19.04.202515:20
ተመስገን🙏

18.04.202512:42
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እንዲህ አለ
“ዘበእንቲአሃ ለቤተክርስቲያን ተጸፋእከ በውስተ ዐውድ ከመ ትቀድሳ በደምከ ክቡር።
ዘበእንቲአሃ ዝግሐታተ መዋቅሕት ፆረ። ወተዐገሠ ምራቀ ርኩስ እንዘ አልቦ ዘአበሰ አምላክ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቅለ።”
ምን ማለት ነው? ትርጉም፦
ለቤተክርስቲያን (ለነፍሳት ለምእመናን ለሰው ልጅ ሁሉ) ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው።
ለርስዋ ሲል ታሥሮ መጐተትን የቻለ፤ የበደለውም በደል ሳይኖር ርኩስ ምራቅን ሲተፉበት የታገሠ አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ።
ዲያቆን ቡሩክ ተስፋዬ

✍️ዲያቆን ቡሩክ ተስፋዬ
@Father_advice

03.04.202519:40
+ ከአንተ ባላውቅም .+
በገነተ አበው (The Paradise of fathers) መጽሐፍ ላይ ይህ ታሪክ ተጽፎአል::
አንድ መነኩሴ በበአቱ ቁጭ ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብ አንድ ቃል ሊገባው አልቻለም:: ለመረዳት በጣም ሲያስቸግረው "ይኼን ቃልስ እንዲገልጽልኝ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አለብኝ' ብሎ ወሰነ:: ነቢያቱ ያደርጉት እንደነበረውም እግዚአብሔር የቃሉን ፍቺ እስኪገልጽለት ድረስ መጾምና መጸለይ ጀመረ:: ነገር ግን ለሰባ ሳምንታት ያህል እየጾመ ቢጠባበቅም ምንም ነገር ሊገለጽለት አልቻለም:: በየሳምንቱ መጨረሻ ቃሉን ደግሞ ሲያነበውም የበለጠ እየተወሳሰበበት ሔደ እንጂ ጨርሶ ሊገባው አልቻለም::
በመጨረሻም ተስፋ ቆረጠ:: ስለዚህ ሌላ መነኩሴ ጋር ሔዶ ስለዚህ ቃል ትርጉም ሊጠይቀው ወሰነ:: በአቱን ዘግቶ መንገድ ሊጀምር ሲዞር ግን የእግዚአብሔር መልአክ በፊቱ ቆሞ ታየው::
"አይዞህ አትፍራ የፈለግኸውን የቃሉን ትርጉም ልገልጽልህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬያለሁ' አለው::
መነኩሴው ግራ ገባው "የጌታ መልአክ ሆይ ሰባ ሳምንት ሙሉ እየጾምሁ እንዲገልጥልኝ ስለምን ቆይቼ ምንም መልስ አላገኘሁም:: አሁን ተስፋ ስቆርጥ እግዚአብሔር ስለምን መለሰልኝ" አለ በፍርሃት ውስጥ ሆኖ
"እግዚአብሔር ሰባ ሳምንታት ከጾምኸው ጾም ይልቅ ወንድምህን ለመጠየቅ በመሔድ ያሳየኸውን ትሕትና ተቀብሎታል' አለው::
አላዋቂ መስሎ መታየትን ያህል የምንፈራው ነገር የለም:: "አላውቀውም አንተ ንገረኝ” ከማለት ይልቅ ብዙ ሰው ሞት ይመርጣል:: ትንሽ ተምሬያለሁ የሚል ሰውማ ጥያቄ መጠየቅ ዲግሪውን ማቃጠል ይሆንበታል:: የብዙዎቻችን ትሕትና የማፈቅድልን ሰዓት ለመጠየቅ ብቻ ነው:: "ከአንተ አላውቅም ...' ብለው የሚጀምሩ ዐረፍተ ነገሮች ራሱ ልብ ብለን ከሰማናቸው ይዘታቸው “ከእኔ አታውቅም ነው::
የእውቀታችንን ውስንነት ለማመን የሚከብደን በሥጋችን ውስጥ ያለችው ለባዊት ነፍሳችን በሥጋዊ እውቀት ራስዋን መገደብ ስለምትቸገርም ነው::እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ''አሁን ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ ብሎ የእውቀትን ውስንነት ማመን ግን ዕረፍት ይሠጣል:: 1ቆሮ. 13:12
በመንፈሳዊው ዓለም እንዲህ ሲሆን ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ እውነታ ነው:: "የቀለም ቀንድ 1 "የእውቀት ምንጭ'' 1 ''መልስ በጉንጩ'፣ 'ተጠያቂው የሚለውን የክብር ሥፍራ ስንፈልግ በማናውቀው ጉዳይ ሌሎችን ከመጠየቅ ይከለክለናል:: አላውቀውም አላነበብኩትም አልሰማሁትም ከማለት ይልቅ ሁሉን አዋቂ ሆኖ ለመገኘት ስንል የምንበላቸው ዕፀ በለሶች ብዙ ናቸው::
'ብዙ የማውቀው ነበረ ሰዓት ገደበኝ እንጂ " ብሎ ውስን እውቀቱን ባሕር ለማድረግ የሚደክምና ሰዎች ከተናገረው ከጻፈው በላይ አድርገው እንዲያሰቡት የሚገፋፋ ሰው የሚወለደው ካላዋቂነት ፍርሃት ውስጥ ነው:: በጥቂት ንባብ ውስጥ ራስን በጥልቅ ምሁር ዓይን ማየትና “እኔ የማውቀው ማወቁን ነው" ማለት የአላዋቂነት ፍርሃት የሚወልዳቸው ኢሶቅራጥሶች መርሕ ነው::
ከሌላው በታች አላዋቂ መስሎ መታየትን እንፈራለን:: ስለዚህ ሌላውን ከመጠየቅና እንደ ጃንደረባው ''የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?” "ነቢዩ ይኼን ስለማን ተናግሮታል?' ብሎ ከመማር ይልቅ በራሳችን ለመረዳት ብንሟሟት እንመርጣለን:: ብዙ የእምነት' denominations የተፈጠሩትም ሌላውን ከመጠየቅ ሞት በሚመርጡ ትዕቢተኞችና እንደገባኝና እንደተረዳሁት” በሚል አስተሳሰባቸው እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል::
"ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር” ፊልጵ. 2:3
©ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
+++ 🌿@father_advice🌿+++

