Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Open reading 🕊⃤ avatar

Open reading 🕊⃤

🈴 Join our association to participate in open book club events!
_ Participatory reading session
- Question and answer contests
- Experience exchange and seminar events for Stay tuned to our Telegram channel!
TGlist रेटिंग
0
0
प्रकारसार्वजनिक
सत्यापन
असत्यापित
विश्वसनीयता
अविश्वसनीय
स्थान
भाषाअन्य
चैनल निर्माण की तिथिJun 28, 2024
TGlist में जोड़ा गया
Sep 11, 2024
संलग्न समूह

रिकॉर्ड

23.04.202523:59
1Kसदस्य
31.10.202423:59
800उद्धरण सूचकांक
24.03.202514:50
2.3Kप्रति पोस्ट औसत दृश्य
24.03.202514:51
2.3Kप्रति विज्ञापन पोस्ट औसत दृश्य
06.04.202523:59
17.39%ER
28.02.202514:51
257.84%ERR

विकास

सदस्य
उद्धरण सूचकांक
एक पोस्ट का औसत दृश्य
एक विज्ञापन पोस्ट का औसत दृश्य
ER
ERR
OCT '24JAN '25APR '25

Open reading 🕊⃤ के लोकप्रिय पोस्ट

ፍልስፍና ሲማር የነበረው ልጅ ትምህርቱን አጠናቆ ቤተሰቡ ለመዘየር ወደ ቀየው ይሄዳል። አባትም ደስተኛ ሁነው ዶሮ አርደውና አዘጋጅተው ይጠብቁታል። ቃለ ምልልሳቸው ከብዙ በጥቂቱ ይህ ነው።

አባት፦ እና አሁን በቃ ዶክተር ሁነሀልና የታመሙ ሰዎችን ማከም ጀመርክ እንዴ?

ልጅ፦ አይደለም አባቴ እኔ ዶክትሬቴን የያዝኩት በፍልስፍና ነው፤ ከህክምና ጋር አይያያዝም።

አባት፦ ደግሞ የሱ ጥቅም ምንድን ነው?

ልጅ፦ ላስረዳህ አሁን እዚህ ጋ የምታየው ዶሮ አንድ ዶሮ ብቻ ነው አይደል?

አባት፦ አዎ

ልጅ፡- በፍልስፍና እውቀቴ መሠረት ግን እዚህ ላይ ያለው ዶሮ አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ናቸው ብየ ላሳምንህ እችላለሁ።

አባት፦ "ማሻአላህ ልጄ ቀድመህ ካሁኑ አሳመንከኝ እኮ"

ልጅ፦ እንዴት?

አባት :- ጠረንጴዛው ላይ ያለውን አንድ ዶሮ እያነሱ "እኔ ይህኛውን ዶሮ እበላለሁ አንተ ካገኘኸው ሁለተኛውን ዶሮ መብላት ትችላለህ አሉት።

◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆

                   ~ @open_reading1 ~

                   ~ @open_reading1 ~
03.04.202515:54
ፋኖስ ይዞ ገበያ ውስጥ ሰው ሲፈልግ የዋለው ፈላስፋ  #ዲዮጋን
....................................................

ፍልስፍናን በመስበክም የሰበከውን በመኖርም በእውን ያሳዬ ፈላስፋ ዲዮጋን ነው! የተወሰኑ ፍልስፍናዎቹንና ድርጊቶቹን እነሆ...

━━━━━━━━
አንድ ቀን ጠዋት የግሪኩ ንጉስ ታላቁ እስክንድር በሰረገላ ሆኖ ታጅቦ እየሄደ እያለ ዲዎጋን መንገድ ላይ ድንጋዩን ተንተርሶ ተኝቶ ፀሀይ ሲሞቅ የእስክንድር አጃቢዎች ያዩና ለእስክንድር ይነግሩታል።
ታላቁ እስክንድር ከሰረገላው ወርዶ ወደ ዲዮጋን ይሄድና እየቀሰቀሰ "ዲዮጋን ተነስ እኔ ታላቁ እስክንድር" ነኝ ይለዋል! ዲዮጋንም እንደተሸፋፈነ "እኔም ለራሴ ታላቁ ዲዎጋን ስለሆንኩ ዝም ብለህ መንገድክን ሂድ" ይለዋል።
እስክንድርም ተገርሞ "አላወቅከኝም መሰል" ይለዋል።
ዲዎጋንም "ገና ቃል ሳትናገር ነው ያወቅኩህ" ይለዋል።
እስክንድርም "ሳታየኝ እንዴት አወቅኝ" ሲለው፤
ዲዮጋን ሆዬ "ፈጣሪ የሰጠኝን የጠዋት የፀሀይ ሙቀት በማን አለብኝነት የሚነጥቀኝ ካንተ ሌላ ስለለሌ ነዋ" በማለት አምባገንነቱን ይነግረዋል። እስክንድር ጎንበስ ብሎ ሲመለከት እውነትም የሚሞቃትን ፀሀይ ጋርዶታል።
እስክንድርም ፍልስፍናውን ስለሚወድለት ከመቆጣት ይልቅ ተለሳልሶ "እባክህ ለምነህ ከምትበላ ና ከእኔ ጋር እንሂድና በቤተመንግስቴ እኔ የምበላውን እየበላህ ኑር" ይለዋል።
ዲዮጋንም "ቤተመንግስት ውስጥ ንጉስን ሲርበው ጠብቆ ጥሩ ነገር ከመብላት በሚፈልጉበት ጊዜ የማይፈልጉትን መብላት ይሻላል" ብሎ ነፃነቱን መርጦ በልመና ኑሮው ቀጥሏል!(እንደታምታውቁት ቤተመንግስት ውስጥ ቢርብም በማንኛውም ጊዜ አምጡ እየተባለ አይበላምና።)

