Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™ avatar
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™ avatar
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™
ሃላፊነት ውሰዱ!
➡️➡️🗣️🗣️
ህይወት አጭር ነች። እጥረቷም አንድም በማይቀየሩ ሁነኛ ለማዶች ስለተሞላች ነው። በእያንዳንዱ ቀናት የምናዘወትራቸው ጠቃሚም ሆኑ ጎጂ ልማዶች የህይወታችን ነፀብራቆች ናቸው። ውጤታማነትን የሚጠላ ማንም የለም፤ ስኬትን የማይመኝ ማንም አይኖርም። ነገር ግን ምኞትና ፍላጎት ብቻውን ስኬታማና ውጤታማ ሊያደርገን አይችልም። ይልቅ ወደ ተግባር በመግባት ስኬታማ የሚያደርጉንን ምርጥ ልማዶች ማዳበር ይኖርብናል። እነዚህን ልማዶች ለመፍጠር የሚከተሉትን መርሆች እንዳቅማችሁ ተግብሩ።

1. የህይወት አላማችሁን በግልፅ አስቀምጡ

በህይወታችሁ ትልቅ ዋጋ የምትሰጡት ነገር ምንድነው? ሳታሳኩት ማለፍ የማትፈልጉት ነገር ምንድነው? ህይወትን እየኖራችሁ እንደሆነ እንዲሰማችሁ የሚያደርጋችሁ ወሳኝ ነገር ምንድነው? አላማ ሲኖራችሁ ያንን አላማ ለማሳካት የሚጠቅማችሁን ልማድ ለመፍጠር አትቸገሩም። ልማድ ተደጋጋሚ እንደመሆኑ መጠን ጠንካራ አላማ ከኋላው ካለ ውጤታማ የሚያደርጋችሁ ልማድ የመፈጠሩ ጉዳይ አጠያያቂ አይሆንም።

2. ቅድመተከተል አስቀምጡ

በተመሳሳይ ሰዓት ብዙ ነገር መሞከር አቁሙ። በዋናነት ከአላማችሁ ጋር የሚሔደው ተግባር ምንድነው? የግል ችሎታችሁን ለማዳበር የሚጠቅማችሁ ስራ ምንድነው? ምኞታችሁን ለማሳካት የሚቀላችሁና አስደሳቹ መንገድ የትኛው ነው? ማዳበር ለምትፈልጉት ልማድ ቅድመተከተል አስቀምጡ። በጣም አስፈላጊ፣ አስፈላጊ፣ በጥቂቱ አስፈላጊና አላስፈላጊ በማለት የአሁን ተግባሮቻችሁንና ወደፊት ማዳበር የምትፈልጉትን ልማዶች በዝርዝር አስቀምጡ። በቅድመተከተሉ መሰረትም ወደ ተግባር ግቡ።

3. አካባቢያችሁን አፅዱ

ውጤታማ ለመሆን አካባቢያችሁን የምታፀዱት ከቆሻሻ ብቻ አይደለም፤ በዋናነት ከሚረብሿችሁና ትኩረታችሁን መሰብሰብ እንዳትችሉ ከሚያደርጓችሁ ነገሮች ነው። ይህም ፅዳት በስራችሁ ወቅት ስልክ ማጥፋት አልያም notification off ማድረግ፣ ኢንተርኔት መዝጋት፣ ቲቪ ማጥፋትና የመሳሰሉትን ማድረግ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም ሊረብሻችሁ የሚችልን ነገር ከዙሪያችሁ አስወግዱ፤ ትኩረታችሁን መስራት የምትፈልጉት አንድ ነገር ላይ ብቻ አድርጉ።

4. ሃላፊነት ውሰዱ 

የምትፈጥሩት ልማድ በዋናነት የሚጠቅመው ለእራሳችሁ እንደሆነ በሚገባ እመኑ። ይህን ልማድ በመገንባት ውስጥም ለምታጡት ነገር ሃላፊነት ውሰዱ፣ ለምታመጡት አመርቂ ውጤትም እራሳችሁን አበረታቱ። አዲስ ውጤታማ የሚያደርግ ልማድ በባዶ የሚገነባ አይደለም። ማጣት ያለባችሁን ጊዜያዊ ደስታ ለማጣት ወስኑ፤ ከጊዜ ቦሃላ ለሚመጣው የላቀ ስኬትና ውጤትም ዋጋ ለመክፈል እራሳችሁን አሳምኑ።

ጥሩ ውጤት ስራን፣ ስኬትም ልባዊ ጥረትን ከማያቋርጥ ትጋት ጋር ይፈልጋል። ህይወታችሁን አንድ እርምጃ ወደፊት ፈቀቅ ለማድረግ ከአላማችሁ ጋር የሚሔድን ጥሩ ልማድ ፍጠሩ፣ እለት እለት እያደረጋችሁት እንዲሰራችሁ ፍቀዱ። በእርግጠኝነት ልማዳችሁ ለተሻለ ስፍራ እንደሚያበቃችሁ እመኑ። በባዶ ሜዳ አትብከኑ፣ ሁሉንም እየነካካችሁ እራካታ የሌለው ህይወት መኖር አቁሙ። በውጤታማ ልማዶች ህይወታችሁን አቅጣጫ አስይዙት፤ ወደፊታችሁን ዛሬ መገንባት ጀምሩ።
ሰናይ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
01.05.202518:58
ፈጣሪያችንን እናስብ!
➡️➡️➡️🗣️🗣️
ነፍሳችን ሰላምን ትሻለች፣ ውስጣችን መረጋጋትን ይመኛል፣ ስሜታችን ሃይባይ ያስፈልገዋል። እንዳሻቸው የሚነዱንም ሆነ አንዳሻን የምንነዳ ግኡዛን አይደለንም። ፈጣሪያችን በጥበቡ የሰራን የእጆቹ ድንቅ ስራዎች ነን። መንፈሱ በውስጣችን ይመላለሳል፣ ከእርሱ የሚታደለን በረከት የሰላማችን ምንጭ ነው፣ መረጋጋታችን፣ እረፍታችን አፅናኝ ቃሉ ነው። ተስፋ ብታጡ እንኳን በእግዚአብሔር አምላካችሁ ተስፋ አትቁረጡ፣ በህይወት አቀበት ቁልቁለት ብትፈተኑ እንኳን እርሱን ተስፋ ማድረጋችሁን እንዳታቆሙ፣ ደክማችሁ፣ ዝላችሁ፣ ውስጣችሁ ታክቶ ብትገቡ እንኳን ወደ አምላካችሁ ለመጠጋት አትስነፉ። ምድር መኖሪያችን ብትሆን፣ ህይወት ፈተናችን ቢሆን እረፍትና ሰላማችን እግዚአብሔር አምላክ ሁሌም ከጎናችን አለ።

