Анатолий Шарий

Реальний Київ | Украина

Лёха в Short’ах Long’ует

Труха⚡️Україна

Николаевский Ванёк

Инсайдер UA

Реальна Війна | Україна | Новини

Лачен пише

Nairaland Pulse | News

Анатолий Шарий

Реальний Київ | Украина

Лёха в Short’ах Long’ует

Труха⚡️Україна

Николаевский Ванёк

Инсайдер UA

Реальна Війна | Україна | Новини

Лачен пише

Nairaland Pulse | News

Анатолий Шарий

Реальний Київ | Украина

Лёха в Short’ах Long’ует

ባ ይ ራ | Bayra
ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine)
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
https://www.facebook.com/share/g/164RfjiHaN/?mibextid=wwXIf
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት
ኢ-ሜይል bayradigital2016@gmail.com

关联群组

ባይራ |Bayra Chat
58
记录
18.05.202523:59
4.3K订阅者08.05.202516:32
300引用指数11.05.202511:27
2.3K每帖平均覆盖率11.04.202504:17
2.3K广告帖子的平均覆盖率14.05.202510:07
5.03%ER11.05.202510:30
54.97%ERR16.05.202504:09
ዕጣ ፈንታ
(ልዑልሰገድ አስማማው)
ነጋ ደግሞ ሩጫዬን ልጀምር፡፡ ህይወት ሩጫም አይደለች? ናት እንዴ ግን? ማነው ሩጫ ናት ያለው? እንጃ አባቱ። ሩጫነቷን ለማስመስከር ማስረጃ ማቅረብ ባልችልም ግን ሩጫ ትመስለኛለች። ባትሆንም ግድ የለኝም።
ለእንደእኔ አይነቷ ተራ ደንብ አስከባሪ ህይወት እንዲህ ናት እንዲያ ናት ብሎ መፈላሰፍ ምን ሊረባ? ተነስቶ ከላይ እስከታች አንደ ጎመን አረንጓዴ የደንብ ልብስ ለብሶ፣ አረንጓዴ ኮፍያ ተኮፍይቶ፣ አረንጓዴ ጫማ ተጫምቶ፣ ሽመል ዱላ አንግቶ መውጣት... ። አለቆቻችን ህገወጥ ነጋዴዎች ያሏቸውን ከመንገድ መንገድ ማባረር፣ ማሳደድ፤ ድል ቀንቶኝ ነጋዴ ወይም ጥሎት የፈረጠጠውን እቃ ከያዝሁ ለአለቃ ማስረከብ፤ ከዚያ ደሞዝ መብላት።
ታዲያ ህይወት ለእኔ ሩጫ ናት ብል ተሳሳትሁ? ማንን ነው የምጠይቀው? እንጃ አባቱ። አሁን አሁንማ ህይወት በራሷ አስጠልታኛለች። ከእንቅልፌ ስነሳ እንኳን የሆነ አርባ ምናምን ወይም ሰማኒያ ወይም መቶ ምናምን ኪሎሜትሮችን ሮጬ ሮጬ ሮጬ... ከጫፉ የደረስሁ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ። ተኝቼ ስነሳ ይደክመኛል። መነሳቱ ሳይሆን ቀጣይ አንድ ቀን ጭማሪ እየኖርሁ እንደሆነ እያሰብሁ ይደክመኛል፤ ስበላ ይደክመኛል፤ ስሄድ ይደክመኛል፣ ስቆምም ሆነ ስቀመጥ ይደክመኛል። ቀኑን ሰድጄ ሳሳድድ ውዬ ወደ ቤቴ ስገባም ይደክመኛል። የሚደክመኝ ግን ሰዶ ማሳደዱ አይደለም። ቀጣይ ሌላቀን እንደሚመጣ ማሰቡ ነው።
