Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
የፍቅር ቴሌግራም ❤️‍🔥™ avatar

የፍቅር ቴሌግራም ❤️‍🔥™

𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 t̑̈ȏ̈ የፍቅር ቴሌግራም™ ❤
💙በዚ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 ላይ
💜ድርሰቶች
💚የፍቅር ግጥሞች
💛ጣፋጭ ታሪኮች
❤️ምክሮች ...
አልፎ አልፎ ቀልዶች ይለቀቁበታል 😂

Since 2016 e.c
❤️ከናተ ሚጠበቀው 𝐉𝐨𝐢𝐧 to request በማረግ ብቻ መከታተል ነው ❤️
👇👇👇
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
LocationЕфіопія
LanguageOther
Channel creation dateFeb 23, 2025
Added to TGlist
Aug 11, 2024
Linked chat

Records

22.04.202511:42
80KSubscribers
24.08.202423:59
200Citation index
09.10.202423:59
1.4KAverage views per post
28.01.202510:16
1.1KAverage views per ad post
04.04.202523:59
252.63%ER
25.08.202423:59
5.79%ERR
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
OCT '24JAN '25APR '25

Popular posts የፍቅር ቴሌግራም ❤️‍🔥™

27.03.202518:30
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
1⃣4⃣

ተመለስኩ ወዴት ልሂድ ቀጥታ ወደ ፅናት መቃብርጋ ሄድኩና አየሽ አደል ያንቺ ግፍ ምን ላይ እንደጣለኝ አየሽ አደል ያንቺ እንባ ምን አይነት ህይወት እንደሚያኖረኝ አንቺ ከመሬት በታች እኔ ከመሬት በላይ ሆንን እንጂኮ ሁለታችንም ሞተናል ብዬ አለቀስኩ ።

ሀና ደጋግማ እየደወለችልኝ ስለነበር ስልኩን አነሳሁላትና የተፈጠረውን ነገርኳት የት ነህ ያለህበት ልምጣ ብላ ለመነችኝ እኔ ግን አይሆንም አልኳት ::
ከመቃብር ቦታው ስመለስ ሁሌም ምሄድበት መጠጥ ቤት ሄድኩና ጥጌን ይዤ ቁጭ አልኩ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰአት ድረስ እየጠጣሁ ቆየሁ ቤዛ ስትደውልልኝ ዛሬ " እንደማልመጣና እናቴጋ እንደማድር ነገርኳት እናቴጋም
ደውዬ ቤዛ ከደወለች እኔጋ ነው እንድትላት ነግሪያት ስልኬን አጠፋሁት ።

ትንሽ ቆይታ ግን ሀና ያለሁበት መጣች፡፡
ቀስ ብላ መጥታ አጠገቤ ተቀመጠችና ጎበዝ እየጠጣህ ነው ትክክለኛ መፍትሄ ነው አለችኝ፡፡
ዝም አልኳት። እሷም ዝም ብላ ተቀመጠች እኔ በላይ በላይ እየጠጣሁ ነው፡፡

ሀና ትኩር ብላ አየችኝና ውይ ይሄንን ያህል ነው
ምትወዳት ባለቤትህን አለች፡፡
ማለት???
በቃ ባትወዳትማ በዚህ ልክ አትናደድም አትበሳጭም ነበር በሚወዱት ሰው መከዳት ነው ሚያመው አየህ ማስታዋል ያልቻልኩው ፍቅር ውስጥህ አለ ማለት ነው አለችኝ።

ከት ብዬ ሳኩና እኔ ቤዛን ሰው ፊት ማማት ፈልጌ አደለም ግን ካወኳት ቀንና ሰአት አንስቶ አንድም ቀን ወድጃት  አፍቅሪያት አላቅም ከመጀመሪያውም እንደማልወዳት እንደማላፈቅራት እያወቀች ነው እናቴን በገንዘብ ደልላ ወጥመድ ውስጥ የከተተችኝ ግን ምን እንደሆነ ታቂያለሽ ሀና በጣም ያናደደኝ ነገር እኔ በሷ ምክንያት ፅናትን መስዋት አድርጌያለሁ ፍቅሬን ትቼ እሷን አግብቻለሁ።

ካገባኋት ቡሀላ ቢያንስ ባልወዳት ባላፈቅራት እንኳን አንድም ቀን በሷ ላይ ማግጬ ሌላ ሴት ተመልክቼ እሷን ለመካድ ለመፍታት ሞክሬ አላቅም ካፌ ክፉ ቃል ወጥቶ አስቀይሚያትም ሆነ ንፅህናሽን አጠብቂም ቤት አታፀጂም ጠረንሽ ተቀይሯል አልተንከባከብሽኝም ብዬ ፊቴን አጥቁሬባት አላቅም።

እኔ ባልም የቤት ሰራተኛም ሆኜላት ነው ማኖራት እእ አንድም ቀን ከቤት ወጥቶ ተሯሩጦ ገንዘብ ማግኘት ምን እንደሆነ አታቅም ግን እሷ ይሄን ሁሉ ወደኋላ ጥላ በኔ ላይ ሌላ ወንድ ደረበች ።

ነገሩን ሳስበው ግብግብ ነው ሚያደርገኝ እናቴ ለገንዘብ ካላት ፍላጎት የተነሳ እኔ እየተረገጥኩ መኖሬ ያበሳጨኛል ሰርቼ አለመመስገኔ ብክንክን ያደርገኛል አልኳት።
ሀና በዝምታ ውስጥ አዳምጣኝ ስትጨርስ በቃ ተነስ ወደቤት ልሸኝህ አለችኝ።

አይ አሌድም አንቺ ወደቤትሽ ሂጂ እኔ እንደማልመጣ ነግሪያቸዋለሁ አልኳት፡፡

ትንሽ ካሰበች ቡሀላ በቃ እዚህ ምትጠጣውን ቤት ይዘን ገብተን ቤት እንጠጣ ስትለኝ ባንዴ በሀሳቧ ተስማማሁ ሳጥን ቢራ ገዝተን በመኪና ጭነን ወደቤቷ ሄድን ቤቷ በመልካም መአዛ ተቀበለችን እንደተለመደው ተውባለች ፏ እንዳለች ናት ውይ ታድለሽ ቀኑን ሙሉ ደክሞሽ ውለሽ እንደዚህ አይነት የተዋበ ቤት ውስጥ መግባትኮ ደስ ሲል አደል አልኳት



ይቀጥላል...



ክፍል
1⃣5⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
30.03.202518:00
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
1⃣7⃣


ማታ ከመቼውም በላይ አምሽቼ ወደቤት ሄድኩኝ ቤዛ መጥታ ስታቅፈኝ ደሜ ፈላ ።
ሰውነቴን ሁላ ሽክክ አለኝ።

ቢሆንም ከአንገት በላይ እየሳኩ ማስመሰሉን ተያያዝኩት ለአንድ ሳምንት ያህል አንድ አልጋ ላይ እየተኛን ግንኙነት ሳናደርግ ሳንተቃቀፍ ቆየን ሳምንቱን ሙሉ ቤዛ ሰላሚዊ ሰው ሆና ነበር እኔ ግን ሰው እንዴት እያስመሰለ
እንደሚኖር እየተለማመድኩ ነበር።

ቀኑ ቅዳሜ ነው ስራ ወጥቼ አመሸሁ እስከማታ ሰርተን ሀኒንም ቤቷ አድርሻት እኔ ወደቤቴ ሄድኩኝ አድካሚ ቀን ስላሳለፍን እረፍት ለማድረግ ጓጉቼ ነው ወደቤት የሄድኩት ከሰራሁት ገንዘብ ቢያንስ 75% የሚሆነውን ወደ ዝግ አካውንቴ አስተላለፍኩትና ወደቤት ገባሁ።

ሰላም ትቻት የወጣሁት ሚስቴ እሳት ጎርሳ እሳት ለብሳ ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ አገኘኋት ገና ከበር ስገባ ምነው እዛው አታድርም ነበር ምን አስመጣህ እንደለመድከውኮ እዛው
ብታድር ጥሩ ነው አለችኝ።

