Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Story's from my diary📝 avatar

Story's from my diary📝

@kalkidanfekadu
TGlist रेटिंग
0
0
प्रकारसार्वजनिक
सत्यापन
असत्यापित
विश्वसनीयता
अविश्वसनीय
स्थान
भाषाअन्य
चैनल निर्माण की तिथिSep 12, 2024
TGlist में जोड़ा गया
Feb 13, 2025
संलग्न समूह

रिकॉर्ड

19.04.202523:59
1.4Kसदस्य
13.04.202518:30
400उद्धरण सूचकांक
17.01.202510:24
1.7Kप्रति पोस्ट औसत दृश्य
18.03.202511:12
1.4Kप्रति विज्ञापन पोस्ट औसत दृश्य
13.04.202518:30
12.28%ER
10.02.202510:24
178.24%ERR

विकास

सदस्य
उद्धरण सूचकांक
एक पोस्ट का औसत दृश्य
एक विज्ञापन पोस्ट का औसत दृश्य
ER
ERR
DEC '24JAN '25FEB '25MAR '25APR '25

Story's from my diary📝 के लोकप्रिय पोस्ट

04.04.202518:27
🏠🏠🏠 የኛ ቤት 🏠🏠🏠

የእናት እና አባቴ ጉዞ

አባቴ ዓለም ላይ ካሉ ሰዎች ለኔ አስገራሚ ሰው ነው ልክ...አሌክስ አብርሃም "በአንድ ፊቱ እየሳቀ በሌላ ፊቱ ሚቆጣ አባት ያለኝ እኔ ብቻ ነኝ" ያለውን የኔም አባት እንደዛ እንደሆነ ብነግረው እንዴት ደስታ እንደሚለኝ

አንድ ቀን ምን ሆነ መሰላችሁ

"እናት እና አባቴ ይጨቃጨቃሉ (አትደንግጡ ፀብ አይደለም የተለመደ የባል እና የሚስት ግብር እየከፈሉ ነው) ታድያ አባቴ ጭቅጭቁ በጠበቀው መንገድ አልሄድ ሲለው ወደኔ ዞሮ ጠራኝ (እኔም አጠገባቸው ቁጭ ብዬ ፊልም እያየው ነበር ለምን አታገላግይም ነበር እንዳትሉ ምክንያቱም በባል እና ሚስት መሃል አይገባም)

"ቃልኪዳን "አለኝ ቆጣ ብሎ

"ወዬ አባ " መለስኩኝ

"ይቺ እናትሽን አንድ በይልኝ" ብሎ ከሷ ጋር ማፋጠጥ እናቴም በአይኗ ጮክ ብላ ስታየኝ እያየዋት የነበረው አይኔን ሰብሬ ወደ አባቴ ዞር አልኩኝ

"ቆይ ምንድነው የተፈጠረው?" ብዬ መጠየቅ አምናለው ቅብጠት ነው.... አያገባኝም ብዬ ብወጣ ይሻለኛል... ግን ያው ነው አያገባኝም ብልም ግልምጫው እና ስድቡ አይቀርልኝም ....ብቻ አባቴን የጠየኩት የጭቅጭቁን መንስኤ ማብራራት ጀመረ....

" እኔና እናትሽ ባለፈው ክፍለ ሀገር አልሄድንም... (አዎ ለማለት ጭንቅላቴን ነቀነኩ) እንደምታቂው የሄድነው በኮንትራት ነው... ግን ከዛ ቡሃላ ያለውን ትንሽ መንገድ በባጃጅ ሄደናል እና የባጃጁን የኔ እና የእናትሽን እኔ ነበርኩኝ የከፈልኩት.... አሁን ስለቸገረኝ የከፈልኩልሽን ብር መልሺልኝ ነው ያልኩት... እኔ የቤት አስቤዛ ገንዘብ በአግባቡ እየሰጠው ነው ከዛ ውጪ ያለው አያገባኝም... ስለዚህ ከእናትሽ ብሬን ተቀበይልኝ" ብሎ የጠየኩትን ጥያቄ አብራራልኝ.... ጨነቀኝ እንዴ ወደሱ ሳይ ኮስተር ብሎ እናቴን እንድጠይቅ ይጠብቀኛል በዛ ስዞር ደሞ እናቴ ፊቷ አጨማዳ "እስኪ ጠይቂኝ" አይነት አስተያየት ታየኛለች ፈርቼ ዝም አልኩኝ ዝምታዬ የፍራቻ መሆኑን የገባት እናቴ

"እስኪ ስንት ብር እንደሆነ ጠይቂው አባትሽን" አለችኝ እኔም ማወራው አገኘው ብዬ የሷን ጥያቄ ቀበል አደረኩና ለአባቴ መጠየቅ... ስንት ብር ቢለኝ ጥሩ ነው... 8ብር... ከዛ የብሩን መጠን ከነገረኝ በዋላ በግማሽ ፊቱ እየሳቀ በግማሽ ፊቱ እየተቆጣ ያየኛል እና አባቴ አያስገርምም ትላላችሁ.....ይሄ ሁሉ እኮ እናቴን ለማናደድ ብቻ ነው .....

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
04.04.202506:36
የኛ ቤት በተሰኘ ፅሁፍ በኑሮዬ የሚገጥሙኝን አስቂኝ አስገራሚ እና አሳዛኝ ገጠመኝ ለማጋራጥ አስቤያለሁ...... ምን ትላላችሁ ቤተሰብ ???

የመጀመሪያውን ዛሬ ማታ ይለቀቃል stay tuned 😊
से पुनः पोस्ट किया:
✍ዮ_ሚን avatar
✍ዮ_ሚን
18.04.202505:14
ተዓምር አይደለም?
ኤልያስ ሽታኹን
~    ~     ~      ~      ~
ሲሸቀጥ ሲነገድ ፍቅር ጉልት ዋለ
በራሱ ቀይ ደም እንጨት ላይ ተሳለ፡፡

ተዘባበቱበት፡፡

ያን ሁሉ ዓለንጋ መቻሉን ረሱ
"እስቲ ይውረድ" አሉ ከመስቀል በራሱ::
እስቲ ተዓምር አድርግ ይሉታል በዓለም
በታናሽ መገረፍ ተዓምር አይደለም?

"እስቲ ድንቅን አድርግ" ይላሉ - አይፈሩምና ጡር
ተዓምር አይደለም? መቸንከር በፍጡር?

ልፍስፍስ ነው አሉት
ደካማ ነው አሉት
ወከባ ነው አሉት አይችልም ማስገረም
እናትን እያዩ መመታት በራሱ ተዓምር አይደለም?

ተዘባበቱበት::
እንደራቆተ ዋለ ባደባባይ
ምድርን ያለበሰ በደመና ሰማይ፡፡
ከንፈር ስንት ገባ? ተጠምቶ አደረ
ውኃ ለሁለት ከፍሎ እንዳላሻገረ፡፡

ማቀፍ ስንት ገባ?
መሳም ስንት ገባ? 
ዋጋው ተወደደ ወይስ ቀዘቀዘ
ዓለምን የያዘ
            በዓለም ተያዘ፡፡

ተዓምር አይደለም?

https://t.me/yomin1_2
से पुनः पोस्ट किया:
🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️ avatar
🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️
02.04.202519:14
CODE 11

ጓደኛ አለኝ ብዬ ነበር ለረጅም ጊዜ የማስበው... ለካ ያልተረዳሁት ብዙ ነበር ...እነሱ እንጂ ጓደኞቼ  የነበሩት እኔ ምናቸውም አልነበርኩም። የሆነ ቀን ከመንገዴ ቆም አልኩ፤ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ ባስብም ጓደኝነታቸው ላይ አንዳች ጥርጣሬ አልነበረኝም።ከእራሴ ጋር ሰጣ ገባ ውስጥ ገባሁ ፤ እነሱን ላለማጣት ይሁን እውነታውን ፈርቼው ራሴው ላይ እንከን መፈለጉን ተያያዝኩት ። ከሁሉም ርቄ ከራሴ ጋር ተማከርኩ፤ ብዙ አሰብኩ።....መጨረሻ ላይ የፈራሁት እውነት ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጥኩ። እንዳላጣው የፈራሁት ጓደኝነት ለካ  ቀድሞውኑ  ያልነበረ ነው፡፡በእኔ ፈላጊነት እና በእነሱ ተፈላጊነት ላይ የተንጠለጠለ ወዳጅነት፤የእኔ ጥረት ብቻ ያስተሳሰረው ቀጭን መስመር መሆኑን ተረዳሁት። አላዘንኩም፤ እንዲያውም በራሴ በማወቄ ደስ አለኝ፤ እንኳንም ሳይጥሉኝ  መገፋቴን ደረስኩበት አልኩ።🪡

