Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ avatar
✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞
✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ avatar
✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞
07.05.202518:24
♡ ምን ሰማህ ዮሐንስ ♡


ምን ሰማህ ዮሐንስ በማሕጸን ሳለህ /2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ /2/


ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር    
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /2/    
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ    
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ /2/


በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት  
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት/ /2/  
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ  
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ /2/


ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም    
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍፁም /2/      
ከማህፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ      
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ /2/


ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
28.04.202518:52
♡ ማነው ማርያምን ተው አትጥራት የሚለኝ ♡


ማነው ማርያምን ተው አትጥራት የሚለኝ
ስሟን ሳወድሳት የሚከለክለኝ
የእርሱን ነፃ ፈቃድ እየተጠቀመ
የእኔን ነፃ ፈቃድ ለምን ተቃወመ



የአንቺን ወዳጅነት አጥብቄ ስለያዝኩ
በፀረ ማርያሞች ብሆን የተወገዝኩ
መቼም ቅር አይለኝ ደስተኛ ነኝ እኔ
የእናትና ልጁ ወዳጅ በመሆኔ
ተዋት ሲሉኝማ ብሶብኛል ጭራሽ
እያልኳት በሀዘኔ ነሽ በጭንቄ ደራሽ
በሚጠሏት መሀል ስሟን እየጠራሁ
የጠላቴን ጭንቀት ሀዘን አበዛለሁ

ከፅንሰት ጀምሮ እስከ እርገቱ ድረስ
ያልተለያዩትን ሊለይ ክፉ መንፈስ
እንቅልፉን በማጣት ሌተቀን ቢዞርም
ሲያምረው ይቅር እንጂ ማርያማን አልተውም
ይከፋዋል ብዬ ወዳጅና ዘመድ
አልል ወደ ኋላ ማርያምን አልተውም
በውስጣቸው ያለው የእመቤቴ ጠላት
ስሟን ሰምቶ ይቃጠል በጩኸት ስጠራት

ፅዮንን ክበቧት እናታችን በሉ
የተባለው ትንቢት እንዲፈፀም ቃሉ
ቀራንዮ ላይ ሰጠን ምስጋና ለእግዚአብሔር
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት እያላት እንዲኖር
በችንካር በጅራፍ በደም የታጠበ
በከባድ ስቃይ ውስጥ ስለኛ አሰበ
የሚወዳት እናቱን ለሚወደን ሰቷል
ታድያ ፍቅር ሌላ በምን ይገለጣል


ጠራው ደጋግሜ ሱስ ሆኖብኝ ስሟ
ስለራቀ በእርሷ የሔዋን መርገሟ
ያልፍ ይሆናል እንጂ የምለው አይበዛ
የልጇ ቤዛነት ነብሴን ስለገዛ
ማርያም ማርያም ይላል ቢመረመር ደሜ
አርጋልኝ እንዲፃፍ በህይወት መዝገብ ስሜ
ጠላት እስከሚያጣ ስሟን ማይሰማበት
አወድሳታለው በቀንም በሌሊት


መምህር ምሕረታብ ተስፋ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
20.04.202515:17
​​
✳️ ከትንሳኤ እሑድ በኋላ የሚውሉ ዕለታት ስያሜ



ሰኞ ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር ማለፍ ማለት ነው በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ከሞት ወደ ሕይወት ከሲኦል ወደ ገነት ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን::


ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል ዮሐ. 20፡27-29::


ረቡዕ አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን::


ሐሙስ አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን::


አርብ ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ይሰበካል ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ነስቶ ስለመመስረቷ እንዳከበራት ይነገራል ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና::


ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል::


እሑድ ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል::


🙏† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †🙏
💗 ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም 💗
============💗=============




🕯 💚 💛 ❤️ 🕯
01.04.202517:44
♡ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ ♡


ተክለሃይማኖት ጻድቅ
ስምህ ያድናል ከመውደቅ
ተክለሃይማኖት ጻድቅ
ስምህ ያድናል ከመድቀቅ
ቅኔ ልቀኝልህ ልዘምር በደስታ
አይቻለሁ በአንተ ችግሬ ሲፈታ[፪]


ስጋዬ ታሞብኝ ተጨንቃ ሕይወቴ
በስምህ ታመንኩኝ ተክለ አብ አባቴ
ከቤቴ ሳልወጣ ገዳምክን ሳስበው
መከራው አልፎልኝ በአይኔ አይቻለሁ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
አገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት


ስፍገመገም ልወድቅ በዝቶ ፈተናዬ
ደገፍከኝ አባቴ መተህ መመኪያዬ
ተስፋዬ ተሟጦ አይኔን እንባ ሞልቶ
ጸበልህ ሲነካኝ አገኘሁኝ ድህነት

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት


በተስፋ ሞልተኸኝ ስመጣ ከደጅህ
የበዛው ሕመሜ ሸፈንከው በጽድቅህ
ሞኝ ነው ይሉኛል ሳያውቁ አባቴ
መሰከርኩ ልጅህ በርትቶ ጉልበቴ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት


ከችግር ከሐዘን ያመነህ ይወጣል
አይኑ ተከፍቶለት አብርቶ ይታያል
በሰው እጅ የመጣ ነበር ይሆን እና
ድኖ ይመለሳል በጽድቅህ ገናና

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት


የደብረ አስቦቱ የኢቲሳው አባት
መሰከረች ዛሬ ጽላልሽ በእውነት
ክንፍን የተሸለምክ የምሕረት አባት
ዳቢሎስ አፈረ ስትታይ በዳሞት

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት



ዘማሪ ዲ/በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
07.05.202518:24
♡ አጎንብሼ ሄጄ ♡


አጎንብሼ ሄጄ ቀና ብዬ መጣው
በዮሐንስ ፀበል ጤናዬን አገኘው
ጌታን ያጠመቁ ክቡራን እጆቹ
ተዓምር ይሰራሉ ዛሬም ለልጆቹ

አልጋዬን አዝዬ በደስታ ዘለልኩኝ
በመጥምቁ ፀበል በእጁ ተዳሰስኩኝ
የመራኝን በትር ከእጄ ላይ ጥያለሁ
በሰባኪው ጸሎት በምልጃው ድኛለሁ

አዝ= = = = =
ለዓለም ያልተቻላት በእምነቱ ለቆኛል
አበቃልህ ያሉኝ እጅግ ተደንቀዋል
በለምጽ የነደድኩት ታደስኩ እንደገና
አዲስ አካል ይዤ ቆምኩኝ ለምስጋና

አዝ= = = = =
ያለፍኩባት ሰፈር በእምባ ተሞልቼ
እልልታዬን ሰማች ድኜ ተደስቼ
የንዕማን ቁስል ተራግፉአል ከላዬ
መሞቴን የማይወድ አሰበኝ ጌታዬ

አዝ= = = = =
አባናና ፋርፋን አስንቁአል ጸበሉ
ዮርዳኖስ በእምነት ለወረዱ ሁሉ
ዮሐንስ በመንፈስ ሲያጠምቅ አይቻለሁ
በእጁ ተፈውሼ ምስክር ሆኛለሁ


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ​⁠
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
💗 እንኳን ለታላቁ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ በዚህ ቀን ተሰይፏል።



✝️ ከበረከቱ ይክፈለን!
ነገ ❶❾. ገብርኤል አባቴ ❣️
.....................................




አብሳሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል
ከክፉ ነገር ይጠብቃችሁ ያሠባችሁትን
የልባችሁን መሻት ይፈጽምላችሁ አሜን




❤️🌹❤️...........❶❾🕯
20.04.202510:30
♡ ይኸው ተነሳ ደስ ይበለን ♡

ኃያል ነው እርሱ ዘላዓለማዊ
የሁሉ ጌታ ሞትን የዋጠው
ድልን ያወጀው የማይረታ

ይኸው ተነሳ ደስ ይበለን ❤️
.
.
.

ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
31.03.202514:40
ፀሐይ ዘልዳ ኮከብ ዘልዳ ዘልዳ ንጉሥ ነዓ ጊዮርጊስ
እምነ ሠናያት ኩሎ እለ ውስተ ባሕር ወየብስ
ሶበ ነጸርኩ በሃሢሥ ዘከማከ አልቦ ጊዮርጊስ



♡ ፀሐይ ዘልዳ ♡

እምነ ሠናያት ኩሎ እለ ውስተ ባሕር ወየብስ(፪)
ሶበ ነጸርኩ በሃሢሥ ዘከማከ አልቦ ጊዮርጊስ(፪)


የመከራ ገፈት ቀምሳ ለሰጠችህ
ልጅ ሆነሃልና ለማርያም እናትህ
ስምዐ ክርስቶስ አርአያ ሰማዕታት
ሆነህ የተሰየምክ የሰማዕታት አባት

