Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
✨ናታኒም avatar

✨ናታኒም

ናታኒም ትርጓሜውም የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነው
መዝሙር ከ እነ ግጥም እና የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ስዕል አድኖውችን እንለቃለን ስለ ተቀላቀሉን እናመሰግናለን ✨✨
Рэйтынг TGlist
0
0
ТыпПублічны
Вертыфікацыя
Не вертыфікаваны
Надзейнасць
Не надзейны
Размяшчэнне
МоваІншая
Дата стварэння каналаFeb 06, 2025
Дадана ў TGlist
Mar 31, 2025

Развіццё

Падпісчыкаў
Індэкс цытавання
Ахоп 1 паста
Ахоп рэкламнага паста
ER
ERR
MAR '25MAR '25MAR '25MAR '25APR '25APR '25APR '25

Папулярныя публікацыі ✨ናታኒም

""" ሕያዉን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ ?  ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም።"""  ሉቃ ፪፬ ÷  ፭
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሠላም ፤
እምይዕዜሰ ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሠላም፡፡”
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳቹ😊

💙💙💙 መልካም በዓል 💙💙💙

@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
ሆሳዕና በአርያም 🌿🌿🌿🌿


እንኳን ለ ሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🌿🌿🌿🌿

@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
30.03.202518:04
@ስንት_ነው_ኪሎዬ?
        
እኔ ኃጢአተኛ ልጅህ የማልረባ፤
በአገልጋይነት ስም ሰው ግራ እማጋባ።
ለመታየት ብቻ ከላይ ታች መሮጤን፤
ልሳኔ እስኪዘጋ ቀን ከሌት መጮኼን፤
በበጎነት ቆጥረህ ተመልከተኝ እኔን።
ከቤትህ ባልጠፋም በደሌን አዝዬ፤
በፍቅር ሚዛንህ ስንት ነው ኪሎዬ?
                 ***
እስኪ ተመልከተኝ ልቦናዬን መርምር፤
ኩላሊቴን ፈትሽ የኃጢአቴን ክምር።
ሰው እንደሚለኝ እውን ትልቅ ሰው ነኝ?
በፊትህ ክብርን ሞገስን የማገኝ።
እባክህ ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ?
ሳይነጣጠሉ ነፍስና ሥጋዬ፤
በጽድቅ ሚዛንህ ሲለካ ሥራዬ፤
ጎደሎዬን ልወቅ ስንት ነው ኪሎዬ?
                 ***
ቅዳሴውን ስቀድስ በተዋበው ዜማ፤
መዝሙሩን ስዘምር ሩቅ እስኪሰማ፤
አንተን ነው እኔን ነው የማገለግለው፤
በምእመናን ጭብጨባ ልቤ የታወረው።
ኋላ ተገላልጦ ድብቁ ሥራዬ፤
ኃፍረት እንዳይውጠኝ ስትመጣ ጌታዬ፤
እባክህ ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ?
ለጽድቅ ልዘጋጅ ይቅና ልቡናዬ ።
                ***
ጥምጣሜን ጠምጥሜ ካባዬን ደርቤ፤
ነጠላ አጣፍቼ ባማረው ቀሚስ ተውቤ፤
መልአክ ብመስል ወንጌልን አንግቤ።
ዲያቆን፣ ቀሲስ፣ ክቡር፣ ዶክተር፣ መጋቤ፣
..... መዘምር ሊቁ እገሌ ቢሉኝ፤
ላንተ ካልተመቸሁ ምኑ ነው ሚጠቅመኝ?
ውስጤንና ውጬን ስትመለከተኝ፤
ስንት እመዝናለሁ በአዛኟ ንገረኝ?
               ***
ወንጌልን ስዘራ በዐደባባይ ቆሜ፤
አንቱታን ናፍቄ እንዲወደስ ስሜ፤
ምእመኑን ባስደምም ቃላትን ቀምሜ።
አፌንና ውስጤን እንደምን አየኸው?
ልብ ኩላሊትን በሚመረምረው፤
በጽድቅ ሚዛንህ ውስጤን ስትለካው፤
የእኔነቴ ክብደት ቅሌቴ ስንት ነው?
እኔ ባዶ ሆኜ ሌላ ማስተምረው።
             ***
አምላኬ ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ፤
በጽድቅ ዐደባባይ የኔ መለያዬ።
በሰው ፊት ዘምሬ ወንጌል አስተምሬ፤
ተራቁቼ እንዳልቀር ባዶ ሆኖ ግብሬ።
ግድ የለም ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ?
ባዶነቴን ልሙላው በቀሪው ጊዜዬ።
            ***
ሰዎች ውጬን አይተው ፤
እንዳይቀልዱብኝ ባለ መቶ ብለው፤
እንዳይዘብቱብኝ ባለ ስልሳም ብለው።
እንቅጩን ንገረኝ ስንት ነው ኪሎዬ?
ሠላሳ ለመሙላት ስንት ነው ቀሪዬ?
ግድ የለም ንገረኝ አዋቂው ጌታዬ፤
ሳይነጣጠሉ ነፍስና ሥጋዬ፤
ንስሐ ልግባና ይሙላ ጎደሎዬ።
by p.belete
     ሻሸመኔ
=> አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር መስሎ ከመታየት ይልቅ ሁኖ መገኘትን በገቢይ መታየትን ያድለን። ገብር ኄር፥ ገብር ምእመን፥ በጎ አገልጋይ ከሚላቸው ደጋግ አባቶች ይደምረን። አሜን።


