Пераслаў з:
💞አውደ💞 ቃል 💞💖

18.04.202518:46
አሻግሬ አየሁት
.
.
በግርግር መሐል ጨርቄን ጥዬ ስበር፣
አሻግሬ አየሁት ከቀራንዮ ጫፍ ከጎለጎታ ስር።
መንገዱን በማያዉቅ እልፍ መንገደኛ መንደሩ ታዉኮ፣
አንዱ ካንዱ ሲጋጭ ከሌላኛዉ ተጓዥ ሳይተያይ ታክኮ፣
አላፊ አግዳሚውን ወጪና ወራጁን ቆሜ ስመለከት፣
ደምግባቱን ያጣ የተራቆተ ሰው አየሁኝ በድንገት፣
በደም ረስርሶ በወዝ የረጠበ ቀይ ከለሜዳ፣
በሀሰት ተከሶ ፍርዱን የሚጠብቅ ከጲላጦስ ዘንዳ፣
ይታየኛል አንድ ሰው........
በአይሁድ ሊቀ ካህናት ግራና ቀኙን ተከቦ፣
በህዝብ መካከል የቆመ በእነ ቀያፋ ተዋክቦ፣
ሲንጠበብ ወዙ ሲነሳ ሲወድቅ፣
በጥፊ ሲመቱት እጅጉን ሲሳቀቅ፣
ይታየኛል ንፁህ ሰው......
በቁርጥራጭ ብረት፣
በተሰበረ አጥንት፣
እረፍት በሌለው በወንበዴ ጅራፍ ጀርባውን ተገርፎ፣
አልባስ ተለይቶት እርቃኑን የዋለ ቀሚሱን ተገፎ፣
ስጋዉ ሲቦጫጨቅ፣
ፅሂሙም ሲነጫጭ፣
ቁጥር በማይቆጥረዉ በአይሁድ ግርፋት ቆዳዉ ተገሽልጦ፣
እዡን እያነባ ህማም አይሎበት ፊቱ ተላልጦ፣
በድካም ሲያጣጥር፣
ይታወቀኝ ጀመር፣
ከአይኔ ተንከባሎ ጉንጩን እያራሰ እንባዬ ሲወርድ፣
ላብ እያጠመቀኝ እግሬ ተብረክርኮ ሰዉነቴ ሲርድ፣
አሻግሬ አየሁት.........
በተሳለ ቅንዋት ለአዳም ሲቸነከር፣
በደሙ ቤዛነት ብድራትን ሲቸር፣
በመስቀሉ ካሳ አርአያ ሊሆነን እንባችንን ሊያብስ፣
ለዘላለም ፍቅሩ ለታመነ ቃሉ እስከመሞት ሲደርስ።
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
.
.
በግርግር መሐል ጨርቄን ጥዬ ስበር፣
አሻግሬ አየሁት ከቀራንዮ ጫፍ ከጎለጎታ ስር።
መንገዱን በማያዉቅ እልፍ መንገደኛ መንደሩ ታዉኮ፣
አንዱ ካንዱ ሲጋጭ ከሌላኛዉ ተጓዥ ሳይተያይ ታክኮ፣
አላፊ አግዳሚውን ወጪና ወራጁን ቆሜ ስመለከት፣
ደምግባቱን ያጣ የተራቆተ ሰው አየሁኝ በድንገት፣
በደም ረስርሶ በወዝ የረጠበ ቀይ ከለሜዳ፣
በሀሰት ተከሶ ፍርዱን የሚጠብቅ ከጲላጦስ ዘንዳ፣
ይታየኛል አንድ ሰው........
በአይሁድ ሊቀ ካህናት ግራና ቀኙን ተከቦ፣
በህዝብ መካከል የቆመ በእነ ቀያፋ ተዋክቦ፣
ሲንጠበብ ወዙ ሲነሳ ሲወድቅ፣
በጥፊ ሲመቱት እጅጉን ሲሳቀቅ፣
ይታየኛል ንፁህ ሰው......
