Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ avatar

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡
TGlist рейтинг
0
0
ТипАчык
Текшерүү
Текшерилбеген
Ишенимдүүлүк
Ишенимсиз
Орду
ТилиБашка
Канал түзүлгөн датаSep 24, 2017
TGlistке кошулган дата
Dec 25, 2024
Тиркелген топ

"ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ" тобундагы акыркы жазуулар

ተወዳጆች ''በእንተ ስማ ለማርያም'' ይህቺን ጎደሎ ሙሉልን

እስከ አሁን ወደ አካውንቱ 40,000 ብር ገብቶልናል ከታሰበው 52,000 ብር ውስጥ 12,000 ይቀራል። በጎ አድራጊዎች "በእንተ ስማ ለማርያም" ብለን ፊታችሁ ቆመናልና  በተጠቀሰው አካውንት እንደ አቅማችሁ ተሳተፉ...

የወልድያ ከተማ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት በ‍ቶች አንድነት ጉባኤ
2071111 0880 89 013
ዓባይ ባንክ

ለተጨማሪ መረጃ  ➛ +251 92195 8461
                         ➛ +251 95 327 5024


ገቢ ያደረጋችሁበትን ለመላክ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ @natansolo ይጠቀሙ
ተወዳጆች ሆይ! ማለፍ መለወጥ በሌለባት በመንግሥተ ሰማያት ጸጋንና ክብርን እናገኝ ዘንድ በምግባር በትሩፋት እናጊጥ፡፡ በዚህ ዓለም የሚኖረን ውበትና ጌጥ ድንገት ታይቶ የሚጠፋ ነው፡፡ የማይቻል ቢኾንም ምንም በሽታ፣ ኀዘን፣ ብስጭት፣ ይህም የመሳሰለ ኹሉ ባያገኘን እንኳን የዚህ ዓለም ውበትና ጌጥ ሃያ ዓመት ነው፡፡ በወዲያኛው ዓለም የሚሰጠው የሚገኘው ክብር ግን በዝቶ ሲሰጥ ይኖራል እንጂ መቼም ቢኾን መች አያልፍም፡፡ አይለወጥም፡፡ እርጅና የለምና ቆዳው አይጨማደድም፡፡ ደዌ ሥጋ ደዌ ነፍስ አያገኘውም፡፡ ኀዘን አያወይበውም፡፡ በዚያ የምናገኘው ክብር፣ ውበት፣ ጌጥ ከዚህ ኹሉ የተለየ ነው፡፡ በዚህ ዓለም የምናገኘው ክብርና ውበት ግን የሚጠፋው ገና ከመምጣቱ ነው፡፡ ቢመጣ እንኳን አድናቂዎቹ ብዙ አይደሉም፡፡ ትሩፋትን ጌጥ ያደረጉ ሰዎች አያደንቁትም፡፡ የሚያደንቁት አመንዝሮች ናቸው፡፡

ስለዚህ ከዚህ ዓለም ከኾነው ክብር ልንለይ ይገባናል፡፡ መንግሥተ ሰማያትን እንወርስ ዘንድ ልንፈልገው የሚገባን ትሩፋትን ነው፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
የፍቅር ሥራ ይህች ናት

ባልንጀራውን የሚረዳውን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ይረዳዋል፡፡
ለወንድሙ የሚነቀፍበትን ስም የሚያወጣውን ፈታሒ በርትዕ እግዚአብሔር እንዲሰደብ ያደርገዋል፡፡ ክፉ ስለ ሠራ ወንድሙን በቤቱ ለብቻው ሆኖ የሚመክረው ሰው ግን በምክሩ ዐዋቂ ይሆናል፡፡ ወንድሙን በዐደባባይ የነቀፈ ግን ኀዘን ያጸናበታል፡፡ ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡ 

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች፡፡ ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡ በጎ ነገር ያደርግልኛል ብሎ በጎ የሚሠራ ኋላ ፈጥኖ ይተዋል፡፡

(ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ - በዲ/ን ሞገስ)
የመረሻውን ግብ እያሰቡ ልጆችን ማሳደግ ማለት እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብ የዋሃን፣ ክፉውን ሳይኾን በጎውን ለማወቅ ትጉሃን፣ የዲያብሎስን ሽንገላ ለማስተዋል ጠቢባን፣ የቅዱሳንን ፋና ለመከተል የቃሉን ወተት የሚጠጡ ንጹሐን አድርጎ ማሳደግ ነው።

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን እኛ አየናቸውም አላየናቸውም በሕሊናቸው ጓዳ በልቡናቸው ሰሌዳ ላይ መንግሥተ እግዚአብሔርን መቅረፅ ነው።

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ስንጠራቸው አቤት ስናዛቸው ወዴት የሚሉንን ሳይኾን ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ እምነትን፣ የውሃትን ራስን መግዛትን፥ በአጭር ቃል የመንፈስ ፍሬዎችን ገንዘብ ያደረጉ ልጆችን ማሳደግ ነው። (ገላ.5፥22-24)

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን የገዛ ክብራቸውን እንዲያውቁና በዚያ መሠረት እንዲያድጉ - ይኸውም የእግዚእብሔር ልጆች ክርስቶስን የሚመስሉ በእግዚእብሔር አርአያና አምሳል ቅዱሳን እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው። (ዘፍ. 1፥26)