02.04.202509:14
መስቀል
" መስቀሉ የምስጢር በር ነው። በዚህ ደጅ አእምሮ ወደ ሰማያዊ ምስጢር እውቀት ይገባል። የመስቀሉ እውቀት የተሰወረው በመስቀሉ መከራ ውስጥ ነው።
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
+++ 🌿@father_advice🌿+++
" መስቀሉ የምስጢር በር ነው። በዚህ ደጅ አእምሮ ወደ ሰማያዊ ምስጢር እውቀት ይገባል። የመስቀሉ እውቀት የተሰወረው በመስቀሉ መከራ ውስጥ ነው።
በመከራውም ተካፋይ በሆንን መጠን በመስቀሉ የምናገኘው ግንዛቤ እየጨመረ ይሄዳል።
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
+++ 🌿@father_advice🌿+++
31.03.202508:33
"ችግር እና መከራ የሌለበትን ህይወት አትመኑ
የምታተርፉት ምንም ነገር የለምና::"
ዮሐንስ አፈወርቅ
የምታተርፉት ምንም ነገር የለምና::"
ዮሐንስ አፈወርቅ

21.03.202510:01
የሰማህ ሰው ሰይጣን ብሎ እንዳይጠራህ ማንንም ሰው አትማ ።
ስያሜውን ከጠላ ሐሜትን የምታፈቅራት ከሆነ ሰይጣን ብለው ሲጠሩህ አይክፋህ
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
🌿@father_advice🌿

