እንተያይ ( እንመካከር )
አሁን አሁን እየቀሩ ካሉ ነገሮች በተለይም በኛ በክርስትያኖች መካከል ብዬ የማስበው ቅዱሳን እርስ በእርስ አለመተያየት ና አለመመካከር ነዉ ።
በቸርቻችን ፣ በህብርቶቻችን ፣ በፈሎዎቻችን ወይም በየትኛዉም የመንፈሳዊም በሆነም ባልሆነም ስፈራ የምናዉቃቸዉን በጌታ እህትና ወንድም የሆኑ ወዳጆችን ምን ያህል ስለ ህይወታቸዉ ፣ ስለ ስራቸው ፣ አሁን ስላሉበት መንፈሳዊ ህይወት ፣ ስለ ቤተሰቦቻቸው እንጠያየቃለን !? መልሱን ለናንተ እተዋለሁ
መጽሐፍ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው
“ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ ( በርሳችሁ #ተመካከሩ) ፤
ዕብራውያን 3፥13
እርስ በእርሳችን መመካከር ና መነጋገራችንን አንድም ሚጠቅመን በአገልግሎት የምናዉቀዉን ብዙ ዋጋ የተከፈለለትን ወንድም ና እህታችንን #በሀጥያት ምክንያት ከህይወት እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንግስት እንዳናጣዉ ይረዳናል ።
እናንተን አጋጥሟችሁ ከሆነ አላውቅም እኔ ግን በትጋትና በብዙ የልብ መቃጠል የጌታ ቃል በማካፈል እንዲሁም በመምራት የማዉቃቸዉን ከእግዚአብሔር ፈት ኮብልለው አስተዉያለሁ ።
#በተለይ አንድ ልጅ አልረሳም ሀይስኩል እያለን ያኔ ብዙ መንፈሳዊ እድገት ላይ ባልነበርኩ ጊዜ እሱ ግን እረፍት ሰዓት ላይ ይሰበስበንና የመጻሕፈ ቅዱስ ጥናት ያስጠናናል ጥቅስ ይሰጠንና ለቀጣይ ቀን ተዘጋጅተን እንድንመጣ ያደርጋል ሌላው በሰዓቱ ብዙዎቻችን ወንጌል ለመናገር በምንፈራበት ጊዜ እሱ በድፈርት ይናገር ና እኛንም ያበረታታን ነበር ።
ከሆነ ጊዜ በኋላ ይሄዉ ልጅ ጌታን እንደተወ ሀይማኖቱን እንደቀየረ ራሱ ስነግረኝ ማመን ነበር ያቃተኝ በኋላም ስጠይቅ ከእናቱ ሞት በኋላ ከክርስትያኖች የጠበቀዉን ያለማግኘቱ ብቸኝነቱ እና ሌሎች ተደራራቢ ምክንያቶች ባክ እንዲያደርግ ጠላት እንደተጠቀመበት ለመስማት ቻልኩ ።
ሁሉንም ባይሆን ለተወሰኑ ከቤተክርስቲያን ወገኖቻችን ምክንያቱም ሰዉ ከህብረት ፣ ከኳየር ፣ ከቸርች ስጠፉ ያሉበትን ሁኔታ አስቀድሞ ከመጠየቅ ና ካሉበት የትኛውም ችግር ( መንፈሳዊ , የገንዘብ , ጊዜ የማጣት , የጤና ና የመሳሰሉት ,,,,,) ከመርዳትና ይልቅ የፈርድንባቸዉ ና
ያጣናቸው ቀላል የሚባሉ አይደሉምና ።
ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን #እንተያይ፤
በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን #እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። ( ዕብ 10 ፥ 24,25 )
ስለዝህ እባካችሁ እንተያይ እላለሁ
✍️ ገነት ዘዉዴ
@revealjesus