Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
❤የልብ ቋንቋ❤ avatar

❤የልብ ቋንቋ❤

🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
Location
LanguageOther
Channel creation dateMar 29, 2025
Added to TGlist
Mar 29, 2025
Linked chat

Records

20.04.202513:36
250KSubscribers
10.04.202516:41
100Citation index
29.03.202523:59
1.2KAverage views per post
29.03.202523:59
1.2KAverage views per ad post
09.04.202509:55
646.15%ER
29.03.202523:59
0.50%ERR
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
30 MAR '2506 APR '2513 APR '2520 APR '25

Popular posts ❤የልብ ቋንቋ❤

26.03.202518:15
  

              
💙  ያልታሰበ ስቃይ 🌹🔸

♥ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

ፀሀፊ ፊደል

                           ክፍል4⃣
7⃣

.....ደብዳቤው እንዲህ ይላል እናቴ ጮክ ብላ እያነበበችው ነበር

" ሰላም የኔ ልጅ የኔ የመጀመሪያ የልጅነቴ !! ልታስበው ከምትችለው በላይ ነው የምወድህ ። ስናፍቅህና ስመኝህ ነበር እድሜዬን ሙሉ ግን እንደምኞቴ አልሆነልኝም ። በመጀመሪያ ህይወትህን ስላበላሸሁብክ ይቅር በለኝ ተውህቦዬንም ( እናቴን ማለቱ ነው ስጦታዬ ) አሳዝኛታለሁ ጎድቻታለሁ ፣ እድሜዋን በብቸኝነት እንድታሳልፍ አድርጊያለሁ ያም እድሜዬን ሙሉ ሲፀፅተኝ ይኖራል ። ፈጣሪ በሚያውቀው ግን የአሁኑ አመት ኤርትራ እስከመጣሁበት ቀን ድረስ እናትህ እንዳገባችና ጥሩ ህይወት እንደምትኖር ነበር የማውቀው ። ግን ጥሩ ህይወት ልትኖሩ ስትችሉ ወደ እዚህ አምጥቼ ያልታሰበ ስቃይ ጫንኩባችሁ አይደል ይቅርታ አድርጉልኝ ሁለታችሁንም በድያለሁ አሁን ግን ዳግም ወደ ህይወታችሁ መጥቼ ላረብሻችሁ የልጅነት ልጄ በአንተ ስም ምዬ አረጋግጥላችዋለሁ  !!! ግን ሁሌም እንድታውቁልኝ የምፈልገው በጣም እንደምወዳችሁ ነው !! ታውቃለህ የኔ ልጅ ወደ እዚ ሀገር ይዣችሁ መምጣቴ ምን አልባትም እናትህና አብነት አንድ ላይ እንዲሆኑ ፈጣሪ ፈልጎት ምክንያት አድርጎኝ ይሆናል ሁሉም ለበጎ ነው !!! ይህ ሁሉ የተፈጠረው በአንድ ሰው ስህተት ነበር ። በመጨረሻም ግን ልጄ ጠረንህ ይናፍቀኛል አንዳንዴ ምናለ እሱ ልዕልት ሆኖ እኔ አገልጋይ ሆኜ ብቀጠር እላለሁ ። እናም በህይወታችሁ ጣልቃ ላልገባ ወስኜ  ፈፅሞ ወደ ማታገኙኝ ቦታ ሄጃለሁ እንዳትፈልጉኝ ከማታፈቅሩት ጋር ከመኖር መሞት ይሻላል ቸር ይግጠማችሁ !!!! ይቅር ይበለኝ አምላኬም !!!!! " ይላል የዛን ቀን ወንድሜ ስለታመመ በስርአት አላነበብኩትም ነበር አሁን ሳዳምጥ በጣም ነው የደነገጥኩት እንባዬ እንደ ጉድ እየወረደ እናቴን ስመለከታት እሷም ፊቷ በፀፀት ተሞልቶ እንባዋ እየወረደ ነው ። በአይምሮዬ የመአት ሀሳብ ተመላለሰብኝና ቀስ ብዬ እናቴ እግር ስር ሄጄ ድፍት አልኩና እንባ በተናነቀው ድምፅ

