Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
...ነጠብጣብ ✨💙 avatar

...ነጠብጣብ ✨💙

✨ትዝታማ አለሽ
የለኝም ብትይኝ እኔም አላምንሽም
በህይወት መንገድ ላይ
ተራምደሽ ሳታልፊ ዛሬ ላይ አልቆምሽም፨
ህይወት ያለ ታሪክ
ቀን ያለ ጨለማ መች ቶሎ ይመሻል
ሰዉ ስለሆንሽ ብቻ
ለሰዉ ምታወጊዉ ቅፅበት ይኖርሻል፨
ትዝታ አለሽ?አዉጊኝ
ትዝታ አለኝ!ላዉጋሽ
..እንዲህ ብናወራስ...ቅፅበታት እናዉጋ.. የልብ ንግግሮችም አይታጡም..ግቡ💙
ለአስተያየታችሁ @bluessoulmate
Рэйтынг TGlist
0
0
ТыпПублічны
Вертыфікацыя
Не вертыфікаваны
Надзейнасць
Не надзейны
Размяшчэнне
МоваІншая
Дата стварэння каналаJul 17, 2024
Дадана ў TGlist
Sep 11, 2024
Прыкрепленая група

Рэкорды

14.04.202523:59
1KПадпісчыкаў
28.02.202523:59
400Індэкс цытавання
18.01.202514:55
599Ахоп 1 паста
05.04.202523:59
965Ахоп рэкламнага паста
01.03.202523:59
16.13%ER
14.09.202423:59
123.61%ERR

Папулярныя публікацыі ...ነጠብጣብ ✨💙

08.04.202508:19
✨✨ሞገደኛው ነውጤ - 1✨✨

ትረካ ሲባል ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው ወጋየው ንጋቱን ነው። ምንም እንኳን በሱ ዘመን ኖሬ ስለሱ ባላውቅም ደጋግሜ የሰማውት የፍቅር እስከመቃብር ታሪክ ድምፀቱ ልቦናዬን ይሰውራታል።

ሌላኛው እንቁ ደግሞ ጋሽ ፍቃዱ ተክለማርያም ናቸው። "ሞገደኛው ነውጤ" ደግሞ በጋሽ ፍቃዱ ድምፀት አብዝቼ የምወደው ትረካ ነው።

ከ እነ ድምፀቱ የባለሃገርን የዋህነት፣ ገራገርነት ቁልጭ አድርጎ አበራ ለማ በመቆያ መጽሃፉ ላይ ፅፎት ጋሽ ፍቃዱ ተክለማርያም በግሩም ድምጸት ተርኮታል።

ተጋበዙልኝ ክፍል አንድ'ን


https://t.me/yeesua_queen
30.03.202510:49
✨✨የልቤ ልቧ ነሽ

ነፍሴን እየሞቃት ነው የምወድሽ
ስትናፍቂኝ የምርም ነው
ከአንቺ ጋር መኖርን እወደዋለሁ

ለአንቺ መኖር ትርጉም ይሰጠኛል
እያንዳንዷን ቀን የተኖረ ነው ጓደኝነታችን
የሌለሽበት ቦታ የለኝም
ልቤን እስኪከብዳት ድረስ ነው 'ምወድሽ
እንኳን ተወለድሽልኝ!!

ታድዬሻለሁ ..'ወድሻለሁ


🦋ልቤ ውስጥ ነሽ በቃ ላወጣሽ አልችልም።ታውቂዋለሽ አውቀዋለሁ የሌለሽበት ገጽ የጎደልሽበት ቀን የለኝም ፨
ለመኖሬ የምርም ሕይወት ትሰጪኛለሽ...ከአንቺ  ጋር መኖር  ሰላም አለው..ሲደክመኝ እንኳን ሳስብሽ እንዳለሽልኝ ሳስታውሰ እበረታለሁ...የሕይወቴ እጅግ ውብ አጋጣሚ ነው አንቺን የሰጠኝ....አምላኬ እንደሚወደኝ ከማውቅባቸው ገፆቼ መኃል ነሽ....

