Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
መዝሙር ቲዩብ™ avatar

መዝሙር ቲዩብ™

👋🇪🇹እንኳን ወደ መዝሙር ቲዩብ በሰላም መጡ::
✟የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የጠበቁ፦
➻ የተለያዩ ትምህርቶች የሚሠጡበት፤ መዝሙሮች እና ግጥሞች የሚለቀቁበት፤
➻ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎችን የምናገኝበት ቻናል ነው።
®️ ማንኛውንም ጥቆማ አስተያየት✆ @emebtemariyam21bot

🎙️መዝሙር ቲዩብ ❷❍❶➆
Рэйтынг TGlist
0
0
ТыпПублічны
Вертыфікацыя
Не вертыфікаваны
Надзейнасць
Не надзейны
Размяшчэнне
МоваІншая
Дата стварэння каналаFeb 06, 2024
Дадана ў TGlist
Apr 20, 2025
Прыкрепленая група

Апошнія публікацыі ў групе "መዝሙር ቲዩብ™"

[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱
[  ረቡዕ  ] - አልአዛር ይባላል ፦

በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱
📌ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ«እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።
የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ  ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....READ MORE
🎁 ልዩ የበዓል ስጦታ
.
.
... see more 🎁
ከትንሳኤ በኃላ ያሉት እለታት ስያሜ

1, ሰኞ– ማዕዶት (ፀአተ ሲኦል)

ማዕዶት የቃሉ ትርጓሜ መሻገር ሲሆን፤ በዚህ ቀን ቤተ ክርስቲያን ነፍሳት በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከሐሳር ወደ ክብር፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት መሻገራቸውንና ፉሲካችን ክርስቶስ መሆኑን ታስባለች::

📲 @mezmurortodox21📱
📲 @mezmurortodox21📱
#እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤ አደረሳችሁ

            ✨ «ትንሣኤ» ✨
የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡
«ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
«ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡
          አከፋፈል
✨አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡

✨ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡ የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡

✨ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡

✨አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡ የእርሰ ትምህርታችንም መሠረት ይኸው እንደሆነ ይታወሳል፡፡

✨አምስተኛውና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡

☦#የትንሣኤ በዓል በቃሉም ምስጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡ «ፋሲካ» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ «ፌሳሕ» በጽርእ በግሪክኛው «ስኻ» ይባላል፡፡ ይህም ወደ እኛው ግእዝና ዐማርኛ ቋንቋችን ሲመለስ ፍሥሕ ዕድወት = ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣ እየተቸኮለ የሚበላ #መሥዋዕት፣ #መሻገር #መሸጋገር ማለት ነው፡፡

☦#ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነት የተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹም ደሰታ፣ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል «ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡

☦#ፋሲካ፣ በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ እስራኤል ዘነፍስ የሆኑት ምእመናነ ክርስቶስ ትንሣኤውን የሚያከብሩበት ዕለት ሆኖ በእርሱ ትንሣኤ #ከኀጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከኀሳር = ከውርደት ወደክብር፣#ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደ #ዘለዓለማዊ ነፃነት፣ #ከአደፈ፣ #ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወት ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገሩበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡

☦#ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት ያከብሩታል፡፡ ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡
          #ባህሉስ
ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባባለ በመጠራራት ዐብሮ ሲበላ ሲጠጣ ልዩ ልዩ ጨዋታ ሲጨዋወት ለንስሐ አባትና ለሽማግሌዎች ለወዳጅ ዘመድም የአክፋይ ዳቦ፣ ወይም የሥጋ ወጥ ግፍልፍል ሲወስድ ይሰነብታል፡

አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!

@emebtemariyam21bot

📲 @mezmurortodox21📱
📲 @mezmurortodox21📱
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''

''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''

ውድ መዝሙር ቲዩብ™ ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።
መልካም በዓል ለናንተ ይሁን አምላከ ቅዱሳን መልካሙን ዘመን ጊዜ ያምጣልን በህመም በ ፀበል በሆስፒታል በ ቤት ያሉትን በችግር በሀዘን በስቃይ በስደት ያሉትን አምላከ ቅዱሳን ያስብልን ምህረት ይቅርታን ፍቅርን ያድልልን መልካሙን ጊዜ ያም ጣልን በሰላም ለትንሳኤው ያድርሰን  
     