አ አ አደይ እ እእእራሱን ሊያጠፋ ነው ??? አልኳትና  ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ  እናቴ ምላሽ ሳትሰጠኝ አቅፋ ጭንቅላቴን እያሻሸች አብራኝ ማልቀስ ጀመረች ። ወዲያው ወንድሜ በሩን ብርግድ አድርጎ ገባ። ሲያየን በጣም ደንግጦ ነበር ። በእጁ  የያዘውን ፌስታል ወርውሮ እየሮጠ መጣና

" ወንድሜ እማዬ ምን ሆናችሁ ነው ምንድነው " አለን እየጬኽ  አንዴ እኔን አንዴ እናቴን በየተራ እየነካካና እየተመለከተ እኔ ማልቀስ ማቆም አልቻልኩም እናቴ ግን ቶሎ ብላ  እንባዋን ጠራርጋ የኔንም እንባ ጠረገችልኝና ወደ ወንድሜ እየተመለከተች

" ደብዳቤውን አንብበከዋል ??" አለችው

" የቱን ... እ አዎ ግን የመጀመሪያውን ብቻ " አለና ሶፋ ላይ ተቀመጠ እናቴ ወረቀቱን አንስታ ወደ መጨረሻው ፅሁፍ እየጠቆመች

" ይሄን አንብበው መጥፎ ነገሮች ተፈጥረው እንዳይሆን " አለችው ። ወንድሜ ተቀበላትና ፊቱን ኩስትር አድርጎ አነበበውና እኔን ተመለከተኝ ። ሲያየኝ በቃ ራሱን ሊያጠፋ ነው አይደል ???? አባቴ ሞተ ብዬ እሪሪ አልኩኝ ። ግን ወዲያው ወንድሜ ያመው ጀመር ። ከእስከዛሬው በበለጠ አመመው
" ራስን ማጥፋት ፣ መግደል ፣ሞት " እያለ እየደጋገመ እየለፈለፈ ይንቀጠቀጣል ። ወንድሜ ታሞ ሳየው   የእራሴን ህመም ረስቼ ወደ ወንድሜ ሄድኩኝ ። እናቴ በብዙ ነገሮች ውስብስብ ስላለባት እንባዋ እየወረደ ነው ።

በነገራችን ላይ አንዳንድ ጊዜ ልባችን ከመጠን በላይ ሲጎዳ ለማልቀስና ለመከፋት ሰበብ ነው የሚያስፈልገን !!!!!  በዛው ልክ ደግሞ እንባችንን ለማቆም አንችልም !!! ይሄ ህይወት እና እውነት ነው !!!!

ብቻ ግን እንደሁሌው እናቴ የአማኑኤል ፀበል ፊቱ ላይ እና ልቡ ላይ ስታደርግለት አደዬ ምግብ በልቷል እኮ አልኳት ግን ሌላ አማራጭ ስለሌለን አድርጋለት አቅፋው ቁጭ አለች ። ትንሽ ደቂቃ ዝም አለና ወደ እራሱ ተመለሰ ። ሁል ጊዜ አሞት ሲነቃ በጣም ያፍራል ፣ ይደብረዋል ፣ ይከፋዋል ሀዘኑ ፊቱ ላይ ያስታውቃል ። ቶሎ ብሎ ከእናቴ እግር ላይ ተነስቶ ሶፋ ላይ ቁጭ አለና በመዳፉ ፊቱን ሸፍኖ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል እኔ ደንግጬ ወንድሜ ብዬ ላቅፈው ስል አደዬ እጄን ይዛ ወደ ራሷ ጎተተችኝ። ለትንሽ ደቂቃ በዝምታ ሲያለቅስ ቆይቶ በረጅሙ ተነፈሰና

" አሰለቸዋችሁ አይደል አለ " ፊቱን እንደሸፈነ

" ተው ልጄ እንደዛ አትበል ይከፋኛል እኮ " አለችው እናቴ በሚያሳዝን መልኩ


" እኔ ሁሌም ይከፋኛል ፣ አይምሮ ህመምተኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል ፣ አይምሮዬ ውስጥ ልጅነቴ ብቻ ነው የሚታየኝ እናቴ የእናቴ ሞት ነው የሚታየኝ እኔ የማልጠቅም ሰው ነኝ አይደል ወይ ለእራሴ አልሆንኩ ወይ ለእናንተ አልሆንኩኝ ለምንድነው የምኖረው የዛኔው እናቴን ተቀላቅዬ ቢሆንስ ኤጭ " አለ እናቴ ማልቀሷን ቀጠለች 


