tapswap community
tapswap community
Binance Announcements
Binance Announcements
tapswap community
tapswap community
Binance Announcements
Binance Announcements
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሴቶች የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ወደ 48 ሊያድግ ነው
**************

የሴቶች የዓለም ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ከ32 ወደ 48 እንደሚያድግ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ ቡድኖቹ በ12 የተለያዩ ምድቦች የሚከፈሉ ሲሆን፣ የውድድሩ ፎርማትም በዚያው አግባብ እንደሚቀየር ነው የተገለፀው።

ይህ ለውጥ 40 ተጨማሪ ጨዋታዎችን በማከል በአጠቃላይ የጨዋታዎቹን ብዛት ከ64 ወደ 104 ከፍ ያደርገዋል።

የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል የተሳታፊዎች ቁጥር ማደጉ "ለብዙ ሀገራት እና ተጫዋቾች የላቀ የውድድር ዕድል ይሰጣል፤ በሴቶች ጨዋታ ላይ ኢንቨስትመንትንም ያፋጥናል" ብሏል።

በተጨማሪም ይህ ውሳኔ "በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች እግር ኳስን ለማሳደግ የሚደረገውን ግስጋሴ እንዲፋጠን ያደርጋል" ብለዋል የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ።

በሴራን ታደሰ

ኢቢሲ የስፖርት ገፅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
በጎ ሥራዋ መልሶ የከፈላት በጎ አድራጊዋ ወጣት
************


ሕይወት መስፍን ትባላለች፤ በማኅበራዊ የትሥሥር ገፆች በምትሠራቸው የበጎ ሥራዎች ብዙዎች ያውቋታል።

ሕይወት አቅመ ደካሞችን የምትደግፍ እና በፈገግታዋ ተስፋን የምትለግስ ለብዙዎችም ተምሳሌት የሆነች ልበ ቀና ወጣት ናት።

እርሷ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀም የጀመረችው ከዓመታት በፊት ዓለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተፈተነችበት ጊዜ ነበር።

በወቅቱ ፌስቡክን ለመረዳዳት እና ለበጎ ዓላማ ማዋል እንዳለባት መወሰኗን ታስታውሳለች።

“በኮሮና ወቅት ማስክ ልገዛ ፋርማሲ ሄጄ ነበር፤ አንድ እናት በዊልቸር ልጅ ይዘው መጡ፤ ነገር ግን የሚፈልጉት መድኃኒት እና ማስክ ዋጋው ተወድዶባቸው አዝነው ሳይገዙ ሲመለሱ አየሁ፤ በወቅቱ ልቤ በእጅጉ ተነካ” ትላለች።

ወትሮም ቢሆን ሰዎችን ማገዝ የሕይወት ጥሪዋ የሚመስለው ወጣት ሕይወት ወዲያው በደሞዟ ማስክ፣ ሳሙና እና ሳኒታይዘር በመግዛት ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ መጣች።

የእርሷን አርዓያነት ተከትለው የማኅበራዊ ትሥሥር ጓደኞቿ እና ተከታዮቿ ከሁለት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሚበቃ ድጋፍ አደረጉላት።

በዚህ መልኩ ታዲያ የበጎ አድራጎት ሥራን በይፋ አሐዱ ብላ የጀመረችው ሕይወት በማኅበራዊ ሚዲያ ዜጎችን በማስተባበር ዘር፣ ሃይማኖት እንዲሁም አመለካከት ሳትለይ በሰብዓዊነት የብዙዎችን ዕንባ ማበስ ችላለች።

ከዓመት በፊት ግን ድንገት አስደንግጭ ክሰተት ያጋጥማታል፤ በአንዱ እጇ ላይ የደም ስር መቀደድ ወይንም “Arterivenous Fistula” ትታመማለች።
በጎ ሥራዋ መልሶ የከፈላት በጎ አድራጊዋ ወጣት