━━━━━━━━
ዲዮጋን የሚተዳደረው በልመና ነበር። ለምን በልመና እንደሚተዳደር ሲጠይቁት
"ሰዎችን ለማስተማር ነው" አላቸው፡፡
ለምንድን ልመናን የምታስተምረው? ሲሉት እኔ የማስምተረው "መስጠትንም" ነው ይላቸዋል። የሚሰጠው ሳይኖረውና ምንም ነገር ሳይሰጥ እንዴት ያስተምራል የሚለው ግራ ገብቷቸው እንዴት አድርገህ? በማለት ሲጠይቁት "መስጠት እንዲኖር ተቀባይ ያስፈልጋላ!" በማለት መልሶላቸዋል።

━━━━━━━━
ዲዮጋን ማንም የሚፈራውን ታላቁ እስክንድርን አይፈራውም ነበር። አንድ ጊዜ ታላቁ እስክንድር ከፊቱ ቀርቦ "ለምንድን ነው ግን እኔን የማትፈራኝ?" በማለት ጠየቀው፡፡
ዲዮጋንም "አንተ ምንድን ነህ? መጥፎ ሰው ነህ ወይስ ጥሩ ሰው?" አለው፡፡
ታላቁ እስክንድርም "ጥሩ ሰው ነኝ" አለው።
ዲዮጋንም "ታድያ ማነው ጥሩ ሰውን የሚፈራ?" አለው ይባላል፡፡

━━━━━━━━
በግሪክ ባህል ከቤት ውጭ ምግብ መብላት ነውር ነበር።
ዴዎጋን ይህንን ባህል ይቃወም ነበር። አንድ ቀን የለመነውን ምግብ ሰብስቦ ገበያ መሀል ቁጭ ብሎ ይመገባል። ህዝቡም ከቦ እያዬ በንቀት ይስቅበታል። በልቶ ሲጨርስ ተነስቶ ቆመና "ምን ያስቃችኃል?" አላቸው። ህዝቡም "ውጭ ላይ የሚበላ ውሻ ስለሆነ ገርሞን ነው" ይሉታል።
"ውሾችስ ሰው ሲበላ ከበው አይን አይን እያዩ ምራቃቸውን የሚውጡት ናቸው" በማለት ነውር የሚሆነው ውጭ መብላት ሳይሆን ከቦ አይን አይን ማየት መሆኑን ነገራቸው ይባላል!

━━━━━━━━
ለንማኛውም ዴዎጋን ማለት በጠራራ ፀሀይ ገበያ ውስጥ ፋኖስ አብርቶ ሰው ሲፈልግ የዋለው ሰውዬ ሲሆን ገበያ ውስጥ ፋኖስ ይዞ ያዩት ሰዎች ምን እያደረግክ ነው ሲሉት
እሱ፦ "ሰው እየፈለግኩ!"
እና በዚህ ፀሀይ ፋኖሱ ምን ያደርግልሀል ሲሉት
እሱ፦ "በዚህም ታግዠ እስካሁን አንድም ሰው አላገኘሁም" በማለት እውነተኛ ሰው መጥፋቱን የገለፀው ሰውዬ ነው!

እኔ የማደንቀው ያኔ የነበረውን ማህበረሰብ ነው! ምክንያቱም ለአንድ በልመና ለሚተዳደር ሰው ፍልስፍናዎች ትልቅ ቦታ በመስጠቱ!


◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
            
04.04.202515:01
ለልጄ እኔ የመረጥኳትን ልጅ ታገባለህ አልኩት

         "እምቢ" አለ

የቢልጌት ልጅ ናት ስለው ተስማማ


ቢልጌትስ ጋር ሄጄ እንዲህ አልኩት "ልጅህን ለልጄ እንትድርልኝ እፈልጋለሁ"

        ቢልጌትስ "አይሆንም" አለኝ

ልጄ የአለም ባንክ ስራ አስክያጅ ነው ስለው ተስማማ።
        
የአለም ባንክ ፕሬዝዳንት ጋር ደውዬ ልጄን ስራ አስክያጅ አድርግልኝ አልኩት።

ፕሬዝዳንቱም እያሳቀ "ቀልድ መሆን አለበት ጭራሽ አይሆንም" አለኝ

እኔም ልጄ የቢልጌትስ ሴት ልጅን እንዳገባ ነገርኩት።

       ያኔም ፕሬዝዳንቱ ተስማማ



(ፖለቲካ እንዲህ ነው የሚሰራው እሺ)😃

|| Source - ከአርምሞ  ገጽ የተወሰደ ..........
▬▬▬  ▬▬▬  ▬▬▬  ▬▬▬  ▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

◎ የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
16.04.202515:45
ዛሬውኑ ጀምረው!!!

1. ቤት እንዲኖርህ ከፈለግክ፣ መሬት በመግዛት ትጀምራለህ።

2. ኢምፓየር እንዲኖርህ ከፈለግክ፣ ንግድህን በማሳደግ ትጀምራለህ።

3. ጥሩ የሰውነት ቅርጽ እንዲኖርህ ከፈለግክ፣ ጤናማ ምግብ በመመገብ ትጀምራለህ።

4. ጥበበኛ መሆን ከፈለግክ፣ መጻሕፍትን በማንበብ ትጀምራለህ።

5. ዓለምን መዞር ከፈለግክ፣ ገንዘብ በመቆጠብ ትጀምራለህ።

6. ደስተኛ መሆን ከፈለግክ፣ አመስጋኝ በመሆን ትጀምራለህ።

7. ሀብታም መሆን ከፈለግክ፣ ገንዘብህን በአግባቡ በማስተዳደር ትጀምራለህ።

8. ጥሩ መሪ መሆን ከፈለግክ፣ መጀመሪያ ራስህን በመምራት ትጀምራለህ።

9. ጥሩ ወላጅ መሆን ከፈለግክ፣ ጥሩ አርአያ በመሆን ትጀምራለህ።

10. ስኬታማ መሆን ከፈለግክ፣ ትናንሽ እርምጃዎችን በመውሰድ ትጀምራለህ።

11. በራስ መተማመን እንዲኖርህ ከፈለግክ፣ በራስህ በማመን ትጀምራለህ።

12. አዲስ ክህሎት መማር ከፈለግክ፣ በየቀኑ በመለማመድ ትጀምራለህ።

13. ፈጠራ ያለው ሰው መሆን ከፈለግክ፣ አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር ትጀምራለህ።

14. ክብር እንዲኖርህ ከፈለግክ፣ ሌሎችን በማክበር ትጀምራለህ።

15. ጠንካራ ግንኙነቶችን መገንባት ከፈለግክ፣ ታማኝ በመሆን ትጀምራለህ።

16. ዓላማዎችህን ማሳካት ከፈለግክ፣ በግልጽ በማስቀመጥ ትጀምራለህ።

17. ሥርዓታማ መሆን ከፈለግክ፣ ቦታህን በማደራጀት ትጀምራለህ።

18. ነጻ መሆን ከፈለግክ፣ ፍርሃቶችህን በመተው ትጀምራለህ።

19. ለውጥ ማምጣት ከፈለግክ፣ መጀመሪያ ራስህን በመለወጥ ትጀምራለህ።

20. ማራቶን መሮጥ ከፈለግክ፣ በየቀኑ በእግር በመጓዝ ትጀምራለህ።

21. ንግድ መጀመር ከፈለግክ፣ ፍላጎትን በመለየት ትጀምራለህ።

22. ሌሎችን መርዳት ከፈለግክ፣ መጀመሪያ ራስህን በመርዳት ትጀምራለህ።

23. ቋንቋ መማር ከፈለግክ፣ በየቀኑ በመለማመድ ትጀምራለህ።

24. ፍሬያማ መሆን ከፈለግክ፣ ጊዜህን በጥበብ በማስተዳደር ትጀምራለህ።

25. እውቀት ማግኘት ከፈለግክ፣ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ትጀምራለህ።

26. ጤናማ መሆን ከፈለግክ፣ አዘውትረህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ትጀምራለህ።
27. ሰላም እንዲኖርህ ከፈለግክ፣ ቂምን በመተው ትጀምራለህ።

28. ጠንካራ መሆን ከፈለግክ፣ ፈተናዎችን በእምነት በመቋቋም ትጀምራለህ።

29. ደግ መሆን ከፈለግክ፣ መጀመሪያ ለራስህ ደግ በመሆን ትጀምራለህ።

30. ተጽዕኖ መፍጠር ከፈለግክ፣ እውነተኛ በመሆን ትጀምራለህ።

ስኬት በአንድ ጀምበር አይመጣም፤ ማንኛውንም ትልቅ ነገር ማሳካት ተከታታይ ጥረትን ይጠይቃል። ቤት መያዝም ሆነ፣ ንግድ መጀመር ወይም ክብርን ማግኘት፣ ጉዞው የሚጀምረው በአንዲት እርምጃ ነው። በፊትህ ባለው የዓላማ ትልቅነት ተስፋ አትቁረጥ። ያቺን የመጀመሪያ እርምጃ በመውሰድ ላይ አተኩር፣ ከዚያም ቀጣዩን፤ ብዙም ሳይቆይ፣ ህልሞችህን እውን ለማድረግ መንገድ ላይ ትሆናለህ። ዋናው ነገር፣ ምንም ያህል ትንሽ ቢሆንም፣ መጀመር እና ጽኑ መሆን ነው።

