Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
REVEAL JESUS avatar

REVEAL JESUS

We have to reveal jesus @revealj
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
LocationЕфіопія
LanguageOther
Channel creation dateApr 25, 2025
Added to TGlist
Feb 04, 2025
Linked chat

Records

25.04.202520:08
7.5KSubscribers
28.02.202523:59
150Citation index
17.02.202513:45
162Average views per post
20.04.202518:29
166Average views per ad post
29.03.202523:59
12.50%ER
16.02.202522:30
2.35%ERR
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
MAR '25APR '25

Popular posts REVEAL JESUS

25.04.202506:48
☀ ሁሉም ሰዉ መሪ ነዉ

☀ ስለዚህ አንተም መራ ነህ

☀ አመራር ደግሞ የሚጀምረው ራስን ከመምራት ነው

Dr eyob mamo
መልካም የፋሲካ በአል ይሁንልን!


ከሰማይ ክብሩን እንደ መቀማት ሳይቆጥር የአብን ፍቃድ ሳይገፋ በፈጠረው ፉጡር ተወልዶ አይተነው እንወደው ዘንድ ደምግባት ሳይኖረው ከሀጢያት በስተቀር በሁሉ ተፈትኖ ያለፈ በድካሙ ድካማችንን የሚረዳ በመከራ ያለፈ መከራችንን የሚያይ ሀጢያታችንን ሊምር እርሱ ራሱ ሀጢያት የሆነ ሁሉን በመስቀል ላይ የፈፀመልን ኢየሱስ እርሱ ብቻ ነው የመዳናችን ፈፃሚ። ሁሉን ፈራጅ የሆነው ጠማማ በሆኑ የፈራጆች ሸንጎ ፊት ለፍርዳቸው የቆመ ጋሻችን የሆነው እርሱ በጦራቸው ስለኛ የተወጋ የክብራችን አክሊል የሆነው መድሀኒተ አለም እርሱ የሾህ አክሊልን አለበሱት ከመቃብር በላይ ስም ያለው እርሱ መቃብር  ቦታው አርገው ቢያኖሩት ከመቃብር በላይ እንደ ሆነም በሶስተኛውም ቀን በመነሳት አሳያቸው።

ፋሲካችን የሆነው እርሱ እንደበግ ታርዶልናል!

@revealjesus
15.04.202518:28
ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ብርቱ የጸሎትን ሴት ከጎረቤቶቿ አንዷ "ሁል ጊዜ ስናይሽ እንደጸለይሽ ነው፤ ግን ደሞ በመፀለይሽ ምን እንደተጠቀምሽ ያየነዉ አንዳች ነገር የለም! ታዲያ ዘዉትር እንዲህ የምትለፊዉ ለምንድነዉ?" ስትል ትጠይቃታለች።

ብርቱዋ ሴትም እኔ ዘዉትር ጸልዬ ከጌታዬ ዘንድ ብዙ ነገር ተቀብያለሁ፤ ነገር ግን ሁሌም እኔ ትኩረት አድርጌ የምጸልየው በዓይን ስለሚታየዉና በእጅም ስለሚዳሠሰዉ ቁስ ሳይሆን፤ ከህይወቴ መወገድ ስላለባቸው ነገሮች እንጂ ስለሌላም አልነበረም!! እነርሱም ደግሞ፦
👉ትዕቢት ነበር ከእኔ ተወግዷል!!
👉ስግብግብነት ነበር ከእኔ ተወግዷል!!
👉ቅናት ነበር ከእኔ ተወግዷል!!
👉ጥላቻ ነበር ከእኔ ተወግዷል!!
👉ንዴት ነበር ከእኔ ተወግዷል!!
👉ሴሰኝነት ነበር ከእኔ ተወግዷል!!
👉ከኃጢያት ልምምድ ነበር ነፃ ወጥቻለሁ!!
👉ተስፋ መቁረጥ ነበር አሁን ከእኔ ዘንድ የለም!!
ታዲያ ከኔ በላይ ጸሎቱ የተመለሠለት ማንስ አለ?" በማለት አስረዳቻት።

ጎረቤቷም ባደመጠችዉ ምላሽ ሀፍረት ይዟት "ለካንስ የመኖራችን ዋናዉ ሚስጥር ይህም ነበር!" በማለት ይቅርታም ጠይቃት ተመለሰች።

እኛስ ታዲያ ዛሬ እየፀለይን ያለነዉ ስለምንድነዉ? ስለሚጠፋዉ ገንዘብ እና ቁስ ወይንስ በሕይወታችን ላይ መቀየር ስላለባቸዉ የዉስጥ ማንነት ነዉ?