አዎ! ጀግናዬ..! ፈጣሪያችንን እናስብ፤ ሃልዎቱን ውስጣችን እናስገባ፣ በስሙ እንድን ዘንድ፣ በፀጋው እንታነፅ ዘንድ ከልባችን እናስገባው። ምን ለማድረግ ምን እስኪታያችሁ ትጠብቃላችሁ? ምንስ ለማትረፍ ምናችሁን አሳላፋችሁ ትሰጣላችሁ? የጨለመ ዘመን ተስፋ ላይኖረው ይችላል እግዚአብሔር ባለበት ግን ከብረሃን በቀር ጨለማ ሊኖር አይችልም። ማልቀስ ካለባችሁ ለሰው ሳይሆን ለፈጣሪያችሁ አልቅሱ፣ መታደስ ካለባችሁ በምድራዊ ጌጣጌጥ ሳይሆን በአምላካችሁ ህያው ቃል ታደሱ፣ እራሳችሁን ማበርታት፣ ከችግራችሁ በላይ መሆን፣ ለሃገር ለወገን መትረፍ ከፈለጋችሁም እምነታችሁን አጠንክሩ፣ ብሩህ ተስፋን ሰንቁ።

አዎ! አለም የምታድነን ይመስል አለም ላይ ብንጣበቅ፣ ሰው ይታደግን ይመስል በሰው ብንታመን፣ የዛሬ ዝናና ንብረታችን ዘላለማዊ ይመስል በእርሱ ብንመካ  መጨረሻችን መና፣ አወዳደቃችንም የከፋ ይሆናል። "ለደስታዬ ሁሉን አድርጌያለሁ፣ ስኬታማ ለመሆን የሚጠበቅብኝን ሃላፊነት በሙሉ ተወጥቼያለሁ፣ ውስጤን ለማሳረፍ መሔድ ያለብኝ ቦታ ሁሉ ሄጄያለሁ።" ልትሉ ትችላላችሁ። ነገር ግን ያጣችሁትን አንድ ወሳኝ ነገር አስታውሱ። እግዚአብሔር ያልታከለበት የደስታ ፍለጋ፣ አምላክ ያልፈቀደው የስኬት ጉዞ፣ በፈጣሪ ያልተመራ የውስጣዊ ሰላም ዳሰሳ በምንም በማንም ቢከናወን ሙሉ ሊሆን አይችልም፣ የሚያሳርፍና አስደሳች ሊሆን አይቻለውም። ብክነታችሁን ቀንሱ ከፈጣሪያችሁ ጋር ግንኙነታችሁን አጥቁ፣ ለሰላማችሁ ቁሙ፣ እውነተኛውን ውስጣዊ ሰላም ከልባችሁ አጣጥሙ፣ ከድካማችሁ ለማረፍ ከአምላካችሁ እቅፍ ተጣበቁ።
የሰላም ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
28.04.202518:26
እራሳችሁን ተረዱ!
➡️➡️➡️🗣️🗣️
የትኛውም ግንኙነት ስጦታ ቢሆንም መልካምና መጥፎ ስጦታ የሚሆንበት ጊዜ ግን አለ። በፍቅር ህይወት ጉዳትና ህመም መኖሩ ግንኙነቱን መጥፎ ቢያደርገውም አጠቃላይ የፍቅርን እይታ ግን ሊያበላሸው አይችልም። ገና ለገና እጎዳለሁ እያላችሁ ፍቅርን አትሽሹ፣ ገና ለገና ዋጋ ያስከፍለኛል፣ ነፃነቴን ይሻማል፣ ህልሜን እንዳልኖር ያደርገኛል ብላችሁ ለብቻችሁ መሆንን አታዘውትሩ። በቀደመ ህይወታችሁ ብትጎዱም፣ ያለፈ ታሪካችሁ የደበዘዘ ቢሆንም ዛሬ ግን ከጉዳታችሁ በማገገም፣ እራሳችሁን በማብቃትና የተሻለ ሰው በመሆን ካለፈው ታሪክ የተለየ ታሪክ መፃፍ፣ ጉዳታችሁን ለመልካም መጠቀም ትችላላችሁ። በህይወታችሁ የምትመሩበት መርህ አስቀምጡ። መርሃችሁ እናንተ ላይ እየሰራ በሂደት እንዲሰራችሁ ፍቀዱ።

አዎ! ከእውነታው ከመታገላችሁ በፊት እራሳችሁን ተረዱ፤ የልብ መሻታችሁን ከመግፋታችሁ በፊት ለምን እንደምትገፉት እወቁ። ብዙዎች በአጥፊነት ቢቆሙም ጥቂቶችም በአልሚነት ተርታ መመደባቸው አይቀርም፤ አንዳንዶች ደጋግመው ቢበድሉም አንዳንዶች በደልን ለመሻር፣ ህመምን ለማከም የሚጥሩ ይኖራሉ። ሰው ያቆሰለውን ልብ ፈጣሪ በሰው ይፈውሰዋል። ያለፈ ታሪክና ህመም ይቅርና እግረመንገዳችሁን የምታገኙት ሰው ትልቅ የህይወት ትምህርት ያስተምራችኋል። እይታችሁን በአቅማችሁ ገድቡት፣ የሚያውካችሁ አጉል የተበዳይነት ስሜት ከውስጣችሁ አስወጡ፤ የእናንተ ህይወት የናንተ ስለመሆኑ እየኖራችሁ አሳዩ።

አዎ! ውድድሩን አቁሙና ለእራሳችሁ ውለታ መዋል ጀምሩ፤ ከንፅፅር ውጡና እራሳችሁን መረዳት ላይ አተኩሩ፤ የደረሰባችሁን በደል መተንተን ተውና ለአዲስ ህይወት እራሳችሁን አዘጋጁ። የገዛ ጉዟችሁ እንቅፋት አትሁኑ፤ እያወቃችሁ ህይወታችሁን ፋታ አትንሱት። ግንኙነታችሁ ምቾት ባይሰጣችሁ ምቾት የመስጠትን ሃላፊነት ውሰዱ፣ ዛሬ ያላችሁበት የህይወት ደረጃ ቢያስጨንቃችሁ ከእርሱ ለመውጣት የምታደርጉትን ጥረት ጨምሩ። ወደፊታችሁ ያምር ዘንድ ታሪካችሁን በመልካሙ መረዳትን ተለማመዱ። ምንም ነገር ቢከሰትባችሁ ቀዳሚው የእናት ህልውና ነው። ከጦርነት የተረፈች ነፍስ የምታተርፈው የጦርነቱን አስከፊነት ደጋግማ ስላወራች ሳይሆን በተሰጣት ሁለተኛ እድል በተሻለ መንገድ ወደአምላኳና የልብ መሻቷ ስትቀርብ ነው። ቢያማችሁም ቻሉትና ጉዳታችሁን ለበጎ ማድረግ ተለማመዱ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
07.04.202519:06
💥📣 መፅሐፍ ከተወደደ አንባቢ ይጠፋል!
ምክንያቱም የመግዛት አቅም የለውምና!!

