Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
09.05.202507:11
ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ለዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ተፋላሚ ሆኑ
**************

በአውሮፓ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ አትሌቲክ ቢልባኦን በድምር ውጤት 7 ለ 1 እንዲሁም ቶተንሃም ቦዶን 5 ለ 1 በማሸነፍ ለዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ደርሰዋል።

ዛሬ ምሽት አትሌቲክ ቢልባኦን በኦልድትራፎርድ ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ 4 ለ 1 አሸንፏል።

የማንቸስተርን የማሸነፊያ ግቦች ሜሰን ማውንት (2) እንዲሁም ካሰሚሮ እና ሆይሉንድ አንድ አንድ አስቆጥረዋል።

አትሌቲኮዎች በመጀመሪያው አጋማሽ 31ኛው ደቂቃ ላይ ድንቅ ጎል አስቆጥረው እረፍት መውጣት ቢችሉም በሁለተኛው አጋማሽ 4 ግቦችን ለማስተናገድ ተገድደዋል።

በዚሁ መሠረት በአትሌቲክ ቢልባኦ ሜዳ 3 ለ 0 አሸንፎ የነበረው የእንግሊዙ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ በድምር ውጤት 7 ለ 1 በማሸነፍ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።

በሌላ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ቦዶን የገጠመው ቶተንሃም ሆትስፐር 2 ለ 0 አሸንፏል።

ባለፈው ሳምንት በሜዳው ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በበላይነት ያጠናቀቀው ቶተንሃም በድምር ውጤት 5 ለ 1 በማሸነፍ ለዋንጫው ከዩናይትድ ጋር የሚፋለም መሆኑን አረጋግጧል።

በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ደግሞ ቼልሲ ዩጋርደንን በድምር ውጤት 5 ለ 1 እንዲሁም ሪያል ቤቲስ ፊዮረንቲናን 4 ለ 3 በማሸነፍ የዋንጫው ተፋላሚ ሆነዋል።

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ካርዲናል ሮበርት ፕሪቮስት 267ኛው የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ መሆናቸው ታወቀ
*******************

ካርዲናል ሮበርት ፕሪቮስት 267ኛው የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው ታውቋል።


ካርዲናል ሮበርት ፕሮቬስት ቺካጎ የተወለዱ የ69 ዓመት ካርዲናል ሲሆኑ፣ ከሰሜን አሜሪካ የመጀመሪያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ካርዲናሉ ስማቸውም ሊዮ 14ኛ ተብሎ ተሰይሟል፡፡

ከ40 ሺህ በላይ ምዕመናን ሁነቱን ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መገኘታቸውን የፖሊስ መረጃን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በለሚ ታደሰ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
የዓለም የምግብ ዋስትና ስጋትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል የተባለለት የሩዝ ዝርያ
************


የቻይና ተመራማሪዎች ውሃ ባልተኛበት ደረቅ መሬት በሚበቅለው የሩዝ ዝርያ ስር ላይ ድርቅን ከመቋቋም ጋር ተያያዥነት ያላቸው የዘረመል ምስጢሮችን ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

ይህም በስፋት የሚመረተውን የመስኖ ሩዝ ድርቅን መቋቋም ወደሚችሉ የሩዝ ዝርያዎች ለመለወጥ ያስችላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ተመራማሪዎቹ ውሃ ባልተኛበት ደረቅ መሬት የሚበቅለው የሩዝ ዝርያ ጥልቅ እና ወፋፍራም ስሮች እንዳይኖሩት ሊያደርግ የሚችለውን ዘረመል መለየት መቻላቸውን አስታውቀዋል። ጥልቅ እና ወፋፍራም ስሮች ድርቅን ለመቋቋም ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

ኤችኤምጂቢ1 ተብሎ የሚጠራው ይህ ዘረመል ከተወገደለት በኋላ ውሃ በተኛበት መሬት የሚበቅለው ሩዝ እንደ ደረቅ መሬት ሩዝ ረጅም ስር ማብቀል እና የተሻለ ድርቅን የመቋቋም አቅም ማዳበር ችሏል።

በዚህም ውሃ በተኛበት መሬት ላይ ብቻ ይበቅል የነበረው የሩዝ ዝርያ ውኃ-አጠር በሆኑ አካባቢዎችም በስፋት ሊለማ እንደሚችል ተረጋግጧል ብለዋል ተመራማሪዎቹ።