ሰው ሲያፈቅር ካፈቀረው ሰው ሃሳብን ብቻ አይደለም ለካ የሚያተርፈው። ኃይሉንም ጭምር ነው የሚጋራው። ያ ኃይል ነበር ለካ ህይወቴን አስደሳች እና አጓጊ የሚያደርጋት። ምክንያቱም ተስፋ ነበረኛ። ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ስራ እንደምሄድ ሳይሆን አሱን ለማየት እንደሆነ ነበር የማስበው። ሲስቅ ሳቁን እያየሁ ልደሰት፣ ሌሊት ለህልሜ የሚሆነኝን ቁመናውን ልመረምር፣ ላጤነው እና ልመዘግብ እንደሆነ እያሰብሁ ነበር የምሄደው።
ማታ ከስራ ወደ ቤቴ ስመለስ ደግሞ ናፍቆቴን ታቅፌ ለተጨማሪ ሌላቀን ላየው እንደሆነ እያሰብሁ፣ ተስፋዬን በልቤ ጉያ፣ ምግቤን በፌስታሌ ሸክፌ ነበር የምጓዘው። አስታውሳታለሁ ያቺን ዕለት። አሱን ያየሁባትን፤ ፍቅር እንደ ንብ እዝዝዝ እያለች መጥታ ጣፋጭ መርዞቿን ከልቤ ላይ የተከለችበትን ዕለት።
ትዝ ይለኛል ጎመኔ ለብሼ፣ ጎመኔ ተጫምቼ፣ ጎመኔ ኮፍያ ኮፍይቼ፣ ወደ ተለመደው ሰዶ ማሳደዴ ሳዘግም፤ እሱ እና የስራ አጋሮቹ ደንብ ሽሽት ካርቶኒያቸውን በእጆቻቸው እንደሸከፉ አስፓልቱን ተሻግረው የሁለቱ መንገዱች አካፋይ ላይ ቆሙ። አንዴ ወደኛ ሌላ ጊዜ ወደ አስፓልቱ ውል ውል እያሉ ድንገት አሱም ሲዞር እኔም ወደ እነሱ ስመለከት ዓይኖቼን በዓይኖቹ ገጫቸው። ዓይኖቼም ተስለመለሙ። ይጨፍኑ ይግለጡ ግራ ገባቸው፡፡
ብቻ ቢጫ ቀይ አረንጓዴ ሃምራዊ፣ ሰማያዊ ምናምን የሆኑ ጉራማይሌ ቀለሞች ታዩኝ። ከዚያን ግዜ ጀምሮ ፍቅር መልኩ እንዴት ነው ቢሉኝ እንደዚህ አይነት ነው ብዬ እናገራለሁ እያልሁ አስባለሁ። ከመስለምለሜ በነቃሁበት ቅፅበት አብረውኝ የነበሩት ተራ አስከባሪዎች ተከትለዋቸው ሄደዋል፟፤ እያሳደዷቸው። እኔ ግን ልቤን ለእሱ አስረክቤ ጓደኞቼ እነርሱን ሲያሳድዱ የኔም ልብ ከእሱ ጋር እንድትሳደድ ፈቅጄ ቆሜ ቀረሁ። ጓደኞቼም አሳደው ሲደክማቸው ይሁን ሲደብራቸው ተመልሰው መጡ። እኔ ግን ካለ ልብ ቀረሁ። ልቤን የተሸከመው ካርቶኒ ውስጥ ከልብሶቹ ጋር ያስቀምጣት አልያም ከልቡ ውስጥ ባላውቅም ልቤ ግን ሄዳለች።
ከዚያች ቀን ጀምሮ በፍቅሩ ተለከፍሁ። ቀርቤ እንኳን የማየት እድሉን ማግኘት አልቻልሁም ነበር። ስቀርበው ይሸሸኛል። እኔ ወደ እሱ ስጠጋ የሚያየው አፍቃሪውን ሳይሆን አሳዳጁን፣ የእህል ውሃውን ገመድ የሚበጥስበትን ጠላቱን ነው። እንዴትስ ብሎ እንድጠጋው ይፈቅድልኛል? የተረገመ ስራ። የተረገመ መገጣጠም። አሁን ካልጠፋ ስራ እኔ ደንብ አስከባሪ እሱ ህገወጥ ነጋዴ መሆን ነበረብን? ምናለበት እኔ የሱቅ ነጋዴ እሱ ሸማች ብንሆን? ወይም ደግሞ እኔ አስተናጋጅ እሱ ተስተናጋጅ ብንሆን? ፍልቅልቅ እያልኩ ሳስተናግደው፤ ፈገግታዬን አይቶ ሲማረክ፤ ተማርኮ በአገልግሎቴ ተደስቶ ቲፕ ሲሰጠኝ፤ አትጥፋ ብዬ በፈገግታ ስመልስለት....። እንደዚህ መሆን አንችልም ነበር?