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን የእኛ ንብረት እንዲኾኑ ሳይኾን የእዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ው። መጥምቁ ዮሐንስ እስራኤላውያንን ለክርስቶስ ያዘጋጃቸው እንደ ነበረ፥ እኛም በዚያ መንገድ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ልጆቸ እንዲኾኑ ማዘጋጀት ነው።

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት የልጆቻችንን መጥፎ ጠባይ ከማራቅና እንዲታዙን ከማድረግ በላይ፡ እግዚአብሔርን በፍጹም ኃይላቸው እንዲወድዱ ማድረግ ነው። ቅዱሳንን እንዲያፈቅሩ በቃል ኪዳናቸው ታምነው እርሱን እንዲመስሉ ማድረግ ነው።

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት እስተዳደግ ማለት ልጆቻችን እንዳይጣሉ ስናደርጋቸው መንፈሳዊ ሕይወትና የቅድስና መንገድ ምን እንደ ኾነ በሚያሳይ መልኩ ማሳደግ ነው። መጀመሪያ ላይ ባነሣሁት ምሳሌ ላይ ለምሳሌ "ዮሐንስ! መጫወቻውን አቀብለኝ" ብለውና እያንገራገረም ቢኾን ቢሰጠኝ፥ እኔም ቀጥዬ "መጫወቻውን እዚህ አስቀምጠዋለሁ፤ ከእራት በኋላም እንዴት በየተራ እንደምትጫወቱ ስትነግሩኝ ልሰጣችሁ እችላለሁ" ብለው ለጊዜው ኹለቱም መፍትሔ ባያመጡም እንደ አሁኑ እንዳልወስድባቸው ለሌላ ጊዜ እንዴት መጫወት እንዳለባቸው ከማሰብ ዝም አሉም።

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን ከላይ ያነሣናቸውን ምግባራት በአንድ ቀን ሊይዙልን እንደማይችሉ ዐውቆ እነዚህን ቀሰ በቀስ እስኪይዟቸው ድረስ ሊማሩ የሚችሉበትን ኸኔታ እያመቻቸን ጊዜ ልንሰጣቸው እንደሚገባን ተረድቶ መታተር ነው። ልጅ ማሳደግ የአጭር ጊዜ ሳይኾን የረጅም ጊዜ ኃላፊነት ነውና። ልጆቻችን በኹለት ሳምንት ወይም በአንድ ወር እንዲያውቁትና እንዲይዙት የምንፈልገው አንድ ነገር አልያዙም ማለት ሙከራችን ስለማይሠራ ነው ማለት ላይኾን ይችላል፤ ጊዜ የሚፈልግ ይኾናል እንጂ። ልጅ ማሳደግ ትዕግሥት ይጠይቃል። ልጆቻችን እንዲይዙት የምንፈልገው ነገር ለመዝ እየጣሩ እንደ ኾነ ርግጠኛ እስከ ኾንን ድረስ ዕድል በመስጠት ልንታገሣቸው ይገባናል።"

(#ትንሿ_ቤተ_ክርስቲያን ገጽ 444-445
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ )
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ አዲስ አበባ ገቡ!

ወደ ሀገር እንዲገቡ ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገቡ

ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ የገቡት አባቶች

* ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣
* ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ እና
* ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ሲሆኑ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዓን አባቶች ተገኝተው አቀባበል እንዳደረጉላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሚዲያ ዘግበዋል።
''በእንተ ስማ ለማርያም''

እስከ አሁን ወደ አካውንቱ 40,000 ብር ገብቶልናል ከታሰበው 52,000 ብር ውስጥ 12,000 ይቀራል። በጎ አድራጊዎች "በእንተ ስማ ለማርያም" ብለን ፊታችሁ ቆመናልና  በተጠቀሰው አካውንት እንደ አቅማችሁ ተሳተፉ...

የወልድያ ከተማ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት በ‍ቶች አንድነት ጉባኤ
2071111 0880 89 013
ዓባይ ባንክ

ለተጨማሪ መረጃ  ➛ +251 92195 8461
                         ➛ +251 95 327 5024


ገቢ ያደረጋችሁበትን ለመላክ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ @natansolo ይጠቀሙ
በመጨረሻም
የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ አፈጻጸማችን በመገምገም ለቀጣዩ ጊዜ የሥራ አቅጣጫን የሚያስቀምጠው የርክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖናዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተጀመረ መሆኑን ለኦርቶዶክሳውያን ሕዝበ ክርስቲያን  እናበስራለን፤

እግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

          አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣
ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
             አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

(ምንጭ EOTC)
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያስተላለፉት  መልእክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

* ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
* ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
*ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!!

እንደዚሁም በዚህ ቀኖናዊና ዓመታዊ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ የተገኛችሁ በሙሉ፤ ጸጋንና ሐዋርያነትን ያጐናጸፈን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ትንሣኤውን በሰላም አክብረን ይህንን ዓመታዊውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለማካሄድ ስለ ሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ የጉባኤው አባላት የሆናችሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም እንኳን ለርክበ ካህናት ጉባኤ አደረሳችሁ! እንኳንም በሰላም መጣችሁ!

