➪ በዛሬው እለት የሚከወነው የኖቲንግሃም ፎረስት እና የቶተንሃም ስፐርስ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ምን ምን ለውጦች በሊጉ ላይ ሊያሳድር እንደሚችል እንመልከት ፦
1. ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታውን ቢያሸንፍ ፦
. ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ለኖቲንግሃም ፎረስቶች ትልቅ እና አሳሳቢ የሆነ ጉዳይ ነው ፤ ምክንያቱም ይህን ጨዋታ ካሸነፉ ወደ አውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ቀጣይ አመት መሳተፋቸውን ለማረጋገጥ አንድ እርምጃ ስለሚሆናቸው ነው ።
. ኖቲንግሃም ፎረስቶች የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ አሁን ካሉበት 6ተኛ ደረጃ ወደ ቀድሞ ቦታቸው 3 ደረጃ የሚመለሱ ይሆናል ።
. በዚህም የለንደኑን ክለብ ቼልሲ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ጭምጭምታ በዛሬው ጨዋታ ሊደፍኑበት ይችላሉ ።
2. ቶተንሃም ጨዋታውን ቢያሸንፍ ምን ሊፈጠር ይችላል ፦
. ቶተንሃም ዘንድሮ ደካማ የውድድር አመትን እያሳለፉ ቢሆንም የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ግን አሁን ያለበትን የውጤት ቀውስ በትንሹም ቢሆን ሊፈታለት ይችላል ።
. ቶተንሃሞች የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ አሁን ካሉበት 16 ተኛ ደረጃ ወደ 13ተኛ ደረጃ ከፍ እንዲሉ ያደርጋቸዋል ።
. ቶተንሃሞች የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ ለኢፒስዊች ደጋፊዎች አሳዛኝ ዜናን የሚናገሩ ይሆናል ፤ በዚህም ኢፒስዊች ቀጣዩን ጨዋታቸውን ከተሸነፉ ወደ ሻምፒዮን ሺፕ መውረዳቸውን እንዲያረጋግጡ ያደርጋቸዋል ።
" SHARE " | @DREAM_SPORT