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202509:39
በማንቸስተር ዩናይትድ እና በአትሌቲክ ቢልባኦ ጨዋታ የተቆጠሩ ጎሎች

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ


ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202507:48
ሩሲያ በልዩ ሁኔታ የምታከብረው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የድል ቀን

ሩሲያ የሁለተኛ ዓለም ጦርነት የድል ዕለትን በየዓመቱ ሜይ 9 በሞስኮ የሚገኘው ቀዩ አደባባይ በደማቅ ወታደራዊ ትርዒት ታከብራለች፡፡ ይህ የሩሲያ አከባበር በዓለም ላይ ካሉት ሀገራት ሁሉ እጅጉን የላቀ ድምቀት ያለው ነው። ይህ ታላቅ ትዕይንት “ሶቪየት ኅብረት” በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት “በናዚ” ላይ ድል መቀዳጀቷን የሚያስታውስ እና ሩሲያውያን ልዩ የሀገር ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ነው። ሰልፉ ከድሉ መታሰቢያነቱ ባሻገርም እንደ ብሔራዊ የመታሰቢያ ቀን የሚታይ ሲሆን፣ ሩሲያ የጦር ኃይሏን አቅም እንዲሁም ታሪካዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ትኩረቷ መግለጫ ሆኖም ያገለግላል።

“ናዚ” አውሮፓን በተቆጣጠረበት ወቅት እጅ ካልሰጡ ሀገራት መካከል ሩሲያውያን ይገኙበታል፡፡ የናዚ ጦር በመጀመሪያው ዙር ጦርነት የ”ሶቭየት ሕብረትን” ጦር አሸንፎ የነበረ ቢሆንም ሩሲያውያን ግን እንደገና ተደራጅተው 24 ሚሊዮን ዜጎቻቸውን ሰውተው አሸንፈዋል፡፡ ይህ የሩሲያ መስዋዕትነት ከ15 እስከ 17 ከሚሆነው የአውሮፓ ሀገራት መስዋዕትነት የላቀ ሲሆን፣ በጦርነቱ ምክንያት በመላው ዓለም ከተከፈለው የሰው ህይወት 40 በመቶውን እንደሚሸፍን የታሪክ ማስረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

የመጀመሪያው የድል ሰልፍ በ”ሶቭየት ሕብረት” የተካሄደው “ናዚ” ከተሸነፈ ከአንድ ወር በኋላ እ.አ.አ ሰኔ 24 ቀን 1945 ነበር። በቀዩ አደባባይ በተካደው ሰልፍ ላይ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ስታሊን የተገኙ ሲሆን፣ ማርሻል ጆርጂ ጁኮፍ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጠው ሰልፉን መርተዋል።

በዚህ የመጀመሪያ ሰለፍ ላይ ከ40 ሺህ በላይ የሶቭየት ወታደሮች ተገኝተዋል፡፡ በዕለቱ በምርኮ ከተያዙ ወታደሮች የናዚ አርማዎችን የመጣል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። ከሁሉም የሶቪየት ጦር ግንባር የተውጣጡ ወታደራዊ ክፍሎች እንዲሁም በጦርነቱ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችም ለእይታ ቀርበውበታል።
ምንም እንኳ የመጀመሪያው ሰልፍ የተካሄደው በፈረንጆቹ ሰኔ ወር ቢሆንም ናዚ ለመጨረሻ ጊዜ እጁን የሰጠው እ.አ.አ ሜይ 8, 1945 በበርሊን ነው። ሶቭየት ሕብረት ሜይ 9 የድል ቀን አድርጋ የምታከብረው በሰዓት አቆጣጠር ልዩነት (Time Zone) ምክንያት ነው፡፡

