ አቆሰለኝ....የሞኝ ውሳኔ ቢሆንም ቫይረሱ እንዳለበት ቢነግረኝ እንደማልተወው ነው የምነግርሽ.....ይሄ ለኔ ልክ ያልሆነ ልክነት ነው.....አልተወውም ነበር....የሄደበት አቋራጭ መንገድ ግን እኔን በአካል ሰጥቶ በመንፈስ ነጠቀው......


ምክንያቱ "እወድሻለሁ" ነበር....ውስጠ ምስጢሩ ጎን ራስ ወዳድነት ነበር....አይገርምም ሁሉም ለራሱ ነው....ሲወድሽ እራሱ ለራሱ ነው....ላንቺ ብሎ የሚወድሽ አምላክሽ ብቻ ነው።


በሽታውን ሲሰጠኝ አስቦበት እንደነበር ሲነግረኝ አላፈረም....ምናል ባይነግረኝ.....ሁሉም መነገር የለበትም አይደል.....ምናል ድንገት ስሜታዊ ሆኜ ምናምን ቢለኝ....."ይሄን በሽታ ካሲያዝኳት ጥላኝ አትሄድም ብዬ ነው ያደረግኩት....ደሞም ልክ ነበርኩ አልሄድሽም.....".....ነበር ያለኝ.....ሞኝ ሆኖ እንጂ ሄጃለሁ....".....አለችኝ እና መጣሁ ያለ እንባዋን በአውራ ጣቷ ወደጎን አሽቀነጠረችው......ልመረመር ከሄድኩበት ክሊኒክ ህመምተኛ መቀበያ ወንበር ላይ የተቀመጠች ጎልማሳ ሴት ታሪክ ነው.....


"ሰው ሲከፋው ከድንጋይ ጋርም ያወራል...."....አለችኝ በትኩረት እያየችኝ.....መገረሜ በታሪኳ ብቻ ሳይሆን  እንዴት ዘርግፋ ነገረችኝ በሚለውም ስለነበር ማስተዋሏ ገረመኝ።


ከሰፈር በጣም ርቄ የሄድኩበት ክሊኒክ ነው....ከሰፈር መራቄ ሀፍረቴን የሚቀንስልኝ መስሎኝ ነበር....አልቀነሰም።


"እድል ሰጠኝ....."......ስሜ ከውስጥ ተጠራ.....


እንደስሜ እድል እንዲሰጠኝ እየተመኘሁ ወደውስጥ ዘለቅኩ።


ከዶክተሩ ጋር አንድ አንድ አንድ ነገር ተነጋገርንና ሌላም ምርመራ ጨምሮ ወደ ላብራቶሪ ክፍል ላከኝ....


ላብራትሪስቷ ደሜን ቀዳች......የገላመጠችኝ መሰለኝ.....ለነገሩ በሶስት ታክሲ ስመጣ ሶስተኛው ታክሲ ውስጥ ጋቢና የተቀመጠው ሰውዬ ራሱ አስተያየቱ ስራዬን እንደሚያውቅ ነገር ነው....ከታክሲ ስወርድ ያየኃቸው አሮጊት አይነ ውሀቸው አላማረኝም....የክልኒኳ ፅዳት ሰራተኛ በምታፀዳው መሬት ፈንታ እኔን ብታፀዳኝ ደስ እንደሚላት አይኗ ነግሮኛል....ዶክተሩም ስራ ሆኖበት ነው.....


አባዬ ደወለ....ባነሳው "አንቺ ባለጌ...." የሚለኝ መሰለኝ....አላነሳሁትም....