አይቻት ፈገግ ብዬ ወደመኝታ ቤት ገባሁ ተከትላኝ መጣችና አንተ እንዴት ብትንቀኝ ነው ጭራሽ እያወራሁህ ትተኸኝ ምትገባው ድሮም ድሀ ሲጠግብ አይቻልም አትርሳ እንጂ ከtaxi ሹፌርነት አንስቼኮ ሱቅ ውስጥ አለቃ ሆነህ ቁጭ ብለህ እንድትውል ያደረኩህ እኔ ነኝ አለችኝ።

ምንም ቃላት ማውጣትም ሆነ ማባከን ስላልፈለኩ ቤዛ እባክሽ በጣም አድካሚ ቀን ነው ያሳለፍኩት እኔ ከስተመር በዝቶብኝ ነው ያመሸሁት ትንሽ እረፍት እንዳደርግ ፍቀጅልኝ አልኳት።
ከት ብላ ከጣራ በላይ ሳቀችና የደከመህ ምን ሰርተህ ሱቅ ውስጥ ነው ወይስ ያቺ ምናምንቴ ቤቷ ወስዳ ስራ አበዛችብህ አለችኝ።

ስለማንና ስለምን እያወራች እንደሆነ ስላልገባኝ ዝም ብዬ አየኋት ምነው ስለሷ ሳነሳብህ አፈጠጥክ እኔ ቤዛኮ ነኝ የማላቅ ነው እንዴ ሚመስልህ ብዙ ነገር አስታውላለሁ ሀናን እንደምትወዳት የማላቅ ነው እንዴ ሚመስልህ ብላ ተጠቅልላ ተኛች፡፡

ልብሴን ቀያይሬ ከጎኗ ተኛሁ ተኛሁ ማለት ግን ከባድ ነው ቤዛ ካፏ ያወጣችው እያንዳንዷ ቃላት ጭንቅላቴ ውስጥ ያቃጭልብኝ ጀመር።

በተለይ በተለይ ሀናን ትወዳታለህ የምትለዋ ሀሳብ ቅዠት ሆነችብኝ ከራሴጋ ግብ ግብ ጀመርኩ ፈጣሪ በሚያቀው አንድም ቀን ሀናን ከእህትነትና ከገበደኝነት ባለፈ ለሷ ምንም አይነት የፍቅር ስሜት ተሰምቶኝም አስቢያትም አላቅም ቤዛ መቼም ለምዶባት ስለምትቀባጥር እንጂ ሀና ፍቅረኛ አላት አደል እንዴ እኔ ምን ልሁን ብዬ ነው ማፈቅራት በቃ ከራሴጋ ዝግ ስብሰባ ሳደርግ ቆየሁና በስተመጨረሻ እንቅልፍ ጣለኝ፡፡

የስራ ሞራል ደስ የሚል ነገር ነው ጠዋት በሞራል ነው ምትነሱት ማታ መመሸቱ በራሱ ያስጠላል አንዳንዴ እየሰራሁ ባደርኩ ብዬ ሁላ ማስብባቸው ቀናቶች በዙ ለቤዛ በፊት ከምሰጣት ብር ላይ በግማሽ ቀነስኩባት ገበያ በጣም እንደቀዘቀዘና ገዢ እንደጠፋ በተደጋጋሚ ልነግራት ብሞክርም እሷ ግን ጭራሽ ሁለት ሆናችሁ ተዘፍዝፋችሁ ከምትውሉ ሀናን አባራታ ለነገሩ ፍቅርህ ላይ ጨክነህ እንዴት ታባርራታለህ የሚሉ ቃላቶችኝ ጣል ማድረጉን ተያያዘችው፡፡

በሷ ወሬ የተነሳ ሳልፈልግ ማታ ማታ ሀና ቀኑን ሙሉ ያደረገችውን የዘፈነችውን የከፈተችውን የዘፈን አይነት ከከስተመርጋ ከሰዎችጋ ብቻ ከጠዋት ጀምሮ ስታደርግ የዋለችውን በጭንቅላቴ እያሰብኩ ማምሸት ጀመርኩ፡፡

አንዳንዴ ሳላስበው የሆነ የሆነ ቦታ ምታደርጋቸው ድርጊቶችና እብደቷ ትዝ ሲለኝ ብቻዬን ክትክት እያልኩ እስቃለሁ....


ይቀጥላል...



ክፍል
1⃣8⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
31.03.202518:25
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
1⃣8⃣


ብቻ እድሜ ለሚስቴ አብሪያት የዋልኳትን ሀናን ማታም ቤት ገብቼ ስሟን መስማቴና ስለሷ ማሰቤ ግዴታ ሆነ ሳልፈልግ እንዳስባት አደረገችኝ እራሴን እስክታዘበው ድረስ ለሀና ደግ መሆን ጀመርኩ ጓደኝነቷን ላለማጣት ሁሉንም መስዋትነት እስከመክፈል የሚያደርስ ስሜት ውስጤ እንዳለ ተሰማኝ።

ግን ፈፅሞ አላፈቅራትም ለፅናት ይሰማኝ የነበረው የፍቅር ስሜት ለሀና እሩብ እንኳን አይሰማኝም እንዲሰማኝም አልፈልግም አሁን ገንዘብ ማግኘት ላይ ብቻ ነው ማተኮር ያለብኝ ብዬ ለራሴ ነገርኩት የነገርኩትንም ተግባራዊ አደረኩት ።
በትንሽ ጊዘሰ ውስጥ ብዙ ገንዘቦችን save ማድረግ ጀመርኩ፡፡

ከኔ በላይ ግን የሀና ፍላጎት ግርም ይለኝ ነበር ስትሸጥ ያላት ደስታ ለመጠየቅ እንኳን ድንገት የገባውን ሰው ሀሳቡን አስቀይራ ሁለት ሶስት ገዝቶ እንዲወጣ ታደርገዋለች ።

ልክ ሸጣ ዞር ስትል ሱቅ ለመክፈት እሩብ ጉዳይ ቀረህ ትልና ብቻዋን ትስቃለች ።
ከጊዚያቶች ቡሀላ የቤዛ ጭቅጭቅ የተለመደና ልክ ሙዚቃ የመስማት ያህል በንግግሮቿ መዝናናት ጀመርኩ።

ቃላቶችን ሁላ ከመሸመደዴ የተነሳ እሷ ስትናገር ከሷ እኩል በውስጤ ማለት ጀምሪያለሁ ከዚህ ነገር ምላቀቅበት ነገር ስላጓጓኝ ካለምክንያት ምትጠፋው እያንዷንዷ ገንዘብ ታሳስበኝ ጀመር፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ አምስት ወራትን ከሰራሁ ቡሀላ ሱቅ ለመፈለግ መዘጋጀች ጀመርን ቀድመን ከሀናጋ የእያንዳንዱን ቦታ የገበያ ሁኔታ ማጥናት ጀመርን ።

በተቻለ መጠን ቤዛ በቀላሉ ልታቀው ማትችለው ቦታ ነበሮ እየፈለግን የነበረው በተጨማሪም ለከስተመሮቻችን የቦታ ጥቆማ ስንሰጥ የማንቸገርበት አይነት እንዲሆን ተመካከርንና ወሰንን።

ሰፋ ያለ ጊዜ ሰጥተን ካሰብንበት ቡሀላ በጣም ቆንጆ ሱቅ አገኘን ኪራዩ ትንሽ ወደድ ቢልም የገበያ ሁኔታው ግን ይለይ ነበር ከዛ ሱቁን የሶስት ወር ቤት ኪራይ ከፈልንበትና አዳዲስ እቃዎችን አስገባን ከመጀመሪያው በጣም ብዙ ልምዶችን ወሰድንና እዛኛው ላይ በተቻለን መጠን ስታንዳርዱን የጠበቀ ሱቅ አድርገን ከፈትነው ።

ጊዜዬን በሙሉ ስራ ላይ ሳደርግ የሚያስጨንቁኝ ነገሮች በሙሉ ተራ ሆነው ታዩኝ ለካ እስከዛሬ ምጨነቀው በትንሹም በትልቁም ቶሎ ምከፋው ብዙ ትርፍ ሰአት ስላለኝና ትርፍ ሰአቴን ደሞ ተራ ነገሮችን በማሰብ ስለማሳልፍ እንደሆነ ገባኝ።

