Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
ፒኤስጂ አርሰናልን አሸንፎ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ደረሰ
**************

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ፒኤስጂ አርሰናልን በድምር ውጤት 3 ለ 1 አሸንፎ ለፍፃሜው ደርሷል።

በመጀመሪያው ጨዋታ አርሰናልን በሜዳው 1 ለ 0 ያሸነፈው ፒኤስጂ ዛሬ ምሽት በሜዳው በተካሄደው ጨዋታም 2 ለ 1 አሸንፏል።

የዛሬውን የፒኤስጂ የማሸነፊያ ግቦች ፋቢያን ሩዪዝ ፔና በ27ኛው ዲቀቃ እና አሽራፍ ሐኪሚ በ72ኛው ደቃቂ ላይ አስቆጥረዋል።

አርሰናልን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ቡካዩ ሳካ በ76ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

ጨዋታውን በድምር ውጤት 3 ለ 1 ያሸነፈው ፒኤስጂ ትናንት ባርሴሎናን በማሸነፍ ለፍፃሜው ካለፈው ኢንተር ሚላን ጋር ለዋንጫ የሚጫወት ይሆናል።
በዮናስ በድሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኳታር ንጉስ ግርማዊ ሼኽ ታሚም አል ታኒ የተላከ መልዕክት በመያዝ የመጡትን የኳታር ሚኒስትር ዶክተር ሞሃመድ ቢን አብዱልአዚዝ አል ካሊፊን ተቀብለው አነጋገሩ።
ማን ለፍፃሜ ይደርሳል?

ስክሪን ሾት እያደርጋችሁ አጋሩን
ትራምፕ በፍቃደኝነት አሜሪካን ለቀው ለሚወጡ ህገ-ወጥ ስደተኞች የ1 ሺህ ዶላር ማበረታቻ አቀረቡ
******************

የአሜሪካ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች አሜሪካን ለቀው ለመውጣት ከወሰኑ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደሚሰጥ እና የጉዞ ክፍያቸውን እንደሚሸፍን አስታውቋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ጉዳዩ ለጋዜጠኞች ሲያብራሩ ህገወጥ ስደተኞች የቀረበላቸውን አማራጭ የሚቀበሉ ከሆነ አንድ ቀን ወደ አሜሪካ የሚመለሱበት ህጋዊ መንገድ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተናግረዋል።

እንዲሁም የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት (ዲ.ኤች.ኤስ) ፀሃፊ ክሪስቲ ኖም፤ ከአሜሪካ በራስ ፈቃድ መውጣት ከእስር ለመዳን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ወጪ ቆጣቢው መንገድ ነው ብለዋል።

የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት አክሎም፤ እቅዱ የገንዘብ ወጪን እንደሚቀንስ ገልፆ፤ እስካሁን ስደተኞችን ለመያዝ፣ ለማሰር እና ከሀገር ለማስወጣት በአማካይ ከ17 ሺህ ዶላር በላይ ወጪ እንደተደረገ አስታውቋል።

በእቅዱ መሰረት የመጀመሪያው ሕገወጥ ስደተኛ ከቺካጎ ወደ ሆንዱራስ ለመብረር አማራጩን እንደተቀበለ ዲፓርትመንቱ መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሴራን ታደሰ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ማስታወቂያ
***

የሲንቄ ባንክ ቪ.አይ.ፒ (VIP) ካርድ በመጠቀም የተሻለ የቀን ወጪ ገደብ እና ምቹ የዲጂታል ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ጋር የተሻለ  ባንኪንግ አገልግሎት ያጣጥሙ።ዛሬውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ ቅርንጫፎቻችን  ሄደው በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡

Kaardii VIP Baankii Siinqee fayyadamuun daangaa mallaqa guyyaatti fayyadamuu dandeessan foyya'aa ta'ee fi Tajaajila Baankii Dijitaalaa mijataa   waliin tajaajila baankii fooyya'aa  dhandhamadhaa. Dameelee baankii keenya isinitti dhihoo jiru deemtanii har'uma galmaa'uun tajaajila addaa kana fayyadamaa!!

