Nairaland Pulse | News

Анатолий Шарий

Реальний Київ | Украина

Мир сегодня с "Юрий Подоляка"

Труха⚡️Україна

Николаевский Ванёк

Инсайдер UA

Реальна Війна | Україна | Новини

Лачен пише

Nairaland Pulse | News

Анатолий Шарий

Реальний Київ | Украина

Мир сегодня с "Юрий Подоляка"

Труха⚡️Україна

Николаевский Ванёк

Инсайдер UA

Реальна Війна | Україна | Новини

Лачен пише

Nairaland Pulse | News

Анатолий Шарий

Реальний Київ | Украина

የ-ትብለጥ ግራኝ ሳቢር
TGlist рейтинг
0
0
ТипАчык
Текшерүү
ТекшерилбегенИшенимдүүлүк
ИшенимсизОрду
ТилиБашка
Канал түзүлгөн датаNov 11, 2022
TGlistке кошулган дата
Apr 27, 2025Тиркелген топ
የ-ትብለጥ ግራኝ ሳቢር chat
3
Рекорддор
17.05.202523:59
305Катталгандар24.04.202523:59
0Цитация индекси17.05.202523:59
921 посттун көрүүлөрү17.05.202512:33
01 жарнама посттун көрүүлөрү15.05.202504:33
11.96%ER15.05.202513:39
31.19%ERRӨнүгүү
Катталуучулар
Citation индекси
Бир посттун көрүүсү
Жарнамалык посттун көрүүсү
ER
ERR
17.05.202505:12
ክፍል 1
"እሺ ተከሳሽ ክሱ ደርሶዎታል?"
(ለምንድነው አንቱ እያለች የምትጠራኝ?)
"አዎ ደርሶኛል"
"የስድስቱንም ሰዎች ህይወት ማጥፋቶን ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል?"
"በሚገባ"
በአይኗ ግልባጭ የምታየኝ ዳኛ ድምፅ ጎርናና ነው (ደግሞ ሲያስጠላባት)
"በምን መንገድ ነበር ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረጉት?"
"በእሳት"
"በእሳት ሲሉ?"
(እዛው ሙሉ ፍርድ ቤቱን አንድጄ እንዳሳያት ነው?)
.
.
.
ድሮ......ብዙ ትውስታዎች....
"አንተ ምን ያንቀጠቅጥሀል? የምታውቀው ሰው አይደል የተሰበሰበው?"
.
.
.
"አንተ!"
.
.
.
"ደደብ! አንተን ለማስተማር መስሎኝ የሰው ፊት የሚገርፈኝ?"
.
.
.
"አንተማ እንደእናትህ ልክስክስ ነው የምትሆነው!"
ወንዶችን አልወድም! በተለይ አፋቸው መጠጥ መጠጥ የሚሸቱትን! በተለይ ወርቅ ጥርስ ያላቸውን! በተለይ መሀሉ ላይ ፅሁፍ ያለው ኮፊያ የሚያደርጉትን! ሁሉም እሱን ይመስሉኛል! ራሱን አክሊሉን!
ሴቶችን አልወድም! በተለይ መሀል ጣታቸው የተሰበሩትን፣ በተለይ ጎርናና ድምፅ ያላቸውን፣ በተለይ ፀጉራቸውን ሁለት ቦታ የሚሰሩትን! ሁሉም ሮማንን ይመስሉኛል፡፡
ትምህርህትቤት መሔድ አልወድም፡፡ የዜግነት ክብር አልወድም፡፡ አስተማሪ አልወድም፡፡ ከጥቁር ሰሌዳ እየበነኑ የሚመጡ የጠመኔ ፍርፋሪዎችን አልወድም፡፡ ሁሉም ያበሽቁኛል፡፡
ዛሬ......
"አዎ ቤት ውስጥ ተቃቅፈው እንደተኙ በእሳት አቃጠልኳቸው!"
በድምፄ ውስጥ ለሰማችው ኩራት የተሰማትን ከአንዱ መመደብ የከበዳት ዳኛ ከስራዋ ይልቅ ሰው መሆኗ በልጦባት መሰለኝ ጥላቻዋ ፊቷ ላይ ታውቆባት ነበር፡፡
ፊቷ ደም እንደለበሰ ለቀጣይ ቀጠሮ ቀን አስቀመጠች፡፡ እጆቼን ወደኋላ ጠፍረው ሲወስዱኝ ወደ ልጅነቴ መለሱኝ፡፡
"አንተ!" ሮማን ት/ቤት ልታስመዘግበኝ ስትሄድ ካልሆነ በስሜ ጠርታኝ አታውቅም፡፡ ድሮ በስሜ የሚጠሩኝ ሁለት ሰዎች ነበሩ ትዕግስት እና ሳሚ፡፡
ትዕግስት የክፍላችን ቆንጆ ልጅ፡፡ ለዛውም አቆላምጣ "አቤልዬ" ትለኝ ነበር፡፡
ሳሚ እንደኔ አስተማሪ እና ትምህርት የሚጠላ ከኋላዬ ይቀመጥ የነበረ ልጅ እሱም "እ አቤል" ይለኝ ነበር፡፡
"አቤት" አባባሌ ዘወትር የማሻሸውን ቀኝ እጄን በቀስታ ወደ ሲዖል እየጎተተ የሚወስድ አምላክ ያለ እንጂ እናቴ የምትጠራኝ አልመስልም ነበር፡፡
"ና ሱቅ ሂድና ሞዴስ ግዛልኝ" ለምን እንደሆነ አላውቅም ሞዴስ መግዛት ያሳፍረኝ ነበር፡፡ በጣም በጣም ያሳፍረኝ ነበር፡፡
ልገዛ በወጣሁበት ግን በዛው ቀረሁ....
የት?

