Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Dn. HaileRaguel avatar
Dn. HaileRaguel
Dn. HaileRaguel avatar
Dn. HaileRaguel
Мөөнөт
Көрүүлөрдүн саны

Цитаталар

Посттор
Репостторду жашыруу
01.05.202514:25
(ነገረ ቤተክርስቲያን - ክፍል ፫)

የሐዋርያዊት ጉባኤ አባላት

፩. ቅዱሳን መላእክት

በጥንተ ዕለት በዕለተ እሑድ አንድ ጊዜ በዝተው የተፈጠሩ ቅዱሳን መላእክት ናቸው፡፡
"ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና'' — ማቴ. ፲፰፥፲
የሚላቸው፤ በሦስቱ ስማያት መንደር መንድረው የሚኖሩ፣ በዕለተ እሑድ ተጋድሏቸውን የጨረሱ ፺፺ኙ ፍጹማን ነገደ መላእክት የቤተ ክርስቲያን ማኅበርተኞች ናቸው።

፪. በገነት ያሉ ነፍሳተ ቅዱሳን

“ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው" — ሉቃ. ፳፫፥፵፫ ተብሎ እንደተጻፈው በክርስቶስ ካሣ በዕለተ ዓርብ የገቡና ድኅረ ዓርብ በዚህ ዓለም የነበራቸውን ተጋድሎ ጨርሰው የገቡ የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የሰማዕታት፣ የሊቃውንት፣ የመነኰሳት፣ የህዝባውያን፣ የጳጳሳት፣ የካህናት፣ የዲያቆናት ቅዱሳን ነፍሳት ናቸው፡፡

፫. በብሔረ ሕያዋን ያሉ ቅዱሳን ሕያዋን

ከሞት የተሠወሩ በብሔር ሕያዋን ያለ ሞት እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ የሚኖሩ ቅዱሳን ሕያዋን ናቸው። “
ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና፡፡” — ዘፍ. ፭፥፳፬


"እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ?” — ዮሐ. ፳፩-፳፫


፬. በብሔረ ብፁዓን ያሉ ጻድቃን

"ስለዚህ በፊቴ የሚቆም ሰው ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን ለዘለዓለም አይታጣም" — ኤር ፵፭፥፲፱ የሚላቸው ቅድመ ጼዋዌ በኢዮናዳብ ተመርተው፣ ድኅረ ጼዋዌ በሚጠት በዕዝራ ነቢይ ተመርተው የገቡ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ከወንጌላውያን ቅዱስ ማቴዎስ፣ ከባሕታውያን ቅዱስ ዞሲማስ ያያቸው ኃጢአትን የማይስሩ አንድ አንድ ሺሕ ዓመት እየኖሩ የሚያርፉ ቅዱሳን ብፁዓን ናቸው፡፡ ገድለ ዞሲማስ፣ ስንክሳር ዘሚያዝያ ፱፣ ገድለ ሐዋርያት

፭. በገጸ መሬት የተሠወሩ ሥውራን

"ለበአል ያልሰገዱትን ሰባት ሺሕ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ" — ሮሜ ፲፩፥፬ የሚላቸው፤ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በየገዳማቱ፣ ከዚህ ዓለም ራሱ ባወቀ የሠወራቸው ቅዱሳን ሥውራን ናቸው፡፡

፮. ከሰው የተለየ ግኁሣን

“አቤሜሌክንም ኤርምያስ ከላከው ቦታ በቀትር ጊዜ በለሱን አመጣ፤ ጽፍቅ ያለች ዱርንም አገኘ!፣ ጥቂትም ያርፍ ዘንድ በጥላዋ ሥር ተቀመጠ፤ በለስ ያለበትንም ሙዳይ ተንተርሶ ስልሳ ስድስት ዓመት ተኛ" — ተረ.ኤር. ፱፥፩ የሚላቸው! እስከ ጊዜው ድረስ ከገጸ ሰብእ ተወግደው እንደ አቤሜሌክ እንደ ባሮክ የሚኖሩ ናቸው፡፡

፯. ገሃዳውያን በተጋድሎ ያሉ ምእመናን

“ሕጉ ለእግዚአብሔር ቅድስት ይእቲ" - (የእግዚአብሔር ሕጉ የተቀደሰች ናት) ሃይ.አበ. ፳፪፥፲፯

በማለት በቅድስት ሃይማኖተ ወንጌል ሁነው መስቀል ተሸክመው ወደ ክርስቶስ የሚጓዙ፤ ተጋድሏቸውን ያልጨረሱ ከግብጽ ተነሥተው ወደ ከነዓን መንግሥተ ሰማያት እየገስገሡ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ናቸው:: ዘፍ. ፴፪፥፪፣ ሉቃ. ፪፥፲፫፣ ግብረ ሐዋርያት ፩፥፲ እነዚህ ከላይ ያየናቸው ፯ቱ አካላት ሁሉ በክርስቶስ ራስነት አንድ የሆነበት ቅዱስ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ይባላል::
በክርስቶስ ራስነት አካላተ ክርስቶስ ሕዋሳት ሁሉ አንድ የሆኑበት ኅብረት «ሐዋርያዊ ጉባኤ» ፣ «አቅሌስያ» ፣ «ቤተ ክርስቲያን» ተብሎ ይተረጎማል::

የነፋስ መንፈስ፣ የውኃ መፍሰስ፣ የብርሃናት መመላለስ የማይገድበው በአካልነት በመንፈስነት ያለ ልዩ ኅብረት ነው:: ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ተጋድሏቸውን ያልጨረሱ በምድር ላይ ያሉ የኅብረቱ አባላት በተወካፌ ምሥጢርነት ለመንጻት፣ ለማየት፣ ለመብቃት፣ ሱታፌ መስኮት ለማድረግ እና ለባሴ ክርስቶስ ለመሆን ደረጃ በደረጃ በሂደታዊ ተጋድሎ የሚተጉባት ኅብረት ናት። እነዚህ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” — ማቴ. ፳፮፥፵፩ የሚላቸው የዕለተ ዓርብ ምእመናን ናቸው፡፡

ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን የዚህ ኅብረት አባል እና አካል ነው፡፡ ነገር ግን ተጋድሎውን ላልጨረሰ ምድራዊ ሰው በኅብረታዊ አካልነቱ ካልጸና በክሕደት በኑፋቄ ከአካልነት ቢለይ ከኅብረቱ አባልነት ሊመተር ይችላል፡፡ “አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጧል። እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል" — ማቴ. ፫፥፲ ብሎ ዮሐንስ መጥምቅ እንዳስተማረን፡፡ ነገር ግን ከኅብረቱ የማይለይ አካል አባል መሆን የሚቻለው በዕለተ ሞት ፍጻሜ ነው፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን በወጪ ወራጅ ፈቃድ ይመላለሳልና አንድ ወገንነቱ አልተፈጸምለትም። ምክንያቱም ይህ ኅብረት የሰማያውያን እና የምድራውያን ማኅበር (የመላእክት እና የደቂቀ አዳም)፣ በአካለ ነፍስ ያሉ እና በአጸደ ሥጋ ያሉ ክርስቲያኖች ማኅበር፣ በብሉይ ኪዳን የነበሩ እና በሐዲስ ኪዳን ያሉ ምእመናን ማኅበር ነውና ለኅብረቱ እንደሚገባ በአንድነት፣ በቅድስና፣ በኩላዊነት፣ በሐዋርያዊነት መኖር ግድ ነው፡፡


ሰማያውያኑ በምድራውያን ልብ ውስጥ አሉ፤ ይኖራሉ፡፡ ማለትም በዚህ ዓለም ሥዕል ተሥሎላቸው፣ ጽላት በስማቸው ተቀርጾላቸው፣ መታሰቢያ ቤተ መቅደስ ተሰጥቷቸው ዘወትር ቅድስናቸው መታሰብ መቻሉ በምድራውያኑ ልቡና በፍቅር፣ በማኅበር፣ በኪዳን፣ በሑሰት ህልው ስለሆኑ ነው:: ይሄውም ለመላእክትም ለቅዱሳን ሰዎችም መታሰቢያ ይደረግላቸዋል:: ቤተ ክርስቲያን የሚቆረስባት ሥጋ፣ የሚቀዳባት ደም ያንዱ የክርስቶስ ብቻ ቢሆንም በመታሰቢያነት ግን ከሰማያውያንም የሚካኤል፣ የገብርኤል፤ የሩፋኤል፣ የኪሩቤል፣ የዑራኤል ወዘተ... እያለ መታሰቢያ ቤተ ክርስቲያን ይሠራላቸዋል:: ከምድራውያኑም በአካለ ነፍስ እና በብሔረ ሕያዋን ላሉት በነቢያት፣ በሐዋርያት፣ በሰማዕታት፣ በመነኰሳት፣ በጻድቃን ወዘተ… ስም ተሠይሞ መታሰቢያቸው ይቆምላቸዋል። "በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" — ኢሳ. ፶፮፥፭ ይህም መሆኑ ሰማያውያኑ በምድራውያን ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ህልዋነ ማኅበር ስለሆኑ ነው፡፡


ምድራውያኑም በሰማያውያኑ ልብ ውስጥ አሉ፡፡ ይህም ማለት ቅዱሳን ሰማያውያን መላእክት እና ደቂቀ አዳም በተጋድሎ ዓለም ያሉ ምድራውያንን በጸሎታቸው፣ በምልጃቸው ማሰባቸው፣ ማማለዳቸው፣ በቃል ኪዳናቸው መራዳታቸው፣ በፍጹም ኅብረታቸው፣ በፍቅራቸው፣ ምድራውያኑ በእነሱ ዘንድ ህልዋን ስለሆኑ ነው:: ይህም ኅብረተ ክርስትና ነው:: ምድራውያኑ ግን በሰማያውያኑ ዘንድ በኅብረት መኖር የሚችሉት በሃይማኖተ ወንጌል፣ በግብረ ሐዋርያት እስከ አሉ ድረስ ነው:: ይህ ቅዱስ ኅብረት አንድ የጸጋ ልጅነት ያለው፤ አንድ ግዕዝ ርትዕት ያለው፣ አንድ ተስፋ ኅሊና ያለው፤ አንድ መንግሥተ ሰማይን ለመውረስ የሚጠባበቅ፣ አንድ የወይን ግንድ ያለው የወይኑ ቅርንጫፍ፣ አንድ ራስ ያለው ሕዋስ ነው:: ኤፌ ፬፥፭፣ ቆላ ፩፥፲፰፣ ዮሐ ፲፭፥፭ በዚህ ዓለም ሁኖ የዚህ ኅብረት አባል መሆን የሚቻለው በሃይማኖት፣ በጥምቀት፣ በቅዱስ ሜሮን፣ በቅዱስ ቁርባን፤ በቅዱስ ተግባረ ክርስትና፣ በተስፋ ሐዋርያት ማለፍ ሲቻል ብቻ ነው:: ዕብ ፲፩፥፩፣ ዮሐ. ፫፥፫፣ ፪ኛ ቆሮ ፩፥፳፩፣ ዮሐ. ፮፥፶፮
30.04.202518:25
በዚህች አካለ ክርስቶስ በሆነች ኦርቶዶክሳዊት ኅብረት ውስጥ ሁኖ ካልሆነ በስተቀር የመዳን በር የለም:: በሌላ ስብስብ ወይም ግላዊነት መዳን አይቻልምም። «እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው» — ዮሐ. ፲፥፩ እንዲል:: በሌላ በር መግባት ሌብነት ወይም መንግሥተ ሰማያትን እሰርቃታለሁ እንደ ማለት ነው::


ለመሆኑ በሐዋርያዊት ጉባኤ ውስጥ አካላተ ክርስቶስ የሆኑ የኅብረቱ አባላት እነማን ናቸው???