በዓሉ በሶብየት ሕዝብረት ውስጥ በተለዋወጡት ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ምክንያት በመሃል ቀዝቀዝ የማለት አዝማሚያ አሳይቶ ቆይቷል፡፡ እ.አ.አ በ1965 እንደገና 20ኛው የድል በዓል ሲታወስ ግን የወቅቱ የሶቭየት ሕብረት ፕሬዚዳንት ሊዮኒድ ብሬዥኔቭ ሙሉ ወታደራዊ ሰልፍ በማድረግ ትውፊቱን እንደገና አነሱ። ይህም ሜይ 9 እንደገና የሕዝብ በዓል ሆኑ እንዲሆን የተደረገበት ክስተት ነበር።

1985 እና 1990 የ40ኛው እና የ45ኛው ዓመት በግዙፍ ሰልፎች ተከብሯል፡፡ እነዚህ ክስተቶች ውስጣዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ዓለም አቀፋዊ ፀረ-ሾሳሊዝም በሰፈነበት ወቅት ሶቭየት ሕብረት የጦር አቅሟን ለዓለም ያሳየችበት ነበሩ።በሰልፎቹ የተደረጉት የድሉን ዐርበኞች በማክበር እና በቀዝቃዛው ጦርነት ምክንያት የተከሰተባትን ጫና መቋቋም እንደምትችል ወታደራዊ አቅሟን በማሳየት ላይ ነበር።

ከሶቭየት ሕብረት መፍረስ በኋላ ባሉት የ1990ዎቹ መጀመሪያዎች ላይ ወታደራዊ ሰልፎች በሩሲያ አልተካሄዱም ነበር። ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ዕለቱ በድምቀት እንዲከበር ማድረግ ጀመሩ፡፡ በ50ኛው ዓመቱ በ1995 በፕሬዝዳንት ቦሪስ የልሲን ዬልትሲን መከበሩ ግን ለበዓሉ መመለስ ወሳኝ ክስተት ነበር። ከ2000 መጀመሪያ እስከ አሁን በፕሬዚዳንት ፑቲን መሪነት በዓሉ በደማቅ ሰለፍ እየተከበረ ሲሆን፣ የሩሲያ ብሔራዊ ማንነት የማዕዘን ድንጋይ ተብሎ ይከበራል፡፡

ትዕይንቱ በሩሲያ ለድሉ አሸናፊዎች መታሰቢያ ከማድረግ ባለፈ የሀገሪቱን አቅም ማሳያ ሆኖ ያገለግላል። በሰልፎቹ የሩሲያን የኑክሌር ብቃት፣ እንደ T-14 Armata ያሉ ልዩ ታንኮች፣ የረቀቁ የጦር አውሮፕላኖች እና ጄቶች ይታዩበታል፡፡ ዜጎች "የማይሞት ሬጅመንት (Immortal Regiment)" የሚል ጽሑፍ ያረፈበት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዘመዶቻቸውን ፎቶግራፍ ይዘው ሰልፉ ላይ ይሳተፋሉ። ምዕራባውያን ሩሲያ ላይ ያላቸውን የተቃርኖ አስተሳሰብ እና ፋሺዝም የሚያወግዙ መልዕክቶች ይተላለፉበታል። ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት በሚያጋጥምበት ወቅት ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከርም ይጠቀሙበታል።

እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሰርቢያ ያሉ ሀገሮች በመሪዎቻቸው ወይም በተወካዮቻቸው አማካኝነት በበዓሉ ላይ ይሳተፋሉ።የምዕራቡ ዓለም ሩሲያ ዕለቱን በመጠቀም የጠበኝነት ፖሊሲ ታራምዳለች በማለት ይወቅሷታል።

የሩሲያ ማኅበረሰብም በዓሉን እንደ ብሔራዊ ኩራት አድርጎ ነው የሚወስደው፡፡ የሩሲያ ትምህርት ቤቶች ታሪክን በስፋት ያስተምራሉ። ቤተሰቦች የቀድሞ አባቶችን ጀግንነት የሚያሳዩ ሜዳልያዎችን፣ ፎቶዎችን እና ታሪኮችን ያሳያሉ። የጦርነት መዝሙሮች፣ ፊልሞች እና ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ዊው በዓል ጋር አብረው ይከበራሉ።