የራሴን ስሜት ሰው ሁሉ ላይ እያየሁት ስሸበር ወጣ ብዬ ተነፈስኩ...."ተረጋጊ እድል ማንም አያውቅም ተረጋጊ.....".....አልኩኝና የቅድሟን ሴትዮ ጥዬ ወደመጣሁበት ወንበር አመራሁ.....የለችም።


ተመልሼ ወጥቼ ሰማዩ ላይ አፈጠጥኩበት.....ደመና ነበር....ወደላይ አንጋጥጬ "አደራህን አምላኬ አደራህን" አልኩት.....
✅ዛሬ አንድ ሱቅ ውስጥ የቀድሞ ፍቅረኛዬ ፍቅረኛዋን ከፊት ለፊቴ እየሳመች አገኘኋቸው፣ እያየዋቸው ነበር።
አየችኝ ከዛ የበለጠ ሳመችው እና እዚህ ምን እየሰራሁ እንደሆነ ጠየቀችኝ?.

💠ባለቤቴ አርግዛ መውለዷን ነገርኳት እና እኔ እዚህ የመጣሁት የልጅ እቃዎችን ለመግዛት ነው በጣም ደስተኛ ነኝ ምናምን ብዬ አቀሳሰርኩ እና  ሱቅ ውስጥ ገባሁ

✅እሷ እያየችኝ ዳይፐር ፣የህፃን ወንበር እና የህፃን አልጋ ስፖንጅ  ፣ብስክሌት ፣የህጻን ልብስ እና የመሳሰሉትን ገዛሁ ከዛ Ride ደወልኩና እቃውን ጭኜ ሄድኩ።
እሷ እና የወንድ ጓደኛዋ ተመስጠው እየተመለከቱኝ ነበር እና ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነበር የሄድኩት...

💠አሁን ወደ ቁም ነገሩ ስገባ የወለደች ሴት የምታውቁ  ዳይፐር፣ የልጅ መቀመጫ ወንበር፣ የአልጋ ስፖንጅ፣ ብስክሌት እና የህፃን ልብስ በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸጥኩ ነው ሚገዛኝ ካለ ወዲህ በሉ...😡

➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
07.05.202519:50
✨✨ፍቅር ቅብ-17✨✨




"እድል.....".....አለኝና ወደ ወንበሩ ጠቆመኝ.....የያዘውን ትኩስ ምድጃ ለማስቀመጥ እንደሚጣደፍ ሰው ተንድርድሬ ተቀመጥኩ....


ከተቀመጥኩ በኃላ ከቫይረሱ ጋር እንዴት እንደሚኖር አጭር መግለጫ ሲሰጥ ውስጤ ሰለለ...የተቀመጥኩበት ወንበር እንዲያሰምጠኝ ተመኘሁ....መሬት አፏን ከፍታ እንድትውጠኝ ተመኘሁ....እንዳለቀ ጢስ መሰወር አሰኘኝ....መጥፋት እና "በፎቶው ላይ የምትመለከቷት ወጣት እድል ሰጠኝ በእለተ ሀሙስ ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም....በእለቱ የለበሰችው ልብስ....."......ምናምን የሚል የራሴን አፋልጉኝ ማስታወቂያ መንገድ ዳር ቆሞ ማንበብ አማረኝ......



"በቃ እንግዲህ እድል እራስሽን አዘጋጂ...."....."መኖር ይቻላል እኮ.....".....ሌላ ሌላም አልኩ....."ግን አባትሽ ምን ይላል..."...."ለእትሽ ምን ትያታለሽ....".....ጡዘት።



"እውነቱን ለመናገር ከበሽታው በላይ በሽታው ወደ እኔ የመጣበት መንገድ ያንገበግበኛል.... ስንት ቀን ለፍቼ ያመጣሁት በሽታ እንደሆነ ብታውቅ....".....አልኩት እና ፈገግ አልኩለት ልጅ እግር ዶክተሩን....ተረጋግቻለሁ.....መረጋጋቴ ለራሴ ራሱ አልገባኝም.....እንዴት እረጋጋለሁ....?....እንዴት አይኔ ደረቀ....?....መርበትበት አልነበረብኝም.....?....እድል ስጠኝ ያልኩትን አምላክ ላይ መጮህ አልነበረብኝም.....ተረጋግቻለሁ.....ጭንቅላቴ ነገርየውን ገና ፕሮሰስ አላደረገውም ይሆን አላውቅም....ተረጋግቻለሁ።



"ይኧውልሽ እድል.....".....ከማለቱ አቋረጥኩት....ትንሽ ትንሽ ገባኝ....ፈግታዬ ከት ወዳለ ሳቅ ተለወጠ...."እንዴት በባዶ ሆዴ ለፍቼ ያመጣሁት እንደሆነ ብታውቅ ትሸልመኝ ነበር ካካካካካ...."....ሳቄ እንባ ቀላቀለ.....አእምሮዬ ከቁጥጥሬ ውጪ ወደመሆን አዘነበለ.....