የዓለም የምግብ ዋስትና ስጋትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል የተባለለትን ይህንኑ የሩዝ ዝርያ በስፋት ለማሰራጨት በሙከራ ላይ መሆናቸውንም ነው የገለፁት።

ለድርቅ ተጋላጭ የሆነው የሩዝ ሰብል የውኃ ፍጆታው ከፍተኛ በመሆኑ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለዓለም የምግብ ዋስትና ስጋት ሆኖ ቆይቷል።

በዚህ ሳቢያ ተመራማሪዎች ውኃ ቆጣቢ የሆነ፣ ድርቅን የሚቋቋም የሩዝ ዝርያ በምርምር ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ትራምፕ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የድል ቀን የአሜሪካ ብሔራዊ በዓል እንዲሆን የሚደነግግ አዋጅ ፈረሙ
*****************

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድል የሚከበርበት ቀን እንዲሆን የሚደነግግ አዋጅ ፈርመዋል።

ግንቦት 8 የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የድል ቀን በመባል ይታወቃል። የዚህ ድል 80ኛ ዓመት በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል።

“በዓለም ዙሪያ፣ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አጋሮቻችን በዚህ ሳምንት እያከበሩ ነው፣ ነገር ግን አሜሪካ የራሳችንን ትክክለኛ በዓል አክብራ አታውቅም፣ እናም ለዚህ ድል መገኘት ዋና ምክንያት እኛ ነን” በማለት ተናግረዋል ፕሬዚዳንቱ።

“ወደዳችሁም ጠላችሁም ወደዚያ ጦርነት ገብተናል ያንን ጦርነት አሸንፈናል፤ እና ከብዙ ታላላቅ ሰዎች ብዙ ታላላቅ አጋሮች ብዙ እርዳታ አግኝተናል” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

“ነገር ግን በዚያ ጦርነት ውስጥ የበላይ ኃይል አይደለንም የሚል ማንም አይኖርም ብዬ አስባለሁ ፤ እናም ይህን አናከብረውም ነበር” ሲሉም ገልጸዋል።

“በሁለት የዓለም ጦርነቶች አሸንፈናል፣ ነገር ግን ለእሱ እውቅና አልሰጠንም ማንም ሰው እንደሚያደርገው” በማለት ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

“በዓለም ዙሪያ ያሉ አጋሮቻችን ሁሉ በእኛ ምክንያት የተገኘውን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድል እያከበሩ ነው” ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ “ይህን የድል በዓል የማታከብር ብቸኛዋ ሀገር አሜሪካ ናት” ብለዋል።

እናም ይህን ማድረግ ልክ አይደለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ የራሷን ድል ማክበር አለባት በማለት አዲስ አዋጅ መውጣቱን ተናግረዋል ሲል ዘ ዋሽንግተን ታይምስ ዘግቧል።

በጌቱ ላቀው

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202507:48
ሩሲያ በልዩ ሁኔታ የምታከብረው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የድል ቀን

ሩሲያ የሁለተኛ ዓለም ጦርነት የድል ዕለትን በየዓመቱ ሜይ 9 በሞስኮ የሚገኘው ቀዩ አደባባይ በደማቅ ወታደራዊ ትርዒት ታከብራለች፡፡ ይህ የሩሲያ አከባበር በዓለም ላይ ካሉት ሀገራት ሁሉ እጅጉን የላቀ ድምቀት ያለው ነው። ይህ ታላቅ ትዕይንት “ሶቪየት ኅብረት” በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት “በናዚ” ላይ ድል መቀዳጀቷን የሚያስታውስ እና ሩሲያውያን ልዩ የሀገር ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ነው። ሰልፉ ከድሉ መታሰቢያነቱ ባሻገርም እንደ ብሔራዊ የመታሰቢያ ቀን የሚታይ ሲሆን፣ ሩሲያ የጦር ኃይሏን አቅም እንዲሁም ታሪካዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ትኩረቷ መግለጫ ሆኖም ያገለግላል።

“ናዚ” አውሮፓን በተቆጣጠረበት ወቅት እጅ ካልሰጡ ሀገራት መካከል ሩሲያውያን ይገኙበታል፡፡ የናዚ ጦር በመጀመሪያው ዙር ጦርነት የ”ሶቭየት ሕብረትን” ጦር አሸንፎ የነበረ ቢሆንም ሩሲያውያን ግን እንደገና ተደራጅተው 24 ሚሊዮን ዜጎቻቸውን ሰውተው አሸንፈዋል፡፡ ይህ የሩሲያ መስዋዕትነት ከ15 እስከ 17 ከሚሆነው የአውሮፓ ሀገራት መስዋዕትነት የላቀ ሲሆን፣ በጦርነቱ ምክንያት በመላው ዓለም ከተከፈለው የሰው ህይወት 40 በመቶውን እንደሚሸፍን የታሪክ ማስረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