የዘንድሮው 80ኛ ዓመት የሁለተኛ ዓለም ጦርነት መታሰቢያ እንደወትሮው በድምቀት እንደሚከበር ታውቋል፡፡ በዚህ በዓል ላይ የቻይና ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከ20 በላይ የሀገራት መሪዎች እና ተወካዮቻቸው እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴም በዓሉ ላይ ለመታደም ሞስኮ ገብተዋል፡፡
ቤላሩስ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ካዛኪዝታን፣ አርሜኒያ፣ ኪርጊስታን እና የሶቭየት ሕብረት የቀድሞ አባላት የሆኑ ሀገራት ዕለቱን ሜይ 9 ብሔራዊ በዓል እድርገው ያከብሩታል፡፡ ከምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ፈረንሳይ ዕለቱን ብሔራዊ በዓል አድርጋ የምታከብር ሲሆን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፖላንድ እና ሌሎች ሀገራት ዕለቱን አስበውት ይውላሉ፡፡ ደቡብ ኮሪያ ደግሞ ኦገስት 15 ዕለቱን አስባ ስትውል፣ ቻይና ደግሞ ሴፕቴምበር 2 ታስበዋለች፡፡

አሜሪካ ሜይ 8 ዕለቱን አስባ ትውል የነበረ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ዕለቱ ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
09.05.202507:11
የ34 አመት ታሪክን የቀየረው ፍሊፖ ኢንዛጊ እና በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ የደረሰው ሲሞን ኢንዛጊ
******************************

ሁለቱ ወንድማማቾች በጣልያን ለበርካታ ክለቦች ተጫውተው አሳልፈዋል። ፍሊፖ ኢንዛጊ እና ሲሞን ኢንዛጊ።

የ51 አመቱ ፍሊፖ ኢንዛጊ በኤሲ ሚላን በጁቬንቱስ አታላንታ እና ሌሎች ክለቦች ድንቅ አጥቂ መሆኑን አስመስክሯል። በተለይ 12 አመት በቆየበት ኤሲ ሚላን የስኩዴቶውን ክብር ሁለት ጊዜ ከማንሳቱ በተጨማሪ ሁለት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ወስዷል።

የ2006 የጀርመን አለም ዋንጫንም ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ማሳካቱ ይታወሳል።

በሁለት አመት የሚያንሰው ሲሞን ኢንዛጊ በላዚዮ እና አታላንታ እንዲሁም በሌሎች ክለቦች ተጫውቶ ቢያሳልፍም የታላቁን ያክል ስኬታማ ነበር ለማለት አያስደፍርም።

በተቃራኒው በተጫዋችነት ታላቅ ወንድሙ ፍሊፖ ኢንዛጊ የገዘፈ ታሪክ ቢኖረውም በአሰልጣኝነት ግን የታናሽ ወንድሙን ያክል ስኬታማ መሆን አልቻለም።

ሲሞን ኢንዛጊ የአሰልጣኝነት ስራውን ከጀመረ 10 አመት እንኳን ባይሞላውም ከተጽዕኖ ፈጣሪዎቹ ተርታ ለመመደብ ግን ጊዜ አላባከነም።

በ2016 ላዚዮን የተረከበው ሲሞን ኢንዛጊ ክለቡን ለበርካቶች ፈታኝ አድርጎ ከመስራቱ በተጨማሪ ከዋንጫዎች ጋር የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆንም አስችሎታል።

በሮሙ ክለብ በገነባው ቡድን ወደ ኢንተር ሚላን ያመራው ሲሞን ከኒርአዙሪዎቹ ጋር የስኩዴቶውን ክብር ሲያሳካ ሌሎች አምስት ዋንጫዎችን ጨምሮ ሁለት ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ አድርሶታል።

