በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በጦርነት ከተጎዱት አካባቢዎች አንዱ በዋግኽምራ ዞን የሚገኛው አበርገሌ ወረዳ ነው። ዮሐንስ ዘሪሁን(ዶ/ር) ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ለአካባቢው ማኅበረሰብ በነጻ አገልግሎት የሚሰጥ ቤተመጽሐፍት እና የፈጠራ ማዕከል ለማቋቋም በዝግጅት ላይ ናቸው። የዚህ ማዕከል ዋና ዓላማ ከጦርነት በማገገም ላይ ያለው አበርገሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶችና ሕጻናት ጊዜያቸውን በአግባቡ የሚያሳልፉበት ነገር በማጣት አልባሌ ቦታ በማሳለፍ ላይ በመሆናቸው እርሱን መቅረፍ እና ከማንበብ አልፈው በቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ በአእምሮ እንዲጎለብቱ ማድረግ ነው።
ለማዕከሉም የተለያዩ መጽሐፍትን እና አስፈላጊ ግብዓት መሆን የሚችሉ ማንኛውንም አይነት ቁሳቁሶች በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ።
እስካሁን ባደረጉት እንቅስቃሴ ከ700 በላይ የሆኑ የተለያዩ መጽሐፍቶች እና የተወሰኑ የኮምፒውተር ቁሳቁሶች መሰብሰብ ችለዋል።
ማንኛውም አይነት መፅሐፍ ያላችሁና መለገስ የምትፈልጉ @yohans0 (0968353446) ን አናግሩት ያላችሁበት ድረስ መጥቶ ከምስጋና ጋር ይቀበላችኋል።