ይሄን መሰረት በማድረግ
የተለያዩ መፅሐፍ በ Pdf  ድርሰቶች አጫጭር ታሪኮችን የሚያዘጋጅ የቴሌግራም ቻናል
ልጠቁማችሁ!!!

ስሙ እንማር ይሰኛል !!
ቀኖትን እያረመ ማታዎትን እያደመቀ ምርጥ ምርጥ መፅሀፎች ይጋብዛቸዋል ።
100%ትወዱታላችሁ


https://t.me/Enmare1988
https://t.me/Enmare1988
06.04.202508:33
ማንም በሌለበት!
፨፨፨/////////፨፨፨
ማንም የለም፣ ማንም አይጠብቅህም፣ ማንም የምትደገፈው፣ ማንም የምትተማመንበት ሰው የለህም። ለራስህ እውታውን ንገረው። ሰውን ስትጠብቅ የባከኑ ውድ ጊዜህን አስታውስ። ብቻህን የምታደርገው ነገር፣ ለብቻህ የምትወስነው ውሳኔ፣ ማንም ሳያይህ የምታደርገው፣ ለማንም ሰይሆን ለእራስህ ብለህ የምትፈፅመው ጀብድ እርሱ ነው ከመሬት አንስቶ ከፍታ ላይ የሚያስቀምጥህ፣ እርሱ ነው ዋጋህን የሚጨምረው፣ እርሱ ነው የተለየ ሰው የሚያደርግህ። ብችህን ስትሆን ምን ታደርጋለህ? ማንም በሌለበት ደጋግመህ የምታከናውነው ተግባር ምንድነው? ተደብቀህ የት ትሔዳለህ፣ ምን ትሰራለህ? ምንስ ታያለህ?

አዎ! ጀግናዬ..! በዛ በጨለማ ማንም በሌለበት፣ ጠያቂ በማታገኝበት፣ አይዞህ ባይ አበርታች፣ በሃሳብም ሆነ በገንዘብ የሚደግፍህ በሌለህ ሰዓት ምን እያደረክ ነበር? ስለሆነብህ እያማረርክ ወይስ ምሬትህን ለመቀየር ጠንክረህ እየሰራህ? ብቸኝነትህን እየረገምከው ወይስ እራስህን ለመገንባት እንደ መልካም አጋጣሚ እየተጠቀምከው? እድለኛ እንዳልሆንክ እያሰብክ ወይስ ሁኔታውን ለመቀየር እየተፋለምክ? ብቻህን ስትሆን የሚኖርህ ማንነት ያንተ ትክክለኛው ማንነት ነው። አንተና ፈጣሪ ብቻ የምታውቁት የግል ሚስጥርህ ይኖራል። በገባህ ልክ እለት እለት ለብቻህ የምትፋለምለት ሃሳብ ይኖርሃል። "ብቻዬን ነኝ፣ ሰው የለኝም፣ የሚያግዘኝ አላገኘውም፣ የማደርገው ነገር በማንም ተቀባይነት አላገኘው፣ ማንም አላመነበትም።" ብለህ አታቆመውም።

አዎ! ብቻህን ስትሆን ስለምታደርገው እያንዳንዱ ነገር ተጠንቀቅ፣ ማንም በሌለበት ወደአዕምሮህ ስለሚመጣ ሃሳብ ደጋግመህ አስብ። በሰዎች መከበብ ትርፉ መዘናጋት እንደሆነ እወቅ፣ ከዚህም ከዛም በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ ቃላት መዋከብ ትርፉ አጉል መኮፈስ ወይም ተሰብሮ መቅረት እንደሆነ አስታውስ። ከቻልክ ለብቻህ ስለራስህ ጊዜ ሰጥተህ አስብ፣ ስላለህበት ሁኔታ፣ ስለምትፈልገው፣ ስለአላማህ፣ ስለልማድህና ስለግል አቋምህ ጠንቅቀህ መርምር። በመዋከብ ጊዜ አታጥፋ፣ እዚም እዛም እየተገኘህ ዋጋህን አታሳንስ፣ በገዛ ፍቃድህ ብኩን አትሁን። ለራስህ ጊዜ ይኑርህ፣ ትኩረትህን እራስህ ላይ አድርግ፣ አንተ ሳትቀየር ውጪው እንዲቀየር መጠበቅ አቁም፣ ማንም ላይ አንድ ጣትህን ስትቀስር የቀሩት አራቱ ወዳንተ እንደሚያመለክቱ አስተውል። እራስህ ላይ ስራ፣ እራስህን አሻሽል የቀረው በጊዜው እንዲስተካከል ተወው።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
04.04.202518:02
እራስህን ገንባ!
፨፨፨//////፨፨፨
"ሌሎች ያላደረጉት ነገር አያሳስብህ።
ዋጋ ያለው አንተ የምታደርገው ነው።"
-Napoleon Hill

ብዙ ጊዜ የምትመለከታቸው ሰዎች የተግባር ሰዎች ላይሆኑ ይችላሉ፣ አካባቢህ ከስራ ወሬን በሚያስበልጡ ሰዎች ሊሞላ ይችላል፣ ያንተን ህይወት በእነርሱ ስንፍና ትለካውም ይሆናል ነገር ግን ሌሎች ያላደረጉት ነገር እኔም ባደረግው ለውጥ አያመጣም ከሚለው እሳቤ ውጣ። እነርሱ ስላላደረጉት ያጡት ነገር ይኖራል፣ እነርሱ የተግባር ሰው ባለመሆናቸው፣ ዋጋ ለመክፈል ባለመድፈራቸው፣ አደጋን በመፍራታቸው ምን እንደጎደላቸው አስተውል። ስኬቱንም ሆነ ውድቀቱን በቅርብህ ካሉ ሰዎች የምትማር ከሆነ ትርጉም ያለው ህይወት የማትኖርበት ምክንያት የለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ማንም ያመነበትን ያደርጋል፤ አንተም እንዲሁ። ከማቀድ አለማቀድን፣ ካማድረግ አለማድረግን፣ ከመጀመር አለመጀመርን፣ ከመጨረስም አለመጨረስን ከሚመርጡ ሰዎች እራስህን ነጥል። የእነርሱ አለማድረግ፣ የእነርሱ አለመቀየር፣ የእነርሱ አዲስ ነገር አለመፍጠር፣ የእነርሱ ባሉበት መቆየት አንተን አያሳስብህ፤ ባንተ ህይወት ላይ አንዳች ነገር የሚጨምረው፦ የእነርሱ አለማድረግ ሳይሆን ያንተ ተሽሎ አድርጎ መገኘት ነው፤ የእነርሱ ጀምሮ ማቆም ሳይሆን ያንተ ጀምሮ መጨረስ ነው፤ የእነርሱ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ያንተ በተስፋ መሞላት ነው፤ የእነርሱ በስንፍና መመላለስ ሳይሆን ያንተ በጥንካሬ መንቀሳቀስ ነው።

