Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ጥበብ ፍልስፍና avatar

ጥበብ ፍልስፍና

ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ ፫፮፱
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
Location
LanguageOther
Channel creation dateAug 25, 2022
Added to TGlist
Sep 07, 2024
Linked chat

Records

23.04.202523:59
2.1KSubscribers
14.04.202517:17
700Citation index
16.04.202517:08
1.6KAverage views per post
16.04.202514:40
1.6KAverage views per ad post
24.03.202516:19
8.14%ER
23.12.202403:03
85.97%ERR

Popular posts ጥበብ ፍልስፍና

አ. .ስ. .ታ. .ው. .ስ!

             ☠️  ትሞታለህ ☠️

/ Memento mori /
(ነግሬሽ ነበር እኮ! ለፈገግታሽ እንጂ ለገላሽ እንደማልሞት!)
¹ አብ ልጁን ለደረው፣ ምን አስቀናት ፀሐይ?
      ፊቷን  ያጠቆረች፣ ዓለሙን እንዳያይ::

² ሊጠቅመው አስቦ፣ አባቱ በመላ
ላጀበው ሰው ሁሉ፣ ፅዋዉን ሳይሞላ
ልጁን ብቻ አጠጣዉ፣ የድግሱን ጠላ።

³ ደሀ አባት ደግሶ፣ ታዳሚዉን ሁሉ
በሬ ሳያዘጋጅ፣ ነው የጠራው አሉ፣
ካጀቡት ቡኋላ፣ ተጠምተው ተርበው
ከልጁ በስተቀር፣ የለም የሚያቀረበው።

⁴ ስንት ቢታረድ ነው፣ ምን ያክል ቢደገስ
ስጋዉ የሚበላዉ፣ እስከ ዛሬ ድረስ?

⁵ የተሰቀለዉን፣ ስጋዉን ሳይቀምሱ
አጃቢዎች ምነዉ፣ ተሻሙ ለልብሱ?

⁶ለሙሽራዉ ሀሞት፣ ምን ያህል ቢጥም ነው?
ለሚዜውቹ እንኳ፣ አላጠጣም ያለዉ?
            

@ethiosecret
20.04.202518:21
ሁላችንም የተፈጥሮ አካላቶች ነን
- ስፒኖዛ

ምንጭ፦ ፍልስፍና ከዘርአያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት፦ ፍሉይ አለም

በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ብዙ ኃይላት አሉ፡፡ ምድር ወደ ላይ በረን እንዳንሄድ ስባ ታስቀረናለች፡፡ ጸሐይ ምድርን በክብ ምህዋር ላይ እንድትዞር ታስገድዳታለች... ብንዘረዝራቸው የማያልቁ ብዙ ኃይላትን በሁለንተና ውስጥ እናገኛለን፡፡ በእያንዳንዱ ቁስ አካል ውስጥም ይፈሳሉ፡፡ በዓለም ሁሉ ያለ ነገር በእነዚህ ሃይሎች ተይዟል፡፡ ሰዎች፣ በባህር ውስጥ ያለ አሳ፣ ከወፎች የሚወጣ ድምጽ... ሁሉም የዚህ ኃይል አካል ናቸው፡፡ ሁላችንም በእነዚህ ኃይላት ታስረናል፡፡

ይህ ሁለንተናን በሌላ መንገድ የመመልከቻ ሃሳብ የቀረበው ባሩክ ስፒኖዛ በተባለ ፈላስፋ ነው፡፡ የፍልስፍናውም ሃሳብ ሞኒዝም ተብሎ ይጠራል፡፡ ሞኒዝም ቃሉ “አንድ ብቻ” የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ ይህም በሁለንተና ውስጥ ያለ ነገር ሁሉ እንደ “አንድ አካል” ነው የሚል አንድምታ አለው፡፡ እኔም አንተም፣ ጨረቃም ጸሐይም - ሁላችንም በአንድ አካል ውስጥ እንዳሉ ህዋሳቶች ነን፡፡

ስፒኖዛ ከአብርሆት ዘመን በፊት የነበረ አውሮፓዊ ፈላስፋ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር በአንድ ዘመን የነበረው ዴካርት በሁለንተና ውስጥ ያሉ ነገሮችን በሶስት ይከፍላቸዋል- አእምሯዊ፣ አካላዊ እና አምላክ (ያልተፈጠረ እና ሁለንተናን የፈጠረ)።