15.05.202504:28
ከረዥም ውሎዬ ለመዳን በድካም የዛለ ጎኔን አልጋዬ ላይ አሳርፌዋለሁ፡፡ በዛ መሀል ፊቴን ለአንዴ አዙሬ አየሁ....
ዕቃዎቼ በየቦታቸው ናቸው፡፡ እንደነበሩት::
በድካም ብር ያለ ዓይኔን ወደ ክፍሌ አንከራተትኩ፡፡
ቀድሜ አየሁ.....
ያ ከንቱ ሰለሞን የ "አትወደኝም?" ጥያቄዬን ሽሽት ከአራት ዓመት በፊት ገዝቶ የሰጠኝ አሻንጉሊት ከጫማ መደርደሪያዬ ላይ ቁጭ ብላ ታየኛለች (ከነ መልኳ ስታናድደኝ ጌታ ምስክሬ ነው)
ዞርኩ....
የማብሰል አቅሜን ያዳከመ ውሎዬን ለማብሸቅ የገዛሁትን የውጪ ምግብ የበላሁበት ካርቶን ከወንበሬ ላይ፡፡
ቀና አልኩ....
ቡኒ እና ወርቃማ ቀለም ያለው መጋረጃ ላይ በየመሀሉ ቁጭ ቁጭ ያሉ ሁሌም ያዘኑ የሚመስሉኝ አርቴፊሻል ቢራቢሮዎች፡፡
በቀስታ ተነስቼ የአስናቀች ወርቁን ሙዚቃ ከፈትኩ፡፡
"እያቅበጠበጠኝ ቅጡን እያጣሁት
ወጡ ተቀምጦ ደረቁን በላሁት"
አሰብኩ፡፡በምን እንደሆነ ባላውቅም በሸቅኩ፡፡ መቼስ የመታኝን ስስ ዝናብ አስቦ ከመብሸቅ ምክንያቱን መርሳቱ ይሻላል፡፡ በሽቄም አልቀረሁ.... ስበሽቅ አዲሱ ፍቅሬ ትዝ አለኝ፡፡ ካላንዴም ያላየሁት፡፡ ለሁሌም የዓይኑን ውበት ብቻ የማወራለት፡፡ ሁሌም በፀጥታዎች መሀል የሚጥለኝን እሱን አሰብኩ፡፡ የመወደድ ልክ አቅሉን ያሳተው ሲመስለኝ ስለ ሽንፈቴ ሳይሆን ስለ ድብቅነቱ በገንኩ፡፡ ደግሞ እወድሻለሁ ይለኛል የውሸቱን...
"ላንተ ይብላኝ እንጂ ለወዳጅ አባይ
እኔማ የዕድሌን አጣዋለሁ ወይ?"
አይኔን ጨፍኜ ሙዚቃውን ሰማሁ....
"ምን አንገበገበኝ እንደ ጣት ቁስል
አንተ ብትቀር ሌላ አጣ ይመስል"
ደግሜ ብሽቅ አልኩ....
በእሱ ምክንያት ያልተካሰስኩት አምላክ፣ ያልተናነቅኩት ነፍስ፣ ያልጠላሁት ሀገር፣ ያልተማረርኩበት የፍቅር ዘፈን የለኝም፡፡ምንም አድርጎኝ አይደለም፡፡ ከነፍሱ አርቆኝ፡፡ ለከንፈሩ አድርሶ ለልቡ ገፍቶኝ....
"አንተ ልበ ደንቆሮ አንተ ልበ ድንጋይ
ሰው ረግጦ ሔዶ ሰው ይገኛል ወይ?"
ቲሽ!