ያንን ባውኩበት ማግስት እነሱን ከልቤም ከህይወቴም  ለማስወጣት መንገድ አልጀመርኩም። ይልቁንም ጭላንጭል ተስፋን ብርሃን አድርጌ የእውነቱን እውነታነት ለማየት ሞከርኩ። ምንም ሳልላቸው ከስራቸው መገኘትን ቀነስኩ፤ምሽጋቸው ድረስ እየሄድኩ አቤት ማለቱን እርግፍ አድርጌ ተውኩት........ እና       ከመድረካቸው መውረዴ ማንንም ምቾት አልነሳውም ነበር  ልክ መኖሬ ምንም እንደማይፈድው ሁላ:: አሁን ግን ቆረጥኩ።ወጣሁ ከህይወታቸው ፤ ወጡ ከህይወቴ :: መኖር  ይቀጥላል አይደል ሚባለው♾️

✍️🏽ቃል

https://t.me/Piece_of_pages
से पुनः पोस्ट किया:
🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️ avatar
🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️
03.04.202517:19
CODE 1

                        አይፍቱኝ አባ

"እና ምን ታስባለህ?" ነበር ያለኝ.... በጥያቄው ተደናግጬ የምለው ጠፍቶብኝ ስደናገር "አቅመ ደካማ ነክ በቂ የሆነ የገቢ ምንጭ የለክም.... ይቺኛዋ ለዘላለሙ አርፋለች እና የቀረችውን ብታተርፍ ይሻልካል.... እኛ ጋር የተፈጠረው ስህተት ለማንም ማትናገር ከሆነ የቀረችውን ልጅ ውጪ ወስደን እናሳክማታለን" አለኝ..... እንዴት እንዳላፈረ ተገረምኩ.... አንዷን ልጄ ላይ ላደረሰው ስህተት የሌላኛዋ ልጄ ነብስ ቁማር ላይ ሲያስቀምጣት...... ንዴት ናረብኝ ተነስቼ አንባረኩበት
"እንዴት እንዲህ ትጠይቀኛለክ?? አባቷ እኮ ነኝ.... ስንት ነገር ያየሁባት ልጄ ናት:: እንዴት በቀላሉ በቃ ሞተች ስተቱ የኛ ስለሆነ ያቺኛዋን እናሳክማት ዝም በል ብለክ ትጠይቀኛለክ?? እንዴት አታፍርም? ህሊና እንዴት አይኖርክም? እንዴት በጥፋትክ እንኳን ኃላፊነት አትወስድም?" ምይዘው ምጨብጠው አጣው......እንደ እብድ አደረገኝ.... አንዷ መሞቷ ሳያንስ ሌላኛዋም እንደምትሞት ሲነግሩኝ እራስነቴን ጠላው.... ድህነቴን እረገምኩት አቅመ ቢስ መሆኔ አስጠላኝ.... ከሰው ሁሉ አነስኩኝ ሰማይ ምድሩ ዞረኝ.....ለአንድ አባት ልጆቹ ማለት አይኑ ናቸው.....የኔ አንዷ አይኔ ጠፋች ሌላኛዋም ትጠፋለች ሲሉ... ሳትጠፋ በፊት የኔ አይን የጠፋ መሰለኝ.... ሁሉም ነገር ጭልም አለብኝ ሰውየው አሁንም አልተመለሰም ከመቀመጫው ተነስቶ " ይሄ የኛ ስህተት አይደለም አላልኩም ግን በአንድ ስህተት የእድሜ ልክ ልፋቴ ከንቱ ሆኖ ሲተን ዝም ብዬ ፍትህ ይቀድማል ብዬ የምቀመጥ ሰው አይደለውም....ጥፋቱን ያደረሱትን ባለሙያዎች ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ.... ግን በራሴ መንገድ" ብሎ አንባረቀ በተራው...... " ሁላችሁም የእጃችሁን ታገኛላቹ" ብዬ ፎክሬ ክፍሉን ለቅቄ ወጣው ።

ከክፍሉ እንደወጣው ባለቤቴ የልጇ ሞት ተነግሯት ለያዥ ለገናዥ አስቸግራ ትጮሀለች ትንሿ ልጄ አንዱን ግድግዳ ተደግፋ ታነባለች..... አንዳች ስሜት ሰውነቴን ወረረኝ እዛው እንዳሉ ጥያቸው ሆስፒታሉን ለቅቄ ወጣው.... አስፓልት ተሻግሬ ሰው ጭር ያለበት አንድ መግቢያ ፈልጌ ወዲህ ወዲያ እየተንቆራጠጥኩኝ ማሰብ ያዝኩኝ ድህነት መጥፎ ነው አባ..... ሃዘንክን እንኳን በአግባቡ እንድትወጣ ዕድል አይሰጥም..... የሞተችውን ልጄን የነብስ ዋጋ ተቀብዬ የቀረችውን ባተርፍስ ብዬ ሳስብ አባትነቴ ልቤን አቆሰለው የመጣው ይምጣ ብዬ የልጄ ጉዳዮች በህግ ብሄድ.... በየትኛው አቅሜ ጠበቃ አቆማለው.... በዛ ላይ ዳኛው ጠበቃው ጠቅላላ የገንዘብ ሰው.... እውነት ይዞ የመጣ ሳይሆን በእጁ ይዞ የመጣን የሚያስቀድሙ ስግብግብ ጭራቆች እንዴት አምኘ ተሟገቱልኝ እላለው.. የቀረችውን ልጄ አንድ ነገር ስትሆን እንዲ ያበደችው ባለቤቴ ምን ትሆንብኝ ይሆን... አባ ለአንድ አባት ለቤተሰቡ በቂ አለመሆን ትልቅ ውድቀት ነው ግን እንደኔ ደሞ የአንዷን ልጄ ሬሳ ረገጦ ሌላዋን የማትረፍ ቁማር ውስጥ የገባን አባት ምን እንደሚባል እንጃ......ነብሴን አርክሼ.... የድህነት ጅራፍ ጀርባዬን እያደማው የወንድነት ክብር ደረቴን ሰብቆ ትንፋሼን እያሳጣኝ....
አንገቴን ደፍቼ ቢሮው ገባው እና በሃሳቡ ተስማማው

ልጄን እያለቀስኩ ቀበርኳት... ለምን ሄድሽ ከሚለው ይልቅ ይቅር በይኝ በሚል ተማፅኖ ከአፈር አስገባዋት ከአንድ ሁለት ሳምንት በዋላ ትንሿን ልጅ ቃል በገቡት መሰረት አሳከሟት...
ጊዜ ባለፈ ቁጥር.... ባለቤቴ በትንሿ ልጅ እርዳታ ፊቷ እየፈካ መጣ ልጄም ቢሆን ከተደረገላት ሕክምና ሰውነቷ ደና ሆነ የኔ ግን ሁለቱንም እየጠፋ መጡ.... ገፅታዬም ሰውነቴም.... ስራዬ ሆን ብሎ ከነሱ መሸሽ ነበር.... ያለ ልክ ጭንቅላቴ ማሰብ እስኪያቆም እጠጣለው..... እንዲጠሉኝ ያልሆኑትን ሆናችሁ ብዬ እሳደባለው..... ባለቤቴ በዚህ ነው አናግረው ብላ የላከቾት አባ እኔ መኖር ሚገባኝ ሰው አደለውም.... የራሴን ስንፍና እና ፍርሃት ነው በልጄ ነብስ የቀየርኩት.... ልጅህን ለማትረፍ ነው እንዳትሉኝ.... እራሴን ለማዳን ነው ያረኩት..... በባለቤቴ አይን ያለኝን ክብር ላለማጣት.... ወልዶ ወልዶ ለሞት ከሚለው የማህበረሰብ ሀሜት ለማምለጥ.... ገፊ እየተባልኩኝ ሰው አፍ እንዳልሰደብ.... የወንድነቴን ክብር ለማትረፍ ነው ልጄን ያተረፍኳት።.....እንደው ባለቤቴ ምን ትለኝ ይሆን አንዷ ልጃችንን ያተረፍኩት የሌላኛዋን ልጄን የሰውነት መብት ገፍፌ ነው ብላት ምን ትል ይሆን? ለልጄስ የእህትሽ ነብስ ነው ባንቺ ነብስ የቀየርኩት ብላት ምን ትለኝ ይሆን??.... በነሱ አይን ለመክበር ብዬ ያደረኩት ነገር በራሴ አይን አወረደኝ ......