" ለምንድነው እንዲህ የምትለው ለእኔ አታስቡም እንዴ ደስተኛ ለመሆን ስሞክር   እኔን ለማስከፋት ትሮጣላችሁ እሺ እኔ ምን ላድርግ ???"' አለች ምርር ባለው ድምፅ በሁለቱ ወሬ መካከል የኔ አባት ጥፋቱ ምኑ ጋር ነው እያልኩኝ  ብቻዬን ተቀምጬ አለቅሳለሁ  አሁን አሁን ሳስበው እንባዬ እየደረቀ ያለ ያክል ነው የሚሰማኝ ሲወርድ እራሱ አያስታውቀኝም ። ምንም ነገር ሳይጎድለኝ በአንድ ሰው ስህተት ህይወቴ ተመሰቃቀለ ፣ እንባ ቤታችንን አጠበው ፣ ብቻ በሁሉም ነገር መሀል ተመስገን !!! ማለትን ተምሪያለሁ  !!!!


ሁላችንም ተሰብስበን እየተላቀስን  እያለ በሩ በሀይል ተንኳኳ ። ደንግጬ ነበር እናቴን ስመለከታት በድጋሜ በሩ በሀይል ተንኳኳ እናቴም ከተቀመጠችበት ተነስታ ፊቷን ጠረገችና ። በቲሸርቷ የወንድሜን እንባ ጠራርጋ ፊቱን እንዲታጠብ ነግራው ወደ በሩ ስንሄድ አሁንም በሩ ተደበደበ እኔ የጊቢው በር ላይ ቆሞ የአባቴን ሞት ልሰማ ነው እያልኩኝ እግሬ እየተንቀጠቀጠ ቆሜ ነበር እናቴም ፈርታ ስለነበር አማትባ ተነፈሰችና በሩን ከፈተችው ...



ይቀጥላል.....


ክፍል
4⃣8⃣ ከ️ 1⃣5⃣0⃣ Vote በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍ሼር ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 
https://t.me/yefkr_tube ❤️
❤️ https://t.me/yefkr_tube ❤️
Deleted15.04.202515:20
15.04.202514:16
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

በአጭር ጊዜ ህይወታቹን የሚቀይሩ የተረጋገጡ ጨዋታዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ 👇

betting ሁሌ ማሸነፍ ከፈለጋቹ ይሄንን ቻናል ተቀላቀሉ🏆👇
Deleted03.04.202510:25
📹🎥🍿🎥🎬📺📱📺🍿⭐️

ዛሬ ከስራ እና ከክላስ መልስ ምሽቱን ምርጥ ምርጥ ሲሪየስ ፊልሞችን እና ተከታታይ ድራማዎችን እያያችሁ ማሳለፍ የምትፈልጉ ከሆነ ሊንኩን በመንካት ይቀላቀሉ (JOIN) የሚለውን ይጫኑ።


https://t.me/addlist/e3BXRkE7LZYyMzJk
06.04.202517:39
ቤተሰብ አንዴት ከረማችሁ አዲስ ታሪክ ይጀመር ወይ ይጀመር እምትሉ 300 ላይክ ሲሞላ እንጀምራለን ቶሎ አንዲጀመር Like እያደረጋችሁ
26.03.202517:34
♥♥♥♥
እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ    ያልታሰበ ስቃይ   ክፍል 47 ሊለቀቅ ነው   
ዝግጁ ናችሁ?
Deleted20.04.202513:32
🌐 ሰበር ዜና 🌐

✅ ቴሌ ነፃ ኢንተርኔት 🎉 ለ 7 ቀን  የሚቆይ ስጦታ መስጠት ጀምሯል፡፡😍❤️😍
👇ከታች #JOIN ብላቹ ሴቲንጎቹን በማስተካከል መጠቀም ትችላቹ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Deleted31.03.202509:56
30.03.202505:43
      