እንዲያም ቢሆን ግን ተስፋ ሳልቆርጥ ያገኘሁትን አጋጣሚ ለመጠቀም መሞከሬን አላቆምሁም። እሱም መሸሹን አልተወም። ታዲያ በአንደኛው ሌሊት ከእርሱ ጋር ስላፋ፣ ስሳሳም እና ስተሻሽ፣ ተሻሽቼም ስተቃቀፍ፣ ተቃቅፌም ደረቱን ተንተርሼ ስተኛ፤ የደረቱ ጸጉር ኮሰኮሰኝ። እና ከእንቅልፌ ባነንሁኝ። ሌሊቱ ነግቶ ነበር። ከእንቅልፌ ስነቃ ትንፋሽ እንደማጠር፣ የልቤም መምታት እንደማቆም አደረገኝ። ከጉንጬም ከጭኖቼ ላይም አንደመቀዝቀዝ አይነት ስሜት ተሰማኝ። ስቅስቅ ብዬ አነባሁ።
ከስራዬ ቀርቼም ቢሆን አሳዳጁን ሳይሆን አፍቃሪውን ሆኜ ላገኘው፣ ፍቅሬንም ልናዘዝለት አሰብሁኝ። ግን ደግሞ ስራዬስ? ምን ምክንያት ሰጥቼ ከስራዬ ልቅር? "ህገ ወጥ ነጋዴ ስላፈቀርሁ የደንብ ልብሴን ለብሼ ላናግረው ብል ይሸሸኛል። ስለዚህ ከስራ ቀርቼ ላግኘው" ብላቸው ይሰሙኛል? ለነሱ ፍቅር ምናቸው ነው? ቢያንስ የመጀመሪያ ቀን እንደምንም ልሞክር እና ካልሆነ ግን ስራዬንም መስዋዕት አድርጌ አግኝቼው በውስጤ ያመቅሁትን ስሜት እተነፍሳለሁ ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ።
ተነሳሁም አረንጓዴ ለበስሁ፣ አረንጓዴ ተጫማሁ፣ አረንጓዴ ተኮፈየሁም። ከቤቴ ወጥቼ እነርሱ ወደሚሰሩበት ቦታ አመራሁ። ድንገት ልቤ ድው... ድም... ድው... እያለች ስትደልቅ አካባቢዬን ቃኘት ቃኘት አደረግሁ። የማፈቅረው ልጅ ድሬድ ጸጉሩን ወደኋላው አስሮ፣ ጥቁር ሆኖ ፊቱን የሞላው ጺሙን አጎፍሮ፣ ከመንገዱ ዳር ቆሞ ሸሚዞች በእጁ ይዞ የቀረውን ልብስ በካርቶኒው አድርጎ አግሩ ስር አስቀምጦ አየሁት። ለየሁትም።
ቀጥታ ወደእሱ ለማምራት ፈለግሁ። ግን ፊት ለፊቱ ስሄድ ካየኝ ሳልቀርበው በሩቁ ይሸሸኛል ብዬ አሰብሁ። መንገድ ቀይሬ ከኋላው ለመምጣት እንዲመቸኝ አስፓልቱን እነሱ ካሉበት በብዙ እርቄ ተሻገርሁና በሰዎች መሃል እየተከለልሁ አጠገቡ ልደርስ፣ ጥቂት ሜትሮች ምናልባትም አስር የማይሞሉ ያህል ሲቀረኝ ድንገት ዞር አለ። ዓይን ዓአይን ተገጣጠምን። ለማመን በሚቸግር ፍጥነት ከእግሩ ስር ያለው ካርቶኒ አንስቶ አስፓልቱን ለመሻገር ሲፈተለክ፣ የመኪና ፍሬን ሲንሳጠጥ፣ የሰው ኡኡታ ሲቀልጥ፣ እኔም በቆምሁበት ሲጨልምብኝ እኩል ሆነ።
ስነቃ ልብሴ በውሃ ርሷል። አካባቢዬን ስቃኝ የእግረኛ መንገድ ላይ ተኝቻለሁ። የሆነ የማላውቀው ኃይል አስገድዶኝ ዓይኖቼን ወደ አስፓልቱ ወረወርሁ። አስፓልቱ ቀይ ምንጣፍ የተነጠፈበት መስሏል። ከምንጣፉ ጎንም ጸጉሩን ያደረደ፣ ጺሙን ያጎፈረ ወጣት እንደኔው መንገድ ላይ ተኝቷል።
ከ ባይራ ቅጽ 1 ቁጥር 4 ላይ የተወሰደ
ያንብቡ፣ ያጋሩ፣ ቤተሰብ ይሁኑ።
በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ!
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