በቁርጥራጭ ብረት፣
በተሰበረ አጥንት፣
እረፍት በሌለው በወንበዴ ጅራፍ ጀርባውን ተገርፎ፣
አልባስ ተለይቶት እርቃኑን የዋለ ቀሚሱን ተገፎ፣
ስጋዉ ሲቦጫጨቅ፣
ፅሂሙም ሲነጫጭ፣
ቁጥር በማይቆጥረዉ በአይሁድ ግርፋት ቆዳዉ ተገሽልጦ፣
እዡን እያነባ ህማም አይሎበት ፊቱ ተላልጦ፣
በድካም ሲያጣጥር፣
ይታወቀኝ ጀመር፣
ከአይኔ ተንከባሎ ጉንጩን እያራሰ እንባዬ ሲወርድ፣
ላብ እያጠመቀኝ እግሬ ተብረክርኮ ሰዉነቴ ሲርድ፣
አሻግሬ አየሁት.........
በተሳለ ቅንዋት ለአዳም ሲቸነከር፣
በደሙ ቤዛነት ብድራትን ሲቸር፣
በመስቀሉ ካሳ አርአያ ሊሆነን እንባችንን ሊያብስ፣
ለዘላለም ፍቅሩ ለታመነ ቃሉ እስከመሞት ሲደርስ።
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
Пераслаў з:
💞አውደ💞 ቃል 💞💖

30.03.202518:04
@ስንት_ነው_ኪሎዬ?
እኔ ኃጢአተኛ ልጅህ የማልረባ፤
በአገልጋይነት ስም ሰው ግራ እማጋባ።
ለመታየት ብቻ ከላይ ታች መሮጤን፤
ልሳኔ እስኪዘጋ ቀን ከሌት መጮኼን፤
በበጎነት ቆጥረህ ተመልከተኝ እኔን።
ከቤትህ ባልጠፋም በደሌን አዝዬ፤
በፍቅር ሚዛንህ ስንት ነው ኪሎዬ?
***
እስኪ ተመልከተኝ ልቦናዬን መርምር፤
ኩላሊቴን ፈትሽ የኃጢአቴን ክምር።
ሰው እንደሚለኝ እውን ትልቅ ሰው ነኝ?
በፊትህ ክብርን ሞገስን የማገኝ።
እባክህ ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ?
ሳይነጣጠሉ ነፍስና ሥጋዬ፤
በጽድቅ ሚዛንህ ሲለካ ሥራዬ፤
ጎደሎዬን ልወቅ ስንት ነው ኪሎዬ?
***
ቅዳሴውን ስቀድስ በተዋበው ዜማ፤
መዝሙሩን ስዘምር ሩቅ እስኪሰማ፤
አንተን ነው እኔን ነው የማገለግለው፤
በምእመናን ጭብጨባ ልቤ የታወረው።
ኋላ ተገላልጦ ድብቁ ሥራዬ፤
ኃፍረት እንዳይውጠኝ ስትመጣ ጌታዬ፤
እባክህ ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ?
ለጽድቅ ልዘጋጅ ይቅና ልቡናዬ ።
***
ጥምጣሜን ጠምጥሜ ካባዬን ደርቤ፤
ነጠላ አጣፍቼ ባማረው ቀሚስ ተውቤ፤
መልአክ ብመስል ወንጌልን አንግቤ።
ዲያቆን፣ ቀሲስ፣ ክቡር፣ ዶክተር፣ መጋቤ፣
..... መዘምር ሊቁ እገሌ ቢሉኝ፤
ላንተ ካልተመቸሁ ምኑ ነው ሚጠቅመኝ?
ውስጤንና ውጬን ስትመለከተኝ፤
ስንት እመዝናለሁ በአዛኟ ንገረኝ?
***
ወንጌልን ስዘራ በዐደባባይ ቆሜ፤
አንቱታን ናፍቄ እንዲወደስ ስሜ፤
ምእመኑን ባስደምም ቃላትን ቀምሜ።
አፌንና ውስጤን እንደምን አየኸው?
ልብ ኩላሊትን በሚመረምረው፤
በጽድቅ ሚዛንህ ውስጤን ስትለካው፤
የእኔነቴ ክብደት ቅሌቴ ስንት ነው?