አዝ= = = = =

የገድልህን ነገር ጆሮአችን ሲሰማ
ልባችን ይቀልጣል ለጽናትህ ዜና
የጌታህን ትዕግሥት ቀራንዮን እያሰብክ
በወጣትነትህ ተጋድሎህን ፈጸምክ

አዝ= = = = =

በጭንቅ በመከራ ጽናትህ ሲፈተን
ከአምላክ ተምረህ ቁጣን ሳትናገር
ሁሉን ስለ ጌታ ችለህ ታግሰሃል
የብርሃን አክሊልን በሰማይ ደፍተሃል

አዝ= = = = =

ስዕለ ገጽህን ዘወትር እያየን
ነገረ ገድልህን ሁልጊዜ እያደነቅን
ፍቅርህ በልባችን ስለተሳለብን
ይኸው አንዘምራለን ጊዮርጊስ እያልን

መዝሙር
ደብረብርሃን ሰ/ት/ቤት
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gtmoch
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
07.05.202518:24
♡ በማህፀን ቅኔ ♡


በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማ አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው
ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው


የእናቱ ማህፀን የቅኔ እርስት ሆነች
ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች
በሀሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ
ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ

አዝ።።።።።።
በድንግል ማህፀን ስላየ ጌታውን
ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን
ትንቢቱ ሲፈፀም በሆዷ ሲነግስ
ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንስ

አዝ።።።።።።
ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ
ተፈጥሮ መች ቻለ ነብዩን ለማገድ
አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና
በእናቱ ማህፀን ድምፅን አሰማና

አዝ።።።።።።
የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ ገረማት
ልጇ በማህፀን ቅኔን ሲቀኝባት
ድምጿን ከፍ አረገች አለም እንዲሰማ
ሞላት መንፈስ ቅዱስ በመዝሙር በዜማ

አዝ።።።።።።
የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ ገረማት
ልጇ በማህፀን ቅኔን ሲቀኝባት
ድምጿን ከፍ አረገች አለም እንዲሰማ
ሞላት መንፈስ ቅዱስ በመዝሙር በዜማ


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

28.04.202519:29
♡ እንዘ ተሐቅፊዮ ♡


እንዘ ትሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ንኢ ማርያም(፪)
ንኢ (፫)ማርያም (፪)



የዋኖስ እናት ነሽ የእርግብ ወላዲቱ
ንኢ ሰናይትዬ ንኢ ናዛዚቱ
የእምነታችን ሙዳይ መንበር ለመስዋዕቱ
        
ገብርኤልም ይምጣ የደስታው አብሳሪ
ነይ ከሚካኤል ጋር ጨለማውን አብሪ
የሕግ ታቦት ሆይ በእኛ መኃል ኑሪ

        
ነጭ እና ቀይ ነው የአንቺ ፅጌሬዳ
የተዋሕዶ አክሊል መለኮት ፀአዳ
በቀይ ስጋ ደሙ አራቀን ከፍዳ
        
በሰቆቃው ሐዘን በማኅሌት ደስታ
በአንድ የሚሰማብሽ ለቅሶ እና እልልታ
የጽጌ ምሥጢር ነሽ የእጣኑ ሽታ



መዝሙር
ዘማሪት ትዕግስት ስለሺ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
26.04.202517:07
♡ ገብርኤል ነው እሱ ♡


ገብርኤል ነው እሱ አስደሳች መልአክ
አብሳሪሃ ለእመ አምላክ /፪/


ቂርቆስ ኢየሉጣ ከእሳት ሲጣሉ
ውሃ ሆነ ጠፋ ነበልባሉ /፪/

ቤተ መቅደስ ስትኖር ድንግል እመቤት
አበሰራት የአምላክን ልደት /፪/


ሠለስቱ ደቂቅም ከእሳት ሲጣሉ
ውሃ ሆነ ጠፋ ነበልባሉ /፪/

ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያዳነ
ገብርኤል ዛሬም ያድህነነ /፪/


┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
❣️❣️❣️

''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''

''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''


ውድ የመዝሙር ግጥሞች ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።



ሚያዚያ 11/2017 ዓ.ም
01.04.202517:45
♡ አባ ተክለሃይማኖት ♡

የእምነት ገበሬ መልካም ዘር የዘራ
በአምላኩ ታምኖ መቶ እጥፍ ያፈራ
አባ ተክለሃይማኖት የነፍሳችን ጌጥ
በጸና ኪዳኑ ምሕረትን የሚያሰጥ/2/