አዎ! ማንን እንደምትከተል ጠንቅቀህ እወቅ፣ በማን መርህ፣ በማን አቋም እንደምትመራ በሚገባ ለይ። በቅርበት የምታገኛቸው ሰዎች በራሳቸው መንገድ ይሰሩሃል፣ ረጅም ጊዜ አብረሃቸው የምታሳልፈው ሰዎች የህይወትህ መሪዎች ናቸው። ቁብነገር ያለው፣ ዋጋህን የሚጨምር፣ በለውጥና በእድገት የተቃኘ ህይወት ለመኖር ጥራት ያላቸው ብርቱና ጠንካራ ሰዎች ያስፈልጉሃል። ስለሃገሪቷ ተስፋ ማጣት እያወሩ ተስፋቢስ ከሚያደርጉህ፣ ስለስራቸው አለማስደሰት እየተነተኑ ለስራህ ያለህን ጥሩ አመለካከት ከሚቀይሩ፣ ተምረው ከማያስተምሩህ፣ ለራሳቸው ዋጋ ሰጥተው ያንተንም ዋጋ ከማይጨምሩ ሰዎች ራቅ፣ በተገነባ አካባቢ ውስጥም እራስህን ገንባ
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
07.05.202516:02
📣💥 ለሰው ርካሽ አትሁኑ!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/-FCbDxKmOn0?si=yi7HpBb3sXYL5xCx
30.04.202518:41
🔴💥 ደግ መሆን አቁሙ!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/Mkgk-vfs_vU
28.04.202517:18
🔴💥 ዋጋቹን በእጥፍ የመጨመር ድብቅ ጥበብ!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/d5jKZpIAWi4
07.04.202518:31
በስራህ አሳርፋቸው!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
በህይወትህ ሁለት ሰዎችን አትርሳ፣ በዘመንህ ሁሉ ሁለት ሰዎችን ችላ አትበል፣ በህይወት እስካለህ ለሁለት ሰዎች ፊትህን አታዙር፣ በእድሜህ ሁለት ሰዎች እንዲያዝኑብህ አታድርግ። አንዱ አንተ ታሸንፍ ዘንድ፣ አንተ ቀና ብለህ ትራመድ ዘንድ፣ አንተ ደረትህን እንድትነፋ፣ ከፍ ብለህ እንድትታይ፣ ከጓደኞችህ እንዳታንስ ሁሉ ነገሩን መሱዓት ያደረገው አባትህ ነው። ሁለት በህመምህ ወቅት፣ በችግርህ ጊዜ፣ ሰው በራቀህ፣ ወዳጅ ባጣህ ሰዓት አይዞህ ልጄ የምትልህን፣ የማያልቀውን ንፁ ፍቅሯን የምትመግብህን፣ ሁሌም እንደ ስስት ልጇ የምትመለከትህ እናትህ ነች። ማናችንም አንዴ ከሚሰጡን ቤተሰቦች በቀር ሌላ የለንም፣ አባት አንድ ነው እናትም አንድ ነች። በህይወት እያሉ ሊከበሩና ሊኮሩብን ይገባል። ምናልባት ከእኛ እርዳታን ላይፈልጉ ይችላሉ የእኛ እራስን ችሎ ጥሩ ቦታ መገኘት ግን ትልቁ ደስታቸው ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! በስራህ አሳርፋቸው፣ አኩራቸው፣ ባንተ ደስ ይበላቸው፣ በምግባርህ፣ በማንነትህ ስማቸውን አስጠራ። ይኑራቸው አይኑራቸው፣ ያግኙ ይጡ፣ ይንደላቀቁ ይቸገሩ ቤተሰቦቻችን ሁሌም ቤተሰቦቻችን ናቸው፤ ስጋ ሁሌም ሰጋ ነው። ምንም ቢሆኑ ወደዚህ ዓለም የመምጫ መንገዳችን ናቸው። ማንም ቤተሰቡን መርጦ አልተወለደም፤ ማንም ፈልጎ ከቤተሰቡ አልተቀላቀለም። የመረጠልን የሚወደን ፈጣሪያችን እግዚአብሔር አምላክ ነው። ምንም እንኳን ነገሮች ሁሉ ባይመቹን፣ ምንም ያደረጉልን ነገር በቂ አይደለም ብለን ብናስብ፣ ምንም እንኳን ብዙ ነገር ፈልገን ባናገኝባቸው ቤተሰቦች ግን መቼም በልጆቻቸው ምክንያት እንዲሰበሩና ተስፋ እንዲቆርጡ ማድረግ አይገባም። ልጅ በረከት ነው፣ ልጅ ፀጋ ነው።

አዎ! አንደኛው ትልቁ መቼም በጀመርከው መንገድ ተስፋ የማትቆርጥበት ምክንያት፣ ለፈተናዎችህ እጅ የማትሰጥበት፣ እለት እለት የምትደክምበት፣ ሁሌም ሳትሰለች የምትደክምበት ምክንያት የቤተሰቦችህ ኩራትና ደስታ ነው። በአጭሩ ህይወት ለሚወዱት ሰው ብሎ አሸንፎ መገኘትን ትፈልጋለች። በድህነት ተቸግረው ላሳደጉህ ቤተሰቦችህ የመድረስ ግዴታ አለብህ፣ ላንተ ለዛሬ መብቃት ዋጋ የከፈሉ ሰዎችን የማስታወስ ሃላፊነት አለብህ። በተራብን ሰዓት ያጎረሱንን፣ በተጠማን ወቅት ያጠጡን፣ በለቅሷችን ጊዜ እንባችንን የጠረጉልንን እጆች አንረሳም፤ በከፋን፣ ሆድ በባሰን፣ ሰው ባጣን፣ በተሰበርን ሰዓት ከጎናችን የቆሙትን፣ አይዟችሁ ያሉንን ሰዎች በፍፁም ችላ አንልም። ማናችንም ዛሬ ላለንበት ለመድረሳችን እያንዳንዱ ወደ ህይወታችን የገባ ሰው የእራሱን አስተዋፅዖ አድርጓልና የትናንት ወዳጆቻችሁን አትርሱ፣ ውለታቸውን ባትመልሱ ውለታቸውን መስክሩ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
04.04.202507:49
አንድ ነገር ከመጀመራችሁ በፊት!
፨፨፨፨፨፨///////////////፨፨፨፨፨፨
ከማንኛውም ሰው ጋር ባላችሁ ንክኪ ሊያሳባችሁና ጥንቃቄ ልትወስዱ የሚገባችሁ ነገር ቢኖር የአጀማመራችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ሁኔታው የንግድ አጋርነት፣ የፍቅር ግንኙነት፣ ትዳር፣ የስራ ሁኔታም ሆነ ሌላ ማሕበራ ጉዳይ፣ የትክክለኛ አጀማመርን ሕግ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት አንድን ነገር የጀመርንበት ሁኔታ በቀጣይነቱና በአጨራረሱ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ስላለው ነው፡፡

አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት . . . 

1. ከፍጻሜው ተነሱ
ከፍጻሜው መነሳት ማለት የምትጀምሩትን ነገር እስከወዲያኛው በማሰብ ወደየት ልትወስዱት እንደምትፈልጉ፣ ምን ያህል ርቀት እንዲሄድ እንደምትፈልጉና ከነገሩ ምን ውጤት እንደምትጠብቁ በሚገባ በማሰብ መጀመር ማለት ነው፡፡ የቅርብ እይታ፣ አጭርና ስንኩል ጉዞን ይፈጥራል፤ ረጅም እይታ ደግሞ ረጅምና ስኬታማ ጉዞን ይሰጠናል፡፡

2. የመነሻ ሃሳባችሁን አስተካክሉ
የመነሻ ሃሳብን ማስተካከል ማለት ከአንድ ሰው ጋር አንድን ነገር ስትጀምሩ ያንን ነገር ለምን ለመጀመር እንደፈለጋችሁ የመነሻ ሃሳባችሁን ለይታችሁ በማወቅ ሃሳቡ ጤናማና ትክክለኛ መሆኑን ማወቅ ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር የምትጀምሩት ለማይሆንና ለተዛባ ምክንያት ከሆነ ጅማሬው ላይ ምንም ያህል ተለሳልሳችሁና ተግባብታችሁ ብትቀራረቡም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መበላሸቱ አይቀርም፡፡

3. የሚጠበቀውን ነገር ግልጽ አድርጉ
የሚጠበቀውን ነገር (Expectations) ግልጽ ማድረግ ማለት እናንተ ከሰዎቹ የምትጠብቁትን፣ እነሱ ደግሞ ከእናንተ የሚጠብቁትን ነገር በግለጽ መነጋገርና የጋራ ግንዛቤና ተግባቦት መፍጠር ማለት ነው፡፡ ትልቁ የሕብረተሰባችን አለመግባባትና መንስኤው አንዱ ከሌላው ምን እንደሚጠብቅ በግልጽ ከመነጋገር ይልቅ ሁኔታውን በስሜት ጀምሮ እግረ-መንገድ እየፈጠሩና ግራ እየተጋቡ የመሄድ ጉዳይ ነው፡፡
ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
06.05.202516:42
📣💥 ዘወትር ከመኝታ በፊት አዳምጡት!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/yHfm0fYihtM
29.04.202518:33
🔴💥 ብቸኝነት ሲሰማችሁ አዳምጡት!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/0-354lJWT_c?si=4zxq1jZxpWLgVaJs
27.04.202518:25
አያውቁህም!
➡️➡️🗣️🗣️
ያውቁኛል ብለህ የምታስባቸው አያውቁህም አትልፋ፣ እነርሱ ላንተ ህይወት ግድ የላችውም አትጨነቅ፣ እንደማንኛውም ሰው የእራሳቸው ችግር አለባቸውና ያንተ ጉዳይ ምናቸውም አይደለምና አትሸበር። ጉዞ በጀመርክ ማግስት ይፋ የምትወጣ፣ ለትቺት የምትጋለጥና ብዙ ተከታይ የምታፈራ አይምሰልህ። የግል ጉዞ የሚጀምረው በተጓዡ ደጋፊነትና በደጋፊው ተጓዥነት መሆኑን አትርሳ። ለብዙዎች የማትታይ፣ ትኩረት ሰጥቶ ለሚመለከታት እንጂ የማትገለጥ  ትንሽዬ ችግኝ በጊዜ ብዛን ጎልታ ትታያለች፣ ለብዙዎች ፍሬ ትሰጣለች እንደመጠለያም ታገለግላለች። አለም ስታብብ የሚታያቸው ጥቂቶች ናቸው፣ አለም ስትጠፋ የሚታያቸው ግን ብዙ ናቸው። ተዓምራት በእጅህ ላይ ቢገለጥ፣ ማንነትህ በድንቅ ተግባር ቢታጀብ ሰው ማየት የሚፈልገውን ያያልና ላትታወቅ እንደምትችል አስብ።

አዎ! ጀግናዬ...! አያውቁህም! እንዲረዱህ ብትጠብቅም እነርሱ ግን ከመሰረቱ አያውቁህም፤ ከጎንህ እንዲቆሙ፣ ድጋፍ እንዲሆኑህ ብትመኝም እነርሱ ግን ጉዳያቸውም አይደለም። አወቁኝ አላወቁኝ፣ ተናገሩኝ አትተናገሩኝ፣ ደገፉኝ አልደገፉኝ ሳትል በዚህ ሩጫ በበዛበት አለም ፋታ እየወሰድክ ወደፊት መጓዝህን ቀጥል። ለብዙዎች መቆም መፍትሔ ሊመስላቸው ይችላል፣ ስቃይን እንደመፍትሔ መከራንም እንደ መልካም እድል የሚቆጥሩ ጥቂቶች ግን ትርፋቸው ብዙ፣ ስጦታቸውም የላቀ ነው። የተዘጉ በሮች ምንም ቢዘጉ መከፈቻ መንገድ አያጡም፣ ያንተም ሃሳብ ምንም እንኳን ወደውጭ ባይገፋ፣ ድጋፍ ባይኖረው እስከፈለክ ድረስ ወጥቶ መገለጡ አይቀርም።