“ረከብነ ጸጋ ወተሰየምነ ሐዋርያተ ከመ ናስምዖሙ ለኣሕዛብ ወይእመኑ በስሙ፡- ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን” (ሮሜ.፩÷፭)፤ይህ ሐዋርያዊ አስተምህሮ የኛን ተልእኮና ተልእኮው ያስፈለገበትን ምክንያት አጉልቶ ያሳያል፤ የተቀበልነው ስጦታም ምን ያህል ታላቅ እንደ ሆነ ምንባቡ ያስረዳል፤ ሐዋርያው በዚህ መልእክት የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ ዋና ግብ ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ማድረግ ነው በማለት ያስተምረናል፤ እውነት ነው ድሮውኑም ቢሆን ለእግዚአብሔር መታዘዝ አቅቶን ነው የወደቅነው፤ ዛሬም የምንነሣው ከእምነት የተነሣ መታዘዝን ገንዘብ ስናደርግ ነው፤ ከሁሉ በፊት እምነት ይቀድማል፤ ከሱ በኋላ ደግሞ ለእምነቱ በሙሉ ልብ መታዘዝ ይከተላል፤ ይህ ሲሆን መዳንና ትንሣኤ ይገኛል፤

ዓለም በእግዚአብሔር እየተደረገላት ያለ ጥሪ ይኸው የመታዘዝ ጥሪ ነው፤

ይህንን መለኮታዊ ጥሪ ለዓለም የማድረስ ኃላፊነትም ለኛ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተሰጠ እንደሆነ ሐዋርያው አስገንዝቧል፤ ኃላፊነቱ ሲሰጠን ከነ መሳርያው ነው፤ እሱም ጸጋና ሐዋርያነት ነው፤ እኛም እሱን ተቀብለናል፤ እንግዲያውስ የተቀበልነውን ጸጋና ሐዋርያነት በዓለም ውስጥ ላለው ሕዝበ እግዚአብሔር አገልግሎት ማዋል ከኛ ይጠበቃል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!! 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአሁኑ ጊዜ የሌለበት ክፍለ ዓለም የለም፤ ምክንያቱም የዚህ ሲኖዶስ ወኪሎች ሊቃነ ጳጳሳት በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በካናዳና በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በእስያና በአውስትራሊያ ወዘተ የሚገኙ ሕዝበ እግዚአብሔር ምእመናንን በማገልገል ላይ ይገኛሉና ነው፤ ይህ ዕድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መለኮታዊ ተልዕኮውን በአጽናፈ ዓለም ሁሉ ለማድረስ ምቹ መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ከዚህም በመነሣት በየክፍለ ዓለሙ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃነ ጳጳሳት ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ባሻገር የየአካባቢውን ሕዝብ በማስተማርና በማቀፍ የተጣለባችሁን ሐዋርያዊ ተልእኮ በትጋትና በንቃት መወጣት ይኖርባችኋል፡፡
በማእከል ሆኖ እየመራ የሚገኝ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚህ ተልእኮ ምቹ መደላድል የመፍጠር ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ይገባዋል፡፡ በተለይም ትምህርተ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን  የተማሩና በጥልቀት የተገነዘቡ፣ ብስለትም ያላቸው፤ እንዲሁም በቋንቋና በሥነ ልቦና ዕውቀት የላቀ ሀብተ ጸጋ ያላቸውን በሐዋርያነት እያሠለጠነ በአጽናፈ ዓለም ሁሉ  ሊያሰማራ ይገባል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! 
በብሂለ አበው (ፀሐይ ለመስኮቷ ሳታበራ…) እንደሚባለው ለሌላው በብቃት መድረስ እንችል ዘንድ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሲኖዶሱ መንበር በሚገኝባት ምድረ ኢትዮጵያ ከመቸውም የተሻለ ሥራ በመሥራት ለእግዚአብሔር መታዘዝ ሕዝቡንም ማገልገል ይገባናል፤ ሁላችንም እንደ የምንገነዘበው በሲኖዶሳችን ያልታቀፉ ብዙ ወገኖች በሀገር ውስጥ አሉን፤ እነዚህ ወገኖች አንዳንዶቹ በተለያየ ምክንያት ከኛ የወጡ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የሄዱት ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ፣ ሌሎችም ወደ መንጋው እንዲቀላቀሉ በርትቶ መሥራት የዚህ ጉባኤ ተቀዳሚ ተልእኮ ነው፤ ምክንያቱም ጸጋንና ሐዋርያነትን የተቀበልንበት ዋናው ምክንያት ይህንን ለማድረግ ነውና፡፡ ከዚህ አኳያ የቤተ ክርስቲያናችን ተደራሽነት በሳሳበት ኣካባቢ ሁሉ የተለየ ትኵረት ሰጥተን መስራትና ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል፤       
       
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!  
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ክህነትና ምእመናን የሆን ሁላችን፣ ከሁሉ በፊት ያለንን ዓቅምና ብቃት በአግባቡ መገንዘብ ይኖርብናል፤  ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁንና ለፈጣሪው በቈራጥነት የሚታዘዝ ምእመን፣ ወጣት፣ ካህን አለን፤ ይህ ትልቅ ጸጋ ነው፤ ይህንን ጸጋ እግዚአብሔር፡ ለእግዚአብሔር መንግሥት በሚመች ሁናቴ ዝቅ ብሎ ማገልገል የክብር ክብር ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሐቅ፣ በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ቆመን ካገለገልነውና አባትነታችንንና መሪነታችንን በመልካም አሠራር በትክክል በኅሊናው እንዲቀረጽ ካደረግን፣ ይህ ኃይል ከጐናችን እንደማይለይ እርግጠኞች መሆን እንችላለን፤ ይህንን ካሳካን ለኛ የተሰጠ ኃይልና ብቃት በየትም አይገኝም፡፡