ለእውነት የመነነ ጽኑ ተጋዳይ
የጸጋ እንጀራ የማያልቅ ሲሳይ
በረከተ ብዙ የደሃ ድልባቸው
ቢበሉት ቢጠጡት የማያልቅባቸው

አዝ= = = = =

ከምድር እስከ ሰማይ የተተከለ ዐምድ
ሥላሴ ዘንድ ቀርቦ ለእውነት የሚማልድ
ቅዱስ ተክለሃይማኖት በሁሉ የሚወደድ
ጥግ ላደረጉት ሞገስ የዓለም ዘውድ

አዝ= = = = =

በተዋህዶ አምኖ ተዋህደን የኖረ
የምድራችን ብርሃን ጨለማን ያስቀረ
ዳግማዊ መቃርስ ለጽድቅ የጀገነ
ኢትዮጲያን አድኖ ለዓለም ጨው የሆነ

አዝ= = = = =

ሰይጣን ክህደትን መንቆሮ ያጠፋ
በኪዳኑ የሚያኖር የድኩማን ተሰፋ
የዓለም ፀሐይ ነው የተመረጠ ዕንቁ
የዓለም ፀሐይ ነው የተመረጠ ዕንቁ

መዝሙር
መምህር ፍስሀፅዮን ካሳ

       ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
     @maedot_ze_orthodox
      ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
🌷​​​​​​
እንኳን ለዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብር ኄር እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። መልካም ዕለት ሰንበት (ገብር ኄር)ና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።




┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gtmoch
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

፨🌸፨🌸፨🌸፨🌸፨🌸፨🌸፨
05.05.202522:38
♡ የማይሸረሸር አለቴ ♡

     
የማይሸረሸር አለቴ
የማይናጋ መሰረቴ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሞገሴ
አንተነህ የፅድቅ ልብሴ


ቀራንዮ ላይ የቆመ
በፍቅር የተተለመ
ከፊቴ ተነሰነሰ
ደምህ ህይወቴን ወረሰ/2/
እፎይ ልበል ልዘምር
ሆነህኛል ጌታ ክብር /2/


የሲና ምድር ህብስቴ
የተከተልከኝ አለቴ
መርገሜን ሰብሮ አለፈ
ሰላምህ ዉስጤ ጎረፈ /2/
እፎይ ልበል ልዘምር
ሆነህኛል ጌታ ክብር /2/

የማትደፈር ክልሌ
የድል አርማዬ አክሊሌ
ዓለምን ማሸነፊያዬ
አንተ ነህ ክንዴ ጌታዬ /2/
እፎይ ልበል ልዘምር
ሆነህኛል ጌታ ክብር /2/


መዳፎችህን አይቼ
በእንባ እረጠቡ ጉንጮቼ
ትዝታዬ ነዉ ዘወትር
የጅህ ወለላ ያ ፍቅር
ትዝታየ ነዉ ዘወትር
መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር
እፎይ ልበል ልዘምር
ሆነህኛል ጌታ ክብር /2/

ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻድቅ
https://t.me/maedot_ze_orthodox
28.04.202518:52
♡ ማርያም ማርያም ብዬ ♡



ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራው
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወለደኝ/2/


ገና በማህፀን በእናቴ የምጥ ቀን
ደጋግሜ ሰማሁ ሲጠሩት ስምሽን
በሰከንዳት እድሜ የማውቃት አንዲት ቃል
ልቤላይ ያለው ስም ማርያም ማርያም ይላል
ማርያም...ማርያም


አዝ= = = = =

ሔዋን ምጧ ቀሎ ልጆቿን ታቀፈች
በአመላጅነትሽ እናቴም ታመነች
በተወለድኩባት በመጀመሪያው ቀን
ስምሽን እየሰማሁ ወጣሁ ከማህፀን
ማርያም...ማርያም

አዝ= = = = =

ከቃልኪዳን ስም ጋር አደኩኝ አብሬ
ምልጃሽ ሳይለየኝ አለሁ እስከዛሬ
የሕይወቴን ፈደል ካንቺ ላይ ቆጠርኩኝ
በልጅሽ አምኜ ዳግም ተወለድኩኝ
ማርያም...ማርያም