"እድል!!!......".....አለና ጠረጴዛውን አንድ ጊዜ በመዳፉ ለጠፈው....


"እድለ ቢስ ብትለኝ አይሻልም....".....አፈጠጥኩበት።



"አንድ ጊዜ ተረጋግተሽ.....".....አሁንም አቋረጥኩት.....



"ስለምን መረጋጋት ነው የምታወራኝ....የምስራች እንደሚነግር ሰው ነጭ ለብሶ መቀመጥማ ቀላል ነው.....ቀላል ነው.....ከቫይረሱ ጋር መኖር ይቻላል ማለትማ ቀላል ነው.....ቆይ መኖር ምንድን ነው.....?....መኖር ላንተ ምንድን ነው.....በየእለቱ አየር መማግና መስደድ ነው ....?......"......እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ......


ወትሮም የምኖር አይመስለኝም.....አንዳንዴ 'መኖር አስጠላኝ' እልና መልሼ 'እየኖርኩ ነው እንዴ' እላለሁ.....ለኔ መኖር እንዲህ አይደለም።



"ዶክተር ፍቅር ይዞኛል እኮ.....ልቤ የሚያርፍበት አጊኝቷል እኮ....ዶክተር አልገባህም.....አባቴ ፊቴን አያየውም ከንግዲህ....እናቴ የለችም እኮ....አታውቅም አንተ ታናሽ እህት አለኝ እኮ......"......ከዚህም ከዚያም እያማታሁ ማልቀስ ጀመርኩ....



***



መረጋጋቴን ሲጠብቅ የነበረው ዶክተር ዝምታውን ሰበረ.... ነጩን ጋውን አውልቆ ከረባቱን ፈታ.... ከተሰየመበት ወንበር ተነሳና ፊትለፊቴ ተቀመጠ.....


"እንዳትመክረኝ ዶክተር...መኖር ይቻላል እንዳትለኝ ዶክተር....አውቃለሁ....አውቃለሁ እሱን....እኔን ያንገበገበኝ......".....ከማለቴ ሰፌድ በሚያክለው መዳፉ አፌን ያዘና "ከቫይረሱ ነፃ ነሽ!!!" አለኝ።



*



ውበት አይን ይመርጣል....እንደተመልካቹ ነው.....ለኔ ነፃነትንም እንደዛው ነው..... ነፃ መሆንን ካላወቅንበት ራሱ መታሰር ሊሆን ይችላል......



ህመምን ያለ መድሀኒት አይሰጥም....መድሀኒታችን ምን አልባት እኛ እንደምናስበው አይነት መድሀኒት ላይሆን ይችላል.....ምናልባት የሚፈወሰው መንፈሳችን ይሆናል.....ምናልባት ምግባራችን .....ምናልባት ግንኙነታችን.....ምናልባት ስብእናችን....ምናልባት እኛነታችን።


ወዲያው ትናንት በቤተክርስቲያን ደጃፍ ሳልፍ ጆሮዬን የያዘው ትምህርት ትዝ አለኝ....."እረኛ በጎቹን መጀመሪያ በድምፅ ይገስፃቸዋል.....አልመለስ ካሉ በጅራፍ ከገደል አፋፍ ይመልሳቸዋል....በሽታችሁ ከገደል አፋፍ የመለሳችሁ የላችሁም.....?".....ጥያቄ።




*



እንባዬን ጠራርጌ ልጅ እግሩን ዶክተር አመሰገንኩ....ለሌላ ጊዜ ነፃነትን ለማወጅ እንዲህ የሰው ልብ ከፍ ዝቅ እስኪል ባይጠበቅ መልካም እንደሆነ አሳሰብኩ.....