በዚህ ልክ ሰው መውደዴን የማውቀው አንቺ ጋር ነው።ባትኖሪልኝ ምን አይነት እኔን አንደምሆን አላውቅም።የቱ ጋር ምኔ ጋር እንደሆንሽ አላውቅም..የሕይወቴን ደማማቅ ቀናቶች የማስበው ከአንቺ ጋር ነው።

ቃላት ሆኖላቸው እቺን መግለጽ ባይችሉም ሃሳቤን በስሱም ቢሆን ሊነግሩሽ ጉድ ጉድ ሲሉ ማየት ቆንጆ ነው፨


እንኳን ተወለድሽልኝ:እንኳንም አወኩሽ እንኳንም ተሰጠሽኝ እንኳንም ጓደኛዬ...እህቴ ታላቄ ሆንሽልኝ


እ'ወድሻለሁ እሳሳልሻለሁ  የከፍታ ቀናቶችሽ ላይ ላይሽ እመኛለሁ የመውደድ ጥጌ ነሽ....ሁሌም ሳቂልኝ...ወድሻለሁ

💙💙💙


መልካም ልደት ጓደኛዬ....🤍🤎

https://t.me/yeesua_queen
02.04.202507:34
✨...ምንድን ነው እንደዚህ መልፈስፈስ? ምንድን ነው እንደዚህ ቶሎ መሸነፍ ?ምንድን ነው የነካችሁ?

ማን ነን እኛ?

ዘመነኞችሽ! እኩዮችሽ!!

ቶሎ መደሰት:ቶሎ ማዘን:ቶሎ መፈንጠዝ:ቶሎ መተከዝ:ወዲያው ስኬት:ወዲያው ደስታ:ወዲያው ተስፋ መቁረጥ እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት ማለት እኔ...እኔ...እኔ...
አቋራጭ...አቋራጭ...አቋራጭ...ከጠፋ ክልትው?! ምንድን ነው እንደዚህ ማነስ?ምንድን ነው እንደዚህ መልፈስፈስ?

እኔ የማውቀው የራሴን ብቻ ነው! ደግሞ ሕይወትን መቀጠል ካልተቻለ መኖር ግዴታ አይደለም።

መኖር ግዴታችን ነው ሁላችንም!!የሞተ ተጎዳ ብሎ ነገር የለም።ሁላችንም ነን የምንጎዳው።ሁላችንም ነን የምንጎድለው።አንዴ መጥተናል የመጣንበትን ሳንጨርስ በራስ ፈቃድ በራስ ቀን መሔድ እፍርታምነት ነው!!

የሚያስከፋን ጠፍቶ:ተስፋ የሚያስቆርጠን አጥተን አይደለም የምንኖረው።መኖር ግዴታችን ስለሆነ ነው።አለበለዚያማ እፍርታምነት ነው!

እፍርታምነት?

አዎን እፍርታምነት!!ኑር እኔም እኖራለሁ ብሎ ጨዋታ ውስጥ ከገቡ በኋላ ጨዋታው ሲከብድ ወይም በግብ ሲመሩ በክፉ በደጉ ያልተለየውን ሰው ሁሉ ደጋፊ የራሱ ጉዳይ ነው ብሎ ከጨዋታ መውጣት እፍርታምነት ነው።

ሕይወት ጨዋታ አይደለማ !!

አዎን ሕይወት ጨዋታ አይደለም!!ሕይወት ሲፈልጉ የሚያቋርጡት ሲያሻ የሚቀጥሉት ጨዋታ አይደለም።ከፈጣሪ ጋር ከሰውም ጋር የሚገቡት ግዴታ አለበት።ራስን ማሰናበት ቀላል ቢመስልም በውስጡ ያለው ፍርሃትና ጭካኔ ግን ሰብዓዊ አይደለም።

በእናት ጨክኖ: በእህት ወንድም ጨክኖ:በወዳጅ ዘመድ ጨክኖ: ከሁሉ በላይ በራስ በክቡር ሰውነት ላይ ጨክኖ የፈሪ ድርጊት ነው።አንቺም ፈሪ ነሽ!!

ፈሪ ለእናቱ..

ለእናት መሆን እንዲህ ነው እንዴ....???