አዎ! "እውቅና ለማን ጠቀመ?" ብትል በእርግጥም ከእራሳቸው ኪስ በበለጠ በጎ ለሚሰሩበት፣ ለሚንቀሳቀሱበት፣ ብዙ ነፍሳትን፣ ብዙ ትውልድን ለሚያንፁበት፣ ወገናቸውን ለሚያሳርፉበት፣ ከአምላካቸው ዘንድ በረከትን ለሚታደሉበት ጠቅሟቸዋል። በጊዜው ለሚመጣ እውቅና አትጨነቅ፣ በፍላጎት ከሚደረግ ድጋፍ ብዙ አትጠብቅ። እራስህን እያዳመጥክ ተጓዝ፣ ውስጥህን እያረጋጋህ መንገድህን ቀጥል። የተጓዝከውን መንገድ ታውቀዋለህና የሰመረልህ እለት ብዙ አትደነቅ። የልፋትህ ዋጋ እንደሚከፍልህ ከጅምሩ አውቀህ ተነሳ፣ የጀመርከው መንገድ የምርም እንደሚያዋጣህ ልብህን አሳምነው። በአልታወቅም ተስፋ አትቁረጥ፣ በትኩረት ማጣት ከጉዞህ አትገታ፣ እለት እለት ብርታትህን አስቀጥል።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
07.04.202516:39
🔴 አስፈሪ ሰው ሁኑ!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/4_QLKCtB93I?si=GvE-ymF02uQt38Js
05.04.202518:43
🔴 ከመኝታ በፊት አዳምጡት!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/0TjPTYI3OQk?si=q7DLO_vnCcDMWsR3
03.04.202520:11
⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ✅


የቻናሉ Link👇👇

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
02.05.202518:13
💥 በገንዘብ የማይገዛ ድብቅ ጥበብ!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/oqLmbsa4Txo?si=ZyyK6MBjMekiYcUH
የገባችሁን ኑሩት!
➡️➡️🗣️🗣️
ባለፈው ታሪካችሁ ውስጥ ምን ይታያችኋል ብክነት ወይስ ትርፍ፣ ኩራት ወይስ እፍረት፣ በእራስመተማመን ወይስ ፍረሃት፣ ጥንካሬ ወይስ ስንፍና። የየትኛው ድምፅ ጎልቶ ይታያችኋል? የትኛው በጉልህ ያስተጋባባችኋል? የትኛውስ ይደጋገምባችኋል? የምትሰሙትን ውስጣዊ ድምፅ የማስተካከል ስልጣን እንዳላችሁስ ብታውቁ ዛሬም በስብራትና በህመም፣ በመገፋትና በመጠላት፣ በመሰበርና በፍረሃት ስሜት ውስጥ ታጥራችሁ ባልኖራችሁ ነበር። ህይወት በገባችሁ ልክ ገብቷችኋል ነገር ግን በገባችሁ ልክ እየኖራችሁት እንደሆነ መርምሩ። እርግጠኝነትን ፍለጋ ብዙ ትደክማላችሁ፣ ፍረሃታችሁን ሽሺት ከእራሳችሁ ጋር ድብብቆሽ ትጫወታላችሁ፣ አስተውሎታችሁን ላለመፈተን፣ ጥንካሬያችሁን ላለመግለፅ በየጊዜው ምክንያት ትደረድራላችሁ፣ ሰበብ ታበዛላችሁ፣ ሸክማችሁን ትቆጥራላችሁ፣ በተገደበው የውስንነት እሳቤ ትታሰራላችሁ።

አዎ! የገባችሁን ኑሩት! የተረዳችሁትን በተግባር ግለጡ፣ ያወቃችሁትን አሳውቁ፣ በሚቀላችሁ፣ በምትወዱት፣ በሚያነቃችሁ ዘርፍ እስከመጨረሻው ታገሉ። በተግባራችሁ ህይወታችሁን ማቅለል፣ በእያንዳንዱ እርምጃችሁም የተሻለውን ማንነታችሁን መፍጠር እንደምትችሉ አስታውሱ። ገደብ አልባ ህይወት የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፣ ነፃ ፍቃድ ያደለን ፈጣሪያችን ነው። የሚታየን፣ የምንሰማው፣ የምናስበው ሁሉ እውነት ላይሆን ይችላል ውስጣችን ያለው የአምላካችን መንፈስና ፅኑ ፍላጎታችን ግን እውነት ነው፣ መሰረት አለው፣ የእራሱ ሃይልና ብርታት አለው። እኛ ከምንረዳው በላይ ማንም ሊረዳው አይችልም።

አዎ! ጀግናዬ..! ወደፊትህ በእጅህ ነው፤ የህይወት ትርጉምህ ካንተ የሚመጣ ነው፤ የቀናው መንገድ፣ የምትሰራበት ጉዞ ባንተ ይሁንታ የሚመረጥ ነው። አንዳንድ የህይወት መርህ ላይገባህ ይችላል ነገር ግን የገባህን በገባህ ልክ ኑረው፤ አንዳንድ የአለም አሰራር ሊወሳሰብብህ ይችላል ነገር ግን በእድሜህና በአስተውሎትህ ልክ የተረዳሀው አሰራር ይኖራል። የተወሳሰበብህ እስኪገለጥልህ የተረዳሀውን ተግብር ፈፅም፤ የምትፈልገውን እስክታገኝ ባለህ የምትፈልገውን አድርግ። በፍቃድህ እራስህ ላይ ጫና አታብዛ፣ በምርጫህ የእራስህን ውስብስብ አለም አትፍጠር። የእራስህን ፍቃድ የሚሻ ማንነት በልብህ እንደያዝክ አስለውል፣ ሃሳብና ፍላጎትህ በተግባር ይገለጥ ዘንድ ያንተን ይሁንታ እንደሚጠብቅ ተረዳ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
22.04.202513:29
⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ✅


የቻናሉ Link👇👇

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
06.04.202518:17
ሙከራን ልመዱ!
፨፨፨////////፨፨፨
አዳዲስ ነገሮች ውስጥ ምን አለ? ከፍረሃታችሁ ጀርባ ምን የሚጠብቃችሁ ይመስላችኋል? ሃሳባችሁን እንዴት እውን ማድረግ ትችላላችሁ? ከተስፋና ከእምነት የትኛውን ይበልጥ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ? የአኗኗር ዘይቤ (lifestyle) በራሱ ህይወት ነው። የምንኖረው ህይወት እንደ ልማድ ከምናደርጋቸው ተግባሮች የተለየ አንድምታ የለውም። አብዝተን የምንገኝበት ስፍራ፣ ደጋግመን የምናደርገው ነገር፣ ረጅም ጊዜ አብረናቸው የምናሳልፋቸው ሰዎች፣ ብዙ ሰዓት የምናከናውነው ተግባር ህይወታችን ነው። ማናችንም ብንሆን እግዚአብሔር እስከፈቀደ ድረስ እንኖራለን፣ በፈጣሪ እገዛ ብዙ ከባድ ነገሮችን አልፈናል ወደፊትም እናልፋለን። የእያንዳንዱን የህይወት ስጦታዎች ጠዓም፣ የእያንዳንዱን አዲስ ተግባሮች ክብደት መለካት ደግሞ የሁላችንም ግዴታ ነው።