14.05.202504:44
ግማሽ ጨረቃ
(ሩት ሐብተማርያም)
የዛ ማዶ ሰዎች ዘፈን አያምራቸው
አጅሬ ትዝታ አልገባም ቤታቸው
.
.
.
... ቀያይ ጭኖቼን አጋልጦ የሚያሰጣ ቀሚስ ለብሼ ከባንኮኒው ላይ ተሰይሜአለሁ። በአጭሩ የተቆረጥኩት ፀጉሬ አንገቴን ይኮሰኩሰኛል። ረጅም ነበረ። ምፅፅፅ ከንፁህ ህፃንነቴ ጋር ተቆረጥኩት። አይኖቼ አስቀድቼ በመዳፌ መሃል ከማንከላውሰው ብርጭቆ ላይ ተሰፍቷል። ሴተኛ አዳሪ ነኝ። ጨዋ ሴተኛ አዳሪ ታውቃላችሁ? ሃሃሃ እሺ ፍቅር የያዛት ሴተኛ አዳሪስ ታውቃላችሁ? አታውቁም። ምክንያቱም ሁሉቱንም እንዳትሆን መስመር አበጅታችሁላታል። ፍቅር የእናንተ ግዛት ነው። ጨዋነት ደሴታችሁ ነው።
እዚህ ጎዳናው ላይ ከሚተሻሸው የሰው ጥላ መሃል ያልነካኝ ጥቂቱ ነው። ያልዳበስኩት ፎረፎር ፤ ያልዳሰስኩት ገላ ፤ ያላተናፈገኝ የታመቀ የሰውነት ጠረን ጥቂት ነው። ከገላዬ ተሻሽተህ ስንት ትከፍለኛለህ? ስንት አወጣለሁ? ባንተ ሚዛን ስንት ነኝ? ስል አምሽቼ ዋጋዬ የመሰለውን ከከፈለኝ እና ከቆነጠረልኝ ሰው ጋ ተጋድሜ አድራለሁ። ነገሩ እንዲህ እንደማወራው አይቀልም። ሀብሀብ እንደመቁረጥ፤ የአሃያ ዝንጣፊ ዘንጥፎ ጥርስ መሃል እንደመሰንቀር ፤ ነገሩ ቀላል አይደለም። በእርግጥም ከማያውቁት ሺህ ገላ ጋ መጋደምም ሩቅ ሆነው እንደሚያስቡት ከባድ አይደለም። ቤተሰቡ እጁን አሰፍስፎ ለሚጠብቀው ሰው ፤ በአራስ ልጇ ጉሮሮ ወተት ለማንቆርቆር ለተሳናት እናት፣ ትይዘው ትጨብጠዉ ላጣች ነገሩ እንብዛም ከባድ አይደለም። ያው እንደ መዛኙ ይለያያል።
... ብዙ ወንዶች በህይወቴ መጥተው ሄደዋል። ገላዬ ልክ እንደ ገንዳ ነው። ሁሉም ያሻውን ደፍቶ ይሄዳል። ታዲያ እያንዳንዱ ወንድ የሚለያየው ለገንዳው ያለው እሳቤ ነው። አንዳንዱ ለገንዳው የሚጥለው ቆሻሻ በረከት ሲመስለው በተግባሩ ከገንዳው የተሻለ የሚመስለው ነው። አንዳንዱ ደሞ ገንዳው የጋራ መሆኑን ረስቶ የግሉ እንዲሆን ተመኝቶ የሚቀና ነው። አንዳንዱ እንደ ወንፊት ገንዳውን ካልጠፈጠፈ የማይሆንለት ነው። አንዳንዱ ደሞ ንፅህናውን በገንዳው መቆሸሽ ይለካል። መሄጃ የሌለው ይሄ ገንዳ እኔ ነኝ። ይሄን ገንዳ እንዳሻቸው እንዲሆኑበት የፈቀድኩት እኔው ነኝ።