" ላለፉት ሁለት አመታት በዚህ መልኩ ነው ውጤት የምንናገረው...." አለኝ እየሳቀ.....


"ያልታመመውንም ሰው....?".....በአግርሞት ጠየቅኩ።


"አዎ አለኝ በልበ ሙሉነት...."


"ለምን...."....መልሱን ለመስማት ጓጓሁ።


"ኤቲክሱ ግን ብለሽ የማትከራከሪኝ ከሆነ እነግርሻለሁ....".....አለኝና ያስቀመጠውን ጋውን ለበሰ....


"የልብ ድካም አልያም ሌላ severe case ከሌለባቸው በስተቀር ነፃነታቸውን ከማወጃችን በፊት ነፃነታቸውን ለደይቃዎች እንነጥቃቸዋለን.....አለመያዛቸውን ከመናገራችን በፊት ለደይቃዎች መያዝን አእምሯቸው ውስጥ እንከታለን...."


"እኮ ለምን....?......"


"በነፃ የተገኘ ነፃነት አይዘልቅም.....ያላየነው ስሜት አያስፈራንም....ለማናውቀውን መጥፎ ስሜት አንታገልም....ነፃነት አክባሪውን ያከብራል.....በነፃ አንሰጣቸውም".......አፌን ከፍቼ ቀረሁ።




አላለቀም.....





✍ሸዊት




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
ባሸንፍ እንኳ ያልቅልኛል፡- ፍልሚያን የመምረጥ ምስጢር
(“ትኩረት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ወቅቱ ግሪክና ሮም የጦርነት ፍጥጫ ላይ የነበሩበት ዘመን ነው፡፡ በሁለቱም ወገን 40 ሺህ የሚያክል ጽኑ የጦር ሰራዊት ተሰልፏል፡፡ የግሪኩ ንጉስ ፓይረስ (King Pyrrus) አይኖቹን ሮም ላይ ተክሏል፡፡ “ሮምን ካላሸነፍኩ አላርፍም” ያለ ይመስላል፤ ማንም ሰው ከዚህ አቋሙ ሊመልሰው እስከማይችል ድረስ ቆርጦ ነበር፡፡ የጦር መሳሪያ አይነት፣ ለውጊያ የሚጠቀምባቸውን ዝሆኖች ሁሉ ሳይቀር ሰብስቧል፡፡

ከዚህ በፊት የተፋለመውን ፍልሚያ ሁሉ በማሸነፍ የታወቀ ንጉስ ነው፡፡ የሮም አገዛዝ ያበቃለት ይመስላል፡፡ ውጊያው ጀምሮ ብዙ መራራ ቀናትን ካስቆጠረ በኋላ ማንም የማያሸንፍበት የእልቂት ፍጥጫ ሆነ፡፡ ሆኖም፣ በድንገት ግሪኮች ድልን ተቀዳጁ፡፡ ግዙፍ ዝሆኖቻቸው በብዙ ቁጥር ሆነው ወደ ሮማውያን ክልል ጥሰው በመግባታቸው ከሞት የተረፉት ሮማውያን ወደ ኋላ መሸሽ ግድ ሆነባቸው፡፡

የንጉስ ፓይረስ ሰራዊት ግን እጅግ ደክሟል፡፡ ጉልበትን ለመሰብሰብ ባለበት ስፍራ ከሰራዊቱ ጋር ተከማችቶ እንዳለ አንድ ወዳጁ ስላገኘው ድል “እንኳን ደስ ያለህ” አለው፡፡ ንጉስ ፓይረስ የመለሰው መልስ እንዲህ የሚል ነበር፣ “ከአሁን ወዲያ አንድ ፍልሚያ ተፋልሜ ባሸንፍ እንኳ ያልቅልኛል”፡፡