አሁን የመጣውት አባ ባለቤቴ እዳለችው ከእርሶ ጋር ተማክሬ ለመስተካከል አይደለም ወይም ሀጥያቴን ተናግሬ እንዲፈቱኝም አይደለም..... የልጄ ድምፅ እንቅልፍ ነስቶኛል..... እርሶ ለፈጣሪ ስለሚቀርቡ እንዲህ ብለው ይንገሩልኝ አባ..... በምድር ጠብቃት ብለክ የሰጠከኝ አባቷ የልጅቱን ነብስ ከራሱ ክብር አስበልጦ ማየት አልቻለም እና አንተው የሰማይ አባቷ ጠብቃት..... ምንም የማታውቅ የዋህ ነብስ ናትና አንተው ከልብህ አቆያት ....የምድር አባቷ ያጎደለባትን ፍቅር እና ፍትህ አንተ በቤትህ ሙላላት .....ያልተገባትን ሆናለችና የሚገባትን ስጣት" በሉት አባ ይቅር እንድትለኝ አይደለም ብቻ ነብሷን እንድትረጋጋልኝ ይንገሩት.... አባቷ ደካማ ሆኖ ነው እንጂ ለውድ ልጄ ያ ተገብቷት አይደለም.... እኔ ስራዬ ነው እስከለተ ሞቴ እራሴን ጠልቼ እና ወቅሼ እንድኖር ያደረገኝ ስራዬ ነው.... እሷ ምን በወጣት ነብሷ ይታወክ...... አባ ለሚያምኑት አምላክ ይሄን ይንገሩልኝ ....እኔ በምድር የሰራሁትን በምድርም በሰማይም ቅጣቴን እቀበላለሁ... የልጄን ነብስ ብቻ እንዲያረጋጋ ለፈጣሪ ይንገሩልኝ ...እኔ ጥፋቴ ነው አባ ይቅርብኝ አይፍቱኝ..... አይፍቱኝ አባ.....

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
06.04.202509:02
01.04.202519:25
                       
                   ስንት አይነት ሞት አለ

"ስንት አይነት ሞት አለ?" ጠየኩት..... ደስታዬን መቆጣጠር አቅቶኝ ፊቴ አንደ በራ ጥርሴም እንደ ገጠጠ ነው ያለሁት ....እሱ ግን ዝም አለ....... ተናደድኩ....... ወዳሰርኩት እጅ አመራሁና ገመዱን ጥብቅ አደረኩት..... ጮኸ ደስ አለኝ.......የፊቴን ፈገግታ ሳልቀንስ ፊት ለፊት ካለው ወንበር በድጋሚ ተቀመጥኩ...... ጥያቄውንም  በድጋሚ አቀረብኩኝ........

"ስንት አይነት ሞት አለ?"

"የአሟሟት አንጂ የሞት አይነት  አለው እንዴ" አለኝ በብዙ ትንፋሽ በታገዘ ድምፅ

"አለው አንጂ...... በደንብ አለው"በስመአብ መቼም ፈገግታዬ ለጉድ ነው....... በዓለም ላይ ቁጥር አንድ ሃብታም በአንድ ቀን ብሆን አንኳን አንዲህ ደስ የሚለኝ አይመስለኝም.... ፊቴም ሰዉነቴም መንፈሴም ሁሉም እርካታ እና ደስታ ነው የሚያፀባርቁት "እኔ አነግርሃለሁ ካላወክ እሺ.... እንዴ ሳታውቅማ አትሞትም "ሃሃሃሃሃ ሌላ ሳቅ

"የመጀመርያው የሞት አይነት....... ሕያው አያልኩኝ ነው የምጠራው........ ስጋቸውን አደብ አስገዝተው ነብሳቸዉን ያከበሩ የዓለምን ከንቱ ሞኞት እና ሕልም ረስተው አምላካቸውን ያነገሱ  የሰማይም የምድርም ጀግኖች...... ሥጋችን ሞቷል ብለው በቁማቸው ተዝካር የሚደገስላቸዉ የምድራችን አንቁዎች...... ሞተዋል ብለው ባረከሱት ሥጋቸው አምላካቸዉን በማስቀደም ያከበሩት ነብሳቸው ሁለቱም ሕያው አድርገው የሚኖሩ በዚህ እሾህ ዓለም መሀል ለምልመው የበቀሉ የምድር አበቦች ናቸው......

እሱም ያዳምጠኛል እኔም በራሴ ፍልስፍና የፈጠርኩትን የሞት መደብ የመጨረሻ የምድር የሚሰማው ተረት አድርጌ እተርክለታለው.... ቀጠልኩ

ሁለተኛው የሞት መደብ....የሰው ሞት ...ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ሰርክ ተነስተው የለት ግብራቸውን የሚያከናውኑ ፍጥረቶች.... በደላቸው ይብለጥ ጥፋታቸው የለት ተለት ጥያቄ የሆነባቸው.... አንድ ሰሞን ነጠላ አደግድገው ቤቱ ደፋ ቀና ይላሉ.... ሌላውን ቀን ደሞ ቤተ ክርስቲያን ለምኔ ብለው በዓለም ደስታ ይዋጣሉ ...ስጋቸውም ይሁን ነብሳቸዉ ከምድር ይሁን ከሰማይ ሳይለይላቸው እንዲሁ እንደተደናበሩ ይሄን ውዝግብ ዓለም ጥለው የሚያልፍ ምስኪን ነብሶች ናቸው ሁለተኞቹ....

አይዞክ እኔና አንተ ይሄኛውም ውስጥ የለኝም ገና ነው የእኔና ያንተ መደብ.... የእኔና ያንተ መደብ ሶስተኛው ነው.... አንተ በዳይ እኔ ተበዳይ ብንሆንም ወርደን ወርደን አንድ ምንሆንበት ብቸኛው አንድ የሚያረገን ነገር ነው.... ልነግርህ አይደል ተረጋጋ ....ሃሃሃ

ሶስተኛው የሞት አይነት.... የቁም ሞት እለዋለሁ ... ስሥጋችንን ብለን ነብሳችንን የገደልን.... በበቀል እና በንዋይ የደነዘዝን በምድር ብቻ የምንኖር የሚመስለን ግብዞች...በምድር ፈላጭ ቆራጭ ስለሆንን የሰማዩንም ማዘዝ የምንችል የሚመስለን የሰው እንቅፋቶች..... ሰውነታችንን በነጠላ ሸፍነን ቤቱ ቆመን ይቅር በለን እያልን ስቀለው ብለው ከሚጮሁት ጋር አብረን የምንጮህ ቂመኞች...... በስሙ  ተጠርተን አንገታችን ላይ ያንጠለጠለውን ማህተብ ሳንፈራ ህጉን በህጋችን ሽረን በተቸነከሩት  እግሮቹ  እዥ እያፈሰስን ቁስሉን የምናመረቅዝ እስስቶች - - -    የስልጣን ልባችንን ወንሮ የሰውን ደም እንደ ውሃ በየቦታው የዘራን የምድር ጭራቆች ....የምንገባበት ለማወቅ ምፅሀት የማያስፈልገን ሴጣንን አክብረን ቀድሰን አንግሰን የምንኖር  ከላይ እግዜርን  በውስጥ ሴጣንን የምናመልክ አስመሳይ እባቦች እኛ ነን ሦስተኞቹ       

ሁሉን ያቅር ብያለዉ ከቤት አውጥታ የጣለችኝን የእንጀራ እናቴን ....በሚስቱ ፍቅር ታወሮ የልጁን  ህመም ማየት ያልቻለውን ጅሉን አባቴ  .....ላሳድግሽ ብላ የቤት ሰራተኛ የረገችኝን አክስቴን ....ብትናገርም ማንም አይምናትም ብሎ ቀን ከሌት ሲጫወትብኝ የነበረው ጨካኙ የአክስቴ ባል ... ሁሉንም ይቅር ብያለው .... ያንተን ግን ልቤ እምቢ አለኝ ።

ከመቀመጫዬ ተነሳሁ ውስጤን ያነቀኝን እንባ በመቋጠር ሞከርኩኝ አልሆነልኝም እንደ ዠረት በዚና እ በዛ እንባዬ ወረደ..... የቅድሙ ደስታ ጠፋና በምትኩ በቀል እና ንዴት ሰውነቴን ወረረው ....በመማፀን ይሁን መለመን በማላቀው ድምፅ ጠየኩት "እናቴን ለምን ገደልካት? ነብሷን እንዴት ከስልጣን ረከሰብክ? ንገረኝ እሷን ገለክ ያገኘሀውን ንብረት እሳት አልሆነብክም?? የኔ የዘመናት  እንባ ውስጥን አላቃጠለውም?ንገረኛ?? ጮኩኝ የዘመናት ጥያቄዬን በልመና ጠየኩኝ