እዚህኛው ሱቅ እኔ ልውል እዛኛው ሱቅ ደሞ ሀና ልትውል ተስማማን ከስተመር አያያዝ ላይ በጣም ጎበዝ ስለሆነች በቀላሉ ሰዎችን ደንበኛ ማድረግ እንደምትችል ስለገባኝ ሀላፊነቱን በሙሉ ለሷ ሰጠሁ።

ቢዝነስ ካርድ አሳተምንና እዚህኛው ሱቅ የሚመጡትን አሪፍ አሪፍ ከስተመሮች አዲሱ ሱቃችን እንዲመጡ ከመጡም ለነሱ አሪፍ discount እንደምናደርግ ማሳወቁን ተያያዝኩት ።

ከሀናጋ በየሰአቱ ለማለት በሚቻል መልኩ እንደዋወላለን የመጡትን ከስተመሮች እንዴት አይነት አቀባበል እንዳደረገችላቸው ትነግረኛለች እስከ አሰራአንድ ሰአት ከቆየሁ ቡሀላ እሷጋ እሄድና አብረን እናመሻለን ከመቼው ከሰዎችጋ ተግባብታ በዛ ልክ ጎረቤት እንደሆነች ሳያት እገረማለሁ።

ብቻ ነገሮች በጣም አሪፍ መሆን ሲጀምሩ ሀኒ ባሏን እራት መጋበዝ እንደምትፈልግና አራታችንም አብረን እራት እንድንበላ ጠየቀችኝ ደስ ባይለኝም እሺ አልኳትና ለቤዛ ደውዬ እራት እንደምንበላ ነገርኳት።

ማታ ሁለት ሰአት አካባቢ ቤዛን ሄጄ ከቤት ይዣት ወጣሁ ዝንጥ ብላ ለብሳ ሽቶዋን ተቀባብቲታ ነበር እኔ ግን ሳያት መንገድ ላይ የማቀው አንድ ተራ ሰው መሰለችኝ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ቤዛ በጣም ብዙ ጊዜ ቺት እንዳደረገችብኝ ባውቅም ከመከፋት ይልቅ ደስታ ነበር ሲሰማኝ የነበረው እንደመጀመሪያው መናደድ መበሳጨት እንዴት በኔ ላይ ቺት ታደርግብኛለች ብሎ ማዘን ሙሉ በሙሉ አቁሜ ነበር። በተቃራኒው ነገ የተሻለ ቦታ ቆሜ ስታየኝ መልሷ ምን እንደሚሆን እያሰብኩ ነው የቆየሁት

___ መጀመሪያ ሰሞን ምናልባት ቤዛ ፍቅር ይዟት ይሆናልኮ ቺት ምታደርግብኝ እኔ ከልቤ አላፈቅራትም አደል ለምን ከሌላ ወንድጋ መሆን እንዳትችል መንገዱን እዘጋባታለሁ ብዬ ስላሰብኩ እሷን መከታተል ጀምሬ ነበር በቃ ጠዋት ተነስታ ቤት አፅድታ ተጣጥባ ቁርስ አቅርባ በሰላም ከሸኘችኝ ሌላ ወንድ ቤቴ ሊመጣ እንደሆነ ስለማቅ መከታተል ጀመርኩ ግን ቤዛ እኔ ካሰብኳት በላይ ናት ዛሬ የመጣው ወንድ ነገ ደግሞ አይመጣም የተለያዩ ወንዶች ናቸው ቤት የሚመጡት እሱን ሳይ በጣም ገርሞኝ ቆይ ምን ብላ እያወራቻቸው ይሆን ማታ ቤት ገብቼ ስልክ ስትይዝ አላያትም መቼ መቼ እያወራቻቸው ነው ብዬ አስቤ ትዝ ሲለኝ ደሞ ለካ ቤዛ ቀኑን ሙሉ አልጋ ላይ ተኝታ ነው ምትውለው አንዱን አውርታ ስትጨርስ አንዱ ይተካል ለዛ ነው ለካ ጠዋት ቁርስ የበላሁበት ሳህን ከጠረጴዛ ላይ ሳይነሳ ሚጠብቀኝ የሚል ውሳኔ ላይ ደረስኩ።

ብቻ የተቀጣጠርንበት ቦታ ደረስን ሀኒም ከባሏጋ ለባብሳ ወጥታ ቀድመው ደርሰው ጠበቁን። ቤዛ ገና እንደደረሰች ሀናን በግልምጫ አነሳቻት ። ሀኒ ነገሮችን እንዳላወቀ ሆና ቀለል አድርጋ አለፈች ።

እራታችንን እየበላን ሀኒና ባሏ እንዴት እንደተዋወቁ በየተራ ይተርኩልን ጀመር በዛውም ስለፍቅራቸውና ስላሳለፏቸው ጣፋጭ ጊዜዎች ተረኩልን።

ሁለቱም ፊታቸው ላይ የሚታየው የፍቅር ስሜት በጣም ያስቀናል ሀኒ አይን አይኑን ታየዋለች እሱም ቢሆን አይቶ አይጠግባትም፡፡

ቤዛ ሁሉንም ሲያወሩ ከሰማች ቡሀላ በጣም ደስ የሚል የፍቅር ታሪክ አላችሁ ፈጣሪ በመሀላችሁ ከሚገባ ሴጣን ይጠብቃችሁ ብላ እኔን አየችኝ ግራ ቢገባኝም ዝም አልኳት ቀጠል አደረገችና ውይ ሀኒ ካይን ያውጣልሽ እንጂ ታይቶ ማይጠገብ ባል ነው የሰጠሽ በጣም ቆንጆ ነው ለነገሩ አንቺም ቆንጆ ነሽ ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳል አደል ሚባለው አለቻት።

ሀና ፈገግ አለችና አመሰግናለሁ ቤዚዬ ግን ምን መሰለሽ ባሎቻችንንም ይሁን ጓደኞቻችንን ብቻ የቅርብ ሰዎቻችን እጃችን ላይ እያሉኮ ብዙም አናስታውላቸውም ልክ ካጠገባችን ዞር ሲሉ ነው ምን ያሀል ቆንጆ አስተዋይ ወይ ደሞ የዋህ እንደሆኑ የሚገባን በነገራችን ላይ አለቃዬም ወንዳወንድና ቆንጆ ባል ነው አደል አለቻት።

በቅኔ መነጋገሩ ከዚህ በላይ ከቀጠለ የእራቱ መጨረሻ ጥሩ እንደማይመጣ ገባኝ።


ይቀጥላል...



ክፍል
1⃣9⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
28.03.202518:19
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
1⃣5⃣


ታዲያ ምን ስራ አለኝ ጓደኛዬ ቤቴ ናት እሷ አምሮባት ሳይ እኔም ደስ ይለኛል አለችኝና ወንበሯን እያስተካከለች እንድቀመጥ ጋበዘችኝ።

እኔም ግብዣዋን ተቀብዬ አረፍ አልኩና ያቆምኩትንመጠጥ ቀጠልኩኝ እሷ ከአልጋው ላይ ደርባ ያነጠፈችውን ፍራሽ አውርዳ መሬት ላይ አነጣጠፈች አንሶላዋንም ካስተካከለች ቡሀላ ፍራሹ ላይ አረፍ እንድል ጋበዘችኝና ፈልሰስ ብዬ ተቀመጥኩ።

እኔ ደሞ የሴት ወጉ አደለ ጉድ ጉድ ልበል አለችና ምግብ ማዘገጃጀች ጀመረች ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፍታ እየሰማች ነበር: እኔ በቤዛ መከዳቴ በጣም እያንገበገበኝ ነበር ።

ቢያንስ ታማኝ መሆን እንዴት ያቅታታል እውነት ለኔ ይሄ ነው ሚገባው እያልኩ መጠጣቱን ተያያዝኩት ሀኒ ከመቼው ሰርታ እንደጨረሰች ባላቅም እራት ደርሷል ብላ እጄን አስታጠበችኝ ምግቡ ገና በሽታው ብቻ ያጠግባል ግን እኔ ከሳህኑ አንስቼ አፌ ላይ የማድረስ አቅሙ ሁላ አልነበረኝም፡፡ ሁኔታዬን ቀድማ ተረድታ እያጎረሰችኝ እራታችንን በልተን
ጨረስን።