በዚህም በዚያም ሃይማኖቱ የሚጠይቀውን ስብእና እና ቁመና ይዘን ከተገኘን፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ ያለውን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን ሳይቀር ለመስጠት ወደ ኋላ የማይል የእግዚአብሔር ሕዝብ አለን፤ ስለዚህ ይህንን ማሳካት እንችል ዘንድ ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንድናስገኝ የተቀበልነውን ጸጋና ሐዋርያነት በክብር እንያዝ፤

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!!
ለሕዝበ እግዚአብሔር የምናበረክተው አገልግሎት በመንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚውና በማኅበራዊው አገልግሎትም ጭምር ነው፤ ከዚህ አንጻር ሕዝባችን የተሻለ ማኅበራዊ አገልግሎት እንዲያገኝ፣ በኢኮኖሚውም ከድህነት የተላቀቀ እንዲሆን፤ እንደዚሁም ሰላሙና አንድነቱ የተጠበቀ እንዲሆን፣ በማስተማርም በተግባር በመሳተፍም የሕዝቡ መሪዎችና አርአያ ሆነን መሥራት ይገባናል፤

በተለይም ከሰላም እጦት የተነሣ በእጅጉ እየተጎዳ ያለውን ሕዝባችን ሰላምና ፍትሕ እንዲያገኝ በጸሎትም በትምህርትም፣ በምክርም ተግተን መሥራት አለብን፤እንዳጋጣሚ ሆኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንግልት የተላቀቀበት ጊዜ ብዙ እንዳልሆነ ይታወቃል፤ ለእንግልት እየተዳረገ ያለውም የሌሎች እጅ ባይለየውም በዋናነት በገዛ ልጆቹ ነው፤ እናት በገዛ ልጆቿ ስትንገላታ ማየት እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው፤ እንደዚህ ያለው ነገር በደንብ ያልታሰበበት አካሄድ በብስለትና በንስሓ ማስተካከል አሸናፊነትን እንጂ ተሸናፊነትን አያሳይምና እንዲታሰብበት እንመክራለን፤ ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ልማትና ዕድገት እናሻግራለን ብላችሁ እየደከማችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን እባካችሁ መለስ ብላችሁ እናታችሁ የተንገላታችበትን እዩና በቃ በሉ፤ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ፤ በዚህ አማራጭ እናት ሀገር እፎይታ እንድታገኝ አድርጉ፤ ይህንም ለውድ እናት የሚደረግ ካሣ አድርጋችሁ ውሰዱት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መልእክትና ጥሪም ይህ ነው፤
ልዩ ፍርድ ቤት

ብዙዎቻችን ወንድሞቻችንን ለማማት የፈጠንን ነን፡፡ የራሳችንን ግንድ ትተን የሰውን ጉድፍ ለማውጣት የምንቻኮል ነን፡፡ በወንድሞቻችን ላይ ለመፍረድ፥ እኅቶቻችንን ለመኰነን የምንጣደፍ ነን፡፡

ወዳጄ ሆይ! መፍረድ የእግዚአብሔር እንጂ ያንተ ሥልጣን አይደለምና ተጠንቀቅ፡፡ እህቴ ሆይ! በአምላክ ዙፋን ላይ ለመቀመጥ አታስቢ፡፡

ወዳጄ ሆይ! መፍረድ አማረኽን? እንኪያስ ምንም ወቀሳ የሌለበት፣ ይልቁንም ብዙ ጥቅም የሚያስገኝ የፍርድ ችሎት አለልህ፡፡ በራስህ ላይ መፍረድ ትችላለህና ተቀመጥ፡፡ ከኹሉም አስቀድመህ የበደልህን መዝገብ በፊትህ አኑረው፡፡ ነፍስህ የሠራችውንም ወንጀል በሙሉ በጥንቃቄ መርምር፡፡ ከዚያም “ነፍሴ ሆይ! ይኽንና ያንን በደል የፈጸምሽው ስለምንድነው?” በላት፡፡ የበደለችበትን ምክንያት ትታ በሌሎች ላይ ለማሳበብና በሌሎች ላይ ለመፍረድ ከዠመረችም “የተከሰስሽው በራስሽ ወንጀል እንጂ በሌላ ሰው ወንጀል አይደለም፡፡ እዚኽ ፍርድ ቤት የመጣሽው ስለእነዚያ ሰዎች ለመመስከር አይደለም፡፡ ስለዚኸ ንገሪኝ! ይኽን ያኽል በደል የፈጸምሽው፣ ይኽን ያንን ኹሉ ጥፋት ያጠፋሽው ስለምንድነው?” በላት፡፡ ዘወትር ይኽን የመሰለ አስጨናቂ ጥያቄ ጠይቃት፡፡ አፍራ የምትመልሰው ከሌላትም አስፈላጊውን ፍርድ (ቀኖና) ወስንባት፡፡ ይኽን ልዩ ፍርድ ቤት ዘወትር የምትቀመጥ ከኾነ ያንን የእሳት ባሕር፣ ያ እሳቱ የማይጠፋው ትሉ የማያንቀላፋው ስቃይ በልቡናህ ይቀረጻል፡፡