#አጋፋሪ

https://t.me/yeesua_queen
24.03.202504:20
አንዳንዴ ህይወት ያደክመናል ምንወዳቸውን እንጠላለን ማለፍ  ያምረናል። ነገሮች ሁሉ ሚጠሙብን እኛን ብቻ ይመስለናል። አውቆ አልሳካ ይላል የነበረው በትንሽ ንግግር ሊያውም እንደቀልድ በተናገርነው  የስንት ጊዜ ልፋት በዛች ትንሽዬ ስንኝ ይፈርሳል ጥፍት እንዳልነበር ይሆናል ያ ሲያናድደን የነበረን ይሸሸናል ይርቀናል እንደማይተዋወቅ ባስ ሲል እንደ ጠላት መተያየት እንደዚህ ሚሰማን ጊዜ ይደጋገማል ያስጠላል ግን አልፏል ሚመጡትም ያልፋሉ የሚያሳልፍ ፈጣሪ ስላለን ተመስገን🙏🏾🩵

https://t.me/yeesua_queen
07.04.202509:44
✨✨✨.........ችግሬን ሁሉ በመደበቅ እሸሻት ይመስል ኮሽ ባለኝ ቁጥር መሮጥ መሸሽ ከአለም መደበቅ ያምረኛል። መዞር እወዳለው። ድንገት ተነስቼ ከአለም እሰወራለው........... ከዛ ራሴን  አንድ ተራራማ ቦታ አገኘዋለው።
.........ከዓለም መሸሸግ አምሮኝ  ኮፊያ ያላትን ጃኬቴን(ሁዲ) ብቻ ተከናንቤ ነበር የወጣሁት። በመኪናው ጥጋት ላይ ተቀምጬ መስኮት መስኮቱን ሳማትር ነው። የተዋወቅኳት። በትከሻዋ ተጠጋልኝ አይነት ነገር ስታሳብቅ ነበር። የባጥ የቆጡን አላወራንም ሰው ሁሉ አጠገቡ ካለው ጋር ሲሳሳቅ ሲጨዋወት ዞርም ብዬ አልገረመምኳትም። ለማውራት በሚመስል ቅላጼ በየቆይታው ድምጽዋን ትጠርጋለች። ዓለምን ሽሽት  ድምጼን ሳላሰማ በአርምሞ ጉዞ ላይ ነኝ። ድንገት እንደመደገፍ አይነት መጥታ ትከሻዬ ላይ ጋደም አለችበት። ምቾት አልነሳኝም አልቆረቆረኝም።

ደቂቃዎች ደቂቃዎችን እየወለዱ ሳታስበው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ከትማለች ትከሻዬን የያዘችው አያያዝ አትልቀቀኝ አይነት ጥብቅ አድርጋ ነው። ከነፍሴ ነው ምወድህ አይነት ነገር.......የሲሳይ ንጉሱ ወጉን የጀመረ ያክል ምተውን መሰለኝ!

ጠይም ናት መልከ ስሯዋ አነጋገሯ ሁሉ ያቺ ሰመመን በብእሩ የሳላት  አቤልን በፍቅር ክንፍ ያደረገችው ትዕግስትን ትመስላለች። "ጠይም ናት ፤ ካውያ ያልነካው ፀጉርዋ ከማጅራቷም ባያልፍ ለማበጠር የሚያስቸግር አይነት አይደለም። ቁመቷ አጭር ነው ፤ አለባበሷ እንደነገሩ ይመስላል ፤ ገና ሲያያት አጠገቧ ካሉት ልጃገረዶች ጋር በሆነ ጨዋታ ትሣሣቅ ነበር። ስትስቅ ጉንጮቿ ስርጉድ ይላሉ...