ይሄኛው ሳምንት ለሁለቱ ወንድማማቾች የተለየ ሆኖላቸዋል። የቀድሞው የኤ ሲሚላን አጥቂ ፍሊፖ ኢንዛጊ በጣልያን 2ኛው የሊግ እርከን (ሴሪ ቢ) ይሳተፍ የነበረውን ፒሳን ወደ ሴሪ ኤው እንዲያድግ በማድረግ ታሪክ ሰርቷል።

አሰልጣኝ ፍሊፖ ኢንዛጊ በ1991 ከሊጉ የወረደውን ክለብ 34 አመት በኋላ እንዲመለስ ማድረጉ አድናቆት እንዲቸረውም አድርጎታል።

ሲሞን ኢንዛጊ ደግሞ በዚሁ ሳምንት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ባርሴሎናን ከዚያ ድንቅ ጨዋታ ጋር አሸንፎ ሙኒክ ላይ ለሚደረገው ፍጻሜ ያለፈበት ነው።

ወንድማማቾቹ በቀጣይ አመት በሴሪ ኤው እርስ በርስ የሚያደርጉት ፍልሚያ የሚጠበቅም ይሆናል።

በአንተነህ ሲሳይ
የደንበኞች አገልግሎትን ታቀላጥፋለች ተብላ ተስፋ የተጣለባት የመኪና ሽያጭ ሠራተኛዋ ሮቦት
***********************

የቻይናው የቼሪ አውቶሞቢል ብራንድ በቅርቡ ‘ሞርኒን' የተሰኘች በመኪና መሸጫ ቦታዎች የሽያጭ እገዛ የምታደርግ ሮቦት አስተዋውቋል።

ሞርኒን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የተደረገችው እ.አ.አ በ2023 ቢሆንም፤ የመጀመሪያ ሥራዋን የጀመረችው ገና በቅርቡ (በ2025) በኩዋላ ላምፑር የመኪና መሸጫ ውስጥ ነው።

በመኪና መሸጫ ቦታዎች ደምበኞችን ለማስተናገድ በማሰብ የተሰራችው ሞርኒን ታዲያ ከደንበኞች ጋር ታወራለች፣ የመኪኖችን ባህሪያትን ታብራራለች፣ ጥያቄዎቻቸውንም ትመልሳለች ተብሏል።

እንዲሁም ሞርኒን የሰዎችን መልዕክቶች እና ትዕዛዞች በትክክል እንድትገነዘብ እንዲሁም በምትሰራበት አካባቢ ነገሮችን እንድትዳስስ የሚያስችል መሳሪያ ተገጥሞላታል።

ከዚህም በተጨማሪ ሮቦቷ ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲረዳት እና ግላዊ ምላሾችን እንድትሰጥ የሚያስችላትን የ‘ዲፕ ሲክ’ ቋንቋ ሞዴሎችን እንደምትጠቀም ተገልጿል።

የሞርኒን አምራች ኩባንያ ሮቦቷ ወደፊት እንደ ገበያ ማዕከላት፣ ሲኒማ ቤቶች እና ኤግዚቢሽኖች ባሉ ቦታዎችም ተሰማርታ የምትሰራበትን አማራጭ እያሰበ መሆኑን አስታውቋል።

በቅርቡ ወደ ሥራ የገባችው ሞርኒን ምንም እንኳን እስካሁን በጣም አስደናቂ የሚባል አፈፃፀም ባይኖራትም፤ ቼሪ አውቶሞቢል ወደፊት ለሞርኒን ትልቅ ዕቅድ እንዳለው አመላክቷል።

በሴራን ታደሰ
ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ
ኢቢሲ ድረ ገፅ
ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202510:36
ሪፎርም እንዴት እንደሚሠራ ቋሚ ዐውደ ርዕይ የሚሆን ውጤት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተመለከትን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
******

ሪፎርም እንዴት እንደሚሠራ ቋሚ ዐውደ ርዕይ የሚሆን ውጤት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተመልክተናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ 70 ዓመት በጥሩ መሠረት ላይ መገንባቱን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አንስተዋል፡፡