"ይቅርታ ልጄ.... ስልጣን መጥፎ ነው ህሊናን ያሳጣል....የእናትሽ ነብስ የእግር እሳት ሆኖብኝ ዘወትር ንስሃ እየገባው እንኳን አልነፃ ያለኝ የነብስ እዳ ነው.... ባይገባኝም ይቅር በይኝ..... በበቀል ሕይወትሽ አይጨልምብሽ የሰው ነብስ እርግማን ነው ዘላለም ታጥበሽው የማይለቅ ቆሻሻ.... ተይ ቆሽሼ አላቆሽሽሽ ተይ ልጄ " ሃሃሃሃ የቅድም ደስታዬ ተመለሰ እንደዋንጫ የጋዙን ጄሪካን አንስቼ በደምብ እንዲያየው በእጆቼ ከፍ አደረኩት.... አጠገቡ ሄጄ ሰውነትቱን በነዳጅ አለበስኩለት......" ተይ ብሎ ነገር የለም.... ቅድም ሁለታችንም አንድ ነን ያልኩት ለምን ይመስልካል በእናት እጦት የተሰቃየውትን ስቃይ በወዳጆቼ በደል ወደ በረዶነት የተቀየረውን ልቤን ያንተን ሰውነት አቃጥዬ አቀልጠዋለው በጩኸትክ ጩሀቴን እሽርበታለው.... በለቅሶክ እንባዬን አብስበታለው.... በሕይወትክ ኖረክ ባታስተካክለውም  ለስልጣንም ይሁን ለገንዘብ ለክብር ይሁን ለንግስና የሚገበር ጥፋት ሁሌ ዞሮ ዞሮ ተጠያቂው ነፍስ መሆኗን ትማርበታለክ እኔም በእድሜ ልክ የበቀል ጥማት እፎይ እላለው ....ክብሪቱን ለኩሼ እግሩ ላይ ወረወርኩት መንደዱን ሳይ  ፊቴን አዙሬ ጉዞዬን ጀመርኩኝ.... ጩሀት እና ልመናው ከዋላዬ ቢሰማኝም... የደነገገውን ልቤን አላራራልኝም....

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
03.04.202517:19
Eyegebachu vote aderegu beteseb🙏🙏🙏🙏
से पुनः पोस्ट किया:
🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️ avatar
🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️
25.03.202507:52
CODE 1    

               ምን ለብሼ ነበር

"እጠብቅሻለሁ.... በማውቀው እና በምወደው ነገር ሁሉ እምልልሻለው እርግጠኛ ሆነሽ የኔ እስክትሆኚ ድረስ እጠብቅሻለሁ.... ብቻ አንድ ተስፋ ስጪኝ....እንድጠብቅሽ  ብርታት የሚሆነኝ..... ሰዎች ከሚያወሩት ስታልፊ አይናቸውን አስከትለው ከሚያሙሽ በሙሉ እጠብቅሻለሁ.... በውስጥሽ ከምትፈሪው ብዙ ወንዶች መንገድ ላይ ስታይ በፍርሃት ልብሴን ጨምድደሽ እንድትይዥ ከሚያረገው የሰቀቀን ስሜትሽ እጠብቅሻለሁ  ....አትገቢም ብሎ ከሚያሳንስሽ ሁሉ አንግሼ ክብርሽን አሳያቸው..... እንደ አምላክ እያመለኩሽ ዘላለሜን እኖራለሁ.... ሴት ልጅ በራሳነቷ እንጂ ሌላ በምንም መከበር እንደሌለባት ለዓለም አሳያለው.... ብቻ ፍቀጂልኝ" ነበር ያለኝ ትናንት ማታ ላይ ቢለኝም አሁን የተናገረ ይመስል እያንዳንዱ ቃል ጭንቅላቴ አንዱንም ቃላት ሳይስት ደጋግሞ ይለዋል

እንደሚጠብቀኝ አውቃለሁ.... ዛሬ ቃል አውጥቶ ተናገረ እንጂ የየለት ተግባሩ እሱ ነው.... ቤተሰቤ ከነሱ ውጭ ሚያምኑት ሰው ቢኖር እሱን ብቻ ነው... እንደዛ ቢቻላት ሰው ከሚያመኝ እና ከሚጠቋቆሙብኝ ተመልሳ ወደ ሆዷ ማስገባት ምትፈልገው እናቴ እንኳን እሱ ጋር ስሆን ነው ምትረጋጋው.... ጎረቤታሞች ሆነን ነው ያደግነው እኔ ላይ የደረሰው ነገር እኔን ቀየረኝ እንጂ እኔም እንደዚ እንደሱ ነበር ምንሰፈሰፍለት.... ከደረሰብኝ ጥቃት በዋላ ግን የወንድ ሰውነት ሳይ ስቃይ እና ጩኸቴን እያስታወሰኝ ወንድ የተባለ ማየት እንኳን ፈራው.... በብዙ መከራ እና ትግስት ነበር እሱን መቅረብ የጀመርኩት.... የሰፈሩ ሰው ሁሉ ምን ብታስነካው ነዉ ከዚህ ሁሉ ነገር በዋላ እንደዚህ ስሯ የሚርመጠመጠው ብለዉ ቢፈርዱበት እንኳን ሁሌ ከኔጋ ሲሆን ሽልማት እንዳገኘ ሰው ነው አለሙን ሚረሳው... እኔም አልነገርኩትም እንጂ ከሱ ጋር ስሆን ነፃነት ይሰማኝ ጀምሮአል ቤተሰቦቼ እኔን ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ቅጥ ያጣ ቁጥጥር የሆንኩትን ነገር ቀን በቀን ያስታውሰኝ ነበር እሱ ጋር ስሆን ግን እንደ ማንኛውም ሰው ለመሆን ነበር ምሞክረው.... ታዲያ ለምን ልጠብቅሽ ሲለኝ ዝም አልኩት???

ጥቃት ሲደርስብኝ የለበስኩት ልብስ በደም ተጨማልቆ የቀረው ደሞ የመሬቱን አፈር ይዞ ሰውነቴ ጠቅጡ አይታይም ነበር.... ፊቴም በእንባ ተሞልቶ ሰውነቴም በማምለጥ ካረገው ያልተሳካ ትግል ምክንያት ዝሎ ነበር .....እዛው በተኛሁበት የሞት አፋፍ ላይ ጥለውኝ ሄደው የሰፈር ሰዎች ነበር አግኝተው ሆስፒታል የወሰዱኝ... ሆስፒታል ውስጥ የእናቴ ጩሀት የአባቴ እና የወንድሜ የቁጣ ንግግር የእህቴ እናቴን በማፅናናት የምታደርገው ጥረት... ከተኛሁበት ክፍል ሆኖ ይሰማኝ ነበር... ሆስፒታሉ ሪፖርት ስላደረገ ፖሊሶች መተው ጥያቄ ይጠይቁኝ ጀመር

"ታስታውሻለሽ የሆነውን?"
ዝም

"ምታስታውሺውን ብቻ ንገሪኝ?"

ዝም

"ጥቃት ያደረሱብሽን ታስታውሻቸዋለሽ?"