አዎ! ሙከራን ልመዱ! እራሳችሁን ለአደጋ ማጋለጥ ተለማመዱ፣ ለመውደቅ ደፋር ለመነሳትም ፈጣን ሁኑ። የምትኖሩትን ህይወት ከቁጪት ነፃ አድርጉት። የምንፈልገውን ህይወት ለመኖር በሰዓቱ የማያስደስተንንና የማይመቸንን ተግባር እንደምንወደውና እንደተመቸን አድርገን የመስራት ግዴታ አለብን። እራስን ምቾት መንሳት ደስ አይልም፣ እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ያስፈራል፣ አውቆ እራስን መፈተን ያስጨንቃል ነገር ግን ከዚህ ቀደም ያልተገኘን ውጤት ያስገኛል፣ ከዚህ በፊት ያልተደረሰበት ስፍራ ያደርሳል፣ ታይቶ የማይታወቅ ዓለም ውስጥ ይከታል። አንድ ቦታ ቆማችሁ ከምትጨነቁ ሁሉን በመሞከር እራሳችሁን ግራ አጋቡ፣ በፍረሃታችሁ ታስራችሁ ከምትቀሩ በየደረጃው ፍራሃታችሁን ተጋፈጡት፣ ዘመናችሁን በሙሉ በስጋትና በማንአለብኝነት ከምታሳልፉ ለገዛ ህይወታችሁ ሃላፊነት ውሰዱ። ከእያንዳንዱ የህይወት ክስተቶቻችሁ ስትማሩ፣ ከየትኛውም ችግራችሁ ለመውጣት ስትሞክሩ እግረመንገዳችሁን እራሳችሁን እያሻሻላችሁና የሚያኮራ ማንነትን እየገነባችሁ ትመጣላችሁ።

አዎ! ጀግናዬ..! የበዪ ተመልካች አትሁን ተቀላቅለህ የሚበሉትን ብላ፣ የሚሞክሩትን ሞክር፣ የሚያደርጉትን አድርግ። ባለህበት ቆመህ የሚፈጠር ተዓምር የለም፣ በየአቅጣጫው ተንቀሳቀስ፣ እንዳቅምህ እራስህን ፈትነው፣ ተስፋህን ለመጨበጥ፣ እምነትህን ተግባራዊ ለማድረግ በትንሹ ወደፊት ተራመድ፣ በልክህ ጥረትህን ጨምር። ማድረግ እንደምትችል እያወክ ምንም ነገር ሳታደርገው እንዳያመልጥህ። ሁሉም ቦታ መገኘት፣ ሁሉንም መሞከር  ብክነት ሊሆን ይችላል ነገር ግን በእቅድና በአለማ ሲፈፀም ግን ትልቁ ህይወት ቀያሪ ክስተት ይሆናል። አቅሙ እንዳለህ ታውቃለህ፣ የውስጥህን ፍላጎት ተረድተሃል፣ ምን ስታደርግ ምን እንደምታገኝ ግልፅ ነው። ካልሞከርክ ግን ዛሬም ነገም ውጤት አልባ እውቀት ተሸክመህ ትቀራለህ። ሙከራን የአኗኗር ዘይቤህ አንድ አካል አድርገው፣ አዲስ ነገርን የመጋፈጥን ድፍረት እንደ ግል አቋምህ አራምደው።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
05.04.202510:30
ሰላሜ በዝቷል!
፨፨፨//////፨፨፨
ከራስ ጋር ንግግር፦ "በቀደመው ዘመን አንተ በሌለህበት ህይወት፣ አባትነትህን በሸሸውበት፣ ልጅነቴን በካድኩበት፣ ውለታህን በዘነጋውበት፣ ጥበቃህን ቸል ባልኩበት፣ አብሮነትህን ባልፈለኩበት በዛ ክፉ ዘመን አንተ ያው ሩህሩህ ጌታ ደግ አባት ነበርክ እኔ ግን እኔ አልነበርኩም። መታመኛዬ ዓለም ነበረች፣ መደበቂያዬ ዳንኪራው፣ ሱሱና ክፋቱ ነበር። የሆንኩልህን አላውቅም ያደረክልኝ ግዛ እጅግ ብዙ ነው፣ ያደረኩልህ ምንም ነው ያደረክልኝ ቁጥር ስፍር የለውም። እስከ ጥግ ወደሀኛል፣ እስከመጨረሻው ምረሀኛል፣ በይቅርታህ ጥፋቴን ሽረህልኛል፣ የጠፋው ልጅህን ወደቤትህ መልሰሀኛል፣ ዓለም የናቀችውን፣ ነውር ያረከሰውን፣ ጥፋት መገለጫው የሆነውን ባሪያህን ከከፋው አጥፍቶ ጠፊነት፣ መጨረሻ ከሌለው የስቃይ ህይወት ታድገሀዋል።

አዎ! ባንተ ሰላሜ በዝቷል፣ ባንተ ነፍሴ ተረጋግታለች፣ ባንተ ህይወቴ ሙሉ በርቷል፣ ባንተ ውስጤ ፈክቷል፣ ደምግባቴ ተመልሷል፣ ክብሬ ከፍ ብሏል፣ ባንተ ከድካሜ ሁሉ አረፍኩ፣ እንግልቴ ሁሉ ጠፋ፣ ንፁውን ፍፁም ደስታም ካንተ አገኘውት። አባትነትህ ምነኛ ፍፁም ነው? ርህራሔህ ምነኛ ድንበር አልባ ነው? መውደድህስ ቢሆን ምን ይሆን ገደቡ? ወደህ ፈቅደህ ወደእቅፍህ ጠርተሀኛል፣ ፈልገህ አለኝታ ሆነሀኛል፣ ሳትጠየፈኝ ዝቅ ብለህ አንስተሀኛል። አንድ ዘላለም የምኮራበት ነገር ቢኖር ያንተ የእግዚአብሔር አምላኬ ልጅ በመሆኔ ነው። ማንም በሌለበት በድቅድቁ ጨለማ አልያም በሃሩሩ በረሃ ብገኝ እንኳን አንተ አብረሀኝ እንዳለህ አውቃለሁና አንዳች አልፈራም፣ ፍቅርህ ከልቤ፣ ማዳንህም ከማንነቴ ተዋህዷልና ሁሌም ኩራቴ ነህ፣ ዘወትር መመኪያዬ መጠጊያዬም ነው። እወድህ ዘንድ የማንም ፍቃድ አልሻም፣ አክብሬህ እከብር ዘንድ መርጬህም እመረጥ ዘንድ አንዳች ግፊት አንዳች ግዴታ የለብኝ። አምላኬ እወድሃለሁ፤ አባቴ አከብርሃለሁ።"