የመጀመሪያው የድል ሰልፍ በ”ሶቭየት ሕብረት” የተካሄደው “ናዚ” ከተሸነፈ ከአንድ ወር በኋላ እ.አ.አ ሰኔ 24 ቀን 1945 ነበር። በቀዩ አደባባይ በተካደው ሰልፍ ላይ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ስታሊን የተገኙ ሲሆን፣ ማርሻል ጆርጂ ጁኮፍ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጠው ሰልፉን መርተዋል።

በዚህ የመጀመሪያ ሰለፍ ላይ ከ40 ሺህ በላይ የሶቭየት ወታደሮች ተገኝተዋል፡፡ በዕለቱ በምርኮ ከተያዙ ወታደሮች የናዚ አርማዎችን የመጣል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። ከሁሉም የሶቪየት ጦር ግንባር የተውጣጡ ወታደራዊ ክፍሎች እንዲሁም በጦርነቱ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችም ለእይታ ቀርበውበታል።
ምንም እንኳ የመጀመሪያው ሰልፍ የተካሄደው በፈረንጆቹ ሰኔ ወር ቢሆንም ናዚ ለመጨረሻ ጊዜ እጁን የሰጠው እ.አ.አ ሜይ 8, 1945 በበርሊን ነው። ሶቭየት ሕብረት ሜይ 9 የድል ቀን አድርጋ የምታከብረው በሰዓት አቆጣጠር ልዩነት (Time Zone) ምክንያት ነው፡፡

በዓሉ በሶብየት ሕዝብረት ውስጥ በተለዋወጡት ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ምክንያት በመሃል ቀዝቀዝ የማለት አዝማሚያ አሳይቶ ቆይቷል፡፡ እ.አ.አ በ1965 እንደገና 20ኛው የድል በዓል ሲታወስ ግን የወቅቱ የሶቭየት ሕብረት ፕሬዚዳንት ሊዮኒድ ብሬዥኔቭ ሙሉ ወታደራዊ ሰልፍ በማድረግ ትውፊቱን እንደገና አነሱ። ይህም ሜይ 9 እንደገና የሕዝብ በዓል ሆኑ እንዲሆን የተደረገበት ክስተት ነበር።

1985 እና 1990 የ40ኛው እና የ45ኛው ዓመት በግዙፍ ሰልፎች ተከብሯል፡፡ እነዚህ ክስተቶች ውስጣዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ዓለም አቀፋዊ ፀረ-ሾሳሊዝም በሰፈነበት ወቅት ሶቭየት ሕብረት የጦር አቅሟን ለዓለም ያሳየችበት ነበሩ።በሰልፎቹ የተደረጉት የድሉን ዐርበኞች በማክበር እና በቀዝቃዛው ጦርነት ምክንያት የተከሰተባትን ጫና መቋቋም እንደምትችል ወታደራዊ አቅሟን በማሳየት ላይ ነበር።

ከሶቭየት ሕብረት መፍረስ በኋላ ባሉት የ1990ዎቹ መጀመሪያዎች ላይ ወታደራዊ ሰልፎች በሩሲያ አልተካሄዱም ነበር። ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ዕለቱ በድምቀት እንዲከበር ማድረግ ጀመሩ፡፡ በ50ኛው ዓመቱ በ1995 በፕሬዝዳንት ቦሪስ የልሲን ዬልትሲን መከበሩ ግን ለበዓሉ መመለስ ወሳኝ ክስተት ነበር። ከ2000 መጀመሪያ እስከ አሁን በፕሬዚዳንት ፑቲን መሪነት በዓሉ በደማቅ ሰለፍ እየተከበረ ሲሆን፣ የሩሲያ ብሔራዊ ማንነት የማዕዘን ድንጋይ ተብሎ ይከበራል፡፡