ዝም

ከሁሉም የገረመኝ ጥያቄ "ምን ለብሰሽ ነበር?" የዚን ጊዜ አምርሬ አለቀስኩኝ... ለምን እንደዛ እንዳለቀስኩኝ በሰዓቱ ግልፅ አልሆነልኝም ነበር....አሁን ሳስበው ግን ይመስለኛል ያለቀስኩት .....ሴትን ልጅ ባደረገችው ልብስ ብቻ ጥቃት ይድረስባት አይድረስባት ብለው ከሚወስኑ የሕግ ሰዎች ጋር እንደምኖር አስቤው ነው መሰል ወይም........ ሴትነታቸውን ለባህል እና ለወግ ሽጠው አንድ ሴት ጥቃት ሲደርስባት እንደማገዝ እንዳበቃላት እና ተስፋ እንደሌላት ከሚያስቡ ሴቶች መሃል ስለምኖር ይሆን አልያም........ የእንስሳነት ስሜት ይዟቸው አንዲትን ሴት ያለፍላጎቷ ከተጫወተባት ሰው ይልቅ የተጠቃችው ሴት ከጥቃቱ ይበልጥ ህመም ከማህበረሰቡ እንደምታገኝ ተገንዝቤ ይሆን????? ታድያ ለምን አለቀስኩኝ?? ባለፍኩኝ ቁጥር እየተከታተሉ ብቸኝነቴን እና የበታችነቴን የሚነግሩኝ ሴቶች ነበሩ.... ሴትነታቸውን በምን ለክተው ይሆን ብዬ አስባለው...... ሴት ልጅ ክብሯ ከሌለ ሰውነቷ ያበቃል ማለት ነው?? የሴትነት ዋጋስ በምንድነው ሚተመነው?? እነሱ ከኔ በምን ተሽለው ነው ዋጋቸው ከኔ ከፍ ያለው.... እኔ በግድ የተነጠኩትን አስተሳሰብ እነሱ በፍቃድ ተቀብለው የወንድ ልጅ ባርያ መሆን ከፈለጉት ዋጋዬ በምንድነው ያነሰው?? ደፋሪዎቼ ተይዘው ለፍርድ ቢቀርቡም የፖሊሶቹ ጥያቄ ግን አሁንም ጭንቅላቴን ያናውጠዋል.... በጩሀቴ እና በቅዘቴ መሃል ከእንቅልፌ ስነቃ መጀመሪያ ጭንቅላቴ ላይ ሚመጣው ጥያቄ "ምን ለብሰሽ ነበር?" ነው ምን ብለብስ ነበር ከጥቃት ማምለጥ እችል የነበረው? ምን ለብሼ ቢሆን ነው ሰዎቹ አው አጥፍተዋል ይባል የነበረው? ማይሆን ልብስ ብለብስ ኖሮ ልክ ናቸው ይለኝ ይሆን? ምናልባት ለአንዳንዶቹ ጥያቄው ከአንድ እራሱን ካረከሰ የሕግ አካል የወጣ የወረደ ጥያቄ ይሆናል.... ለኔ ግን ከእለት ተለት ቅዘት እና የውድቀት ስሜት ያወጣኛል ብዬ የማስበው ጥያቄ ነው....... ምን አልባት የለበስኩት ባስታውስ እና የለበስኩት ልብስ ተገቢ ቢሆን ማህበረሰቡ ጥቃቴን ተቃውሞ እኔን ይቀበለኝ ይሆን?? ቤተሰቦቼን አንገታቸውን ቀና አድርገው መሄድ ይችሉ ይሆን?? እኔም እንድትጠብቀኝ እፈልጋለሁ ብዬ ለሱ መንገር ያስችለኝ ይሆን..... እሱ የወረደ ጥያቄ ጠይቆ ጭንቅላቴን ሃሳቤን ያዘቀጠው ያ ፖሊስ ፈጣሪ ህይወቱን ያጨልምበት ብቻ ከዚህ ሁሉ መከራዬ እንድድን... እኔ ማስታወስ አልቻልኩም.... ካስታወሳቹ እናንተ ንገሩኝ እና ከህመሜ ገላግሉብኝ....... ምን ለብሼ ነበር??

✍️kalkidan

ማር ማር የሆኑ ድርሰቶቼን ለማግኘት በዚህ https://t.me/storyweaver36 የቴሌግራም ቻናሌ ላይ ፎሎው አድርጉኝ ትላችኋላች። join እያረጋችሁ።
से पुनः पोस्ट किया:
ቅዳጅ ገፆች🫀📝 avatar
ቅዳጅ ገፆች🫀📝
24.03.202519:16
ርዕስ አልተገኘለትም(ርዕሱ ነው)

ነጭ ግድግዳ የተባለ ነገር እያስጠላት መጥቷል።ሞት ሞት የሚሸት ክፍል መታጎሯ ለማን ጥቅም እንደሆነ አይገባትም ፤ለእርሷ ወይስ ለእነሱ?ሁሌ ወደ ክፍሏ ሱክ ሱክ እያሉ ወጣ ገባ የሚሉት ሰዎች ነጭ የለበሱ አውሬዎች ይመስሏታል፤ልክ እንደዛች ሴት...

ዛሬም እንደ ትናንቱ ሁሉ አንድ ነጭ ለባሽ ፍጥረት ፊት ለፊቷ ተቀምጧል።
"እስኪ ስለቀንሽ ነገሪኝ።" መነፅሩን ገፋ እያደረገ ጠየቃት።
"ቀኔ...ቀኔ...ቆንጆ ስጋ በስሱ የተቆረጠ..." ለራሷ በሚመስል ድምፅ ዝም ብላ ታወራለች።ዶክተሩ አንዳች ነገር ቸከቸከ እና በድጋሚ ቀና አለ
"አሌክሳንድራ! እባክሽ ከእኔ ጋር ሁኝ" ትዕዛዝ ይሁን ልምምጥ ባልገባው ድምፅ ተናገረ።እርሷም ቀና ብላ አየችው።ጭንቅላቷን በእሺታ አወዛውዛ ዞር ልትል ስትል መልክ አየች፤የሰው ሊያውም የሴት፤ሌላ የትም አደለም እዚያው መነፅሩ ውስጥ።የት እንደምታውቃት ለማስታወስ ሞከረች።ፀጉሯ ሊተኮስ እንደተሰየመ ደረቅ ሳር ቆም ቆም ያለ፤ፊቷ ከአዲስ ወረቀት የነጣ ሴት ፊት።የት ነበር ምታውቃት...?ዶክተሩ በፅሞና ሲያያት ቆየና
"ምን እያሰብሽ ነው?"ብሎ ጠየቃት፤የምርም ጓግቶ ነበር።
"መነፅርህ ውስጥ ሴት አየሁ።ማን ናት እያልኩ ነበር።ድክተርዬ አቃታለሁ መሰል..."ምታስብ መስላ ዝም አለች።ከአፍታ በኋላ ፍለጋው ቀንቷት ይሆን አድክሟት ቀና ብላ እርሱኑ ማየት ጀመረች።እርሱም ምናልባት ከወራት በኋላ የተለወጠ ነገር ያለ ስለመሰለው መናገር ቀጠለ።
"እርሷ አሌክሳንድራ ስቲቨንስ ትባላለች።ሀርላንድ የሚባል ባል እና ክርስቲ ምትባል ቆንጅዬ ልጅ ነበረቻት።ባሏ የሚሰራው በቤት ሽያጭ ጉዳዮች ነበር።እርሷ ደግሞ አራሷን ክርስቲን ይዛ የቤት እመቤት፤ውብ ወይዘሮ ነበረች። እጅግ ደስተኞች ነበሩ።ከአመት አመት በፍቅር እንደ አዲስ እፍ የሚሉ ቤተሰቦች..."ፊቷን አስተዋላት።ጉንጯን እጆቿ ላይ አስደግፋ በተመስጦ ነበር ምታዳምጠው።ቀልቡ ጥሩ ነጥብ ላይ እንደደረሰ ሹክ አለው።ቀጠለ
"...የሆነ ቀን ላይ ተነስታ ማንም ያላሰበውን አደረገች።ባሏን፤ የልጀነት ምኞቷን፤ስለ ፍቅሩ የመነነችለትን አዳሟን...ገደለችው።ቆራርጣ ማቀዝቀዣ ውስጥ አስቀመጠችው።...ትንሿ ክርስቲ ነገሩ ሳይገባት ከማልቀስ በቀር ምንም አላለችም።አሌክሳንድራም ልጇን አንስታ..."ይሄን እንዳለ አቆመና ለደቂቃዎች ሁኔታዋን አጤነ።ፊቷ ከበፊቱም ይባስ ነጥቶ እና ገርጥቶ ነበር።ጥርሷን ምታኝከው ይመስል አስሬ ሰቅጣጭ ድምፅ ያወጣል።ከእግሯ እንቅጥቃጤና ከክፍሉ ዝምታ ጋር ተዳምሮ ክፍሉ አንዳች ደመናን ያረገዘ መሰለ።ያቋረጠውን አስታውሳ ቀዝቃዛ ንግግር ከፈተች።
"...ካሪን አንስታ አይዞሽ የስጋ መረቅ ልሰራልሽ ነው አለቻት።...ፖሊሶች ከሰዓታት በኋላ ስለ ባሏ መሰወር ከጎረቤት ሰምተው ለፍለጋ በራቸውን አንኳኩ..."ማልቀስ ጀመረች።ከእምባዋ ጋር የፀፀት፤የብቸኝነት፤የበደል ስሜቷን አብራ አነባችው።ዶክተሩ ወራት የለፋበትን ውጤት በማግኘቱ ውስጥ ውስጡን ደስ ቢለውም የአሌክሳንድራ ሁኔታ ግን ወደ ጥልቅ ሀዘን ልቡን ለመክተት ብዙ አልፈጀበትም።ስለማፅናናት ቢያስብም ከግል ስሜቱ ስራውን አስቀደመ።
"ምክንያቷ ምን ነበር ብለሽ ታስቢያለሽ አሌክሳንድራ? ጥርጣሬ፣ጥላቻ፣ቅናት፣ቂም ወይስ ንዴት ነበር በአንዲያ ፍቅሯ ላይ ጨክና ቢላ እንድታሳርፍ ያረጋት?"
ምንም አላለችም ከልቧ አነባች ልቧ ደምን አነባ።የምድር ጫፍ ላይ ብቻዋን ያለች መሰላት።በድኗ ቀረ።ልቧ ሞተ።
ለሰዓታት ተንሰቀሰቀች።ዶክተሩ ከነበረበት ሳይነሳ እስከምትጨርስ አብሯት ነበር።ከጎኗ መለየት አልቻለም ነበር።ድንገት"ወደ ክፍሌ እንዲወስዱኝ ንገራቸው"
ለመቃወም ድፍረት አልነበረውም።ነርሷ እና አንዲት ፖሊስ መጥተው ወሰዷት።