19.04.202510:44

18.04.202508:07
ስትሰቀል ብኖር አልጠራጠርም
መዳኛ ነውና ሞትህ ለእኔ ጥቅም
እንደ ምል
ይ ሰ ቀ ል
መዳኛ ነውና ሞትህ ለእኔ ጥቅም
እንደ ምል
ይ ሰ ቀ ል
03.04.202513:32
በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሒሳብ ትምህርት ሲሰጥ አንድ ተማሪ እንቅልፍ ወስዶት ነበረና የክፍል ጓደኞቹ ሲያወሩ ከእንቅልፋ ነቃ። ትምህርቱ ሲያልቅ አስተማሪው በነጭ ሰሌዳው ላይ ሁለት ችግሮችን እንደጻፈ አስተዋለ። ከእንቅልፋ የነቃው ተማሪ እነዚህ የቤት ስራዎች ናቸው ብሎ ስለገመተ በኋላ ለመፍታት ወደ ማስታወሻ ደብተሩ ላይ ጻፈ ።
ችግሮቹን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሞክር በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አገኛቸው። ሆኖም ግን ፈታኝ ቢሆንም ከችግሮቹ አንዱን ለመፍታት እስኪችል ድረስ በቤተ መፃህፍቱ ውስጥ ሰዓታትን አሳልፎ ማጣቀሻዎችን እየሰበሰበና እያጠና በጽናት ቀጠለ።
በቀጣይ ቀን አስተማሪው ትላንት ሰሌዳ ላይ ፅፎት ስለነበረውና መልስ የላቸውም ስላላቸው ጥያቄዎች ሳያነሳ ወደ ቀጣይ የትምዕርት ርዕስ ገባ ።
ከእንቅልፉ የነቃው ተማሪ የማወቅ ጉጉት ስለነበረው እጁን አውጥቶ ሲፈቀድለት ከመቀመጫው ተነስቶ "ዶክተር፣ ትላንት ሰሌዳ ላይ ፅፈኸው ስለነበረው ጥያቄ ለምን አልጠየቅክም?"
አስተማሪው "አስፈላጊ ነው? የግዴታ አልነበረም። ሳይንስ እና ሳይንቲስቶች እስካሁን ያልተፈቱትን የሂሳብ ችግር ናቸው ተብለው ከሚጠቀሱት ለምሳሌ ያህል ያመጣዋቸው ናቸው ። መልስ ባልተገኘለት ጥያቄ ላይ ጊዜ ማባከን ስለሌለብን ነው ያላነሳሁት ።"
ተማሪው በሁኔታው ተደናግጦ " ዶክተር እኔ ግን አንዱን በአራት ወረቀት ፈታሁት!"
ከእንቅልፋ የነቃው ተማሪ ያገኘው መፍትሄ በመጨረሻ ለእሱ እውቅና ተሰጥቶት በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተመዝግቧል። በጉዳዩ ላይ የጻፋቸው አራት ወረቀቶች አሁንም በተቋሙ ለእይታ ቀርበዋል።
ተማሪው ችግሩን መፍታት የቻለበት ቁልፍ ምክንያት አስተማሪው "ማንም መፍትሄ አላገኘም" ሲል አለመስማቱ ነው። ይልቁንም ችግሩ ሊፈታ የሚገባ መሆኑን አምኖ በመጨረሻ ተሳክቶለታል።
ወዳጄ ሆይ :— አንድ ነገር ማሳካት እንደማትችል የሚነግሩህን አትስማ። አንዳንድ ሰዎች ሆን ብለው የውድቀት እና የብስጭት ዘሮችን ይተክላሉ።
አላማህን ለማሳካት፣ እንቅፋቶችን ለማሸነፍ እና ምኞቶችህን ለማሟላት የሚያስችል ኃይል አለህ። በቀላሉ በፈጣሪ ታመን እና ሞክር።