ትዕይንቱ በሩሲያ ለድሉ አሸናፊዎች መታሰቢያ ከማድረግ ባለፈ የሀገሪቱን አቅም ማሳያ ሆኖ ያገለግላል። በሰልፎቹ የሩሲያን የኑክሌር ብቃት፣ እንደ T-14 Armata ያሉ ልዩ ታንኮች፣ የረቀቁ የጦር አውሮፕላኖች እና ጄቶች ይታዩበታል፡፡ ዜጎች "የማይሞት ሬጅመንት (Immortal Regiment)" የሚል ጽሑፍ ያረፈበት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዘመዶቻቸውን ፎቶግራፍ ይዘው ሰልፉ ላይ ይሳተፋሉ። ምዕራባውያን ሩሲያ ላይ ያላቸውን የተቃርኖ አስተሳሰብ እና ፋሺዝም የሚያወግዙ መልዕክቶች ይተላለፉበታል። ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት በሚያጋጥምበት ወቅት ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከርም ይጠቀሙበታል።

እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሰርቢያ ያሉ ሀገሮች በመሪዎቻቸው ወይም በተወካዮቻቸው አማካኝነት በበዓሉ ላይ ይሳተፋሉ።የምዕራቡ ዓለም ሩሲያ ዕለቱን በመጠቀም የጠበኝነት ፖሊሲ ታራምዳለች በማለት ይወቅሷታል።

የሩሲያ ማኅበረሰብም በዓሉን እንደ ብሔራዊ ኩራት አድርጎ ነው የሚወስደው፡፡ የሩሲያ ትምህርት ቤቶች ታሪክን በስፋት ያስተምራሉ። ቤተሰቦች የቀድሞ አባቶችን ጀግንነት የሚያሳዩ ሜዳልያዎችን፣ ፎቶዎችን እና ታሪኮችን ያሳያሉ። የጦርነት መዝሙሮች፣ ፊልሞች እና ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ዊው በዓል ጋር አብረው ይከበራሉ።

የዘንድሮው 80ኛ ዓመት የሁለተኛ ዓለም ጦርነት መታሰቢያ እንደወትሮው በድምቀት እንደሚከበር ታውቋል፡፡ በዚህ በዓል ላይ የቻይና ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከ20 በላይ የሀገራት መሪዎች እና ተወካዮቻቸው እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴም በዓሉ ላይ ለመታደም ሞስኮ ገብተዋል፡፡
ቤላሩስ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ካዛኪዝታን፣ አርሜኒያ፣ ኪርጊስታን እና የሶቭየት ሕብረት የቀድሞ አባላት የሆኑ ሀገራት ዕለቱን ሜይ 9 ብሔራዊ በዓል እድርገው ያከብሩታል፡፡ ከምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ፈረንሳይ ዕለቱን ብሔራዊ በዓል አድርጋ የምታከብር ሲሆን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፖላንድ እና ሌሎች ሀገራት ዕለቱን አስበውት ይውላሉ፡፡ ደቡብ ኮሪያ ደግሞ ኦገስት 15 ዕለቱን አስባ ስትውል፣ ቻይና ደግሞ ሴፕቴምበር 2 ታስበዋለች፡፡

አሜሪካ ሜይ 8 ዕለቱን አስባ ትውል የነበረ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ዕለቱ ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
09.05.202507:11
የ34 አመት ታሪክን የቀየረው ፍሊፖ ኢንዛጊ እና በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ የደረሰው ሲሞን ኢንዛጊ
******************************

ሁለቱ ወንድማማቾች በጣልያን ለበርካታ ክለቦች ተጫውተው አሳልፈዋል። ፍሊፖ ኢንዛጊ እና ሲሞን ኢንዛጊ።

የ51 አመቱ ፍሊፖ ኢንዛጊ በኤሲ ሚላን በጁቬንቱስ አታላንታ እና ሌሎች ክለቦች ድንቅ አጥቂ መሆኑን አስመስክሯል። በተለይ 12 አመት በቆየበት ኤሲ ሚላን የስኩዴቶውን ክብር ሁለት ጊዜ ከማንሳቱ በተጨማሪ ሁለት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ወስዷል።

የ2006 የጀርመን አለም ዋንጫንም ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ማሳካቱ ይታወሳል።

በሁለት አመት የሚያንሰው ሲሞን ኢንዛጊ በላዚዮ እና አታላንታ እንዲሁም በሌሎች ክለቦች ተጫውቶ ቢያሳልፍም የታላቁን ያክል ስኬታማ ነበር ለማለት አያስደፍርም።