እኔ ባዶ ሆኜ ሌላ ማስተምረው።
***
አምላኬ ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ፤
በጽድቅ ዐደባባይ የኔ መለያዬ።
በሰው ፊት ዘምሬ ወንጌል አስተምሬ፤
ተራቁቼ እንዳልቀር ባዶ ሆኖ ግብሬ።
ግድ የለም ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ?
ባዶነቴን ልሙላው በቀሪው ጊዜዬ።
***
ሰዎች ውጬን አይተው ፤
እንዳይቀልዱብኝ ባለ መቶ ብለው፤
እንዳይዘብቱብኝ ባለ ስልሳም ብለው።
እንቅጩን ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ?
ሠላሳ ለመሙላት ስንት ነው ቀሪዬ?
ግድ የለም ንገረኝ አዋቂው ጌታዬ፤
ሳይነጣጠሉ ነፍስና ሥጋዬ፤
ንስሐ ልግባና ይሙላ ጎደሎዬ።
by p.belete
ሻሸመኔ
=> አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር መስሎ ከመታየት ይልቅ ሁኖ መገኘትን በገቢይ መታየትን ያድለን። ገብር ኄር፥ ገብር ምእመን፥ በጎ አገልጋይ ከሚላቸው ደጋግ አባቶች ይደምረን። አሜን።

05.03.202514:55
፪ #ቅድስት
ቅድስት ፦ ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን
የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ሰለ ሚያወሳ ነው።
እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ።
ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት #ቅድስት ተብላለች ።
@NA_TA_NI_M

15.04.202519:49
የሰሙነ ሕማማት
ሦስተኛው ቀን
#ምክረ አይሁድ
#የመልካም መዓዛ
#የእንባ ቀን
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
ሦስተኛው ቀን
#ምክረ አይሁድ
#የመልካም መዓዛ
#የእንባ ቀን
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
Пераслаў з:
💞አውደ💞 ቃል 💞💖

30.03.202504:38
እንኳን ለዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብር ኄር አደረሳችሁ!
🩵መኑ ውእቱ ገብር ኄር? 🩵
➡️ ገብር ኄር ማለት ገብረ እና ተኄረወ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጡ የሁለት ቃላት ጥምር ስም ሲሆን ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ይህም “መኑ ውእቱ ገብር ኄር” ከሚለው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሥያሜውን አግኝቷል። በገብር ኄር ሳምንት በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25፥14 ላይ የተጻፈው ታሪክ ይወሳል። “ቦ ለዘወሀቦ ፭ተ መክሊተ” እንዲል ማቴ. 25፥14 አንድ ባለጸጋ ነግደው ያትርፉበት ብሎ ባሮቹን ጠርቶ ለአንዱ አምስት፣ ለአንዱ ሁለት፣ ለአንዱ አንድ መክሊት ሰጠ። 5 የተቀበለው ሌላ 5፣ 2 የተቀበለው ሌላ 2 ነግደው ሲጨምሩበት 1 የተቀበለው ግን ምድርን ቆፍሮ የጌታውን ወርቅ ቀበረ።
➡️ ከብዙ ዘመን በኋላ ጌታቸው መጥቶ በተሳሰባቸው ጊዜ አምስት የተቀበለው ቀርቦ “እነሆ አምስት መክሊት ሰጠኸኝ ሌላ አምስት ጨምሬ አተረፍኩበት” አለው። ጌታው “ኦ ገብር ኄር ወምእመን በኅዳጥ ምእመነ ኮንከ” እንዲል ማቴ. 25፥21 “በጥቂቱ ታመንክ” ብሎ አመሰገነው። ሁለት የተቀበለውም ቀርቦ “እነሆ ሁለት መክሊት ሰጠኸኝ ሌላ ሁለት አተረፍኩኝ” አለው። “ኦ ገብር ኄር ወምዕመን” ብሎ ያመሰግነዋል።