ነገር ግን ከዘመን ጋር ካልተጓዙ መቅደም ብቻውን መብለጥን አያመጣም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ቀድሞ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ ሊቀድመው ይችላል ብለዋል።

አያይዘውም እየፈጠኑና እየፈጠሩ ዘመኑን ካልቀደሙት፣ ጊዜው ራሱ ይቀድማል ሲሉ ገልጸዋል።

ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሦስት ዓመት ለሠራተኞቹ ደሞዝ መክፈል ተስኖት እንደነበር አስታውሰው፤ ዕዳ እንደ መርግ ተጭኖት ነበር ብለዋል።

በተሠራው የሪፎርም ሥራ፣ ዛሬ ከ1500 ኩንታል የቀን ምርት ወደ 7000 ኩንታል በቀን ለማደግ መቻሉን ነው የገለጹት።

ከዚህም ባሻገር ለ14 ዓመታት ከሥራ ውጭ የነበረው የብዙዎች ትዝታ፣ ደስታ ከረሜላ እንደገና መመረት ጀመሩን ጠቅሰዋል።

በሌማት ትሩፋት በቀን 3000 ሊትር ወትት እና 20 ሺህ ዕንቁላል ማምረት የሚችል ሥራ መሰራቱን ገልጸው፤ ግቢው እና መስኩ ለዓይን ይማርካል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ወንጂ ዘንድሮ የፈተናውን ዘመን አልፎ፣ በዘጠኝ ወር ውስጥ 8.7 ቢልዮን ብር ገቢ ማስገባቱንም ጠቁመዋል።

ይሄ ጠንካራ የሪፎርም ውጤት በሌሎቹ ፋብሪካዎች እንደሚደገም ይጠበቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከሠራን ነገን እንቀድመዋለን ብለዋል በመልዕክታቸው።

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202509:06
የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የድል ቀን 80ኛ ዓመት አከባበር ላይ ፕሬዚዳንት ፑቲን ያደረጉት ንግግር

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202507:36
ሩሲያ በልዩ ሁኔታ የምታከብረው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የድል ቀን ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን ንግግር አድርገዋል

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202506:14
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ እና ለበርካታ የዓለም መሪዎች በክሬምሊን ቤተመንግሥት ያደረጉት የአቀባበልና የእራት ግብዣ መርሐ-ግብር

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ፒኤስጂ ለፍፃሜ ጨዋታው 600 የቡድኑን ሰራተኞች ይዞ ሊጓዝ ነው
*****************

ፒኤስጂ በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም ከኢንተር ሚላን ጋር ለሚያደርገው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታው 600 የቡድኑን ሰራተኞች ይዞ ወደ ሙኒክ ሊጓዝ ነው።

የፒኤስጂው ፕሬዚዳንት ናስር አል-ካሊፊ ለ600ዎቹ የክለቡ ሰራተኞቹ ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ እንዲሄዱ ነፃ ትኬቶችን እንዳዘጋጁላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ቡድኑ ከጨዋታው የሚገኘውን ገቢ ለሰራተኞችም እንደሚሰጥ ፕሬዚዳንቱ ማሳወቃቸው እየተዘገበ ይገኛል።

ፒኤስጂ የፍፃሜ ጨዋታውን ቅዳሜ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም ሙኒክ አሊያንዝ አሬና ስታዲየም ላይ ከኢንተር ሚላን ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

በሴራን ታደሰ

ኢቢሲ የስፖርት ገፅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202510:36
09.05.202510:06
አዲሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው ማን ናቸው?
*************

በቫቲካን ሲቲ ሲደረግ የነበረው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ ሲጠናቀቅ ካርዲናል ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት 267ኛው የሮማን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመርጠዋል።