(ክፍል ፫ ይቀጥላል .... )
ማንንም አልተቀየመችም

በምድር ላይ እንደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያዘነ ሊያዝንም የሚችል ሰው በምድር ላይ ሊኖር አይችልም። አንድ ልጇን ይዛ ገና በልጅነቷ ነበር ወደ ማታውቀው ስደት የገባችው፤ ከጠላት ለመደበቅ ቀንና ሌሊት ያለ እረፍት ተጉዛለች። 

ልጇ በሠላሳ ዓመቱ ወደ አደባባይ ወጥቶ ሲያስተምር በብዙ ሲፈተንና ሲነቀፍ አይታለች።

ምንም በደል ሳይኖርበት በሐሰት ተከስሶ ሲፈረድበት “ልጅሽ በአደባባይ ሊሰቀል ነው ነይ እይ” ተብላ ስትጠራ በጅራፍ ሲገረፍ፣ ራቁቱን አደባባይ ላይ ተሰቅሎ ምንም ልታደርግለት እንደማትችል ምስኪን ከመስቀል ስር ቆማ ደም አልቅሳለች። 

እኔን የሚደንቀኝ ይሄ ሁሉ ሆኖባትም እርሷ ግን ማንንም አልተቀየመችም፥ ኧረ ቂሙን ተዉት ማዘኗን እንኳ አልነገረችንም። ዓለም ተሰብስቦ አንዱን ንጹሕ ልጄን ሰቀሉብኝ ብላ አልተናገረችም፤ ጴጥሮስን 'ለምን ልጄን ጥለኽው ሸሸህ?' አላለችውም። ሁሉንም በልብዋ ጠበቀችው። 

እኛ ልጃችን ተሰቅሎ አይደለም 'ሰው ገላመጠኝ ፤ ክብሬን ነካው' ብለን የምንጣላና የምንኳረፍና የምንጠላላ ግብዞች አሁን እውን እመቤታችንን «እናቴ» የማለት ምግባር አለን? እንደው ትኩር ብለው ቢያዩን ምናችን የድንግል ማርያም ልጅ ይመስላል?

ሰአሊ ለነ ቅድስት!

❝ምንተኑ ንሰምየኪ ኦ ምልዕተ ጸጋ? አንቀጸ መድኃኒት አንቲ፤ ኆኅተ ብርሃን አንቲ፤ ወለተ መንግሥት አንቲ፤ ሰማይኑ ንብለኪ? ፀሐየ ጽድቅ ወልድኪ ... ❞ — አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
27.04.202516:41
፩. ይቅር ያለውን/ንስሐ የተገባበትን ኃጢአት አያውቀውም ፤ ፈጽሞ ይረሳልናልና
፪. ተስፋ የሌለውን ኃጢአተኛ አያውቀውም ፤ ንስሐ እስከገባ ድረስ ሁሉም ሰው ተስፋ አለውና
፫. የፈጠረውን ትንሽ ሰው አያውቀውም ፤ በኣርዓያ ሥላሴ የተፈጠረ ትንሽ ሰው የለምና
፬. የሠራውን ከንቱ ቀን አያውቀውም ፤ ሁሉን ውብ አድርጎ ሰርቷልና
፭. የማይችለውን ኃይለኛ አያውቀውም ፤ ከክርስቶስ ጋር ችሎ ማን ይቆም ና .... ብቻ ብዙ ብዙ ነገር እግዚአብሔር እያወቀ እንደማያውቅ ዝም ይላል።


ዘሠለስቱ ምዕት በቅዳሴያቸው እንደነገሩን ስንገልፀው ደግሞ እግዚአብሔር ".... እንደማይሰማ ቸል ይላል፤ እንደማያይ ዝም ይላል፤ እንደማያውቅ ይታገሣል፤ እንደማይሰጥ ያዘገያል...."



የኤማሁስ መንገደኞች ሰንበትን ውለው አርፈው የጀመሩት ጉዞ ቢሆንም ጠውልገው ነበር። ውስጣቸው ደክሞ ነበርና እግራቸውን ማንሣት አቅቷቸው፣ በተሰላቸ ድምፀትም ቢሆን ስለ ክርስቶስ ሞት ይናገሩ ነበር። ሰዎች ክርስቶስን ስለ ሰቀሉበት ምክንያታቸው እንጂ ክርስቶስ ስለ ተሰቀለበት የሥላሴ ፈቃድ አልተረዱም ነበር። ሁሉም ነገር ከምድር ስናየውና ከሰማይ ስናየው ልዩነት አለው። ተኝተን ብናድርም፣ ዐርፈን ጉዞ ብንጀምርም ውስጣችን ተስፋ ከቆረጠ አሁንም እንደ ደከምን ነው። ተኝቶ አለመንቃት፣ በልቶ አለመበርታት ከተስፋ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው ነገር።

እግዚአብሔር የቆምንበት ስውር እጅ፣ የምንነሣበት የትንሣኤ ምሥጢር ነው። የኤማሁስ መንገደኞች ስለ ክርስቶስ ሞት ሲያወሩ ሁለት ሰዎች የሚናገሩ ብቻ አይመስሉም። የደመቀ ጉባዔ ይመስል ነበር። ይነጋገሩ ነበርና ሁለቱም አድማጭም ተናጋሪም ነበሩ፤ ይመራመሩም ነበረ። ለምንና እንዴት እያሉ ይጠይቁ ነበር። በዚህ ጊዜ ክርስቶስ አብሮአቸው ሦስተኛ ሁኖ ይጓዝ ነበር። እነርሱ ግን ልብ አላሉትም ነበር ። "እንዳያውቁትም ዓይናቸው ተይዞ ነበር" ይለናል ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ምዕራፍ ፳፬፥፲፮ ላይ። ክርስቶስን ዐይናማዎች፣ አሻግረው የማየት አቅም ያላቸው ሳይሆን የሚያምኑ ብቻ ያዩታል። ጉዞአቸው ወደ ፀሐይ መጥለቂያ በመሆኑ ምንም ነገር እንዳያዩ ተሰናባቿ ፀሐይ ጋርዳቸው ነበር። «በቃ ሁሉም ነገር አብቅቷል» በሚል ስሜት ተስፋቸው ልትጠልቅ ተቃርባ ነበር። ተስፋ መቍረጥና ጨለማ ሁለቱ ከባድ ናቸው። ወደ ሁለቱም ይጓዙ ነበር። ተስፋ የቆረጡ ልጆቹ ባያዩትም ክርስቶስ አብሯቸው ይጓዛል። ምክንያም ሰይጣን ተስፋ የቆረጡትን በጣቱ ወደ ሲኦል ቢገፋቸው ጥልቁ ላይ ይገኛሉ ። ተስፋ መቍረጥ ለሰይጣን በፈቃድ እጅን  መስጠት ነው። ለዚያ ነው ለክርስቲያኖች ተስፋ መቁረጥ ፈጽሞ የማይፈቀደው። ሃይማኖትን እንደመካድ ይቆጠራልና!

ትሑቱ ጌታ ንግግራቸውን በትሕትና አቋረጠ። ስለ እርሱ ከመናገሩም በፊት ስለ እርሱ እንዲናገሩ ፈቀደ። ስለ እርሱ የሚናገሩት ነገር በሙሉ ጨለማ ያጠላበት ቢሆንም እርሱ ግን ተሸናፊ አይደለሁም ብሎ ቸኩሎ ራሱን አላስተዋወቀም።
እግዚአብሔር ነገሮችን የሚሰራበት የራሱ ጊዜ አለው፤ ፈጽሞ አይቸኩልም፥ ለሰከንድም ደግሞ አይዘገይም።

እርሱም፦ "እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሯቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው?" አላቸው። የልባቸው ብሎን እንደ ላላ፣ ለመበተን እንደ ተቃረቡ ተረድቷል። እኛን ሳያስፈቅድ ልባችንን የማየት፥ ልብንና ኩላሊትን የመመርመር አቅም አለው። ልባችን የእርሱ ነበር፣ ቀጥሎ ሁለት ቁልፍ ቀርፆ አንዱን በእጁ ሲይዝ አንዱን ለእኛ ሰጠን። መጠውለጋቸው በፀሐይ ትኩሳት አልነበረም፣ ሰዓቱ ሠርክ ነውና። አንድም መጠውለጋቸው የመንገድ ድካም ብቻ የወለደውም አልነበረም፤ ተስፋ መቍረጥ ጉልበታቸውን መትቶባቸው፣ ፊታቸውን አጨልሞባቸው ነበር። ተስፋ የሚሰጠውን ማማር አጥተውት ነበርና አዘነላቸው።

ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ፦ "አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን?" አለው። «ለቀባሪው አረዱት» የተባለው ተፈጸመ። ክርስቶስ በርግጥ ለዚህች ምድር እንግዳ ነበረ፣ ዓለም ግን አልተቀበለችውም፤ ሲወለድም በበረት የተወለደ ትልቅ እንግዳ ነበር  ሰዎች ልባቸውን ዘግተውበት መስቀል ላይ የዋለ ትልቅ እንግዳ። ደቀ መዛሙርቱ ትተውት ቢሸሹም የአባትነት መነሻ የሆነው እግዚአብሔር አብ ከእርሱ ጋር ነው።
ብቸኝነት ያለ እግዚአብሔር መኖር እንጂ ያለ ሰው መኖር አይደለም። ከብቸኝነት የማይሻሉ፣ ከባዶ ቤት ከፍ የማይሉ ሰዎች አጠገባችን አሉ። ኖረው የሌሉ፣ ተገኝተው የሚያደክሙ፣ ራሳቸውን እንጂ ስሜታችንን ለማዳመጥ ያልታደሉ አሉ። መጠውለግን የሚያነብብ፣ ስሜትን የሚረዳ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ለዚህ ነው በዚህ ዓለም ስንኖር ከሰዎች ጋር ለመኖር ስሜትን መቆጣጠር ግድ የሚለን። ከነእኛነታችን የሚቀበለን መድኃኔዓለም እርሱ ብቻ ነው። ራሳችንን እንኳን በሸሸን ሰዓት የተቀበለን፥ ራሳችንን ለማየት ባፈርን ጊዜ በእቅፉ አሳርፎ ያረጋጋን አባታችን አማኑኤል ብቻ ነው።


እርሱም፦ "ይህ ምንድር ነው? አላቸው ። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤ እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው። እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው። ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን፤ ሥጋውንም ባጡ ጊዜ፡- «ሕያው ነው» የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር። ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።”

በጣም የሚገርም ነገር እኮ ነው እየሆነ ያለው እዚህ ጋ። በእውነት! እግዚአብሔር ስለ እግዚአብሔር ጠየቀ። ሊተርክ የሚገባው ሟች ስለ ራሱ ሲተረክለት ዝም ብሎ ሰማ። ሉቃስና ቀለዮዻ እስራኤልን ነጻ ያወጣል ብለው ጠብቀውት ነበረ፣ እርሱ ግን የመጣው መላው ዓለምን ነጻ ለማውጣት ነው። ምክንያቱም እርሱ የነፍስ ነጻ አውጪ ነው። የመነሣቱን ዜና ቢሰሙም፣ መቃብሩ ባዶ መሆኑን ሴቶች ቢያረጋግጡላቸውም እነርሱ ግን አላመኑም ነበር። አለማመን ተስፋ አስቆረጣቸው። ከሶስት ዓመት የሐዋርያነት ሕይወት በኋላም ወደ መኖሪያ ከተማቸውም እንዲመለሱ አደረጋቸው። የተዉትን መጀመር፣ የጀመሩትን መተው ከተስፋ መቍረጥ ውስጥ ይወጣል። ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው የተዉትን ጀምረው፣ የጀመሩትን ወንጌል ጥለዋል።

እርሱም፦ "እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ?” በማለት ገሠጻቸው። ተግሣጹን ስለ ተቀበሉ ቀጣዩን ምሥጢር አወቁ። የክርስቶስ ሞት ገዳዮች መግደል ስለቻሉ ያከናወኑት ሳይሆን መላው ብሉይ ኪዳን እውነት የሆነበት ነው። ምክንያቱም በተስፋ፣ በምሳሌ፣ በመሥዋዕት፣ በትንቢት፣ በክህነት ፣ በመቅደስ የክርስቶስ ሞት ሲነገር ኑሯልና።

በሌላም ቦታ የገላትያ ሰዎችም የተሰቀለውን ክርስቶስ ስለረሱ «እናንተ የማታስተውሉ!» ተብለዋል በቅዱስ ዻውሎስ።
01.05.202514:25
የኅብረቱ አባል የሆነ አማኝ የግሉ ሕይወት፣ የግሉ ዓለም፣ የግሉ ራስ፣ የግሉ ግንድ፣ የግሉ ክርስቶስ፣ የግሉ ድኅነት፣ የግሉ መረዳት፣ የግሉ ክህነት፣ የግሉ ትምህርት፣ የግሉ ተስፋ፣ የግሉ ቤተ መቅደስ፣ የግሉ ሥጋ ወደም፣ የግሉ ጥምቀት፣ የግሉ ትንሣኤ ወዘተ... የለውም:: በክርስቶስ ዓለምነት ይኖራል፤ በክርስቶስ ራስነት ሕዋስ ይሆናል፤ በክርስቶስ የወይን ግንድነት ቅርንጫፍ ይሆናል፣ በኀብረቱ ውስጥ ሁኖ ለመዳን የሚያሻውን ሁሉ ያገኛል እንጂ፡፡ የጸናች በሕገ እግዚአብሔር የተቀጸረች የኅብረት ሀገሩም በተስፋ ልቡናው ውስጥ ናት፡፡ ይህችውም በማይጠፋ ብርሃን የምታበራ ዓለም ናት:: “ሀገሩ ለንጹሕ በውሳጤ ልቡ ይእቲ ወፀሐይኒ ዘይሠርቅ በውስቴታ ብርሃነ ሥሉስ ቅዱስ" - (የንጹሕ ሰው ሀገሩ በልቡ ውስጥ ናት በውስጧ የሚያበራውም የሥላሴ ብርሃን ነው::) — አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን ፩