02.04.202505:44
✍️ እውነተኛ እና ሐሰተኛ ሰባኪ
ይህ ቃል ሁሉም የኦርቶዶክስ ታላላቅ አባቶች የጻፉት ፣ የተናገሩት፣ ያስተማሩት ለእኛም ያቆት ታላቅ መመርያና መስገንዘቢያ ነው ። በረከታቸው ይድረሰን።
✝️ " ሳይማር የሚያስተምር ዕውርን እንደሚመራ ዕውር ነው፤ ሁለቱም ወደ ጕድጓድ ይወድቃሉ።"
✝️"ያለ እውቀት መናገር ከእንጀራ ይልቅ መርዝ መመገብ ነው"
"ያልተማረው መምህር እንደ መካን ዛፍ ነው - ፍሬ የለውም ቅጠል ብቻ ነው."
✝️ " የማያውቀውን ለማስተማር የሚተጋ አሳሳች እንጂ እረኛ አይደለም።"
✝️ "ማስተዋል የጎደለው መምህር የነፍስ ሌባ ነው እውነትን እየነጠቀ ነው።" –
✝️ "መጀመሪያ ሳይማር ማስተማር ማለት መሠረት የሌለው ቤት መሥራት ነው."
✝️"አንድ ሰው መጀመሪያ ሌሎችን ከማጥራት በፊት መንጻት አለበት፤ ሌላውን ከመሙላቱ በፊት መሞላት አለበት።"
✝️" አላዋቂ ሰባኪ እንደ ደረቅ ጉድጓድ ነው - ውሃ ቃል ገብቷል ነገር ግን የለውም." -
✝️ " ሐሰተኛ ሰባኪ የበግ ለምድ ለብሶ መንጋውን ከማሰማት ይልቅ እንደሚበላ ተኩላ ነው።"
✝️ " ኩሩ እና አላዋቂ አስተማሪ ከግልጽ መናፍቅ የበለጠ አደገኛ ነው።" .
✝️ " ሰነፍ መምህር በአሸዋ ላይ ይገነባል፤ ማዕበሉ ሲመጣ ስራው ይፈርሳል።"
✝️ "ያለ እውቀት የሚያስተምሩ ፍርደኞች ናቸው"
✝️ "እውነትን የማያውቅ ሰባኪ በነፋስ እንደሚወጣ ገለባ ያለ ቃል ይናገራል።" –
✝️"ሐኪሙ ከታመመ እንዴት ሌሎችን ይፈውሳል?"
✝️ " ዕውር መሪ ሰዎችን ወደ ጥፋት ይመራል."
✝️ " ያልተማረ አስተማሪ ያፈርሳል እንጂ አይገነባም,
✝️ " ቅዱሳት መጻሕፍትን ያላጠና መምህር ሰይፍ እንደሌለው ወታደር ነው።"
✝️" አላዋቂ መምህር ከራሱ ሁለት እጥፍ የገሃነም ልጆችን ደቀ መዛሙርት ያደርጋል።"
✝️ " ሳይገባው ቢያስተምር ራሱንም ሰሚዎቹንም ያታልላል።"
✝️ "ከመናገርህ በፊት ስማ፤ ከማስተማርህ በፊት ተማር"
✝️ " በትክክል ለማስተማር በመጀመሪያ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን አለበት."
✝️ "ጥበብን የሚፈልግ ያገኛታል፤ ጥበብ አለኝ ብሎ የሚገምት ግን በጨለማ ይቀራል።"
✝️" ሰባኪ ለብዙዎች ማሰናከያ እንዳይሆን አስቀድሞ በሚሰብከው መሠረት ይኑር።"
✝️"ቃልህ ውሸት እንዳይሆን የማታደርገውን አታስተምር።" -
✝️ "መምህሩ በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ አለበት."
✝️" ሰባኪ በትዕቢት ወድቆ ራሱን እንዳያበላሽ አስቀድሞ ከፍ ከፍ ሳይል ይዋረድ።"
✝️" ትህትና የሌለበት እውቀት በእብድ እጅ እንዳለ ሰይፍ ነው።"
✝️ "ለጥበብ መጀመሪያ ካልጸለይክ በኋላ ለመናገር አታስብ።"
✝️ "አንድ ሰባኪ በቃላቱ ብቻ ሳይሆን በመልካም ባህሪው መታወቅ አለበት."
✝️ "እያንዳንዱን ሰበኪዎችን በቅዱሳት መጻሕፍትና በቅዱሳን አባቶች ትምህርት ፈትኑ"
✝️ " ለእውነት ፍቅር ሳይሆን ለጥቅም ከሚያስተምሩ ተጠንቀቁ።"
✝️ " አታላዩ ሰባኪ ብዙ ይናገራል ነገር ግን ምንም አይጠቅምም."
✝️ " ሰባኪ ከአባቶች ትውፊት ጋር የሚጋጭ ከሆነ ከእግዚአብሔር አይደለም." –
✝️ " እውነተኛው ሰባኪ የክርስቶስ አገልጋይ እንጂ በራሱ ትምክህት አይደለም።"
✝️ "መናፍቅ በጣፋጭ ቃል ይናገራል ልቡ ግን ተንኰል ሞልቶበታል" -
✝️ "የውሸት አስተማሪዎች ጭብጨባ ይወዳሉ፣ እውነተኛ
አስተማሪዎች እውነትን ይወዳሉ።" .
✝️"ሰባኪ መሆን የሚፈልግ ሰው በመጀመሪያ ትእቢቱን መግደል አለበት." –
✝️ " እውነተኛ መምህር ከሰው ምስጋና ይልቅ የእግዚአብሔርን ፍርድ ይፈራል።"
✝️ "ስለ ራሱ ብዙ የሚናገረውን እና ስለ ክርስቶስ ትንሽ የሚናገር ሰባኪ አትከተል."
✝️"ጥበብ የሌለው ሰባኪ ዘይት እንደሌለበት መብራት ነው - በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይጠፋል."
✝️ "ከመናገር እና ከማሳሳት ዝም ማለት መማር ይሻላል"
✝️" እውነተኛ ሰባኪ የእግዚአብሄርን ክብር እንጂ የራሱን ዝና አይፈልግም።"
✝️"ብልህ ሰባኪ በራሱ ማስተዋል አይታመንም ነገር ግን ከአባቶች ምክርን ይፈልጋል።"
✝️ "ያልሰለጠነ አእምሮ ሌሎችን በጽድቅ ማሰልጠን አይችልም" –
✝️" የማይማር ሰባኪ ቀድሞ ጠፍቷል."
✝️ " ስለ ክርስቶስ የሚናገሩ ሰባኪ ሁሉ ክርስቶስን የሚያውቁ አይደለም ።"
✝️ "ታላቁ ሰበኪ በአርአያነቱ የሚያስተምር ነው።"
✝️ "ከሰው በላይ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰባኪ ሁሌም እውነትን ይናገራል"