“ወደ እኔ መጥቶ ነው፤ እርሱ አታልሎኝ ነው፤ እርሱ ፈትኖኝ ነው" እያለች በዲያብሎስ እንድታመካኝም አትፍቀድላት፡፡ ይልቁንም፡- "አንቺ ባትፈቅጂ ነው እንጂ እነዚኸ ኹሉ በአንቺ ላይ ሥልጣን የላቸውም" ብለህ ንገራት፡፡ "እኔ እኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ የምኖረውም በዚኽ ኃጢአት በሞላበት ዓለም ነው" ካለችህም "ይኽ ኹሉ ሰበብና ምክንያት ነው፡፡ ብዙዎች አንቺ የለበስሽውን ሥጋ ለብሰው በዚኽ ዓለም ኑረው ጻድቃንና ሰማዕታት ኾነዋል፡፡ አንቺ ራስሽ አንዳንድ ጊዜ መልካም ምግባራትን ስታደርጊ ይኸ አኹን የምታሳብቢበትን ሥጋ ለብሰሽ ነው" በላት፡፡ ይኽን ስትላት ቢያማትም እጅህን አታንሳባት፡፡ ምክንያቱም ቀኖናው ከሞት የሚታደጋት መንፈሳዊ ልምምድ እንጂ የሚገድላት ቅጣት አይደለምና፡፡ ስለዚኽ ምክንያት የምታበዛብህ ከኾነ “እባብ አሳተኝ" ብላ ከተጠያቂነት ያለመለጠችውን ሔዋንን አስታውሳት፡፡

ይኽን ኹሉ ስታደርግም ከአጠገብህ ማንም አይኑር፡፡ የሚረብሽህ ሰው ከአጠገብህ አይገኝ፡፡ ይልቁንም ዳኛ በፍርድ ወንበር ላይ እንደሚቀመጥ አንተም በፍርድ ወንበር ፈንታ በምቹ ጊዜና ቦታ በጽሞና ተቀመጥ፡፡ ነቢዩ “በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ" እንዳለው /መዝ.4፥4/ ይኽ ቦታና ጊዜ ከኹሉም ይልቅ ተስማሚ ነውና እራትህን ከበላህ በኋላ ዘወትር ይኽን የፍርድ ወንበር ወደ መኝታ ክፍልህ ይዘኸው ሒድ፡፡ ዕለት ዕለት ይኸን የምታደርግ ከኾነ ሐዋርያው “እኛ በራሳችን ብንፈርድ ኖሮ ባልተፈረደብንም ነበር" እንዲል (1ኛ ቆሮ.1፥31) በዚያ አስፈሪው የፍርድ ወንበር ፊት ያለ ፍርሐት ትቆማለህ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች ገጽ 42-42 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
“ደጋግመህ ኃጢአት ብትሠራም ደጋግመህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተክርስቲያን ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
''በእንተ ስማ ለማርያም''

እስከ አሁን ወደ አካውንቱ 40,000 ብር ገብቶልናል ከታሰበው 52,000 ብር ውስጥ 12,000 ይቀራል። በጎ አድራጊዎች "በእንተ ስማ ለማርያም" ብለን ፊታችሁ ቆመናልና  በተጠቀሰው አካውንት እንደ አቅማችሁ ተሳተፉ...

የወልድያ ከተማ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት በ‍ቶች አንድነት ጉባኤ
2071111 0880 89 013
ዓባይ ባንክ

ለተጨማሪ መረጃ  ➛ +251 92195 8461
                         ➛ +251 95 327 5024


ገቢ ያደረጋችሁበትን ለመላክ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ @natansolo ይጠቀሙ

Рекорддор

16.05.202523:59
45.3KКатталгандар
13.04.202519:14
200Цитация индекси
21.03.202505:44
5.7K1 посттун көрүүлөрү
14.05.202513:51
4.8K1 жарнама посттун көрүүлөрү
02.05.202523:59
13.21%ER
21.03.202505:44
13.13%ERR
Катталуучулар
Citation индекси
Бир посттун көрүүсү
Жарнамалык посттун көрүүсү
ER
ERR
JAN '25FEB '25MAR '25APR '25MAY '25

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ популярдуу жазуулары

09.05.202508:47
"ኢያቄምና ሐና በጸለዩ በአለቀሱ ጊዜ ለሁላችን ምእመናን መጠጊያ የምትሆን ኃጢአትን ይቅር የምታስብል ሴት ልጅ አገኙ፤ ሁለቱ ሽማግሌዎች ሰማይን ወለዱ፤ ሰማያቸውም ፀሐይን አስገኘች።"

ነግሥ ዘልደታ
18.04.202514:05
ከአረጋዊ መንፈሳዊ
(ዓርብ ምሽት አስራ ሁለት ሰዓት የሚነበብ)

ለአልዓዛር አዝነህ ያለቀስክና ዕንባን ያፈሰስክ አምላክ ሆይየመረረ ሐዘኔንና ዕንባዬን ተቀበል።

ሕማሜንም በሕማምህ ፈውስ፤ ቊስሌንም በቍስልህ አድን፤ ደምህንም በደሜ ጨምር፤ የቅዱስ ሥጋህንም የሕይወት መዐዛ ከሥጋዬ ጋር አንድ አድርግ።