ነገር ግን ስፒኖዛ እንዲህ ይላል - ከሁላችንም በላይ የሆነ እና ሁላችንንም የሚያውቅ አምላክ ካለ፣ ይህ አምላክ በሆነ መንገድ ከሁላችንም ጋር ይገናኛል ማለት ነው፡፡

“አቤቱ፣ ፈትነኝ መርምረኝም፤ ኩላሊቴንና ልቤን ፈትን:: እንዳለው መዝሙረኛው ዳዊት፣ ልብ እና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ በልብም፣ በኩላሊትም ውስጥ መገኘት አለበት ይለናል ስፒኖዛ፡፡ የአካላቸው ክፍል የሆኑ ነገሮችን ብቻ ነው ልንመረምር የምንችለው... አምላክም እኛን ሊመረምር የሚችለው እኛ የእርሱ አካል እስከሆንን ድረስ ብቻ ነው፡፡ እግርህ ላይ ያለ ህመም የሚሰማህ እግርህ የአንተ አካል ስለሆነ ነው፡፡ አምላክም የእኛ ህመም የሚሰማው እኛ የእርሱ አካል ስለሆንን ነው፡፡

በተመሳሳይም በሁለንተና ውስጥ ያሉ ሁሉም ነገሮች እንደ አንድ አካል ናቸው፡፡ አእምሮም፣ አካላዊ ቁሶችም የአንድ ግዙፍ ስርዓት አካል ናቸው፡፡ እንደ አንድም ይንቀሳቀሳሉ። ሁሉም ነገር ስረ መሰረቱ አንድ ነው፡፡ ያንተ ህሊናም፣ የጉንዳኖች ጉዞም፣ የአንዲት የብርሃን ቅንጣት፣ አንዲት ጠብታ ውሃም መዳረሻቸው አንድ ነው ...
ሞኒዝም፡፡
አንስታይን ስፒኖዛን ይወደው ነበር፡፡ የስፒኖዛ ፍልስፍና ለእርሱ ሒሳባዊ ቀመሮች የሚፈይድለት ነገር ኖሮ አይደለም፤ ነገር ግን ስፔኖዛ ተፈጥሮን እንደ አምላክ አድርጎ ስለሚገልጻት ነው። አንስታይንም ተፈጥሮን አምላክ ብሎ ይጠራት ነበር፡፡

ስፒኖዛ ከጥቃቅን ነገሮች ወይም ተፈጥሮን/አምላክን ለመረዳት መጓዝ አለብን ይለናል፡፡ በተፈጥሮ ሁነቶች ተነስተን ውስጥ ራሳችንን እያስመጥን ስንመጣና ከተፈጥሮ ጋር ፍጹም አንድ ስንሆን፣ መታበያችን ከእኛ ይርቃል። እኔ እንዲህ ነኝ ማለትንም እናቆማለን፡፡ ራሳችንንም ነጥለን የምንኮራበት አልያም የምንወቅስበት ምክንያት አይኖርም... ምክንያቱም “እኔ” የሚባል ማንነት
አይኖረንም...


ስፒኖዛ የሰው ልጆች ሕይወታቸውን አወሳስበው ይኖራሉ ይለናል። ልክ እንደ ህጻናትም በጸደይ አበባ መሃል ከመቦረቅ ይልቅ፣ በብዙ ጥቃቅን ጉዳዮች ራሳችንን አስረነዋል። ይህ የሚገባን ግን እድሜያችን ሲገፋ ብቻ ነው፡፡ በእርጅና ዘመናችን በወጣትነታችን የነበሩ አላስፈላጊ ጭንቀቶቻችን እና ፍርሃቶቻችን ይገለጡልናል። ሕይወታችን ውስጥ ያሉ ነገሮችንም መውደድ እና ማድነቅ እንጀምራለን፡፡
28.03.202518:21
የቀጠለ

እውን ኢትየጵያ ሥልጡን ሀገር ነበረችን?


