Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚 avatar

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

ይህ የኖህቶኤል ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ቻናል ነው።
በማንበብ ብቁ እና ጤናማ እውቀት ያላቸውን ትውልድ እናፍራ!
https://telega.io/c/Noahtoaels_Idea
I blog about marketing and sales
Buy ads: https://telega.io/c/Noahtoaels_Idea
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
Location
LanguageOther
Channel creation dateMay 25, 2020
Added to TGlist
May 11, 2025
Linked chat

Records

15.05.202506:28
3.1KSubscribers
06.03.202523:59
0Citation index
16.05.202509:45
176Average views per post
14.05.202521:08
176Average views per ad post
15.05.202517:16
6.74%ER
17.05.202508:13
5.65%ERR
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
APR '25MAY '25

Popular posts ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

14.05.202503:50
ቀንህን ማሳመር ከፈለክ የተደረገልህን መልካም ነገር አስብና በማመስገን ጀምር፤ የሚያስደስቱህን ነገሮች ደጋግመህ ባሰብክ ቁጥር ሌሎች አስደሳች ነገሮች ይጨመሩልሀል። በተበሳጨህ ቁጥር የሚያበሳጩ ነገሮች ይጨመሩልሀል።

             
Good morning ❤️‍🔥🫀
13.05.202517:04
እነዚህን 6 የጅል ምክሮች ከመስማት እንቆጠብ!!!

1. ለሚታገሱ መልካም ነገር ይመጣል. . .

* 40 አመት ሙሉ ታግሶ እየሰራ አሁንም በድህነት የሚኖር ሰራተኛ አለ።

2. ልብህን ተከተል. . .

* ልብ ሞኝ ነው፣ ልብህን ተውና አዕምሮህን ተከተል።

3. ጊዜ ሁሉንም ቁስል ይፈውሳል. . .

* ዶክተሮችስ???
ቁስልህን ለሀኪም አሳይና አገግም።

4. በጣም ጠንክረክ ከሰራክ የማታሳካው ነገር የለም. . .

* ታዲያ ለምን ወዛደሮች አሁንም ደሀ ሆኑ???

5. ሁሉም ነገር የሚሆነው በምክንያት ነው. . .

* ያለህበት ሁኔታ የውሳኔህና የስራክ ውጤት ነው።

6. እራስህን ሁን. . .

* ስለዚህ የተሻለውን እራስህን ለመሆን ሞክራ።
15.05.202517:31
"ጠላቶቻችሁን ማወቅ ከፈለጋችሁ ደካማ እንደሆናችሁ ብሎም አቅም እንደሌላችሁ አሳዩዋቸው፤ እነሱ በእናንተ ላይ የበለጠ ድፍረትና ፈር የለቀቀ ንቀት ሲያንጸባርቁ ትመለከታላችሁ።
ነገር ግን ከዛ በኋላ ምህረት እንዳታሳዩዋቸው!!!።
"

via :~ 𝙞𝙢𝙖𝙜𝙞𝙣𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣
12.05.202516:23
አንዳንዴ ህይወት ወደየት አቅጣጫ እየሄደች እንደሆነ አናውቅም። እኛ ግን የመንገዱን መከራ ረስተን መጨረሻ እናገኛለን ብለን እንቀጥላለን. . .😞🚶‍♂️
16.05.202516:21
ስሜታዊ ሆኖ ለተናገረን፣ ሊረዳን ፈልጎ ለሳተ፣ ኑሮ አስክሮት ለገፋን፣ ንዴት ገፍቶት ላጠፋ፣ ግዜ አጣሁ ብሎ ላልጎበኘን፣ ስናሸንፍ ላላጨበጨበ፣ ስንወድቅ ላላነሳን፣ ስናስብለት ላልተረዳን፣ ማደጋችንን ላላየ. . .