ከጠላቶች እጅ የጠጣኸው ከርቤ ክፉ ሐሞት ኃጢአትን ለጠጣች ለነፍሴ ጣዕም ይሁናት።

በዕፀ መስቀል ላይ የተዘረጋው ሥጋህ ልቡናየን ወደ አንተ የተዘረጋ ያድርገው፤ እነሆ በሰይጣን ድል ሆኖአልና።

በመስቀል ላይ ዘንበል ያለው ራስህ በርኵሳንና በክፉዎች አጋንንት ዘንድ የተደበደበ ራሴን ከፍ ከፍ ያድርገው።

በከሐድያን አይሁድ በችንካሮች የተቸነከሩ የከበሩ እጆችህ በአንደበትህ ተስፋ እንዳስደረግህ ከክፉ ጒድጓድ ወዳንተ ይምጠቁኝ።

ከወንጀለኞች ርኩስ ምራቅንና ውርደትን የተቀበለ ፊትህ በኃጢአት የጨለመውንና የከፋውን ፊቴን ያብራው።

በመስቀል ላይ በሥልጣንህ የተለየችው ነፍስህ በቸርነትህ ወደ አባትህ ወደ አንተ ታድርሰኝ።

የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ የማትመረመር የቸርነትህን ብዛት አደንቃለሁ፤ ዓለምንና በውስጥዋ የሚኖሩትን እንዳያጠፉ መላእክትን የከለከለቻቸው።

ልቡናዬን አራራ አለቱም እንደተሠነጠቀ አንተን ከመፍራት የተነሣ ይሠንጠቅ። ሙታንም እንደተነሡ ምውት ልቡናዬን አንሣው።

አቤቱ ወደ ከበረች መቃብርህ እንድመለስ አድርገኝ። ልመናው በረከቱ ለዘላለሙ ከእኛ ጋር ይኑር፤ አሜን

(ከአረጋዊ መንፈሳዊ የተገኘ ሃያ አምስተኛው ድርሳን - ግብረ ሕማማት)
02.05.202504:51
"ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡"

(ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
05.05.202500:16
"ኹሌም በሄድኩበት የምናገረው አንድ ነገር አለኝ"!

"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣
ምልኩስና እና
ክህነት ናቸው።


እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር፣ በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ "እንዴት?" ካልን፦
የተከበረ ትዳር የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል።
የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ!
ተምረን ማግባትና፣ ተምረን መመንኮስም ሆነ  ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
22.04.202511:06
በዓለ ኀምሳ እና ንስሓ

ብዙዎች "በበዓለ ኀምሳ ንስሓ መግባት ይቻላል ወይ?" ብለው ይጠይቃሉ። መልሱ "አዎ ይቻላል" ነው። ሰው በአጽዋማት ጊዜም በበዓላት ጊዜም ንስሓ ገብቶ ቀኖና ሊሰጠው ይችላል። ነገር ግን ካህኑ የሚሰጡት ቀኖና ሊለያይ ይችላል። ለምሳሌ በበዓለ ኀምሳ መጾም፣ የቀኖና ስግደትን መስገድና የመሳሰሉትን ማድረግ እንደማይገባ በፍትሐ ነገሥት ተገልጿል። ስለዚህ በበዓለ ኀምሳ ንስሓ የገባ ሰው ጹም፣ ስገድ አይባልም። ምናልባት መጽውት፣ ይህን ጨምረህ ጸልይ እና የመሳሰሉ ቀኖናዎች ሊሰጡት ይችላሉ። ይህንን እንደሁኔታው ንስሓ አባቱ የሚወስኑት ነው። በጾም ጊዜም ጨምረህ ጹም፣ ስግደት ጨምር ተብሎ ሊታዘዝ ይችላል።

የሆነ ሆኖ ግን በማናቸውም ጊዜ በደልን መናዘዝ፣ ንስሓ ገብቶ ከኃጢአት መራቅ ይገባል። ንስሓን አረጋዊ መንፈሳዊ እመ ሕይወት (የሕይወት እናት) ይላታል። ምንም እንኳ እግዚአብሔርን በድለን ሰውን አሳዝነን ከነበረ ንስሓ ገብተን ከክፉ ሥራችን መራቅ ይገባናል። ሁልጊዜም ከክፉ ነገሮች ወጥተን መልካም ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርገን በመልካም ሥራ መኖር ይገባናል።

(መምህር በትረ ማርያም አበባው)
04.05.202518:16
"አንድ ወንድና አንዲት ሴት የተጋቡት (የሚጋቡት) መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ አብረው እየተጋገዙ ለመሔድ ከኾነ፥ ትዳራቸው ታላቅ የኾነ ደስታን ያመጣላቸዋል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
06.05.202506:28
"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ከኃጢአት ፍላጻ የመደበቂያ ጽኑ መከላከያ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍትን አለማወቅ በአዘቅት እና በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ መኖር ነው።"

ቅዱ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ
07.05.202516:44
ራስን መግዛት (ክፍል -፩)

መንፈሳዊው ሰው ካሉት ብቃቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ራስን መግዛት ነው፡፡ እርሱ ራሱን ለሥጋ ምኞትና ለፍላጎቶቹ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ሕሊናው የኃጢአትን ምኞት ሲናፍቅ ይህን አሳቡን በመቃወም መንፈሱ እንድትመራው በማድረግ ራሱን አጥብቆ ይገዛል:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- «በመንፈሱ ላይ የሚገዛ (መንፈሱን የሚገዛ) ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል፡፡» ምሳ. 16፥32

እንደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ራሱን የሚገዛ ወይም የሚመራ ማለት ሥጋው የጠየቀውን ሁሉ የማይሰጥ ይልቁኑ የሚቃወም ማለት ነው:: «ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፤ነፍሱን በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል፡፡» ዮሐ. 12፥25።

ራስን መግዛት በውስጡ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉት እርግጥ ነው፡፡ እነርሱም፤-

1. ምላስን መግዛት
2. #አሳብን መግዛት
3. ልብን መግዛት (ፍላጎትንና ምኞትን በመግዛት)
4. ስሜትን መግዛት
5. ሆድን መግዛት (ምግብን በተመለከተ) ናቸው፡፡

ራሱን የሚመራ ሰው እርሱነቱን ለእሴትና ለዓላማ እንዲሁም ለሕግና ደንብ ያስገዛል፡፡ ራሱን መምራት የማይችል ሰው ግን በእርግጥ እርሱነቱን ለጥፋት ይጋብዛል፡፡ ራሱን የሚገዛ ሰው ነፍሱን በእውነተኛ ፍቅር ይወዳታል:: ራሱን የሚያቀናጣ ግን ነፍሱን ከማጣቱም በላይ ሌሎችም ከእርሱ ጋር አብረው እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ ራሱን አጥብቆ የሚጠብቀው በትጋቱ ነፍሱን ስለሚጠብቃትና በመልካም ሁኔታ ስለሚይዛት ያድናታል፡፡ አልፎ ተርፎም ሌሎችን ለማዳን ምክንያት ይሆናል፡፡ የራሱን አመለካከትና ግንኙነት በቅደም ተከተል ያደራጃል፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ያስቀድማል፤ በመቀጠል ሰዎችን ያስከትላል፤ በመጨረሻም ራሱን።

ምላስን መግዛት

መንፈሳዊው ሰው ቃላት ወይም አሳቦች ያቀበሉትን ወደ አእምሮው የመጡትን ሁሉ በአንደበቱ አይናገራቸውም፡፡ እያንዳንዱን ቃል ከአንደበቱ ከማውጣቱ በፊት ይመዝናል:: የእርሱ ሚዛን የሚለካው የቃሉን ፍሬ ነገር ብቻ ሳይሆን ትክክል መሆኑንና አለመሆኑንም ጭምር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእርሱ ዋና ዓላማው ቃሉ በሌሎች ሰዎች ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ፣አፀፋና ውጤቱን ጭምር ነው::

የምላስ ወይም የአንደበት ስህተት ውጤት ሥጋን ማሳደፉንና የፍጥረትንም ሩጫ ማቃጠሉን የሚያውቅ ሰው ከመናገሩ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል:: ያዕ. 3፥5-6:: ከነቢዩ ከዳዊት ጋር ሆኖም:- «አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ፡፡» ይላል፡፡ እርሱ አንዴ ከአፉ የወጣው ቃል ተመልሶ ሊገባ እንደማይችል ያውቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከአፉ የወጣው ቃል አድማጮቹ ጆሮ ከደረሰ በኋላ የተናገረውን መልሶ ሊውጠው፣ ወይም ይቅርታ ሊያገኝበት እንደማይችል አስቀድሞ ያውቃል:: ከዚህ በኋላ ስህተቱን ለማስተካከል ቢጥርም ጥፋቱ በእርሱ ላይ ዕዳ ሆኖ እንደሚቆጠር አጥብቆ ይረዳል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ጌታ እንደተናገረው እንደሚኮነንበት ያውቃል፡ . . . ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና፤ ከቃልህም የተነሣ ትኮነናለህ፡፡» ማቴ. 12፥37::

ይቀጥላል...

(በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
መንፈሳዊ ሰው መጽሐፍ  ገጽ 122-128
#በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)
05.05.202516:04
እንኳንም ተሳሳትኩ

በአንድ ወቅት አንዲት የሒሳብ መምህርት የሚከተለውን በሰሌዳ ላይ ጻፈች፦

👉 9×1= 7
👉 9×2= 18
👉 9×3= 27
👉 9×4= 36
👉 9×5= 45
👉 9×6= 54
👉 9×7= 63
👉 9×8= 72
👉 9×9= 81
👉 9×10= 90

ጽፋ እንደጨረሰችም ወደ ተማሪዎቿ ዞራ ስትመለከት ሁሉም እየሳቁባት ነው፣ የመጀመሪያውን እኩልታ (equation) ተሳስታለችና

ይህን ጊዜ መምህርቷ እንዲህ አለች፦ "የመጀመሪያውን ስህተት የጻፍኩት በዐላማ ነው፤ ከነገሩ ጠቃሚ ትምህርትን እንድትወስዱ ስለፈለኩኝ። ይኸውም፥ በውጪ ያለው ዓለም እንዴት እንደሚቀበላችሁ ታውቁ ዘንድ ነው። 9 ጊዜ ትክክለኛ ነገር እንደጻፍኩ ማየት ትችላላችሁ ይሁንና አንዳችሁም ስለዛ አላበረታታችሁኝም፤ ነገር ግን ሁላችሁም ስለ ሠራሁት አንድ ስህተት ሳቃችሁብኝ፣ ነቀፋችሁኝ!