እንግዲህ መጸለይ ካለብን ከእግዚአብሔር ዘንድ መቀበል የምንፈልጋቸው ነገሮች እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ እድገት እንዳናሳይ የሚያደርጉን ነገሮች ሁሉ ከህይወታችን ላይ እንዲወገዱ መሆን ይኖርበታል!!

ፀሎት ኃይል ይሰጣል፣ ያሳድጋል፣ ነጻ ያደርጋል፤ ከእግዚአብሔር አምላክ ጋር በቀጥታ የምንገናኝበት ድልድይ ነውና ሁላችሁ ዘዉትር እንዲህ ላለም ጸሎት ብርቱ ሁኑ!!

@revealjesus
30.03.202511:48
ሰላም ለሁላችሁ!

“የታደሰ አእምሮ” በተሰኘው ርእስ ስር ባለፈው የተመለከትናቸው ሃሳቦች . . .

1. “ሰማያዊ አመለካከት”

2. “ንጹህ አመለካከት”

3. “ስልታዊ አመለካከት”

4. “ሰፊ አመለካከት” የሚሉትን ነው፡፡

ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት ደግም የምንመለከተው፣ “ትልቅ አመለካከት” የሚለውን ሃሳብ ነው፡፡

ትልቅ አመለካከት

“እግዚአብሔር ታላቅነው” (መዝ. 48:1)፡፡ አለቀ! እርሱን ለመምሰል እንደተመከርን ሰዎች የእርሱን ትልቅነት ለመካፈል ይህ መሪ ጥቅስ በቂ ነው፡፡ ትልቅ አመለካከት ከተለመደው ምድራዊውና አናሳው አዙሪት የሚያወጣ አመለካከት ነው፡፡ ትልቅ አመለካከት ላቅ ብለን ተገኝተን ሌሎችንም ወደዚያ ከፍታ የምወጣበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡

ትልቅነት ማለት ሌላውን ማለት በተለያዩ ምድራዊ የፖለቲካ፣ የንግድና የመሳሰሉት ማሕበራዊ ጡዘቶች ውስጥ እንደሚስተዋለው የበላይ ሆኖ ሌላውን መናቅና መጨቆን ማለት አይደለም፡፡ አየህ እንደ እግዚአብሔር ትልቅ አምላክ የለም፤ ሆኖም እርሱ እንደኳን ወደር የሌለውን ትልቅነቱን ሌሎች ለማንሳት ነው የሚጠቀምበት፤ ከዚያም አላማው ንቅንቅ አይልም፡፡

“እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤ ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው” (ኢዮ. 36፡5)፡፡

የዚህ ክፍል አላማ አንድ አማኝ ስለ ትልቅ አመለካከት ሊያውቃቸው የሚገባውን መሰረታዊ እውነታዎች መግለጽ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የምናጠናቸው አምስት ዋና ዋና እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ከትንሽነት አመለካከት መውጣት

“ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ” (መዝ. 139፡14)፡፡

2. ከትንንሽ ንግግሮች መላቀቅ

“ደካማውም ሰው፣ እኔ ብርቱ ነኝ ይበል” (ኢዩ. 3፡10)፡፡

3. ከትንንሽ ገጠመኞች በላይ መኖር

“እርሱ ነውርን (ውርደትን) ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና” (ዕብ. 12፡1-2)፡፡

4. ከትንንሽ ጸሎቶች አልፎ መሄድ

“ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል” (ማር. 11፡23)፡፡

5. ከትንንሽ ዘሮች ዘልቆ መሄድ

“በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል” (2ቆሮ.9፡6)፡፡

Will See you tomorrow morning!
19.04.202507:21
በእኔ ላይ
ምህረቱ ነው የበላይ

ትርጉም አይገኝም ስለእርሱ ምህረት
ፈጽሞም አያልቅም ቢባል ቢባልለት
ልገልጸው አልችልም እኔም አቅቶኛል
በእኔ ላይ ምህረቱ እጅግ በዝቶልኛል

በእኔ ላይ
ምህረቱ ነው የበላይ

ከተወለድኩበት እስክ አሁን ቀን ድረስ
በዚህች በምድር ላይ ቆሜ ስመላለስ
በህይወቴ ዘመን የበዛው ጥበቃ
ነፍሴን አሳረፋት ምሳቀቋ በቃ