➡️ አንድ የተቀበለው ግን መጥቶ “አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንክበት የምትሰበስብ ጨካኝ እንደሆንክ አውቄ በመፍራቴ በምድር ቀብሬ አስቀምጫለሁ ገንዘብህ እነሆ” ይለዋል። ጌታውም “ጥርስ ማፏጨትና ልቅሶ ወዳለበት የጨለማ ቦታ ውሰዱት” ይላል። ይህን ምሳሌ መስሎ ጌታ ያስተማረው ትምህርት የሚነገርበት ሳምንት ነው። ማቴ. 25፥21
➡️ ከዚህም የተነሣ ገብር ኄር፣ ገብር ምእመንና፣ ገብር ሃካይ የሚባሉት እንደ ባለቤት ተወስደው ይነገርባቸዋል። ይህም ምሳሌ ነው። ገብር ኄር፤ ገብር ምእመን የተማሩትን የሚያስተምሩ መምህራን ካህናት ያገኙትን የሚመጸውቱ አብዕልት ምሳሌ ናቸው።
✨ገንዘብ የቃለ እግዚአብሔር እና የምጽዋት ምሳሌ ነው።
➡️ ገብር ሃካይ የሚለው የተማረውን የማያስተምር መምህር ያገኘውን የማይመጸውት ባዕለ ጸጋ ሰው ምሳሌ ነው። በዚህ ሰሞን ገብር ኄር እና ገብር ምእመን መክሊታቸውን ማባዛታቸው ገብር ሃካይ አንዷን መክሊት በጨርቅ ጠቅሎ መቅበሩ በገብር ሃካይ መፈረዱ፤ ገብር ኄርና ገብር ምእመን መሸለማቸው ወዘተ ይነገራል። ታአማኝ አገልጋይ ሁነን እንድንገኝ እግዚአብሔር ይረርዳን።
💠 💠
╭══•|✣:❖๑✟๑❖✣|: ══╮
https://t.me/awdekalat_2121
╰══•|✣:❖๑✟๑❖✣|: ══╯
09.03.202513:48
🕊 💖 🕊
[ የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ]
💖
[ 🕊 ም ኵ ራ ብ 🕊 ]
[ እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ]
†
[ ምኵራብ ! ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ 🕊 ክብርት ቤተክርስቲያን 🕊 ]
[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ ! ]
❝ ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እም ኩሉ ሕዝብ ❞
[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላምታ ይገባል። ] [አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]
" በመላእክት ፊት እዘምርልኻለሁ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ። " [መዝ.፻፴፯፥፪ ]
† † †
ቤተ ክርስቲያንን “ ቅድስት ” አላት ስለምን ቢሉ ?
የቅድስት ሥላሴ አንድነት ሦስትነት ይነገርባታልና ፤ አንድም ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ አክብሯታልና። አንድም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ለምእመናን ይሰጥባታልና፡፡ አንድም በኀጢአት የረከሰ ሰው በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆባት ይቀደስባታልና።
“ ማኅደረ ስብሐት ” [ የምስጋና ማደሪያ ] አላት ፦
የልዑል እግዚአብሔር ምስጋና በጸሎተ ኪዳን ፣ በስብሐተ ነግህ ፣ በጸሎተ ቅዳሴ ፣ በማሕሌት ፣ በሰዓታት ፣ በሰባቱ ጊዜያት ኹሉ ይነገርባታልና።
“ የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] ” አላት ፦
የመንግሥቱ ወንጌል በሚነገርበት ፣ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ በሚፈተትበት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የጸለዩትን ጸሎት ለማሳረግ በቀን ስድስት መቶ በሌሊት ስድስት መቶ መላእክት ይጠብቋታልና።