03.05.202504:48
ህፃናት ገና ት/ቤት ገብተው መማር ሲጀምሩ የመጀመሪያው ትምህርት ነጠብጣቦችን አገጣጥሞ ትክክለኛውን ፊደል ከዛ ከፍ ሲል ደግሞ ቃላትን መስራት ነው (ትሬስ ማድረግ)
እኔም እንደዛ አንዳንድ ጊዜ "ሀ" ብዬ - በህይወቴ ወደ ልጅነት ተመልሼ በእርምጃዎቼ መሀል ያሉትን ክፍተቶች ሞልቼ ጥርት ያለውን ምስሌን ልፈጥር ያምረኛል፡፡ በዛ መጠን ቀላል ቢሆንልኝ ኖሮ፡፡
ከእርምጃዎቼ መሀል....ላጠራ ያልቻልኩትን ያውቁልኝ ዘንድ እሄድ ነበር፡፡
"እሺ ትብለጥ እንዴት ነሽ?"
"ደህና ነኝ ዶክተር"
"ቆየሽ ከመጣሽ እንዴ ብዙ ቆየሽ?"
"አይ ብዙ አይደለም"
ስጋዬ አሁን ላይ ቢሆንም ሀሳቤ ትናንት ላይ ነበር፡፡ ማክሰኞ እና አርብ ከት/ቤት መልስ አባቴ ሰፈሮችን እያስጠናኝ፣ በየመሀሉ ፍዝዝ ስል መሪ ባልያዘ እጁ እየኮረኮረ እያሳቀኝ "ደስ ብሎሻል?" እያለ በተደጋጋሚ የሚጠይቀኝ ዶክተር ጋር ይወስደኝ ነበር፡፡
"ትብለጥዬ"
"......"(ሁሌም በማላውቃቸው ሰዎች ስጠራ አቤት አልልም)
"ይኼ ስንት ቁጥር ነው?"
"አምስት"
"ጎበዝ" (አይደንቀኝም ነበር)
(በአስር እና በሀያ ስምንት ዕድሜ ያለ የእኔ አንድ ዓይነት መሆን)
ለእኔ ቢሆንልኝ ኖሮ መደነቅ እነ መምህር "ደ" የክፍል ጓደኞቼን እንደሚስሟቸው ቢስሙኝ፣ እኔን ሲያዩ ቢስቁልኝ፣ በመኖሬ ባይማረሩ እንጂ እዚህ ዶክተር ጋር መመላለስ አልነበረም፡፡ የእሱ ፈገግታ ለደቂቃዎች ለማገኘው ሁኔታ እንጂ ወጥቼ ስለምጋፈጠው የመምህራኖቼ ሁኔታ ዋስትና አይሆነኝም ነበር፡፡ ለዛ ግን ጎበዝ ተማሪ ሆኜ ቀብድ መክፈል ነበረብኝ!!!
የሚወዷት ዓይነት ተማሪ አልነበርኩም፡፡ ቤት ደረጃ ላይ ቁጭ ብዬ ከመተከዝ ለመትረፍ ት/ቤት ልውደድ እንጂ ትምህርት አልወድም ነበር፡፡ መምህራኖቼም የዕለቱን ዕቅዳቸውን አሰርተው ከመውጣት እና ላልሰራሁት ከመውቀስ እና ከመምታት ውጪ አስበውኝ አያውቁም ነበር፡፡ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት ሳመጣ ትናንቴን እያጣቀሱ "ያኔ ዋንጫ ተሸላሚ እንዳልነበርሽ ዛሬ እንዲህ የማትረቢ ትሆኚ?" ከማለት ውጪ ምንም ያሰቡት ነገር አልነበራቸውም፡፡