ማመንህን ቀጥል፣ እድገትንም ታያለህ።

◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
31.03.202517:37
ታማኝነትህን እና ለራስህ ያለህን ክብር ጠብቅ!
   
#ሁለቱ_አልማዞች
...............................................................

የግመል ነጋዴው በገበያው ለሽያጭ ከቀረቡት ግመሎች መካከል በአንዱ እጅግ ስለተሳበ ከሻጩ ጋር ድርድር ጀመረ።

በኃላም በዋጋ ተስማምቶ ግመሉን ገዝቶ ወደ ቤቱ ሄደ። የግመል ነጋዴው ቤቱ እንደደረሰ አገልጋዩን ጠርቶ የግመሉን ኮርቻ እንዲያወርድ ይነግረዋል። አገልጋዩ የግመሉን ኮርቻ ሲፈታ ከኮርቻው ሥር  አነስተኛ መጠን ያላት የተቋጠረች ከረጢት ያገኛል።

ከረጢቷን ሲፈታ በውድ የአልማዝ ማእድን ተሞልታለች። አገልጋዩም "አለቃ የገዟት ግመል በነጻ ጭና ያመጣችውን በረከት ይመልከቱ!" ሲል በደስታ ተሞልቶ ጮኸ። ነጋዴውም  በአገልጋዩ መዳፍ ላይ በጸሐይ ብርሀን የሚንቦጎቦጉ የአልማዝ እንክብሎች ሲመለከት እጅግ ተደነቀ...

ይሁንና "ግመሏን እንጂ አልማዞቹን አልገዛኋቸውም። አሁኑኑ ለባለቤቱ መመለስ አለብኝ" አለ - ነጋዴው።አገልጋዩም "ምን የማይረባ አለቃ ነው ያለኝ?!" ሲል በሆዱ ካወራ በኋላ "ማንም ሰው የአልማዞቹን ትክክለኛ ባለቤት ሊያውቅ አይችልም! ሲል ተናገረ...ይሁንና ነጋዴው ምክሩን ችላ ብሎ ጊዜ ሳይወስድ ባለቤቱን ፍለጋ ወደ ገበያው ተመለሰ።

ብዙም ሳይለፋ የተቀሩ ግመሎችን ለመሸጥ ገዢ ሲጠብቅ የነበረውን የግመል ሻጭ አግኝቶ ትንሿን ከረጢት መለሰለት።የግመል ሻጩም እጅግ ተደስቶ " እጅግ የከበሩ ማእድናቴን በኮርቻው ስር መደበቄን ዘንግቼ ነበር።

አሁን ሽልማት እንዲሆንህ በከረጢቱ ውስጥ ካሉት አልማዞች ውስጥ ለዐይንህ ደስ ያሰኘህን ውሰድ!' አለው..."ለከፈልኩት ገንዘብ ጥሩ ግመል ሽጠህልኛል። ተጨማሪ ሽልማትም ስጦታም አልቀበልም።" አለ - ነጋዴው።

ነጋዴው ስጦታውን አልቀበልም ቢልም ግመል ሻጩ እንዲቀበለው ይወተውተው ጀመር። በመጨረሻም ነጋዴው በፈገግታ ተሞልቶ "ከረጢቱን ልመልስልህ ስወስን ሁለት እጅግ የከበሩ አልማዞችን እራሴ ዘንድ አስቀርቻለሁ! ከእነርሱ የሚልቅ ሽልማት የለም!" አለው።

የግመል ሻጩ የነጋዴው የእምነት ቃል ሲሰማ እጅግ ተበሳጭቶ በከረጢቱ ውስጥ ያሉትን ውድ አልማዞች የጨርቅ እራፊ ላይ ደፍቶ ይቆጥራቸው ጀመረ።

ይሁንና ቆጠራውን እንደጨረሰ በእፎይታ ተሞልቶ "በከረጢቱ ውስጥ ከነበሩት አልማዞቼ መካከል አንድም አልጎደለም። የትኞቹን ውድ አልማዞች ነው ለራሴ አስቀርቻለሁ ያልከኝ?"