አንዳንድ ጊዜ በፊታችን የመጣውን ፍልሚያ ሁሉ መዋጋትና ማሸነፍ ያለብን ይመስለናል፡፡ የተጫረ ጸብ ውስጥ ሁሉ ራሳችንን እንጨምራለን፣ ለተናገረን ሰው ሁሉ መልስ ለመስጠት ጊዜ አይፈጅብንም፣ ለነካን ሰው አጸፋ ሳንመልስ እንቅልፍ አይወስደንም፡፡ በዚህ “ብርታታችን” ከዚህ በፊት ብዙዎችን አንበርክከን ሊሆን ይችላል፡፡

መለስ ብለን ሕይወታችንን ስናጤነው ግን አንድ ሺህ ፍልሚያዎችን አሸንፈን፣ ነገር ግን አንድን ነገር ለመገንባት ጊዜ ያጣን ሰዎች ሆነን ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡ ብዙ የተዋጋናቸው ሁኔታዎችና ሰዎች በታሪካችን ተመዝግበው አንድም የገነባነው ቁም ነገር ከሌለ ትኩረት የተነጠቀ ሰው የመሆናችን እውነታ አከራካሪ አይደለም፡፡

የሕይወትን ውጣ ውረድ በሚገባ ስንቃኘውና ስንጨምቀው እውነተኛ ፍልሚያን ልንፋለምባቸው የሚገቡን ነገሮች በጣም ጥቂት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

ብዙ ሰዎች በሞት አልጋቸው ላይ ሆነው ሲጠየቁ ወይም የመናገር እድል ሲያገኙ በሕይወት ዘመናቸው በወሰዷቸው አንዳንድ እርምጃዎችና ውሳኔዎች ላይ የሚናገሩት ነገር አላቸው፡፡

አንዳንዶች፣ “እገሌን ጥሩልኝና ይቅርታ ልጠይቀው” በማለት በዘመናቸው ሲጋፉት የኖሩትን ሰው በመጨረሻ ትንፋሻቸው ሊያቅፉት ይሞክራሉ፡፡ ሌሎች፣ “ለእገሌ የወሰድኩበትን ይህንና ያንን ነገር እባካችሁ መልሱልኝ” በማለት በውጊያ የወሰዱትን በልመና ሊመልሱ ይመኛሉ፡፡

“ይህንን ንብረቴን ለእገሌ አውርሱልኝ” በማለትም በብዙ ፍልሚያ የሰበሰቡትን ንብረት መልቀቅ ምርጫ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ አይተውና አሳይተው የሚያልፉም ብዙ ናቸው፡፡

ሕይወት ምንድን ነች? ሕይወት ሁለተኛ እድል የማትሰጥና ከራሳችን አልፈን ለሌላው የሚጠቅም ነገር አድርገን አጣጥመናት ልናልፋት የምትገባ ትእይንት ናት እንጂ ሕይወት በጠላት የተከበበችና ለፍልሚያ የተወሰነች የጦርነት ሜዳ አይደለችም፡፡

ለአንዳንዶች ግን ይህ የሕይወት ስእል በፍጹም ተቀባይነት የማያገኝ ጉዳይ ነው፡፡ የሚያውቁት ሌላ ነውና፡፡ በእርግጥ ነው በዚህች ምድር ላይ ስንኖር የማንፈልጋቸው ሙግቶችና ትግሎች አልፈው ወደ እኛ ይመጣሉ፡፡ ስለሆነም፣ ሕይወት ከምንም ችግር ነጻ የሆነች ጎዳና ነች ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡

ለማለት የተፈለገው የመጣውን ግፊያ ሁሉ መጋፋት፣ የተነሳውን ውድድር ሁሉ መወዳደር፣ የተከሰተውን ፍትጊያ ሁሉ የመፋተግ ግዴታ የለብንም፡፡ የምንፋለማቸውን ፍልሚያዎች የመምረጥ እድሉም ሆነ ብቃቱ አለን፡፡