በተቃራኒው በተጫዋችነት ታላቅ ወንድሙ ፍሊፖ ኢንዛጊ የገዘፈ ታሪክ ቢኖረውም በአሰልጣኝነት ግን የታናሽ ወንድሙን ያክል ስኬታማ መሆን አልቻለም።

ሲሞን ኢንዛጊ የአሰልጣኝነት ስራውን ከጀመረ 10 አመት እንኳን ባይሞላውም ከተጽዕኖ ፈጣሪዎቹ ተርታ ለመመደብ ግን ጊዜ አላባከነም።

በ2016 ላዚዮን የተረከበው ሲሞን ኢንዛጊ ክለቡን ለበርካቶች ፈታኝ አድርጎ ከመስራቱ በተጨማሪ ከዋንጫዎች ጋር የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆንም አስችሎታል።

በሮሙ ክለብ በገነባው ቡድን ወደ ኢንተር ሚላን ያመራው ሲሞን ከኒርአዙሪዎቹ ጋር የስኩዴቶውን ክብር ሲያሳካ ሌሎች አምስት ዋንጫዎችን ጨምሮ ሁለት ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ አድርሶታል።

ይሄኛው ሳምንት ለሁለቱ ወንድማማቾች የተለየ ሆኖላቸዋል። የቀድሞው የኤ ሲሚላን አጥቂ ፍሊፖ ኢንዛጊ በጣልያን 2ኛው የሊግ እርከን (ሴሪ ቢ) ይሳተፍ የነበረውን ፒሳን ወደ ሴሪ ኤው እንዲያድግ በማድረግ ታሪክ ሰርቷል።

አሰልጣኝ ፍሊፖ ኢንዛጊ በ1991 ከሊጉ የወረደውን ክለብ 34 አመት በኋላ እንዲመለስ ማድረጉ አድናቆት እንዲቸረውም አድርጎታል።

ሲሞን ኢንዛጊ ደግሞ በዚሁ ሳምንት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ባርሴሎናን ከዚያ ድንቅ ጨዋታ ጋር አሸንፎ ሙኒክ ላይ ለሚደረገው ፍጻሜ ያለፈበት ነው።

ወንድማማቾቹ በቀጣይ አመት በሴሪ ኤው እርስ በርስ የሚያደርጉት ፍልሚያ የሚጠበቅም ይሆናል።

በአንተነህ ሲሳይ
ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሩሲያ የድል በዓል የአቀባበል ስነ-ስርዓት ላይ ተሳተፉ
*************

ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በ80ኛው የሩሲያ የድል በዓል ለሚሳተፉ የሀገራት መሪዎች ማምሻውን በክሬምሊን ቤተ-መንግስት በተካሄደው የአቀባበል እና የእራት ግብዣ ስነ-ስርዓት ላይ ተሳትፈዋል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በድል ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ለመጡ የሀገራት መሪዎች አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃቱን ተከትሎ በተለይም ደግሞ የቀድሞው ሶቪየት ኅብረት ጦር የተቀዳጀውን ድል በማሰብ ነገ በሩሲያ መዲና ሞስኮ ለ80ኛ ጊዜ በዓሉ ይከበራል።

የድል በዓሉ ለሩሲያ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ክብረ-በዓል ነው።

በነገው የአከባበር ስነ-ስርዓት በሞስኮ የቀይ አደባባይ የሚካሄደውን ከፍተኛ ወታደራዊ ትርኢት ጨምሮ ሌሎች መርሃ ግብሮች ይከናወናሉ።

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ተተኪው የሮማ ካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መመረጡን የሚያስታውቀው ነጭ ጭስ ታየ
***********

በቫቲካን እየተካሄደ ባለው የሮማ ካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ ነጭ ጭስ በመታየቱ የሮማ ካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መመረጡ ታውቋል፡፡

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡት ምዕመናንም ደስታቸውን እየገለፁ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ካርዲናል አባ ብርሃነ ኢየሱስን ጨምሮ 133 ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ካርዲናሎች በምርጫው ላይ እየተሳተፉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
08.05.202511:27
ፒ ኤስ ጂ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋገጠ

****

በፓርክ ደፕሪንስ አርሰናልን የገጠመው ፒ ኤስ ጂ 2 ለ1 አሸንፏል፡፡

ዮሴፍ ሹምዬ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202507:36
ሩሲያ በልዩ ሁኔታ የምታከብረው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የድል ቀን ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን ንግግር አድርገዋል