በእኔ ላይ
ጥበቃው ነው የበላይ

ለውድ ድር ብዬ ፍቅሩን አላቀርብም
የአምላክ ፍቅር ከሰው ምድቡም አይግጥምም
ይእርሱስ የተለየ መውደዱም ልዩ ነው
በእኔ ላይ የበላይ የአምላኬ ፍቅር ነው
የኢየሱስ ፍቅር ነው

በእኔ ላይ
ፍቅሩ ነው የበላይ

ቆጥቦ ሰስቶ ወስኖ አይሰጠኝም
ቸር ነውና እርሱ ደጅ አያስጠናኝም
ለህይወቴ ዘመን የሚያስፈልገኝን
በኔ ላይ ይሞላል ቸር ነው አይነሳኝም
ቸር ነው አይነጥቀኝም

በእኔ ላይ
ቸርነቱ ነው የበላይ

ከሞትና ሲዖል ወጣሁ ከሰቀቀን
በጣም ተደላደልኩ ጌታን ያገኘሁ ቀን
በህይወት መዝገብ ላይ ስሜን አሰፈረ
ሰይጣን ላያገኘኝ ዘላልም አፈረ ዘላለም ከሰረ

በእኔ ላይ
ማዳኑ ነው የበላይ
Reposted from:
ልባም ሴት 👸 avatar
ልባም ሴት 👸
27.03.202508:50
👉ለኔ ፦ ልባም ሴት የህይወት መርኋን ከውድቀቷ ፣ ከጎዷት ሰዎች ፣ ከስብሯቷ ፣ ከጓደኞቿ ፣ ከጊዚያዊ ደስታዋ "የምትቀዳ ሳትሆን ፤ ልባም ሴት የህይወት መርኋን ከአምላኳ ቃል እና እንዲሆንላት በምትፈልገው ከአላማዋና ከህልሞቿ ላይ ነው የህይወት መርኋን የምትቀዳው።

ውድቀቷ አይደለም መርኋ ፣
የጎዷት ሰዎች አይደሉም መርኋ ፣
ፈተናዎቿ አይደለም መርኋ።

ራሷን በአምላኳ ቃል እየመዘነች ፣ በአላማዋ እውነት እየከበደች ፣ ለራሷም ለአላማዎቿም ታማኝ በመሆን በመኖሯ ውስጥ መኖሯን የሚመጥን ህይወት ትኖራለች።

እንስራ ተሸክማ ውሃ  ልትቀዳ ከቤቷ የተነሳች ሴት ፣ ውሃን ለመቅዳት "ወንፊትን ለመቅጃነት ይዛ አትነሳም።
  👉ይልቅ ከእንስራዋ ጋር መቅጃ ጆክ ወይም ማንቆርቆሪያ ይዛ ነው የምትሄደው።

       የቱ ጋር ነሽ. . ?

    
13.04.202519:36
ከማን መስማት እንዳለባችሁ ለዩ

አንዳንድ ሰዎች አሉ አምናችሁበት እርግጠኛ ሆናችሁ አላማ ብላችሁ  መንገዳችሁን በመጓዝ ላይ ሳላችሁ
ይመጡና

     ለምን ስለዝህ ነገር ዋጋ ትከፍላለህ ብቀር አይሻልም ፣ ኤኬሌ ኮ ሄዶ አልተሳካለትም ፣ የያዝከውን መንገድ እርግጠኛ ነህ ?

የምሉ መልካም ለናንተም የሚጠቅም የሚመስሉ ሀሳቦችን በውስጣቸው ግን ድጋሚ እንዳትነሱ የህልማችሁን አከርካሪ የሚመቱ ገና ነገሩን ሳታዩት እድትደክሙ የሚያርጋችሁን ሀሳብ ና አስታያየት በፍጹም #አትስሙ

ከመጻሕፍ ቅዱስ ታስታዉሳላችሁ
ያን የሙኩራብ አለቃ የነበረውን

#ኢየሱስን ልጄ ልትሞት ነዉ አድንልኝ ብሎት አብርዉ መንገድ ጀምረው ልያድንለት እየሄደ

መጡኦ ሀሳብ ሰጭዎች :
ልጅህ ሞታለች፤ ስለ ምን መምህሩን አሁን ታደክመዋለህ? አሉት።
( ማር 5: 35)

🤔 እነዚህ ሰዎች አሁን የምር ልጁ መሞቷን ልነግሩት ፈልገዉ ነዉ ? ወይስ ኢየሱስ እዛ ሄዶ እዉነትም ይደክመዋል ብለዉ አስበዉ ነዉ ?

