Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
TIKVAH-MAGAZINE avatar
TIKVAH-MAGAZINE
TIKVAH-MAGAZINE avatar
TIKVAH-MAGAZINE
ለ23 ዓመታት የቪዲዮ መገናኛ ሆኖ የቆየው ስካይፒ ተዘግቷል።

ማይክሮሶፍት ስካይፒን እንደሚዘጋ ቀድሞ አስታውቆ የነበረ ሲሆን ዛሬ አገልግሎቱ በይፋ ተቋርጧል።

የስካይፒ አገልግሎትን በነፃ እና በክፍያ ያገኙ ለነበሩ ሁሉ የተቋረጠ ሲሆን የቢዝነስ አገልግሎቱ አልተቋረጠም ተብሏል።

በ2003 በማይክሮሶፍት ስራ የጀመረው ስካይፒ ለዘመናት ተመራጭ የቪዲዮ መገናኛ የነበረ ሲሆን የዙም እና ጎግል ሚት መተግበሪያዎች መምጣታቸውን ተከትሎ ተፈላጊነቱ ቀንሶ ነበር።

ማይክሮሶፍት ስካይፒ ይጠቀሙ የነበሩ ሰዎች በስካይፒ አካውንታቸው ወደ ማይክርሶፍት ቲምስ መግባት እና መረጃዎቻቸውን እንዲያዘዋውሩ ጠይቋል።

@tikvahethmagazine
05.05.202517:06
ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረትና ለኢጋድ ይፋዊ ግብዣ አቀረበች።

የደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መንደይ ሰማያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር መሐመድ አሊ የሱፍንና የኢጋድ ምክትል ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ወደ ጁባ እንዲመጡ ይፋዊ ጥያቄ አቅርበዋል።

እንደ ደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መረጃ አመራሮቹ ወደ ጁባ የተጋበዙት ቀጣናዊ ትስስርን በተለይ ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት ለማጠናከር እና የሃገር ውስጥ ግጭትን ለመፍታት የሚያስችል ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ነው።

ደቡብ ሱዳን ከወራት በፊት ወደ አዲስ ግጭት የገባች ሲሆን ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር አሁንም እስር ላይ ናቸው።

የአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ተወካዮቻቸውን ከዚህ ቀደም ወደ ጁባ ልከው የነበረ ቢሆንም ውጤታማ የሚባል ነገር አልተገኘም ነበር።

Source: Eastleigh Voice

@tikvahethmagazine
" በቁንፅል የምናስተምረው ፓን አፍሪካኒዝም "

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ኢትዮጵያ ጨምሮ ስለ ፓን አፍሪካኒዝም በታሪክ ትምህርታቸው ውስጥ በማካተት ተማሪዎቻቸውን ቢያስተምሩም÷ የሚሰጠው ትምህርት መሰጠት በሚገባው ልክ ተሰጥቷል የሚለው ግን ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ነው፡፡ 

በሐሳብ አለኝ ቁ.2 መጽሔት በብዕር ስም የተሳተፈው ያሬድ አግማስ " በቁንፅል የምናስተምረው ፓን አፍሪካኒዝም " በሚል ርዕስ ይህንን ጉዳይ እንድንጠይቅ የሚያስችል ጹሑፍ አቅርቦልናል።

በዚህ ጹሑፍ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች፤ መምህራን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና መምህራን ሀሳባቸውን አካፍለዋል።

ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ https://concepthub.net/article/11

@tikvahethmagazine
በቺሊ እና አርጀንቲና የባህር ዳርቻ በ7.4 ሬክታር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የአሜሪካ ብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት በቺሊ ሱናሚ ሊከሰት ስለሚችል መንግስት በባህር ዳርቻው የሚኖሩ ሰዎችን እንዲያስወጣ አሳስቧል።

በመሬት መንቀጥቀጡ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ያልተዘገበ ሲሆን የአርጀንቲና መንግስት እና የቺሊ መንግስት የሱናሚ ስጋት በመኖሩ በባህር ዳርቻ ላይ የሚኖሩ ዜጎቻቸውን ማስወጣት ጀምረዋል።

Source: CBS

@tikvahethmagazine
#kenya

በኬንያ ያለው የኃይል ፍላጎት በመጨመሩ ሃገሪቷ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ልታስገባ ስለማሰቧ ተዘግቧል።