የሆነች ነፍስ ትከሻዬ ያመነች መሰለኝ እና ደስአለኝ። አምናኝ የተጠለለችብኝ መሰለኝ ሙሉ ሰው የሆንኩ መሰለኝ ። የግራ እጄን ኩምትር አድርጋ እንደያዘች በደስታ ፈገግ አልኩ ። በቀኝ እጄ ሉጫ መሳይ ጸጉሮቿን መዳበስ ያዝኩኝ ይበልጥ ተጠጋችኝ እንደ እናት ጉያ ሽሽግ አለችብኝ። እጄን አመቻችቼ አቀፍኳት  መኪናው እንዳያንገላታት ይበልጡኑ ወደራሴ ሳብኳት። ታሳዝናለች ራሴን በሷ ውስጥ ሳልኩት። ያመንኳቸው የተደገፍኳቸው እንዲህ ቢያቅፉኝ ብዬ ተመኘው። ለምንድን ነው የምወደው ነገር ሳፈጥበት ገሸሽ የሚለው ? ብዬ አፈጠጥኩባት የሆነ ምታደምጠኝ ያህል ተሰምቶኝ በአርምሞ እጠይቃታለው የምጠላው ሳይቀር እኮ መውደድ ስጀምር ጥላ ያጠላበታል ። እያጡ ማዘን እኮ  ደከመኝ። ተረግሜ  ፣ተደግሞብኝ  ወይ ደግሞ አይነጥላ ይሆን?  እንጃ? በስስት አይኔ እያየዋት በስሱ ግንባሯን ስስማት ነቃች። ሰርቆ እንደተያዘ ሌባ ቅብዝብዝ አልኩ። እጆቼን በፍጥነት ሰበሰብኩ ደግሜም ማየት አሳፈረኝ..........
እሷ ግን ዓይኗን መግለጥ የፈራች ይመስል እዛው እኔን ላለማየት ዓይኖቿን ጨፍና ትንሽ ቆየች በአንድ ዓይኗ አጮልቃ ወደኔ አየችኝ:: መልሳ አይኗን አላዞረችም። ረጅም ዝምታ ውስጥ ድረስ ሚሰብር ዝምታ.........ምን እያሰበች ይሆን?.......

የመጋቢትን የሚጋረፍ ቀዝቃዛ አየር  ለመከላከል ሁዲዬን እስከላይ ድረስ ተከናንቤው ከመኪናው ወረደኩ፡፡ እንደ ጩቤ የሚዋጋው ብርድ ነበር የተቀበለኝ፡፡
ሁለት እጆቼን  የሱሬዬ ኪሶች ውስጥ ከትቼ ወደተራራማዋ ቤቴ  መገስገሴን ተያያዝኩ...............


✍ዮዳሄ
https://t.me/yeesua_queen
Пераслаў з:
ኖኅ Book Delivery avatar
ኖኅ Book Delivery
27.03.202504:40
እውነት ለመናገር እሱን ነው ማግባት የምፈልገው።

ጨዋ ነው ፣
ኋላፊነት መውሰድ ይችላል ፣
አይጨቃጨቅም፣
የስራ ሰው ነው፣
ባል መሆን የሚችል አይነት ነው፣

ግን ማግባት ከበደኝ። አልቻልኩም!!

ረብሻ ለምጃለሁ መሰለኝ፣ ትንሽ የሚቀና ፣
ደመ ሞቃት ፣ሳጠፋ የሚናደድ ሰው  እፈልጋለሁ፣ በቅናት ውስጥ መውደድ እንደሚታይ የማምን ነኝ።  ትንሽ ቆፍጠን የሚል ነው የምፈልገው ።

ከሱ ጋር ስሆን ጊዜው አይሄድም፣ አይናፍቀኝም። እወድሻለሁ የሚለኝን መንገድ አልወደውም። የሴት ቋንቋ አይገባውም።

የሚያኖረው ፍቅር ብቻ  ይመስለዋል። የሚያኖረው ሕግ እና ፍቅር ቦታ እየቀያየረ እንደሆነ አልተረዳም። ፍቅርን እንደ ስራ ነው የሚያየው መሰለኝ Formal ነገር ነው። ጨዋነቱ ነፃ እንዳልሆን ያደርጋል ።

ምን ተብሎ እንደሚታማ አላውቅም።... ግን ነብሴ ጋር አልደረሰም። አንዳንዴ ሲደውል ነው የማስታውሰው። ጉብዝናው፣ ጨዋነቱ ፣ መውደዱ ልቤ ላይ አልደርስ አለኝ...።

ስለሱ ሳወራ 'ጥሩ ሰው!' ነው ብቻ ነው የምለው...