ነጋዴውም በኩራት ተሞልቶ "እኔ ዘንድ ያስቀረኋቸው ውድ አልማዞች
#ታማኝነቴና #ለእራሴ_ያለኝ_ክብር ናቸው!" ሲል መለሰለት።

                   ምንጭ: Afrimereja

◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆
                   ~ @open_reading1 ~

                   ~ @open_reading1 ~
18.04.202504:03
"ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ"

ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወንዙ ጥልቀት ለማወቅ ከወንዙ በወድያኛው ዳር
ያለውን ግመል ጠየቀው። ግመሉም ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ እንደሆነ ነገረው።

ቀበሮውም ጉልበት ድረስ ከሆነማ አያሰምጠኝም በማለት ለመሻገር ወደ ወንዙ ገባ። በሚያሳዝን ሁኔታ ወንዙ
ያሰምጠው ጀመረ። ይሄኔ ቀበሮው ግመሉ እንደሸወደው ተረዳና እንደምንም ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ተመለሰ፤ ራሱንም ከሞት አተረፈ።

ይሄኔ በንዴት ጮክ ብሎ "አንተ ያምመሀልን? ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ ነው አላልክምን?" አለው።

ግመሉም "አዎና! ታዲያ በራሴ ጉልበት ነው እንጂ ያልኩህ ባንተ ጉልበት መች አልኩህ?" በማለት መለሰለት። ቀበሮው በልምድ የቀደመውን አካል መጠየቁ ትክክል ቢሆንም የግመሉን ማንነት መርሳቱ ግን ስህተት ነበር። ግመሉም ልምዱን ማካፈሉ ትክክል ቢሆንም የቀበሮውን ማንነት ግን መርሳት አልነበረበትም።

✍ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እንደየራሳቸው ተሞክሮ ቢነጋገሩም የአንዱ ልምድ ለሌላው መፍትሔ ሊሆን ግድ አይደለም።
ባይሆን የአንደኛውን የህይወት ልምድ ለሌላኛው መጥፊያው ሊሆን ይችላልና ጥንቃቄ ማድረጉ ግድ ይላል። ለምሳሌ አንድ ሁለት ሴቶች አረብ ሀገር ሰርተው ተመልሰው ውጤታማ ቢሆኑ ሁሉም አረብ ሀገር የሄደ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ የሰዎችን የህይወት ተሞክሮ ወደ እራሳችን ህይወት አምጥተን ለመትግበር ስንዘጋጅ ማስተዋልና ጥንቃቄ አይለየን፡፡


               -  @open_reading1 -
@open_reading1  -  @open_reading1
አንድ ነጋዴ በመጋዘኑ ውስጥ ስራ ላይ እያለ በጣም የሚወደው የእጅ ሰዓቱ ይጠፋበታል፡፡ በመጋዝኑ ውሰጥ እየተመላለሰም በፍለጋ ቢወድቅ ቢነሳ ሊያገኘው ባለመቻሉ እውጭ ጨዋታ ላይ ያሉት ልጆች እንዲያግዙት፤ ሰዓቱን ላገኘለት ልጅም ሽልማት እንደሚሰጣቸው ነግሮ አሰማራቸው፡፡

ልጆቹም ሽልማት እንዳለው ባወቁ ጊዜ በፍጥነት እየተራኮቱ ወደ መጋዝኑ በመግባት ሁሉን ቦታ በአንድ ጊዜ አዳረሱት፡፡ ነገር ግን ሰዓቱን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ መጋዘኑ ውስጥ ያለውን እቃ ቢያነሱ ቢጥሉት ማግኘት አልቻሉም፡፡ ነጋዴው ልጆቹ እንዳላገኙት ባወቀ ጊዜ ተስፋ በመቁረጥ የሰዓቱን ፍለጋ ሊያቆም ሲል አንድ ትንሽ ልጅ ጠጋ ብሎ አንድ እድል እንዲሰጡት ጠያቃቸው፡፡ ነጋዴውም እስኪ ይሞክር በሚል ስሜት ፍቃደኛ ሆኑለት፡፡ ከቆይታ በኋላ ትንሹ ልጅ ሰዓቱን እጁ ላይ አንጠልጥሎ ተመለሰ፡፡

ነጋዴውም በሰዓቱ መገኘት እጅግ ደስ እያለው ሌሎቹ ልጆች ማግኘት ያልቻሉትን እንዴት ሊያገኘው እንደቻለ ተደንቆ ጠየቀው ትንሹ ልጅም “እኔ ምንም አላደረኩም ፡፡ ያደረኩት ነገር ከመጋዘኑ መሀከል ላይ በጸጥታ በመቆም ማዳመጥ ነበር፡፡ በፀጥታው ውስጥም የሰዓቱ መቁጠሪያ የሆኑት ዘንጎች ሲዞሩ የሚፈጥሩት ጠቅ…ጠቅ የሚለው ድምጽ ተሰማኝ ይህን አቅጣጫ ተከትዬ ስመለከት ሰዓቱን አየሁት” አላቸው፡፡