በኬንያ የኃይል ፍላጎት የጨመረ ሲሆን ሊያጋጥም የሚችልን የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ለማስገባት እንዳቀደች ተነግሯል።

የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆሴፍ ሲሮር ከኢትዮጵያ ተጨማሪ ከ50-100 ሜጋ ዋት ኃይል ለማስገባት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ንግግር ስለመጀመሩ ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አሁን የተጠየቀው ጥያቄ እስካሁን እየገባ ካለው የ200 ሜጋ ዋት በተጨማሪ መሆኑን ሲገልፁ ኃይሉ የተፈለገው ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ባለበት ከምሽት 12 ሰዓት እስከ ምሽት 4 ሰዓት ድረስ መሆኑን ገልፀዋል።

በ2024 የኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንደገለፀው ኬንያውያን ከሚጠቀሙት ዕለታዊ የኃይል ፍጆታ ውስጥ 11 በመቶው ከኢትዮጵያ እንደነበር መግለፁ ይታወሳል።

ኬንያ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ከኡጋንዳ እና ከታንዛኒያ ታስገባለች።

Source : Business Daily

@tikvahethmagazine
አሜሪካ  እና ዩክሬን ወራትን ከፈጀ ድርድር በኋላ በመጨረሻ የማዕድን ስምምነትን ተፈራርመዋል።

የኬይቭ ባለስልጣናት አሁን የተፈረመው ስምምነት ከበፊቶቹ ከቀረቡት ስምምነቶች ለዩክሬን የተሻለ ጥቅም የሚሰጡ ናቸው ያሉ ሲሆን ለትግበራው ስምምነቱን የዩክሬን ፓርላማ ማፅደቅ ይጠበቅበታል።

በስምምነቱ መሰረት አሜሪካ የዩክሬን ወሳኝ የሚባሉ ማዕድናትን የምታገኝ ሲሆን በምላሹ ከጦርነቱ በኋላ ዩክሬንን ለመገንባት ድጋፍ ታደርጋለች።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከዚህ በፊት አሜሪካ ለዩክሬን 350 ቢሊየን ዶላር ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ደግፋለች ሲሉ እንደነበር ሲታወስ ዕዳዋን በማዕድን መክፈል አለባትም ብለው ነበር።

በስምምነቱ መሰረት የአሜሪካ- ዩክሬን ፈንድ የሚቋቋም ሲሆን የትኛው ማዕድን እና የት እንደሚወጣ ሙሉ ለሙሉ የመወሰን መብት ለዩክሬን ተሰጥቷል።

አሜሪካ ለፈንዱ በቀጥታ ወይም በወታደራዊ መልኩ ድጋፍ ስታደርግ ዩክሬን ከማዕድን ማውጣት የሚገኘውን ግማሽ ያህል ገቢ ታዋጣለች ተብሏል።

ዩክሬን ስምምነቱ ያለፈውን የአሜሪካ ድጋፍ በተመለከተ አይደለም ያለች ሲሆን ስምምነቱ የወደፊት ድጋፍን በተመለከተ ነው ብላለች።

ዩክሬን ከፈንዱ የሚገኘው ድጋፍ በመጀመሪያዎቹ 10 አመታት በዩክሬን ኢንቨስትመንት ላይ ይውላል ብላ እንደምትጠብቅም ገልፃለች።

ዩክሬን በአውሮፓ ህብረት ወሳኝ ተብለው ከተለዩ 34 ማዕድናት ውስጥ 22ቱ ያሏት ሲሆን በ2022 የአለምን አቅርቦት 5 በመቶ የሚሆኑም ነበሩ ተብሏል።

Source: AP, ALJAZEERA

@tikvahethmagazine
#Africa #US

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአፍሪካ ልማት ፈንድ የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ በ555 ሚሊየን ዶላር እንዲቀንስ ሊያደርጉ ነው።

ለአሜሪካ ኮንግረስ የቀረበው ሰነድ እንደሚያሳየው ለአፍሪካ ልማት ባንክ ዋነኛ የልማት ፈንድ ከአሜሪካ የሚቀርበው ድጋፍ በ555 ሚሊየን ዶላር የሚቀንስ ሲሆን በቀጣይ አመት ድጋፉ ሙሉ ለሙሉ ይቋረጣል።

የበጀት ቅነሳው የአሜሪካ መንግስት እየከተለ ያለው የውጪ ወጪ ቅነሳ አካል መሆኑ ሲዘገብ ፈንዱ በአሁኑ ወቅት ከአሜሪካ ቀዳሚ ፍላጎቶች ጋር አይጣጣምም ተብሏል።