“ እመ ኵሉ ሕዝብ ” የሕዝብ ኹሉ እናት ይላታል ፦
እናት ልጆቿን እንድታሳድግ ፣ እንድትጠብቅ ፣ ወደ ቀና ጐዳና መርታ እንድታደርስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በምስጢረ ቤተ ክርስቲያን ይልቁኑ በሥጋውና በደሙ እናድግባታለን ፤ በርቱዕ ትምህርቷ ከክሕደት እንጠበቅባታለን ፤ በመጨረሻም ወደ አምሳያዋ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት መርታ ታደርስናለችና። [ ገላ.፬፥፳፮-፳፯ ] ❞
🕊 ክብርት ሰንበት 🕊
† † †
[ " ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና።
ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል ፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።" [ ማቴ . ፳፩ ፥ ፲፪ ]

13.04.202518:55
ሆሳዕና በአርያም 🌿🌿🌿🌿
እንኳን ለ ሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🌿🌿🌿🌿
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
እንኳን ለ ሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🌿🌿🌿🌿
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112

23.03.202520:15
እንኳን ለበዓለ ደብረ ዘይት በሰላም አደረሳችሁ።

08.03.202516:38
አፈራርሰህ ስራኝ እባክህ
ጉብዝናዬን በጭፈራ
ወዝ እድሜዬን በዳንኪራ
የመስቀሉን ድንቅ ዓላማ ሳልዋኃድ
ሽቅብ ቁልቁል እንደባዘንኩ እንደሰደድ
ጽድቅ ምግቧን ሳልመግባት ለአንዲት ነፍሴ
ሳይጸጽተኝ በሀጢያት መልከስከሴ
ፍርድ እንዳለ ሰይፍ ሲኦል ጉብዝናዬ እንደጠፋው
ውብ ዘመኔን በእኩሌታው አትገድበው
የአምልኮ መልክ ብቻ እንደያዝኩኝ
በጤናዬ ሳልረዳህ ሳትገባኝ
በፌዝ ድንዝዝ እንዳለሁኝ
አትተወኝ
እኔ ልምጣ አንተ አሱሩጠኝ
ጅማሬዬን አስጨርሰኝ
የድል አክሊል መድሀኒቴ
አንተን እንድወርስ ደጉ አባቴ
ዓለም ጣዕሟን እንድከዳ
በሳሙናህ ከእድፌ እንድጸዳ
ለአዳኜ(ላልቶ) እኔ ራሴን እንድሰዋ
ስለ አንተ መራራ ሞት እንድታገስ
የድንግል ልጅ በልቤ ውስጥ ተመላለስ።
አቅም ጉልበት ሐይል ሳይከዳኝ
ወኔ ጤና ደምግባቴ ሳይለየኝ
ወጣት ሆኜ እንድወድህ
ለወደድኩህ እኔነቴን እንድሰጥህ
አፈራርሰህ ስራኝ 'ባክህ🙏
@NA_TA_NI_M
@NA_TA_NI_M
@NA_TA_NI_M
ጉብዝናዬን በጭፈራ
ወዝ እድሜዬን በዳንኪራ
የመስቀሉን ድንቅ ዓላማ ሳልዋኃድ
ሽቅብ ቁልቁል እንደባዘንኩ እንደሰደድ
ጽድቅ ምግቧን ሳልመግባት ለአንዲት ነፍሴ
ሳይጸጽተኝ በሀጢያት መልከስከሴ
ፍርድ እንዳለ ሰይፍ ሲኦል ጉብዝናዬ እንደጠፋው
ውብ ዘመኔን በእኩሌታው አትገድበው
የአምልኮ መልክ ብቻ እንደያዝኩኝ
በጤናዬ ሳልረዳህ ሳትገባኝ
በፌዝ ድንዝዝ እንዳለሁኝ
አትተወኝ
እኔ ልምጣ አንተ አሱሩጠኝ
ጅማሬዬን አስጨርሰኝ
የድል አክሊል መድሀኒቴ
አንተን እንድወርስ ደጉ አባቴ
ዓለም ጣዕሟን እንድከዳ
በሳሙናህ ከእድፌ እንድጸዳ
ለአዳኜ(ላልቶ) እኔ ራሴን እንድሰዋ
ስለ አንተ መራራ ሞት እንድታገስ
የድንግል ልጅ በልቤ ውስጥ ተመላለስ።
አቅም ጉልበት ሐይል ሳይከዳኝ
ወኔ ጤና ደምግባቴ ሳይለየኝ
ወጣት ሆኜ እንድወድህ
ለወደድኩህ እኔነቴን እንድሰጥህ
አፈራርሰህ ስራኝ 'ባክህ🙏
@NA_TA_NI_M
@NA_TA_NI_M
@NA_TA_NI_M
Пераслаў з:
😍የጥበብ አለም ✍✍

02.04.202521:21
@yetbebaleme
@yetbebaleme
@yetbebaleme
@tsedi12m ከ ገጣሚ Eyob z mariyam የተወሰደ
@yetbebaleme
@yetbebaleme
@tsedi12m ከ ገጣሚ Eyob z mariyam የተወሰደ
16.03.202514:38
🕊 💖 🕊
[ የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት ]
💖
[ 🕊 መ ጻ ጉ ዕ 🕊 ]
አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹መጻጒዕ› ይባላል፡፡
ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩ ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል የተወሰደ ነው፡፡ በዚህ የወንጌል ክፍል ጌታችን በቤተ ሳይዳ ሕሙማንን እንደ ፈወሰ ተነግሮአል፡፡ ብዙ ሕሙማን ፈውስ ሽተው አንዲት የመጠመቂያ ሥፍራን ከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያች ሥፍራ ቀድሞ የወረደ እና የተጠመቀ አንድ በሽተኛ ብቻ ይፈወስ ነበር፡፡
ጌታችን በዚህ ሥፍራ ተገኝቶ በሽተኞችን ጐብኝቷል፡፡ በዚያም ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸው አምስት ዓይነት ሕሙማን እንደ ነበሩ ተገልጧል ፤ እነዚህም ፦ ሰውነታቸው የደረቀ ፣ የሰለለና ያበጠ ፤ እንደዚሁም ዕውራን እና ሐንካሳን ነበሩ፡፡ ከዚህ አምስት የተለያየ ዓይነት በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ደዌው የጸናበት ፣ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ ፣ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የኖረው ፤ ከደዌው ጽናት የተነሣ ‹መጻጒዕ› ተብሎ የተጠራው በሽተኛ አንዱ ነበር፡፡
መጻጒዕ ስም አይደለም፡፡ ደዌ የጸናበት በሽተኛ ሕመምተኛ ማለት ነው እንጂ፡፡ ሰውየው ከበሽታው ጽናት የተነሣ ስሙ ጠፍቶ በበሽታው ሲጠራ የነበረ ነው፡፡ አምላካችን ይህን ሰው "አልጋህን ተሸክመህ ሒድ" ብሎ ሠላሳ ስምንት ዘመን የተኛበትን አልጋ ተሸክሞ ወደ ቤቱ እንዲገባ ማድረጉ የሚነገርበት ወቅት በመኾኑ ሳምንቱ ‹መጻጒዕ› ተብሎ በተፈወሰው በሽተኛ ስም ተሰይሟል፡፡ [ሙሉ ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩-፲፯ ይመልከቱ]፡፡
ዛሬም ቢኾን በሰዎች ላይ ልዩ ልዩ ደዌያት አሉ ፤ የሥጋውን ደዌ ሐኪሞች ያውቁታል፡፡ ከዚህ የከፉ የነፍስ ደዌያት እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡ በኃጢአት ብዛት ልባቸው የደረቀና ያበጠ ፤ ሰውነታቸው የሰለለ ፤ ዓይነ ሕሊናቸው የታወረ ፤ እግረ ልቡናቸው የተሰበረ ብዙዎች ሕሙማን አሁንም አሉ፡፡ ፈውስን ይሻሉ ፤ ድኅነትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ መጻጕዕ ቦታቸውን ሳይለቁ እግዚአብሔርን በተስፋ ቢጠብቁት አንድ ቀን ይፈወሳሉ፡፡
https://t.me/awdekalat_2112

07.03.202517:24
የዐቢይ #ጾም
3ተኛው ሳምንት
#ምን
በመባል
#ይጠራል ?
@NA_TA_NI_M
@NA_TA_NI_M
@NA_TA_NI_M
3ተኛው ሳምንት
#ምን
በመባል
#ይጠራል ?
@NA_TA_NI_M
@NA_TA_NI_M
@NA_TA_NI_M
Паказана 1 - 13 з 13
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.