      
❤️ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
ማኔ


                        ክፍል 
1⃣6⃣


ይሄን ሱቅ መጀመሪያ ስንከፍተው ቤዛ ገንዘበን ሰጠችኝ ግን ምን ላይ ደረስክ እንዴት ሆነልህ የከፈትከው ሱቅ ምን አይነት ነው ሰዎች እየገዙህ ነው ወይስ አይገዙህም ብላ እንኳን አልጠየቀችኝም ሱቅ ሁላ የት አካባቢ እንደከፈትኩ ያወቀችው ቆይታ ነው በየቀኑ ዛሬ ስንት ሰራህ ይሄን ያህል ብራ አምጣ ከማለት ውጭ አንድም ቀን በርታ ወደፊት ይስፋፋል ብላኝ አታቅም ግን እኔ ሳይሰለቸኝ እየሰራሁ ብር ሴቭ እያደረኩ አንቺ እስክትመጪ የነበረው ደረጃ ላይ አደረስኩት።

ግን ሁሌም ሁሉም ነገር የሷ እንደሆነ ነው ምታወራው እኔ ደሞ ለፍቶ መና ሲሆንብኝ ግዴለም እያልኩ ዝም እላለሁ ግን ጭራሽ በራሴ አልጋ ላይ ከሌላ ወንድጋ ከባድ ነው አልኳት፡፡

እየውልህ ተረጋግተህ ስማኝ አንዳንዴ ሰዎች ትክክለኛ የኛ ጥቅምና ለኛ ያላቸው ፍቅር የሚገባቸው ካጠገባቸው ዞር ስንልና ከበፊቱ የበለጠ አምሮብን ጠንክረን ሲያዩን ነው፡፡

ስለዚህ በቃ ትናት ቤዛን ከሌላ ወንድጋ እንዳላየሀት ቁጥረው ቺት አላረገችብኝም ብለህ አስብ እራስህ ላይ ስራ ከዛሬ ጀምሮ በደንብ ሰአታችንን ስራ ላይ እናሳልፍ የገባ ከስተመር ሳይገዛ እንዳይወጣ እንታገል ከዛ ከሷ ለሱቅ መክፈቻ የተበደርካትን ገንዘብ መልስላት እሷ የማታቀው በደንብ ገበያ ያለበት ቦታ ሂድና በራስህ ገንዘብ በራስህ ተነሳሽነት የራስህን አዲስ ሱቅ ክፈት የዛኔ በራስ መተማመንህ ይመጣል እስከዛ ግን ምንም ነገር ቤዛ ላይ እንዳትቀየርባት አለችኝ
ሀሳቧ በደንብ ነበር የተመቸኝ በአዲስ ሞራል በአዲስ የስራ ፍላጎት ከቤት ተያይዘን ወጣን በለበስኩት ልብስ አድሬ እንደዛው ስራ ቦታ ስሄድ ስለደበረኝ ከተሰቀሉት ውስጥ አንዱን ሸሚዝ አንስቼ ለበስኩት ።

ገና በስርአት እቃ አወጣጥተን ሳንጨርስ ቤዛና እናቴ እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው ሱቅ መጡ ሀኒ ስታያቸው ወደኔ ዞረችና ጠቀሰችኝ እኔም ገና ሳያቸው ምንም እንዳልተፈጠረ ውይ እማዬ ቤዚዬ ምነው በሰላም ነው በጠዋት የመጣችሁት አልኳቸው ሁለቱም ንዴታቸው ፊታቸው ላይ እየታየ የታባህ ነው ያደርከው እ ለቤዛ እናቴጋ ነው ማድረው ብለህ ዋሸህ እ ይሄ ምን የሚሉት ቅሌት ነው የት ስትንዘላዘል አድረህ ነው አለችኝ እናቴ ለመምታት እየቃጣት።

ነገሩን ለማብረድ ፈገግ እያልኩ አይ እማ ቤዚን የመሰለ ሚስት ቤት አስቀምጬ ሌላጋ ልንዘላዘል ምሄደው ምን አጥቼ ነው ብዬ ቤዛን ወደኔ ሳብ አድርጌ አቀፍኳት ባንዴ የጠቆረው ፊታቸው ወደደስታ ተቀየረ ዝም ብዬ የተሰቀሉትን ልብሶች እያሳየሁ እነዚህንኮ ላመጣ ሄጄ ማታ መሽቶብኝ ነው ይቅርታ አስደነገጥኳችሁ አይደል በቃ ኑ እንደካሳ እንዲሆነኝ ቁርስ ልጋብዛችሁ ብዬ ይዣቸው ወጣሁ።