ከቀናት በኋላ ራሷን ማጥፍቷን ሰማ።የአልጋዋን ብረት ነቃቅላ ራሷን ልክ እንደ ባሏ ቆራርጣ ተገኘች።በባሏ ያረፉት እጆቿ ለእራሷም መጥፊያ አረገቻቸው።

ከአመታት በኋላ ዲያሪዋ ተገኘ።ሙሉ ህይወቷ ነበር የተተየበበት።ከባሏ ሞት በፊት ከባድ ድብርት ውስጥ መግባቷን ፅፋ ነበር።ስለ መሞት ማስቧም ተገልጿል።የገደለችው ለት የፃፈችው ገፅ አጭር ነበር።
"ውድ ማስታወሻዬ
ዛሬ በስሱ የተቆራረጠ የስጋ መረቅ አምሮኝ ነበር።ሀርሊ እንዲገዛልኝ ስጠይቀው ስለ ገንዘብ ችግር አውርቶ ተጣላን እና መታኝ።እኔም ጭንቅላቱን በጠርሙስ ብዬው ወደቀ።ከዛም ያማረኝን ስጋ
በላሁ።ካሪም ጠጥታለች ግን አልወደደችውም መሰል ካጠጣኋት በኋላ ተኛች፤አልተነፍስ አለች ደግሞ.....ሰው እያንኳኳ ነው መጣሁ..."
ይል ነበር ልጇንም የገደለቻት እርሷ ነበረች?
ለዚ ርዕስ ይሰጣል?ምንስ ተብሎ?

✍️🏼ቃል

https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages
09.04.202515:35
  ❤️❤️❤️❤️  እወዳታለሁ ♥️♥️♥️♥️

"ሌባ ሌባ" ተብሎ ተጮኸ .... ሁሉም በአጠገቡ የሚሮጥ ሰው ሲፈልግ.... ሁሉም የነተበ ልብሴ እና በስካር የጨረጨሰ ፊቴ ላይ ትኩረታቸውን አደረጉ.... ከዋላ አንዱ ባልታሰበ ሰረባ ከመሬት ዘረረኝ... የሱን ጠረባ ተከትሎ ብዙ ሰዎች ከበው የየድርሻቸውን እጃቸውን አሳረፉብኝ ድብደባውን ያየ ፖሊስ ከነሱ አላቆ... ትከሻዬን ጨምድዶ ይዞ የተፈጠረውን ጠየቃቸው... በአንድ ድምፅ "ሌባ ነው" አሉት... ያላዩትን ያልሰሙትን በልብሴ ብቻ ሌባ ነው አሉኝ.... ፖሊሱም የነሱን ቃል ተቀብሎ እያዳፋ ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰደኝ.... እዛ እንደደረሰም የሰረኩትን እንዳመጣ ያፋጥጡኝ ጀመር እንዳልወሰድኩ ደጋግሜ ብናገርም የጠጣሁጥ መጠጥ ከመልሱ ቀድሞ አፋቸው ጋር እያደረሰ በየት በኩል ይመኑኝ... እንደዛ እንዳለን በሩን በርግዳ መጥታ ፊቴ ለፊቴ ቆመች....

"እውነት ነው የሰማውት" ብላ የመጠጡ ሽታ ሳያሳስባት ተጠግታ ጠየቀችኝ...በድብድባ በበለዘው ፊቴን እያየች... የደቀቀ ሰውነቴን በአቧራ የተነከረ ልብሴን እያየች... አላመነችም... እኔ እስካልነገርኳት ምንም ነገር አታምንም

"ምን ይመስልሻል?" ብዬ ደግሜ ጠየኳት... እጆቼን በሰንሰለት አስረው ውጪ እንድጠብቅ ነገሩኝ... በምን እንዳሳመነቻቸው እንጃ እንድሄድ ፈቀዱልኝ...... ይሄኔ ያላትን ሁሉም አራግፋ ሰጥታ ይሆናል... ከክፍሉ ወጥታ በካቴና የታሰሩ እጆቼን አስፈትታ እጄን ይዛ ከዛ ፖሊስ ጣብያ ይዛኝ ወጣች..... ሌባ እያሉ የሚጮሁት ሁሉ ዝም ብለው መንገድ ለቀቁልን... እሷ በኩራት አንገቷን ቀና አድርጋ እጄን ጠበቅ አድርጋ ይዛ ትሄዳለች... እኔ በሐፍረት አንገቴን ደፍቼ እከተላታለው ከዛ ቀን በዋላ ለራሴ ማልኩኝ... አላማዬ አንድ እና አንድ ብቻ አደረኩት እሷን በኩራት ሁሌ ቀና ማድረግ... አሁን እንዲ መሽቀርቀሬን አትይ... ልብሱ እላዩ  ተሰፍቷል እስክባል ድረስ እላይ ላይ በተጣበቀው በአዳፋው ልብሴ ነው የወደደችኝ.... አሁን እንደዚ በሰው መከበቤን አትይ ሰው ሁሉም ሌባ ብሎ ሲሸሸኝ ነው አደለም ብላ መስረቅ አለመስረቄን ሳታውቅ ደረቷን ነፍታ የተከራከረችልኝ.... ታድያ እሷን አለመውደድ እንዴት ይቻላል.... ምን ያክል ነው ምትወዳት? ነበር አደል ጥያቄክ? እኔም አላውቅም ብቻ ግን እወዳታለሁ.....በአዳፋው ልብሴም በአዲሱ ልብሴም በቆሸሸው ስሜም በከበረ ስሜም በትላንቴም በዛሬዬም በነገዬም በአሁኑም እወዳታለሁ.... ይሄን ብቻ ነው ማውቀው.... መለስኩልክ??

በትክክል ብዬ ቀጣዩን ጥያቄ ለመጠየቅ... የጥያቄ ዝርዝሮቼን መመልከት ያዝኩኝ

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
से पुनः पोस्ट किया:
ቅዳጅ ገፆች🫀📝 avatar
ቅዳጅ ገፆች🫀📝
29.03.202511:36
Guys lets be friends on ig🫶🏼

Follow , i will follow back📌

https://www.instagram.com/classy__kal?igsh=MWNycmhjN3plMWFscQ==
24.03.202519:00
                        አይፍቱኝ አባ