  🌺  መልካም ጊዜ🙏🏾

Рэкорды

23.04.202502:31
31.2KПадпісчыкаў
19.04.202515:29
33Індэкс цытавання
20.04.202523:59
312Ахоп 1 паста
20.04.202511:29
359Ахоп рэкламнага паста
16.04.202517:13
2.67%ER
20.04.202515:29
1.00%ERR

Развіццё

Падпісчыкаў
Індэкс цытавання
Ахоп 1 паста
Ахоп рэкламнага паста
ER
ERR
MAR '25MAR '25MAR '25APR '25APR '25APR '25

Папулярныя публікацыі መዝሙር ቲዩብ™

20.04.202506:00
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''

''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''

ውድ መዝሙር ቲዩብ™ ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።
18.04.202504:43
"ስቅለት - ኑ እንስገድለት"
ኪራላይሶ አቤቱ ይቅር በለን!
እንደ ቸርነትህ እንደ የኛ ኃጢያት ሳይሆን።
እንስገድ ለእግዚአብሄር እንፀልይ እንፁም፣
እሱ የልብን ያያል እኛ ባናየውም።
ለንስሀ ጊዜ ለሁላችን ሰጥቶን፣
የዛሬዋን ዕለት ማየት ስለቻልን፤
የፈጠረን ጌታ እግዚአብሔር ይመስገን።
ስለሰው ልጅ ብሎ መውደዱ ፀንቶበት፣
ከርሱ ጋር ሊያኖረን በዘላለም ሕይወት፣
ከኃጢአት ሊያነጻን ወደደን እስከ ሞት።
ሲገርፉት ሲወግሩት ሁሉን እየቻለ፣
የዓለማት ጌታ በመስቀል ላይ ዋለ።

ኪራላይሶ አቤቱ ይቅር በለን!
እንደ ቸርነትህ እንደ የኛ ኃጢያት ሳይሆን።

ምን አይነት ፍቅር ነው የጌታ ውለታ፣
የኛን ሞት በመሞት ሞትን ድል የመታ።
የመስቀሉን ሚስጥር ማነው የሚፈታው፣
ጌታ ያስተማረን ፍቅር ማለት ይህ ነው ።
ምሳሌ የሆነን በፍቅር እንድኖር፣
ተነግሮ የማያልቅ እውነት ታላቅ ሚስጥር፤
እውነት ማለት ጌታ እሱ ነው እግዛብሄር ።
ሆኖም ሰዎች ዛሬም የሱን ህግ እየሻርን፣
ከዘፍጥረት ጀመርን - ምፅዓት ላይ ደረስን።

ኪራላይሶ አቤቱ ይቅር በለን!
እንደ ቸርነትህ እንደ የኛ ኃጢያት ሳይሆን።

አቤት ክፋታችን ምህረቱን ይስጠን፣
ይቅርታው ብዙ ነው እግዚኦ ይማረን።
ለእግዛብሄር ክብር ዘወትር ጧት ማታ፣
ኑ እንስገድለት ለታላቁ ጌታ፤
ስግደት ያንስበታል ለዋለው ውለታ።
ኪራላይሶ ጎብኘን ጌታሆይ በል ይቅር፣
እማጸንሃለው ወድቄ ከእግርህ ስር።
አንተ እንዳከበርከኝ እስኪ እኔም ላክብርህ፤
ለሠጠኸኝ ፍቅር እንዴት ልሁንልህ።
ላንተ ክብር ሢባል እኔን ብታስችለኝ፣
እኔን ይደብድቡኝ እኔንም ይግረፉኝ፤ እኔን ያንገላቱኝ ይዘባበቱብኝ፣
አኔን ውሃ ይጥማኝ ሆምጣጤ ያጠጡኝ፤
በረሃብ በውሃ ጥም አሠቃይተው ይግደሉኝ፣
አምናለሁ አምላኬ ሥትመጣ በክብርህ እንደምታስበኝ።
       
ኪራላይሶ አቤቱ ይቅር በለን!
እንደ ቸርነትህ እንደ የኛ ኃጢያት ሳይሆን።

ወርቅ ላበድረ ጠጠር ሆኖ ትርፉ፣
በደልን አረጉ ሠዎች ሆነው ክፉ።
በደነደነ ልብ እጅግ በጨከነ፣
ወደፊት የማይሆን በሠው ላይ ያልሆነ፤
ለኛ ሢል ክርሥቶሥ ግፍን ተቀበለ፤
ሥለ የሰው ልጅ ፍቅር በመሥቀል ላይ ዋለ።
አይሁድ በሀገራቸው አይሁድ በጊዜያቸው፣
በጌታ ላይ ፈርደው አሳልፈው ሠጥተው፤
በጅራፍ ገረፉት ወደኋላ አሥረው ።
መሥቀል አሸክመው ወዲያ እየጎተቱ ወዲ እየሳቡት፣
የአለማት ጌታን እንዲያ እያንገላቱት፤
ማንም የማይችለውን የቻለውን ጌታ፣
አሠቃይተው ወሥደው ሠቀሉት ጎልጎታ።