እንደ ማንኛውም ሴት ነኝ። ሁሉም ሴቶች የሚሰማቸው ሁሉ ይሰማኛል። ሴተኛ አዳሪ ናት ብለው የማይተውኝ ስሜቶች አሉኝ። አፈቅራለሁ ፤ እናፍቃለሁ ፤ በፍቅር መሳም መነካት ያምረኛል ፤ ከልቤ ከት ብዬ እስቃለሁ ፤ እቀናለሁ ... ምናምን ብቻ ብዙ። ስለማይተውኝ እንጂ ሁሉም ቢተውኝ እወድ ነበር። እሺ ቆይ በሞቴ ለእኔ ማፍቀርና መናፈቅ ምን ይሰራልኛል? አንድ ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ ሁለቱ ስሜቶቼ ከፊቴ ቆመው
"ሰማሽ አንቺ ሴት ... እስካሁን አብረን ቆየን። ብዙም የጠቀምንሽ አልመሰለንም። ብንሄድና ብንርቅሽ ሳይሻል አይቀርም። አንቺም እዚህ ስላለን ደስ ያለሽ አትመስይም። " ብለው ከአጠገቤ እርምጃ ቢጀምሩ እኔ እንጃ ታግዬ ማስቀረቴን። እሰይ! እሰይ! በቸር ግቡ። 'ማረፊያችሁን ያሳምርላችሁ።' አለማለቴንም እንጃ።
...
ተማሪ ነበርኩ። መቼ ወደዚህኛዉ ዓለም እንደመጣሁ አላውቅም። ብቻ ግን እየሳቅሁ እጄን ይዞ እያሳሳቀ ወደ ስርቻው እንዳመጣኝ አውቃለሁ። ይሄኛዉ ኑሮ!! መጀመሪያ አካባቢ ይሞቅ ነበር። ልክ እንደአዲስ ፍራሽና ብርድልብስ በምቾት ነበርኩኝ። ኦህ የልጅነት ሙቀትና ሳቅ!! ሁሉም ከሰፈፌ መቅዳት ሲፈልግ ፤ እዛኛዉ ጥግ ያለው ከዚህኛው ሲጣላብኝ ፤ ሴቶች በእኔ ሲቀኑ ጥሩ እየኖርሁ ልዕልት የሆንሁ መሰለኝ። ጉዱ በኋላ እንደሆነ የትኩስነት ወላፈን የገረፈው አእምሮዬ አላሰበም ነበር። ሁሉም የፈለኩትን እንዳላገኝ ሴተኛ አዳሪነቴ ልክ እንደመታወቂያ እንደሚከተለኝ የተረዳሁት ዘግይቼ ነው። የኛ ሰው መለያ መስጠት አይከብደው። እከሊት እኮ እንዲህ ናት ማለት መች ደክሞት?
ሙዚቃ እወዳለሁ። ብዙ ነገሬን ስለሚያስረሳኝና ከሰዉነቴ ጋር ለመግባባት ትግል ስለማይጠይቀኝ ሙዚቃ ወዳጅ ነኝ። አንዳንድ ማለዳ ድንገት ተነስቼ ክፍሌ ዉስጥ ሁሉን ረስቼ በከፈትኩት ሙዚቃ አቅሌን አጥቼ ስወድቅ ስነሳ ዓለም የሞላልኝ እመስላለሁ። መቼም ለተመልካች አጀበኛ ትርኢት ነው። እንደዚህ የማደርገዉ መንገዱን የቱ ጋ እንዳቆምሁ ሲጠፋኝ ፤ የነገ አቅጣጫዉ ወዴት እንደሆነ ስስት ፤ የቱን አንስቼ የቱን እንደምለቅ ግራ ሲገባኝ እንደሆነ መንገደኛ የት ይገባዋል? መንገደኛ ፈራጅ ነው። በራሱ የሰኞ ማክሰኞ ጨዋታ የሰውን አጨዋወት የሚለካ ግራ የገባው ፍጥረት ነው።
...