አነሳሳችና አጠጣባ እቃዋን ቦታ ቦታው መለሰች አንዴ አይንህ ጨፍን ልብሴን ልቀይር ነው አለችኝ።
ዝም ብዬ ፍራሹ ላይ ድፍት አልኩኝ ልብሷን ቀያይራ ስትጨርስ ካጠገቤ ቁጭ አለችና እስከ ስንት ሰአት የመጠጣት እቅድ አለህ አለችኝ
አላቅም ንዴቴ በረድ እስኪል መጠጣት ነው ምፈልገው አልኳት።

እሺ በቃ ጠጣ እኔ ትንሽ ስለደከመኝ ልተኛ ብላኝ ከጎኔ ብርድ ልብሷን ለብሳ ዘፈኖቿን እየቀያየረች ተቀመጠች ።

የትዝታ ዘፈን ግን ለምንድነው ምትወጂው ብዬ ጠየኳት። እኔጃ ብቻ ጩኸት የሌለበት ረጋ ያለ ዘፈን መስማት ደስ ጠዋት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰችኝ።

ቡና ተቀራርቧል ቁርሱ በአይነት ተዘጋጅቷል የእጣኑ ሽታ ቤቱን ይዞታል ጭሱ እየተቡለቀለቀ ሳየው ፈገግ አልኩ አየኋትና ከመቼው ተነስተሽ ነው እንደዚህ ያሰማመርሽው አልኳት 1 1 ሰአት ነው የተነሳሁት እራስ ምታትህ እንዲለቅህ ብዬ ነው ቡና ያፈላሁልህ አሁን ተነስተህ ታጠብና ቁርሳችንን እንብላ ሱቅ እንዳይረፍድብን አለችኝ።
እዛው ከአልጋ ላይ ሳልወርድ አስታጠበችኝና ቁርሳችንን በላን እኔ ምልሽ ሀኒ አሁን ከፍቅረኛሽጋ ስትጋቡ ሁሌ እንደዚህ እያደረግሽ ነው ምትቀሰቅሽው አልኳት።

አረ አንተ ያምሀል እንዴ ይሄ ምንድነው እሱ ደስ ሚለው ከሆነ ማታ እግሩን ሳይቀር አጥቤ ነው ማስተኛው ቁርስ መስራትኮ የሚስትነት ግዴታዬ ነው አለችኝ።

ቁርሳችንን በላን ቡናችንን ጠጣንና ስንጨርስ ከፈለክ አሁን ስለማታው ማውራት እንችላለን ቀንህን ላበላሸው ፈልጌ ሳይሆን ማውራቱ ቀለል ስለሚልህ ነው አለችኝ፡፡

ምኑ ይወራል ብለሽ ነው ???
ከዚህ በላይ ሚወራ ነገር የለም ማታ ስትጠጣ ዝም ያልኩህ በውስጥህ ይዘህ መብሰልሰል ስለሌብህ ነው ተናደህ ነበር ንዴትህን የሚያበርድልህ ነገር መጠጥ መስሎ ስለተሰማህ እንድትጠጣ ተውኩህ ዛሬ ደሞ አዲስ ቀን ነው ማታም ተናደህ ተመልሰህ ወደመጠጥ ቤት መሄድ የለብህም እንደጓደኛህ ካየኸኝ ሚሰማህን አውራኝ እኔም ማድረግ ያለብህን ላማክርህ አለችኝ።

በቃ ሚሰማኝ ስሜት በጣም ብዙ ነው ከሰዎች ሁሉ ያነስኩ አይነት ስሜት ይሰማኛል ልክ ቤዛ ገዝታ እንዳስቀመጠችው እቃ ስትቆጥረኝ ውስጤ ባዶ ይሆናል ይሰማኛል ይከፋኛል እንደሰው የተባረከ ትዳር አፍቅሮ መፈቀር ልጅ መውለድ ብቻ ምናለፋሽ ኖርማል ህይወት መኖር ናፍቆኛል ባይገርምሽ



ይቀጥላል...



ክፍል
1⃣6⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
07.04.202518:45
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
2⃣2⃣


ሀኒጋ ጠዋት ጠዋት ቁርስ መብላቱን በጣም ወድጄዋለሁ ባንድ በኩል ቆንጆ ቁርስ በልቶ ተሳስቆ ወደስራ መሄድ የራሱ የሆነ ሰላም አለው በሌላ በኩል ደሞ ጠዋት ጠዋት መብላቴ ካልቀረ በ አስቤዛ ለማገዝ ለኔ ከባድ አይሆንም እንደውም በቀጥታ ብሩን ከመስጠት ብዙ ነገሮችን ገዝቼ ባሟላላት ይሻላል ብዬ አሰብኩ።

ለ15 ቀን ያህል ከቆየሁ ቡሀላ ማታ ቤት ስላልተኛሁ ቤትሽ ሄጄ ልተኛ ብያት ቁልፉን ተቀብያት ሙሉ አስቤዛ የማደርግበት ቦታ ሄድኩ ከትንሽ እስከትልቅ የሚባለውን አስቤዛ ገዛዛሁ ክኖር ሳይቀር አረሳሁም ነበር ሁሉንም በመኪናዬ ጭኜ ወደቤት ሄድኩና ቦታ ቦታ አስያዝኩላት አትክልት መደርደሪዋን በሙሉ ሞላሁት ማታ ስትገባ ምን ያህል ደስ ሊላት እንደሚችል እያሰብኩ ብቻዬን ፈገግ እያልኩ ነበር።

ስጨርስ ወደሱቅ ተመልሼ አብረን አመሸን ማታም ቤት አድርሻት እየተመለስኩ ብዙም ሳትቆይ ደወለችልኝ።

አቤት !አንተ ምንድነው ይሄ ሁሉ እኔኮ ባልየው መስሎኝ ደውዬ ምን ታይቶህ ነው ይሄ ሁሉ አስቤዛ ስለው የምን አስቤዛ ብሎ አደናገረኝ ከስንት ጭቅጭቅ ቡሀላ ነው እሱ እንዳልሆነ ያወኩት ቆይ ምን አስበህ ነው አለችኝ፡እኔማ የበላሁትን ልክፈል ብዬ ነው አልኳት፡፡

አረ አንተ አይደረግም ለማንኛውም ግን አመሰግናለሁ ከምር ሳየው ብቻዬን ፈገግ እያልኩ ነበር ግን ይሄን ሁሉ ወጪ ማውጣት አልነበረብህም አሁንኮ ብር save ምታደርግበት ሰአት ነው ለማንኛውም እየነዳህ ስለሆነ ብዙ አላድርቅህ ከምር አልጠበኩም እሺ በጣም ነው ማመሰግነው ደና ደር በቃ አለችኝና ስልኩ ተዘጋ፡፡

ቤዛና እሷን ማወዳደር ጀመርኩ ቤዛ ሚሊየን ብር ለሷ ስል ባጠፋ አጠፋህ አትልም ከዛ ውስጥ የጎደለው አይታ ነው ምትነታረከኝ ሀና ግን አሁን ይሄን ብር ስላጠፋሁ ስታመሰግነኝ ገረመኝ።

ቤት ገብቼ ልብሴን ቀያይሬ መኝታ ቤት ገባሁና ቤዛን ጠየኳት ሱቁን ከምን አደረሽው ያለብኝን ብር ስሰጥሽ አዳዲስ እቃዎችን ታስገቢያለሽ ያሉት ተሽጠው አለቁ እንዴ አልኳት፡፡

አላቅም ሰራተኛዋ ምንም ያለችኝ ነገር የለም እኔ እዛ መሄድ ስላስጠላኝ ሄጄ አላየሁትም ደሞስ ቢከስር ባይከስር ምናገባህ ብላ በነገር ጀመረችኝ። ስልችት ስላለኝ ፎጣውን ይዤ ወደሳሎን ወጥቼ ሶፋ ላይ ተኛሁ፡፡ ስልኬን እዛው እንዳስቀመጥኩት ስለነበር አንስቼ መነካካት ጀመርኩ ከሀና sms እንደተላከልኝ አየሁ፡፡

አንተ ባለሙያ መሆንህን አሁን አደል እንዴ ያረጋገጥኩት ቆይ አሁን ጨው,ክኖር, ሻይቅጠል እንዴት ትዝ አለህ እኔ እንኳንኮ ካላለቀብኝ ትዝ አይለኝም ከምር አድንቄሀለሁ ቤዛ አላወቅችበትም እንጂ አፍሶ ነው የሰጣት አለችኝ። ሳነበው ፈገግ አልኩ ያው ምን ይደረግ ብለሽ ነው የናቴ ልጅ አደለሁ አልኳት።