የሆነ ነገር ሲፈጠር ልነግረው አልቸኩልም፤ የሚወደውን ነገር ለማድረግ አልጣጣርም። የሱ በመሆኔ ልቤ አይኩራራም።

ለካ 'አንተ ጥሩ ሰው ነህ! እኔ ለአንተ አልሆንም።' ብለው ሰዎች የሚለያዩት ለዚህ ነው።

የተሰማኝን ውስጣዊ ስሜት Shutdown ማድረግ አልተቻለኝም።

ሳሳዝን!!

ናፍቆት የሌለው ፤ መናፈቅ የሌለው፤ መጃጃል የሌለው ጥምረት ሁሉ ነገር ኖሮት፤ ካለ ጨው እንደተሰራ ምግብ ዓይነት ነው። ጓጉተው የማይበሉት  ዓይነት...

አንዳንድ ማጣፈጫ ድርሻው ከዋናው ግብዓት አይንስም!

አንዳንዴ ማብራራት የማንችለው ጉድለት ሲሰማን የምንለጎመው፤ የምንዋሸው ትዝብት ውስጥ እንዳንወድቅ ሰግተን ነው ለካ።

በርግጥ ጎደለብን  የምንለው ለሌላው ቅንጦት ሊሆን ይችላል !!
     © Adhanom Mitiku

⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
Пераслаў з:
መቅረዝ avatar
መቅረዝ
23.03.202519:36
✨✨እንዴት አመሻችሁ!! ዕለተ ሰንበት ሸጋ አለፈች?😊
ዛሬ በቃላችን መሰረት አንድ ቻሌንጅ አዘጋጅተናል እናንተን የሚያሳትፍ.......

ይህም ቻሌንጅ የወግ(የስነጽሁፍ) ቻሌንጅ ነው። ደጋግ ሰዎችን ምናወድስበት ለዛሬ መቆማችን ምክኔያት የሆኑን ክብር ምንሰጥበት ቻሌንጅ ነው።

ጽሁፉ ሁለት አንቀጽ ያለው መሆን አለበት። አጭር ልብወለዱ ወይም ወጉ የሚለየው ነገር የሁላችንም ፅሁፍ የሚጀምረው አልያም ደግሞ የሚጨርሰው በተመሳሳይ አረፍተ ነገር መሆኑ ነው።
በዚህች ቃል " ክብር ላንተ/ቺ ለዛሬ መቆሜ ሞገስ ለሆንከኝ/ሽኝ" በሚል ቃል ነው። ይህ ቃል መጀመሪያ አልያም መጨረሻ ላይ መግባት አለበት።
ይህም ትንሽ ለየት ያሉ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።

፩ መጻሕፍ (Hard copy)
፪ package
፫ Admin

ይህ ቻሌንጅ ቤታችንን 1.5K ስትገባ መቋጫ ይሆናል። ፀሃፊያንን ጽሁፋችሁን
@Elnu_03 ማስገባት ይቻላል።
ዳኝነቱንም ባገኛችሁት ላይክ ብዛት ይሆናል። መልካም እድል

https://t.me/MekrezeTibebe
05.04.202519:42
ተማሪዎች ወደ ዚህ ቤት ጎራ እያላችሁ🌟💫

https://t.me/stuentsE
27.03.202518:42
“…..እንደምታውቁት ተፈጥሯችን ከአንድ ቦታ ተተክለን እንድንኖር ያስገድደናል፡፡ ይህ ውብ ተፈጥሯችን ግን የተለየ ጸጋ ነበር፡፡
ፈጣሪ ከአንድ ቦታ ተተክለን እንድንኖር አድርጎ ሲፈጥረን ትልቁ ምሥጢር ችግር መፍታት እንጅ ችግርን መሸሽ ተፈጥሯችን እንዳልሆነ ሲያጠይቅ ነበር…. እኛ እንደ እንስሳት ችግር በመጣ ጊዜ እየፈረጠጥን ከአንዱ ወደ አንዱ ልንሄድ አይገባንም፤ አያስፈልገንምም…….'

ፍካሬ
✍✍አለማየው ዋሴ
https://t.me/yeesua_queen
03.04.202512:45
ውስጠኛው እኔ -

ፃፊለት ፃፊለት ይለኛል፡😊
ታዲያ ልፅፍልህ እነሳና ምላሹን እፈራዋለሁ ፤ ዳግም እንዳይሰብረኝ ..
እንደበፊቱ መነሳት እንዳይከብደኝ ...😔

ምን ተሻለኝ ?


