Notcoin Community
Notcoin Community
Proxy MTProto | پروکسی
Proxy MTProto | پروکسی
Proxy MTProto | پروکسی
Proxy MTProto | پروکسی
iRo Proxy | پروکسی
iRo Proxy | پروکسی
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች avatar
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች avatar
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
Мөөнөт
Көрүүлөрдүн саны

Цитаталар

Посттор
Репостторду жашыруу
✔️ይህ በመቃብሩ ላይ ሀውልት የተሰራለት ውሻ BUBOY ይባላል ቡቦይ የአንድ የፕሮፌሰር ማርሴሎ የተባለ ደግ አስተማሪ የቅርብ ጓደኛ ነበር በየእለቱ ቡቦይ የሚወደውን ሰው ለማየት ብቻ ፕሮፌሰሩ ወደ ሚያስተምርበት ትምህርት ቤት ይመጣ ነበር...

ፕሮፌሰሩም ቡቦይን በፍቅር ተቀብለው ምሳቸውን ያካፍሉታል እንደ እውነተኛ ጓደኛም ያወሩት ነበር። አንድ ቀን ግን አንድ አሳዛኝ ነገር ተከሰተ። ፕሮፌሰሩ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ጓደኛው የት እንደሄደ ማንም ለቡቦይ ማስረዳት አልቻለም...

ለሁለት ሳምንታት ያህል ይህ አፍቃሪ ውሻ ወደ ትምህርት ቤት እየመጣ በመምህሩ ቢሮ በር ላይ እየጠበቀ ነበር። ጓደኛውን እንደገና ለማየት ተስፋ በማድረግ በሩ ላይ ይቧጭርና ዙሪያውን ይመለከት ነበር። የት/ቤቱ ሰዎች ቡቦይ በህይወት የሌለቱን ፕሮፌሰር ሲጠብቅ ሲመለከቱ በጣም ያዝናሉ...

በፕሮፌሰሩ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲሰናበታቸው ለማለት ወሰዱት። ቡቦይ ጓደኛውን ምን ያህል እንደናፈቀው ሲመለከቱ እዚያ ያሉት ሁሉ በእንባ ተሞሉ ። ቡቦይ ለረጅም ግዜ ጓደኛውን በመፈለግ እና ተመልሰው ይመጣሉ ብሎ በመጠበቅ እውነተኛ ጓደኝነት ምን ማለት እንደሆነ አሳይቷል...ታማኝነቱንም አስመስክሯል ....

ቡቦይ በኋላ ሲሞት በልዩ የቤት እንስሳት መቃብር ቀበሩት። የእሱ ታሪክ በጣም ልዩ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች ዛሬም ስለ እሱ ያወራሉ። ቡቦይ ዛሬ ህይወቱ ቢያልፍም ግን የማያልፍ አንድ አስደናቂ ነገር አስተምሯል ውሾች በሙሉ ልባቸው ይወዱናል ። ሀብታሞችም ብንሆን ድሆችም ብንሆን ..ብናጣም ብንገረጣም ደንታ የላቸውም። ስለ ማንነታችን ብቻ ይወዱናል...ሚለውን


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ቴምር በቫይታሚን B6 የበለፀገ ሲሆን ይህም የማስታወስ አቅምን ይጨምራል. ቴምርን ከወተት ጋር መጠቀም የአንጎልን ጤና ያጠናክራል እና ቀልጣፋ እንዲሆን ያደርጋል

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ዋሽንግተኒያን መፅሄት በባለፈው እትሙ ‹‹አንድ ሳምንት የዘለቀው ድንቅ ሠርግ›› በሚል አንድ ዘገባ አቅርቧል፡፡ እንደዘገባው ኤለን የጥርስ ሀኪም የሆነ ህንዳዊ ነው፡፡ አሜት ደግሞ በቨርጂኒያ ነዋሪ የሆነችና የአይቲ ኢንጂነር የሆነች ኤርትራዊት ናት፡፡