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
09.05.202506:14
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ እና ለበርካታ የዓለም መሪዎች በክሬምሊን ቤተመንግሥት ያደረጉት የአቀባበልና የእራት ግብዣ መርሐ-ግብር

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የዓለም ሰላም ድልድይ እንድትሆን እሰራለሁ - ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ
***************

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የዓለም ሰላም ድልድይ እንድትሆን እሰራለሁ ሲሉ አዲሱ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከምርጫው መጠናቀቅ በኋላ ለምዕመናኑ ባደረጉት ንግግር፣ "እግዚአብሔር ሁላችንንም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይወደናል" ብለዋል፡፡

"ሰብአዊነት ክርስቶስ ጋር ለመድረስ እንደ ድልድይ ነው፤ እግዚአብሔር ጋር ለመድረስ ሰብአዊነትን እንደ ድልድይ መጠቀም ያስፈልጋል፤ እርስ በርሳችንም እንረዳዳ፤ ድልድዮቻችንንም እንምረጥ" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ኃላፊነታቸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የዓለም ሰላም ድልድይ እንድትሆን እንደሚሠሩም ጠቅሰዋል፡፡

በለሚ ታደሰ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ከአንድ ሔክታር የሚገኝ ምርትን በ2 ነጥብ 7 እጥፍ የሚያሳድግ ዘዴ
**************


አዲሱ ዳጌ ይባላል፤ በሆሳዕና ሊችአምባ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን አነስተኛ ቦታ ላይ ከፍተኛ ምርት የሚያስገኘውን ዘዴ - (Vertical gardening) ተጠቅሞ አቮካዶ፣ ቡና፣ ሙዝ እና እንሰትን የመሳሰሉ ምርቶችን እያለማ ይገኛል።

ከአነዚህ በተጨማሪም ሰላጣ፣ ቆስጣ፣ ካሮት እና ጎመንን በስፋት ያመርታል።

ዘዴው ቦታን እና ጊዜን የሚቆጥብ ስለመሆኑ የሚናገረው ወጣት አዲሱ፣ ማንኛውም ሰው ከ2 ካሬ ጀምሮ ባለው ክፍት ቦታ ላይ የምግብ ፍጆታውን ከማሟላት ባለፈ ገቢውን ሊያሳድግበት የሚችል ቴክኖሎጂ ስለመሆኑ ገልጿል።

ከአንድ ሔክታር መሬት የሚገኝ ምርትን በ2 ነጥብ 7 እጥፍ የሚያሳድገው ዘዴ የምርት ጥራትን እንደሚጨምር እና በአጭር ጊዜያት ውጤታማ የሚያደርግ መሆኑንም አብራርቷል።

ለማሳያነት በመደበኛ የግብርና ሥራ በአንድ ሔክታር መሬት 60 ኩንታል ወይንም 6 ሺህ ኪሎ ግራም ሽንኩርት ማልማት እንደሚቻል ተናግሯል።

በዚህ ዘዴ ግን 160 ኩንታል ወይም 16 ሺህ ኪሎ ግራም ምርትን ምርት ማምረት እንደሚቻል ነው የገለጸው።

ወጣቱ ከኢቲቪ ጋር ያደረገውን ቆይታ በነገው የአዲስ ቀን ዝግጅታችን ይቀርባል።

በአሸናፊ እንዳለ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
የፑቲን አጋር
******
የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ
አቀባበል በሞስኮ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
08.05.202507:03
አዲስ ሊቀጳጳስ መመረጡ የሚበሰርበት ነጭ ጭስ በቫቲካን ታይቷል

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
08.05.202513:33
ሻምፒዮኑን  አሰናብቶ  ከሻምፒዮንሱ የተሰናበተው አርሰናል

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
በላምበርጊኒ ሞዴል መኪና የሠራው የሻሸመኔው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪ
*******************


የሻሸመኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪው የሆነው አወል አመጂ በላምበርጊኒ ሞዴል የመዝናኛ መኪና ሠርቷል።

ተማሪው የሠራት መኪና ሁለት ሰው መያዝ የምትችል እንዱሁም የላይኛው ጣሪያዋ እንደ አስፈላጊነቱ የሚከፈት እና የሚዘጋ የመዝናኛ መኪና ናት።