@poethaymi
Пераслаў з:
Thoughts avatar
Thoughts
07.04.202513:54
....የቀጠለ
ፀሃይ የዘረጋችውን ብርሃኗን አፋፍሳ እየሄደች ጨለማ መጣሁባችሁ ማለቻው ላይ.....ሲቃዥ እንደነበረ እራሴን ብንን ብዬ ነው ያገኘሁት.....እኔ ስለመሆኔም እጠራጠራለሁ....መንፈሴ ይሆን?.....ደንግጠው ተጠጉኝ...."ተረጋጊ እሺ ብርዬ ብርዬ ተረጋጊ" አቀፈችኝ  የባለቤቴ ሁለተኛ እናቱ የእናቱ ወዳጅ, ጓደኛ አብሮአደግ.....ለምንድነው ለምንድን ነው ጥቁር የለበሳችሁት ኤላሜስ ይሳ ይሳዬ ዋጋዬስ....አብረን አልነበርን? እየሄድን እየሄድን አልነበር?  መኪናው መኪናው ....የሚሉኝን የሚያረጉኝን አጡ....ከሁሉም አይን ላይ እንባ ይጎርፋል.......እርርርርርርርርርርርርርሪሪሪሪሪ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ.....ሊያስቆሙኝ ሞከሩ አልጋ የያዝኩ ታካሚ ሳልሆን ጎልያድን ነበር የመሰልኩት.....የታሉ የታሉ ወንድምዓለሜ ባለቤቴ ተቅበዘበዝኩ አወራለው የማወራውን ግን አላውቅም.....እኔ ብሄድ እስትንፋስ እፍፍፍ ብዬ አስነሳቸው ይመስል ተቁነጠነጥኩ....እዛ መሆኔ የገደላቸው ይመስል ብርርርር ብሎ ውልቅ ብሎ መሄድ ተመኘው....አደረኩትም ጎንበስ ቀና  እያልኩ እየተደፋው የከዳኝ ጉልበቴን ከራሴ የለየኝ መሪር ሀዘን አስገድዶ አስቆመው.....

በሰማይ ይሁን በምድር እንጃ ደረስን የአያትሽ ቤት አልመሰለኝም ነበር ምንም የማላውቀው ሆኖ ታየኝ ነጠላ አዘቅዝቀው የለበሱ እናቶች ዋይታ, ጥቁር ሻርብ የለበሱ እንስቶች, ወንድነታቸው ያልበገረው እንባን በእንስቅስቅ  የሚያፈሱ አባቶች, ጋቢ የለበሱ ቤተዘመዶች.....በር ላይ ስብርብር ብዬ ወደኩ በቀኝና ግራ ደግፈው እግሬን እየጎተትኩ ገባሁ.. ሁ...ሁ ለት ሁለት የ አ..አአስ..ስ..የአስክሬ....ን ሳ...ሳ....ሳ...ጥ......"በቃ በቃሽ ተይው ይቅር ይቅር ይቅር..ይቅር....በቃ አብቅቷል እሺ ይቅር አትንገሪኝ "አልኳት እየተነፋረኩ አንገቴ ውስጥ ጥብቅ አርጌ አቅፊያት....እንደህፃን ታቅፋልኝ ሳግ የበዛው ጮክክ ያለ ለቅሶን ተንሰቅስቃ አለቀሰችብኝ ብርሃኔ ማረፊያዬ መፅናኛዬ አለቀሰችብኝ....ልቤ በሀዘን ቁርምትምት ብርድርድ ስትል ተሰማኝ....አሳዘነችኝ....ተንሰፈሰፍኩ....

"ብርዬ እናቴዋዬ በቃን በቃ እሺ ሌላ ጊዜ ደሞ እ?" እንባዋን እየጠራረኩ ተለማመጥኳት...."lifetime ትግል.....መሸነፍ የሌለበት ላለመሸነፍ መጠንከር.....የኔዋ ቡችላ ነገምኮ ዛሬ ነው ለኔ....." አለችኝ ድክመቷን ባደከመ ጥንካሬዋ መቻልን በመውደድ እየፈገገችልኝ....ልክ ናት ያንን አይቼባታለው...የእሷ ትላንት ሁልጊዜዋ ነው....እኔና ትላንቷ ነን ቀለቧ..