@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
30.03.202504:38
እንኳን ለዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብር ኄር አደረሳችሁ!



🩵መኑ ውእቱ ገብር ኄር?
🩵

➡️ ገብር ኄር ማለት ገብረ እና ተኄረወ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጡ የሁለት ቃላት ጥምር ስም ሲሆን ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ይህም “መኑ ውእቱ ገብር ኄር” ከሚለው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሥያሜውን አግኝቷል። በገብር ኄር ሳምንት በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25፥14 ላይ የተጻፈው ታሪክ ይወሳል። “ቦ ለዘወሀቦ ፭ተ መክሊተ” እንዲል ማቴ. 25፥14 አንድ ባለጸጋ ነግደው ያትርፉበት ብሎ ባሮቹን ጠርቶ ለአንዱ አምስት፣ ለአንዱ ሁለት፣ ለአንዱ አንድ መክሊት ሰጠ። 5 የተቀበለው ሌላ 5፣ 2 የተቀበለው ሌላ 2 ነግደው ሲጨምሩበት 1 የተቀበለው ግን ምድርን ቆፍሮ የጌታውን ወርቅ ቀበረ።

➡️ ከብዙ ዘመን በኋላ ጌታቸው መጥቶ በተሳሰባቸው ጊዜ አምስት የተቀበለው ቀርቦ “እነሆ አምስት መክሊት ሰጠኸኝ ሌላ አምስት ጨምሬ አተረፍኩበት” አለው። ጌታው “ኦ ገብር ኄር ወምእመን በኅዳጥ ምእመነ ኮንከ” እንዲል ማቴ. 25፥21 “በጥቂቱ ታመንክ” ብሎ አመሰገነው። ሁለት የተቀበለውም ቀርቦ “እነሆ ሁለት መክሊት ሰጠኸኝ ሌላ ሁለት አተረፍኩኝ” አለው። “ኦ ገብር ኄር ወምዕመን” ብሎ ያመሰግነዋል።

➡️ አንድ የተቀበለው ግን መጥቶ “አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንክበት የምትሰበስብ ጨካኝ እንደሆንክ አውቄ በመፍራቴ በምድር ቀብሬ አስቀምጫለሁ ገንዘብህ እነሆ” ይለዋል። ጌታውም “ጥርስ ማፏጨትና ልቅሶ ወዳለበት የጨለማ ቦታ ውሰዱት” ይላል። ይህን ምሳሌ መስሎ ጌታ ያስተማረው ትምህርት የሚነገርበት ሳምንት ነው። ማቴ. 25፥21

➡️ ከዚህም የተነሣ ገብር ኄር፣ ገብር ምእመንና፣ ገብር ሃካይ የሚባሉት እንደ ባለቤት ተወስደው ይነገርባቸዋል። ይህም ምሳሌ ነው። ገብር ኄር፤ ገብር ምእመን የተማሩትን የሚያስተምሩ መምህራን ካህናት ያገኙትን የሚመጸውቱ አብዕልት ምሳሌ ናቸው።