የዘርፉ ባለሙያዎች አንድ ጥንታዊ ስልጣኔ የተሟላ ስልጣኔ ነው ለመሰኘት ቢያንስ ከተሞች፣ የማህበረሰብ አወቃቀር፣ ሐይማኖት፣ የተደራጀ መንግሥት፣ የጽሕፈት ቋንቋ፣ ባህልና ሳይንሳዊ ፈጠራን ያካተተ ሊሆን ይገባል ይላሉ፡፡ በእርግጥ ከናፓታም ተነሳን ከዬሐ ኢትዮጵያ እንደ አክሱም፣ አዱሊስ፣ ሐረር፣ ጎንደር የመሳሰሉ ታላላቅ ከተሞች ነበሯት፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር አብዛኛው አውሮፓዊ እንደ ዘላን በዋሻዎች መካከል እየኖረ የበቆሎ ገንፎ በሚበላበት ዘመን ኢትዮጵያዊያን ግን በራሳቸው ፊደል ይጻጻፉ ነበር፡፡

ሞዛርትና ቪትሆቨን ከመወለዳቸው አንድ ሺኅ ሁለት መቶ ዓመታት በፊት፣ አሜሪካ እንደ ሀገር ከመቆርቆሯ ሺኅ ዘመናት አስቀድሞ ኢትዮጵያዊው ያሬድ ግን ሙዚቃን በኖታ እየጻፈ ይራቀቅ ነበር፡፡

ታሪክ የመዘገበውን ብቻ እንኳን ብንጠቅስ ከክርስቶስ ልደት 1000 ዓመታት በፊት ጀምሮ ኢትዮጵያ ንጉሣዊ መንግሥታት ነበሯት፡፡
ነገሥታቶቿ ትልልቅ መርከቦችንና የመስኖ ቦዮችን ያስተዳድሩ ነበር፡፡ በዚህ አግባብ ካየነው በእርግጥ ኢትዮጵያ ስልጡን ሀገር ነበረች! ወሰኑ በየጊዜው ሊሰፋ ሊጠብ ቢችልም ቅሉ ከህንድና ከቻይናም በላይ የኢትዮጵያ ሥነ መንግሥታዊ ሥርዓት ከቅድመ አክሱም ዘመን ጀምሮ ሳይከስም መቀጠሉን ሪቻርድ ፓንክረስትና መሰል የዘርፉ ጠበብት ደጋግመው መስክረዋል፡፡

ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን ከተሞች ቢኖሯቸው ቅሉ ነገሥታቱ ዘላኖች(nomads) ሆነው አልፈዋል፡፡ የነገሥታቱ አጀብ ለሺኅ ዓመታት እንደ አንበጣ መንጋ የሚያልፍባቸውን አካባቢዎች ሁሉ ጠራርጎ የሚበላ ገና በሩቅ ሲጠራ ለነዋሪዎቹ ሽብርን የሚነዛ ወራሪ ተሰሪ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብቸኛው የፊደል ገበታ ባለቤት ብትሆንም ቅሉ የሚራቀቁበት ጥቂት  ደብተራዎች ብቻ እንደነበሩ መናገር ለቀባሪ ማርዳት አይሆንብኝ ይሆን? ሌላው ሕዝብ እና አንዳንድ ጊዜ ነገሥታቱም ሳይቀር ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ጨዋዎች ሆነው አልፈዋል፡፡

ላሊበላን ከሚያህል አስደናቂ የውቅር አብያተክርስቲያናት ስብስብ ጥቂት መቶ ሜትሮች ርቀት ዛሬም ድረስ የሰዎች መኖሪያ የሆኑ ያዘመሙ ጎጆዎች ይታያሉ፡፡
ከእነዚያ መከረኛ ቤቶች በባዶ እግር እየተረማመዱ የሚወጡ ጉስቁል ፍጡራን በምናቤ ይታዩኛል፡፡ ዛሬም ድረስ በየመንገዱ የሚጸዳዱ ሰዎች አሉ፡፡ ከተማዋ በምሽት ለሚመለከታት በመብራት እጦት ከፈል በድን ሆና በኩራዝ ብቻ የምትስለመለም የሙታን ከተማ ትመስላለች፡፡
ከፋሲል ግንብ ጥቂት መቶ ሜትሮች ርቀት እንኮዬ መስክ የመሸገውን ዘቀጠ ሕይወት ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ ዘወትር በምሽት ስንሸራሸር ፋሲል  ከሕዝቡ የአኗኗር ስልት ጋር መጣጣም ተስኖት ለብቻው ጎንቁሎ ፣ እንግዳነት የተሰማው መስሎ ሳየው እድጌያለሁ፡፡
የአክሱማዊያኑም እውነት ከዚህ የተለየ አይመስለኝም፡፡ ታዲያ እነዚህ እኒህን እፁብ ድንቅ ሀውልቶችና ኪነ ሕንጻዎች ከሰሩ በኋላ የት ሄዱ? በኑሯቸው ሳይገለጽ ቀረ? የምርስ ስልጣኔ ነበረን???!
- ለምሳሌ በ6ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ ስፔኖች ደቡብ አሜሪካ ሲደርሱ በእርሻ ልማትና በኪነ ሕንጻ ጥበባት የተራቀቁብት ኢንካዎችና እዜቴዝኮች የፊደል ዘር መኖሩን እንኳን የማያውቁ መሀይማን ሆነው አግኝተዋቸዋል፡፡ በእርግጥ ኢትዮጵያዊ ስልጣኔ ብሎ ነገር ነበር! ግን ምን ዓይነት ስልጣኔ? የኦሮሞዎችን የገዳ ስርዓት ጨምሮ ወደ ሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ሲኬድ የሚታየው የሀገረሰብ ጥበብና ዕውቀት ገና ያልተጠናና በቅጡ የማይታወቅ ቱባ ነው፡፡ በቅርቡ Korra Gorra የተሰኘ ጣሊያናዊ የጻፈውን መጽሐፍ አንብቤ በኮንሶዎቹ ረቂቅ እሳቤዎች እና የአኗኗር ጥበባት በግርምት አፌን ይዣለሁ፡: እንቀጥል..