አሜሪካ እ.ኤ.አ ከ1976 ጀምሮ የልማት ፈንዱን ትደግፍ እንደነበር ሲዘገብ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሁለተኛዋ ባለድርሻም ነች።

የአሜሪካ ውሳኔ በቀጣይ ወር በሚካሄደው የልማት ባንኩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወደ አመራር ስፍራ ለሚመጡ አመራሮች ትልቅ ፈተና ይሆናል ተብሏል።

Source: Semafor

@tikvahethmagazine
05.05.202509:35
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ የፖርት ሱዳን ከተማ ላይ ጥቃት ሰነዘረ።

የሱዳን ጦር የሚመራው መንግስት መቀመጫ በመሆን እያገለገለች ያለችውን ከተማ ኃይሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ማጥቃቱን የሱዳን ጦር ገልጿል።

ጥቃቱ በድሮን የተፈፀመ ስለመሆኑ የተነገረ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመው በፖርት ሱዳን ከተማ በሚገኘው ወታደራዊ ኤርፖርት ላይ ነው ተብሏል።

በጥቃቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም የተባለ ሲሆን በተወሰነ መልኩ የንብረት ውድመት ደርሷል ተብሏል።

የድሮን ጥቃቱ ለ4 ሰዓታት የቆየ ሲሆን አብዛኞቹን ጦሩ ማክሸፉን የሱዳን ጦር ቃለ አቀባይ ተናግረዋል።

በተጨማሪ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሱዳንን የባህር ከተማ ከማጥቃቱ በተጨማሪ በኤርትራ ድንበር ላይ በምትገኘዋ የካሳላ ከተማ ላይም የድሮን ጥቃት ፈፅሟል።

የሱዳን የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሚያጠቃባቸውን ድሮኖች ከማስታጠቅ እንድትቆጠብ ሲጠይቅ የድሮን ጥቃቶቹን እንደ ግብፅ፣ ጂቡቲ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ኩዌት ያሉ ሃገራት ማውገዛቸው ተዘግቧል።

Source: BBC, SUDAN TRIBUNE

@tikvahethmagazine
04.05.202517:12
የሳምንቱ የቀጣናው ዐበይት ዲፕሎማሲያዊ ሁነቶች

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በሳምንቱ ከሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ከአንጎላው ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ፕሬዚዳንት ጆኣዎ ጎንካልቬስ ጋር በካይሮ መክረዋል።

ፕሬዚዳንት አልሲሲ በሁለቱም ውይይቶች ወቅት የአባይ ውሃን በተመለከተ ጥያቄ ማቅረባቸው ተዘግቧል።

ፕሬዘዳንቱ ከሱዳን ጦር መሪ ጋር በነበራቸው ውይይት የአባይ ወንዝ የሁለቱም ሃገራት ብሔራዊ ጥቅም መሆኑን አንስተው በወንዙ ላይ የሚካሄድ የተናጥል ውሳኔን ተቃውመዋል።

ሁለቱም መሪዎች የአባይ ወንዝ አጠቃቀም ፍትሃዊ በሆነና የአለም አቀፍ ህጉን ባከበረ መልኩ መሆን አለበት ብለዋል።

የግብፁ ፕሬዚዳንት በተመሳሳይ በሳምንቱ መጀመሪያ ከአንጎላው ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ፕሬዚዳንት ጆኣዎ ጎንካልቬስ ጋር በመከሩበት ወቅት ግብፅ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን አቋም ገልፀዋል።

አልሲሲ የግድቡን ሙሌት እና ኦፕሬሽን በተመለከተ አፋጣኝ የሆነ ህጋዊ ስምምነት መፈረም አለበት ብለዋል። አልሲሲ ህጋዊ ስምምነት መኖሩ የግብፅን፣ ሱዳንን እና ኢትዮጵያን ጥቅም ያስጠብቃል ብለዋል።

የአንጎላው ፕሬዚዳንት በውሃ አካላት ላይ የሚነሱ ግጭቶቸ በአፍሪካዊ ንግግሮች መፈታት አለባቸው ሲለ በአባይ ተፋሰስ ላይ ያሉ ሃገራት መተባበር እና መረጋጋትን ማስጠበቅ ይገባቸዋል ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ካይሮ ሄደው ከመከሩ በኋላ ተወካያቸውን እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ወደ አዲስ አበባ የላኩትም በሳምንቱ አጋማሽ ነበር።