ምሳ ሰአት ላይ ሀኒ ባሏ መጥቶ ይዟት ወጣ ።
እኔ ግን ሀሳቤ ሁላ ገንዘብና ገንዘብ ማግኘት ላይ ብቻ ስለነበር ምሳ ሰአቱንም ሳልዘጋ እዛው ቁጭ አልኩ።

ወደሱቄ የመጣው ሰው ሁሉ
በክብር እያስተናገድኩ መሸኘቱን ተያያዝኩት,,,



ይቀጥላል...



ክፍል
1⃣7⃣ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️
Deleted07.04.202512:32
07.04.202510:43
ከ30 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???
Deleted12.04.202517:21
12.04.202516:08
የ ስንተኛ ክፍል ተማሪ ናችሁ?
28.03.202518:10
ታሪኩ እንዲቋጭ ያህል አሁን ላይ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሶስተኛ አመት ተማሪ ሆኛለሁ ፣ ወንድሜ በግሉ እየተንቀሳቀሰ ከአንድ ቆንጅዬ ወጣት ጋር ፍቅር ጀምሯል ፣ እናቴና አብነት ሁለት ታናሽ እህት ሰተውኛል ፣ አባቴ ከባለቤቱ ጋር ስኬታማ ሆኖ እኔንም እየመጣ ይጠይቀኛል ፣ የሚያሳዝነው መጨረሻ አያቴ የያዘችውኝ እውነት እንደያዘችው ከዛሬ ሶስት ዓመት በፊት አርፋለች !!!! እኔም ታሪኬን በዩንቨርስቲ ትርፍ ጊዜዬ ጓደኛ ስለሌለኝ ለእናንተ ላካፍላችሁ ፈልጌ ስለነበር ነው ። ከኔ ታሪክ ምን ተማራችሁ ??? እያልኩ በዚሁ ልጨርስ ............

እንደመሰናበቻ ግን በታሪኩ ውስጥ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ ። አንዳንድ ጊዜ ህይወት እኛ ባሰብናት መንገድ አትሄድም !!! በህይወታችን ውስጥ ብዙ የማይመለሱልን ጥያቄዎች አሉ !!!! አንዳንዴ እውነታውን ሳናውቅ ወይ ሚስጢር ያዡ ወይም እኛ ከዚች አለም እንጠፋና አፈር ይጫንብናል !! ሰው እስከሆንን ድረስ አፈር ያለበሱን እጃቸው ሲደርቅ እኛም አብረን እንደርቃለን !!! የጠወለገ ፅጌረዳ ከቤት እንደሚጣል ሁሉ እኛንም ከልባቸው ያወጡናል !!!! ማንም ሆንን ማን እንረሳለን ልላችሁ ፈልጌ ነው !!

ፍልስፍና አይደለም!!!___
በኔ ታሪክም እንደምንረዳው አክስቴ ለምን እንደሞተችና ወንድሜ አባቴን ሲያየው ለምን እንደሚታመም ከወንድሜና ከፈጣሪ በቀር ማንም አያውቅም ። አንዳንድ ሚስጢሮች ሚስጢር እንደሆኑ ከመቃብር ስር ይውላሉ !!!!!

እና ምን ልላችሁ ነው ምንም ሆነ ምን ምንም ቢፈጠር ምንም ህይወት ይቀጥላል .....!!!! ምን ተማራችሁበት ???