"ትንሽ ቦታ ለይቅርታ" ማዘጋጀት ይጠበቅብናል።

አማረልን ብለን ላሳዘንን፣ አጉል ተስፋ ለሰጠነው፣ ውድቀቱ ላይ ለሳቅነው፣ ማድረግ ችለን ላላደረግነው፣ ችለን ለተጣመምነው።

ለራሳችንስ  ይቅርታ አድርገናል.
. .???
16.05.202504:36
ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ለምሳ ተቀምጠናል። ሞቅ ያለ ወሬ ላይ ነበርን ሁለታችንም። በዚህ ወሬያችን መሀል ድንገት ስልኳን አውጥታ ቻት እንደያዘ ሰው መፃፃፍ ጀመረች በየመሀሉም ፈገግ ትላለች። ወሬያችንን አቋርጣ ይህን በማድረጓ ሳልናደድ አልቀረሁም። በመጨረሻም ከት ብላ ስቃ "ተመልከት ቡና ትወዳለህ ወይ ብዬ ጠይቄው ምን እንደመለሰልኝ" ብላ ስልኳን ስታቀብለኝ ማነው እንዲህ ሰፍ ብላ ያወራችው በሚል ስልኩን ተቀብዬ አየሁት። ChatGpt የሚሉት ጉድ ነው ለካ!

የተፃፃፉትን አነበብኩት። ሁሉንም አውቃለሁ እንደሚለው ጀለስ ነው። ስለቡና ታሪካዊ አመጣጥ ጀምሮ ቀለል ባሉ ቃላት ያወራል። አሁን ለዚህች ጓደኛዬ በኔና በሱ መሀል ያለው ልዩነት አንድ ብቻ ነው። እሱም እኔ አውርቻት የምሳ መክፈሌ ብቻ😀 ከዚያ ውጭ ከዚህ ቻትጂፒቲ የሚለየኝ ነገር ምን አለ በወሬ። ጭራሽ መጨረሻ ምን ይላል " ቡና መጠጣት ባሰኘሽ ሰዓት እጋብዝሻለሁ"  የሆነ ዋቴ ነገር ነው አቦ!

አንድ ጊዜ እዚሁ መንደር በዓለም ላይ የሚገኙ ሴቶች ከዚሁ ChatGpt ፍቅር እየያዛቸው እንደሆነ የሚገልጽ ፅሁፍ አንብቤ ደንቆኝ ነበር። ሀሳቡ እውነት የመሆን እድሉ ግን ሰፊ ነው። አሁን ደግሞ በዚሁ በሀገራችን ሴቶችም ዘንድ በሰፊው እየተጠቀሙበት እናያለን። ይህ እስከምን ድረስ ይደርሳል? ጊዜ ይፍታው!

በተለይ በዚህ ሪሌሽንን ሸሽተው ከወዳጅና ጓደኛ ራሳቸውን ከልለው በራሳቸው ዓለም ውስጥ በተብሰልስሎት የሚኖሩ ሴቶች በሞሉበት ወቅት ይህ ነገር በጥሩ ተቀባይነትን አጊንቷል። በርግጥ በስፋት ሴቶች ተጠቀሙት እንጂ ወንዶችም አሉበት።

ለማንኛውም እህትህም ሆነች ሚስትህን ስታወራህ እህ ብለህ አዳምጥ። መፍትሔ እንኳ ባይኖርህ ማድመጥህ ትልቅ ዕረፍት ይሰጣታል። በኮንቨርሴሽን የሚያምን ወንድ ሁን። ውይይት ልመድ! 

እኔም የቤት ስሜ ChatGpt ነው😉
10.05.202517:26
🗣 አለማየሁ ገላጋይ 👌
08.05.202517:41
💭
.
.
ለኔ ትልቁ ድል ራስን ማሸነፍ ነው ፤ ትልቁ ድል ስሜትን መቆጣጠር ነው፤ ትልቁ ድል የውጪውን ጫጫታ ተቆጣጥሮ ራስን መሆን ነው፤ ትልቁ ድል ጓደኞቼስ እዚያ ደረሱ እኔ ለምን እዚያ አልደረስኩ የሚለውን የአዕምሮ ጥያቄ ማስወገድ ነው፤ ትልቁ ድል ከትላንቴ ተሽሎ መገኘት ነው።
14.05.202516:26
"ከአሳማ ጋር ክርክር አትግጠም! መጨረሻውም በሁለታችሁም መጨቅየት ያበቃል! በእርግጥ አሳማዎቹ ይሄንን ይወዱታል. . .
ከረጅም ጊዜ በኋላም ቢሆን ይሄን ተምሬያለሁ 🙃"