Elevate your Banking Exprience with Siinqee Bank's VIP card.Get High withdrawal limit and dedicated support  for your extensive  premium and corporate needs. Apply today and experience the difference !!
#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ  #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan
#EMPOWERED_TOGETHER
ኢንተርሚላን 2 - 2 ባርሴሎና
************

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና ከእረፍት በፊት የነበረውን የ2 ለ 0 ውጤት ቀይሮ ጨዋታው 2 ለ 2 ሆኗል።

ኢንተርሚላኖች ላውታሮ ማርቲኔዝ በ21ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሃካን ቻልሃኖግሉ በ45ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች እየመሩ ወደ መልበሻ ክፍል ቢያመሩም፤ ባርሴሎናዎች ከእረፍ መልስ ኤሪክ ጋርሺያ በ54ኛው እና ዳኒ ኦልሞ በ60ኛው ደቂቃዎች ባስቆጠሯቸው ግብ አቻ ሆነዋል።

ሁለቱ ክለቦች በድምር ውጤት 5 ለ 5 ላይ ይገኛሉ፤ ጨዋታውን አሸንፎ ወደ ፍፃሜው የሚያልፈው ማን ይሆን?

በዮናስ በድሉ
07.05.202521:00
07.05.202514:40
እዚህ የተገኘነው ታሪክ ለመስራት ነው አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ

ኢቢሲ የስፖርት ገፅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ኢንተር ሚላን ባርሴሎናን 2 ለ 0 እየመራ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል
***************

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በሳንሲሮ ኢንተር ሚላን ባርሴሎናን በላውታሮ ማርቲኔዝ እና ሃካን ቻልሃኖግሉ ግቦች 2 ለ 0 እየመራ ወደ እረፍት አምርቷል።

በድምር ውጤት ኢንተር ሚላን 5 ለ 3 እየመራ ሲሆን፤ ባርሳ ውጤቱን ይቀለብሳል ወይስ ኢንተር ውጤቱን አስጠብቆ ወደ ፍፃሜው ያልፋል? ቀሪ 45 ደቂቃዎች ለሁሉም መልስ ይሰጣሉ።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ
አርሴናል በፒኤስጂ 1 ለ 0 እየተመራ ወደ እረፍት አመራ
**************

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ አርሴናል በፒኤስጂ 1 ለ 0 እየተመራ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቅቆ ወደ እረፍት ሰዓት አምርቷል።

የፒኤስጂን ግብ ፋቢያን ፔና በ27ኛው ዲቀቃ አስቆጥሯል።

ፒኤስጂ ጨዋታውን በድምር ውጤት 2 ለ 0 እየመራ ይገኛል።

አርሴናል ጨዋታውን ቀልብሶ ለፍፃሜው ይደርስ ይሆን?

ሐሳባችሁን በአስተያየት መስጫው ሳጥን ያጋሩን።
07.05.202517:28
07.05.202512:51
ቀጣዩን የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ ለመምረጥ የሚደረገው ሚስጢራዊ ጉባኤ
********************

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጥብቅ ዲሲፕሊን ከምትከውናቸው ሥርዓቶች መካከል የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ ዋነኛው ነው፡፡

የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመረጡበት ሚስጥራዊ ሂደት "ኮንክሌቭ" ለረጅም ዓመታት የዘለቀ ታሪክ አለው።

ይህ ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ያላት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተተኪ ምርጫ ሚስጢራዊ እና ተዓማኒ እንዲሆን አስችሎ የቀጠለ ነው።

በዚህ የምርጫ ሂደት የሚሳተፉት ካርዲናሎች ዕድሜያቸው ከ80 ዓመት በታች መሆን አለበት፡፡

መራጮቹ ማንኛውንም ሚስጢር ላያወጡ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ፣ ይህን ቃላቸውንም እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ይጠብቁታል፡፡

በሚስጥር በሚከናወነው በዚህ የምርጫ ስነ-ስርዓት ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ከ130 በላይ ካርዲናሎች ዛሬ በቫቲካን ስብሰባቸውን ጀምረዋል፡፡