መኪናዋን የሠራት የላምበርጊኒን ሞዴል በማየት እና የራሱን ሐሳብ ጨምሮበት እንደሆነ ይናገራል።

አወል መኪናዋን የሠራት ከአከባቢው ካገኛቸው እና ከገዛቸው ቁሳቁሶች ሲሆን መኪናዋን ሠርቶ ለማጠናቀቅም አንድ ወር ፈጅቶበታል።

መኪናዋ ብዙ ነዳጅ አትፈልግም ያለው አወል፣ በ60 ኪሎ ሜትር 2 ሊትር ቤንዚን ብቻ እንድትጠቀም አድርጌያታለው ይላል።

የተማሪው የፈጠራ ውጤት የሆነችው ይህቺ መኪና ሙሉ ለሙሉ ተሠርታ ስትጠናቀቅ በሯ ያለ ሰው ንክኪ በራሱ እንደሚከፈት አወል ተናግሯል።

በሴራን ታደሰ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
08.05.202507:02
ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ
********************

በኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት ከአሰልጣኞች አስከ ስመ ጥር የእግር ኳስ ኮከቦች ወደ ፓሪሱ ቤት ቢኮበልሉም የሚፈለገው የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሊመጣ አልቻለም።

ኔይማርን ከባርሴሎና፤ ኪልያን ምባፔን ከሞናኮ ያስፈረሙት ፒኤስጂዎች በተለይ በኪልያን ምባፔ ላይ ጥገኛ የሆነ ቡድን የተለያዩ አሰልጣኞች ሰርተዋል።

የኪልያን ምባፔ ልብ በተደጋጋሚ ወደ ሌሎች የአውሮፓ ክለቦች ሲያማትር፤ ፒኤስጂ ምባፔን በእጅ መንሻነት በአውሮፓ ከፍተኛው ተከፋይ አድርጎት እንዲጫወትለት አግባብቶት ነበር።

በእርግጥ ምባፔ በፒኤስጂ ቤት አሰልጣኞች ሲቀያየሩ አቋሙ ሳይለዋወጥ የክለቡን ግብ የማስቆጠር ሀላፊነት በብቃት ሲወጣ ቢቆይም፤ በአውሮፓ መድረክ ከፒኤስጂ ጋር ውጤታማ መሆን አልቻለም።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን ሲቀላቀል በብዙ ምክንያቶች የፓሪሱ ክለብ ይጎዳል ተብሎ ነበር።

በአንድ በኩል፥ በርካታ ሚሊዮን ፓውንዶች ለምባፔ ሲከፍል የነበረው ፒኤስጂ ተጫዋቹ በነፃ ዝውውር ማድሪድን ሲቀላቀል በፋይናስ በኩል ተጎጂ ነበር።

በሌላ በኩል፥ ምባፔ ላይ ጥገኛ የነበረው ፒኤስጂ እንዴት ያለ እርሱ መጫወት ይችላል የሚለው አሳሳቢው ጉዳይ ነበር።

ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ማፈላለግ ላይ የቆዩት ስፔናዊው ታክቲሺያን ሊዊስ ኤኔሪኬ ምባፔን ተጠባባቂ በማድረግ ጨዋታዎችን ያለ ምባፔ ለመጫወት ሞክረዋል።

ይህ ጥረታቸው ፍሬ አፍርቶ ምባፔ ማድሪድን ቢቀላቀልም በወጣቶች የተገነባ ውብ እግር ኳስን የሚጫወት ቡድን ገንብተዋል።

ፒኤስጂ የፈረንሣይ ሊግ ‘ኧ’ን ገና በጊዜ ነበር ማሸነፉን ያረጋገጠው። በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ደግሞ የእንግሊዞቹን ሊቨርፑል፣ አስቶንቪላ እና አርሰናልን በማሸነፍ ለሙኒኩ ፍፃሜ ደርሷል።

ኪልያን ምባፔ በሩብ ፍፃሜው ከማድሪድ ጋር በአርሰናል 5 ለ 1 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሲሆን፤ የቀድሞ ክለቡ አርሰናልን በደርሶ መልስ 3 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ፍፃሜው አልፏል።

ፒኤስጂ ያለ ኪልያን ምባፔ የሚናፍቀውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያሳካው ይሆን? ከኢንተር ሚላን ጋር በአልያንዝ አሬና የሚደረገው ጨዋታ ለዚህ መልስ ይኖረዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ
Көрсөтүлдү 1 - 24 ичинде 1 605
Көбүрөөк функцияларды ачуу үчүн кириңиз.