የሁለቱም የጋራ ጓደኛ የሆነ ልደት በዋሽንግተን ዲሲ በሚከበርበት ወቅት ትውውቃቸው መጀመሩን አስረድቷል፡፡ ከዚያም በጆርጅ ታውን ራት ተቀጣጥረው ከተገናኙ በኋላ ግንኙነታቸውን ማጠናከራቸውን ገልጿል፡፡ ይህ ከሆነ ከአምስት አመት በኋላ በአሊንግተን ውስጥ ኤለን ተንበርክኮ ታገቢኛለሽ የሚል ጥያቄ ሊያቀርባለት ችሏል፡፡ ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ሁለቱ ጥንዶች ስለሰርጋቸው ማሰብና ማቀድ ይጀምራሉ፡፡ ውጥናቸው ተሳክቶም አንድ ሳምንት የፈጀ ልዩና ድንቅ ሠርግ ለማድረግ እንደቻሉ ዘገባው አስረድቷል፡፡

ይህ ሠርግ አንድ ሳምንት ሊዘልቅ የቻለው የህንድና የኤርትራ ባህል በሙሉ መካተት ስለነበረበት ነው፡፡ በመሆኑም ከህንድና ከኤርትራ ድምፃዊያን ተጠርተውና ዘመድ ወዳጆቻቸው ተገኝተው የሠርግ ስነስርአቱ ሊከናወን እንደቻለ ዘገባው አስታውቋል፡፡ ጥንዶቹ ለሳምንት በዘለቀለው በዚህ ሠርግ ደስታቸውን ካጣጣሙ በኋላ ከድካማቸው ለማረፍና ለጫጉላ ሽርሽር ወደኢንዶኔዥያ ባሊ ሄደዋል ብሏል ዘገባው፡፡
ህንዳዊ ነው ሲያሻው መኪናን በሰማይ የሚያሽከረክር ሲለውም በአውራ ጣቱ አፈናጥሮ ከገደል የሚጨምር። ከአንበሳ ጋር ተናንቆ የሚረታ በሰማይ የሚምዘገዘግን ጥይት ሽል ማለት የሚችል ተዋናይ አሚር ኻን ይሰኛል።

አንድ አንድ ኪሎ ፍርኖ ዱቄት ለችግረኞች መስጠት ፈለገና በይፋ አሳወቀ። የሚፈልግ ብቻ ቤቴ ድረስ ይምጣ አለ። ከሚሊየነሮች ተርታ የሚመደብ፣ ቢዘገን የማያልቅ ኃብት ሸክፎ አንድ አንድ ኪሎ ዱቄት ሊሰጥ መሆኑ ሀገሬውን አስገረመ። ስስታም ቆንቋና እያሉ ሰደቡት።

ና ከእኛ ውሰድ እያሉ ፎቶውን በዱቄት አቀናብረው ተሳለቁበት። ድንቄም አንድ ኪሎ ዱቄት ቱ እያሉ ረገሙት። መኪና በጣቱ እየጎተተ አሽቀንጥሮ ከገደል ሲወረውር ነበርና የሚታወቀው እየተወነ ይሆን በማለት ሰዎችን አጀብ አሰኘ።
ቀኑ ደረሰና እርዳታውን ለመቀበል ሚስኪኖች ከደጃፉ ላይ ተኮለኮሉ። በገዛ እጁ የቋጠረውን አንድ አንድ ኪሎ ዱቄት ከትልቅ ትህትና ጋር የተቸገሩትን እያቀፈና እየሳመ መስጠቱን ተያያዘው። አጀብ የዚህ ሰው ነገር አሰኘ።

ሙሉ ቤተሰብን ቁርስና ምሳ አጥግቦ የማያበላ፣ በመጠኑም በይዘቱም ትንሽ የሆነ፣ ታይቶ የማይታወቅ ሰደቃ እየሰጠ ጭራሽ አቅፎ ይስማቸዋል?! የቀየው ሰው ተዓጀበ።