- የአሜሪካ ቀደምት ሕዝቦች ቀይ ህንዶች «ምድርን ከልጅ ልጆቻችን ተዋስናት እንጂ ከአያቶቻችን አልወረስናትም፡፡›› ይላሉ፡፡ ይሄ አባባል ለታሪክም ግጥም አድርጎ ይሠራል፡፡ ወደዳችሁም ጠላችሁም አድዋን የወረሥነው ከንጉሥ ምንይልክ፣ ከራስ አሉላ ወይም ከደጃዝማች ባልቻን ከመሳሰሉት አይደለም፡፡ አድዋ የልጅ ልጆቻችን የትውስታ ጌጥ ነች፡፡ አያቶቻችን በአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች ተረተር በዚያች ቀውጢ የሰንበት ማለዳ ከሞት ጋር የተናነቁት ለእያቶቻቸው ዝና አልነበረም፤ ምናልባት ለራሳቸው ክብርና ሞገስም ነበር ለማለት አልደፍርም፡፡

የዚያ ሁሉ ኣሰቃቂ ትንቅንቅ ምክንያት ለልጅ ልጆቻቸው የሚተርፍ ባርነትን ላለመሸከም የተደረገ መራር ተጋድሎ ይመስለኛል፡፡ ላሊበላንም ሆነ አክሱምና ፋሲል ለልጅ ልጆቻችን የተተው ውድ ሀብቶች ናቸው፡፡ እናም የወረሱትን እንጂ የተዋሱትን ነገር መሸጥ ሆነ ማውደም በእውነቱ የተገባ አይደለም፡፡ እንዲያውም በቅጡ ማጥናትና አጉልቶ ማስረከብ የትውልድ ግዴታችን ይመስለኛል፡፡

ታሪክ እና ስልጣኔ ግን በጊዜ ቅደም ተከተል የተሰደሩ የሁነቶች ጥርቅም ብቻ አይደሉም፡፡ ከዚያም ይረቃሉ፡፡ ፈረንሳያዊው ፈላስፋ ቮልቴር ‹‹History should be Written as philosophy.” ይላል፡፡ በቅርቡ እንደ ሀገር ከተመሰረተት በቅጡ 300 ዓመት እንኳን ባልሞላት አሜሪካ በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ሸክላ ሰሪዎች በሸክላዎቻቸው ላይ ያስተላለፏቸውን መልዕክቶች የሚያጠና በቅፆች የተደራጀ መጽሐፍ አንብቤ በቅናት
ተብከንክኛለሁ፡፡


