የአሜሪካ ኢኮኖሚ ከ2021 በኋላ ዝቅተኛውን ስራ የያዙ ሰዎች ቁጥር አስመዝግቧል።
ወሩ በገባ በመጀመሪያው አርብ ይፋ የሚሆነው የNON FARM PAYROLL DATA በአሜሪካ የኢኮኖሚው ማሳያ ተደርገው ከሚወሰዱ ዋና ዋና ማሳያዎች ውስጥ አንዱ ነው።
NFP በየወሩ ከግብርና፣ከመንግስትና በግል ከሚሰሩ ሰዎች ውጪ በወሩ ምንያህል ሰዎች ስራ እንደያዙ የሚገልፅ Data ሲሆን በዚህ ወር ለ106,000 ሰዎች ስራ ይፈጠራል ተብሎ ቢጠበቅም ከደቂቃዎች በፊት በወጣው report ግን የተፈጠረው ለ12,000 ሰዎች ብቻ ነው።
ይህንን ተከትሎም FED በቀጣይ ሳምንት ሌላ የወለድ ምጣኔ ቅነሳ ሊያደረግ እንደሚችል ተነግሯል።
FED ከወር በፊት በ0.5% የወለድ ምጣኔውን የቀነሰ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ሌላ የ0.25% ቅነሳ ሊያደርግ እንደሚችል ተነግሯል።
FED ይህንን እርምጃ ከወሰደ የአሜሪካ ዶላር ከሌሎች ASSETS ጋር ያለውን ዋጋ ሊያዳክም እንደሚችል ተተንብይዋል።