#በመሰረቱ ብትሞትም ማስነሳቱ አይቀር እሱ ጌታ ነዉ አዲስ ሰዉነትም መፈጠር ይችላል የሞተ ለሱ እንደተኛ ነዉ

#ስቀጥልም ለኢየሱስም አዝነው አደለም የሰቀለው ይሄዉ ህዝብ ነዉ

በአጭሩ ልጁን እንዲፈውስለት ከኢየሱስን መሄዱን እንዲተው ነዉ አላማቸው አስቡት እስቲ አምኗቸዉ ተስፍ ቆርጦ ትቶ ብመለስ አሮሩጠዉ ልቀብሩ ና አንድ ሳምንት ልስለቅሱት እንጂ

ወገኖች ህልማችሁን ማንም እንድቀብርባችሁ አትፍቀዱ ብበዛ ካስቀበሩ በኋላ ብያስለቅሱ ነዉ

ብቻ እግዚአብሔር በተናገራችሁ አላማዬ ነዉ አሳካዋለዉ ብላችሁ ከጀመራችሁት መንገድ የሰዉን ሀሳብ ሰምታችሁ አትመለሱ

የእግዚአብሔር ድምፅ ሰምታችሁ ቀጥሉ እንጂ

ኢያኢሮስ እንዳርገዉ

🙌 ኢየሱስ ግን ,,, ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው።

just keep going
✍️ Genet zewdie
19.04.202518:50
    ለአይምሮችን  ጥንቃቄ ስባል ጨርቅ ጣል አደረጉበት እንጂ አዳኜ የተሰቀለው እርቃኑን ነዉ

ብዙ አይነት ዉርደት አዉቃለሁ እንደ ጌታዬ ግን የተዋርደ ከዉርደትም ያለ ልክ የተዋረደ አላዉቅም ።

  ብዙ አይነት ክብር አዉቃለሁ እንደ ጌታዬ ግን የከበረ ከክብርም ያለ ልክ የከበረ አላዉቅም ።

   ቤዛዬን በመስቀል ያኖረው የተመታበት ሚስማር ሳይሆን የተላከበት ፍቅር ነው !
       የማን ?    
                     የኔ ና የአለም

እንኳንም ተሰቀልክልን እንኳንም ሞትክልን
እንኳንም ተነሳህልን
በዝህ ሁሉ ሞተህ  የወደድከን ብቸኛዉ  ወዳጅ መሆንህን አየን ኢየሱስ ❤️

Genet zewdie
20.04.202510:42
አብ ባለሞያ ነዉ ድግስ ያውቅበታል፣
አንድ በግ ሰውቶ ዓለም ጠግቦበታል።

የ reveal jesus ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ!!❤️🙌

✍️ ገነት ዘዉዴ
23.04.202519:45
እንተያይ ( እንመካከር )

አሁን አሁን እየቀሩ ካሉ ነገሮች  በተለይም በኛ በክርስትያኖች መካከል ብዬ የማስበው ቅዱሳን እርስ በእርስ አለመተያየት ና አለመመካከር ነዉ ።

በቸርቻችን ፣ በህብርቶቻችን ፣ በፈሎዎቻችን ወይም በየትኛዉም የመንፈሳዊም በሆነም ባልሆነም ስፈራ የምናዉቃቸዉን በጌታ እህትና ወንድም የሆኑ ወዳጆችን ምን ያህል ስለ ህይወታቸዉ ፣ ስለ ስራቸው ፣ አሁን ስላሉበት መንፈሳዊ ህይወት ፣ ስለ ቤተሰቦቻቸው እንጠያየቃለን !? መልሱን ለናንተ እተዋለሁ

መጽሐፍ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው

    “ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ  ( በርሳችሁ #ተመካከሩ) ፤
 
     ዕብራውያን 3፥13

እርስ በእርሳችን መመካከር ና  መነጋገራችንን  አንድም ሚጠቅመን  በአገልግሎት የምናዉቀዉን ብዙ  ዋጋ የተከፈለለትን ወንድም ና እህታችንን #በሀጥያት ምክንያት ከህይወት እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንግስት እንዳናጣዉ ይረዳናል ።