ቢሆንም ከምር ጎበዝ ነህ ሳላደንቅህ አላልፍም ወደፊት ቤዛ ሁሉም ነገር ሲገባት አሪፍ ህይወት እንደምትኖሩ አልጠራጠርም አለችኝ።
ዝም አልኳት የቤዛ ነገር ምን ያህል ተስፋ እንዳስቆረጠኝ የገባኝ ያኔ ነበር።

ጠዋት ሀኒጋ ሄጄ ሱቅ ካደረስኳት ቡሀላ እኔ ወደበፊቱ ሱቃችን ሄድኩ የሆነች ልጅ ውስጥ ቁጭ ብላለች ማስቲካውን አፏ ውስጥ ታንገላታዋለች አስተኛኘኳ ያስፈራል መጀመሪያ ስገባ ቀጣይ እኔንም እንዳትበላኝ ፈርቼ ነበር ።

ጠዋት ሆኒጋ ሄጄ ሱቅ ካደረስኳት ቡሀላ እኔ ወደበፊቱ ሱቃችን ሄድኩ የሆነች ልጅ ውስጥ ቁጭ ብላለች ማስቲካውን አፏ ውስጥ ታንገላታዋለች አስተኛኘኳ ያስፈራል መጀመሪያ ስገባ ቀጣይ እኔንም እንዳትበላኝ ፈርቼ ነበር ።

ገብቼ እቃዎችን አየኋቸው ሁሉም እንደነበሩ ናቸው ብል ማጋነን አይሆንብኝም እንደከስተመር ሆኚ ዞር ዞር ብዬ ካየሁ ቡሀላ ይሄኛው ስንት ነው ብዬ ጠየኳት የቱ አለችኝ ከስልኳ ላይ አይኗን ቀና ሳታደርግ ይኸኛው ነው አናግሪኝ እንጂ አልኳት ቆጣ ብዬ ቀና ብላ አየችኝና 5ዐዐ ብር ሚሸጠውን ልብስ 12ዐዐ ብር አለችኝ፡፡
አረ ተይ እንደዛ አያወጣም ቀንሽልኝ አልኳት መጨረሻው 1ዐዐዐ ብር ከዛ ምንም የለውም አለችኝ፡፡

ይኼኮ ሌላ ቦታ 5ዐዐ ብር ነው ሚሸጠው ምን ሆነሽ ነው አንድሺ ምትይው አልኳት ሌላ ቦታ 5ዐዐ ከሆነ ሌላ ቦታ ሄደህ መግዛት ነዋ ታዲያ ብላኝ ሄዳ ቁጭ አለች በጣም ስላናደደችኝ በጥፊ ልላት ነበር ግን እራሴን ተቆጣጥሬ ዝም ብዬ ወደውጭ ወጣሁና ቤዛጋ ደወልኩ ቤት ተኝታለች በአስቸኳይ ሱቅ እንድትመጣ ነገርኳት 1 ሰአት ጠብቀኝ እመጣለሁ አለችኝ።

በፊት የማቀው አንድ ካፌ ቁጭ አልኩና ሀኒጋ ደውዬ የተፈጠረውንና የተናደድኩበትን ነገርኳት እሷም አንዳንድ ሰውኮ እንደዚህ ነው አንተ ግን ተረጋጋ ብላ አረጋጋችኝ፡፡

ቤዛ እንደደረሰች ስትነግረኝ ከካፌው ወጣሁና ይዣት ወደሱቅ ገባሁ ልጅቷ ስታያት በድንጋጤ ደርቃ ቀረች እኔ ወደሷ ተጠጋሁና ታምራት እባላለሁ የዚህ ሱቅ ባለቤትና የቤዛ ባል ነኝ አልኳት ልጅቷ ተርበተበተች እኔ ድጋሜ ወደልብሱ ጠጋ አልኩና ይሄ ልብስ ስንት ነው አልኳት 500 አለችኝ እና ለምን ከአንድ ሺ ብር አይቀንስም አልሽኝ ብዬ ጠየኳት። ዝም አለች ቤዛ የዛኔ ቶግ አለችና በጥፊ አጋጨቻት፡፡ ጎበዝ ቤዛ የልቤን ነው ያደረሽልኝ እያልኩ በውስጤ....



ይቀጥላል...



ክፍል
2⃣3⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
29.03.202518:03
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
1⃣6⃣


ይሄን ሱቅ መጀመሪያ ስንከፍተው ቤዛ ገንዘበን ሰጠችኝ ግን ምን ላይ ደረስክ እንዴት ሆነልህ የከፈትከው ሱቅ ምን አይነት ነው ሰዎች እየገዙህ ነው ወይስ አይገዙህም ብላ እንኳን አልጠየቀችኝም ሱቅ ሁላ የት አካባቢ እንደከፈትኩ ያወቀችው ቆይታ ነው በየቀኑ ዛሬ ስንት ሰራህ ይሄን ያህል ብራ አምጣ ከማለት ውጭ አንድም ቀን በርታ ወደፊት ይስፋፋል ብላኝ አታቅም ግን እኔ ሳይሰለቸኝ እየሰራሁ ብር ሴቭ እያደረኩ አንቺ እስክትመጪ የነበረው ደረጃ ላይ አደረስኩት።

ግን ሁሌም ሁሉም ነገር የሷ እንደሆነ ነው ምታወራው እኔ ደሞ ለፍቶ መና ሲሆንብኝ ግዴለም እያልኩ ዝም እላለሁ ግን ጭራሽ በራሴ አልጋ ላይ ከሌላ ወንድጋ ከባድ ነው አልኳት፡፡

እየውልህ ተረጋግተህ ስማኝ አንዳንዴ ሰዎች ትክክለኛ የኛ ጥቅምና ለኛ ያላቸው ፍቅር የሚገባቸው ካጠገባቸው ዞር ስንልና ከበፊቱ የበለጠ አምሮብን ጠንክረን ሲያዩን ነው፡፡

ስለዚህ በቃ ትናት ቤዛን ከሌላ ወንድጋ እንዳላየሀት ቁጥረው ቺት አላረገችብኝም ብለህ አስብ እራስህ ላይ ስራ ከዛሬ ጀምሮ በደንብ ሰአታችንን ስራ ላይ እናሳልፍ የገባ ከስተመር ሳይገዛ እንዳይወጣ እንታገል ከዛ ከሷ ለሱቅ መክፈቻ የተበደርካትን ገንዘብ መልስላት እሷ የማታቀው በደንብ ገበያ ያለበት ቦታ ሂድና በራስህ ገንዘብ በራስህ ተነሳሽነት የራስህን አዲስ ሱቅ ክፈት የዛኔ በራስ መተማመንህ ይመጣል እስከዛ ግን ምንም ነገር ቤዛ ላይ እንዳትቀየርባት አለችኝ
ሀሳቧ በደንብ ነበር የተመቸኝ በአዲስ ሞራል በአዲስ የስራ ፍላጎት ከቤት ተያይዘን ወጣን በለበስኩት ልብስ አድሬ እንደዛው ስራ ቦታ ስሄድ ስለደበረኝ ከተሰቀሉት ውስጥ አንዱን ሸሚዝ አንስቼ ለበስኩት ።

ገና በስርአት እቃ አወጣጥተን ሳንጨርስ ቤዛና እናቴ እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው ሱቅ መጡ ሀኒ ስታያቸው ወደኔ ዞረችና ጠቀሰችኝ እኔም ገና ሳያቸው ምንም እንዳልተፈጠረ ውይ እማዬ ቤዚዬ ምነው በሰላም ነው በጠዋት የመጣችሁት አልኳቸው ሁለቱም ንዴታቸው ፊታቸው ላይ እየታየ የታባህ ነው ያደርከው እ ለቤዛ እናቴጋ ነው ማድረው ብለህ ዋሸህ እ ይሄ ምን የሚሉት ቅሌት ነው የት ስትንዘላዘል አድረህ ነው አለችኝ እናቴ ለመምታት እየቃጣት።