ግብረ ገባዊ ትምህርቱ በጽሞና ውስጥ የሆነ አዕምሮ ነገሮችን ለይቶ መረዳት ይችላል፡፡ አርቆ ለማሰብም ፋታ ያገኛል።

ስለሆነም ኳኳታ በበዛበት ዓለም ካለን ሰዓት ውሰጥ የተወሰኑትን ደቂቃዎች ለጽሞና ማዋል ከእራስ ጋር ለመነጋገርና መድረስ ወደምንፈልግበት የሕይወት ዓላማ አቅጣጫችንን ለማስተካከል ይረዳናል


◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆
                   ~ @open_reading1 ~

                   ~ @open_reading1 ~
01.04.202507:05
በጣም ዘግናኝ ነገር ማለት አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ሲሞት ሐዘኑ ሳያንስ "አባቴ አባቴ"  እያለ መቸና የት እንደተወለደ የማይታወቅ ግድንግድ ልጅ ከች ማለቱ....!

ያኔ ሚስቶችን አለማየት ነው..!  አስከሬኑንን ሁሉ በጀበና ቢፈነክቱት ደስታቸው) ብዙ ወንዶች ድብቅ ናቸው!

በኋላ ነው ጣጣቸው እየተጎተተ የሚመጣው...!

እና ሰውየው ጨዋ ነበሩኮ....
(ሰባት ዓመት ተጠናንተው ሁሉ የታጋቡ)

በሠፈሩ "ትዳርማ እንደሳቸው" የተባለላቸው...

የሁለት ልጆች አባት! ከሥራ ቤት ከቤት ሥራ

"ምነው ልጅ ጨመር ብታደርጉ ሀብት አላነሳችሁ"

ሲባሉ

"ምንድነው ልጅ ማብዛት ያሉትን በወጉ ማሳደግ ነው ዋናው " የሚሉ!

እና ድንገት ሞቱ ...

ልክ የቀብሩ ቀን ሶስት እግዜር ዲኤንኤ ውጤታቸውን በመልካቸው የፃፈባቸው ፣ ቁርጥ ሟቹን የመሰሉ ጠረንገሎ ጎረምሶች አባቴ አባቴ እያሉ ተግተልትለው አልመጡም...!?

ሚስትም ልጆችም ሐዘኑን እረስተው በድንጋጤ ታዛቢ ሆኑ

"ይሄ ሁሉ ልጅ" እያሉ...

ወዲያው አስከሬን ሊወጣ ሲል አዲሶቹ ልጆች

"አሁን አይቀበርም አህህህህ" ብለው  እያለቀሱ እየተናፈጡ ምናምን ከለከሉ ..!

ለምን ይባላሉ...

"አራት እህቶቻችን ከኋላ እየመጡ ነው እንጠብቃቸው
"

(በአሌክስ አብረሃም)
ከእንማር የተወሰደ...
20.04.202517:15
በሕይወት

ትልቁ መሰናክል— ፍርሃት

አስቀያሚው ስሜት— ጥላቻ

ትልቁ ስህተት— ተስፋ መቁረጥ

ምርጡ ስጦታ— ይቅርታ

ትልቁ ጥንካሬ— እምነት

በጣም ቆንጆው ነገር— ፍቅር

@open_reading1
@open_reading1
1-ድግስ ላይ አንዲት ቆንጆ ልጅ አይተ በመሄድ "ሃብታም ነኝ አግቢኝ" ብትላት፤ ይህ “Direct marketing” ቀጥታ ማርኬቲንግ ነው።

2-የሆነ ግብዣ ላይ ቆንጆ ሴት አይተህ አንዱ ጓደኛህ ወደዛች ልጅ በመሄድ ወደ አንተ እየጠቆመ ሀብታም ነው አግቢው ካለ ይህ “Advertising” ማስታወቂያ ነው።

3-አንዲት ቆንጆ ልጅ ወደ አንተ በመምጣት፡-"ሀብታም ነህ አግባኝ" ካለችህ ይህ “Brand” የምርት ስም እውቅና ነው።

4-አሁንም እቺ ልጅ ጋር ተጠግተህ "ሀብታም ነኝ አግቢኝ" ስትላት በምላሹ በጥፊ ብትመታህ ይህ “Costumer feedback” የደንበኛው አስተያየት ነው።

5-ግብዣው ጋር ወዳለችው ሴት ሄደህ ልታወራ ስትል አንድ ሌላ ቦርጫም ሰውዬ መጥቶ "ሀብታም ነኝ አግቢኝ" ቢላት ይሄ “competition” ውድድር ይባላል።

6-አንተ የፍቅር ጥያቄ አቅርበህላት እሷ ግን ከባሏ ጋር ብታስተዋውቅህ ይህ “Supply and demand gap” የአቅርቦት እና የፍላጎት ክፍተት ነው።

7-አንተ ወደ እርሷ ሄደህ ምንም ከማለትህ በፊት ሚስትህ ብትመጣ እነዚህ አዳዲስ ገበያዎች ወደ አንተ እንዳይመጡ የቀረጥና የቦታ ገደቦች ተጥሎብሃል እንደማለት ያለህ ነው።

ይህ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ ፕሮፌሰሩ ስለማርኬቲንግ ለተማሪዎቻቸው በአሪፍ እውነታ ምሳሌዎችን በመስጠት ያስረዱት ነው!
◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆
                   ~ @open_reading1 ~

                   ~ @open_reading1 ~
|| ዛሬ ዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀን ነው!