እናንተን አጋጥሟችሁ ከሆነ አላውቅም እኔ ግን በትጋትና በብዙ የልብ መቃጠል የጌታ ቃል በማካፈል እንዲሁም በመምራት የማዉቃቸዉን ከእግዚአብሔር ፈት ኮብልለው  አስተዉያለሁ ።

#በተለይ አንድ ልጅ አልረሳም ሀይስኩል እያለን ያኔ ብዙ መንፈሳዊ እድገት ላይ ባልነበርኩ ጊዜ እሱ ግን እረፍት ሰዓት ላይ ይሰበስበንና የመጻሕፈ ቅዱስ ጥናት ያስጠናናል ጥቅስ ይሰጠንና ለቀጣይ ቀን ተዘጋጅተን እንድንመጣ ያደርጋል ሌላው በሰዓቱ ብዙዎቻችን ወንጌል ለመናገር በምንፈራበት ጊዜ እሱ በድፈርት ይናገር ና እኛንም ያበረታታን ነበር ።

ከሆነ ጊዜ በኋላ ይሄዉ ልጅ ጌታን እንደተወ ሀይማኖቱን እንደቀየረ ራሱ ስነግረኝ ማመን ነበር ያቃተኝ በኋላም ስጠይቅ ከእናቱ ሞት በኋላ ከክርስትያኖች የጠበቀዉን ያለማግኘቱ ብቸኝነቱ እና ሌሎች ተደራራቢ ምክንያቶች ባክ እንዲያደርግ ጠላት እንደተጠቀመበት ለመስማት ቻልኩ ።

  ሁሉንም ባይሆን ለተወሰኑ ከቤተክርስቲያን ወገኖቻችን ምክንያቱም ሰዉ ከህብረት ፣ ከኳየር ፣ ከቸርች ስጠፉ ያሉበትን ሁኔታ አስቀድሞ ከመጠየቅ ና ካሉበት የትኛውም ችግር ( መንፈሳዊ , የገንዘብ , ጊዜ የማጣት ,  የጤና ና የመሳሰሉት ,,,,,)  ከመርዳትና ይልቅ የፈርድንባቸዉ  ና
  ያጣናቸው ቀላል የሚባሉ አይደሉምና ።


ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን #እንተያይ፤

በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን #እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።  ( ዕብ 10 ፥ 24,25 )

    ስለዝህ እባካችሁ እንተያይ እላለሁ

           ✍️ ገነት ዘዉዴ

@revealjesus
01.04.202510:01
ከትንንሽ ንግግሮች መላቀቅ

“ደካማውም ሰው፣ እኔ ብርቱ ነኝ ይበል” (ኢዩ. 3፡10)፡፡

ከትንንሽ ንግግሮች ነጻ መውጣት ማለት ካለሁበት እውነታ በላይ በሚያደርጉኝ ንግግሮች መሞላት ማለት ነው፡፡ እውነታው ደካማነቴ ቢሆንም እንኳን ብርታትን ማወጅ፤ እውነታው ጨለማ ቢሆንም እንኳን ብርሃንን ማወጅ፤ እውነታው አለመሳካት ቢሆንም እንኳን ጌታ ሁኔታዎችን እንደሚለውጥ ማወጅ

ይህ ከላይ የጠቀስነው ልምምድ እንዲሁ አይመጣም፡፡ ምስጢሩ መለኮታዊ፣ መነሻው ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያለ የጠበቀ ሕብረት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ስናደርግ በአይነ-ስጋችን ከምናየው አልፈን በአይነ-ህሊናችን እርሱ የሚያየውን ማየት እንጀምራለን፡፡

በአይነ-ስጋችን ከምናየው አልፈን ወደ መንፈሳዊው እይታ ስንገባ፣“አይናችን የሚያተኩረው በሚታየው ነገር ላይ ሳይሆን በማይታየው ላይ ነው፤ የሚታየው ጊዜያዊ ነውና፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው” (2ቆሮ. 4:17)፡፡