ኪራላይሶ አቤቱ ይቅር በለን!
እንደ ቸርነትህ እንደ የኛ ኃጢያት ሳይሆን።

ሮዳሥና አዴራ ዳናትና ሣዶር እንዲሁም አላዶር ፣
እጅና እግሮቹን ወገቡን ደረቱን ቸንክረው በምሥማር ፤
የሾህ አክሊል ደፍተው ሆምጣጤ አጠጡት፣
ምራቅ እየተፉ ተዘባበቱበት።
እራሡን በመቃ ፊቱንም በጥፊ አይሁድ እየመቱት፣
ይህም ሣያንሣቸው ጎኑን በጦር ወግተው ደሙን አፈሰሱት።
       
ኪራላይሶ አቤቱ ይቅር በለን!
እንደ ቸርነትህ እንደ የኛ ኃጢያት ሳይሆን።

ይህን ሁሉ ሥቃይ መከራ ሢቀበል፣
አንዴ መጥቷልና በደልን ይቅር ሊል፤
እንዲያ ሢያስቃዩት ችሎ ዝም ብሏቸው፣
እየከፋ ሢሄድ ይኸው በደላቸው፤
የሚያስደንቅ ፍቅር ጭራሽ ወደዳቸው፣
ለመነላቸውም ፍቅሩ ቢያስገድደው፣
ምን እንደሚያደርጉ አያውቁትምና እያለ ማራቸው።

ኪራላይሶ አቤቱ ይቅር በለን!
እንደ ቸርነትህ እንደ የኛ ኃጢያት ሳይሆን

📲 @mezmurortodox21📱
📲 @mezmurortodox21📱
መልካም በዓል ለናንተ ይሁን አምላከ ቅዱሳን መልካሙን ዘመን ጊዜ ያምጣልን በህመም በ ፀበል በሆስፒታል በ ቤት ያሉትን በችግር በሀዘን በስቃይ በስደት ያሉትን አምላከ ቅዱሳን ያስብልን ምህረት ይቅርታን ፍቅርን ያድልልን መልካሙን ጊዜ ያም ጣልን በሰላም ለትንሳኤው ያድርሰን  
     
  🌺  መልካም ጊዜ🙏🏾
Пераслаў з:
ኢትዮ መረጃ - NEWS avatar
ኢትዮ መረጃ - NEWS
ሰውን በገንዘብ የሚሸጥ ትውልድ ይሁዳን ማማት አይችልም” ብጹዕ አቡነ አብርሃም‼️

እንደ ይሁዳ ሁሉ ዛሬም የንፁሕ ደም የሚያፈስሱ፤ ንጹሕን አሳልፈው የሚሰጡ፤ እውነተኛውን ጻድቁን የሚያስገደሉትን ኢትዮጵያ መታቀፏን ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡

ንጹሕ ደም ማፍሰስ፤ ጻድቁን አሳልፎ መስጠት ምንም እንደማይጠቅም ከይሁዳ እንማር፤ በደላችንን አምነን አምለካችን ኾይ ማረን እንበለው ብለዋል፡፡

ይሁዳ ለራሱ ቢጎዳም ለእኛ ግን አስተምሮናል ነው ያሉት፡፡ እኛ ከይሁዳ መሻል አለብን፤ ዛሬ ላይ እንደ ይሁዳ ሰው የሚሸጥበት ዘመን ደርሰናል፤ "ሰውን በገንዘብ የሚሸጥ ትውልድ ይሁዳን ማማት አይችልም" ብለዋል። ከይሁዳ የተሻለ ትውልድ አልተገኘም፤ ከልብ ጸጸት የሌለበት፤ የከንፈር ብቻ ጽድቅ ያለበት ዘመን ነው ብለዋል፡፡