የቀን ወራሪ የሌሊት ሰባሪ የማይገባባት ጽንዕት ልቡና በመንፈስ ቅዱስ ማኅተም የታተመች፣ ጠቢብ ወልድ ያደረባት የጸናች የተቀጸረች ሀገር ናት:: ምሳ. ፳፩፥፳፪
እግዚአብሔርን ዓለም፣ ቦታ አድርገን በብርሃነ ሃይማኖት እንኖር ዘንድ ቤተ ክርስቲያንን በአካልነት ወደ እርሱ አቀረባት:: "ናሁ ብርሃን ዘአልቦቱ ዘመን ለጸዳል ዘመናዊ ረሰዮ አሐደ ምስለ ርእሱ" - (ዘመን የማይወስነው ጌታ ዘመን የሚወስነው ፍጹም ሰውን ከርሱ ጋራ አንድ አደረገው::) —(አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን ሣልስ አርእስት ፵፰) - ይህ ከፈጣሪ ለፍጡራን በሐዋርያዊት ኅብረት ውስጥ ላሉ የሚሰጥ የጸጋ ተዋሕዶ ነው:: ኅብረቱ አንድ ቢሆንም መጠኑም በየአንዳንዱ ቅዱስ እንደ ተጋድሎ ጸጋው መጠን ይለያያል::


ብረትን ከእሳት እንዳቀረቡትና እንዳራቁት መጠን የእሳትን ባሕርይ እንዲሳተፍ ሰውም ከሱታፌ መንፈስ ቅዱስ እንደራቀበትና እንደቀረበበት መጠን ከሥላሴ የጸጋን ተዋሕዶ በጸጋ ይዋሐዳል። "ቅረብዎ ስእግዚአብሔር ወይቀርበክሙ" - (ወደ እግዚአብሔርቅረቡ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል) — ያዕ. ፬፥፰ እንዲል፡፡


ጸጋ ማለት ስጦታ ልግስና ማለት ስለሆነ እንደ ወጪ ወራጅ ኅሊናው መጠን ሊነሣም ሊጸናም፣ ሊያድርም ሊለይም፣ ሊጨመርም ሊያንስም ይችላል:: “ወናሁ እመጽአ ፍጡነ ወአጽንዕ ዘብከ ከመ አልቦ ዘይነሥአ አክሊለከ" - (እነሆ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ) — ራእ. ፫፥፲፩።  ያገኙትን ጸጋ አጽንተው ካልያዙት ዛሬ የተሰጠውም ወደፊት የሚስጠውም ተስፋ ይታጎላል:: እያንዳንዱ ፍጡር ጸጋው እንዳይለይበት በኅብረተ ሐዋርያት ውስጥ ሁኖ ነቅቶ፣ ጸንቶ፣ ተግቶ የጸጋው ግምጃ ቤት፣ የመለኮት ተሳታፊ ለመሆን የሃይማኖት እና የምግባር ርቱዕነት ይጠይቀዋል፡፡ ሐዋርያ ጽድቅ ቅዱስ ጳውሎስ “ንቁ፣ በሃይማኖት ቁሙ፣ ጎልምሱ፣ ጠንክሩ" — ፩ ቆሮ. ፲፮÷፲፫ ያለው ለዚህ ነውና፡፡


የጉባኤ ሐዋርያት ባሕርያዊ መገለጫዎች

የኅብረቱ አባላት በክርስቶስ ራስነት ያሉ መላእክት፣ ነፍሳተ ቅዱሳን፣ ሕያዋን ሰዎች፣ ብፁዓን ሰዎች፣ ሥውራን ሰዎች፣ ግኁሣን ሰዎች፣ ተነሳሕያን ሰዎች የሚተባበሩበት ጉባኤ ነው ብለናልና ጉባኤ ሐዋርያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትገለጥባቸው ባሕርያዊ መገለጫዎች አራት ናቸው። እነርሱም፦
፩. አንዲትነት
፪. ቅድስትነት
፫. ኲላዊትነት እና
፬. ሐዋርያዊትነት ናቸው።


እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በቀጣይ ክፍል ከላይ የዘረዘርናቸውን አራቱን መገለጫዎች አንድ በአንድ በተወሰነ መልኩ አይተን የዚህ የነገረ ቤተክርስቲያን ጽሑፍ ፍፃሜ ይሆናል።

(ክፍል ፬ - [የመጨረሻው ክፍል] ይቀጥላል ... )
30.04.202518:25
ሐዋርያዊነት (+) ኀብረታዊነት = ሐዋርያዊ ኅብረታዊነት


ሐዋርያዊነት የሚፈጸመው ሐዋርያት በሰበሰቧት አንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊት፣ ኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ አማካኝነት ነው:: ይህች ሐዋርያዊት ጉባኤ ሐዋርያዊ ትምህርትን፣ ሐዋርያዊ ትውፊትን፣ ሐዋርያዊ አረዳድን፣ ሐዋርያዊ ክህነትን፣ ሐዋርያዊ ሥርዓተ አምልኮትን ጠብቃ የምትጓዝ ሐዋርያት የጠሯት፣ የሰበሰቧት፣ ያሳመኗት፣ ያጠመቋት፣ ያቆረቧት፣ ያጸኗት፣ የሃይማኖተ ወንጌል ተቀባዮች ኅብረት ናት። "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንተ ላዕስ ኵሉ ጉባኤ ሐዋርያት" - (ሐዋርያት በስበሰቧት ከሁሉ በላይ በምትሆን በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን) — ሃይማኖተ አበው ፲፯፥፲፪ እንዲል። ሐዋርያዊት ኅብረትነቷ ሊጸናና ሊፈጸም የሚችለው የሕያው አካል የክርስቶስ ራስነት የተፈጸመላቸው ሕዋሳት ምእመናን አንድ ሁነው የሚገኙበት ጉባኤ ስለሆነ ነው።


ከሐዋርያት በኋላ የተነሡ አበውም በዚሁ መንገድ ሐዋርያውያን ሁነው በክህነት፣ በትምህርት፣ በልጅነት፣ በትውፊታዊነት ስንሰለቱን ይዘው ጠብቀው ይጓዛሉና በቅተው፣ ክርስቶስን ለብሰው፣ ለባሴ መስቀል ሁነው፣ ሕግን ፈጽመው፤ ራሱን በዘፈቀደ በሚችሉት መጠን እንደ ሃይማኖታቸው ጽንዐት እንደ አእምሯቸው ስፋት ገልጾላቸዋል። ነገር ግን በሐዋርያት ጉባኤ ተገብተው ይነገራሉ እንጂ ተለይተው አይነገሩም:: በዚያው ባሉበት ሐዋርያውያን አበው ተብለው ይነገራሉ እንጂ። በዓቂበ ሕግ ኑረው ምሥጢር ተገልጾላቸው እግዚአብሔርን በዘፈቀደ ማየት እንደሚችሉም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ ትምህርቱ "ዘቦቱ ትእዛዝየ ወየዓቀቦን ውእቱ ዘየፈቅረኒ ወለዘአፍቀረኒ ያፈቅሮ አቡየ ወአነሂ አፈቅሮ ወአርዕዮ ርአስየ" - (ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ) — እንዲል ዮሒ ፲፬፥፳፩፡፡

ጉባኤ ሐዋርያት በብዙ የተመሰለች በብዙ የተሰበከች የአንዲት የክርስቶስ ጉባኤ ናት፡፡ ራሷ ክርስቶስ አንድ ሲሆን በብዙ ኅብረ አምሳል የተመሰለለት እና በብዙ ኅብረ ትንቢት የተነገረለት እንደሆነ እርሷም አንድ ስትሆን በብዙ ይመሰልላታል፤ በብዙ ይነገርላታል:: ለቤተ ክርስቲያን ያልተመስለ ምሳሌ ያልተነገረ ትንቢት በየትም አይገኝም። ጥንቱን መጽሐፍ የተጻፈው እና ምሳሌ የተመሰለው በቤተ ክርስቲያን እና ለቤተ ክርስቲያን ነውና።

የሐዋርያት ጉባኤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሁሉም በላይ በተቀደስች በድንግል ማርያም አማናዊ አምሳልነት ትገለጻለች። ድንግል በድንግልና የጸናች እንደሆነች ቤተ ክርስቲያንም በድንጋሌ ሃይማኖት የጸናች ናት፤ ድንግል አካላዊ ቃልን በሥጋ እንደ ወለደች ቤተ ክርስቲያንም የምሥራች ቃሉ ወንጌልን ሰምታ በጎ ምግባርን የወለደች ናት:: ድንግል የድንግልና ወተትን በሚደንቅ ምሥጢር ለልጇ እንደ መገበች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ምግባር ትሩፋቷን ለልጇቿ የምትመግብ ባገኘችው ጸጋ ነዳያነ ጸጋን የምታጸና ናት፡፡ ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ እመቤታችንን በገለጸበት አንቀጽ ቤተ ክርስቲያን ተመሥጥራ ትገለጻለች ... "የሚደንቅ የሚጨንቅ ነገርስ ድንግል በድንግልና ሳለች እነሆ ወተትን አስገኝላተችና ይህ ሥራ በሰው ልቡና ከመመርመር ፈጽሞ የራቀ የረቀቀ ነው:: ሴቶች በልማዳቸው ከወንድ ሳይገናኙ ወተትን አያስገኙምና ያለዘርዐ ብእሲ እንደ ፀነሰችው እንዲሁም ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ በድንግልና ወለደችው፣ አምላክያደረገውን ድንቅ ሥራ ፍጹም ለማድረግ እንዲሁ በድንግልና ወተት ተገኘ።" — ሃይማኖተ አበው ፻፱፥፲፯ ብሎ በተናገረው ምሥጢር ቤተ ክርስቲያንም በጉባኤዋ ፍጽምት፣ ድንግል፣ የጸጋ ወተት ያስገኘች ድንግልም የብዙኃን ምእመናን እናትም ናት፡፡

ቤተ ክርስቲያን የሕያዋን መላእክት እና ደቂቀ አዳም ስብስብ እንደመሆኗ መጠን በሕያው መንፈስ ቅዱስ የጸጋ ተዋሕዶ ሕይወት ጸጋዊ ያላት፣ የማትበየን፣ በአካልነት ያለች የማትመረመር፤ የሚታወቅ እና በፍጡር የማይታወቅ ማንነት ያላት፣ የጸጋው ግምጃ ቤት፣ የክርስቶስ መላቱ ማደሪያው አካሉ ናት፡፡ "እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት" ኤፌ ፩፥፳፫ እንዲል፡፡ ጥንቱን ቅድስት ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን በመጀመሪያ በቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮ ኅብረት ሁና በተፈጥሮ ተገለጸች:: ዲያብሎስ ከማኅበረ መላእክት ከወጣ በኋላም በመላእክትና በሰው ተፈጥሮ ኅብረት ሁና በልዕልና መንፈስ በፍጻሜ ፍጥረት ዕለት በዕለተ ዓርብ ታወቀች፡፡ ከአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ኋላም በአካላዊ ቃል ሥግውነት አካለ ክርስቶስ ሕዋሰ ክርስቶስ ሆነች— (ቆላ ፩፥፲፰)


ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምሥጢር ጉባኤ ናት። ስለሆነችም ምናብ፣ ሐሳብ፣ ህልም ወይም አካል የለሽ አይደለችም::