የሕይወታችን ጥራት የሚለካው ባሸነፍናቸው ፍልሚያዎች ሳይሆን በመረጥናቸው የፍልሚያ አይነቶች ነው፡፡ የምትሰለፍለት ዓላማና የምትከራከርለት ነጥብ የውስጥህን አመለካከት ጠቋሚ ነውና፡፡ ተራ ሰው ለተራ ነገር ይጋፋል፣ የከበረው ሰው ደግሞ ፍልሚያዎቹን መዝኖ ለከበረውና ለዘላቂው ነገር ራሱን ያቀርባል፡፡ ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው፡፡


➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
እጀግ በሚገርም ሁኔታ የዓለምን የበላይነት ማለትም በእኮኖሚ በጦር ሚዛን እና በመሳሰሉት የበላይነትን ለመቀዳጀት ሲባል የሩሲያ KGB እና የአሜሪካነ CIA በሰው ሃገር ላይ ያገባኛል በማለት ተፋጠዋል ( ማን ይሳካለት ይሆን?

የ KGBው የስለላ መረብ ሃላፊ ላቀደው ታላቅ ሴራ ማስፈፀሚያ የሰውን ልጅ እንደ እንስሳ ከመጠቀሙም በላይ እንደ ቀልድ እያደባ ይህን ታላቅ ሚስጢር የሚፈፅምበት ቀን ተቃርቧል ይፈፅመው ይሆን?

የ CIA ዋ ሰላይ አንድ አስደንጋጭ የ KGBን ሚስጥር ከመስማትም አልፋ ትደርስበታለች ግን አለቆቿ ሚስጢሩን በማጣጣል ሰማ በማጣቷ ራሷ ሕይወቷን አደጋ ላይ በመጣል ትጋፈጠዋለች::ታጋልጠው ይሆን?

KGB ያጠመደው የኒውክለር ቦንብ CIA ሳይደርስበት የመፈንጃው ጊዜ ደግሞ ተቃርቧል ይህ ጓረቤት ሀገርንም ሆነ አካባቢውን የሚያጠድም ታላቅ > የቦንቡ ሚስጢር ከተሰማ በኃላ ሃገሮችን ሽብር ውስጥ ከመክተቱም --- በላይ እልህ አስጨራሽ እርብርብ ይደረጋል :: ይከሽፋ ይሆን?

እሷ ከደረሰባት የእንሰሳዊ ድርጊት እና እሱ ክደረሰበት በደል የተነሳ የመበቀያ ጊዜና ሁኔታ በመድረሱ እንዳረሩት የልባቸውን የበቀል መልስ ለመመለስ ተቃርበዋል ይፈዕሙት ይሆን፡፡

ይህ መፅሐፍ ለፍቅር ሲባል ከአላማ ውጪ የሚደረግ ጉቦን ፤ለገንዘብ ሲባል የጣምራ ሰላይነት ሚናን ፣ ክደረሰባቸው በደል የተነሳ የበቀል ዕዋን የመጐንጨት እና የተጠበቀው እንዳልተጠበቀ የሆኑና ያልሆነ ድርጊቶች እየተፈፀሙ የአንባቢን ቀልብ በመግዛት ከመጀመሪያ ገፅ እንስቶ ሚስጢሩ አስከሚፈታ የመጨረሻው ገፅ ድረስ በጉጉት የሚነበብ መፅሐፍ ነው።

✅✅መፅሐፍ በ Pdf ማታ 3 ሰአት ይለቀቃል


➡️ @Enmare1988
➡️@Enmare1988
➡️@Enmare1988
🕯ፎሬክስ በአማርኛ መሉ ትምህርት

📈ለጀማሪ

📈ለመካከለኛ

📊ለ ትሬደር

📉ለሁሉም

ቻናሉን በመቀላቀል ይማሩ

⚡️⚡️⚡️

https://t.me/EthioLearning19/3749
https://t.me/EthioLearning19/3749
https://t.me/EthioLearning19/3749
दिखाया गया 1 - 24 का 1 297
अधिक कार्यक्षमता अनलॉक करने के लिए लॉगिन करें।