በረዥሙ ተነፈሰች..."ህህህኡኡኡኡኡፍፍፍ"....አተነፋፈሷ ሸክምን እንደመዘርገፍ ያለ ነበር ሰላም አለው....ተጋባብኝ....ከአፍታ መረጋጋት በኋላ ቀጠለች...."ሳምንታት ነጎዱ....ሰፈርተኛው ጓደኞቼ አገር ምድሩ መማርያው ሆንኩ"...."እንዴት?" አልኩ ግራ ገብቶኝ...."ሁሉም ሰው አንድ እንደሆነ ምን ጠንካራ ቢሆን ልፍስፍስነትም አብሮት እንዳለ ዘላለም ብርቱ ጠንካራ ከሰው ልጅ እንደሌለ...ሰው ደካማና ብርቱ እንጂ ብርቱ ወይ ደካማ ብቻ እንዳልሆነ....."በቃ አበደች!" እስኪሉ ከራሴ ተለያየው ደቀቅኩ ተናነስኩ በዘመኔ የጠነከርኳቸው ጥንካሬዎቼ ሁሉ ሂሳባቸውን አወራረዱብኝ....

ጥንኩር ሰው የጠነከረውን ያህል ሲሰበርም ስብራቱ ወጌሻውን እስኪሰብር ይደርሳል ......በድኔ ነበር ሚንቀሳቀሰው....በአንድ ወቅት ተሰብስበን ስንጨዋወት በሕይወታችሁ እምነታችሁን  የቀየረና ተምራችሁ ያለፋችሁበት እጅግ የሚያስገርማችሁን  አጋጣሚ አጫውቱንስኪ ሲባል ጎረቢታችን ተሽቀዳድማ ስለኔ"በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት አንድም ቀን ብርሃንን ከጥንካሬዋ ተናንሳ አያታለው ብዬ ለማሰብኳ አስቤ አላውቅም ሁሌም ደምቃ እንዳበራች የምትኖር እስኪመስለኝ ሁሌም በሁሉም ቦታ ወጋገኗ ያስገርመኝ ነበር ጥንካሬዋን ሳይ እውነት ብርሃንም እንደኛ ሰው ናት እል ነበር....የሰፈራችን ድምቀት ተምሳሌት የኔ የዋህ የደረሰባት ሀዘን ግን ድቅቅ ስብርብር አርጓት ሳይ ተንሰፈሰፍኩ እማደርጋት እገባበት አጣሁ...ሰው ለካ ደካማም ነው አልኩ....እርሱ ምን ይሳነዋል ተመስገን  ያም ጊዜ አልፎ እያወራነው ነው ሆይይ ተ   አምር "  ያለችው ለዚ ነበር....ልክ ናት እኔም ስለራሴ ብቻ ሳይሆን ሰው ስለሚባል ሁሉ ከምን ጊዜውም በላይ የተማርኩበት ጊዜ ነበር

ከዘለገ ዝምታ በኋላ በስሱ ፈገግ አለች...."ቅርፍዝ ፍዝዝ እንዳልኩ ዝምም እንዳልኩ....ከቤታችን ደጅ በዛ ካሉ አፅናኞቻችን ጋር ነበርን.....

ምን ቀና አረገኝ? እንዴት ቀና አልኩ? እንጃ ቀና አልኩ በር..በር ላይ.....አንቺንአየሁ...አ...አ..ን...ቺ...ን....አ...የሁ.... አየው...አየሁሽ...."  አለችኝ የስሜን ቃላቶች እንደፊደል ቀስበቀስ እየቆጠረች በሩ ላይ እንባ ያቀረሩ ዓይኖቿን ተክላ
ሚጢጢዬ እራሴን እስካይ ድረስ ታየችኝ... ከዛን በፊትም ይሁን በኋላ ያንን የሚያክል እናቴ ለኔ ያላትን ያስረዳኝ አላገኘሁም.....ሀሴት የታቀፈ እንባ ተስፋ ጉጉት ዳግም መወለድ ያዘለ እንባ ሚያምር አዲስ የተወለደ ልጇን ለመታቀፍ እጅ እንደመዘርጋት ያለ እንስፍስፍት....ልቤ ላይ ቅርፅ አወጣ ምስሏ.....