"እና ምን ታስባለህ?" ነበር ያለኝ.... በጥያቄው ተደናግጬ የምለው ጠፍቶብኝ ስደናገር "አቅመ ደካማ ነክ በቂ የሆነ የገቢ ምንጭ የለክም.... ይቺኛዋ ለዘላለሙ አርፋለች እና የቀረችውን ብታተርፍ ይሻልካል.... እኛ ጋር የተፈጠረው ስህተት ለማንም ማትናገር ከሆነ የቀረችውን ልጅ ውጪ ወስደን እናሳክማታለን" አለኝ..... እንዴት እንዳላፈረ ተገረምኩ.... አንዷን ልጄ ላይ ላደረሰው ስህተት የሌላኛዋ ልጄ ነብስ ቁማር ላይ ሲያስቀምጣት...... ንዴት ናረብኝ ተነስቼ አንባረኩበት
"እንዴት እንዲህ ትጠይቀኛለክ?? አባቷ እኮ ነኝ.... ስንት ነገር ያየሁባት ልጄ ናት:: እንዴት በቀላሉ በቃ ሞተች ስተቱ የኛ ስለሆነ ያቺኛዋን እናሳክማት ዝም በል ብለክ ትጠይቀኛለክ?? እንዴት አታፍርም? ህሊና እንዴት አይኖርክም? እንዴት በጥፋትክ እንኳን ኃላፊነት አትወስድም?" ምይዘው ምጨብጠው አጣው......እንደ እብድ አደረገኝ.... አንዷ መሞቷ ሳያንስ ሌላኛዋም እንደምትሞት ሲነግሩኝ እራስነቴን ጠላው.... ድህነቴን እረገምኩት አቅመ ቢስ መሆኔ አስጠላኝ.... ከሰው ሁሉ አነስኩኝ ሰማይ ምድሩ ዞረኝ.....ለአንድ አባት ልጅ ማለት አይኑ ናቸው.....የኔ አንዷ አይኔ ጠፋች ሌላኛዋም ትጠፋለች ሲሉ... ሳትጠፋ በፊት የኔ አይን የጠፋ መሰለኝ.... ሁሉም ነገር ጭልም አለብኝ ሰውየው አሁንም አልተመለሰም ከመቀመጫው ተነስቶ " ይሄ የኛ ስህተት አይደለም አላልኩም ግን በአንድ ስህተት የእድሜ ልክ ልፋቴ ከንቱ ሆኖ ሲተን ዝም ብዬ ፍትህ ይቀድማል ብዬ የምቀመጥ ሰው አይደለውም....ጥፋቱን ያደረሱትን ባለሙያዎች ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ.... ግን በራሴ መንገድ" ብሎ አንባረቀ በተራው...... " ሁላችሁም የእጃችሁን ታገኛላቹ" ብዬ ፎምሬ ክፍሉን ለቅቄ ወጣው ።

ከክፍሉ እንደወጣው ባለቤቴ የልጇ ሞት ተነግሯት ለያዥ ለገናዥ አስቸግራ ትጮሀለች ትንሿ ልጄ አንዱን ግድግዳ ተደግፋ ታነባለች..... አንዳች ስሜት ሰውነቴን ወረረኝ እዛው እንዳሉ ጥያቸው ሆስፒታሉን ለቅቄ ወጣው.... አስፓልት ተሻግሬ ሰው ጭር ያለበት አንድ መግቢያ ፈልጌ ወዲህ ወዲያ እየተንቆራጠጥኩኝ ማሰብ ያዝኩኝ ድህነት መጥፎ ነው አባ..... ሃዘንክን እንኳን በአግባቡ እንድትወጣ ዕድል አይሰጥም..... የሞተችውን ልጄን የነብስ ዋጋ ተቀብዬ የቀረችውን ባተርፍስ ብዬ ሳስብ አባትነቴ ልቤን አቆሰለው የመጣው ይምጣ ብዬ የልጄ ጉዳዮች በህግ ብሄድ.... በየትኛው አቅሜ ጠበቃ አቆማለው.... በዛ ላይ ዳኛው ጠበቃው ጠቅላላ የገንዘብ ሰው.... እውነት ይዞ የመጣ ሳይሆን በእጁ ይዞ የመጣን የሚያስቀድሙ ስግብግብ ጭራቆች እንዴት አምኘ ተሟገቱልኝ እላለው.. የቀረችውን ልጄ አንድ ነገር ስትሆን እንዲ ያበደችው ባለቤቴ ምን ትሆንብኝ ይሆን... አባ ለአንድ አባት ለቤተሰቡ በቂ አለመሆን ትልቅ ውድቀት ነው ግን እንደኔ ደሞ የአንዷን ልጄ ሬሳ ረገጦ ሌላዋን የማትረፍ ቁማር ውስጥ የገባን አባት ምን እንደሚባል እንጃ......ነብሴን አርክሼ.... የድህነት ጅራፍ ጀርባዬን እያደማው የወንድነት ክብር ደረቴን ሰብቆ ትንፋሼን እያሳጣኝ....
አንገቴን ደፍቼ ቢሮው ገባው እና በሃሳቡ ተስማማው

ልጄን እያለቀስኩ ቀበርኳት... ለምን ሄድሽ ከሚለው ይልቅ ይቅር በይኝ በሚል ተማፅኖ ከአፈር አስገባዋት ከአንድ ሁለት ሳምንት በዋላ ትንሿን ልጅ ቃል በገቡት መሰረት አሳከሟት...
ጊዜ ባለፈ ቁጥር.... ባለቤቴ በትንሿ ልጅ እርዳታ ፊቷ እየፈካ መጣ ልጄም ቢሆን ከተደረገላት ሕክምና ሰውነቷ ደና ሆነ የኔ ግን ሁለቱንም እየጠፋ መጡ.... ገፅታዬም ሰውነቴም.... ስራዬ ሆን ብሎ ከነሱ መሸሽ ነበር.... ያለ ልክ ጭንቅላቴ ማሰብ እስኪያቆም እጠጣለው..... እንዲጠሉኝ ያልሆኑትን ሆናችሁ ብዬ እሳደባለው..... ባለቤቴ በዚህ ነው አናግረው ብላ የላከቾት አባ እኔ መኖር ሚገባኝ ሰው አደለውም.... የራሴን ስንፍና እና ፍርሃት ነው በልጄ ነብስ የቀየርኩት.... ልጅህን ለማትረፍ ነው እንዳትሉኝ.... እራሴን ለማዳን ነው ያረኩት..... በባለቤቴ አይን ያለኝን ክብር ላለማጣት.... ወልዶ ወልዶ ለሞት ከሚለው የማህበረሰብ ሀሜት ለማምለጥ.... ገፊ እየተባልኩኝ ሰው አፍ እንዳልሰደብ.... የወንድነቴን ክብር ለማትረፍ ነው ልጄን ያተረፍኳት።.....እንደው ባለቤቴ ምን ትለኝ ይሆን አንዷ ልጃችንን ያተረፍኩት የሌላኛዋን ልጄን የሰውነት መብት ገፍፌ ነው ብላት ምን ትል ይሆን? ለልጄስ የእህትሽ ነብስ ነው ባንቺ ነብስ የቀየርኩት ብላት ምን ትለኝ ይሆን??.... በነሱ አይን ለመክበር ብዬ ያደረኩት ነገር በራሴ አይን አወረደኝ ......

አሁን የመጣውት አባ ባለቤቴ እዳለችው ከእርሶ ጋር ተማክሬ ለመስተካከል አይደለም ወይም ሀጥያቴን ተናግሬ እንዲፈቱኝም አይደለም..... የልጄ ድምፅ እንቅልፍ ነስቶኛል..... እርሶ ለፈጣሪ ስለሚቀርቡ እንዲህ ብለው ይንገሩልኝ አባ..... በምድር ጠብቃት ብለክ የሰጠከኝ አባቷ የልጅቱን ነብስ ከራሱ ክብር አስበልጦ ማየት አልቻለም እና አንተው የሰማይ አባቷ ጠብቃት..... ምንም የማታውቅ የዋህ ነብስ ናትና አንተው ከልብህ አቆያት ....የምድር አባቷ ያጎደለባትን ፍቅር እና ፍትህ አንተ በቤትህ ሙላላት .....ያልተገባትን ሆናለችና የሚገባትን ስጣት" በሉት አባ ይቅር እንድትለኝ አይደለም ብቻ ነብሷን እንድትረጋጋልኝ ይንገሩት.... አባቷ ደካማ ሆኖ ነው እንጂ ለውድ ልጄ ያ ተገብቷት አይደለም.... እኔ ስራዬ ነው እስከለተ ሞቴ እራሴን ጠልቼ እና ወቅሼ እንድኖር ያደረገኝ ስራዬ ነው.... እሷ ምን በወጣት ነብሷ ይታወክ...... አባ ለሚያምኑት አምላክ ይሄን ይንገሩልኝ ....እኔ በምድር የሰራሁትን በምድርም በሰማይም ቅጣቴን እቀበላለሁ... የልጄን ነብስ ብቻ እንዲያረጋጋ ለፈጣሪ ይንገሩልኝ ...እኔ ጥፋቴ ነው አባ ይቅርብኝ አይፍቱኝ..... አይፍቱኝ አባ.....