ለመሆኑ ልዩ ስነ-ስርዓት ያለው የሮማ ካቶሊክ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ እንዴት ይከናወናል? መረጃውን ለማግኘት ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፦ https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=11043&fbclid=IwY2xjawKINmpleHRuA2FlbQIxMABicmlkETFJb05uWFRiQUpzTkRMUFVkAR6lpYvopmHrMqy575AGX9nRGPprQrL5oUnzSM4D5Y3aOxsWBLsM6oS-iBKJVg_aem_7SPbSyizlakAYHvqmqLMVQ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
07.05.202509:19
ካንሰርንም ባርሴሎናንም ያሸነፈው :- ፍራንቺስኮ አቼርቢ
*******************************

ህይዎት የእሱን ያክል የፈተነችው ያለ አይመስልም። ከታላላቆቹ የአውሮፓ ሊጎች አንዱ በሆነው ጣልያን ሴሪ ኤ ለመጫዎት ያለፈበት መንገድ እጅግ ፈታኝ ነው።

በሚላን ቪዞሎ የተወለደው ፍራንቺስኮ አቼርቢ በሀገሪቱ 2ኛው የሊግ እርከን ለብዙ ክለቦች ተጫውቷል።

በተለይ በ2010/11 በሴሪ ቢ ይሳተፍ የነበረውን ሬጊናን ወደ ሴሪ ኤ ለመመለስ የከፈለው ዋጋ እና በመከላካሉ ያሳየው ድንቅ ብቃት የትልልቅ ክለቦች አይን ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።

ከዚህ በኋላ በቼቮ ቬሮና፣ ጀኖዋ፣ እና ኤሲ ሚላን ቢየሳልፍም በሚፈልገው ልክ የመጫዎት ዕድል አላገኝም።

አቼርቢ 2013 ላይ ወደ ሴሪ ኤ ያደገውን ሳሱሎን በ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዩሮ ተቀላለቀ። ተከላከዩ ለሊጉ አዲስ ወደ ሆነው ክለብ ካመራ በኋላ አንድም ጨዋታ ሳያደርግ በሰውነቱ ውስጥ የካንሰር ምልክት እንደሚያሳይ በዶክተሮች ተነገረው።

በሚላን የተሳካ ህክምና አድርጎ ዳግም ወደ ጨዋታ ተመለሰ። ከህክምናው በኋላ ለአዲሱ ክለቡ ድንቅ ብቃቱን ቢያሳይም በህይወቱ ፈተና የማያጣው አቼርቢ ከ13 ጨዋታዎች በላይ ማድረግ አልቻለም።

በሳሱሎ እያለ በተደረገለት ምርመራ ሳያውቅ በተጠቀመው መድሀኒት ለስፖርተኞች የተከለከለ እና በህገወጥ መንገድ ጥቅም ላይ የዋለውን ቴስቲስትሮን የሚጨምር (gonadotropin) የተባለ አበረታች ንጥረ ነገር በሰውነቱ ውስጥ በመገኝቱ በጣልያን እግር ኳስ ፌደሬሽን እገዳ ተጣለበት።

የእግር ኳስ ህይወቱ አደጋ ላይ የወደቀው ፍራንሲስኮ አቼርቢ እገዳ ላይ እያለ በተሰማው የህመም ስሜት ወደ ሆስፒታል ሲያመራ ቀድሞ የታየበት የካንሰር ህመም ወደ ሌላ ደረጃ ተሸጋግሮ የዘር ከርጢት ካንሰር እንዳለበት ተረጋገጠ።

የካንሰር ደረጃው አይደለም ዳግም ብዙ ወደ ሆነለት እግር ኳስ መመለሱ ይቅርና በህይወት የመቆየቱን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ከተተው። በርካታ የጣልያን ጋዜጦችም የአቼርቢ የእግር ኳስ ህይወት በሚያሳዝን ሁኔታ ተጠናቀቀ በማለት ዘገባዎች ሰሩ፡፡

ለነገሮች በፍጹም እጅ መስጠት የማያውቀው ጣልያናዊው ተከላካይ ለ6 ወራት የእግር ኳስ ልምምዱን ከህክምናው ጋር በሚገባ ሲከታተል ቆይቶ 2014 መጋት 15 ቀን አሁን ሁሉም ነገር ተጠናቋል ለጨዋታ ዝግጁ ነኝ በማለት በፌስቡክ ገጹ አስነበበ፡፡