እርሱ ዘንድ ተሰብስበው የመጡት ግን ይህ በመጠኑ ትንሹሽ የሆነው ዱቄት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ብቻ ነበሩ።

በረሐብ ጠኔ የተገረፉ መሳኪኖች። የዕለት ጉርስ የቸገራቸው ከፊታቸው ገፅ ላይ ርሀብ የሚነበብባቸው ቅልስልስ ኩምሽሽ ያሉ ድሆች።ዱቄቱን ተቀብለው ወደ ቤታቸው አቀኑ።

እሳት አያይዘው ቂጣ ጋግረው ሊበሉ አቡክተው ከምጣዱ ሊጋግሩ ፌስታሉን ሲከፍቱ 15 ሺህ ብር ተጠቅልሎ ከዱቄቱ ላይ አገኙ። የእውነት ለተቸገሩት ሰዎች እርዳታው ደረሰ።
ሰደቃቸው ለትክክለኛ ሰዎች እንዲደርስላቸው የሚመኙና የሚተጉ ሙተሰዲቆች አጀብ ተሰኙበት።

"....በምልክታቸው ታውቃቸዋለህ፡፡ ሰዎችን በችክታ አይለምኑም" ለተባለላቸው ሚስኪኖች ሰደቃን በትክክል ማድረስ ይሉሀል ይህ ነው


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ፓፕ ፍራንሲስ በኬሚስትሪ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው ።

✅@Amazing_fact_433
😄ግራፊክስ ዲዛይን በአማርኛ መሉ ትምህርት

ለጀማሪ
ለፎቶግራፊ ባለሞያዎች
ለአርክቴክቸር ተማሪዎች
ለቴክስታይል ኢንጂነሪግ ተማሪዎች

ቻናሉን በመቀላቀል ይማሩ

⚡️⚡️⚡️

https://t.me/EthioLearning19/2778
https://t.me/EthioLearning19/2778
https://t.me/EthioLearning19/2778
🔵“በዚህ ዘመን በየትኛውም ሁኔታ በጣም ግዜ የለኝም፣ እረፍት የለኝም ብለህ የምታስብ ቢሆን እንኳን ለማንበብ የግድ ግዜ መስጠት አለብህ። ይህን አላደረክም ማለት ግን በገዛ ፍላጎትህ ራስህን አላዋቂ እያደረከው ነው ማለት ነው።” ኮንፊሽየሥ

የተለያዩ መፅሐፍ በ Pdf  ድርሰቶች አጫጭር ታሪኮችን የሚያዘጋጅ የቴሌግራም ቻናል
ልጠቁማችሁ!!!


ስሙ እንማር ይሰኛል !!
ቀኖትን እያሳመረ ማታዎትን እያደመቀ ምርጥ ምርጥ መፅሀፎች ይጋብዛቸዋል

100%ትወዱታላችሁ

💬https://t.me/Enmare1988/2522
💬https://t.me/Enmare1988/2522
💬https://t.me/Enmare1988/2522
የአሳ ነባሪን የልብ ምት ከ 3ኪሜ ርቀት መስማት ይቻላል ።
ከ1850 በፊት የግራ የቀኝ እግር የሚባል ጫማ የለም ሁለቱም አንድ አይነት ነበር።

⭐️ @Amazing_fact_433
<ደጉ ተቧቃሽ ማይክ ታይሰን>

"ገንዘብ የተሳሳተ የደህንነት ስሜትን ይፈጥራል። አንዳንድ ሰዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ስላገኙ የማንነካ ነን ብለው ያስባሉ። ገንዘቡ ሞትን የሚከላከልላቸው ወይም ሞት ፈፅሞ የማይደፍራቸው ይመስላቸዋል ። እውነታው ግን ይሄ አይደለም።

ሕይወት በቅጽበት ልታከትም ትችላለች ። በአንዲት ትንኝ ጠቅታ፣ በአንድ የተሳሳተ ግንኙነት፣ ወይም በአንዲት ጥይት አማካይነት ሕይወት በዐይን ጥቅሻ ፍጥነት ልታበቃ ትችላለች ።