!!!!!!!ህይወት ይቀጥላል🙏❤️



❤️❤️❤️❤️


ታሪኩን እንደወደዳችሁት እና እንደ ተማራችሁበት እምነታችን ነው።
በቅርቡ አዲስ ታሪክ እንጀምራለን ሀሳብ አስተያየታችሁን እንዲሁም ማስተካከል ያለብን ነገር ካለ  comment ላይ አድርሱን እናመሰግናለን።
❤️

      ‌‌‌‌‌‌ ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
❤️ https://t.me/yefkr_tube ❤️
❤️ https://t.me/yefkr_tube❤️
27.03.202518:01
  

              
💙  ያልታሰበ ስቃይ 🌹🔸

♥ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

ፀሀፊ ፊደል

                           ክፍል4⃣
8⃣


....... በረጅሙ ተነፈሰች እና በሩን ከፈተችው ። ማን እንደሆነ  እንኳን ሳላውቅ እግሬ እየተንቀጠቀጠ ነበር ። ግን በሩን ስትከፍተው በሚያናድድ ሁኔታ አብነት ነበር ። እናቴ ስታየው ተናዳ


" ያምሀል እንዴ  ለምንድነው እንደዚህ የምታንኳኳው  " አለችው በጣም ተኮሳትራ እየጮከች እሱም ደንግጦ  እናቴን  ትንሽ ሲመለከታት ቆየና  ወደ እኔ ዞረ እኔ ግን እያየሁት ራሱ ለመስማት የተዘጋቸሁትን ነገር እያሰብኩኝ ድንዝዝ እንዳልኩ ቀረሁኝ ።  ወዲያው ወንድሜ መጣ እና


" ምንም አይፈጠርም እሺ ተረጋጋ ምንም አይሆንም እሺ "ብሎ አቀፈኝና  ፀጉሬን አሻሽቶ ወደ ቤት አስገባኝና።  ትንሽ ደቂቃ ቆይተው እነሱም ወደ ውስጥ ገብተው ተቀመጡ ።


" ምን ተፈጥሮ ነው ምን ሆናችሁ ነው ????" አለ አብነት ግራ በመጋባት ሁላችንንም በየተራ  እየተመለከተን ። እናቴም በጣም ደንግጣ ስለነበር መናገር ከበዳት ሁላችንም ዝም ስንል


" እኔን አሞኝ ነበር " አለ ወንድሜ ቀልጠፍ ብሎ


" ግን እኮ አሁን ደህና ነህ እሱ ብቻ ነው ??" ሲለው ወንድሜ ዝም አለ እኔም ጉሮሮዬ ሲደርቅ ቀዝቃዛ ውኃ አምጥቼ ጠጣሁኝ ። እና ትክዝ ብዬ ስቀመጥ እናቴ ወደ እኔ መታ  አቅፋኝ ታባብለኝና ምንም እንደማይፈጠር ልታሳምነኝ ሞከረች ። እኔ ግን ውስጤ ሊረጋጋልኝ አልቻለም ነበር ።


" ምንም አይሆንም ተመስገንን አውቀዋለሁ ምንም አያደርግም " አለችኝ እናቴ ገና የአፏን ሳትጨርስ


" እንዴ የምር ነው እንዴ " አለ አብነት እየጮከ እና አይኑን በትልቁ ከፍቶ ምኑ አልኩት ምላሹን ለመስማት ቸኩዬ


" ስለ ተመስገን የሚወራው ነዋ ??" አልኩት ተስፋ በመቁረጥ መልክ ሆኜ ምን ተባለ አልኩት ። ወንድሜና እናቴም በእኩል ድምፅ " ቆይ ቆይ መጥፎ ዜና ከሆኗ ተወው " አሉት እኔ ምን ያህል እንደምጎዳ ስለሚያውቁ ። እኔም ፈጠን ብዬ መስማት እፈልጋለሁ ምንም ይሁን ንገረኝ አልኩት ።


" አረ ተረጋጉ ያን ያህል መጥፎ አይደለም ሚስቱንና ልጆቹን ሰብስቦ ሄዱዋል ሲሉ ሰምቼ ነው " አለ ትንሽ ደቂቃ  አይኔን ጨፍኜ ፈጣሪዬን አመስግኜ ተረጋግቼ ወዴት ነው የሄደው?? አልኩት