«ቤተ ክርስቲያን» የተባሉም አካለ ክርስቶስ የተባሉ በአካልነት የሚታወቁ ሕያዋን ባለ አእምሮዎች ማኅበረ መላእክት እና ማኅበረ ምእምናን ናቸው እንጂ — ዕብ. ፲፪፥፳፩-፳፫። በኅብረቱ ውስጥ በእርሱ ፈጻሚነት የልቡና ሕግን እና የጽሑፍ ሕግን ሁሉ ፈጽመው ያለ ሕግ የሚኖሩ ተጋድሏቸውን የጨረሱ ቅዱሳን ሰዎች እና ቅዱሳን መላእክት እንዳሉ ሁሉ፤ ሕግን ለመፈጸም በሕግ የሚኖሩ ገና በተጋድሎ ጎዳና በዚህ የፍዳ ዓለም በውጣ ውረድ ዓለም መስቀል ተሸክመው ያሉም አሉ፡፡ መድኅን ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በገለጸበት በደብረ ታቦርተራራ ሕያዋን እና ሙታን፣ በአካለ ነፍስ ያሉ እና በአካለ ሥጋ ያሉት እንደነበሩ ልብ ይሏል — ማቴ. ፲፯፥፫ በአማናዊት ደብረ ታቦር በቤተ ክርስቲያንም በታቦር ተራራ የተገለጸው ኅብረት በአካልነት ይገለጽባታል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ምድራዊ፣ ሰው ሠራሽ ተቋም ወይም ድርጅት አይደለችም። በምድር ባለው ጉባኤዋ ለተቋም የሚኖሩ እንዳሉ ሁሉ በተቋምም የሚኖሩም አባላቶቿ ግን አሉ፡፡ ጉባኤ ሐዋርያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከምድራዊ ተቋምም፣ ከምድራዊ አስተዳደር፣ አደረጃጀት በላይ ናት፡፡ በየትኛውም ሚዛን ብትመዘን ምድራዊ ተቋምም፣ ምድራዊ ድርጅትም አይደለችም። ማኅበረ ሐዋርያትን ጉባኤ ቤተ ክርስቲያንን በተቋም፣ በድርጅት መወሰን ክሕደት ኑፋቄ ነው፡፡ እርሱ ካለበት የምትኖር የክርስቶስ አካሉ ናትና በምድራዊ ድርጅት አትበየንም:: አንድን ሰው ወይም ቡድን ድርጅቱ ተቋሙ ቢበድለው «ቤተክርስቲያን በደለችው» ሊባል አይችልም። የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይኖራል የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል" — ዮሐ. ፲፪፥፳፮ እንዲል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ባለበት የምትኖር አካሉ ሙላቱ ናት እንጂ።

ኅብረተ ሐዋርያት የማትበየን የምትጨበጥ፤ የምትበየን የምትነገር፤ የማትመረመር የምትታወቅ፤ የማትወሰን የምትወሰን መንፈስም አካልም የሆነች ጉባኤ ናት — ፩ ቆሮ. ፪፥፲፭። ስለሆነም ሁሉም ነገር ከቤተ ክርስቲያን በታች ነው:: "እንተ ላዕለ ኵሉ" - (ከሁሉ በላይ) የሚባል ግላዊ ሰውና ግላዊ መልአክ የለም። ኅብረተ ሐዋርያት ግን ከሁሉ በላይ ናት። “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ሐዋርያት" - (ሐዋርያት በሰበሰቧት ከሁሉ በላይ በምትሆን በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን) ሃይ.አበ. ፲፯፥፲፪ እንዲል።
27.04.202517:33
እግዚአብሔር ቢወድድ እና ቢፈቅድ ሰሞኑን ነገረ ቤተክርስቲያን ላይ የሚያተኩር ጽሑፍ ይኖራል የምለቅቀው። አልጨረስኩትም ግን ልየውና በጣም ከረዘመ በተከታታይ ክፍል፣ ካልሆን በአንዴ እለቅቀዋለሁ። "ረዘም ያለ ጽሑፍ ባትጽፍ ጥሩ ነው ብዙ ሰው ረጅም ነገር አይመቸውም" ብላችሁ አስተያየት የሰጣችሁኝ የምወዳችሁ እህቶቼና ወምድሞቼ በጣም ከብዙ ይቅርታ ጋር እኔ በሃሳባችሁ አልስማማም። ሲጀመር የምጽፈው ብዙ ሰው እንዲከተለኝ አይደለም። እንደዛ ቢሆን ፌስቡኬን delete ማድረግ አያስፈልገኝኝም ነበር።

ከህፃንነቴ ጀምሮ አባቶቼ፣ ታላላቅ ወንድሞቼ እንዲሁም ትንሽ ያነበብኳቸው መጻሕፍቶቼ ያስተማሩኝን ለእናንተ የምጽፈው አደራም ጭምር ስላለብኝ ለራሴ ዕዳ በደል እንዳይሆንብኝ ነው። ደግሞ ሁሉ ነገር እኮ Context እንደሌለው እንደ ቲክቶክ ቪዲዮ የግድ አጭር መሆንም የለበትም። በተለይ ሃይማኖት ነክ ነገር ጊዜ ተወስዶ የሚነበብ፣ የሚመረመር እንዲሁም የሚጠየቅ ስለሆነ። ከላይ ከላይ 'ዕውቀት' እንዴት የመናፍቃን መጫወቻ እንዳደረገን ብናውቅ የት በደረስን!

ለማንኛውም አይ እኔ አጭር ነገር ነው የሚመቸኝ ያንተስ በዛ የምትሉ ይሄ ቻነል ለናንተ አይሆንምና Leave channel እያላችሁ ብትወጡ ቅር እንደማይለኝ ይኸው ዛሬ ነገርኳችሁ። ሌሌቻችሁ ግን ጓደኞቻችሁን ወደዚህ ቻነል መጋበዝን፣ የሚለቀቁ ጽሑፎችን ብዙ ሰው አንብቦ እንዲጠምባቸው ሼር ማድረግን ቸል አትበሉ። ጥያቄ ያለባቸውንም ሰዎች ጥያቄ እንዲያቀርቡ አበረታቷቸው።

እዚህ ቻነል የሚፃፈውን ጽሑፍ አንድም ሰው አንብቦ ከተጠቀመ ለኔ አገልግሎቴ ተፈጸመ ማለት ነው፤ ቢያንስ መክሊቴን አልቀበርኩም።  ዓለም ላይ ያሉ ነገሮች ሁሉ ተደምረው ከአንዲት ነፍስ ዋጋ እንደማይበልጡ ጠንቅቄ ስለምረዳ በዚህ ጉዳይ ሃሳቤን አልቀይርም።

"ኦ አኃው፥ አንብብዋ ለዛቲ ጽሕፈት በተዓቅቦ ወበኅድዓት፤ እመኒ ኅዳጥ በንባብ፤ ብዝኅት ይእቲ በረባሕ፥ ወበቁዔት" እንዲሉ አባቶቻችን (ወንድሞች ሆይ፥ ይችን ጽሑፍ በጥንቃቄና በጸጥታ ተመልከቷት፤ በንባብ ጥቂት ብትሆን፥ ረብሕ ጥቅም በመሆን ብዙ ናትና)።

አንብቡ [እናንብብ] ግድ የለም አይገድለንም፤ ደግሞስ ማን አንብቦ እንደሞተ እኛ እንሞታለን???
27.04.202505:45
"እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን" — ዮሐ ፳፥፳፰


የዳግም ትንሳኤ ምሥጢር

ቶማስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነስቶ ለሐዋርያት በተዘጋው በር ገብቶ «ሰላም ለእናንተ ይሁን» ብሎ የትንሳኤውን ብሥራት ሲነግራቸው አልነበረምና 'ካላየሁ አላምንም' አለ።

ቶማስ 'ካላየሁ አላምንም' ማለቱ ሌሎቹ ሐዋርያት ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ 'አየን፥ ዳሰስን' ብለው ሲያስተምሩ እርሱ ግን 'አየሁ፥ ዳሰስሁ' ብሎ ሳይሆን 'ሰማሁ' ብቻ ብሎ የሚያስተምር ነውና እንደ ወንድሞቹ 'ሰማሁ' ከማለት ይልቅ 'አየሁ' ብሎ ማስተማር የበለጠ ተአማኒነት ይኖረዋልና ለዚህ ነው።

ጌታችንም በመጀመሪያው ትንሣኤ ለአሥሩ ደቀ መዛሙርት በተዘጋ በር እንደታየ ዳግመኛ ለሁለተኛ ጊዜ በዳግም ትንሣኤ በተዘጋ በር ገብቶ «ሰላም ለእናንተ ይሁን» ብሏቸዋል፤ ለቶማስም ያንኑ የወደደውን አደረገለት።

ነገር ግን ቶማስ የክርስቶስን ጎን ሲዳስስ እጁ ተቃጠለበትና «ጌታዬ፥ አምላኬ» ብሎ ተናገረ።


እንግዲህ ስለ ክርስቶስ 'ካላየሁ አላምንም' ያለ ቶማስ ክርስቶስን አይቶ ምን ተማረ?

፩. የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነትና ጌትነት ተረዳ።

ይኸውም «አምላኬ» ብሎ አምላክነቱን ፤ «ጌታዬ» ብሎ ጌትነቱን ተናገረ።


፪. የተዋሕዶን ምሥጢር

ይኸውም ክርስቶስ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው። በመሆኑም መለኮት የሥጋን ሥጋ የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ እንዳደረገ ተረዳ።

ክርስቶስ የሚዳሰስም የማይዳሰስም፥ ግዙፍም ረቂቅም አምላክ መሆኑን ተረዳ። ሥጋ የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ እንደማድረጉ ሥጋ በመለኮት አይዳሰስም። ይህም ሊታወቅ ቶማስ የክርስቶስን ጎን ሲዳስስ የዳሰሰችበት እጁ ተቃጠለች። የማይዳሰስ ረቂቅ እሳት ብቻ ነው እንዳንል ደግሞ ተዳሰሰ። የሚዳሰስ ግዙፍ ሥጋ ብቻ ነው እንዳንል ደግሞ አቃጠለው።


፫. በተዘጋ በር መግባት

የእኛ ግዙፍ ሥጋ በተዘጋ በር መግባት አይቻለውም። ክርስቶስ ከእኛ ነስቶ የተዋሐደው ሥጋ ግን የመለኮትን ገንዘብ ረቂቅነትንም ገንዘቡ አድርጓልና ረቂቅም ግዙፍም ነው። በመሆኑም በተዘጋ በር ገብቶ ረቂቅ ዘእም ረቂቅ (ከረቂቆች ሁሉ በላይ የረቀቀ) መሆኑን አስረዳ።


ጌታችን ቶማስን «እመን እንጂ አትጠራጠር!» ብሎታልና እኛም አምላክ በሥጋ ገንዘብነት ያደረጋቸውን ማለትም መራብ መጠማቱን፤ መያዝ መሰቀሉን መሞቱን ስናይ ፍጡር እንደሆነ በማሰብ ልንጠራጠር በመለኮት ገንዘብነት ደግሞ ሙት ሲያነሳ፣ ዐይን ሲያበራ፣ ሲሰወር ስናይ 'ይህማ ፈጣሪ ቢሆን ነው እንጂ' እያልን መጠራጠር እንደማይገባን እኛም ከቶማስ ልንማር ይገባናል።

እንኳን ለዳግም ትንሣኤ አደረሳችሁ!
"ስለቀናች ሃይማኖት ነፍስህን አሳልፈህ የሠጠህ ጊዮርጊስ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል" — መልክዐ ጊዮርጊስ።

ሃገራችንን ለሰከንድ እንኳን የማይዘነጋት ብርቱ ገበዛችን ነው ጊዮርጊስ። በረከቱ ትደርብን።

እኛ የዛሬ ክርስቲያኖች ግን አሁን ላይ ስለ ጊዮርጊስ ሰማዕትነት ዘመናችንን ሁሉ ተምረን ሰማዕት መሆን ቢያቅተን እንደው ቢያንስ ቢያንስ እንደ ጊዮርጊስ ፈረስ መጋለብ እንኳ ብንችል እንዴት ጥሩ ነበር!
29.04.202519:52
ነገረ ቤተክርስቲያን 
(ክፍል ፩)