የዚህ አይነቱ እምነት የተሞላው የሕይወት ዘይቤ ምንጩ፡-

1. ደካማነትን እንደዘር የማየት መገለጥ

“በድካም ይዘራል፣ በኃይል ይነሳል” (1ቆሮ. 15:43)፡፡

ከትንንሽ ንግግሮች አልፈን ለመሄድና ተቃራኒውን ለመናገር ድፍረትን የሚሰጠን በሕይወታችን ያለ ማንኛውም በድካም የሚዘራ ዘር በእኛ ዘንድ በሚኖረው የክርስቶስ የትንሳኤ ኃይል አማካኝነት በኃይል የመነሳት ብቃት ስላለው ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ምስጢር ሲገባን ማንናውንም ደካማ ጎናችንን ከማስተጋባት በማለፍ በእኛ ውስጥ የሚሰራውን የክርስቶስ ኃይል የሚመጥን ንግግር መናገር እንጀምራለን፡፡

2. ደካማነትን የጌታ ኃይል መገለጫ እንደሆነ ማየት

“ኃይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና” (2ቆሮ. 12:9)

ከትንንሽ ነግሮች እንድንወጣ የሚነሳሳን ሌላኛው መንፈሳዊ ምስጢር የጌታ ኃይል በእኛ ደካማ ጎን ወደፍጽምና የመምጣቱ ብቃትና ኪዳን ነው፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ የእኛን ታናሽነት የእርሱን ታላቅነት ለመግለጥ፣ የእኛን ደካማነት ደግሞ የእርሱን ብርታት ለማሳየት፣ የእኛን መሸነፍ የእርሱን አሸናፊነት ለማወጅ መጠቀም ይፈልጋል፡፡ የእኛ ሃላፊነት ከተራና ከትንንሽ ንግግሮች ወጣ በማለት እርሱ የሚውጀውን ማወጅ ነው፡፡

3. ደካማነትን በጌታ ተደግፎ የመታደሻ መንገድ እንደሆነ ማመን

“እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኃይላቸውን ያድሳሉ” (ኢሳ. 40፡31)

በአናሳ ሁኔታው ውስጥ ሆነን አናሳነትን የማናወራው፣ በድካም ውስጥ ሆነን እንኳን ደካማነትን የማናወራው፣ በማይሆን ሁኔታው ውስጥ ሆነን እንኳን አለመሆንንና አለመሳካትን የማናወራው በጭፍንነት እውነታውን ለመካድ ሳይሆን የተሃድሶ ተስፋ ስላለን ነው፡፡ በምንም ሁኔታው ውስጥ ብንሆን ያለንበት ልምምድ የእኛ ልምምድ እንጂ እኛ የያዘን ጌታ ልምምድ እንዳልሆነ ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ እኛን ያስፈራን እርሱን አያስፈራውም፤ እኛን ትንሽ እንደሆንን ያሳየን ሁኔታ እርሱን አያሳንሰውም፡፡ ስለዚህ ከአናሳ ንግግሮች እንወጣና ጌታ የሚለውን እናስተጋባለን፡፡

የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ከትንንሽ ገጠመኞች በላይ መኖር”
28.03.202510:56
👐ተራራ ላይ ማዳን የቻለው ሸቆው ውስጥም ኃይል የእርሱ ነው!
18.04.202519:46
ለትውልድ የሚዘልቅን ዘር መዝራት

“የሚመጣ ትውልድ፥ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ” (መዝ. 78፡6)፡፡

ሁሉንም  ነገር ዛሬና ዛሬ ብቻ እኔው ከምጠቀምበት አንጻር መመልከት የክስረት ሁሉ ክስረት ነው፡፡ ዘላቂ አመለካከት ከሚወክላቸው እውታዎች አንዱ አንዳንድ ጊዜ በውጤቱ እኔ ጥቅምየማላገኝበትን ስራ መስራትና የግድ እኔ መብላት የሌለብኝን ዘር መዝራት ይገኝበታል፡፡ ይህ እጅግ ልናስብበት የሚገባ እውነታ ነው፡፡

ካለፉት አባቶቻችንን የወርሰነውን ነገር መለስ ብለን ስናስብ፣ ምናልባት፣ “ከዚህ የተሻለ ነገር አውርሰውኝ ቢሆን ኖሮ” በማለት የምንጸጸትባቸው ሁኔታዎች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ምልባትም፣ እንኳን ይህንን ነገር አወረሱኝ ብለንም የምንኮራባቸው ሁኔታዎ አይጠፉም፡፡

ከቀደሙት አባቶቻችን የወረስናቸው ሁኔታዎች ይህን ያህል ስፍራ ካላቸው፣ እኛ ለሌላው የምናወርሰውን ነገር ምን ያህል ልናስብበት ይገባል!