የአንጎላ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴቴ አንቶኒዮ በአዲስ አበባ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ጋር መክረዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከውይይቱ በተጨማሪ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆኣዎ ጎንካልቬስ የተላከን መልዕክትም አድርሰው ነበር።

@tikvahethmagazine
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ስታርሊንክ በሃገሯ እንዲሰራ ፈቃድ ሰጠች።

የሳተላይት የኢንተርኔት አቅራቢ የሆነው ስታርሊንክ በአፍሪካ ተደራሽነቱን እያሰፋ ሲሆን ባለፈው ወር በሶማሊያ እና ሌሴቶ ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል።

30% ህዝቧ የኢንተርኔት ተጠቃሚ በሆነባት ኮንጎ ባለስልጣናቷ የሳተላይት ኢንተርኔቱን አማፂያን ሊጠቀሙበት ይችላሉ በሚል ስጋት ስታርሊንክን አግደው መቆየታቸው ተዘግቧል።

ስታርሊንክ በተጨማሪ በኡጋንዳ አገልግሎቱን ሊጀምር እንደሚችል ሲዘገብ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ከድርጅቱ ተወካዮች ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

Source : Reuters

@tikvahethmagazine
#SouthSudan

ደቡብ ሱዳን በሃገሯ የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለማስፋት ከኢትዮጵያ እና ሱዳን የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮችን ልታስገባ ነው።

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪ አሁን ሃገሪቷ ካላት ከኬንያ እና ከኡጋንዳ ከሚመጣ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመር በተጨማሪ ከኢትዮጵያ እና ሱዳን ማስገባት የባህር በር የሌላትን ሃገር ወደ ኢንተርኔት ማዕከልነት እንደሚቀይር ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በተጨማሪ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ መስመሮች መኖራቸው ሊኖር የሚችልን የኢንፎርሜሽን ስርዓት መፋለስ የሚቀንስ መሆኑን ያነሱ ሲሆን የባህር በር የሌለው ሃገር የሲስተሞችን አለመስራት ለመከላከል ብዙ አማራጮች ያስፈልጉታል ብለዋል።

ደቡብ ሱዳን በተጨማሪ በኃይል አቅርቦት እየተፈተነች መሆኑን ሚኒስትሩ ሲያነሱ ያለው የኃይል እጥረት የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፉን እንደጎዳው ጠቅሰዋል።

የደቡብ ሱዳን 70 በመቶ ወጣት መሆኑ ሲገለፅ የተደራጁ መሰረተ ልማቶች ባለመኖራቸው በሃገሪቱ ኢንተርኔት ውድ ከሆነባቸው ሀገራት ተርታ ትገኛለች።

Source: eye radio

@tikvahethmagazine
01.05.202520:59
የሀገራት አማካኝ የቀን ገቢ ስንት ነው ?

የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ከጊዜ ወደጊዜ የሚያገኙት ገቢ ከኑሮ ውድነቱ ጋር እየተጣጣመ አይደለም። በአብዛኛው ሃገራት በተለይ እያደጉ ባሉ ሃገራት የዜጎች የቀን ገቢ በጣም አነስተኛ ስለሆነ ዜጎች ለመኖር ሲፈተኑ ይታያል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ በ2023 በነበረ ቁጥራዊ አኀዝ ግማሽ ያህሉ ህዝብ በቀን ከ3.06 ዶላር በታች ባለው ገቢ የሚኖር ሲሆን 19.54% ያህሉ ህዝብ ደግሞ በቀን ከ1.9 ዶላር በታች ያገኛል።

በተጨማሪ UNDP በ2024 ባወጣው ሪፖርቱ በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ወይም በቀን ከ2.15 ዶላር በታች ገቢ የሚያገኝ ነው።

ይህ አነስተኛ ገቢ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ታዳጊ ሃገራትም የሚታይ መሰረታዊ ችግር ነው።

በጎረቤት ሃገር ኬንያ በተመሳሳይ መረጃ በ2023 ግማሽ ያህሉ ህዝብ በቀን ከ3.1 ዶላር በታች የሆነ ገቢ ሲያገኝ  31.25% በመቶ ያህሉ ህዝቧ በቀን ከ1.9 ዶላር በታች ያገኛል።