ኢትዮጵያዊያን እደጥበበኞች ከአክሱም ዘመን በፊት ጀምሮ ሸክላን በመሳሰሉት ጥበባት ላይ ሲራቀቁ ቢያሳልፉም ማንም ምንም ብሎላቸው አያውቅም፡፡ በዓለም ታሪክ ውስጥ ከነበሩ ቀደምት ስልጣኔዎች ሁሉ በቅጡ ያልጠና፣ የተረሳ፣ በየታሪክ መጻሕፍቱ ሁሉ ኩርማን ገጽ ብቻ የሚሰጠው፣ ይህ ነው የሚባል ስም ያልወጣለት ስልጣኔ ቢኖር የኢትዮጵያ ስልጣኔ ብቻ ነው፡፡ ከእኛው ስልጣኔ ጋር የመወራረስ ዝንባሌ ያለው የግብፅ ጥንታዊ ስልጣኔ የተሰጠውን አለም አቀፍ ትኩረት መመልከት ይበቃል።

የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ቀለማት ከአክሱምና ድኅረ አክሱም ዘመን ጀምረን ለመመርመር ከሞከርን ግን ነገሩ ሌላ ገጽ ይላበሳል፡፡ ግርማ ሞገስ የተሰኙ ጸሐፊ በ2006 ዓ.ም ለንባብ ባበቁት መጽሐፋቸው ከአክሱም ወርቃማ ዘመናት ጀምሮ ኢትዮጵያ በድምሩ ከ500 ዓመታት በላይ በእርስ በእርስ ጦርነት ስትናጥ አሳልፋለች ይሉናል፡፡ ታሪካችን ሙሉ ለሙሉ የጦርነትና የሁከት እንደመሆኑ ነገሩን እንደገና በቅርበት ለሚያጠናው በብጥብጥ የባከነወ ጊዜ ከ800 እስከ እንድ ሺኅ ዘመናት ከፍ ሊል እንደሚችልም እገምታለሁ::ዛሬም ከዚያ እዙሪት አልወጣንም፡፡ የሆነስ ሆነና ራሱ ሥልጣኔ ምንድን ነው? ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ «Modernity: Its title to the uniqueness and its advent in Ethiopia” በተሰኘ አጭር መጣጥፋቸው «pluralism is the deep fact of Modernity›› የሚል ሀሳብ ኣንስተዋል፡፡ ዝመና እና ስልጠና(ል ጠብቆ ይነበብ) የቅርብ ርቀት ልዩነት ሊኖራቸው ቢችልም ቅሉ ዶክተር እጓለ ገብረዮሐንስ ‹የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ›› በሚል ርዕስ በሰየሙት መጽሐፋቸው ስልጣኔን በቅጡ ለመረዳት ካልቸር የነፍስ የመንፈስ ወይም ውስጣዊ ሥልጣኔ) እና ሲቪሊዜሽን (አካላዊ ወይም አፋዊ ስልጣኔ) የሚሉ ሁለት ቃላት ጠቃሚ መሆናቸውን በአጽዕኖት አብራርተዋል፡፡ ዶ/ር እጓለ ይቀጥሉና የአውሮፓ የስልጣኔ ጉዞ አንድ አቅጣጫ ብቻ የተከተለ አልነበረም፡፡ የአውሮፓ የህዳሴ ጉዞ ሁሉንም ሰብዓዊ፣ ኪናዊ፣ ፖለቲካዊና ሳይንሳዊ ዘርፎች ባሻገር የቻለ ሁሉን አቀፍ የለውጥ ሂደት ነበር፡፡ ይላሉ፡፡
06.04.202518:21
ማንነት

ልጅ ሳለህ የተነሳኸውን ፎቶ ተመልክተኸው ታውቃላህ ? ምን ትዝ ይልሀል? ምንስ ታስታውሳለህ? ትንሹ አካልህ በግዙፍ አካል ተቀይሯል። የምታስባቸው ነገሮች ፣የምትመርጣቸው ነገሮች ልጅ ከነበርክበት ጊዜ በእጅጉ ተቀይሯል።ሰለዚህ ማንነትህ ተቀይሯል ማለት እንችላለን ? በእርግጥ ስለባለፈው ማንነትህ ትውስታ ይኖርሀል። ትውሰታህን በሙሉ አትጠተህ  ማንነትህ በሌላ ማንነት ቢቀየርስ አንተ አለህ ማለት እንችላለን?