«ነገረ ቤተ ክርስቲያን» ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለው ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ምን እንደ ሆነ የምንማርበት የትምህርት ዘርፍ ነው፡፡ ምንም እንኳን ትምህርቱ እጅግ ጥልቅና ራሱን የቻለ ብዙ መጽሐፍ የሚወጣውና በጣም ብዙ ሰፊ አሳቦችን በውስጡ የያዘ ቢሆንም በዚህ ጽሑፍ ግን በተለያዩ አካላት ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚነሡ ጥያቄዎችን ለመመለስ ያህል ብቻ በጥቂቱ እናያለን፡፡ የጽሑፉ ዋና ዓላማም “ቤተ ክርስቲያን ድርጅት (ተቋም) ዲኖሚኔሽን ናት፤ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ድኅነት ይገኛል፤ ለቤተ ክርስቲያን ስግደት አይገባም፤ ቤተ ክርስቲያን መሔድ አያስፈልግም፤ ቤተ ክርስቲያን ትሳሳታለች፣ ስለዚህ መታደስ/ይቅርታ መጠየቅ ... አለባት” የሚሉ የተሳሳቱ አሳቦችን ለሚያነሡ አካላት መልስ መስጠት ነው፡፡

«ቤተ ክርስቲያን» የሚለው ቃል ሦስት ዓይነት ሰዋስዋዊና ዘይቤያዊ ትርጕም አለው ይሉናል አባ ጎርጎርዮስ ፲፱፻፸፰ በፃፉት መጽሐፋቸው ገጽ ፲፪-፲፯ ላይ፡፡

፩. የመጀመሪያው  ትርጉም

ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ያመለክታል፡፡ ይኸውም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡- “ወደ ማኅበር ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለሁ”  — ፩ኛ ቆሮ. ፲፩.፲፰። እንዳለው የክርስቲያኖች ቤት፣ የክርስቲያኖች መኖሪያ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ባወቀ የክርስቶስ ደም በነጠበበት የምትተከል፣ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሜሮን የከበረች፣ ሥላሴ በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገኑባት፣ የክርስቶስ ሥጋዌ የሚነገርባት፣ ሥጋውና ደሙ የሚፈተትባት ቅድስት መካን ቤተ ክርስቲያን ተብላ እንደተጠራች ቅዱሳት መጻሕፍት በስፋት ይገልጻሉ፡፡

“ቤተ ክርስቲያን እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ” (መዝ. ፻፳፩፥፩)፤

 “በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ” (ሐዋ. ፲፩፡፳፮) የሚሉት ንባቦች የቤተ ክርስቲያን አንደኛው ዘይቤያዊ ትርጕም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ዳግመኛም “የእግዚአብሔር ቤት” (ዘፍ. ፳፰፥፲፯)፣ 
“በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ” (መዝ. ፭፥፯)፣
 “የአባቴ ቤት” (ሉቃ. ፪፡፵፱)፣ “የእግዚአብሔር ቤት” (ዕብ. ፲፡፳፩) የሚሉት ይህን የሚያስረዱ ማሳያዎች ናቸው፡፡

በተለይም ቅዱስ ጳውሎስ በመንፈስ ለወለደው ልጁ ለጢሞቴዎስ፦ “ብዘገይ ግን፣ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፣ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው” (፩ኛ ጢሞ. ፫፡፲፭) በማለት የገለጠው የእግዚአብሔር ቤት (ሕንፃ) ቤተ ክርስቲያን እንደሚባል ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡


፪. ሁለተኛው ትርጉም

እያንዳንዱ ምእመን (ክርስቲያን) ቤተ ክርስቲያን የሚባል መሆኑን የሚያስገነዝብ ትርጕም አለው፡፡

ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ” (፩ኛ ቆሮ. ፫፥፲፮)፣ 

“… ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ” (፩ኛ ቆሮ. ፮፡፲፱) በማለት የገለጸው ይህን ነው፡፡ ይኸውም በመንፈሳዊና በምሥጢራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ፥ እርሱ አድሮባቸው የሚኖሩ፥ በቅዱስ ሜሮን የታተሙ (፩ኛ ዮሐ. ፪፥፳) እና ሥጋውንና ደሙን የተቀበሉ ምእመናንን ለማመልከት ነው፡፡

፫. ሦስተኛው ትርጕም ደግሞ “በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል” (፩ኛ ጴጥ. ፭፡፲፫) እንዲል የክርስቲያኖችን ኅብረት ወይም አንድነት (ማኅበረ ምእመናንን) የሚያመለክት ነው፡፡ በሰማይ ያሉ የድል ነሺዎች፣ በምድር ያሉ ከፍትወታት፣ ከኃጣውእና ከርኵሳን መናፍስት ጋር የሚጋደሉ የክርስቲያኖች አንድነትና ኅብረት ማለት ነው፡፡ ይህች ኅብረትና አንድነት ራሷ ክርስቶስ የሆነላት፣ የክርስቶስ አካል ናት፡፡

ኅብረታችንም “በደስታ ከተሰበሰቡት አእላፋት መላእክት፣ በሰማያትም ከተጻፉ ከበኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ከሚሆን ከእግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ከሆኑት ከጻድቃን መንፈሶች” (ዕብ. ፲፪፡፳፪-፳፬) ጋር እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ነግሮናል፡፡ እኛም በዚህ ክፍል ትኵረት የምናደርገው በዚሁ በሦስተኛው ትርጓሜ ላይ ነው፡፡

እኛ በግእዝ ቋንቋ “ቤተ ክርስቲያን” የምንለውን ጽርዓውያን (ግሪካውያን) “ኤክሌሲያ” ይሉታል። ትርጓሜውም “ለአንድነትና ለአንድ ልዩ ዓላማ የተጠሩ” ማለት ነው፡፡ ይኸውም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡- “ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” (፩ኛ ቆሮ. ፩፡፱) ብሎ ከገለጸው ጋር የተስማማ ነው፤ የቤተ ክርስቲያን ዓላማ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር አንድነትና ሰማያዊ ዓላማ በሃይማኖት መጥራት ነውና፡፡

ግሪኮች “ኤክሌሲያ” የሚለውን ቃል መጀመሪያ አንድን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይም አስተዳደራዊ ችግር ለመፍታት ለተሰበሰቡ ሽማግሌዎች መጠሪያ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በ፪፻፹፬ ከክርስቶስ ልደት በፊት ብሉይ ኪዳንን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ የተረጐሙት ሰብዓ ሊቃናት ግን “ቀሃል” የሚለውን የዕብራይስጥ ቃል “ኤክሌሲያ” ብለው ተርጕመውታል፡፡ ትርጕሙም የእስራኤልን ጉባኤ የሚገልጽ ነው፡፡

እንደ ምሳሌም የሚከተሉትን ኃይለ ቃላት እንመልከት፥

“ማኅበሩንም ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስባቸው” (ዘሌ. ፰፡፫)፡፡ እዚህ ላይ "ማኅበሩ" ተብሎ የተገለጠው በምሥጢር ስለዚህች ጉባኤ ነው፡፡ በዚህች ጉባኤም አሮን ሊቀ ካህን ሆኖ ተሾሟል (ዕብ. ፭፡፬)፡፡

ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም እንዳስተማረው፥ ይህ የአይሁድ ጉባኤ የቤተ ክርስቲያን አምሳል፣ መርገፍ ወይም ጥላ ነበር (The Catechetical Lectures of St. Cyril, Archbishop of Jerusalem, P. 335)። እንደ ሊቁ አስተምህሮ አብዛኞቹ አይሁዳውያን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ባለማመናቸው ምክንያት ከዚሁ ጉባኤ ቢወጡም ጉባኤው ግን አልተበታተነም፤ ሊበታተንም አይችልም፡፡

ይልቁንም ጌታችን፦  “በዚህም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን (ጉባኤዬን) እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም” (ማቴ. ፲፮፡፲፰) በማለት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ጉባኤ አጸናት እንጂ፡፡

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም በሰዎች አመለካከት የተለያየ ዓይነት ስያሜ (እንደ አይሁዳውያኑና አሁን እንደምንሰማው ብዙ ስም) ቢሰጠውም ይህ የሰዎች የተሳሳተ ግንዛቤ የባሕርይ አምላክነቱን ሊለውጠው አይችልም፡፡

 “ቤተ ክርስቲያን የገሃነም ደጆች አይችሏትም” የሚለው ኃይለ ቃልም ይህን ጥልቅ ነገረ ሃይማኖታዊ ጽንሰ ሐሳብ በውስጡ የያዘ ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ይህቺ ጉባኤ (ቤተ ክርስቲያን) በቅድስት ሥላሴ ባለው እምነቷ ህልውናዋን የጀመረችው በዓለመ መላእክት ማለትም ሰው ከመፈጠሩ በፊት ነው፡፡ ከዚያም ከአቤል ጀምሮ እስከ ሐዲስ ኪዳን መግቢያ ድረስ በነበረው የደጋግ ሰዎች አንድነት ቀጠለች፡፡
27.04.202516:41
የኤማሁስ መንገደኞች ነገር .............

“እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው”  — የሉቃስ ወንጌል ፳፬፥፳፩

ጌታችን ከሙታን በተነሣ ቀን ልባቸው አዝኖ ወደ ኤማሁስ የሚጓዙ ሁለት ሉቃስና ቀለዮጳ የሚባሉ ደቀ መዛሙርት ነበሩ። ዓለም ክርስቶስን በመስቀሏ ታላቅ ተስፋ መቍረጥ ገጥሟቸውም ነበረ። ደግ ገድሎ ደግ ነገር መጠበቅ፣ ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ የተለመደ የዓለም ጨዋታ ነው። በነጻ የመጣው ከሄደ በዋጋ፣ ያለ ልፋት የመጣው ከሸሸ በታላቅ አሰሳም ተመልሶ አይገኝም። የፈወሰ እጅ መቸንከሩ፣ ያጽናና አንደበት ሆምጣጤ መጋበዙ፣ አልዓዛርን የፈለገ እግር በችንካር መታሠሩ፣ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስን የሸሸገ ጎን በጦር መወጋቱ እንደ ሰው ሰውኛ ሲያዩት ተስፋ በእውነትም የሚያስቆርጥ ነው። ክርስቶስ ግን የሞተው በአብ ፈቃድ፣ በራሱም ፈቃድ፣ በመንፈስ ቅዱስም ስምረት መሠረት ነው። የክርስቶስን ሞት በሥጋዊ አእምሮ ሲያስቡት ዕለቱን ተከስሶ ዕለቱን መሞቱ፣ ሊሰቀል ታስቦ ቀድሞ መገረፉ፣ ዳኛው ቀያፋ ምስክሩ ሎሌው መሆኑ በዓለም ተስፋ አስቆርጧቸው ነበር። ከሕግ አኳያ የክርስቶስን ሞት ሲያዩት ፍርድ አጉዳይ ዓለም አሳዝናቸው ነበር።

መግደላዊት ማርያም በድኑን ተኝቶ አገኘዋለው ስትል በአትክልቱ ስፍራ ቆሞ አየችው፤ የኤማሁስ መንገደኞችም በቃ ሞቷል አሁንማ ብለው ከጀርባቸው ጥለውት በኀዘን ሲጓዙ አብሮአቸው ይጓዝ ነበረ። «ክርስቶስ የለም» እያሉትም ከአጠገባቸው አለ፤ ሲክዱት የማይክድ ታማኝ ወዳጅ ነው እርሱ። አንዳንዴ ተስፋ መቍረጥ የእግዚአብሔር ሀልወት በአጠገባችን እንዳለ ራሱ ያስረሳናል። ሌላ ጊዜ ተስፋ የሚሆኑ ነገሮች ተስፋን አይሰጡም፤ ግን እኮ ተስፋ ራሱ እግዚአብሔር ነው። በራሱ እግዚአብሔር ተስፋ ካላደረግን ጭላንጭሎች ወደ ጨለማ፣ ፀሐይ ወደ ጽልመት፣ ጨረቃ ወደ መሰወር፣ ከዋክብት ወደ ደመና ሲገቡ ልባችን መፈራረስ ይጀምራል። ጭላንጭል አዲስ ወዳጅ፣ ፀሐይ የንጉሥ ፊት፤ ጨረቃ ደግ መካሪ ፣ ከዋክብት ትውልድ ናቸው። አዲስ ወዳጅ ብቅ ጥልቅ ሲል፣ ንጉሥ ቃሉን ሲያብል/ሲዋሽ፣ ደግ መካሪዎች የክፋት ሰባኪዎች ሆነው ብቅ ሲሉ፣ ትውልድ የሞት ልጅ ሲሆን ልብ በጽኑ ይደክማል። ተስፋ ግን እግዚአብሔር ነውና አሁንም ይቀጥላል።


ተስፋ ...