ሕሊናቸውን ለእግዚአብሔር የተሰጡ፤ ከዓለም የተገለሉ፣ ደጋግ ሰዎች ስላሉ በቸርነቱ እንኖራለን ነው ያሉት፡፡

በድያለሁ የሚለውን እንመን ያሉት ብጹዕነታቸው አምላክ በድለነው ሳለ ለእኛ መከራ ተቀብሏል፤ እኛ ግን በድለንም በድለናል አንልም ብለዋል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ግርጌ እናት ሰጥቶናል፤ ያለ እናት አልተወንም ነው ያሉት፡፡ ስለ ሰላም እንጸልይ፤ ስለ ሀገራችን እንጸልይ፤ ክርስቲያን ስለ ዓለም ሁሉ ይጸልያልና ስለ ዓለም ሁሉ እንጸልይ፤ የተፈናቀሉትን እንዲመለሱ፤ ሰላም እንዲነግስ፤ ንጹሕ ደም መፍሰስ በቃ እንዲለን ተግተን እንጸልይ በማለትም ብፁዕነታቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

@Sheger_Press
@Sheger_Press
20.04.202506:04
#እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤ አደረሳችሁ

            ✨ «ትንሣኤ» ✨
የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡
«ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
«ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡
          አከፋፈል
✨አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡

✨ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡ የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡

✨ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡

✨አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡ የእርሰ ትምህርታችንም መሠረት ይኸው እንደሆነ ይታወሳል፡፡

✨አምስተኛውና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡

☦#የትንሣኤ በዓል በቃሉም ምስጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡ «ፋሲካ» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ «ፌሳሕ» በጽርእ በግሪክኛው «ስኻ» ይባላል፡፡ ይህም ወደ እኛው ግእዝና ዐማርኛ ቋንቋችን ሲመለስ ፍሥሕ ዕድወት = ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣ እየተቸኮለ የሚበላ #መሥዋዕት፣ #መሻገር #መሸጋገር ማለት ነው፡፡

☦#ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነት የተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹም ደሰታ፣ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል «ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡

☦#ፋሲካ፣ በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ እስራኤል ዘነፍስ የሆኑት ምእመናነ ክርስቶስ ትንሣኤውን የሚያከብሩበት ዕለት ሆኖ በእርሱ ትንሣኤ #ከኀጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከኀሳር = ከውርደት ወደክብር፣#ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደ #ዘለዓለማዊ ነፃነት፣ #ከአደፈ፣ #ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወት ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገሩበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡

☦#ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት ያከብሩታል፡፡ ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡
          #ባህሉስ
ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባባለ በመጠራራት ዐብሮ ሲበላ ሲጠጣ ልዩ ልዩ ጨዋታ ሲጨዋወት ለንስሐ አባትና ለሽማግሌዎች ለወዳጅ ዘመድም የአክፋይ ዳቦ፣ ወይም የሥጋ ወጥ ግፍልፍል ሲወስድ ይሰነብታል፡

አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!

@emebtemariyam21bot

📲 @mezmurortodox21📱
📲 @mezmurortodox21📱
19.04.202505:25
                         †                         

🕊    †      ቀዳም ሥዑር    †     🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

†  ቀዳም ሥዑር  [ የተሻረች ቅዳሜ ]  †

--------------------------------------------------

የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት ፦

[    ቀዳም ሥዑር     ]  ፡-

በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር [ የተሻረች ] ተብላለች፡፡ በዓል መሻርን አይመለከትም፡፡ በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡ በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

-----------------------------------------------

[     ለምለም ቅዳሜ    ]  ፦

ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል [ ቃለዓዋዲ ] እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡

[ የቄጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)

-----------------------------------------------

[    ቅዱስ ቅዳሜ    ]  ፡-

ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

[  ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ  ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

📲 @mezmurortodox21📱
📲 @mezmurortodox21📱
20.04.202517:03
ከትንሳኤ በኃላ ያሉት እለታት ስያሜ

1, ሰኞ– ማዕዶት (ፀአተ ሲኦል)

ማዕዶት የቃሉ ትርጓሜ መሻገር ሲሆን፤ በዚህ ቀን ቤተ ክርስቲያን ነፍሳት በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከሐሳር ወደ ክብር፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት መሻገራቸውንና ፉሲካችን ክርስቶስ መሆኑን ታስባለች::

📲 @mezmurortodox21📱
📲 @mezmurortodox21📱
23.04.202519:48
[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱
23.04.202517:03
[  ረቡዕ  ] - አልአዛር ይባላል ፦

በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
23.04.202516:57
[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱
23.04.202516:45
📌ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ«እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።
የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ  ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....READ MORE
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.