በዚህ ቀን መመስገን ካለባቸው ሰዎች አንዱን ላመስግን?

የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር) የመጽሐፍ የብርሃን መንገድ!!

በዚህ ዘመን ካሉ የሥነጽሑፍ ሰዎች መካከል ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር ) "ከጥቁር ሰማይ ስር"፣ "በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ስራዎቹ" መጻሕፍትን ጨምሮ እጅግ የተዋጣላቸው መጻህፍትን ለአንባቢያን ከማድረሱ በተጨማሪ የንባብ ባህል እንዲጎለብት፣የሀሳብ ውይይት እንዲዳብር እየሰራ የሚገኘው ስራ እጅግ አድናቆት የሚገባውና በብዙ መንገድ መበረታታት ያለበት ነው ብዬ አምናለሁ።

ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ በ"ዛጎል መጻሕፍት ባንክ"በኩል ሀገር እየገነባ ነው። የመጻህፍትን የብርሃን መንገድነት ለትውልዱ እያመላከተ ነው።

በኢትዮጵያ የተለየ ሀሳብ ይዘው ስራ ላይ ከሚገኙ ተቋማት መካከል አንደኛው የሆነው "ዛጎል መጻሕፍት ባንክ" ከ40ሺ በላይ መጻሕፍትን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሚገኙ ት/ቤቶች ፣ ማረሚያ ቤቶች ፣ በገጠር ከተማ ለሚገኙ ቤተ-ንባቦች ማሰራጨቱን ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል።

 ጋሽ
እንዳለጌታ ከበደ እንዱ ለሀገርም ፣ለትውልድም፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ለምትሰራው ስራ እጅግ የላቀ አክብሮት አለኝ።

## ምንጭ - ኤቨንት አዲስ - (Natty manaye)

                    መልካም የመጽሐፍ ቀን!
◆━━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
ሀገር ማፍረስ ከፈለጋችሁ አህዮቿን ከታሰሩበት ፈታችሁ ልቀቁ!
*****

ሰይጣን ከግንድ ጋር ታስሮ ያገኘውን አህያ እንዳሻው እንዲቦርቅ ቋጠሮውን ፈትቶ ለቀቀው። ነፃነቱን ያገኘው አህያም ወደ አንድ ሰው ማሳ ዘልቆ ከእርጥቡም ከደረቁም በጥርሱ ይግጠው ጀመር።

የአትክልቱ ባለቤት ሚስት በመስኮት በኩል ዘልቃ ስትመለከት ማሳው በአህያው ጥርስ ታጭዶ አገኘችውና ደነገጠች። ማሳቸው በአንዴ እንዲህ መሆኑ እያበገናት መሳርያዋን አቀባብላ ተኮሰችበት። በተደጋጋሚ የተለቀቀው ጥይት ሆዱን ዘርግፎ ከመሬት አጋደመው።

የአህያው ባለቤት የተኩስ ድምጽ ሰምቶ ከቤት ሲወጣ ከግንድ ጋር ያሰረው፣ በጀርባው ተሸክሞ ከወዲህ ወዲያ እያመላለሰ የሚያገለግለው አህያ በደም ተጨማልቆ ከመሬት መዘረሩን አየና ልቡ አዘነ። ሴትዮዋ በመስኮት ብቅ ብላ መሳርያዋን እንደሸከፈች በኩራት አህያህን ገደልኩልህ አይነት የጀግና አስተያየቷን ሲመለከት ክላሹን ወደ ሴትዮዋ አነጣጥሮ ደረቷን ብሎ ሲጥላት ባሏ በቦታው ደረሰ። ከኋላው ነበርና ተኩሶ የአህያውን ባለቤት ገደለ።

ሰይጣን ተጠየቀ። ምንድነው ያደረከው ተባለ።
አህያውን ፈታሁ እንጂ ምንም የሰራሁት ነገር የለም በማለት መለሰ።

ሀገር ማፍረስ ከፈለጋችሁ አህዮቿን ከታሰሩበት ፈታችሁ ልቀቁ ከታሪኩ የምናገኘው ትምህርት ይህ ነው።

◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
10.04.202513:23
መምህሩም እንዲህ አለ" ጥያቄህን እመልስል ዘንድ ወደ ስንዴው ማሳ ሂድና ከሁሉም መሃል ረጅሙን ቆርጠህ ይዘህ ና" "ግን አንድ ህግ አለ... አለ