ተስፋ ከልብ ሲታጣ ፊት የኀዘን አደባባይ ይሆናል። አካል ቀፎ ነው፣ ተስፋ ግን ሞተር ነው። እግር ካላቸው ተስፋ ቢሶች እግር የሌላቸው ተስፈኞች ፈጥነው የፈለጉበት ይደርሳሉ። ፍትሕ ከዚህ ዓለም ዳኞች፣ እውነት ከመሪዎች፣ ጽድቅ ከካህናት፣ እምነት ከደቀ መዛሙርት ቢጠፋም ገና ተስፋ አለ። ተስፋ የጋረደንን ደመና ሰንጥቀን መንበረ ሥላሴን ስናይ የሚመጣ እጅግ ብርቱ ነገር ነው። ሁሉም ነገር ከስፍራው ይታጣል፣ እግዚአብሔር ግን በማይናወጥ መንግሥቱ ለዘለዓለም ይኖራል።

ተስፋ በጆሮ ሹክ ሲል ገና ነው ይላል፤ ሬሳ እየተጋዘም ገና ነው። ተስፋ በዐይን ላይ ሲያርፍ ከተራራው ጀርባ ያለውን ያያል፤ ተስፋ አፍንጫ ላይ ሁኖ የሕይወትን መዓዛ ያውዳል። ተስፋ አፍ ላይ ሁኖ “ይህም ያልፋል” ይላል፤ ተስፋ እጅ ላይ ሁኖ ድሆችን ከውድቀት ያነሣል። ተስፋ ደርሶ ወደ ጨለሙ መንደሮች ይገባል፤ ተስፋ ሰማይ ቆሞ ምድርን ያስጀምራል፤ ተስፋ የአሁኑን ሳይሆን የሚመጣውን፤ የሆንነውን ሳይሆን የምንሆነውን ያወራል። ተስፋ ዜና አይሰማም፣ ነገር ግን እኔ ራሴ አንድ ቀን ዜና ነኝ ይላል። ተስፋ ትዕግሥትን ጣፋጭ፣ ፍቅርን ብርሃን፣ እምነትን ቆራጥ ያደርጋል።
ቀላል ነገር አይደለም — ተ ስ ፋ!


ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ ..........

ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ሞቱ ላይ ቀርተው ትንሣኤውን አልሰሙም ነበር። ኀዘን በደስታ መተካቱን ያበሰራቸው አልነበረም። ተስፋ ትንሣኤውን ለማብሰር ሐዋርያ ባይሄድላቸው የተነሣው ጌታ ራሱ ሐዋርያ ሁኖ ያሉበት ድረስ ሄደላቸው። ሐዋርያ ሲሰብክ «ክርስቶስኮ ተነሣ!» ይላል፤ ክርስቶስ ግን ሲሰብከ «ይኸው ተነሣሁ!» ብሎ ነው። በብርቱ ስናዝን ራሱ ወደ እኛ በይመጣል። ለዚህ ነው ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትን በመዝሙሩ፦
"ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ፤ ወያድኅኖሙ ለትሑታነ መንፈስ።" — ( እግዚአብሔር  ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል) ብሎ ሲያመሰግን የምናገኘው — መዝ ፴፬፥፲፰።

ሉቃስና ቀለዮጳ ከኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን አቅጣጫ ቀጥሎ ወደ ምዕራብ አድርገው ወደ ኤማሁስ አሥራ አንድ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘዋል። መንገዳቸው ግን ፋሲካ በዓል ላይ እንደ ቆየ በደስታና በጉልበት ሳይሆን ዓለም ስለ ሰቀለችው ስለ ክርስቶስ በማሰብ ኀዘን የሞላበት ነበረ። ስለ ዓለምና ስለ ሰው በጥልቀት ለማወቅ መሞከር በመጨረሻ ተስፋ መቍረጥ ያመጣል። "ኵሉ ቃል ዘበሕማም ኢይክል ብእሲ ለተናግሮ ኢይጸግብ ዓይን በርእይ ወኢይመልእ እዝን በአጽምኦ።" እንዲል ሲራክ በመጽሐፈ መክብብ ፩፥፰ ላይ። (ነገር ሁሉ ያደክማል ሰው ይናገረው ዘንድ አይችልም፤ ዐይን ከማየት አይጠግብም፥ ዦሮም ከመስማት አይሞላም) እንደማለት።

ደስ የሚለው ነገር እነዚህ ሁለት ሰዎች ተስፋ ቢቆርጡም የሚያወሩት ስለ ክርስቶስ ነበረ። ስሙ በተነሣበት ለመቅረት የማያስችለው ጌታም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ምክንያቱም ትዝ ካላችሁ በማቴዎስ ወንጌል ፲፰፥፳ ላይ እንዲህ ሲል ቃል ገብቶ ነበርና፦ "እስመ ኀበ ሀለዉ ክልኤቱ ወሠለስቱ ጉቡአን በስምየ ህየ ሀለውኩ አነ ማእከሎሙ።" — (ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና)። ክርስቶስ የቁጥር ችግር የለበትም፤ ሁለት ሚሊየንም እንሁን ሁለት፣ በስሙ ተሰብስበን ከጠራነው መሀከላችን ሊገኝ የታመነ ጌታ ነው።



ሰዓቱ ሠርክ እየተቃረበ ያለበት፣ አቅጣጫው ወደ ምዕራብ ወደ ፀሐይ መጥለቂያ ነበረ። የማታው ፀሐይ ዐይናቸው ላይ አርፋ መንገዳቸውን በእምነት እንጂ በማየት እየረገጡ አልነበረም። አጠገባቸው ያለውንም ጌታ ማየት አልቻሉም። ፀሐይ ስትጠልቅ የማይጠልቅ የጽድቅ ፀሐይ አለ፤ እርሱም ያመንነው ክርስቶስ ነው።

የልባቸው ስብራት አርያም ድረስ ደርሶ ክርስቶስ ሊታደጋቸው አብሮ ይሄድ ነበረ። «ለቀባሪው አረዱት» እንደሚባለው ስለ ክርስቶስ ለክርስቶስ ይናገሩ ነበረ። ጥልቅ ስሜታቸውን ሲገልጡ ጥልቅ እውቀትን ነገራቸው፤ ልባቸውን ሲቆርሱለት እርሱ ደግሞ የታወረ ዐይናቸውን የሚያበራ እንጀራ ቆረሰላቸው። እነርሱ ስለ ቅርቡ የዕለተ ዓርብ ፍርድ ሲያወሩ ስለ ነቢያት ትንቢት ከስር ጀምሮ ተረከላቸው፤ ድብቆች ከክርስቶስ ምንም አያገኙም። ደግሞስ እነርሱ አላዩትም ማለት አላያቸውም ማለትም አይደለም፤ አላመኑም ማለት አልተነሣም ማለት አይደለም። ክርስቶስ እኛ እስክናየው ቢጠብቅማ ኖሮ እስከ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ወደፊትም አንድንም ነበር። ይሄ ኃጢአት ያወረው ዐይናችን አይደለም ክርስቶስን አጠገባችን ሆነው የሚጫወቱብንን አጋንንት የማየት አቅም ስለሌለው አይደል ይኸው የሚበጀንን ትተን በማይበጀን ስንባዝን የምንኖረው።

እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው ስንል ማወቁ በምንም ስለማይጠረጠር ነው። ግን ሁሉን እግዚአብሔር እያወቀ አውቆ የማያውቃቸው ነገሮች ደግሞ አሉ። ለምሳሌ፦
ኤማሁስ ......

ተጓዦችሽ በጎዳናሽ
መልካም ነገርን ሲያወሩ
የአምላክን መከራ ሞት
በተመስጦ ሲናገሩ
መድኃኔዓለም መምህራቸው
ተገኝቶ መሃላቸው
እያወቀ እንዳላዋቂ
ቢሆንባቸው ጠያቂ
ያልነበረ በሀገሩ
እንግዳ ለመንደሩ
መስሏቸው ተረኩለት
የሆነውን አወጉለት፡፡

ሲጓዙ ውለው ቢመሽ ቀኑ
ቤታቸው እንዲያድር ተማፀኑ፡፡
ጌታም አይቶ እንዳላወቁት
ሊያፀናቸው በሃይማኖት
ቢሰጣቸው መዓዱን አበርክቶ
እርሱን አዩ ልቦናቸው በእምነት በርቶ፡፡

እኛም እንደ ሉቃስ ቀለዮጳ
ብንመገብ የሕይወት ምግብን
ተከፍቶልን ልቡናችን
ይታየናል አምላካችን፡፡
30.04.202518:25
ሐዋርያዊነት በነገረ ቤተክርስቲያን
(ነገረ ቤተክርስቲያን - ክፍል ፪)

ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊ፣ ክሡታዊ፣ ሐዋርያዊ፣ ኅብረታዊ፣ ቅብብሎሻዊ ሃይማኖት አለኝ ማለት የሚቻለው ከጥንቱ ከመሠረቱ ሳይበጣጠስ "ነቅዕ ንጹሕ ዘአምአንቅዕተ ሕግ ንጹሓን" (ከንጹሐን የሕግ ምንጮች የተገኘ ንጹሕ ምንጭ) ተቀብሎ በሐዋርያዊነት መጽናት ሲቻል ብቻ ነው::
አንድ ኦርቶዶክሳዊ ሰው ርቱዕ ሃይማኖት በርቱዕ ትምህርት ተቀብያለሁ ለማለት የተገለጠውን ትምህርተ ሃይማኖት ሐዋርያዊ አድርጎ፣ ሰንሰለቱን ጠብቆ፣ በኅብረት ሁኖ ሳይቀንስ፣ ሳይጨምር ተቀብሎ፣ የተቀበለውን መጠበቅ፣ የጠበቀውን ለተተኪ ትውልድ መስጠት ሲችል ነው::


«ሐዋርያዊነት» ማለት ክርስቶሳዊነት ማለት ነው። የሐዋርያት ነቃቸው፣ አለቃቸው፣ ሐዋርያቸው ክርስቶስ ነውና። ሐዋርያ ጻድቅ ቅዱስ ጳውሎስ "ወይእዜኒ አኀዊነ ቅዱሳን ወጽዉዓን አምሰማይ ከማነ ርእይዎ ለዝንቱ ሐዋርያክሙ ሊቀ ካህናት ዘኪያሁ ትትአመኑ ኢየሱስ ክርስቶስ" - (ስለዚህ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ) — ዕብ. ፫፥፩ ብሎ የክርስቶስን ሐዋርያነት ገልጾልናል፡፡ መድኅነ ዓለም ክርስቶስ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን ዙሮ አስተምሮ፣ ሐዋርያ ተብሎ፣ አምነውበት ለጊዜው በእግር ፍጻሜው ግን በግብር የተከተሉት ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያትን ሐዋርያት አሰኝቷቸዋል፡፡ ምክንያቱም «ሐዋርያዊነት» ማለት ክርስቶሳዊነት፣ የክርስቶስ ደቀ መዝሙርነት ማለት ነውና፡፡


ቅዱሳን ሐዋርያት ትምህርታቸውን፣ መረዳታቸውን ከምድራዊ ሐዋርያ ያገኙት አይደለም፤ የሐዋርያት አምላክ ከሆነው፣ የጽድቅ ሐዋርያችን ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ነው እንጂ፡፡ ከእውነተኛ እምላክ ሲሆን በዘመነ ሥጋዌው ባደረገው የፈቃድ ተልእኮው ሐዋርያ ክተስኘው ከክርስቶስ የተማሩ ሐዋርያት የነቁ (የምንጩ) ተቀባዮች ናቸውና የእነሱን ሁለንተና ወንጌላዊነት እንደ ሐዋርያት ደቀ መዝሙር ሁነው የተቀበሉ ሁሉ «ሐዋርያውያን፤ ኦርቶዶክሳውያን» ይባላሉ። በምንጭነት፣ በነቅዕነት የትምህርት፣ የክህነት፣ የወንጌል ባለቤት እርሱ ብቻ ነውና:: ክርስቶስ የሐዋርያት ሐዋርያቸው ነው፡፡ "ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያነ መልአክ" -  (ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ወጥቶ ወርዶ ያስተማረን ሐዋርያችን ነው) እንዳለ ደራሲ በመልክአ ኢየሱስ።