31.03.202505:36
አለማመኔን እርዳው🙏
ማር. ፱፥ ፳፬
ማር. ፱፥ ፳፬

20.03.202519:05
ነገሮች የምሸከምበት ጥንካሬን እንዲሰጠኝ እግዚአብሄርን ለምኜው ነበር።
እርሱ ግን በእርሱ ግን በእርሱ ላይ እንድደገፍበት የሚያደርገኝን ድካም ሰጠኝ
ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ
🌿@father_advice🌿
በራሱ ትግል ከሚታመን ሀያል ይልቅ እግዚአብሄርን ጉልበት የሚያደርግ ደካማ ይበረታል እግዚአብሄር ከሚያስረሳ ጥንካሬ ይልቅ እርሱ ላይ የሚያስደግፍ ድካም ይሻላል ✍️ዲ/ን አቤል ካሳሁን

18.04.202523:09
ጌታ በመስቀል ከሞተ በኃላ ሰንበት ገብቶ ጸጥታ ሆነ፡፡ እውነትም ለሁላችን የእረፍት ሰንበት ሆነ፡፡ገዳዮቹም ሰንበትን ለማክበር ቤታቸው ተቀመጡ፡፡ ነገር ግን ኃጢአተኞች ነበሩ፡፡ ህግ ከ10ሩ በአንዱ እንኳ መበደል ኃጢአት ነው ይላልና፡፡ ጠዋት ገደሉ ማታ ሰንበት አከበሩ፡፡ ዛሬ ጸጥ ብሏል፡፡ ገዳዮቹ አሸናፊነት እየተሰማቸው በኩራት ተቀመጡ፡፡ እነማርያም መግደላዊት ከቀመሙት ሽቶ ጋ የሰንበትን መውጣት ይጠባበቃሉ። መቃብር ከበታቹ ቅዱስ ኃያል ጌታን በጭንቀት ተሸክሟል፡፡ ክርስቶስ በማህጸነ ማርያም እንደተመሰገነ በመቃብርም ለታረደው በግ ኃይል ክብር ማዳን ይገባዋል እየተባለ እየተመሰገነ ነበር፡፡ በመቃብር ጸጥታ ውስጥ ትልቅ ሥራ ነበር፡፡ በወህኒ ለነበሩ ነጻነትን እየሰበከ ነበር፡፡ በጸጥታ ውስጥ የበጉ መዝሙር እያንጎደጎደ ነበር፡፡ በአይሁድ ህሊናም ፍርሃት እየነደደ ነበር፡፡ ስለዚም መቃብሩ በጭፍራ ተጠበቀ፡፡ ሞቶ የሚያስፈራ እንደጌታ ኢየሱስ ማን ነው? ንጹህ የገደለ ሲደነብር ይኖራል፡፡ የጌታ ንግግር ብቻ ሳይሆን ዝምታውም ያስፈራል፡፡ ሞቶ ታሪኩ ያበቃ እንጂ ሞቶ የሰራ ማን ነው?
✍️ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም
✍️ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም

04.04.202517:02
"ኸረ እኔ ዕውር አይደለሁም"
አንድ ዓይነ ሥውር በእጁ ደማቅ ብርሃን ያለው ፋኖስ ይዞ በጨለማ በመንደር ውስጥ እየሔደ ነው:: አንድ ሰው ድንገት ሲያልፍ አየውና ፋኖሱን ሲያይ ተገርሞ ጠየቀው::
"ይቅርታ ወንድሜ:: በእጅህ ፋኖስ አብርተህ ይዘሃል:: እንዳትደናቀፍ ነው እንዳልል እንደማይህ ዓይነ ሥውር ነህ:: የማታይ ከሆነ የፋኖሱ ብርሃን ምን ይጠቅምሃል?" አለው::
"ልክ ነህ የፋኖሱን ብርሃን አላይም:: የምይዘው እኔ በጨለማ ውስጥ ስሔድ እንዳልደናቀፍ አይደለም:: ሆኖም በጨለማ ውስጥ ብርሃን ሳልይዝ ከሔድኩ ሰዎች እኔን ስለማያዩኝ ከእኔ ጋር እንዳይጋጩ ወይንም እንዳይደናቀፉ ነው:: ፋኖሴንን ከያዝሁ በብርሃኑ እኔን ያዩኛል" ብሎ መለሰለት::
ወዳጄ በዚህች ጨለማ ዓለም ስትሔድ የልብህ ዓይን በመታወሩ ምክንያት የማታያቸው ብዙ እንቅፋቶች አሉ:: "ኸረ እኔ ዕውር አይደለሁም" ካልክ "ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፡ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ" ነው:: (ራእ 3:17)
በጨለማው ዓለም ስትሔድ ለራስህ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ማሰብ ትገደዳለህ:: እውነተኛውን ፋና ክርስቶስን በጉያህ ከያዝክ ሰዎች እሱን አይተው በአንተ ከመሰናከል ይድናሉ:: አለዚያ ግን በአንተ ምክንያት የሚደናቀፈው ሰው ብዙ ነው::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