የጵጵስና ስማቸውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው ሆኗል። ታዲያ የእርሳቸው መመረጥ በቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ የመጀመርያው የአሜሪካ ሰው በመሆን አዲስ ታሪክ ሆኗል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው ውልደታቸው መስከረም 14 ቀን 1955 በአሜሪካ ቺካጎ ኢሊኖይስ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከፈረንሳይ እና ካናዳ ከሆኑ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ቤተሰቦች ነው የተገኙት።

ታዲያ እኚህ አባት በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ያደጉ ሲሆን በ1982 ደግሞ የመጀመርያውን የክህነት ማዕረጋቸውን ከቅዱስ አውግስቲን ተቀብለዋል።

በሚሲዮናዊነት ወደ ፔሩ በማቅናትም በሥነ መለኮታዊ ዕውቀታቸው ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው አሁን 267ኛው የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከመመረጣቸው በፊት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ብዙ ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በፔሩ የቺክላዮ ኤጲስ ቆጶስ ሆነው አገልግለዋል።

በቆይታ ወደ ሮም የተጠሩት እኚህ አባት በዓለም ላይ ያሉትን ኤጲስ ቆጶሳት የመምረጥ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ቆይተዋል።

በዚህ አገልግሎታቸውም ዓለም አቀፋዊ ክብርን አግኝተዋል።

በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባላቸው የሥነ መለኮት እውቀት ብቻ ሳይሆን ስለ ማህበራዊ ፍትሕ በሚያደርጉት ስራ እና በሚሲዮናዊነት ስራቸው ምስጉን መሆናቸው ይመሰከርላቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ባደረጉት የመጀመርያው ንግግራቸው "ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን " በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቢታንያ ሲሳይ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
የቅዳሜ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ
********************

ቅዳሜ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በእንግሊዝ ፕሪሚየሪ ሊግ ሳውዝሀምፕተን ከማንቸስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ይህን ጨዋታ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመዝናኛ ቻናል በቀጥታ ያቀርብላችኋል።

ከጨዋታ በፊት ትንታኔዎችን ጨምሮ ጨዋታው በመዝናኛ ቻናል ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

ኢቢሲ የስፖርት ገፅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ
************

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለሊዮ 14ኛ ሊቀ ጳጳስ የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ለሊዮ 14ኛ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሊዮ 14ኛ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ በመሆን በመመረጣቸው የተሰማቸውን ልባዊ ደስታ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ገልጸው፤ "እንኳን ደስ አለዎ ለማለት እወዳለሁ" ብለዋል።

የምድራችን ችግር በልዩ ልዩ ፈተናዎች እየጨመረ የመጣ መሆኑን የጠቆሙት አቡነ ማትያስ፥ "በእግዚአብሔር ኃይል የተመረጡ ሰዎችና መሪዎች ችግሮቹን በቀላሉ ማሸነፍ እና ፍሬ ማፍራት ስለሚችሉ፤ ቅዱስነትዎ ፈተናዎችን በሙሉ በቀላሉ በማለፍ የቤተ ክርስቲያንዎን ተልእኮ በላቀ ስኬት እንደሚወጡ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።

አያይዘውም፥ "በአገልግሎትዎ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ከጎንዎ እንዲሆን እመኛለሁ" ማለታቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
Видалено09.05.202513:56
ሪፎርም እንዴት እንደሚሠራ ቋሚ ዐውደ ርዕይ የሚሆን ውጤት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተመለከትን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**********

ሪፎርም እንዴት እንደሚሠራ ቋሚ ዐውደ ርዕይ የሚሆን ውጤት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተመልክተናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ 70 ዓመት በጥሩ መሠረት ላይ መገንባቱን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አንስተዋል፡፡

ነገር ግን ከዘመን ጋር ካልተጓዙ መቅደም ብቻውን መብለጥን አያመጣም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ቀድሞ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ ሊቀድመው ይችላል ብለዋል።