" እሱን ማንም አያውቅም " አለኝ ። በትንሹ ልቤ ቀለል ቢለኝም ልቤ ግን ተደውሎ መጥፎ ዜና ይነገረኛል በሚል ስቆዝም ዋልኩኝ ። በብዙ ነገሮች እየተጨናነኩ ነበር ። በዛ ላይ ደግሞ አስተማሪያችን የሚኒስትሪ ጥያቄ በጣም ከባድ እንደሆነ እና ሁላችንም ከምንወድቅ እንድናነብ መክሮን ነበር ። አሁን አሁን ደግሞ የመአት ነገር አጠናና እራሴን ስፈትን ሁሉንም ነገር እረሳዋለሁ ። ትምህርት መውደቅ ደግሞ በጣም የምፈራው ነገር ነው ። ብቻ ግን ሁሉም ነገር አስጠሊ ነበር በቻልኩት መጠን ለማጥናት ሞከርኩኝ ። ይህን ሳምንት '''_ የሰቀቀን ሳምንት __'' ብያታለሁኝ ። የጭንቀት ጊዜ ነበር ። እንደምንም ለመሸምደድ እየሞከርኩም እየፈራሁም እየታመምኩም ሳምንቱን ጨረስኩትና  የፈተና ቀናችን   ደረሰች !!! ስለ አባቴ አንድም የሰማሁት ነገር ሳይኖር ሳምንት አለፈው ። የፈተና ቀን ጠዋት ከወንድሜ ጋር ቤተ ክርስቲያን ሄደን ፀበል ተጠመቅን መጣን ከዛ ቁርስ በልቼ በፍራቻ ወደ ፈተና ገባሁኝ ። ወደ ምድብ ክፍላችን ስንገባ ሶስት ወንበር ለብቻው ጥግ ላይ ተቀምጧል ከሌሎቹ ራቅ ብሎ ። ደግሞ ይሄ ምንድነው እያልኩኝ ። ሄጄ ክፍል የምቀመጥበት ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ ። በልቤ ብዙ ነገር እያሰብኩ ነበር አይምሮዬ ውስጥ ያለው ። ትወደቃላችሁ የሚለው የአስተማሪያችኝ ንግግር ነበር ። ፈታኝ አስተማሪዎች ሁለት መጡ ። ገና ከመግባታችው " አብልኮት ተመስገን " አሉ ። ምን ሊሉኝ ነው እያልኩ እየተርበተበትኩ አቤት አልኩኝ ።

" ተነስ ከእሱ ጋር " ብሎ ለብቻቸው ብላክ ቦርዱ ፊት ለፊት ወደተቀመጡት ወንበሮች ጠቆመኝ ጥር ገብቶኝ ሄጄ ቁጭ አልኩኝ ።

" አብላካት ሰለሞን " አለ የስማችን መመሳሰል ገርሞኝ ዞር ስል አንድ ቆንጅዬ ልጅ
" አቤት " አለች እርግት ባለ ድምፅ

" አንቺ እና አብርሀም ስዩም ተነሱ " አለ ሴቷ መሀል ተቀመጠች ። የምታምር ልጅ ናት ግን በእርግጠኝነት እድሜ ትበልጠኛለች ። ከዛን አስተማሪው መጣና

" እናንተ ተጠንቅቃችሁ ስሩ ወደ ዃላ እንዳትዞሩ እሱ ፈተናውን ከቀደደባችሁ እኔ ምንም ላግዛችሁ አልችልም " አለን ይበልጥ እየፈራሁ ነበር ። የመጀመሪያ ፈተና ተሰጠን ። እጅግ በጣም ቀላል ነበር ። ከማስበው እና ከጠበኩት በላይ ቀላል ነው እንኳን እኔ የ አንደኛ ክፍል ተማሪም ይሰራዋል ። በአስር ደቂቃ ሰርቼ ጨረስኩኝ ለተጨማሪ አስር ደቂቃ ሁሉንም ደጋግሜ ቼክ አደረኩኝ ። ማጥቆር እንዳልሳሳት ወንድሜ በደንብ ነው ያስተማረኝ ። ከዛን ፈተናዬን መልሼ ልወጣ ስል ሁሉም ሳይጨርስ መውጣት አትችልም ገና አንድ ሰአት አለ አለኝ ። ይህን ያክል ሰአት አብሬ መቀመጥ እንደሚጨንቀኝ ስላወኩ ሱፐርቫይዘር ሲመጣልኝ ዳይሬክተሩ ጋር ይዞኝ እንዲሄድ ጠየኩት ። እሱም ይዞኝ ሄደ ዳይሬክተሩ ገና ሲያየኝ