በUNDP የ2024 ሪፖርት መሰረት ደግሞ ኬንያ 36.1 በመቶ ያህል ዜጎቿ በቀን ከ2.15 ዶላር በታች የሚያገኙ ወይም ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ናቸው።

ግብፅ በ2023 በወጣው መረጃ ግማሽ ያህሉ ህዝቧ በቀን ከ5.07 ዶላር በታች የሚያገኝ ሲሆን በUNDP የ2024 ሪፖርት መሰረት 1.5 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ በቀን ከ2.15 ዶላር በታች ያገኛል።

እንደ ሉግዘምበርግ ባሉ ያደጉ ሃገራት ይህ የቀን ገቢ ተገላቢጦሽ ነው። በሉዘምበርግ ግማሽ ያህሉ ህዝብ ከ69.48 ዶላር በታች ገቢ በቀን ያገኛል።

በሉግዘምበርግ በቀን ከ1.9 ዶላር በታች የሚያገኘው 0.28% የሚሆነው ህዝብ ብቻ ነው።

እነኚህ ቁጥሮች በታዳጊ ሃገራት ያሉ ዜጎች የሚኖሩትን ኑሮ መደምደሚያ ባይሆኑም አመላካች ሲሆኑ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች ተደርገው የዜጎች ኑሮ መሻሻል እንዳለበት የሚያሳዩ ናቸው።

Source: UNDP, WISE VOTER

@tikvahethmagazine
05.05.202517:49
የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አመሻሹን ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ኢትዮጵያ እና እስራኤል የረጅም ዘመን ታሪክ ግንኙነት አላቸው ያሉ ሲሆን በሃገራቱ የጋራ ግንኙነት ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
05.05.202509:34
#Kenya

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ንግግር እያደረጉ በነበረበት ወቅት በተወረወረ ጫማ ፊታቸውን ተመተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ትናንት በሱና ዌስት ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ንግግር እያደረጉ እያለ ከህዝብ መሃል በተወረወረ ጫማ ፊታቸውን ሲመቱ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭቷል።

ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ 3 ሰዎች በፖሊስ መታሰራቸው የተነገረ ሲሆን የደህንነት ኤጀንሲዎች ለፕሬዚዳንቱ የሚደረግ ጥበቃ መጠናከር አለበት ብለዋል።

ሩቶ በጫማው ከመመታታቸው በፊት በአካባቢው መንግስት ስለሰራቸው ቤቶች እየተናገሩ እና በሃገሪቱ መንግስት የእርሻ ወጪን ለመቀነስ እያደረገ ስላለው ጥረት እያወሩ ነበር ተብሏል።

የፀጥታ ሃይሎች ከሶስቱ ግለሰቦች በተጨማሪ ሌሎች ሰዎች ሊያዙ ይችላሉ ያሉ ሲሆን ተግባሩ በፖለቲካ ተነሳሽነት ቀድሞ የታቀደ ሊሆንም ይችላል ብለዋል።

Source: The Kenya Times

@tikvahethmagazine
የባህር አማራጭ የሌላቸው 3ቱ የሳህል ሀገራት የባህር በር አማራጭ ከሞሮኮ ሊያገኙ እንደሚችሉ ተጠቆመ።

የቡርኪናፋሶ ፣ማሊ እና የኒጀር ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከሞሮኮው ንጉስ መሐመድ ስድስተኛ ጋር በራባት መክረዋል።

ሶስቱም ሀገራት ውስጥ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የያዙ ወታደሮች የሚያስተዳድሩ ሲሆን ከኢኮዋስ በመውጣት የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን የሚል የራሳቸውን ህብረት መመስረታቸው ይታወሳል።

ሞሮኮ በሀገራቱ የፋይናንስ እና ግብርና ዘርፍ ላይ ዋነኛ ኢንቨስተር ስትሆን በ2023 ኢኮዋስ ሶስቱ ሃገራት ላይ የንግድ ማዕቀብ ከጣለ በኋላ የንግድ አማራጭ እንዳቀረበች ተነግሯል።

ውይይቱ የተደረገው ሶስቱ የሳህል ሀገራት ከሞሮኮ ጋር ቁርሾ ውስጥ ካለችው አልጄሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ካቋረጡ በኋላ መሆኑ ተዘግቧል።