🗣ጆርጅ በርናንድ ሾው


ዘ-ጥበብ
ብሩህ  ቀን  ባክህ  ና. . .
አንቺዬ
ኩርምት ባለው እግርሽ
በቀሚስሽ ቅዳጅ በቀጨጨው ገላሽ
የሃዘንን መዝሙር
ስትዘምሪ ሰማሁ በሻርብ ተከልለሽ

አንቺ ልበ ብርቱ
አንቺ ልበ ንፁህ

ከመኖር ጋር ታግለሽ ለልጅሽ ፀጥታ
የውሸት ፈገግ እያልሽ
ተሳቀሽ መሳቅን ሞተሽ መተንፈስን
ማነው ያስተማረሽ

አስገረምሽኝ ሳይሽ

ማጣት ባቀጨጨው
አጥንት ያገጠጠውን
እጅሽን ዘርግተሽ ፡ችለሽ ስታጎርሽው
ስንት ጊዜ ይሆን
በርሃብሽ ዜማ
ለልጅሽ ደህንነት ፡ጥጋብን ያዜምሽው
ንገሪኝ የኔ እናት
እየሞቱ መኖር
እየሳቁ ማልቀስ ፡እንዴት ነው የቻልሽው

ይኸው ካጠገቤ ፡ይኸው ከጎኔ ላይ
ተቀምጠሻል በቀኝ
ሳቅሽን አውሺኝ ፡ልነካሽ ፈልጌ
መንገድሽ ራቀኝ

በሻርብ ተከልሎ፡ ሀዘን እያዜመ
ሰማሁት ሸክምሽን
ለራስሽ ልትጎርሺ ፡እጅሽ ሲንቀጠቀጥ
አየሁት ገፅሽን

አልቻለም ውስጠቴ
አልቻልኩም እናቴ

አንቺ ያገር ተስፋ ኩርምት ላለው እግርሽ
ኮንጎ የተጫማሽው
ለልጅሽ አይደለ? ይሄ ቆንጆ መልክሽ
በሻርብሽ ያጠርሽው
ምንል ጀግና እንደሆንሽ ቁንጅናሽን ሁሉ
በመስታወት ባየሽው

አንቺ ውብ ኮረዳ
አንቺ ያገር ተስፋ

ራስሽን ቀብረሽ  በልጅሽ ህይወት ላይ
በሳልሽው ማንነት
በቀሚስሽ እድፈት ባጥንትሸ ስጥመት ውስጥ
አየሁ አናትነት

አጥንትሽ ቢቆጠር ስጋ ሸሽቶት ኖሮ
ምን ቢከሳ አካልሽ
ይኸው ይታየኛል አልበገርም ባይ
ታጋይ ማንነትሽ

እናቴ

ልክ ልጅሽ ሲተኛ
ስንት ለሊት ይሆን
አንገትሽን ደፍተሽ ስታለቅሺ የኖርሽው
ስንት ፊቶች ይሆን
ልጅሽን ለማኖር ስታይ የቆየሽው
እኔ አንገቴን ልድፋ
የኔ አካል ይገፋ
ምነው ቢያስቀረኝ
አንቺን ከሚያሳየኝ

ተሰማኝ ህመምሽ
ከበደኝ ሸክምሽ
ጨነቀኝ ጭንቀትሽ
ተሰማኝ መዝሙርሽ
አስለቀሰኝ እንባሽ

የመከራን ዘመን ከላይሽ ነጥቄ
ደስታን እንደለብስሽ
ከናትነትሽ ጋር ኑሪና በህይወት
ነገዬን ላውስሽ
Reposted from:
ታዖርያ avatar
ታዖርያ
14.05.202519:32
i miss my ልጅነት🥹🥹