✨ገንዘብ የቃለ እግዚአብሔር እና የምጽዋት ምሳሌ ነው።


➡️ ገብር ሃካይ የሚለው የተማረውን የማያስተምር መምህር ያገኘውን የማይመጸውት ባዕለ ጸጋ ሰው ምሳሌ ነው። በዚህ ሰሞን ገብር ኄር እና ገብር ምእመን መክሊታቸውን ማባዛታቸው ገብር ሃካይ አንዷን መክሊት በጨርቅ ጠቅሎ መቅበሩ በገብር ሃካይ መፈረዱ፤ ገብር ኄርና ገብር ምእመን መሸለማቸው ወዘተ ይነገራል። ታአማኝ አገልጋይ ሁነን እንድንገኝ እግዚአብሔር ይረርዳን።


           💠  💠

       ╭══•|✣:❖๑✟๑❖✣|: ══╮
       https://t.me/awdekalat_2121
       ╰══•|✣:❖๑✟๑❖✣|: ══╯
@yetbebaleme
@yetbebaleme
@yetbebaleme


@tsedi12m ከ ገጣሚ Eyob z mariyam የተወሰደ
15.04.202519:49
የሰሙነ ሕማማት
ሦስተኛው ቀን
#ምክረ አይሁድ
#የመልካም መዓዛ
#የእንባ ቀን




@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
18.04.202518:46
አሻግሬ አየሁት
.
.
በግርግር መሐል ጨርቄን ጥዬ ስበር፣
አሻግሬ አየሁት ከቀራንዮ ጫፍ ከጎለጎታ ስር።

መንገዱን በማያዉቅ እልፍ መንገደኛ መንደሩ ታዉኮ፣
አንዱ ካንዱ ሲጋጭ ከሌላኛዉ ተጓዥ ሳይተያይ ታክኮ፣

አላፊ አግዳሚውን ወጪና ወራጁን ቆሜ ስመለከት፣
ደምግባቱን ያጣ የተራቆተ ሰው አየሁኝ በድንገት፣

በደም ረስርሶ በወዝ የረጠበ ቀይ ከለሜዳ፣
በሀሰት ተከሶ ፍርዱን የሚጠብቅ ከጲላጦስ ዘንዳ፣

ይታየኛል አንድ ሰው........

በአይሁድ ሊቀ ካህናት ግራና ቀኙን ተከቦ፣
በህዝብ መካከል የቆመ በእነ ቀያፋ ተዋክቦ፣

ሲንጠበብ ወዙ ሲነሳ ሲወድቅ፣
በጥፊ ሲመቱት እጅጉን ሲሳቀቅ፣

ይታየኛል ንፁህ ሰው......

በቁርጥራጭ ብረት፣
በተሰበረ አጥንት፣

እረፍት በሌለው በወንበዴ ጅራፍ ጀርባውን ተገርፎ፣
አልባስ ተለይቶት እርቃኑን የዋለ ቀሚሱን ተገፎ፣

ስጋዉ ሲቦጫጨቅ፣
ፅሂሙም ሲነጫጭ፣

ቁጥር በማይቆጥረዉ በአይሁድ ግርፋት ቆዳዉ ተገሽልጦ፣
እዡን እያነባ ህማም አይሎበት ፊቱ ተላልጦ፣

በድካም ሲያጣጥር፣
ይታወቀኝ ጀመር፣

ከአይኔ ተንከባሎ ጉንጩን እያራሰ እንባዬ ሲወርድ፣
ላብ እያጠመቀኝ እግሬ ተብረክርኮ ሰዉነቴ ሲርድ፣

አሻግሬ አየሁት.........

በተሳለ ቅንዋት ለአዳም ሲቸነከር፣
በደሙ ቤዛነት ብድራትን ሲቸር፣

በመስቀሉ ካሳ አርአያ ሊሆነን እንባችንን ሊያብስ፣
ለዘላለም ፍቅሩ ለታመነ ቃሉ እስከመሞት ሲደርስ።

በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.