ሀብት የማይበገር ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል። ነገር ግን ደስታን አያረጋግጥም.።

ብዙ ገንዘብ በማግኘት ብቻ ደስተኛ እንደማይኮን ብዙ ጊዜ ለሰዎች እነግራቸዋለሁ። በገንዘብ ደስተኛ እሆናለሁ ብለህ ካመንክ ምናልባት ብዙ ገንዘብ አግኝተህ አታውቅም ማለት ነው።

ለእኔ፣ የገንዘብ ትክክለኛው ዓላማ ከሌሎች ጋር መኖር፣ ሰዎችን መርዳትና በእነዚህ ግንኙነቶች ደስታን ማግኘት ነው። ማንም ሰው ሁሉንም ነገር ለራሱ በማዋል ዘላቂ ደስታን አያገኝም።

እውነተኛ ደስታ የሚመጣው የተቸገረን ሰው በመርዳትና ፊታቸው ላይ ያለውን ፈገግታ ስንመለከት ነው። ለእኔ አስፈላጊ የሆነው ሀብት ይሄ ነው." - ማይክ ታይሰን


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
PUBG የሚባለው ጌም በቀን $689,000 ዶላር ያስገባል ።
PUBG Earns $689,000 Per Day
🤩

@Amazing_fact_433
Өчүрүлгөн22.02.202519:50
22.02.202512:12
ዛሬ የሚደረጉ የሊጉን ጨዋታዎች በቀጥታ ይከታተሉ..
የአንድ ሰው የጭንቅላቱ መረጃ የመያዝ መጠን 2.5 ሚልዮን ጂቢ ይደርሳል ።

@Amazing_fact_433
#የታይታኒክ_ባልንጀራ

ዛሬ የዝነኛዋ ታይታኒክ መርከብ ስትሰጥም የተወለዱትን የ112 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው ሰው ታሪክ ለግርምታችን እናወሳለን።

ዝነኛዋ ታይታኒክ መርከብ በሰመጠችበት ዓመት የተወለዱት የዓለማችን የዕድሜ ባለፀጋ ጆን አልፍሬድ ቲኒስዉድ 112ኛ ዓመት ልደታቸውን በእንግሊዝ በሚገኝ የአዛውንቶች መንከባከቢያ ማዕከል ባለፈው የፈረንጆቹ ነሐሴ ወር አክብረዋል።

ጆን አልፍሬድ ቲኒስዉድ የተወለዱት እ.ኤ.አ ነሐሴ 26 1912 በሊቨርፑል ከተማ ሲሆን ይህም ዝነኛዋ የታይታኒክ መርከብ ከሰመጠች ከአራት ወራት በኋላ ነበር።

በያዝነው ዓመት መጀመሪያ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ በዓለማችን ላይ ካሉ ወንድ ሰዎች ሁሉ በዕድሜ ትለቁ ለመሆናቸው እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

ረጅም እድሜ ለመኖራቸው ምስጢሩን ሲጠየቁም “ምንም የተለየ ምስጢር የለውም፣ እንዴት እንደሆነ አላውቀውም” ብለዋል።

ወጣት እያሉ ብዙ የእግር ጉዞ ያደርጉ እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያዘወትሩ እንደነበር የተናገሩት ጆን ቲኒስውድ “ነገር ግን ከሌሎች የተለየ ያደረግኩት ነገር የለም” ማለታቸውን ዩፒአይ አስነብቧል።