ነገሩን ለማብረድ ፈገግ እያልኩ አይ እማ ቤዚን የመሰለ ሚስት ቤት አስቀምጬ ሌላጋ ልንዘላዘል ምሄደው ምን አጥቼ ነው ብዬ ቤዛን ወደኔ ሳብ አድርጌ አቀፍኳት ባንዴ የጠቆረው ፊታቸው ወደደስታ ተቀየረ ዝም ብዬ የተሰቀሉትን ልብሶች እያሳየሁ እነዚህንኮ ላመጣ ሄጄ ማታ መሽቶብኝ ነው ይቅርታ አስደነገጥኳችሁ አይደል በቃ ኑ እንደካሳ እንዲሆነኝ ቁርስ ልጋብዛችሁ ብዬ ይዣቸው ወጣሁ።

ምሳ ሰአት ላይ ሀኒ ባሏ መጥቶ ይዟት ወጣ ።
እኔ ግን ሀሳቤ ሁላ ገንዘብና ገንዘብ ማግኘት ላይ ብቻ ስለነበር ምሳ ሰአቱንም ሳልዘጋ እዛው ቁጭ አልኩ።

ወደሱቄ የመጣው ሰው ሁሉ
በክብር እያስተናገድኩ መሸኘቱን ተያያዝኩት,,,



ይቀጥላል...



ክፍል
1⃣7⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
30.03.202517:07
ቤተሰብ አንዴት አመሻችሁ    ሀና  ክፍል 17 ሊለቀቅ ነው ዝግጁ ናችሁ ?
29.03.202516:55
ቤተሰብ አንዴት አመሻችሁ   ሀና  ክፍል 16 ሊለቀቅ ነው ላይክ እያደረጋችሁ እንጅ ወገን
04.04.202518:10
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
2⃣0⃣


ሀኒ ግን ሁሌ እንዳስገረምሽኝ ነው በጣም የበሰልሽ ልጅ ነሽ አልኳት።

ከልቧ እየተሽኮረመመች አይ እንግዲ አንተ ደሞ አታሳፍረኛ ሆ ብላ ሳቋን ለቀቀችው ።
ከሰአት አካባቢ ብዙ ከስተመር ስለነበር አብረን እዛው አመሸን።

ማታ ላይ ወደቤት ከገባሁ ቡሀላ ብዙ ነገሮችን ማሰብ ጀመርኩ ቤዛን በምን መልኩ ሱቁን ስራ አቁሚያለሁ እንደምላት ግራ ገባኝ ።

ሌላ ስራ ጀምሪያለሁ ብላት መቼስ ልታብድ ነው
ምትደርሰው በቃ እንዴት ብዬ አሮጌን ሱቅ ለሷ ትቼ እንደምሄድ ሲጨንቀኝ ተነስቼ ወጣሁና ለናጋ ደወልኩ ጠዋት አይደርስም እንዴ ባለትዳር ሴትጋ በዚህ በምሽት ይደወላል እንዴ ብላ ከቀለደችብኝ ቡሀላ ሲነጋ በአካል በደንብ ብናወራ እንደሚሻል ነገረችኝ።
ጠዋት ወደሱቅ እንደሄድኩ ሀና ቀድማ ጠብቃኝ ስለነበር ማውራት ጀመርን ።

ስለዛኛው ሱቅህ ምንም እንዳታወራ እዚህ ሱቅ
ያሉትን እቃዎች እንዳለ ዋጋቸውን እንስራና ምን ያህል እንደሚያወጡ እንደምር ከዛን ቡሀላ ቤዛ ለዚህ ሱቅ ምን ያህል እንዳበደረችህ ስለምታቅ ከእቃው ግምት ላይ ጥሬ ገንዘቅ ጨምረህ ስጣት ከዛ እሷ ትሰራበታለች በዛውም መዋያ ይሆናታላ ከሰው ለመግባባት ለመቀራረብ ይረዳታል አለችኝ፡፡

ሀሳቧን ተቀብዬ እሷን ወደሱቅ ሸኘሁና እኔ ወደቤት ሄድኩ ቤዛ ከአልጋ ላይ ሳትወርድ ስልኳ ላይ ተተክላ አገኘኋት :ምንሄድበት እንዳለ ነግሪያት ለባብሳ ወጣችና ወደሱቅ ተመለስን ።

ሱቅ ውስጥ ቁጭ ካደረኳት ቡሀላ እንገዲህ ከዛሬ ጀምሮ ይሄ ሱቅ ያንቺ ነው እኔ ስራ ለቅቂያለሁ ሀናንም ቢሆን አባሪሪያታለሁ አሁን ልብሶችን ቆጥረን ከነዋጋቸው ርክክብ እናደርግና ለመነሻ የሰጠሽኝን በሙሉ እመልሳለሁ ማለት ነው አልኳት።

አይኗ ሊወጣ እስኪመስል አፈጠጠችና ምን ማለት ነው አንተ ምን ልትሰራ ነው ይሄንን ምትለቀው ወይስ አንተ በተራህ ቤት ልትውል እኔ እየሰራሁ ላበላህ ፈልገህ ነው አለችኝ፡፡

ተረጋግቼ አይ ቤዚዬ እንደሱ አደለም እኔ ለአንድ ድርጅት ሹፌር ሆኜ ለመቀጠር ስላሰብኩ ነው ደሞዜን በጣም ቆንጆ ነው የዚህ የሱቁን አንቺ ትሰሪያለሽ እኔ ደሞ ወጥቼ እሰራለሁ አለቀ አልኳት።

ከምንም በላይ ምን እንደሚቆጨኝ ታቃለህ ይሄንን ሁሉ ውሳኔ ስትወስን እኔን አለማማከርህ ያማል ለነገሩ ምን እከክህን አራግፌልህ ሰው አደረኩህና በሁለት እግርህ መቆም ቻልክ ለማንኛውም ልብሶቹን እራሴ አስገምቼ አሳውቅሀለሁ ሂሳቡንም እነግርሀለሁ አሁን ከፊቴ ውልቅ በል አለችኝ በእጁ ወደበሩ እየጠቆመች



ይቀጥላል...



ክፍል
2⃣1⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
27.03.202517:43
እንዴት ከረማችሁ ቤተሰብ ለሁለት ሳምንታት  ተቋርጦ የነበረው ተከታታይ ታሪክ ከዛሬ ጀምሮ ይለቀቃል ክፍል 14 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ? እስኪ መኖራችሁን በLike አሳውቁን
31.03.202517:58
ቤተሰብ አንዴት አመሻችሁ    ሀና  ክፍል 18 ሊለቀቅ ነው ዝግጁ ናችሁ ?
Deleted05.04.202504:12
🌹በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ💋❓❓

🌹በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ💋❓❓

❤️ስለፍቅር ❤️ጥልቅ እውቀት እንዲኖርሽ እና እንዲኖርክ ከስር ያለውን link ብቻ ተጫኑ👇

https://t.me/addlist/e3BXRkE7LZYyMzJk
05.04.202518:02
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
2⃣1⃣


እንኳን ውጣ ብለሽኝ እንዲሁም ሂድ ሂድ ይለኛል እያልኩ መኪናዬን አስነስቼ ወጣሁና ሀናጋ ሄድኩኝና አብሪያት አመሸሁ። ማታ ቤት እንደገባሁ ቤዛን ውሎ እንዴት እንደነበር ጠየኳት፡፡

ገልመጥ አድርጋ አየችኝና ምናገባህ ምነው እዛ ሱቅ የዋልኩ መስሎህ ነው እኔ ቤዛ ነኝ እንዲ ከማንም ኩታራጋ በዚህ ዋጋ ግዛኝ አትግዛኝ እያልኩ ስለፋደድ ምውለው ዘግቼው ነው የመጣሁት አለችኝ።

ለምን ብትሰሪበት አይሻልም አንድ ምታግዝሽን ልጅ ቀጥረሽኮ ማሰራት ትችያለሽ ያን ያህል ከባድ አደለምኮ አልኳት። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አቃለሁ አይመለከትህም ትተኸው ሄድክ አደል ብላኝ ፊቷን አዙራ ተኛች።