የፍልሰፍና ማዕድ መፅሀፍ ውስጥ ይሄን  ፁሁፍ አገኘሁ

"ፊሊፕ ዲክ የተባለ ደራሲ በጻፈው We can remember it for you wholesale በተሰኘ የአጭር ልቦለድ ታሪክ ውስጥ አርኖልድ ኮነን የተባለ ገጸ ባህሪ እናገኛለን፡፡ ኮነን አንድ ቀን ደስ የማይል ነገርን አገኘ፡፡ ኮነን በጭራሽ አርኖልድ ኮነን አይደለም፡፡ ወይም በሌላ አነጋገር የቀድሞ ማንነቱ ሌላ ነበር። ግራ ተጋባ።

ታሪኩን ሲመረምርም  ስለቀድሞ ማንነቱ ያውቃል። ሲወለድ የተሰጠው ስም አለን ውድ ነበር፡፡ ውድ መልካም ሰው አይደለም። ራስ ወዳድ፣ ጨካኝ እና ምህረት አልባ ነበር፡፡ ከሁለት አመት በፊትም  ከወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር ጥልቅ የሆነ ችግር ውስጥ ገባ። እሱም ሁለት አማራጭ አቀረቡለት፤ ጭንቅላቱ ውስጥ ያሉት መረጃዎች በሙሉ ተደምስሰው በሌላ እና ልቦለዳዊ በሆነ የውሸት ሰው እንዲተኩ አልያም ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግበት እና ስቃይ ባለው እስር ቤት ውስጥ እድሜውን ሙሉ እንዲያሳልፍ፡፡

ትውስታዎቹ እንዲደመሰሱለት መረጠ፡፡ እናም አለን ውድ ጥልቅ የሆነ መደንዘዝ ውስጥ እንዲገባ ተደርጎ ትውስታዎቹ በአዳዲስ እና በውሸት ትውስታዎች ተተኩለት፡፡ ሲነቃም እስከዛሬ የነበሩትን የሕይወት ትውስታዎች ሁሉ ዘንግቷል፡፡ እሱም የሚያውቀው ኮነንን እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

አሁን ላይ ኮነን፣ በቀድሞ ሕይወቱ አለን ውድ'ን እንደነበር አውቋል፡፡ እናም ይህ ሰው ማን ነው? ውድ ወይስ ኮነን?
የኮነን/ውድ የማንነት ቀውስን ለመፍታት ቀላል የሚመስል ችግር ቢሆንም፤ መልሱ ግን እንደምናስበው ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች የኮነን እውነተኛ ማንነቱ የቀድሞ ማንነቱ እንደሆነ ይደመድማሉ።
የአብዛኞቻችን ማንነት ከአዕምሮ እና ከሰውነት እድገታችን ጋር የተቆራኘ ነውና እንዲህም ማሰባችን ተገቢነት ይኖረዋል። እስከ ዛሬ ሁለት አመት ድረስም ይሄ ሰው ወንጀለኛው አለን ውድ ነበር፤ አሁን አለን ውድ የለም የምንል ከሆነ፣ አስክሬኑ የታል፣ የታልስ የሞተው? ማንም የሞተ ሰው የለም፤ እና አለን ውድ የት ሄደ? ይሄ ሰውስ ማን ነው?

አርኖልድ ኮነን (በውሸት የተፈጠረው ማንነት) የአዕምሮ ጤና ሃኪም ነው፡፡ ስለ ልጅነቱም ሆነ ስለ ጉርምስናው የሚያስታውሰው አንዳችም ነገር እውነት አይደለም፡፡ ውድ የእውነት እንደሆነ ሁሉ ኮነን የውሸት ነው፡፡ አሁንስ ላይ ኮነን የውሸት ነው ብለን መደምደም እንችላለን? ለምሳሌ ኮነን፣ ወንጀለኛው ውድን መሆን ይፈልጋል? ከመልካም ሰውነትስ ጭራቅ የሆነውን ውድ'ን መምረጥ ይፈልጋልን?"

መምረጥ ቢችል የትኛውን ማንነት መምረጥ ይኖርበታል  ውድን ወይስ ኮነን?
Johannes Moreelse
"Heraclitus"
1630 #Moreelse
ኢትዮጵያ ዉስጥ በአሁን ሣአት ብዙ ንፁሀንን እያስጨረሰ ያለዉ Red Mercury
12.04.202518:21
የስነ ልቦና አማካሪዎች (Psychologist) ደንበኞቻቸውን በሚያማክሩበት ወቅት የሚጠቀሙትን  ዘዴዎ ላካፍላቹ።

አሁን አሁን ሰዎች በተለያዩ ምክንያት ቶሎ የመከፋትና የማዘን ነገር እየበዛ መጥቷል እና የሆነ ሰው ጓደኛህ ወይ ቤተሰብህ ሊሆን ይችላል ማንኛውንም ችግር ይሆናል ወይ ያለበትን ጉዳይ ሲያዋይህ ይህን አድርግ:-