በአሁኑ ወቅት የዓለማችን የዕድሜ ባለፀጋዋ ሰው ጃፓናዊቷ ቶሚኮ ኢቶካ ሲሆኑ በዚህች ምድር ላይ 116 ዓመታትን ኖረዋል።

(ጋሸ ጆን አልፍሬድ ቲኒስዊድ ፀሎት ሲያደርጉ "ጌታ ሆይ እድሜዬን ጨምርልኝ" ይሉ ይሆን
?
___

@Amazing_fact_433
21.02.202510:59
በኢትዬጲያ ትልቁን የስፖርት ቻናል ይቀላቀሉ👇
ቢልጌትስና የቀድሞ ባለቤቱ ማሊንዳ ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁት እሱ የማይክሮሶፍት CEO እሷ ደግሞ በዛው ካምፓኒ የአንድ ክፍል ሀላፊ ሆና ተቀጥራ ስትሰራ ነው ።
በዚህ መልኩ ግንኙነታቸው የአለቃና የሰራተኛ ሆኖ ቆይቶ ከአመታት በኋላ ወደ ፍቅር ተቀየረ ።
......
ይህንን ግንኙነት ለረጅም ጊዜ በሚስጥር ይዘውት ቆይተውም ፡ አንድ ቀን ስታዲየም ገብተው የቅርጫት ኳስ ጨዋታ በመመልከት ላይ እያሉ ማሊንዳ ተጎንጭታ ያስቀመጠችውን ኮካ ቢልጌትስ አንስቶ ሲጠጣው በጋዜጠኞች ካሜራ ውስጥ ገባ ።
.....
ትንሽ ፍንጭ የሚፈልጉት ሚዲያዎች የማይክሮሶፍቱ መስራች ቢልጌትስ. . ከ Melinda Ann French ጋር ፍቅር ጀምረዋል እያሉ ዜናውን አጮሁት ።
....
በዚህ ሁኔታ በፍቅር የቆዩት ቢልጌትስና ማሊንዳ ልክ አዲስ አመት ሲገባ January 1, 1994 ዋረን ቡፌትን የመሳሰሉ ጥቂት ታዋቂ ሰወች ብቻ በተገኙበት ሀዋይ ውስጥ በምትገኘው ላናይ ደሴት ላይ በይፋ ደግሰው ሊጋቡ ወስነው ለሰርጉ ስነስርአት መዘጋጀት ጀመሩ ።
...
ቢልጌትስ. . የሰርጉ ስነስርአት ተከናውኖ እስኪያበቃ ሚዲያዎች ጋር እንዳይደርስ ቢፈልግም ፡ ከጋዜጠኞች አይንና ጆሮ መደበቅ እንደማይቻል ግን አውቋል ።
እና. . ሳይጠሩ እየተገኙ የነሱንም ሆነ የተጋባዥ እንግዶችን ፕራይቬሲ የሚረብሹትን ፓፓራዚዎችና ሌሎች የሚዲያ ሰወችን ከሰርጉ ቦታ ለማራቅ አንድ ዘዴ አሰበ ።
....
ከዛም በጎብኝዎች ተመራጭ የሆነችውን በላናይ ደሴት የሚገኙ የሆቴል ክፍሎችን በሙሉ. . ከሰርግ አዳራሾቻቸው ጋር ተከራየ ።
አሁን ሳይጠሩ ከተፍ ብለው ያልተፈቀደ ፎቶና የግል ነጻነትን በሚጋፋ መልኩ የሚዘግቡት ጋዜጠኞች ወሬው ቢደርሳቸው እንኳን ሁሉም ሆቴሎች ስለተያዙ የትኛው ሆቴል ሰርጉ እንደሚደገስ አያውቁም ። ማረፊያም አያገኙም ።
....
ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም ፡ ፓፓራዚዎቹ ሁሉም ሆቴሎች ተይዘው የሰርጉ ቦታ የት እንደሆነ ካላወቁ በቀጣይ የሚያደርጉት ፡ ከአየር ላይ ሆነው ፎቶ ለማንሳት ሄሊኮፕተሮችን ተከራይተው ሰርገኞቹን መፈለጋቸው አይቀርም ።
ስለዚህ ከደቂቃዎች በኋላ ሊደርሱባቸው ይችላሉ ።
ቢልጌትስ ለዚህም መፍትሄ አገኘለት
እና በዛች ደሴት ውስጥ የሚገኙ የግል ሄሊኮፕተሮችን በሙሉ ለአንድ ቀን ተከራያቸው ።
.....
በዚህ መልኩ ፡ በላናይ ደሴት ላይ የሚገኙ ሆቴሎችን በሙሉ ከያዘና ፡ በደሴቲቱ የሚገኙትን ሄሊኮፕተሮቹን በጠቅላላ በቁጥጥር ስራ በማድረግ ፡ በፓፓራዚና ፡ በሌሎች ሚዲያዎች ሳይረበሹ ሰላማዊ የሰርግ ስነ ስርአት ማክበር እንዲችሉ ነገሮችን ካመቻቸ በኋላ ፡ ከከፈለባቸው ትላልቅ የሆቴል መናፈሻዎች በአንደኛው የሰርጉን ፕሮግራም አካሄደ ።