1.  ለዘር የሚዘልቅ ኪዳን

“በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ” (ዘፍ. 17፡7)፡፡

ቤተቦችህ ከጌታ ጋር የጠለቀ የጸሎትና የቃሉ ሕብረት ኖሯቸወ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ምን አይነት ሕይወት ይኖርህ ነበር?በዘር ሃረግህ ውስጥ የሚገኙ ቀደሙህ ሰዎች ለልጅ ልጅ የሚወርድ ኪዳን ከጌታ ተቀብለው ቢሆን ኖሮ ሕይወትህ ወደየት አቅጣጫ ሊሄድ እንደሚችል አስበህ ታውቃለህ? በጌታ ፊት በጸሎት በመትጋትና ለአንተና ለዘርህ የሚተርፍን ኪዳን ከጌታ መቀበል እጅግ ውብ የሆነ ነገር ነው፡፡

2.  ለዘር የሚዘልቅ ፈርሃ-እግዚአብሔር

“ሃሌሉያ። እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ የተባረከ ነው። ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች”(መዝ. 112፡1-2)፡፡

ለልጆችህ ልታወርሳቸው ክምትችላቸው ታላላቅ ነገሮች መካከል ፈርሃ-እግዚአብሔር አንዱ ነው፡፡ ልጆቻችን ንግግራችንን ብቻ ሳይሆን ተግባራችንን ጭምር እየቀሰሙ እንደሚያድጉ ሲገባን በንግግራችንም ሆነ በተግባራችን “ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ” (መዝ. 34፡11) ማለትን እንጀምራን፡፡

3.  ለዘር የሚዘልቅ ብልጽግና

“ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤ የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል”(ምሳ. 13፡22)፡፡

አንተ ካለፍክ በኋላ ልጆችህ የማይቸገሩበትን የኢኮኖሚ መስመር ዘርግተህ እለፍ፡፡ ይህ የደግና የለጋስ ሰዎች ባህሪይ ነው፡፡ ይህ የቅዱስ ቃሉ ምክር ነው፡፡ ይህ ብዙዎች የማያስተውሉትና መንገድ ነው፡፡ ይህንን ምክር ለመለማመድ ግን ዛሬ በእጅህ ያለው ነገር የአንተ ብቻ እንዳልሆነና ለልጅ ልጆች ሊተላለፍ እንደሚገባው ልትገነዘብ ይገባሃል፡፡

ቀደም ሲል እንደተመለከትነው፣ ቤተሰቦችህ አንድ እርምጃ አራምደው አስጀምረውህ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ምን አይነት ሕይወት ሊኖርህ እንደሚችል አስብ፡፡ ስለዚህም፣ ሁሉን ነገር ከራስህ አንጻር ብቻ አትመልክት፡፡ ዘላቂ አመለካከት ይኑርህ፡፡

ይህ ክፍል ተጠናቀቀ! በክፍል ሰባት እስከማገኛችሁ ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ

@revealjesus
05.04.202518:12
ለሚያወራህ ውበት ለሚለብስህ ጌጥ
ሮጦ ለተጠጋህ የማምለጫ አለት
ህይወት ከሞት ወዲያ እርስቱ ላረገህ
ለአፍታ እንኩዋን የማትጎድል ለሰው ሙላቱ ነህ
አንተን ነው እንጂ ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ
ማልዶ በጠዋት በአንተው እጅ ደምቆ መዋል ደጅ እየጠኑ
አንተን ነው እንጂ ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ
ማልዶ በጠዋት በአንተው እጅ ነቅቶ መዋል ደጅ እየጠኑ

አይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ
ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ
ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ
ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ
እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ
ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋ
ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ
ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ

በድነቴ ጠዋት በገባኸኝ ማግስት
ጨዋታ ወሬዬ መወደዴን ማድነቅ
ዘምሬህ አልጠግብ አውርቼህ አልረካ
ይቺህ ትንሽ ልቤ ለፍቅርህ ሸፍታ

አልደግ አንተላይ እራሴን አልቻል
አጓጉል ነው ሁሉም ያላንተ መች ያምራል
መጠበቂያ አጥሬ መሰንበቻዬ ነህ
ልኑር እንደፈዘዝኩ አይኔ አንተን እያለ

ጉዳዬ አንተው ነህ
መናፈቄ መምጣትህን
ጉጉቴ አይኔ እስከሚያይህ

| @revealjesus
| @revealjesus
Log in to unlock more functionality.