እነዚያ ሞቱን ሲጠብቁ የነበሩ ጋዜጦች ስለ አስገራሚው ሰው ታሪክ መጻፍ ጀመሩ። እሱም ለህይወቱ አደጋ የሆነውን ካንሰር አሸንፎ ለሳሱሎ በአጠቃላይ 157 ጨዋታችን አደረገ፡፡

2018 ላይ ወደ ላዚዮ ያመራው አቼርቢ በሴሪ ኤ ታሪክ በ149 ተከታታይ ጨዋታች ላይ በመሰለፍ 162 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ከቻለው ሀቪየር ዛኔቲን በመቀጠል ሌላ ታሪክም ሰርቷል፡፡

በ2022 ከላዚዮ ወደ ኢንተር ሚላን የተዛወርው ፍራንሲስኮ አቼርቢ ትላንት ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሌላ ተአምር የሰራበትን ምሽት አሳልፏል።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ባርሴሎናን አሸንፎ ለፍጻሜ እንዲደርስ ትልቁን ሚና ተወጥቷል።

በጁሴፔ ሜዛ በተደረገው ጨዋታ እስከ 90ኛው ደቂቃ 3 ለ 2 ሲመራ የነበረው ኢንተር ሚላን በ3 አመት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ለፍጻሜ ለመድረስ ያለው ተስፋ ቢያበቃም የዳኛው ፊሽካ ሲጠበቅ በባከነ ደቂቃ ከካንሰር ያመለጠው ሰው የኢንተርን 3ኛ ግብ ከመረብ አሳረፈ።

በአቼርቢ ግብ ወደ ጨዋታ የተመለሰው ኢንተር በተጨመረው 30 ደቂቃ አንድ ግብ አስቆጥሮ ከ15 አመት በኋላ በአውሮፓ መድረክ ለመንገስ ለፍጻሜ የደረሰበትን ውጤት አስመዘገበ።

አውሮፓ ላይ ካሉ እንደ ሃላንድ፣ ሃሪ ኬን እና ሮሜሉ ሉካኩ አይነት ታላላቅ አጥቂዎች ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ የአንድ ለአንድ ግንኙነቶችን ያሸነፈው ፍራንቺስኮ አቼርቤ በምሽቱ ፍልሚያ የባርሴሎናን አስፈሪ አጥቂ ተቋቁሞ ከሚጠበቅበት መከላከል በላይ አጥቂ ሆኖ ተአምር የሰራበትን ምሽት አሳልፏል።

በአንተነህ ሲሳይ
የሳንሲሮው ሕልም መሳይ ጨዋታ በኢንተር ሚላን አሸናፊነት ተጠናቀቀ
****************


በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ኢንተርሚላን ከባርሴሎና በሳንሲሮ ያደረጉት ጨዋታ በኢንተር ሚላን 4 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ኢንተር ሚላኖች 2 ለ 0 እየመሩ ወደ መልበሻ ክፍል ቢያመሩም ባርሳዎች ከእረፍት መልስ 2 ግቦችን በማስቆጠር አቻ ከመሆን አልፈው 3ኛ ግብ አስቆጥረው 3 ለ 2 መምራት ችለው ነበር።

ሆኖም ኢንተር ሚላኖች የአቻ ግብ አስቆጥረው ጨዋታው ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ እንዲያመራ አድርገዋል።

በስተመጨረሻም ኢንተርሚላኖች የ30 ደቂቃው የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ በዴቪድ ፍራቴሲ አማካኝነት የማሸነፊያ ግብ አስቆጥረዋል።

የብዙዎችን ቀልብ በሳበው በዚህ አስደናቂ ጨዋታ ኢንተር ሚላኖች 4 ለ 3 አሸንፈው በድምር ውጤት 7 ለ 6 በሆነ ውጤት ለ2025ቱ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ደርሰዋል።

ብርቱ ትግል ያደረጉት ባርሴሎናዎች አሳዛኝ ተሸናፊ ሆነው ከዘንድሮው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በግማሽ ፍፃሜው ተሰናብተዋል።