"አንቺንአየሁ......ባንቺ ሁልነገሬን አበራው.....በአንቺ "ብርሃን ብርሃን ተነሽ" አለኝ መቃብሬን ባንቺ ፈነቀለው መጨረሻ አይደለም አላለቀም አለኝ.....ትኩር ብላ እያየችኝ ቁጭ እሱንኮነው ምትመስዪው.....መከታነትሽ ለሰው ሟችነትሽ ደሞ ኤላዬን....

ተንደርድረሽ ስትጠመጠሚብኝ የጨለመው ዓለሜ ላይ ፀኃይ እጅ እግሯን ዘረጋግታ ስትንጠራራ ተሰማኝ.....ናፍቆት... ፍቅር ...አጥቶ ማግኘት ሲያብሩ...መቼም እንደማታገኝው ተስፋ የቆረጥሽበት ድንገት ላንቺ ሲባል ሲሰጥሽ ያለ አይነት ስሜት, ልብሽን ፍንቅል አርጎ በደስታ ሚያስለቅስ ስጦታ ታውቂያለሽ? እንደዛ ነው የሆንሽልኝ...እኖርለት ዘንድ ምክንያት እንዳለኝ አንቺን አሳየኝ ጥንካሬዬ አደረገልኝ መኖር ጀመርኩ ባንቺ ላንቺ ....ለመኖር ቀመር አንድ አለኜ ሆንሽኝ....አንድ አለኝ አንድ አለሽኝ" አለችኝ በዓይኗ ዓይኔን አልፋ ልቤን የምታይ በሚመስል መውደድ ባደመቀው ሀሴት በወረሰው ስስት በለበሰ እይታ ትኩር ብላ እያየችኝ ድንገት እንባዋ ኩልል አለ.....

"ለልጅ ጥሩ አይደለም ብለው እኔም ከራሴ ጋር ስላልነበርኩ ሌላ ቦታ ወስደውሽ ነበር
በጣም እያለቀስሽ ስታስቸግሪ ከዚ በላይስ ብለው ይዘውሽ መጡ.....

አንቺንአየሁ በአንቺ ውስጥ ሁሉን አየሁ.....አንቺን ማየቴ ድልድይ ሆነኝ አንቺንአየሁ ብዬም ሰየምኩሽ.........ከመቅፅበት ብድግ ብዬ  ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ጉንጮቿን በእጆቼ ይዤ ግንባሯን ሳምኳት....አልበቃኝም ጥምጥምምም አልኩባት...."ኧረ ልተንፍስበት ልቤን አስጨነቅሻት ልብድካሜ ይነሳ ደሞ...." ደማቅ ሳቅ ረፍት ያለው ሳቅ ተሳሳቅን(እህ ልብድካሟ ልብምቷም እኔዉ ነኛ)


#በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ላጡና ሰዋቸውን ላሳጣቸው ሁሉ መታሰቢያ ይሁንልኝ

     
✍️ጎዳዳዬ


https://t.me/justhoughtsss
25.03.202515:55
✨ ቆንጆ ብዕር አላት፨ቤቷ ጎራ ብትሉ ትስማማላችሁ፨ እግረ መንገድ እስኪ ይሄን ጽሑፍ አይታችሁ መስክሩ....በዛው ❤ vote እያደረግን..😉


https://t.me/ende_libe1/24873
04.04.202513:37
✨ እነሆ 1k ቤተሰቦቻችን እናመሰግናለን !!

(ልዩ ምስጋናችን ይድረስልን https://t.me/justhoughtsss 👸𝓷𝓪𝓷𝓲 )

ለሃሳብ አስተያየታችሁ @bluessoulmate አድርሱን🤍
✨ 🅴ⓘⓓ 🅼ⓤⓑⓐⓡⓐⓚ....❤️


https://t.me/yeesua_queen
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.