ትምህርቱም ይህ ነው
የሰው ልጅ ሚሊዮን መልካም ሥራን ብትሠሩ አያበረታታችሁም ግን አንድ የሠራችሁትን ስህተት ይዞ ይነቅፋችኋል። በዚህ ግን ተስፋ ልትቆርጡ አይገባም... ሁልጊዜም ቢሆን ከሳቅና ከነቀፋ በላይ ወጥታችሁ ቁሙ፣ ጽኑ፣ በርቱም!"

ልብ እንበል
መሳሳትን ከፈራን መሞከር አንችልም፤ መሳሳት መጨረሻችን አይደለም የማወቅ መነሻ እንጂ። ምናልባት የተማርነውን እንረሳ ይሆናል፣ የተሳሳትነውን ግን አንረሳም። ከብዙዎች የስንፍና ፍፁምነት ይልቅ የእኛ የመሥራት ስህተት እንደሚሻል እናስብ።

(ፌስቡክ ላይ የተወሰደች)
21.04.202503:59
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

ሰኞ
ማዕዶት ይባላል፡-
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ
ቶማስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ
አልአዛር ይባላል
፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ
አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

አርብ
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

ቅዳሜ
ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

እሁድ
ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
17.04.202520:27
አስጨናቂዋ ምሽት

ይህች ምሽት እንጀራውን የበላ ይሁዳ እግሩን አንስቶ ሕዝብ ለጥፋት እየመራ ወደ ጌታ የመጣባት ምሽት ነች፣ የይሁዳ እግሮች ታጥበው አንድ ቀን ሳያድሩ ዝቅ ብሎ ያጠባቸውን ጌታ አሳልፈው ለመስጠት ለጥፋት እንዴት ተፋጠኑ? በእውነት እርሱን በተቀበለበት አንደበቱ በሽንገላ ከንፈር ጌታውን ለመሳም እንዴት ቻለበት?

ይህች ምሽት ጌታ ነፍሱ እስከ ሞት ድረስ እጅግ ያዘነችበት እንደዋና ይታዩ የነበሩት (ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ) ከደቀመዛሙርቱ ለአንዲት ሰዓት እንኳ ከርሱጋ ሊተጉ ያልቻሉባት፣ እርሱ ተጨንቆ ሁሉም እንቅልፍ እንቅልፍ ያላቸው ሰዓት፣ እረኛው ክርስቶስ ሲቀርብ ለእስራት በጎቹ የጌታ ደቀመዛሙርት ጨርቃቸውን እስኪጥሉ ድረስ የተበተኑባት አስጨናቂ ምሽት። ጌታ የጠራው ጴጥሮስ አላውቅህም ብሎ ሲናገር የተሰማበት አስጨናቂ ምሽት።

የሊቀ ካህናቱን ባሪያ ጆሮ ከጴጥሮስ ሰይፍ ጥፋት ከተቆረጠችበት ሲያድን እያዩ ሊያስሩ የደፈሩበት፣ እኔ ነኝ በሚለው ድምጹ የኃይሉን ብልጭታ ሲያሳያቸው ሁሉ ወደኋላ ተፍገምግመው የወደቁበት፣ ከወደቁበት እንዲነሱ ኃይል ሆኗቸው ለሁለቱም ድርጊቱ የምስጋና ምላሽ ሳይሆን የተረፈው ለእጁ ሰንሰለት ነበር።

በእውነት ይህች ምሽት አስጨናቂ ምሽት ናት። ባለፈው ጊዜ አይደለም ሊይዙት በመጡበት ጊዜ ሁሉ ለሚያደርገው በጎ ነገር በጎ ምላሽ ያላገኘበት፤ ያደረጋላቸው የተበተኑበት የሚያደርግላቸውም ያልመከቱለት ይልቁን በእጁ ላይ ሰንሰለትን ለማድረግ የተፋጠኑበት አስጨናቂ ምሽት።

እኛስ በሕይወት እንዲህ አይነት ምሽት አይገጥመን ይሆን?
🙏
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው፡ አለው።”
የማቴዎስ ወንጌል 26፥4

ዲያቆን ቡሩክ ተስፋዬ

ይቀላቀሉ
t.me/Orthodxia t.me/Orthodxia
t.me/Orthodxia      t.me/Orthodxia
t.me/Orthodxia      t.me/Orthodxia
23.04.202517:39
ቢሠዋብንም፣ ምንም እንኳን ትችቱም ሽቅብ ቢሆንብንም ይኸንን ማድረጋችን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን ደኅንነት ሲባል የተጋባ ነበር፡፡ መሰል ክሶችን፣ ጩኸቶችንና ቁንጽላዎችን መታግስ ዋጋ አስከፍለውን ስለተማርን ወደፊትም ይኸንን በማድረጋችን እንቀጥላለን፡፡

ይኸው ነው!!!
ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ!

ሲዖልን ይበዘብዝ ዘንድ ወደ ሲዖል ወረደ!

ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም!

ከንቱ አድርጓታልና መረራት!

ሸንግሏታልና መረራት!

ሽሯታልና መረራት!

ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!

[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤
ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!

ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ?

ሲዖል መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Көбүрөөк функцияларды ачуу үчүн кириңиз.