አልጄሪያ ከሞሮኮ ጋር ያላትን ግንኙነት ካቋረጠች በኋላ የምዕራባዊ ሰሃራ ነፃነትን የሚደግፉ ታጣቂዎችን እየደገፈች እንደሆነ ሲሰማ ሞሮኮ በአንፃሩ ምዕራባዊ ሰሃራን እንደራሷ ግዛት በመቁጠር በግዛቲቱ የ1 ቢሊየን ዶላር ወደብ እየገነባች ነው።

ባለፈው ወር አልጄሪያ የማሊ ድሮን ድንበሬን ጥሶ ገብቷል ብላ መትታ ከጣለች በኋላ ሶስቱ የሳህል ሀገራት ከአልጄሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቋረጣቸው ይታወሳል።

የባህር በርን በተመለከተ የተደረገው ውይይት ፍሬያማ ስለመሆኑ ሲገለፅ ሀገራቱ በአትላንቲክ ወደብ በኩል አማራጩን እንደሚያገኙ ተስፋ ተደርጓል።

Source: Reuters

@tikvahethmagazine
በዚህ ልክ ዋጋ ቀንሶ አያውቅም!

ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት አጠገብ

አፓርታማ በ5.7 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ዋጋ

90 ካሬ

ባለ ሁለት መኝታ

ለ1 ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (direct/ Whatsapp):-  በ 
0972874496 ወይም  0917899736 ይደውሉ
በሱዳን በኮሌራ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ60,000 አለፈ።

ባለፈው ሳምንት ብቻ 498 አዳዲስ የኮሌራ ተጠቂዎች የተገኙ ሲሆን አብዛኞቹ ተጠቂዎች ከካርቱም መሆናቸው ተነግሯል።

በሱዳን ኮሌራ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከ60,000 በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን 1617 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው አልፏል።

የአካባቢ ጤና ባለሙያዎች በ5 ግዛቶች በሚገኙ 1922 የውሃ ምንጮች ምርመራ ለማድረግ አቅደው 78% ያህሉን ሲመረምሩ 480 ያህሉ የደህንነት ስታንዳርዱን አያሟሉም ተብሏል።

በሱዳን የመድሃኒቶች ስርጭት በግዛቶቿ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ አይደለም ሲባል በአንዳንድ ግዛቶች የመድሃኒት እጥረት ስለመኖሩ ተዘግቧል።

በጦርነት የጤና መሰረተ ልማቶቿን እያጣች ባለችው ሱዳን ከኮሌራ በተጨማሪ እንደ ኩፍኝ እና ሄፓታይተስ ያሉ በሽታዎች ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ስለመጨመሩ ተነግሯል።

Source: Sudan Post

@tikvahethmagazine
01.05.202520:23
"ከ340ሺህ በላይ የውጭ ሃገር የሥራ እድሎች እና ከ45ሺህ በላይ የርቀት ስራዎች ተመቻችተዋል" - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የዓለም የሠራተኞች ቀን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ቀኑን የኢንዱስትሪ ሰላምን፣ የሥራ ላይ ደኅንነትንና የሠራተኞችን ክሕሎት ማሳደግን ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚከበር ገልጿል።

ለግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች በመካከለኛ ደረጃ የሠለጠኑ ሠራተኞች ለማቅረብ ሰፋፊ የክሕሎት ሥልጠናዎችን በቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና በተለያዩ አማራጮች እያቀረበ ይገኛልም ብሏል።

በተጨማሪም በዚህ ዓመት በሁሉም የኢኮኖሚ መስኮች ከሦስት ሚሊዮን በላይ ስራዎች ተፈጥረዋል ያለው መግለጫው ከ340ሺህ በላይ የውጭ ሃገር የሥራ እድሎች እና ከ45ሺህ በላይ የርቀት ስራዎች (remote jobs) መመቻቻቸውን ገልጿል።

ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethmagazine
05.05.202517:23
ሺሻ (ሁካ)ማጨስ በህግ ያስቀጣ ይሆን?