እንዴት እንቁም? እንጃ! እንዴት እንውደቅ እንጃ! እንዴት እንሙት? የት እንቀበር? እንጃ! ዓለሙ ሁሉ ለጥያቄዎቹ መልስ የለውም። በርግጥ የረባም ጥያቄ የለንም። ከተውነው ላይ እንጀምራለን።
መጀመሪያ ያየሁት የምሰራበት ቦታ ነው። ጠይም፤ ፂማም ደሞ ባለክምክም ጎፈሬ።
ላስተናግደው ስሄድ ያወጣት "ቢራ አገኝ ይሆን" የምትል ቅላፄውና ትህትናው ሰውነቴን ከፈሉት። ኦህ "ቢራ አገኝ ይሆን?" ጥዑም ሙዚቃን ያስንቅ ነበር። ቀልጠፍ ብዬ አመጣሁለት። ፀጉሬን ቀሚሴን አስተካከልሁ። ኦህ! ያ ሁሉ ወንድ በዓይኑ ሲከተለኝ ኬር የማይሰጠኝ ልጅ መታየት አማረኝ። እንዲያየኝ ፈለግሁ። እሱ እቴ። ያንን ፂሙን እየፈተለ እንኳን ሊያየኝ ራሱንም ረስቷል። ኤጭ!! ሲያምር ግን ...
እንጀራ አልፈልግም፣ ምን ያደርግልኛል
ትዝታውን ይዤ፣ ልሂድ ይበቃኛል።
...
በተደጋጋሚ ሲመጣ ተለማመድን። ደሞ የሚቀባው ሽቶ የዝባድ ነው መሠል ከሱ ውጭ ማንም ጋር አጣጥሜው አላውቅም። ኦህ ጠረኑ!! ከጎኑ ቁጭ እላለሁ። እንጀራዬን እረሳለሁ። ራሴን እረሳለሁ። ከንፈሩን እያየሁ ከንፈር የሚመጠጥለት ህይወቴን ረሳለሁ። ስለምደው ባሰብኝ። ለማላውቀው ገላ ገላዬን አስገዝቼ ማንም እንዳይነካኝ ተከላከልሁ። ርሃብ ሲፀናብኝ አንዳንዴ አልፎ አልፎ ብቻ መርጬ እሄዳለሁ። እንደዛም ሆኖ ጠረናቸው ከገላዬ እንዳያድር በውሃ አፀዳለሁ። ህሊናዬን ባያፀዳውም። እሱን ብቻ ቤቴ ወስጃለሁ። ትራሴ ላይ ያለው ጠረን የእሱ ብቻ ነው። እንደንግስት አሰብኩት ራሴን። ጥሩ ለመሆን ጣርኩ።
...
የመጨረሻ ቀን ሲመጣ ደስ ብሎት ነበር። ምነው ስለው ለእሱም ለእኔም ቢራ አዞ ወደ እኔ ዞረ። እ ንገረኛ በሚል ዓይን ሳየው የምወዳት ፍቅረኛዬ የጋብቻ ጥያቄዬን ተቀበለችኝ አለኝ። አልደነገጥኩም። አልቀናሁም። ድንዝዝ አልኩ። እንባዬ ብቻ ታዘዘኝ። አንድ ጠብታ ብቻ የምጠጣው መጠጥ ላይ ገብታ ወደ ሆዴ ገባች። የምወድሽ ጓደኛዬ ነሽ አለኝ። ካንቺ ጋር ያደረግነው ያው ስህተት ቢሆንም ግን ህይወቴ ውስጥ ግን የማልፍቀው ትዝታ ነው አለኝ። ከፍሎ ሄደ። ስንት ሰዓት እንደተቀመጥኩ አላውቅም። ወንበር ሲነሳሳ ገላዬን እየጎተትኩ ወጣሁ።
....
ዛሬ ሰርጉ ነው!!!
ገላዬን እንደአዲስ እያዘዝኩ ነው።
ፀጉሬ አሁንም ይኮሰኩሰኛል።
ያምራል ብሎኝ ነበር።
ሚስቱ እንዲህ ተቆርጣ ይሆን??
.
.
አብረን እንደር?
ከ ባይራ ቅጽ አንድ ቁጥር ሁለት ላይ የተወሰደ