አዎ! ጀግናዬ..! ከምድራዊ ህይወት እረፍትን መጠበቅ፣ ከዓለም ንብረትና ዝና እንዲሁ ከደካማው የሰው ልጅ ፍፁም ሰላምን መፈለግ ድክመት ነው። ከአባትህ ቤት መጥፋትህን አስብ፣ ከመገናኛችሁ መራቅህ ይታወቅህ፣ ከበረከቱ መጉደልህ ይግባህ። ስለምን ነገ የሚጠፋውን የዓለም ጌጥ ፍለጋ ያለእረፍት ትደክማለህ? ስለምን ቦሃላ በትሹ በሚሰበረው ሰውነትህ ትመካለህ? ስለምን ጊዜ በሚሰጥህ እግዚአብሔርም ባስረከበህ ስልጣን ልጆቹን ትበድላለህ? ስለምን ስህተትህን እንደ መልካም ስራ፣ ጥፋትህንም እንደ ጀብድ ትደጋግማለህ? ወደ ፈጣሪህ እቅፍ ተመለስ፣ ወደቤቱ ቅረብ፣ ዝቅ ብለህ ተማፀነው፣ ክብርን ከእርሱ አግኝ፣ ፍፁም ሰላምህን ከእርሱ ውሰድ። ፍቅሩን ተረዳ፣ ማዳኑን ተመልከት፣ እለት እለት ከበረከቱ ተካፈል፣ ውስጥህን አድስ፣ በመኖርህ ተደሰት።
ፍፁም ሰላማዊ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
03.04.202518:31
ሁሉም አይሆንህም!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
ማንም ማስተማር የሚፈልግ ያስተምራል፣ ማንም ሃሳቡን ማጋራት የሚሻ ሃሳቡን ያጋራል። እንዲሁ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ነገር ያጋራል፣ ሁሉም ሰው ስለገባው ያወራል፣ ማንም ስለሚያስደስተው ብቻ ይተነትናል። እናንተም የሚወራውን ሁሉ የምታምኑ ከሆነ፣ የተነገራችሁትን ሁሉ የምትቀበሉ ከሆነ፣ የተማራችሁትን ሁሉ ለመተግበር የምትጥሩ ከሆነ ከምኑም ሳትሆኑ እንደምትቀሩ እወቁ። መረጃ ማብዛት አዋቂ አያስብልም፣ ስለሁሉም ማውራትም እንዲሁ ተፅዕኖ ፈጣሪ አያደርግም። እናንተ አንድ እስከሆናችሁ ድረስ የሚሆናችሁም አስር ሳይሆን አንድ ብቻ ነው። ህይወታችሁን ለመቀየር እስከ ዛሬ የሰማችሁት ሳይሆን ዛሬ የሰማችሁት አንድ መረጃ በቂ ነው። ከሚነገራችሁ ሁሉ በጥበብ መምረጥ ካልቻላችሁ ጊዜም ሆነ አቅማችሁን እንደምታባክኑ አስተውሉ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም አይሆንህም! ወርቅ ተብሎ የሚሰጥህ ሁሉ ወርቅ አይደለም፤ ላንተ ተብሎ የሚዘጋጅ በሙሉ ያንተ አይደለም። ከቀረበልህ ሁሉ የሚሆንህን የመምረጥ ጥበብ ያስፈልግሃል። ብዙ ሰው በመከተል የሚደረስበት ስፍራ አይኖርም፣ ለሚነገረው መረጃ ሁሉ ጆሮ እየሰጡም ሁሉን መተግበር አይቻልም። መዝናኛውም ያንተ፣ ፖሎቲካውም ያንተ፣ የትምህርት ስረዓቱም ያንተ፣ የማህበረሰቡ ችግርም ያንተ፣ ስፖርቱም ያንተ እንደሆነ እያሰብክ የትኛውንም በእጅህ ማስገባት አትችልም። የራስህን ነጥለህ ውሰድ የቀረውንም ለባለቤቱ አስረክብ። እራስህን በየአቅጣጫው በትነህ ለፈላጊውም አስቸጋሪ አትሁን። እስካሁን ባለህበት ቆመህ ከሆነ በላህ እውቀት ልክ በድፍረት ወደሚያዋጣህ ዘርፍ ተቀላቀል። ተጨማሪ እውቀት ቢመጣ ማጠናከሪያ እንጂ መሰረት ላይሆንህ እንደሚችል አስብ።

አዎ! ስላማረህ ብቻ የማትበላው ምግብ ይኖራል፣ በዘርፉ የተሳካላቸውን ሰዎች ስለተመለከትክ ብቻም አንተም እንደነሱ ስኬታማ የማትሆንበት አጋጣሚ ይኖራል። ማንም ልትሆን ትችላለህ፣ ምንም አይነት ሃሳብ ሊኖርህ ይችላል፣ የትኛውንም የተለመደ አካሔድ ልትከተል ትችላለህ፣ ከማንም የስኬት መንገዱን ልትኮርጅ ትችላለህ ነገር ግን ህይወትህ ከማንም ጋር አንድ አይንት ሊሆን አይችልም። ልዩነትህ በመልክህ፣ በቁመናህ ወይም በገቢህ ብቻ አይደለም ህይወትህ በሙሉ ከየትኛውም ሰው ህይወት የተለየ ነው። ለዚህም ነው ስዎች ስኬታማ የሆኑበት መንገድ በሙሉ ላንተም እንዲሰራልህ መጠበቅ የሌለብህ። ልብ ወዳደላበት፣ ንፍስህ ወደመረጠችው፣ ስሜት ወደሚሰጥህ፣ አቅሙ እንዳለህ ወደሚሰማህ አንድ ዘርፍ ጠቅልለህ ካልተቀላቀልክ ሁሌም ነዋሪ ሳትሆን አኗኗሪ፣ ተደናቂ ሳትሆን አድናቂ፣ አስከታይ ሳትሆን ተከታይ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሳይሆን መካከለኛ ሰው ሆነህ ትቀራለህ። መረጃ በማሳደድ ጊዜህን አታጥፋ፣ በሁሉም አቅጣጫ ስኬትን አትፈልግ፣ ተረጋግተህ ፍላጎትህን ፈልገው፣ እራስህን ስጠው፣ እስከመጨረሻውም በፍቅር ኑረው።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
Көрсөтүлдү 1 - 24 ичинде 425
Көбүрөөк функцияларды ачуу үчүн кириңиз.