ኢቢሲ የስፖርት ገፅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
የተጠባቂው የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል
********************

በባለሜዳው ኢንተር ሚላን በኩል የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው ሲባል የነበረው ላውታሮ ማርቲኔዝ ቋሚ ሆኖ ጀምሯል። ኢንተር ሚላን 3-5-2 አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል።

በባርሴሎና በኩል አጥቂው ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በተቀያሪ ወንበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ወሳኙ ተከላካይ ኩንዴ በጉዳት ከስብስቡ ውጪ ነው። ባርሳ በ4-2-3-1 አሰላለፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ተገልጿል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

ኢቢሲ የስፖርት ገፅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
የተጠባቂው ጨዋታ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል
*****************

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ ከ አርሰናል አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።

አርሰናል 4-3-3 አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ የሚገባ ሲሆን በአማካኝ መስመሩ ላይ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ያልነበረው ቶማስ ፓርቴ በዛሬው ጨዋታ ወደ አሰላለፍ ተመልሷል።

በፒኤስጂ በኩል ወሳኙ ተጨዋች ኡስማን ዴምቤሌ ተጠባባቂ ሆኖ ጨዋታውን ይጀምራል። ፒኤስጂም በተመሳሳይ 4-3-3 አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ ይገባል።

በሀ/ሚካኤል ክፍሉ
07.05.202517:26
ራሱን ለዓለም ያሳየበትን ፒኤስጂን የሚገጥመው ሚኬል አርቴታ
************************

በ1990ዎቹ መጨረሻ የ18 ዓመት ወጣት የነበረው ሚኬል አርቴታ በፒኤስጂ ቤት ራሱን ለዓለም ያሳየበት ጊዜ ነበር።

እግር ኳስን በባርሴሎና ቢ ቡድን የጀመረው አርቴታ የነ ሊዊስ ኤኔሪኬ፣ ፔፕ ጋርዲዮላ፣ ፊሊፕ ኮኩና ኢማኑኤል ፔቲ ድንቅ የአማካኝ መስመር ጥምረት ለስፔናዊዉ አማካኝ ወደ ዋና ቡድኑ ለመቀላቀል ነገሮችን አክብደውበታል።

በዚህም ወደ ፈረንሳይ አቅንቶ የዋና ከተማዋን ክለብ ፒኤስጂን በመቀላቀል ገና በጊዜ ነበር ታላላቅ ጨዋታዎችን ማድረግ የጀመረው።

በዚህም ከኤሲ ሚላን ጋር በነበረው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ አማካኝ መስመሩ ላይ ጅናሮ ጋቱሶ እና አንድሬ ሼቭሼንኮን የተቆጣጠረበት መንገድ ቀልብን የሚስብና ዛሬም ድረስ የሚታወስ ነው።

ሚኬል አርቴታ በሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ራሱን ለዓለም ያሳየበትን ቡድን ዛሬ አስልጣኝ ሆኖ በሜዳው ፓርክ ደ ፕሪንስ ይገጥማል።

ከምንም በላይ ደግሞ በባርሴሎና ቡድን ውስጥ ከሊዊስ ኤነሪኬ አትሻልም ተብሎ ወደ ፒኤስጂ የተሸኘው አርቴታ ቦታ ያሳጠውን የሀገሩን ልጅ ኤንሪኬን አሸንፎ ለማለፍ ትልቅ ፈተና ይጠብቀዋል።

ከሊዊስ ኤንሪኬ መምጣት በኋላ እንደ ቡድን መጫወት የጀመረው ፒኤስጂ በገነባው ወጣት ቡድን አርሰናልን 1 ለ 0 አሸንፎ መምጣቱ ለአርቴታው ቡድን ጨዋታውን ከባድ አድርጓታል።

ነገር ግን ፒኤስጂ በአውሮፓ መድረክ አንድ አስከፊ ታሪክ አጋጥሞት ያውቃል ባርሴሎናን በሜዳው 4 ለ 0 አሸንፎ በመልሱ ጨዋታ 6 ግቦች ተቆጥረውበት መሸነፉ አሁንም ቢሆን በደጋፊዎች ዘንድ አይረሴው ክስተት ነው።