15.05.202504:41
አልቻልሁም አግዙኝ!
(ሳምራዊት ንጉሤ)
አባት ልጁን ይዞ እየሄደ እያለ፥ በመንገዳቸው ዛፎችን ያያሉ። ከዚያም ልጁ አባቱን "አባቴ ይሄንን ዛፍ አነቃንቄ ቅጠሎቹን ማንቀሳቀስ እችላለሁ?"ብሎ ጠየቀው።
አባቱም "አዎ! ሙሉ አቅምህን ከተጠቀምህ በደንብ ትችላለህ" አለው። ልጁ አባቱ እንዳለው ወደ ዛፉ ይሄድና ዛፉን መነቅነቅ ይጀምራል።
ቆይቶ ወደ አባቱ እያየ "አባቴ አልቻልሁም" አለው።
አሁንም አባቱ "ሙሉ አቅምህን ተጠቀም ትችላለህ" አለው።
ልጁም እንደገና ሞከረ አልቻለም። አባቱንም "አባቴ ሙሉ አቅሜን ተጠቀምሁ ግን አልቻልሁም" አለው እያዘነ።
"ሙሉ አቅምህን አልተጠቀምህም"። እኔ አብሬህ አለሁ። እንዳግዝህ ግን አልጠየቅኸኝም!"አለው አባትየው።
እርዳታ መጠየቅ ክብራችንን የሚቀንስብን የሚመስለን ስንቶቻችን ነን? “አግዘኝ” ማለት ሞት የሆነብን። "እሱን እርዳኝ ከምል ብሞት ይሻለኛል" ብለን እናውቃለን እኮ።
አቅም እናድርጋቸው። አንዳንዶች "በእኔ ነው እኮ እዚህ የደረሰው እንጂ እሱ ምኑን ችሎት"ይላሉ። ይበሉ! ለእኛ መወጣጫ አድርጎ ካዘጋጃቸውስ? እሱን ፈርተን አይደል “እርዱኝ”፥ “አግዙኝ" የማንለው። "ኧረ በኋላ ጉራውንም አልችለው"እያልን ስንቱ አመለጠን?
አንዳንዶቻችን ለመርዳት፤አንዳንዶቻችን ለመረዳት የተፈጠርን ቢሆንስ? ግን ደግሞ "ይሄ አለኝ ይሄን ጨምርልኝ፤እስከእዚህ መጣሁ የቀረውን አግዘኝ"፥ ለማለትም ትንሽም ይኑረን። ሰዎች ጥረታችንን ሲያዩ ደስ እያላቸው ይረዱናልና።
ከ ባይራ ቅጽ 1 ቁጥር 3 ላይ የተወሰደ

23.04.202512:28
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
ታላላቆች ነን!

09.05.202504:41
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን!
Stay tuned.
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
Stay tuned.
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

08.05.202513:34
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ቅጽ 2 ቁጥር 1
ነገ ምሽት ይጠብቁን።
Stay tuned!
በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com
ኑኒ ባይራክ

09.05.202518:14
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ቅጽ ሁለት ቁጥር አንድ

登录以解锁更多功能。