እኔም ከጎኗ ጋደም አልኩ ግን ጭንቅላቴ እረፍት
አልሰጥ አለኝ ድብልቅልቅ ያለ ሀሳብ ውስጥ ገባሁ ቤዛን እየበደልኳት ያለሁ ያህል ተሰማኝ በላይዋ ላይ ድራማ እንደሰራሁባት ነገር በቃ የሆነ ፀፀት ተሰማኝ መልሼ ደሞ ለራሴ አልጋህ ላይ ምትቀያይራቸዎን ወንዶች አስብ እንጂ እስቲ ቤዛ ሞኑጋ ነው ጥሩ የሆነችልህ እሷኮ የፅናት ገዳይ ከመሆኗም በላይ እንደሰራተኛ እየተጫወተችብህ ነው የኖርከው አንድ ቀን እንደባል አክብራህ አታቅም ብዬ ነከርኩት።

በሌላ በኩል ደሞ የሀኒ ነገር ያሳስበኛል አሁን እየሰራችበት ያለው ደሞዝ ከሷ ልፋት አንፃር በጣም ትንሽ ነው የተሻለ ነገር ስታገኝ ትታኝ ብትሄድስ ይቺን የመሰለች ጎበዝ ልጅ አጥቼ የስራ መንፈሴ ቢጠፋስ ብዬ አስብኩ።

በጠዋት ሱቅ ሄጄ እኔ ከፍቼ ጠበኳት እንደመጣች ሞቅ ያለ ሰላምታ አቀረብኩላትና ሁሉንም ነገር ነገርኳት ስለቤዛ ማታ የተሰማኝን ስነግራት አሁን እራስህን መቀየሩ ላይ በደንብ ትኩረት አድርግ እሷ ሳታቅ በኢኮኖሚ በደንብ ከተሻሻልክ ወደፊት በሀብት እኩል ከሆናችሁ እሷም አክብራህ አብራችሁ ትሆኑ ይሆናል እስከዛ ግን ቆራጥ መሆን አለብህ አንተ ሰራህ እንጂ ምን አደረክ ከሷ ውጭ ሌላ ሴትጋ አልሄድክ አልሰረክ አላመነዘርክ የሚፀፅትህን ምንም ነገር አላደረክም ብላ ልቤን አረጋጋችኝ።

በመቀጠል ደሞ ስለደሞዝ ጭማሬ እያሰብኩ እንደሆነና ከደሞዝም በተጨማሪ እያንዳንዳቸው ልብሶች ላይ የራሷን ትርፍ በደንብ መያዝ እንደምትችል ነገርኳት።

እውነት ለመናገር የደሞዝ ጭማሬውን ነገር እኔም እያሰብኩት ነበር ቤት ኪራይ የወር ቀለብ አሁን ደሞ ትራንስፖርት ስለሚኖርብኝ ትንሽ የገንዘብ ጉዳይ አስቸጋሪ እየሆነብኝ ነው ግን በራሴ ሰአት እጠይቅሀለሁ አሁን ገና እንደ አዲስ ምንነሳበት ሰአት ነው በደንብ ሱቁን አደራጅተን ከዛ እናወራለን።

አሁን አንተ ከምትይዘው ትርፍ ላይ እኔም ሌላ ትርፍ ስጨምር ዋጋችን ውድ ስለሚሆንባቸው ሰዎች አይመጡም ታቃለህ ደሞ ገበያ ላይ የሆነን እቃ 1ዐዐ ብር ከምትለውና 99 ብር ከምትለው ሁሉም ሰው 99 ብሯን ነው ሚያየው በትንሽዬ ለውጥ የሰዎችን ትኩረት ማግኘት ትችላለህ ቆይ ትንሽ እንቆይና አሳውቅሀለሁ አሁን አትጨነቅ አለችኝ።

ስለሁሉም ነገር በደንብ ካመሰገንኳት ቡሀላ በቃ ቢያንስ ደሞዝ እስኪጨመርልሽ ድረስ እኔ ጠዋት እየመጣሁ ከቤት ልውሰድሽ ማታ ደሞ ቤትሽ ላድርስሽ ለኔ አይከብደኝም ምክንያቱም ያንቺን ቤት አልፌ ነው ወደኔ ቤት ምገባው አልኳት።
ትንሽ አሰበችና እሺ በቃ ካልተቸገርክ እንደሱ እናድርግ አለችኝ።

በተስማማነው መሰረት በሚቀጥለው ቀን በጠዋት ተነስቼ ለባብሼ ሀኒ ቤት ሄድኩ ስደርስ ደውዬላት እንድትወጣ ነገርኳት እንግዳ ከበር አይመለስም ና ግባ ስትለኝ አይኔን ሳላሽ ተከተልኳት ቡና አፈላልታ ቤቷን አሰማምራ ቁርስ ሰራርታ ነበር ሳያት ግርም ብሎኝ አይ ሀኒ ሌሊቱን አተኝም እንዲ እኔ ስራ ሰርተሽ ፀጉርሽን ልብስሽን ጨራርሰሽ የጠበቀሽኝ አልኳት፡፡

ጠቀስ አደረገችኝና ሴት ልጅ እንደዚህ ቀልጠፍ ስትል ነው ሚያምርባት እንቅልፍ ብር አይሆን ምን ያደርጋል አለችኝና ቁርሳችንን በላን ቡናችንን ጠጣን ሳይረፍድብን ወደስራችን ሄድን በጠዋቱ በደስታ የተጀመረ ቀን ያመረና የተዋበ ሆኖ ነው ሚያልቀው ፈገግ እንዳልኩ ነበር ቀኑ ያለቀው፡፡

በሚቀጥለው ቀንም በተለመደው ሰአት ሀኒጋ ስሄድ ቁርስኮ እየጠበኩህ ነው ግባ እንጂ ብላኝ ወደውስጥ ገባሁ ስገባ ግን በቡና ፈንታ ሻይ ጥዳ ነበር ምነው ዛሬ ደሞ ሻይ ነው ቡና የለም እንዴ ከልኳት በቀልድ አዋዝቼ።

አረ ታሜ እኔኮ ቡና ላይ ብዙም አደለሁም ግን አንተ ምትፈልግ ከሆነ ሁሌ ጠዋት ጠዋት አፈላልሀለሁ አለችኝ።

አረ በፍፁም እኔኮ ቡና ያን ያህል አልወድም ሲገኝ እጠጣለሁ እንጂ ግን ታቂያለሽ ቤት ውስጥ ቡና ቅርብርብ ብሎ ሳይ በጣም ደስ ይለኛል አልኳት።

ያው እንግዲ ሰፊ ቤት ቢኖረኝ ሁሌ ሲኒና ረከቦቱ
እንደተቀራረበ እተወው ነበር ግን ቤቴ እንደምታያት ናት ወደፊት ሰፊ ቤት ሲኖረኝ አቀራርቤ እተወዋለሁ አሁን ቁርሳችንን በልተን ወደስራችን እንውጣ አለችኝ።



ይቀጥላል...



ክፍል
2⃣2⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
02.04.202518:17
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
1⃣9⃣


እእ በቃ እየመሸ ስለሆነ ወደቤት እንሂድ አልኳቸው። ቤዛ ቆጣ ብላ ገና መቼ ትንሽ ፈታ እንበል እንጂ በዚህ ሰአት ቤት ገብቼ ካንተጋ መነታረክ አልፈልግም አለችኝ።

ሀና ትኩር ብላ አየቻትና እየሳቀች ተይ እንጂ ቤዚ አንዳንዴኮ private የሆኑ ብዙ ጉዳዮች አሉ አሁን እኛ እንደምትጨቃጨቁ አናቅም እሱ ገመናችሁን ደሞ ሰው ፊት ማውጣት የለብሽ ትዳር በራሱ ትልቅ ሚስጥር ነው ሚስጥሩ ግን የባልና የሚስቲቱ ነው አለቻት።

ቤዛ ብድግ አለችና ውይ አንቺም ከሱ የባሽ ነዝናዛ ነገር ነሽ ና በቃ እንሂድ መቼስ ሰራተኞቹ እናንተ ናችሁ ከፍላችሁ ኑ ብላ ወጣች ሂሳባችንን ከፋፍለን ተከትለናት ወጣን፡፡