03.04.202503:12
መንግስተ ሰማያት ቀርባለች እና ንስሐ ግቡ ፦ ንስሐ ምንድን ነው?
1) "ንስሐ እንደ አዲስ መታደስ የጸጋ መመለስ ነው።
2) "ቤተ ክርስቲያን የኃጢአተኞች ሆስፒታል እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችም።"
3)፡ "የንስሐ ደጅ ሁል ጊዜ ክፍት ነው ጌታም ይቅር ለማለት አይታክትም።"
4)- "ንስሐ የትሕትና ልብ ፍሬ ነው።"
5)- "ንስሐ ሰው ወደ ሰማይ የሚወጣበት መሰላል ነው።"
፡- "እውነተኛ ንስሐ በኃጢአት ከወደቀ በኋላም በትልቁ የጸሎት እንደገና መቆም ነው።"
6) "ንስሐ ነፍስን ታነጻለች ገላን እንደሚያነጻ ሳሙና ነው"
7፡- “ንስሐ የነፍስ ወደ መጀመሪያዋ ወደ እግዚአብሔር መመለሷ ነው።
8) "ንስሐ ለኃጢአት ማዘን ብቻ ሳይሆን ወደ ኃጢአቱ ላለመመለስ ቁርጥ ውሳኔ ነው።"
9 “) ንስሐ ኃጢአት በኃጢአት የቆሸሸውን ያነጻል።
10) "ንስሐ የመዳን የመጀመሪያው እርምጃ ነው።"
11)“ንስሐ የተመመች ነፍስ ፈወስ የጎሰቆለ ልብን መታደስ ነው ።
12) - "ንስሐ ወደ መንግሥተ ለመግባት ሰማያዊ ጉዞ ነው።"
13) “ንስሐ ለመንግስተ ሰማያት ቅርብ የው ።
14) ፡ "ንስሐ ኃጢአትን ማጥፊያ ብቻ ሳይሆን አዲስ ሕይወትን መቀበያ ነው ።"
15) ፡ "የንስሐ አላማ ቃልን ብቻ ሳይሆን ልብን መለወጥ ነው።"
16) ፡“ንስሐ አማኞች በሚገባ ሊረዱት የሚችሉት ትንሽ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
17) ፡ “በንስሐ የሕይወታችን ምንጭ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር መታየት ነው።
18) ንስሐ የመንፈሳዊ እድገት መጀመሪያ ነው"
19) “ንስሐ ወደ ፍፁም የሰው ልጅ ለውጥ ያመራል።”
20)- “ንስሐ የነፍስ ወደ እግዚአብሔር መመለሷ ነው እርሱም መነሻው ነው።
21 ) " ንስሐ ለእግዚአብሔር ያለን ታማኝነት ነው።
22) "የንስሐ ጊዜን ወደ ልባችን የምናቀርበው እኛ ነን"
23) ፡ "እውነተኛ ንስሐ ልብን ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ያቀርባል።"
24) - “ንስሐ ለኃጢአት ቍስል ፈውስ ነው።
25) “ማንም በራሱ ጥበብ ንስሐ ሊገባ አይችልም።
26) ፡- “ዝናብ ምድርን እንደሚያነጻ ንስሐ ነፍስን ታነጻለች።
27)፡ "ንስሐ ወደ እግዚአብሔር ምሕረት የምንቀርብበት መንገድ ነው።"
27)፡ "ንስሐ ወደ እውነትኛ ብርሃን ይመራናል"
28) "ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ኅብረት የምንመለስበት።" የፍቅርና የጸጋ ምሥጢር ነው፤
29) ፡ “ንስሐ ነፍስን ወደ መለኮታዊ ሕይወት መመለስ ነው።
30) "ንስሐ ልባችንን ለማንጻት የሚያስችል መለኮታዊ ስጦታ ነው።"
31)ንስሐጠ በትህትና የተጀመረ መጀመር የመዳን ጎዳና ነው።
32)“ንስሐ የነፍስ መድኃኒት ነች።
33) - "ንስሐ ኃጢአተኛውን ወደ እግዚአብሔር የሚመልስ ስጦታ ነው።"
34) - "ንስሐ የመንግስተ ሰማያትን በር የሚከፍት ቁልፍ ነው።"
35)፡ “ንስሐ ወደ ንጽህናና ወደ ሰላም የመጀመሪያው እርምጃ ነው።
36) "ንስሐ ወደ እውነተኛ ደስታና ድኅነት መንገድ ነው።"
37) “ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን አንድነት የሚመልስ ጸጋ ነው።
38) " ንስሐ የዘላለም ሕይወት መጀመሪያ ኑሮ ነው።"
39) “በንስሐ ልብ ለስላሳና ንጹሕ ይሆናል።
40) "ንስሐ የጸጸት ልብ እና የእግዚአብሔር ምሕረት ልመና ምልክት ነው"
41 “ንስሐ ያለፈውን ኃጢአት ይቅር ማለት ብቻ ሳይሆን ወደፊት ጥፋት ይከለክላል።
42) " ንስሐ መግባት የነፍስን ሕመም የሚፈውስ ብቸኛው መድኃኒት ነው።"
43) ንስሐ በክርስቶስ ፍጹም ለውጥ ነው”
44) ፡- "ንስሐ የእግዚአብሔርን ጸጋ በር ይከፍታል የጠፋውን ይመልሳል።"
45)" ንስሐ መግባት መዳንን የምናገኝበት መንገድ መጀመር ነው።"
46) ንስሐ የመንፈሳዊ ሕይወት መሠረት ነው።
"47) "ንስሐ አንድ ድርጊት ብቻ መተው ሳይሆን የልብን ሙሉ በሙሉ ለውጥ ነው."
48) “እውነተኛ ንስሐ የገባ ያለፈውን መጸጸት ብቻ ሳይሆን መንገዱን ቀይሮ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር ይፈልጋል።
49) ፡- “በእውነት የሚጸጸት አሮጌውን ሰው ትቶ አዲስ ፍጥረት ይሆናል።
50) ፡ "በንስሐ ነፍስ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ትሞላለች።"
መ/ር ቡሩክ አሳመረ