ሐዋርያዊት ሃይማኖት፣ ሐዋርያዊት ትምህርት፣ ሐዋርያዊ ክህነት ብንል ከባለቤቱ ከክርስቶስ የተገኘ፣ በእውነተኛ ተከሥቶ ከምንጩ ከእግዚአብሔር ወልድ የተሰጠን እውነት ማለት ነው፡፡ ከሐዋርያት ጀምሮ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በሐዋርያዊት ሰንሰለት ሥር በሚኖሩት አድሮ ምሥጢር የሚገልጽ ዋጋ የሚሰጥ እርሱ ነውና። "ዘየዐሲ ተወካፊ" - (ሰጪም በሰጠው ዋጋ አድርጎ የሚሰጥም እርሱ ነው) — መጽሐፈ ኪዳን:: በሐዋርያት ላይ አድሮ የሚኖረው፣ ዛሬም ባሉት ሐዋርያውያን አድሮ ያለው፣ ወደፊትም በሚነሡ የሐዋርያት ተከታዮች አድሮ የሚኖር የጸጋ ባለቤት የወንጌል መምህር ሐዋርያ ጽድቅ ክርስቶስ ነው:: ለሠለስቱ ምእት እንኳን በጉባኤ ተገልጾ ከኤጲስ ቆጶሳት እንደ አንዱ ሁኖ አእምሯቸውን እያቀና ከ፫፻፲፰ቱ አንዱ እርሱ ክርስቶስ ከጉባኤው ባለመለየት የቀናች የጸናች ሃይማኖትን ሰጥቷቸዋል:: ከእነሱ አንዱን ኤጲስ ቆጶስ መስሎ የቀናች ሃይማኖትን አስተማራቸው" — ተረ.ቄር፳፭፥፲ እንዲል፡፡ ያለ እርሱ የሚሆን ምንም የክርስትና ጉባኤ፣ ትምህርት፣ እውነት፣ ክህነት የለምና።
ኦርቶዶክሳዊ ሰው ከመጀመሪያ ተቀባዮች ከሐዋርያት አረዳድ ያልተናወጸ መሆን ካልቻለ ከነቁ (ከምንጩ) ከሐዋርያ ጽድቅ ከክርስቶስ የተመተረ የተለየ ይሆናል፡፡
የሐዋርያት ሁላዊ የጸጋ ነቅዕ ክርስቶስ ነው፤ ይህ ነቅዕነት ደግሞ ለተቀባዮች የሚገኘው በሐዋርያዊት ሰንሰለት በኩል ነውና የወንጌል የመንግሥተ ሰማያት ገቢዎችም አግቢዎችም ቅዱሳን ሐዋርያት ናቸው፡፡ የሐዋርያትን ትምህርት፣ ክህነት፣ አረዳድ ወዘተ… ርስት አድርገን ስንቀበል ክርስቶስን አሁን ደቀ መዛሙርቱ ሁነን እየተቀበልን ነው።ሸማቴ. ፳፰፥፲፱ የደቀ መዝሙርነት ስንሰለቱን ያለ ተመትሮ ርስት አድርገን እንድንቀበል ጽኑዕ መሠረቱ ቅዱሳን ሐዋርያትን በምንጭ ተቀባይነታቸው መቀበል ነው:: "ተወከፋ አበዊነ ቅዱሳን እለ ዘእምቅድሜነ ዘከመ ርስት ቅዱስ" - (ከእኛ አስቀድመው የነበሩ አባቶቻችን ሐዋርያትን እንደ ተቀደሰ ርስት አድርጋችሁ ተቀበሉ፡፡) — ሃይማኖተ አበው ፹፬፥፪

በተዋሕዶ ክርስትና ሃይማኖት ያለን ሰዎች ሁሉ ሐዋርያዊ አደራችን እንደ ሐዋርያት የወንጌል አደራን ተቀብለናልና በአሚን፣ በትውክልት በመታመን፤ በአንክሮ፣ በለብዎ ሁነን ሐዋርያዊ ክርስቲያናዊነትን እንድንጠብቅ እንድናስጠብቅ፣ እንድንሰጥ እንድናሰጥ መሆን ነው፡፡ በአንዲት ሐዋርያዊት ጉባኤ ያለመለወጥ ያለ መናወጥ ከእምነት ለዋጮች በጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ተጠብቃ ከአንዲትነቷ ሳይጨመርባት በቅብብሎሻዊ ሰንስለት ለትውልድ የተሰጠች አንዲት ሐዋርያዊት እውነት በአንድ ኅብረት ሁነን የመዳን መሥመራችን ናትና በህላዌ ኅብረተ ክርስቲያን የክርስቶስን መስቀል ተሸክመን መኖር ነው::
ሐዋርያዊ ሰንሰለታችን የሚጠበቀው በዚህ አኗኗር ስለሆነ "ዛቲ ይእቲ ሃይማኖት ሐዋርያዊት አሐቲ ሃይማኖት ጽንዕት ወርትዕት ወርኀቅት እምጽርፈተ ዐላውያን" - (ከሐዋርያት ስትያያዝ የመጣች ሃይማኖት ይህች ናት! የጸናች የቀናች ከመናፍቃን የተለየች ሃይማኖት አንዲት ናት::) — ሃይማኖተ አበው ፹፬፥፳፪

በተቀደሰው ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ያገኘናት የጸናች የቀናች ኀልዮ ይህች ናትና፡፡

ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር የወንጌል ብሥራቱ በትክክል ከእኛ ዘመን አይደርስም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር የመዳን ትምህርት ለሰው ሁሉ ባልተዳረሰም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር የክርስትና ታሪክን የሚያውቅ አይኖርም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር የአባቶችን እምነት የሚያውቅ አይኖርም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር ፈቃደ ሥጋን ከፈቃደ ነፍስ ቢጣሉ የሚያስታርቅ አይኖርም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር ለልበ ምእመናን ከመፍገምገም ድጋፍ የሚሆን አዳኝ ጠጋኝ መልስ የሚሰጥ አይኖርም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር የምናኔን ጣዕም የሚያሳድር አይኖርም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር የሐዋርያነትን ጥብዐት የሚያሳይ አይኖርም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር የክርስትና ርቱዓዊ አረዳድ እስከ አሁን ባልዘለቀም ነበር! ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ባይኖር በምድር ያለች እግዚአብሔር መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ባልቀጠለችም ነበር፤ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የእግ ባይኖር እውነተኛው የመዳን በር ባልተገኘም ነበር፡፡ ያለ ቅብብሎሽም ክርስትና ምንም ነው:: ከኅብረታዊ ቅብብሎሽ የወጣ እና ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ግላዊ ሐሳብም ኑፋቄ፣ ጉሥዓተ ልብ፣ ሰዋዊ ፍልስፍና፣ የውሸት ዕውቀት ነውና። "ጢሞቴዎስ ሆይ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፡፡'" — ፩ ጢሞ. ፮፥፳
29.04.202519:52
በቅዳሴያችን “እግዚአብሔር ይስማዕከ ኵሎ ዘሰአልከ ወይትወከፍ መሥዋዕተከ ወቊርባነከ ከመ መሥዋዕተ መልከ ጼዴቅ ወአሮን ወዘካርያስ ካህናተ ቤተ ክርስቲያኑ ለበኵር"

(እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይስማህ፤ የቀደመችዋ ቤተ ክርስቲያን ካህናት የሚሆኑ የመልከ ጼዴቅንና የአሮንን የዘካርያስንም መሥዋዕት እንደተቀበለ መሥዋዕትህን ቊርባንህንም ይቀበልልህ)

የሚለው ንባብ የቤተ ክርስቲያን ህልውና ግእዛን ያላቸው ፍጥረታት ከተፈጠሩበት ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በመጨረሻ ከላይ እንደገለጥነው በክርስቶስ ደም ጸናች፡፡ አሁንም ይህ ጉባኤ ከሥላሴ ጋር ያለው ግንኙነት ዘወትር አይቋረጥም፡፡


ቤተ ክርስቲያን «ጉባኤ ናት» ሲባል ግን አንዳንዶች እንደሚሉት እንዲሁ የሰዎች ሁሉ ስብስብ ሳትሆን የምርጦች ስብስብ ናት፤ "የተጠሩ ብዙ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና" እንዲል (ማቴ. ፳፥፲፮)፡፡ እነዚህ ጥቂትና የተመረጡትም የልጅነት ሥልጣን የተሰጣቸው (ዮሐ. ፩፥፲፫)፣
እግዚአብሔርን በአንድነቱና በሦስትነቱ የሚያመልኩ፣ 
“ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ” (ማቴ.፲፮፥፲፮) በሚል ጽኑዕ መሠረት የታነፁ ናቸው እንጂ እንዲሁ በአንድ ቤት ውስጥ የተሰበሰቡ ሰዎች አይደሉም፡፡

ቤተ ክርስቲያን አካለ ክርስቶስና ሕያዊት ናት (ኤፌ. ፩፥፳፪-፳፫)፡፡
የክርስቶስ ሙሽራ (መኃ. ፭፥፩፣ ዮሐ. ፫፥፳፱፣ ራእ. ፳፩፥፱)፣ 
የእግዚአብሔር ሕያው ቤተ መቅደስ (ኤፌ. ፪፥፳፩)፣ የእውነት ዓምድና መሠረት (፩ኛ ጢሞ. ፫፥፲፭) ትባላለች፡፡

እነዚህ ስያሜዎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለወጥ የማይስማማው የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካል መሆኗን በግልጽ ያስረዳሉ፡፡ የክርስቶስ አካል ስለሆነች አትሳሳትም፣ አትለወጥም፡፡ ትምህርቷም ከአምላኳ ከእግዚአብሔር የተቀበለችውና በመንፈስ ቅዱስ የሚጠበቅ ስለሆነ ስሕተትና ነቅ አይገኝበትም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ትክክል ለመሆኗ ማስረጃችን መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ለመሆኑ ደግሞ ምስክሯ ቤተ ክርስቲያን ናት።

“ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ” (ኤፌ. ፫፥፲) የሚለው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ለዚህ ሁነኛ ማስረጃ ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ራሷ የሆነላት ቤተ ክርስቲያን 'አርጅታለችና ትታደስ'፣ 'ተሳስታለችና ትመለስ' አትባልም፡፡ እንዲህ ማለት ክርስቶስን ማረም፣ ክርስቶስን ማስተካከል ይሆናልና፡፡

አምላካችን ደግሞ መለወጥ የማይስማማው ፍጹም አምላክ መሆኑን በነቢዩ በሚልክያስ አድሮ “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” (ሚል. ፫፥፮) በማለት የነገረን ሲሆን፤

ቅዱስ ጳውሎስም “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘለዓለምም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ” — ዕብ. ፲፫፥፰-፱ ብሎ በየጊዜው የሚሻሻል አዲስ ትምህርት እንደሌላት በደንብ አስረግጦ ነግሮናል፡፡

ቤተክርስቲያን ተሳስታ አታውቅም። በጣም የሚገርመው ወደፊትም ለዘለዓለም አትሳሳትም። ስለዚህ «ተሳስቼ ነበር ይቅርታ» አትልም። ቤተክርስቲያን የምትባለው የቅዱሳን ሰማዕታት፣ የቅዱሳን መላእክት፣ የቅዱሳን መነኮሳት፣ በጠቅላላው የቅዱሳን ሰዎች፣ እና በዚህ ምድር ያሉ ምእመናን ኅብረት ናት። የኅብረቱ ራስ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህ ኅብረት የሚመራው በቃለ እግዚአብሔር ነው። በዶግማ፣ በቀኖና፣ በሥርዓት ነው። የቤተክርስቲያን ራሷ ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ ደግሞ አይሳሳትም።
                             
ለመዳን ወደእርሷ የተጠጉ ጳጳሳት፣ ምእመናን፣ ካህናት፣ መምህራን ወዘተ ግን ሊሳሳቱ ይችላሉ። በእርግጥ እያንዳንዱ አማኝም በአንደኛው የቤተክርስቲያን ትርጓሜ ቤተክርስቲያን ይባላል። ይኽውም የክርስቶስ ወገን ማለት ነው። ይህ ሊሳሳት ይችላል። ሲሳሳት ግን ራሱን ችሎ ተሳስቻለሁ ይበል እንጂ "ቤተክርስቲያን ነች የተሳሳተችው" ብሎ ማንም አያጭበርብር።

                           
እዚህ ጋር ማስተዋል ያለብን ነገር«ቤተክርስቲያን አትሳሳትም» የምንለው ግን ክርስቶስ ራሷ የሆነላትን ኅብረታዊቷን ቤተክርስቲያን መሀሆኑን ነው። እያንዳንዱ ምእመን ሲሳሳት «ቤተክርስቲያን ተሳሳተች» አይባልም። ልክ ሰሞኑን እንዳየነው ዓይነት ጳጳሱ ሲሳሳት «ቤተክርስቲያን ተሳሳተች» አይባልም። የተወሰኑ የሲኖዶስ አባላት ሲሳሳቱ (አያምጣውና ኧረ ሙሉ ሲኖዶሱ ራሱ ቢሳሳት እንኳን) ቤተክርስቲያን ተሳሳተች አይባልም። የተሳሳተ ሁሉ ራሱን ችሎ 'እኔ ተሳስቻለሁና ይቅርታ መጠየቅ አለብኝ/ልጠይቅ ይገባኛል' ይላል እንጂ በእኔ በደል ቤተክርስቲያን ይቅርታ ትጠይቃለች ብሎ በደሉን በኅብረታዊቷ ቤተክርስቲያን ለመደበቅ መጣር ፈጽሞ አይቻልም፤ ነዉርም ነው።


ለመሆኑ «የቤተክርስቲያን ኅብረታዊነት» ወይም ደግሞ «ቤተክርስቲያን ኅብረታዊት ናት» ስንል ምን እያልን ነው?
ከማን ጋር ነው የምትተባበረው?
ለምንስ ነው የምትተባበረው?