ትዝ ይለኛል 16 አመቴ ነበር ቀኑ አርብ ነበር ከትምህርት ቤት ተመልሼ መጥቼ ቁጭ ብዬ ነበር ለምን እንደሆነ በማላውቀው ጉዳይ ብቻ በሀሳብ ማዕበል ተጉዤ ልጅ እያለሁ እናቴ ፍንደቅ ብዬ ልቤ እስኪጠፋ ስጫወት አልያም እዚህ ግባ የማይባል ነገር ሲያስለቅሰኝ ታይና


"ምፅ አይ ልጅነት" ትልና ......"እንደው አይመለስ" ትላለች ......እኔም ቡረቃውን ወይ ለቅሶውን እቀጥላለሁ እንደው በሀሳብ እንደሄድኩ ትዝ አለኝ ..ግን...
ያኔ እህህ

......

ሳስበው ሳቄ ይመጣል እንዴት ሰዉ ልጅነት ይናፈቅዋል???
አልኩ ቀጠል አረኩና ሰው እንዴት ቁጥጥር ይናፍቀዋል???
አልኩ አይ እማ ሞኝ ናት ልበል አልኩ (እንደሱም ያለ ነፃነት አልነበር)... ነገሩ ገና አልገባኝም ነበር ....."አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል"... ነበር ለካ አለማወቄ ነበር አሁን ነዉ የልጅነት ጥቅሙ የገባኝ ለካስ ፍፁም ነፃ አለም ነበር ...ለካስ ፍፁም አለማወቅ ጥሩ ነበር ........ለካስ ወጣትነት እስር ቤት ነዉ.......ለካስ ማወቅ ሀሳብ ነው ...ለካስ ጎልማሳነት የብዙ ሰዎች ሀላፊነት ነው .....ለካስ ቤተሰብ መምራት ነፃነት ማጣት ነዉ .....ለካስ እርጅና ምርኩዘ የመያዝ ጭንቀት ነዉ ....ሀሳቡ ብዙ ነዉ
ያኔ 16 አመት እያለሁ ምን ሆና ነው የናፈቃት ያልኩት ያ እስርቤት የመሰለኝ ልጅነት ፍፁም ነፃነት ነበር አለማወቅ ሰላም ነበረው ማወቅ ለካስ ጭንቀት ነገን ማሰብ ነው አሁን ሳስበው አለመብሰሌ ነበር እናቴ ሞኝ መስላ እንድትታየኝ ያረገኝ ከመናፍቅ በላይ መናፍቅም የሚገባው ህይወት ልጅነት ነው ።

ልጅነቴን ከምናፍቅባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ቦርቄ መጥቼ እግሬን ሰቅየ ጧ ብዬ የምተኛበት ግዜ ነበር



....''አይ ልጅነት እንደው አይመለስ''.........



Taorya ✍️✍️



https://t.me/taoriia
11.05.202504:15
Happy mother's day for all mother's
.
.
.
.
🥰🙌
Reposted from:
ታዖርያ avatar
ታዖርያ
10.05.202519:55
some days አንዳንድ ሰዎች እንደወፈ ናቸው እንዴት መብረር እንዳለባቸው ታስተምራቸዋለህ ልክ መብረር ሲጀምሩ ይወደዱብሀል



taorya ✍️✍️



https://t.me/taoriia
12.05.202504:27
ብቻ ምን አለፋክ ዛሬ አንተ ያለክን የሚመኙ እና እሱን ለማግኘት ዘወትር የሚፀልዩና የሚለምኑ ብዙ ሺዎች አሉና ሁሌ ከምኝታክ ስትነሳ ማመስገን አትርሳ

ለማንኛውም ነግቷል! ዛሬ ጥዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ድንቅ ሰው እንደሆንክ እና ራዕይህ ከፊትህ እንዳለ ተራ ሰው ሆነህ እንደማትሞት ታሪክ ተናጋሪ ሳይሆን ታሪክ ሰሪ እንደሆንክ ካልተሰማህ አንተ  ጋር አልነጋም ማለት ነው ተመልሰህ ተኛ!
!!
Log in to unlock more functionality.