"በኢትዮጵያ ሺሻን በግል መጠቀምን የሚከለክል ህግ የለም፣ ለንግድ አላማ ማስጠቀም ግን ህጉ ይከለክላል " የህግ ባለሙያ

በኢትዮጵያ ምግብና የመድኃኒት ባለስልጣን አስተዳደር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1112/2011ዓ.ም #ሺሻን በግል ማጨስ ወይም መጠቀምን #አይከለክልም።

ሆኖም የኢትዮጵያ ምግብና የመድኃኒት ባለስልጣን አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 በወጣው የሺሻ ምርት ማስመጣት፣ ማጨስና መጠቀም ከ3 ወር እስከ 3 አመት ቅጣት እንደሚጣልበት ይደነግጋል።

አዋጁ ከወጣ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።

የህግ ባለሙያው ሳሙኤል ግርማ በምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2011 ዓ.ም የፀደቀው አዋጅ ቁጥር 1112 ሺሻን ማስመጣት፣ ማስጠቀም፣ ለንግድ ስራ ማዋል እና ለ3ኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ብቻ በህግ እንደሚያስጠይቅ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቃለመጠይቅ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ " በግል መጠቀምን የሚከለክል ህግ አለመውጣቱ በሀገር ኢኮኖሚ እና በማህበረሰቡ ጤና ላይ ትልቅ ተፅዖኖ እየፈጠረ ነው" የሚል ሀሳብ ያነሳሉ።

አክለውም ፥ " ብዙ ሰዎች ሺሻ መጠቀምን የሚከለክል ህግ የለንም ይላሉ ነገር ግን በግል መጠቀምን አይከልክል እንጅ ሁለት ሶስት ሆኖ በመኖሪያ ቤት ውስጥ እና በንግድ ቤት ማጨስ አይቻልም
። ሁለት እና ከዚያ በላይ ሆኖ ሲጠቀም የተገኘ ግን በህጉ ያስጠይቀዋል " ብለዋል።

የቅጣት እርከኑ በምንድን ነው የሚለያየው?

የህግ ባለሙያው ሳሙኤል " የወንጀል ቅጣት ሥነ-ስርዓት የራሱ የሆነ መጥሪያ ፍርድ ቤት ያወጣው እርከኖች አሉ። ቅጣት ማቅለያ ተብሎ የሚያዝላቸው ቤተሰብ አስተዳዳሪ እና ጥፋቱን ያመነ ከሆነ ዝቅተኛ ቅጣት ነው የሚጣልበት " ብለዋል።

አያይዘውም ፥ ወንጀሉን ሲፈፅም የተገኘ ሰው ከዚህ ቀደም በማስጠንቀቂያ የታለፈ ሆኖ በድጋሜ ከተገኘ፣ ህፃናትን እና ተማሪዎችን የሚያስጠቅም ከሆነ ግን ቅጣቱ ከፍ ሊል እንደሚችል አስረድተዋል።

ሺሻን በግል መጠቀምን የሚከለክል ህግ አለመኖሩ ጉዳቱ ምንድን ነው ?

ለዚህ ጥያቄ ምላሻቸውን የሰጡን የህግ ባለሙያው " በግል መጠቀምን የሚከለክል ህግ አለመኖሩ ሰዎችን ለማስጠቀም ከፍተኛ ክፍተት ፈጥሯል፣ ምክንያቱም አንድ ሰው ለእራሱ አስመስሎ በተለያዩ አፖርታማዎች ተሰባስበው እንድጠቀሙ ያደርጋል። ይህ ደግሞ  በማህበረሰብ ጤና እና በወጣት ሃይል ላይ አሉታዊ ተፆዕኖ ይኖረዋል" ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

በምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የወጣው አዋጅ የሚበረታታ ሆኖ ሳለ ነገር ግን በግል መጠቀምን የሚከለክል ህግ  አለመውጣቱ ወንጀሎችችን ለመቆጣጠር ክፍተት የሚፈጥር በመሆኑ
አዋጁ ሊሻሻል ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን አካፍለውናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
05.05.202509:33
በዚህ ልክ ዋጋ ቀንሶ አያውቅም!

ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት አጠገብ

አፓርታማ በ5.7 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ዋጋ

90 ካሬ

ባለ ሁለት መኝታ

ለ1 ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (direct/ Whatsapp):-  በ 
0972874496 ወይም  0917899736 ይደውሉ
ናይጄሪያ ከቪዛ ጊዜ ቆይታ በላይ በሃገሯ የሚቆዩ የውጪ ዜጎች ከባድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ብላለች።

ከመጪው መስከረም ጀምሮ በናይጀሪያ ከቪዛ ጊዜ ቆይታ በላይ በሃገሯ የሚቆዩ ሰዎች በየቀኑ የ15 ዶላር ክፍያ እንደሚከፍሉ ተገልጿል።

ከሶስት ወር በላይ ያለ ፈቃድ የሚቆዩ ሰዎች በየቀኑ ቅጣት ከመቀጣታቸው በተጨማሪ ለ5 አመት ወደ ናይጄሪያ እንዳይገቡ ይከለከላሉ ተብሏል።