(ክፍል ፪ ይቀጥላል .... )
27.04.202516:41
በመንፈስ ጀምሮ በሥጋ መጨረስ ያለማስተዋል የመጨረሻ ጥጉ ነው።

ሊቅ ኢየሱስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በሙሉ ተረጎመላቸው። እነርሱ ለጊዜው ባያውቁትም እርሱ ግን ጠንቅቆ ያውቃቸው ነበርና። ዋስትናችን በእግዚአብሔር መታወቃችን ነው። የመንግሥተ ሰማያት ደስታም እግዚአብሔር እኛን ማወቁ ነው። እነርሱም እንግዳ ነው ሳይሉ፣ አናውቀውም በማለት ሳይገፉት፣ ለእምነታቸው አስቧልና ለሥጋው አሰቡለት። “ከእኛ ጋር እደር ፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል” ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ። ይህ ተማጽኖ ከዚያ ዘመን ይልቅ ዛሬ ያስፈልጋል። ማታው እየቀረበ፣ ቀኑ እየመሸ ነውና አብሮን ቢያድር መልካም ነው። የጨለማ ወዳጅ እርሱ ብቻ ነውና። የሚያስፈራንን የሚያስፈራው ስለ እኛ የሚዋጋው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

በቤታቸው አስገቡትና የአባወራው ወንበር ላይ አስቀመጡት፤ አባወራው መባረክ የሚገባውን ማዕድ እንዲባርክም ጋበዙት። እንግዳውን አከበሩት፤ ትልቅነታቸውን ለእርሱ ተዉለት። በቤታቸውም ሾሙት። እርሱም እንጀራውን ባርኮ ሲሰጣቸው ዓይኖቻቸው ተከፈቱ፤ ጠውልገው የነበሩ እንደገና ታደሱ። ደክሟቸው የነበሩ እንደገና ተነሡ። ለካ አብሯቸው ዝም ብሎ ሲሰማ የነበረው፣ ዝም ብሎ እንደ መንገደኛ ሲጓዝ የነበረው ያ ተሰቅሎ ሞቷል በቃ ያሉትና ተስፋ የቆረጡለት ጌታ ነው!
ያኔ ይሄንን የመሰለ የምሥራች ዜና ይዞ ማደር ነውር ነው ብለውም አሰቡ። ለአሥራ አንድ ኪሎ ሜትር የዛሉ እግሮች ድካምን ሳይፈሩ፣ በጨለማው ሳይሰቀቁ እንደገና ወደ ሐዋርያት የመነሳቱን ዜና ሊያበስሩ ሲሮጡ ተመለሱ። ቅድም በዝለት አሁን በብርታት፤ ቅድም በተስፋ መቍረጥ አሁን በተስፋ ተመለሱ። ክርስቶስን ሲያገኙ እንደ እነርሱ አዝነው የነበሩት ደቀ መዛሙርት ትዝ አሏቸው። በበረቱበት ምሥጢር ሊያበረቱአቸው ተመለሱ፤ ቀኑ ሳይመሽ ከጌታቸው ጋር ታረቁ። «በቍጣችሁ ፀሐይ አይጥለቅ» ያለው ትርጓሜ «በተስፋ መቍረጣችሁም ፀሐይ አይጥለቅ፥ ነገም ሌላ ቀን ነው» ይላልና በዋሉበት ስሜት እንዳያድሩ አዳምን በምሽት የፈለገ ጌታ ለእነርሱም ሲመሽ ደረሰላቸው።

ዛሬም ሰው ያሸነፈ መስሏችሁ ያዘናችሁ፣ የውግረት ድንጋይ ቀና አላደርግ ብሎሏችሁ በካብ ውስጥ የምታጣጥሩ ሁሉ ክርስቶስ ተነሥቷል። ወደ ኤማሁስ በዝለት የሄዳችሁ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ኢየሩሳሌም የገዳዮች ሳይሆን የምስክሮች ቤት ናት። ወደ ፀሐይ መጥለቂያ ጉዞ የጀመራችሁ፣ እሱ ወድዶና ፈቅዶ በሰጣችሁ አፍ እየተናገራችሁ እንኳ «አይ እኔንስ እግዚአብሔር ትቶኛል» የምትሉ ይህች ጀንበር ሳትጠልቅ ተመለሱ፤ ፈጽሞ ተስፋ እንዳትቆርጡ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ሆኖ በእውነት ተነሥቷል!


በድጋሚ መልካም የዳግም ትንሣኤ በዓል ለሁላችሁም ይሁን!
25.04.202511:42
« ... እኔም አላውቀውም።»

በመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ላይ ነቢዩ ዕዝራ እና አንድ ኢይሩማኤል የተባለ መልአክ ሲነጋገሩ እናገኛለን። መላእክት ከሰው ልጆች ጋር በብሉይም ይሁን በሐዲስ ኪዳን በተለያየ አጋጣሚና ለተለያየ ምክንያት ሲነጋገሩ ስለምናይ ይሄ ብርቅ አይደለም። የነቢዩ ዕዝራንና የመልአኩ ኢይሩማኤልን
ንግግር ግን ለየት የሚያደርገው ነቢዩ ዕዝራ ሱባዔ ገብቶ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት ስለ መጨረሻው ዘመን በጣም ብዙ ነገር ሲጠይቅ ቆይቶ በኋላ ግን ድንገት በንግግራቸው መሐል የሚሞትበትን ቀን ይነግረው ዘንድ መልአኩን ጠየቀው፡፡ መልአኩም የሚያውቀውን ነገር በእዝራ አቅም ልክ (ስለ መጨረሻው ዘመን) መልሶለት ሲያበቃ የማያውቀውን « ... እኔም አላውቀውም።» ብሎ መልሶለታል፡፡

"ስለጠየቅከኝ ምልክትስ ከብዙ በጥቂቱ መንገር ይቻለኛል። ስለሕይወትህ ግን እነግርህ ዘንድ አልተላክሁም፤ እኔም አላውቀውም።" ብሏል — (መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል.፪፥፶፩)።
ለዚህ ምክንያቱ የመላእክት ዕውቀት የጸጋ (በእግዚአብሔር ቸርነት ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው) ስለሆነ ሁሉን አያውቁምና። ሁሉን የሚያውቅ አንድ እግዚአብሔርብቻ ነው። እዚህ ጋር ልብ ልንኔው የሚገባው ነገር መልአኩ ኢይሩማኤል ለነቢዩ ዕዝራ የሚያውቁትን እየተናገሩ የማያውቁትን ጉዳይ አላውቀውም ማለት መልአካዊ ጸባይ መሆኑን በዛው እያስተማረው መሆኑንም ነው፡፡

አንድ ሰው ከመምህር ያልተማረውን፣ ከመጻሕፍት ያላነበበውን፣ ከፈጣሪ ያልተገለጸለትን እንዲሁ በግምት ልቡ የወለደውን ሲናገር «ጉሥዐተ ልብ» ይባላል። «ጉሥዐተ ልብ» ማለት የሰው ልጅ በራሱ ምናብ የፈጠረውን ለሌላው እውነት እንደሆነ አድርጎ መናገር ነው። "ወኢትፍጥሩ ለክሙ ፈጠራ" እንዲል ኦሪት ዘሌዋውያን ፲፱፥፳፰ (ከመጽሐፍ ሳታገኙ፥ ከመምህራን ሳትማሩ፥ ልብ ወለድ አታስተምሩ)። ክርስቲያን የሚያውቀውን ይናገራል እንጂ በግምት በጭራሽ አይናገርም፡፡ "የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን” እንዲል ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ምዕራፍ ፫፥፲፩ ላይ።

እያንዳንዱ ነገር ሚዛን አለው በዚያ ሚዛንነት ይለካል፡፡ ከዚያ ውጭ ማንም ምንም ቢል ማስረጃ ይጠየቃል(ሊቀ ዻዻስም ቢሆን!)፡፡
ደግሞ እንዲሁ በደፈናው አንድን ነገር እኛ ስላልለመድነውና ስላላወቅነው “በቃ ስሕተት ነው!” አይባልም:: የእኛ ልምድና ዕውቀት ያልደረሰባቸው እውነታዎች እልፍ አእላፋት ናቸው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው የሚናገረውን ነገር ልክነት (በተለይ ደግሞ ሃይማኖት ነክ ነገር እያስተማረ ከሆነ) በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በመምህራን፣ በቅዱስ ትውፊት፣ በእግዚአብሔር ቃል ማመሳከር አለበት፡፡ ማስረጃ ሳያቀርቡ እንደው ከመሬት ተነስቶ «ሳይሆን አይቀርም፤ ይሆን ይሆናል» እያሉ መናገር አይገባም፡፡ "ኢትንብቦ ለመኑሂ በዘኢለበውከ ወኢያእመርከ" - (ያልተረዳኸውንና ያላወቅኸውን ነገር ፈጽሞ አታስተምር)፤ ከመ ኢትኀፈር በርእስከ - (ሳታውቅ ሳትረዳ በተናገርከው ነገር ኋላ እንዳታፍር) እንዲል (ማር ይስሐቅ ፩፥፮)። እንዳናፍር ያለ መረጃና ያለ ማስረጃ አንናገር፡፡ አለማወቃችንንም ደግሞ ጠንቅን ማወቅ አለብን፡፡ "እመን ኢያእምሮተከ ኦ መዋቲ" - (አንተ ሟች ሰው ሆይ አለማወቅህን እወቅ!) ተብሎ እንደተጻፈ አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን ፴፪ ላይ።
እኛ ሰዎች ስንባል ዕውቀታችን ሁሉ የጸጋ (ከራሳችን ያልሆነ ግን እግዚአብሔር በቸርነቱ እንደየ መጠናችንና አቅማችን የሰጠን) ስለሆነ ወሰን፣ ገደብ አለበት። መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ "ራስን ካለማወቅ በታች የሚገኝ ድንቁርና የለም። አላዋቂነትን አለማወቅ የድንቁርና ፍጻሜ ነው" ይላሉ፡፡ ማንኛውንም ጉዳይ አንተ ስላላወቅከውና ስላላነበብከው የለም ወይም አልተጻፈም ማለትም የለብህም። «አይ ይሄንንስ አላውቀውም እኔ የሰማሁትና ያነበብኩት እንዲህ የሚል ነው ...» ብለህ ተናገር እንጂ ... ያልደረሱበትን መጠየቅና ማጥናት ሲገባ «በጭራሽ እንዲህ ብሎ ነገር የለም!» ብሎ በድፍኑ መገገም ከበድ ያለ ድንቁርናን እንጂ ሊቅነትን አያሳይም። የማናውቀውን ጉዳይ ለእግዚአብሔር እንተወው። "እንስ ኢይክል እትናገር ዕበዮ ወኢፈጽሞ ውዳሴሁ አላ አኀድግ ዘንተ መካነ ለእግዚአብሔር ዘለሊሁ የእምሮ" -
( ... ምንም ለአነጋገር ቢመች እኔም ገናንነቱን ልናገር አልችልም፤ ምስጋናውንም ፈጽሜ ልናገር አልችልም፤ ይህን [ሁሉን] ለሚያውቀው ለእርሱ ለእግዚአብሔር እተዋለሁ እንጂ ... )

እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በሃይማኖተ አበው ፶፮፥፲፮
Көрсөтүлдү 1 - 16 ичинде 16
Көбүрөөк функцияларды ачуу үчүн кириңиз.