" ምን አጥፍቶ ነው "  አለ ክው ብሎ ። አረ ምንም አላጠፋውም መምህር ፈተናውን ሰርቼ ስለጨረስኩ መቀመጥ ሲጨንቀኝ ቤት ሄጄ ትንሽ የከሰአቱን ላነብ ነው አልኩት ።

" በአስር ደቂቃ ሞልቶ ለመውጣት የቸኮለው ለምንድነው የት ለመሄድ ነው ??? አንድ አመት የማባከን እቅድ አለው መሰለኝ ? አለን ሰውዬው ሰለማያውቀው ሰው የሚያወራ ሰው በጣም ቢያናድደኝም ትህትና ተላብሼ ዝም አልኩኝ ። ዳይሬክተራችንም ፈጠን ብሎ


" Average 99.6 የሚያመጣ ልጅ ነው እኮ ምን ሆነሀል በጣም ጎበዝ ተማሪ እና የተከበረ ቤተሰብ ልጅ ነው " ብሎ አሞጋገሰኝ ሰውዬውም በግርምት ተመለከተኝ የዛን ሰአት ላይ ስለ አባቴ እያወራ እንደሆነ ገብቶኛል ። እንባዬ አምልጦኝ ሊያዋርደኝ ሲል ዋጥ አድርጌ የውሸት ፈገግ አልኩኝ ። ትንሽ አወሩና እንድወጣ ተፈቀደልኝ ። ልክ ከትምህርት ቤት እጥፍ እንዳልኩኝ እንባዬን ለቀኩት  !!! የዛኔ ፊቱ ላይ ያየሁትን ፈገግታ እና የነገረኝን ምክሮች አስታውሼ እንባዬን ለቀኩት ። ትክዝ ብዬ እየተራመድኩኝ ወደ እኛ ቤት መታጠፊያ ጋር ስደርስ ወንድሜን አየውት ። ፊቴን ጥርግርግ አድርጌ እየቦረኩ ወደ እሱ ሄድኩኝ ። ሲያየኝ ደንግጦ ስልኩን አውጥቶ ሰአት አየና ወደ እኔ መቶ


" ምነው ትንሹ ምን ተፈጠረ " አለኝ ከፈተና አባረሩኝ ብዬ ልቀልድ አልኩና ቢያመውስ ብዬ ፈርቼ አልልክ መቼስ ጨርሼ ነው እኔ ያንተ ወንድም አልኩት ።

" ቀሎሀል ማለት ነው " አለኝ ከድንጋጤው ተመልሶ ፈገግ እያል ። አዎ አስተማሪው ዝም ብሎ ነው የሚያስፈራራን መጀመሪያ ሊያደናግጠን ፈልጎ እንጂ እማዬ እራሱ ትሰራዋለች አልኩት ቀለል አድርጎ ። ከዛን ቆይ አንዴ ብሎኝ ከአጠገቤ ዞር ብሎ ስልክ አወራ እና ወደ ቤት ሳልገባ አብረን ሱቅ እንሂድ ብሎኝ ። እኛ ጋር ካለው ሌላ ሱቅ ሄደን ወንድሜ እስከሚገዛ ብዬ የተሳሳትኩት ጥያቄ እንዳይኖር እያልኩኝ ደጋግሜ ወረቀቴን ማንበብ ጀመርኩኝ ። በትልቁ ጥቁር ፌስትል  ሙሉ እቃ ገዛዝቶ ለሁለት ይዘን ወደ ቤት መሄድ ጀመርን ። ምንድነው ብዬ እንኳን አልጠየኩትም ነበር እንጅ ብጠይቀው አስቀድሜ እረዳ ነበር ። ቁልፍ ይዘን ስለነበር ከፍተን ገባንና በሩን ዘግተን ወደ ቤት ቀድሞኝ ወንድሜ ገባ ። እኔ ሽንት ቤት ገብቼ ። ወደ ውስጥ ስገባ ነበር የድንጋጤ .....
27.03.202517:17
♥♥♥♥
እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ    ያልታሰበ ስቃይ   ክፍል 48 ሊለቀቅ ነው   
ዝግጁ ናችሁ?
Log in to unlock more functionality.