ከአንድ አመት በላይ ያለ ፈቃድ የሚቆዩ ሰዎች ከቅጣቱ በተጨማሪ ወደ ናይጄሪያ ዳግም እንዳይገቡ ይደረጋሉ ተብሏል።

በተጨማሪ በናይጄሪያ ያሉ ህገወጥ ስደተኞች በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ እራሳቸውን ህጋዊ እንዲያደርጉ እፎይታ መሰጠቱ የተገለፀ ሲሆን ከ3 ወር በኋላ ስደተኞችን ከሃገር የማስወጣት ዘመቻ ይጀመራል ተብሏል።

Source : Business Insider Africa

@tikvahethmagazine
ሜታ በናይጄሪያ ያለውን የፌስቡክ አገልግሎት ሊያቋርጥ እንደሚችል አስጠነቀቀ።

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሜታ ከሰሞኑ በናይጄሪያ በተለያዩ የህግ ጥሰቶች የ290 ሚሊየን ዶላር ቅጣት እንዲከፍል የተወሰነበት ሲሆን ድርጅቱ በሃገሪቱ የፌስቡክ እና የኢንስታግራም አገልግሎቱን ሊያቆም እንደሚችል አሳስቧል።

የናይጄሪያ መንግስተ ሜታ ከናይጄሪያ ግለሰባዊ መረጃዎችን ከመውሰዱ በፊት ፈቃድ ማግኘት አለበት ሲል ሜታ ይህ በፍፁም ሊሆን የማይችል ነው ብሏል።

ሜታ ከሁለቱ የመገናኛ ዘዴዎች ውጪ ዋትሳፕንም የሚያስተዳድር ሲሆን ስለ ዋትሳፕ አገልግሎት መቋረጥ ያለው ነገር የለም።

ሜታ ከመረጃ እና ከሌሎች ነገሮች ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ክስ እየቀረበበት ሲገኝ በቅርቡ በኬንያ በኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ግጭቶች እንዲባባሱ አድርጓል በሚል መከሰሱ ይታወሳል።

Source: BBC

@tikvahethmagazine
ጤና ማኒስቴር በፊስቱላ ህመም ላይ ጥናት ለማካሄድ የበጀት እጥረት አንደገጠመው ገለፀ።

ጤና ሚኒስቴር 140 ሺህ  ገደማ የሚሆኑ  እናቶች በፊስቱላ ህመም እየተሰቃዩ የህክምና አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን እና ጥናት ለማካሄድ የበጀት እጥረት አንደገጠመውገልጿል።

በተጨማሪም " በፊስቱላ ህመም ምክንያት ሴቶች ራሳቸውን እያጠፉ ነው " ብሏል።

በርካታ በሀገሪቱ የሚገኙ በፊስቱላ የተጠቁ ሴቶች ባዶ ቤት ተዘግቶባቸው እንደሚኖሩና ለከፍተኛ ድባቴ እየተጋለጡ መሆኑ ጠቁሟል።

በፊስቱላ የሚያዙ ሴቶች ህመሙ በሚፈጥረው መጥፎ ጠረን ምክንያት ከማህበረሰብ ተገልለው ከባድ ሕይወት እያሳለፉ መሆኑ አስረድቷል።

በህመሙ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ወደ ሕክምና ተቋማት ለመሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት መቸገራቸውን ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ዙሪያ ጥናት ለማድረግ 100 ሚሊየን ብር የሚጠይቅ ፕሮፖዛል አዘጋጅቸ ነበር ያለ ሲሆን ለዚህ የሚውል በጀት ማግኘት ግን አልቻልኩም ሲል አስረድቷል።

አክሎም " ፊስቱላን እስከ እ.ኤ.አ 2025 ድረስ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ግብ ቢያስቀምጥም አለመሳካቱን የገለፀ ሲሆን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በሰፊው አለመሰራታቸው እንደምክንያት ጠቅሷል።

በባለፈው አመት በተሰራ የጤናና የስነ ሕዝብ ዳሰሳ ከ100 ሴቶች ስለ ፊስቱላ የምታውቀው አንድ ብቻ እንደሆነች አመላክቷል።

Credit: Arada Fm

@tikvahethmagazine
01.05.202520:12
Shown 1 - 24 of 539
Log in to unlock more functionality.