02.04.202505:37
"ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ" ማር ይስሐቅ

22.03.202507:18
"መውደቅ አዳማዊ ነው
ወድቆ አለመነሳት ግን ዲያቢሎሳዊ ነው"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወድቆ አለመነሳት ግን ዲያቢሎሳዊ ነው"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
20.03.202511:44
♡ እንደ ምሕረትህ ♡
እንደ ምህረትህ ብዛት ማረኝ
መተላለፌን ደምስስልኝ
አንተን ብቻ በደልኩኝ
ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ
እጅግ በዛ የኔ ኃጢያት ከፀጉሬ
በመቅደስ እጮሀለሁ አቀርቅሬ
አትቅጸፈኝ በመአትህ አትገስፀኝ
ጌታዬ ሆይ የማዳንህን ደስታ ስጠኝ(፪)
እንደማውቅህ በአደባባይ ምን ብናገር
ስራዬ ግን ይህን እውነት አይመሰከር
ከእልፍኝህ ብሄድ ርቄ ከአንተ ፍቅር
ሁሉን ከሰርኩ አላተረፍኩ አንዳች ነገር(፪)
ማን እንደኔ ከትውልዱ የበደለ
መኃሪ አምላክ ከአንተ በቀር ወዴት አለ
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ እጮሀለሁ
እያነባሁ በጉልበቴ እሰግዳለሁ(፪)
በመዳፈር እንደ አፍኒንና እንደ ፊንሀስ
ሰውነቴን አቆሸሽኩኝ ያንተን መቅደስ
አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ ለኃጢአቴ
እንደ ቀድሞ ልጄ በለኝ ደጉ አባቴ(፪)
├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
├───────────────
🌿@father_advice🌿
እንደ ምህረትህ ብዛት ማረኝ
መተላለፌን ደምስስልኝ
አንተን ብቻ በደልኩኝ
ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ
እጅግ በዛ የኔ ኃጢያት ከፀጉሬ
በመቅደስ እጮሀለሁ አቀርቅሬ
አትቅጸፈኝ በመአትህ አትገስፀኝ
ጌታዬ ሆይ የማዳንህን ደስታ ስጠኝ(፪)
እንደማውቅህ በአደባባይ ምን ብናገር
ስራዬ ግን ይህን እውነት አይመሰከር
ከእልፍኝህ ብሄድ ርቄ ከአንተ ፍቅር
ሁሉን ከሰርኩ አላተረፍኩ አንዳች ነገር(፪)
ማን እንደኔ ከትውልዱ የበደለ
መኃሪ አምላክ ከአንተ በቀር ወዴት አለ
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ እጮሀለሁ
እያነባሁ በጉልበቴ እሰግዳለሁ(፪)
በመዳፈር እንደ አፍኒንና እንደ ፊንሀስ
ሰውነቴን አቆሸሽኩኝ ያንተን መቅደስ
አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ ለኃጢአቴ
እንደ ቀድሞ ልጄ በለኝ ደጉ አባቴ(፪)
├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
├───────────────
🌿@father_advice🌿

18.04.202515:40
ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤
“አሜን በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤ አሜን ።” — ራእይ 7፥12
በነገድ በቋንቋ የከበረውን
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም
በምታውቁት ቋንቋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብላችሁ ፃፉልን🙏
✍️ ✍️ ✍️

04.04.202506:41
ስለ ሌሎች ሰዎች ያለ ማቋረጥ ጸልዩ ወደ እግዚአብሄር ይደርሱ ዘንድ የንስሐ እድል አላቸውና ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ ምላሻችሁ ጸሎት ይሁን
ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ
ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ
02.04.202517:51
“ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች”
ምሳሌ 11፥2
ምሳሌ 11፥2

01.04.202518:30
ንፁህ ልብ ሊሰቃይ የማይችል ልብ አይደለም
የጥንት ቅዱሳን ሁሉም በሚባል ደረጃ ሁሉም በህይወታቸው የጨለማ እና የጭንቀትን ጊዜ ያላለፈ አይኖርም ብዙዎቹ የጭንቀትን ባህር ለማቋረጥ ተገደዋል
በዚህ ፈተና ውስጥ ተስፋ ላለመቁረጥ በመጥፎ መንገድ ላለመሄድ ስንል
የምናለቅሰው ለቅሶ አለ ታዲያ ይሄ ለቅሶ የተቀደሰ መሆኑን መገንዘብ አለብን
ምንም እንኳን በእሳት እና በጎርፍ መሐል ብንከበብም
የልባችን ንፅህና ጋሻ እንደሚሆነን መገንዘብ አለብን

21.03.202520:09
“አንተ መልካም ነህ፤ የምታደርገው መልካም ነው፤ እንግዲህ ሥርዐትህን አስተምረኝ።”
መዝሙር 119:68
“You are good and kind and do good; teach me Your statutes.”
Psalm 119 : 68

20.03.202510:19
አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥
ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ”
መዝሙር 99፥5
🌿@father_advice🌿
Показано 1 - 24 із 37
Увійдіть, щоб розблокувати більше функціональності.