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
24.03.202505:28
CODE 1    

               ምን ለብሼ ነበር

"እጠብቅሻለሁ.... በማውቀው እና በምወደው ነገር ሁሉ እምልልሻለው እርግጠኛ ሆነሽ የኔ እስክትሆኚ ድረስ እጠብቅሻለሁ.... ብቻ አንድ ተስፋ ስጪኝ....እንድጠብቅሽ  ብርታት የሚሆነኝ..... ሰዎች ከሚያወሩት ስታልፊ አይናቸውን አስከትለው ከሚያሙሽ በሙሉ እጠብቅሻለሁ.... በውስጥሽ ከምትፈሪው ብዙ ወንዶች መንገድ ላይ ስታይ በፍርሃት ልብሴን ጨምድደሽ እንድትይዥ ከሚያረገው የሰቀቀን ስሜትሽ እጠብቅሻለሁ  ....አትገቢም ብሎ ከሚያሳንስሽ ሁሉ አንግሼ ክብርሽን አሳያቸው..... እንደ አምላክ እያመለኩሽ ዘላለሜን እኖራለሁ.... ሴት ልጅ በራሳነቷ እንጂ ሌላ በምንም መከበር እንደሌለባት ለዓለም አሳያለው.... ብቻ ፍቀጂልኝ" ነበር ያለኝ ትናንት ማታ ላይ ቢለኝም አሁን የተናገረ ይመስል እያንዳንዱ ቃል ጭንቅላቴ አንዱንም ቃላት ሳይስት ደጋግሞ ይለዋል

እንደሚጠብቀኝ አውቃለሁ.... ዛሬ ቃል አውጥቶ ተናገረ እንጂ የየለት ተግባሩ እሱ ነው.... ቤተሰቤ ከነሱ ውጭ ሚያምኑት ሰው ቢኖር እሱን ብቻ ነው... እንደዛ ቢቻላት ሰው ከሚያመኝ እና ከሚጠቋቆሙብኝ ተመልሳ ወደ ሆዷ ማስገባት ምትፈልገው እናቴ እንኳን እሱ ጋር ስሆን ነው ምትረጋጋው.... ጎረቤታሞች ሆነን ነው ያደግነው እኔ ላይ የደረሰው ነገር እኔን ቀየረኝ እንጂ እኔም እንደዚ እንደሱ ነበር ምንሰፈሰፍለት.... ከደረሰብኝ ጥቃት በዋላ ግን የወንድ ሰውነት ሳይ ስቃይ እና ጩኸቴን እያስታወሰኝ ወንድ የተባለ ማየት እንኳን ፈራው.... በብዙ መከራ እና ትግስት ነበር እሱን መቅረብ የጀመርኩት.... የሰፈሩ ሰው ሁሉ ምን ብታስነካው ነዉ ከዚህ ሁሉ ነገር በዋላ እንደዚህ ስሯ የሚርመጠመጠው ብለዉ ቢፈርዱበት እንኳን ሁሌ ከኔጋ ሲሆን ሽልማት እንዳገኘ ሰው ነው አለሙን ሚረሳው... እኔም አልነገርኩትም እንጂ ከሱ ጋር ስሆን ነፃነት ይሰማኝ ጀምሮአል ቤተሰቦቼ እኔን ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ቅጥ ያጣ ቁጥጥር የሆንኩትን ነገር ቀን በቀን ያስታውሰኝ ነበር እሱ ጋር ስሆን ግን እንደ ማንኛውም ሰው ለመሆን ነበር ምሞክረው.... ታዲያ ለምን ልጠብቅሽ ሲለኝ ዝም አልኩት???

ጥቃት ሲደርስብኝ የለበስኩት ልብስ በደም ተጨማልቆ የቀረው ደሞ የመሬቱን አፈር ይዞ ሰውነቴ ጠቅጡ አይታይም ነበር.... ፊቴም በእንባ ተሞልቶ ሰውነቴም በማምለጥ ካረገው ያልተሳካ ትግል ምክንያት ዝሎ ነበር .....እዛው በተኛሁበት የሞት አፋፍ ላይ ጥለውኝ ሄደው የሰፈር ሰዎች ነበር አግኝተው ሆስፒታል የወሰዱኝ... ሆስፒታል ውስጥ የእናቴ ጩሀት የአባቴ እና የወንድሜ የቁጣ ንግግር የእህቴ እናቴን በማፅናናት የምታደርገው ጥረት... ከተኛሁበት ክፍል ሆኖ ይሰማኝ ነበር... ሆስፒታሉ ሪፖርት ስላደረገ ፖሊሶች መተው ጥያቄ ይጠይቁኝ ጀመር

"ታስታውሻለሽ የሆነውን?"
ዝም

"ምታስታውሺውን ብቻ ንገሪኝ?"

ዝም

"ጥቃት ያደረሱብሽን ታስታውሻቸዋለሽ?"

ዝም

ከሁሉም የገረመኝ ጥያቄ "ምን ለብሰሽ ነበር?" የዚን ጊዜ አምርሬ አለቀስኩኝ... ለምን እንደዛ እንዳለቀስኩኝ በሰዓቱ ግልፅ አልሆነልኝም ነበር....አሁን ሳስበው ግን ይመስለኛል ያለቀስኩት .....ሴትን ልጅ ባደረገችው ልብስ ብቻ ጥቃት ይድረስባት አይድረስባት ብለው ከሚወስኑ የሕግ ሰዎች ጋር እንደምኖር አስቤው ነው መሰል ወይም........ ሴትነታቸውን ለባህል እና ለወግ ሽጠው አንድ ሴት ጥቃት ሲደርስባት እንደማገዝ እንዳበቃላት እና ተስፋ እንደሌላት ከሚያስቡ ሴቶች መሃል ስለምኖር ይሆን አልያም........ የእንስሳነት ስሜት ይዟቸው አንዲትን ሴት ያለፍላጎቷ ከተጫወተባት ሰው ይልቅ የተጠቃችው ሴት ከጥቃቱ ይበልጥ ህመም ከማህበረሰቡ እንደምታገኝ ተገንዝቤ ይሆን????? ታድያ ለምን አለቀስኩኝ?? ባለፍኩኝ ቁጥር እየተከታተሉ ብቸኝነቴን እና የበታችነቴን የሚነግሩኝ ሴቶች ነበሩ.... ሴትነታቸውን በምን ለክተው ይሆን ብዬ አስባለው...... ሴት ልጅ ክብሯ ከሌለ ሰውነቷ ያበቃል ማለት ነው?? የሴትነት ዋጋስ በምንድነው ሚተመነው?? እነሱ ከኔ በምን ተሽለው ነው ዋጋቸው ከኔ ከፍ ያለው.... እኔ በግድ የተነጠኩትን አስተሳሰብ እነሱ በፍቃድ ተቀብለው የወንድ ልጅ ባርያ መሆን ከፈለጉት ዋጋዬ በምንድነው ያነሰው?? ደፋሪዎቼ ተይዘው ለፍርድ ቢቀርቡም የፖሊሶቹ ጥያቄ ግን አሁንም ጭንቅላቴን ያናውጠዋል.... በጩሀቴ እና በቅዘቴ መሃል ከእንቅልፌ ስነቃ መጀመሪያ ጭንቅላቴ ላይ ሚመጣው ጥያቄ "ምን ለብሰሽ ነበር?" ነው ምን ብለብስ ነበር ከጥቃት ማምለጥ እችል የነበረው? ምን ለብሼ ቢሆን ነው ሰዎቹ አው አጥፍተዋል ይባል የነበረው? ማይሆን ልብስ ብለብስ ኖሮ ልክ ናቸው ይለኝ ይሆን? ምናልባት ለአንዳንዶቹ ጥያቄው ከአንድ እራሱን ካረከሰ የሕግ አካል የወጣ የወረደ ጥያቄ ይሆናል.... ለኔ ግን ከእለት ተለት ቅዘት እና የውድቀት ስሜት ያወጣኛል ብዬ የማስበው ጥያቄ ነው....... ምን አልባት የለበስኩት ባስታውስ እና የለበስኩት ልብስ ተገቢ ቢሆን ማህበረሰቡ ጥቃቴን ተቃውሞ እኔን ይቀበለኝ ይሆን?? ቤተሰቦቼን አንገታቸውን ቀና አድርገው መሄድ ይችሉ ይሆን?? እኔም እንድትጠብቀኝ እፈልጋለሁ ብዬ ለሱ መንገር ያስችለኝ ይሆን..... እሱ የወረደ ጥያቄ ጠይቆ ጭንቅላቴን ሃሳቤን ያዘቀጠው ያ ፖሊስ ፈጣሪ ህይወቱን ያጨልምበት ብቻ ከዚህ ሁሉ መከራዬ እንድድን... እኔ ማስታወስ አልቻልኩም.... ካስታወሳቹ እናንተ ንገሩኝ እና ከህመሜ ገላግሉብኝ....... ምን ለብሼ ነበር??

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
अधिक कार्यक्षमता अनलॉक करने के लिए लॉगिन करें।