አያይዘውም እየፈጠኑና እየፈጠሩ ዘመኑን ካልቀደሙት፣ ጊዜው ራሱ ይቀድማል ሲሉ ገልጸዋል።

ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሦስት ዓመት ለሠራተኞቹ ደሞዝ መክፈል ተስኖት እንደነበር አስታውሰው፤ ዕዳ እንደ መርግ ተጭኖት ነበር ብለዋል።

በተሠራው የሪፎርም ሥራ፣ ዛሬ ከ1500 ኩንታል የቀን ምርት ወደ 7000 ኩንታል በቀን ለማደግ መቻሉን ነው የገለጹት።

ከዚህም ባሻገር ለ14 ዓመታት ከሥራ ውጭ የነበረው የብዙዎች ትዝታ፣ ደስታ ከረሜላ እንደገና መመረት ጀመሩን ጠቅሰዋል።

በሌማት ትሩፋት በቀን 3000 ሊትር ወትት እና 20 ሺህ ዕንቁላል ማምረት የሚችል ሥራ መሰራቱን ገልጸው፤ ግቢው እና መስኩ ለዓይን ይማርካል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ወንጂ ዘንድሮ የፈተናውን ዘመን አልፎ፣ በዘጠኝ ወር ውስጥ 8.7 ቢልዮን ብር ገቢ ማስገባቱንም ጠቁመዋል።

ይሄ ጠንካራ የሪፎርም ውጤት በሌሎቹ ፋብሪካዎች እንደሚደገም ይጠበቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከሠራን ነገን እንቀድመዋለን ብለዋል በመልዕክታቸው።
ማስታወቂያ
***

የባንካችንን አገልግሎት በተመለከተ ለሚፈልጉት ማንኛውም መረጃ 871 ላይ በነጻ ይደውሉልን፡፡

Tajaajila baankii keenyaa ilaalchisee odeeffannoo barbaaddan kamiifuu 871 irrati bilisaan nuuf bilbilaa.


#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ  #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan
#EMPOWERED_TOGETHER
09.05.202507:11
ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ለዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ተፋላሚ ሆኑ
**************

በአውሮፓ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ አትሌቲክ ቢልባኦን በድምር ውጤት 7 ለ 1 እንዲሁም ቶተንሃም ቦዶን 5 ለ 1 በማሸነፍ ለዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ደርሰዋል።

ዛሬ ምሽት አትሌቲክ ቢልባኦን በኦልድትራፎርድ ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ 4 ለ 1 አሸንፏል።

የማንቸስተርን የማሸነፊያ ግቦች ሜሰን ማውንት (2) እንዲሁም ካሰሚሮ እና ሆይሉንድ አንድ አንድ አስቆጥረዋል።

አትሌቲኮዎች በመጀመሪያው አጋማሽ 31ኛው ደቂቃ ላይ ድንቅ ጎል አስቆጥረው እረፍት መውጣት ቢችሉም በሁለተኛው አጋማሽ 4 ግቦችን ለማስተናገድ ተገድደዋል።

በዚሁ መሠረት በአትሌቲክ ቢልባኦ ሜዳ 3 ለ 0 አሸንፎ የነበረው የእንግሊዙ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ በድምር ውጤት 7 ለ 1 በማሸነፍ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።

በሌላ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ቦዶን የገጠመው ቶተንሃም ሆትስፐር 2 ለ 0 አሸንፏል።

ባለፈው ሳምንት በሜዳው ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በበላይነት ያጠናቀቀው ቶተንሃም በድምር ውጤት 5 ለ 1 በማሸነፍ ለዋንጫው ከዩናይትድ ጋር የሚፋለም መሆኑን አረጋግጧል።

በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ደግሞ ቼልሲ ዩጋርደንን በድምር ውጤት 5 ለ 1 እንዲሁም ሪያል ቤቲስ ፊዮረንቲናን 4 ለ 3 በማሸነፍ የዋንጫው ተፋላሚ ሆነዋል።

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
Показано 1 - 24 із 1 620
Увійдіть, щоб розблокувати більше функціональності.