"መቼ ነው ሰው የምትሆኚው?" የሚለውም ጥያቄያቸው ብቻዬን እጅ አውጥቼ ባልመረጡኝ ሰዓት ከሚሰማኝ "መቼ ነው የምወደድ ሰው የምሆነው?" ከሚለው ጥያቄዬ በላይ ዋጋ አልነበረውም
መልካምነት ላይ ከመድረስ በፊት መልካምም መጥፎም አለመሆን ይቻላል አይደል? እኔ ግን መለስ ብዬ ሳስብ ስለምጠላው ስሜም መልኬም ተጠያቂዎቹ መምህራኖቼ ነበሩ፡፡
"ትብለጥ...ምን አንቺ ትብለጥ ነሽ ትነስ ነሽ እንጂ" (ልጅነት ሞኙ አሜን ብሎ ይቀበላል)
"ግራኝ...አይሻልሽም ቀኝ" እያሉ በቃረሙት ሳቅ ለብዙ ዓመታት ከስሜ አፋቱኝ፡፡
"ነጫጩባ" እያሉ ለሰደቡት መልኬ ብዙ ዓመታትን ሰው ከማየት አሸማቀውኝ ነበር፡፡
ዛሬ ላይ ብድግ ብዬ ለራሴ ከንፈር እንዳልመጥ የሚያደርገኝ ምክንያት ደህና መሆኔ ነው፡ እናም እኔን የመታኝ ሁሉ ልጆቼን አለመንካቱ፡፡
የመጣልኝን እንዳልሳደብ፣ እንደመጣልኝ እንዳልረግጣቸው፣ እንደተሰማኝ ከክፍል ውጡልኝ የማልልበት በቂ ምክንያቴ ሰው መሆናቸው ነው፡፡ሲያጠፉም ሰዎች ናቸው፣ ዜሮም ሲያመጡ ሰዎች ናቸው፣ ሲደፍኑም ሰዎች ናቸው፣ ሲረሱም ሰዎች ናቸው፣ ሲያስታውሱም እንደዛው፡፡
ትንሽ ለሰሩት ስህተት ሀገር ያጠፉ ይመስል ይኼ ሁሉ ውርጅብኝ ማውረድ፣ የቤት ስራ አልሰራህም አልሰራሽም ብሎ በተማሪ ፊት ማሸማቀቅ፣ መግረፍ ቀርቶ መደብደብ፣ የኑሮን መከራ በልጆች መወጣት ክፉነት ነው፡፡
እንደ መምህርም፣ እንደወላጅም ዛሬ በምናወጣው አንድ ቃል እና ጉልበት የሰውን ህይወት ልናበላሽ እንደምንችል ልናውቅ ይገባናል፡፡
ምን ባደረጉ ይኼን ሁሉ ይቀበላሉ? ቤት የሚያሳልፉትን ማን አወቀላቸው? ሁሉም እኮ ተመችቷቸው አይኖሩም! ቢያንስ እንስማቸው፡፡ እንዲህ ስለነበር ነው እያሉ ስህተታችንን እያስተባበሉ የሚኖሩ ልጆች አንፍጠር፡፡

24.04.202512:01
"አንቺ ግን መቼ ነው ሰው የምትሆኚው?" የሚል የመምህራኖቼ ጥያቄ ውስጤ ከነበረው "መቼ ነው የምወደድ ሰው የምሆነው?" ከሚለው ጥያቄ በላይ ዋጋ አልነበረውም፡፡
08.05.202503:16
Көбүрөөк функцияларды ачуу үчүн кириңиз.