ይህ ዘዴው ውጤታማ ሆኖ ፡ በሰርጋቸው ቦታ ፡ ፓፓራዚም ሆነ ያልተጋበዘ ሚዲያ. . ድርሽ አላለም ነበር


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
አሜሪካ የአቶሚክ ቦንብ ለመጣል ያሳበችው ኮኩራ፤ጃፓን ነበር ነገር ግን በስህተት ናጋሳኪ ላይ ወደቀ ። 

⚡️ @Amazing_fact_433
እግር ጥሏችሁ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ብትደርሱ የዚህን ውሻ ሀውልት በአንድ ባቡር ጣቢያ ውስጥ ታገኙታላችሁ፡፡ ይህ ውሻ ለ10 አመታት ፍቅርን የሰበከ ታማኝነትን ያወጀ በመሆኑ ጃፓናውያን ይኮሩበታል ይወዱታል፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ ውሻ ታሪክ ፊልም ሆኖ ተሰርቷል፡፡ "Hachi: a dogs tale" በ2009 የተሰራው ፊልም ነው።

ይህ ውሻ ስሙ ሀቺኮ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የፕሮፌሰር ኢዛቡሮን ውሻ ነበር፡፡ ፕሮፌሰሩ ውሻውን በፍቅር አሳደጉት፡፡ ሁሌም ውሻው ጠዋት አብሮ ባቡር ጣቢያ ሄዶ ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ይመለሳል ማታ 11 ሰዓት ባቡር ጣቢያ ሄዶ ይቀበለውና ቤት ድረስ አብሮ ይመጣል፡፡

ታድያ ከእለታት ሁሉ በአንዱ ከፉ ቀን በግንቦት 21 - 1923 ዓ.ም ውሻው ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ማታ እንደልማዱ ሊቀበላቸው ባቡር ጣቢያ ቢጠብቃቸው ሰውዬው ለካ በልብ ድካም ሞተው ኖሯል ሳይመጡ ቀሩ፡፡

ውሻው ግን ይመጣሉ ብሎ ፕሮፌሰሩን ጠበቀ 1 ቀን ብቻ አደለም ጥቂት ወራትም አደለም ድፍን 10 አመት እንጂ እሳቸውን ጥበቃ እዛችው ባቡር ጣቢያው ጋር 10 አመት ጠብቆ እዛው ሞተ፡፡ እናም ሀቺኮ ወዳጁን 10 አመት በፅናት መጠበቁ አያስደንቅም
?
አንድ የጉግል ተቀጣሪ ሲሞት ለባለቤቱ/ቷ ከሚከፈለው ከነበረው ግማሹ ለ10 አመት ይከፈለዋል እንዲሁም ለልጆቻቸውም  እስከ 19 አመታቸው 1000$ ይከፍላል ። 

✅ @Amazing_fact_433
📷Kevin Carter - The vulture and the little girl (1994)

@Amazing_fact_433
Көрсөтүлдү 1 - 14 ичинде 14
Көбүрөөк функцияларды ачуу үчүн кириңиз.