በግማሽ ፍፃሜ ታሪክ በሜዳቸው ተሸንፈው ውጤቱን ቀልብሰው ማለፍ የቻሉት አያክስ እና ቶተንሃም ብቻ ሲሆኑ አርሰናል ይህን ታሪክ ለመጋራት ፓሪስ ላይ ከትሟል።

የጆኧ ኔቬስ፣ ቪቲንሀ እና ፋቪያን ሩይስ ጥምረት ከቶማስ ፓርቴ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ እና ዴክላን ራይስ የመሀል ሜዳ ፍጥጫ የጨዋታው ወሳኝ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በሀ/ሚካኤል ክፍሉ
07.05.202511:58
በድምሩ 13 ግቦች በተቆጠሩበት አስደናቂ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ኢንተር ሚላን የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋገጠ፡፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ብቻ 43 ግቦችን ያስቆጠረው ባርሴሎና በመጨረሻም እጅ ሰጥቷል፡፡

ኢቢሲ የስፖርት ገፅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
14 ያለቀላቸውን ግቦች ያዳነው የኢንተሩ ግብ ጠባቂ ያን ሶመር አስደናቂ ምሽት
***********************

የኢንተር ሚላኑ ግብ ጠባቂ ያን ሶመር በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች የባርሴሎናን 14 ያለቀላቸውን የግብ ሙከራዎች አክሽፏል።

ሶመር ባለፉት 15 ዓመታት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ላይ ሁለተኛው ብዙ ግብ ያዳነ ግብ ጠባቂ መሆን ችሏል።

ከዚህ በፊት እንዲህ ያለው አስደናቂ ስራን በመስራት ጂያንሉጂ ቡፎን 17 ኳሶችን ከግብ በማዳን ሪከርዱን ይዞ ይገኛል።

ያን ሶመር ባሳየው የምሽቱ ድንቅ ብቃት የኢንተር ሚላን እና ባርሴሎና ጨዋታ ኮከብ ተጫዋች ተብሎም ተመርጧል።

ኢንተር ሚላን የአሁን የማንችስተር ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናናን በ50 ሚሊዮን ዩሮ ሲሸጥ ያን ሶመርን ከባየር ሙኒክ በአውሮፓውያኑ 2023 በ6 ሚሊዮን ዩሮ ነበር ያስፈረመው።

ታዲያ ኢንተር 50 ሚሊየን ዩሮ በኦናና አትርፎ በ6 ሚሊየን ዩሮ የገዛው የ36 ዓመቱ ሶመር ከተጠበቀውም ከተከፈለውም ገንዘብ በላይ የኢንተር ሚላን ዋስትና ሆኖ ተገኝቷል።

በሴራን ታደሰ

ኢቢሲ የስፖርት ገፅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ባርሴሎና የ2 ለ 0 ውጤትን እየቀለበሰ ነው
************

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና ከእረፍት በፊት የነበረውን የ2 ለ 0 ውጤት ቀይሮ ጨዋታው 2 ለ 3 ሆኗል።

የባርሴሎናን 3ኛ ግብ ራፊንሃ አስቆጥሯል።
ሩስያና ዩክሬን የጦር ምርኮኞች ልውውጥ አደረጉ
*********

ሩስያ እና ዩክሬን የ410 የጦር ምርኮኞች ልውውጥ ማድረጋቸውን የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።

በተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ሸምጋይነት 205 የሩስያ ምርኮኞች የሥነ ልቦና እና የጤና ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ በቤላሩሰ በኩል ለሩስያ ተላልፈው ተሰጥተዋል።

በተመሳሳይ 205 የዩክሬን ምርኮኞችም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ተብሏል።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የጦር ምርኮኞቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ገንቢ ሚና ለተጫወቱ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች እና ሌሎች አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱ ሀገራት ዛሬ ያደረጉት የጦር ምርኮኞች ልውውጥ ከ15 ቀናት በፊት ያደረጉት የ246 የጦር ምርኮኞች ልውውጥ ቀጣይ እርምጃ መሆኑን ዘገባው ያመላክታል።

በላሉ ኢታላ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
显示 1 - 24 1 579
登录以解锁更多功能。