አዝ= = = = =

የክፉ ቀን ስንቄ ያዘልኩሽ በልቤ
የሕይወቴ ምግብ እንጀራ መሶቤ
እንደትላንትናው ዛሬም እጠራሻለሁ
የመስቅል ስር ክብሬን እንዴት እረሳለሁ
የመስቅል ስር ክብሬን እንዴት እተዋለሁ

ማርያም...ማርያም
❤️❤️❤️


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

26.04.202517:07
ገብርኤል ነዓ

በነደ እሳት ሥዑል በጌራ ብርሀን ክሉል
መላዕከ መዊል ወኃይል ገብርኤል ነዓ ለሣህል


ርዕሰ ኃያላን    ቅዱስ ገብርኤል
መላዕከ ሰላም   ቅዱስ ገብርኤል
ተረጋጋ ባንተ የመላዕክት አለም
ባለንበት እንቁም ብለህ በአርያም

ዜናዊ ፍስሀ   ቅዱስ ገብርኤል
ሊቀ ትጉሃን    ቅዱስ ገብርኤል
ለድንግል አበሰርክ እንደምትወልድ ጌታን
ዘመኑ ሲፈጸም ያሰማኸን ደስታን
መላዕከ አድኖ   ቅዱስ ገብርኤል
አርያዋዊ    ቅዱስ ገብርኤል
ናዛዚ ህዙናን ለብስራታዊ
በፊቱ ያቆመህ አምላክ ማህያዊ

ሊቀ መላዕክት   ቅዱስ ገብርኤል
ጎፈ ነበልባል     ቅዱስ ገብርኤል
ወደኛ ቅረብ ለምህረት ወሳይ
አለቃ ገብርኤል ሀያል


በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ት/ቤት



┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
15.04.202519:50
♡ ቀራኒዮ አየሁት ♡


ቀራንዮ አየሁት ቀራንዮ አየሁት
የተጠማሁት ጌታን አገኘሁት
እረፍት ሆኖልኛል ሸክሜን ተሸክሞ
ሕይወቱን በሰጠኝ የኔን ሕይወት ታሞ


ቁስሉ ፈውሶኝ ጌታዬ
ንጹህ ደሙ ነው ዋጋዬ
የኔ አይደለሁም የራሴ
ለዋጀኝ አለኝ ውዳሴ
   
አዝ =====
ልብሴ ነው ለኔ እርቃኑ
ደስታን የሰጠኝ ማዳኑ
የኔን መሰደድ ተሰዶ
በክብር አስጌጠኝ ተዋርዶ
   
አዝ ======
የተቀበለው መከራ
የኔን ጨለማ አበራ
እንባየን ገድቦት ደሙ
በልቤ ሞልቷል ሰላሙ
   
አዝ =====
ፍቅር ያደከመው ኃይለኛ
ይጠብቀኛል ሳይተኛ
ቀድሞ እየወጣ በሰልፌ
ዛሬም አለሁኝ አትርፌ
   
አዝ ======
በምድረ በዳ መንጭቶ
ውሃ ሆነልኝ ተጠምቶ
ስፍራ አዘጋጄ በሰማይ
ጩኸቴን ጨኸ መስቀል ላይ
   
አዝ ======
ሰርጓጉት ሸለቆ ሞልቷል
አጥፊውም ሳይነካኝ አልፏል
ቀራንዮ ላይ ብቃቴን
አግኝቸዋለሁ ንጋቴን


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
01.04.202517:45
♡ አረሳት ኢትዮጵያን ♡

አረሳት ኢትዮጲያን በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው ነው ተወዳጅ በ ሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ



ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠ ከተማ
የእቲሳው ኮከብ የደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ

አዝ= = = = =

ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የእቲሳው አባት ፍስሐጽዮን
እግዚአርያ እናቱ ማህፀነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ

አዝ= = = = =

ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋ ና ቆላውን በመስቀል ባረካት

አዝ= = = = =

ምንጩና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
የአባታችን መስቀል ጽኑ ስለነካው
የተራመደበት የዳሰሰው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርና ቅጠሉ


ሊቀ መዘመራን ይልማ ኃይሉ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
🌷መጋቢት [20] እንኳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት ላስነሳበት ደግ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የጌታችን ቸርነቱ ፡ የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን።







❤️:::::::::::✝️:::::::::::❤️
显示 1 - 24 74
登录以解锁更多功能。