መምህሩ" ... በስንዴው ማሳ ዉስጥ ማቋረጥ የምትችለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ አንዴ በማሳ ውስጥ እያለፍክ ትልቅ ነው ያልከውን ፈልገህ ቆርጠ ይዘክተመጣለህ፡፡ ወደ ኋላ ተመልሶ ሄዶ መቁረጥ ግን አይቻልም፡፡

✔️" ተማሪዉ ወደ ስንዴው ማሳ አቀና፡፡ የመጀመሪያውን ረድፍ አልፎ ሄደ፡፡ አዎን... እዛጋ አንድ ረዥም የስንዴ ዛላ ይታየዋል፡፡ ግን ሌላ ትልቅ ደግሞ መኖሩ አይቀርም፡፡ ስለዚህ እሱን ተሻግሮ አለፈ፡፡ አሁንም ግን ሌላ ረዥም ተመለከተ፡፡ ግን ደግሞ ሌላ የተሻለ ትልቅ ቢኖርስ... ይሄኛውንም አልፎ ነጎደ፡፡

በዚህ መልኩ የማሳዉን ገሚስ አልፎ ሄደ፡፡ አውን ግን አንድ ነገር እየከነከነዉ ነዉ፡፡ አዉን አዉን የሚያያቸው የስንዴ ዛላዎች አልፏቸው እንደመጣው ያህል ረዣዥም አይደሉም፡፡ አውን በርግጥም ከሁሉም በላይ ረዣዥሞቹን ወደ ኋላ ጥላሏቸው እንደመጣ ገባው፡፡ ግን ተስፋ ሳይቆርጥ አሰሳውን ቀጠለ፡፡ ቢሆንም ግን ማሳውን አቋርጦ ወደመገባደዱ ሲደርስ ከሁሉም በላይ ረዣዥሞችን የስንዴዛላዎች ወደ ዋላ ጥሎ እንደመጣ ተረዳ... በዶ እጁን ከማሳው ወጣ፡፡ ከማሳው ባዶ እጁን መዉጣቱን

✅የተመለከተው መምህሩም" እንግዲ ፍቅርማለት ይህ ነዉ አለዉ... ምንጊዜም የተሻለ ትፈልጋለህ ምንጊዜም ! ግን በስተ መጨረሻ ከሁሉም የተሻለዉን ጥለከው እንደመጣህ ትረዳለህ፡፡

ፍቅር ይህ ከሆነ ለመሆኑ ጋብቻስ ምን ይሆን? ጠየቀ ተማሪው፡፡"

ይህንንም ጥያቄ እመልሰልህ ዘንድ... አለ መምህሩ ልክ እንደ ቅድሙ አውንም ወደ ስንዴው ማሳ ትሄዳለ ከዛም ከሁሉም ትልቅ ያልከውን ቆርጠህ ይዘህ ትመጣለህ፡፡ አሁንም ግን ልክ እንደ ቀድሞ በማሳ ውስጥ ማለፍ የምትችለው አንዴ ብቻ ነዉ፡፡ ወደ ኋላ ተመልሶ መቁረጥ ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡ ተማሪው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ማሳው አመራ፡፡

ተማሪዉ እንደበፊቱ ያለመሸወድ ጠንቃቃሆኖዋል፡፡ እናም ማሳው መሃል እንደደረሰ አንዱን በቃ ተልቅ ነው ብሎ ያመነበትን አንዱን የስንዴ ዛላ ቆርጦ ወደ መምህሩ ተመለሰ፡፡

ይሄኔ መምህሩ እንዲ አለ " አየህ አሁን አንዱን ቆርጠህ ይዘ መጣህ፡፡ ሌሎች ተላልቅ ይኖራሉ አንተ ግን በዚህ የስንዴ ዛላ ረክተሃል፡፡ ቆንጆና ትልቅ ነዉ ብለህ እምነትህን ጥለክበታል፡፡ እናም ቆርጠህ ይዘኸው መጣህ፡፡ ይሄ ማለት እንግዲህ ሌላም ሳይሆን ትዳር ነው፡፡

🔸ከመምህሩ ምን እንማራለን እሚለውን ለ እናንተ ትቻለሁ ፡፡ መልካም ቀን ተመኘሁላችሁ፡፡

_ @open_reading1 _
|| በ 99 ዓመታቸው መጸሐፍ የሚጽፉ ጀግና አባት ስላሉን እንኳን አደረሶት ብንል የልጅ ወግ ነው።

           📷 Benju man

◆━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
17.04.202521:49
ሀዘን ሲሰማሽ እኔ እንዳለሁልሽ አስታዉሺ፣ ምናልባት በቂ ላልሆን እችላለዉ ግን ካጠገብሽ እሆናለሁ᎓᎓ ምክንያቱም እወድሻለሁ!

               -  @open_reading1 -
@open_reading1  -  @open_reading1
अधिक कार्यक्षमता अनलॉक करने के लिए लॉगिन करें।