ስለመሸ በኔ መኪና ላድርሳችሁ ብዬ ወደመኪናው አስገባኋቸው ቤዛ ቀድማ ከኋላ ገብታ ስለነበር ሀኒ ጋቢና ገባች ባሏ ደሞ ከቤዛጋ ከኋላ ተቀመጠ።
ዝምተኛ ነገር ነው ብዙ ጊዜ ካልተጠየቀ አያወራም ወሬዎቹ ደርዝ አላቸው የተዝረከረከ አይነት አደለም ንግግሩ።

ሀኒ ስልኳን አገናኝታ ዘፈን ከፈተችና ድምፁን ጨመረችበት ማመን አቃተኝ የህልሜን ንግስት
የኔ አረኩና አዲስ ቀን መጣ ህይወት ሊታደስ ባንቺ እንደገና> እያለ ያቀነቅናል ሀኒም ከዘፈኑ እኩል ተመስጣ እየዘፈነች ነበር።

ቤዛ ነገሮች ምንም አላስደሰቷትም እኔ ምልሽ ሀና ይሄንን ድፍረትና ነፃነት ግን ከየት ከየት ነው ያመጣሽው አለቻት
ሀና : ማለት ?
ቤዛ: አይ በጣም ብዙ ጊዜ አየሁሽ አጉል ደፋር
ካልሆንኩና ነፃነት ካላገኘሁ ትያለሽ፡፡
ሀና: ከልጅነቴ ጀምሮ የመጣ ነው ደሞ ይሄ ድፍረት ሳይሆን እራስን መሆን ነው እሺ ቤዚዬ አለቻት። እነ ሀናን ቤት አድርሰናቸው ተመለስን።

ገና ቤት ሳንገባ ቤዛ ከበር ጀመረችኝ ሀናን እንዴት ስታያት እንደነበር አይቼሀለሁ ለምን ከኔጋ ተፋተህ ከሷጋ አትሆንም ባዶ እጅህን ሳስቀር የዛኔም ትወድህ እንደሆነ እናይ ነበር አለችኝ ዝም ብያት ገባሁ፡፡

እየተከተለች በነገር ትነዘንዘኝ ጀመር ከዛ በላይ መታገስ ስላልቻልኩ ቤዛ አፍሽን ዝጊ አልኳት።
ሀሀሀሀ ጭራሽ እኔን አፍሽን ዝጊ እእ ባልዘጋስ ምን ልታደርግ ነው አለችኝ ኮስተር ብላ።

" በፈጠረሽ እስቲ አንዳንዴ እንኳን እንደ እድሜሽ አስቢ ትንሽ እንደበሰለ ሰው ሁኚ እንጂ ቀኑን ሙሉ ስራ ውዬ ደክሞኝ መጥቼ ቤት እንዳይደብርሽ ኦራት ይዤሽ ወጣሁ አንቺ ግን እዛ እንኳን ክብር እንዳላት ሴት አርፈሽ እራትሽን መብላት አቃተሽ ከዚህ የበለጠ ትልልቅ ቦታዎች ላይ ይዤሽ ለመሄድ በራሱኮ እንዳፍር እያደረግሽኝ ነው፡፡

ደሞ ካሁን ቡሀላ ከስራ በገባሁ ቁጥር የሀናን ስም ካነሳሽ እናቴን ይንሳኝ የመጨረሻ እንጣላለን አልኳትን ከነልብሴ እዛው ሶፋ ላይ ተኛሁ አፏን ዘግታ ገባታ ተኛች፡፡

ጠዋት ተነስቼ ሻወር ወስጄ ወደስራ እስከምሳ ሰአት ቆየሁና ሀናጋ ሄድኩ አብረን ምሳ በላን ከምሳ ቡሀላ ብዙም ሰው ስላልነበር ከሀናጋ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን ቤዛ ማታ ካስከፋችሽ ይቅርታ አልኳት።

አረ አንተ ምን አጠፋህና ነው ይቅርታ ምትለኝ ግን ቤዚ ፀባይዋ ትንሽ ከበድ ይላል ማለቴ ምንም እንኳን ካንተጋ ቅርበት ቢኖረኝም ሚስትህን ማማት እንዳይሆንብኝ እንጂ እኔ ወደፊት ለባሌ አሰልቺ ሚስት መሆን አልፈልግም ደሞም ትዳር ውስጥ በፍፁም ሚስጥርህን ለሶስቸኛ ሰው አሳልፈህ መስጠት የለብህ መሀላችሁ ጭቅጭቅ ፀብ አለመስማማት ቢኖር እንኳን ሸፋፍና ነው ማለፍ ያለባት አለችኝ።

ተሸማቀኩኝ ምመልስላት አጥቼ አየሽ አደል ለዚህ ነው ህይወትሽ ውስጥ ገንዘብ ምንም ዋጋ የሌለው እሷ በገንዘቧ ፀባይ መግዛት አትችልም አልኳት። አይ ታሜ አሁን ገና ተሳሳትክ ህይወትህ ውስጥ ከምንም በላይ ዋጋ ያለው ገንዘብ ነው።

ገንዘብ ካለህ ማስመሰል ሳይጠበቅብህ እራስህን ሆነህ መኖር ትችላለህ ገንዘብ ከሌለህ ግን ገንዘብ ያለውን ስትከተል እያስከፋህ እንኳን ካንገት በላይ እየሳክለት ትኖራለህ፡፡

ገንዘብ ካለህ ሁሉም ወዳጅህ ነው መንገድ ላይ እንኳን ስትሄድ የሰዎች ሰላምታ ሞቅ ያለ ነው።
ፍቅር ኖሮህ ገንዘብ ላግኝ ብትል ትንሽ ከባድ ነው መልፋት አለብህ።

ገንዘብ ኖሮህ ግን ፍቅር ከሌለህ ፍቅርን መግዛት ትችላለህ ለምሳሌ እናትህ ደሀ ብትሆንና አንተን ጨምሮ ሌሎች ወንድ ልጆች ቢኖሯት ከወንድሞችህ ተለይተህ አንተ ቤት ብትገዛላት ከድካሟ ብታሳርፋት የምትፈልገውን ነገር በሙሉ በገንዘብህ ብታደርግላት እናትህ ሌሎች ወንድሞችህን ባትጠላቸው እንኳን ከሁሉም አብልጣ አንተን ትወድሀለች ታከብርሀለች ይሄ ማለት በገንዘብህ ከሌሎች በተሻለ አንተ ፍቅርን ማግኘት ትችላለህ ማለት ነው።

ሌላም ልጨምርልህ ለምሳሌ ሁለት ወንዶች ቀተመሳሳይ ሰአት አንድ ሴት ቢወዱና ሁለቱም ጥሩ ፀባይ ቢኖራቸው እሷ ገንዘብ ያለውን አብልጣ እንደምትወድ አትርሳ።

ገንዘብ ካለህ የሚጠሉህ ሰዎች እንኳን አይጠሉህም ፡ ይቅርታ አድርግልኝና እስከዛሬ አንተን ከቤዛጋ አስሮ ሚያኖረህ ፅናትን በለጋነቷ የቀጠፋትኮ ገንዘብ አለችኝ። አፌን ከፍቼ ስሰማት ከቆየሁ ቡሀላ ለገንዘብ ያለሽ ፍቅር ይሄን ያህል አይመስለኝም አልኳት።

ለገንዘብ ፍቅር ሳይሆን ፍላጎት ነው ያለኝ ገንዘብ ያለውን መከተል አልፈልግም ግን ገንዘብ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ ገንዘብ ማድረግ ማይችለው ብቸኛ ነገር የመሞቻ ቀንህ አያሳልፍልህም እንጂ ታክመህ መዳን, ተከብሮ መኖር, ተናግሮ መከበርንና እና የሌለህን መልክ ሁላ ይሰጥሀል ብቻ አንተ በርትተህ ገንዘብ ማግኘት ብቻ ነው ሚጠበቅብህ ገንዘቡ ሚመጣበትን መንገድ ግን መጠንቀቅ አለብህ በፍፁም ህሊናህን ሸጠህ ገንዘብ ለማግኘት እንዳትሞክር ምክንያቱም መጥቶም ደስተኛ አያደርግህም የለፋህበት ገንዘብ ብቻ ነው ጣፍጦ ሚበላለህ አለችኝ።


ይቀጥላል...



ክፍል
2⃣0⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
Deleted28.03.202503:59
26.03.202522:05
ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲህያዉንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 10-15 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ይቀላቀሉ
Log in to unlock more functionality.