1.አትውቀሳቸው/ አትፍረድባቸው (Don't judge) :- በቻልከው አቅም አትፍረድባቸው። አንዴ ገብተውበታልና እንዴት እንዲ ታደርጋለህ? ምን አይነት ሰው ነህ? አትበሏቸው። ማንም ሰው ችግርን ፈልጎ አይመርጥም ፡ በቃ ምንም አትበላቸው ፀጥ በላቸው ካልሆነ የምትፈርድባቸው ከሆነ ድጋሜ ችግራቸውን ሊያዋዩህ አይመጡም። አለም ሁሉ ይፈርድባቸዋል ታዲያ ቢያንስ አንተ ለየት በልላቸዋ። ለዛ ነው ሰዎች ብዙ ጊዜ ለማንም የማይናገሩት ጉዳይ ለ ንስሀ አባታቸው መንገር የሚቀላቸው ለምን ብትል በጥፋታየው አይወቅሷቸውም።

2. ማዳመጥ (Active Listening) :- አንዳንድ ሰዎች ገና ችግርህን ለመናገር እኔኮ እንደዚ ሆኜ ስትላቸው ወይኔ የኔን ብታይ ምን ልትል ነው? ብለው ችግራቸውን መቀባጠር ይጀምራሉ አንተም የሆድህን ጉድ በሆድህ ይዘ ትመለሳለህ። እና አዳማጭ ሁን በቃ አንዳንዴ ሰዎች የሚያዳምጣቸውን ብቻ የሚፈልጉበት ጊዜ አለ። እንድትመክራቸውም አይፈልጉም የሆነ ጊዜያቶች አሉ ጭንቀቱ ሊያፈነዳቸው ደርሶ ሸክማቸውን ማቅለል ብቻ ነው የሚፈልጉት። አንተም ዝም ብለህ አድምጥ አትምከራቸውም ሰምተህ ዝም እነሱም ቅልል ይላቸዋል። የማዳመጥ ችሎታህ እንዲጨምር ረጃጅም የ YouTube podcast ተመልከት የማዳመጥ ችሎታህ ይጨምርልሀል።

ታዲያ በምታዳምጥበት ጊዜ እየሰማኸው እንደሆነ እንዲያውቅ በመሀል በመሀል ጭንቅላትህን ማነቃነቅ (nodding) እና "አሀ" ማለት በየመሀሉ የዛኔ መስማትህን ሲያውቁ ይበረታታሉ።

3. ሸክማቸውን እንዳንተ ሸክም ማየት (Empathy) :-
ይሄ ደሞ እራስህን በነሱ ባሉበት ቦታ ተክተህ ማሰብ ነው። እኔ በነሱ ቦታ ብሆን ወይ የኔ ቤተሰብ ወይ ፍቅረኛ ቢሆኑስ ምን ማድረግ እችል ነበር? ብለህ ማሰብ ነው። ይሄ ቢያንስ ፈራጅነትህን ይቀንስልሀል።

ውሸታም አለም

እኔ ይሄን ለማወቅ መካነ አዕምሮ (University) ገብቼ ነው የተማርኩት። ለምትኖሩበትም ህይወት ይጠቅማቹሀል እና ተግብሯት።

@ethiosecret
@ourrthought
25.03.202518:21
"እንደወደደ ይሁን እግዚአብሔር ቢሰጠኝ ሁሉን ልገዛ አሣብ ነበረብኝ። እግዚአብሔር ቢነሳኝ አልሞት ኣሳቤ ይህ ነበረ፡፡ ከተወለድሁኝ እስካሁን ወንድ እጄን  ጨብጦት አያውቅም፤ ሰዎቻ ሲሸሹ ተነስቼ ተነስቼ ማራጋት ልማድ ነበረብኝ። ነገር ግን ጨለማ ከለከለኝ፡፡ እንደኔ አያድርጋችሁ።  እንኳንስ የሀበሻ ጠላቴን ኢየሩሳሌም ዘምቼ ቱርኮችን አስለቅቃለሁኝ መስሎኝ ነበር።
ወንድ ያቀፈ ወንድ ተመልሶ አይታቀፍም ። "


አፄ ቴዉድሮስ
Log in to unlock more functionality.